Data Loading...
الحج المبرور5 Flipbook PDF
الحج المبرور5 በሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን ኸሊል የሚተላለፉ አጠቃላይ ትምህርቶችን ለማግኘት በሚከተለው ይፈልጉን ፌስቡክ ይከታተሉን https://www.facebook.com/Mohamm
272 Views
202 Downloads
FLIP PDF 1.78MB
መግቢያ .................................................................................. ح ሀ-የሐጅ ትሩፋቶችና ፋይዳዎች...................................................... 2 ለ-የጉዞ ስነ ስርዐቶች ................................................................... 9 ክፍል አንድ ፡ ቅድሚያ ስለ ዑምራ አፈፃፀም በአጭሩ العمرة.................................................................................. 12 1-1.የዑምራ ትርጉም معنى العمرة.............................................. 12 1-2.የዑምራ ፆሎት ብይን حكم العمرة.................................................................................. 12 1-3.የዑምራ ግዴታዎች أركان العمرة.................................................................................. 12 1-4.የዑምራ ዋጂቦች واجبات العمرة............................................. 12 1-5. የዑምራ ሱናዎች سنن العمرة................................................ 12 ክፍል ሁለት ፡-አል ሐጁ ልመብሩር.............................................. 15 2-1.የሃጅ ትርጉም معنى الحج......................................... 15 2-2.የሐጅ ፆሎት ብይን حكم الحج................................ 15 2-3. የሐጅና የዑምራ ፆሎቶች ትሩፋት በቁርኣን እና በሐዲስ فضل الحج والعمرة في القرآن الكريم............................................ 15 2ኛ ያሉትም አንቀፆች እንዲሁ ይነበባሉ ........................................ 17 4ኛ ሐዲስ አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ አንሁ) ከነቢዩ ﷺየዘገቡት ....... 21 የቦታዎች መበላለጥና ከሱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች .............................. 22 2-4.የሐጅ ፆሎት ፋይዳዎችና ዋና ዋና አላማዎቹ فوائد الحج................ 24 ክፍል ሶስት ፡-የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም ........................................ 25 3-1.የሃጅ አይነቶች انواع الحج............. 25 3-2.የሐጅ ቅድመ ሁኔታዎች شروط الحج........................................ 26 3-4. ስለ ሴቶች ሙህረም ባጭሩ المحرم للنساء.............................. 27 1ኛው ዘመድ ከሷ ጋር በስጋ የሚገናኙ ሰዎች ሲሆኑ እነሱም ፡- ............ 27 2ኛው ከሷ ጋር በጡት መጥባት ምክኒያት የሚገናኙ ሲሆኑ እነሱም ፡- .. 27
3ኛው ከሷ ጋር በጋብቻ ምክኒያት የሚገናኙ ሲሆኑ እነሱም ፡- ............ 28 3-5. ከሌላ ሰው ተወክሎ ሐጅ ማድረግን በተመለከተ الحج عن الغير.................................................................................... 29 3- 6.የሐጅ ማዕዘናት أركان الحج. 29 የሐጅ ማዕዘናት አራት ናቸው ፡፡ ................................................. 29 3-7.የሐጅ ዋጂባቶች واجبات الحج............................................... 29 3-8.የሐጅ ሱናዎች سنن الحج..................................... 30 3-9.የጠዋፍ ዓይነቶች أنواع الطواف......................................... 32 3-10. የጦዋፍ ቅድመ መስፈርቶች شروط الطواف............................ 32 3-11.የጦዋፍ ሱናዎች سنن الطواف............................................. 33 20) ጠዋፍን በተመለከተ ለሴቶች ብቻ የሚሆኑ ጠቃሚ ምክሮች ........ 34 3-12.በጦዋፍ ጊዜ የሚታዩ ስህተቶች أخطاء الطواف....................... 35 3-13.የመሰዋዐት አይነቶች أنواع الفدية........................................... 35 3- 14.የሰዕይ ቅድመ ሁኔታዎች ዘጠኝ ናቸው፡፡ شروط السعي............. 36 3-15.የሰዕይ ሱናዎች سنن السعي............................. 36 3-16.በሰዕይ ላይ የሚታዩ ስህተቶች أخطاء السعي............................. 37 3-17. የሐጅ ስነ-ስርአት ቅደም ተከተል ልክ كيفية الحج مرتبة.. 37 3-18.የኢህራም ማድረጊያ ቦታዎች الميقات.................................... 38 3-19.የሐጅ ኢህራም ማድረጊያ ወራቶች أشهر الحج.......... 39 3-20.በኢህራም ወቅት ከሚታዩ ስህተቶች أخطاء اإلحرام......... 39 3-21.የሐጅ የመጀመሪያው ቀን የሆነው የ8ኛው ቀን ተግባራት أعمال يوم التروية................................................................................. 40 3-22.የሐጅ የሁለተኛው ቀን የሆነው የ9ኛው ቀን ተግባራት أعمال يوم عرفة............................................................................... 40 3-23.የዘጠነኛው ቀን ሱናዎች سنن يوم عرفة....................... 42 3-24.በአረፋ ውሎ ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል በአጭሩ أخطاء يوم عرفة.................................................................................... 42 .
ت
3-25.የሙዝደሊፋ አዳር ተግባራት أعمال ليلة مزدلفة........................ 43 3-26.በሙዝደሊፋ አዳር ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል أخطاء ليلة مزدلفة.................................................................................. 43 3-27.የሐጅ የሶስተኛው ቀን የሆነው የ10ኛው ቀን ተግባራት በአጭሩ أعمال يوم النحر...................................................................... 44 3-28.በጠጠር ውርወራ ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል أخطاء الرمي................................................................................... 44 3-29.የሐጅ አራተኛው ቀን የሆነው የ 11ኛው ቀን ተግባራት أعمال الحادي عشر.................................................................................... 45 የሐጅ አምስተኛው ቀን የሆነው የ12ኛው ቀን ተግባራት اعمال اليوم الثاني عشر............................................................................ 46 3-30.የሐጅ ስድስተኛው ቀን የሆነው የ13ኛው ቀን ተግባራት اعمال اليوم الثاني عشر............................................................................ 46 3-31.ማሳሰቢያ ........................................................................ 46 3-32.በ13ኛው ቀን ከሚስተዋሉ ስህተቶች መካከል በአጭሩ أخطاء اليوم الثالث عشر..................................................................... 47 3-33.በኢህራም ምክኒያት የሚከለከሉ ነገሮች እና ማካካሻዎች ............ 47 محظورات اإلحرام وكفارتها...................................................... 47 የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ፤ ይህ ተግባር የተፈፀማ ከመጀመሪያው መፈታት በፊት ከሆነ ሐጁ ይበላሻል ፡፡ ሆኖም ሐጁን ጨርሶ በሚቀጥለው አመት ቀዷ ማውጣት የኖርበታል ፡፡ ይህም የሚሆነው ለመካ ድሆች የሚከፋፈል አንድ ግመል ከማረድ ጋር ነው ፡፡ ................................ 48 3-34. የሴት ልጅና ጦዋፍ.........................................................54 3-36.የማካካሻ አይነቶች............................................................ 54 እነዚህን ከላይ የተወሱትን ስህተቶች የፈጸመ ሰው ............................ 55 በኢህራም ላይ እያለ ግብር ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ብይን ............ 55 ሐጅ ያመለጠው ሰው ............................................................... 57 الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
የስጦታ አይነቶች ..................................................................... 57 ሀ. ሱንና የሆነ መስዋዕት፡- ........................................................ 57 4-የነብዩ ሙሐመድ ﷺሐጅ አፈፃፀም እንዲህ ነበር ........................... 58 5-ሐጅና ቀደምት ሙስሊሞች ..................................................... 60 5-1.የቀደምት ሙስሊሞችና ሐጅ ................................................. 60 5-2.የቀደምት ሙስሊሞችና የሐጅ ጉዞ ስነ ስርዓት........................... 61 51-የቀደምት ሙስሊሞችና ኢህራም ይህን ይመስሉ ነበር ................... 62 5-4.የቀደምት ሙስሊሞችና ኢባዳ በሐጅ ላይ እያሉ እንዲህ ነበር ........ 62 5-5.ØMƑጠቃሚ ምክሮች ለሑጃጆች .......................................... 63 6-የመካ ስሞች እና ትሩፋቶች اسماء مكة وفضلها............................ 64 6.1 ከመካ ስሞች መካከል ......................................................... 64 6.2.የመካ ክልሎች حدود الحرم المكي.........................................65 6.3.የመካን ትልቅነትና ክብር በተመለከተ የተዘገቡ ሐዲሶች ................ 66 3ኛው ወደ ተከበሩ ቦታዎች የሚደረጉ ጉዞዎች ................................. 71 9ኛ ደምን ስለ ማክበር…….......................................................... 83 10ኛ ሁለቱ ቅዱሳን ከተሞች ከደጃል ወረራ እንኳን ስለ መጠበቃቸው፡፡ 84 11ኛ ለመካ ብቻ የተቸረው የሁል ጊዜ አስተማማኝ ሰላም ነው፡፡........... 86 12ኛው ሐዲስ አክብሮት ዉስጥን ሲቆጣጠር................................... 87 13ኛ አክብሮትና ትልቅነት/ሰላምና ፀጥታ........................................ 89 14ኛ በተከበረው ቤት በመካ የምግብ ረድኤታመነት ......................... 91 15ኛ የመካ ጎረቤት ሁኖ መኖር የሚያስገኘው ልዩ ዒባዳ .................... 93 16ኛ ለቂብላችን ሊሰጠው የሚገባው ክብር .................................... 94 17ኛ ከቂብላ ጋር ሊኖረን የሚገባን ስነ ስርአት ................................. 96 18ኛ የቂብላን ጉዳይ ማክበርን በተመለከተ ..................................... 96 19ኛ የሙስሊሞች በህይወትም ሆኑ ሙተው የሁል ጊዜ ቂብላቸው የሆነው ................................................................................. 98 .
ج
20ኛ መካ ምንጊዜም ጎብኚ አታጣም ............................................ 99 21ኛ ጦዋፍ ማድረግና ሁለቱን ማዕዘናት በእጅ መንካትበመካ የሚፈፀሙ አምልኮታዊ ተግባር ናቸው ፡፡ .................................................. 101 22ኛ በጦዋፍ ዉስጥ መነጋገር ................................................... 103 23ኛው ሐዲስ ባሪያን ነፃ እንደማውጣት ይቆጠራል ....................... 105 24ኛ በሐጀረል አስወድ ላይ የታየው ልዩ ተአምር .......................... 106 25ኛ ዲንጋዩ ሲመሰክር ........................................................... 108 26ኛ ዲንጋዩን በእጅ መንካትና በአፍ መሳም ................................ 109 27ኛ ዲንጋዩን በመሳም ላይ ከፍተኛ ጉጉት ማሳደር ........................ 110 28ኛ ዲንጋዩን በመንከባከብ ላይ ሊጠበቅ የሚገባው ጉዳይ .............. 111 29ኛ በሒጅር ኢስማዒል ዉስጥ መስገድ .................................... 111 30ኛው ሐዲስ በዲንጋዩ ላይ መደፋት/ሱጁድ ማድረግ ተገቢ ስለ መሆኑ ................................................................................ 113 31ኛ በመዕምናን በሶፋና በመርዋ ላይ የሚደረጉት ተክቢራዎች .......... 114 32ኛ ቋሚ የሆነው ግልፅ ተዐምር .............................................. 116 33ኛ ለዝንተ ዐለሙ ጉዞ መዘጋጀት ............................................ 117 34ኛው ሐዲስ ቤተሰብ አጥጋቢው የዘምዘም ዉሃ ......................... 119 35ኛ ልዩ የመካ ስጦታ............................................................ 120 36ኛው ሐዲስ የተውሳኮች ሁሉ ፍቱን መድሐኒት የሆነው የዘምዘም ዉሃ ................................................................................... 120 37ኛ የድሆች ሐጅ ................................................................. 122 38ኛ ልቦች ሁሉ ወደ መካ ይናፍቃሉ ......................................... 123 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ............................................................... 124 39ኛ ሐጅ የተከበረው እንግዳ/ልዑክ .......................................... 125 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ............................................................... 126 40ኛ መካ የእምነት/መደበቂያው/ መሰበሰቢያው ቦታ...................... 127 የመዲና መስጊድ በኢስላም ...................................................... 128 الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
6.1.ከመዲና ከተማ ስሞች ........................................................ 128 የመዲና ከተማ ብዙ ስሞች አሏት አንዳንድ ዐሊሞች ወደ መቶ ያደርሱታል፡ ፡ ....................................................................................... 128 6.2.ስለ መዲና ክልሎች .......................................................... 129 6.4.የቁባን መስጊድ መጎብኘት ያለው ምንዳ ................................. 131 የነብዩ ሙሐመድን ﷺቀብር መጎብኘት................................. 133 6.6.የመዲና ትልቅነትና ክብር ................................................... 134 ዋቢ መፅሐፍት ..................................................................... 136
.
1
بسم هللا الرحمن الرحيم በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እና በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ ፡፡ ለአላህ እንዳዘዘው ሁሉ አያሌ ምስጋና ይገባው ፡፡ ያለ እሱ ምንም አምላክ እንደሌለ ከልቤ አምኜ በአንደበቴ እመሰክራለሁ ፡፡ ነቢያችን መሪያችን ፤ አለቃችን ፤ አርአያችን ፤ ሙሐመድ ብን ዐብዱላህ የአላህ ቅኑ አገልጋይና ታማኝ መልዕክተኛው እንደሆኑም ከልቤ አምኜ በምላሴ እመሰክራለሁ ፡፡ ተልዕኳቸዉን በአግባብ እንደተወጡ ፤ አማናቸዉን በሙሉ እንዳደረሱ እመሰክራለሁ ፡፡ የአላህ ርህራሄና ሰላምታ በእሳቸው ፤ በንፁሃን ቤተሰቦቻቸው ፤ በስራ ባልደረቦቻቸው እና እነሱን እስከ ዐለም ፍፃሜ ድረስ በትክክለኛው መንገድ በተከተላቸው ሰው ሁሉ ላይ ይሁን ፡፡ ይህ መፅሐፍ ሐጅን ወይም ዑምራን መተግበር ለሚፈልጉ ሁሉ በቲኒሹም ቢሆን ይጠቅማል ፡፡ በመቀጠልም ፡-ዉድ ሑጃጆች -አላህ ሐጃችሁን ይቀበላችሁና ከዚህ በታች ያሉትን ትምህርቶች በጥሞና ተመልከቱ ፡፡ስለ ሐጃችሁም ሆነ ስለዑምራችሁ አፈፃፀም በቀላሉ ይረዳችኋል፡፡ሐጅህ ትክክለኛ የሆን ዘንድ ስራህ ተቀባይነት እንዲኖረው ኢኽላስ ወሳኝ መሆኑን እንዳትዘነጋው አድራ፡፡ ቁርኣን እንዲህ አለ ْ د فَ َمن َكانَ يَ ۡرجٞۖ ي أَنَّ َمآ إِ َٰلَهُ ُكمۡ إِ َٰلَه َٰ َو ِح ُوا لِقَآ َء َربِّ ِهۦ َّ َ(قُ ۡل إِنَّ َمآ أَن َ۠ا بَ َشر ِّم ۡثلُ ُكمۡ يُو َح َٰ ٓى إِل ١١١ َٰلِ ٗحا َو ََل ي ُۡش ِر ۡك بِ ِعبَا َد ِة َربِّ ِٓۦه أَ َح َۢ َدا َ َٰ فَ ۡليَ ۡع َم ۡل َع َم ٗل መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነኝ የሚል መልዕክት ወደ እኔ የሚወረድልኝ መሰላችሁ ሰው ነኝ ፡፡ እናም ከጌታው ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ መልካም ሥራን ይሥራ ፡፡ በጌታውም መገዛት ላይ አንድንም አያጋራ በላቸው) አልከህፍ ፡፡ ምክኒያቱም አንቀፅ የወረደበት ምክንያት ፡- ጁንደብ ኢብን ዙሀይር የተባለ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ () መጥቶ ‹‹ስራዎችን ለአላህ ነው የምሰራው ነገር ግን ሰው ሲያውቅልኝ ደስ ይለኛል›› ብሎ ሲጠይቃቸው ነው ይህ አንቀፅ የወረደው ፡፡ ቁርጡቢ። አንድ ሰው ወደ ነብዩ መጥቶ ጂሃድ እወዳለሁ ነገር ግን ክብሬም እንዲታወቅልኝ እመኛለሁ ስላላቸው ነውና፡፡
ሀ-የሐጅ ፋይዳዎች የሐጅ ፋይዳዎች ብዙ ናቸው ፡፡ ቁርኣን ይህንን ጉዳይ በግልፅ (26-33. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ ፡፡ ቤቴንም ለሚዘይሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ ፡፡ ኢብራሂም ሆይ ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ ) አል ሐጅ 27-28. َت أَن ََّل تُ ۡش ِر ۡك بِي َش ۡيا َوطَه ِّۡر بَ ۡيتِ َي لِلطَّآئِفِينَ َو ۡٱلقَآئِ ِمين ِ ) َوإِ ۡذ بَ َّو ۡأنَا ِ ِإل ۡب َٰ َر ِهي َم َم َكانَ ۡٱلبَ ۡي ضا ِمر يَ ۡأتِينَ ِمن َ ِّاس بِ ۡٱل َح ِّج يَ ۡأتُوكَ ِر َج ٗاَل َو َعلَ َٰى ُكل ِ َّ َوأَ ِّذن فِي ٱلن٦٢ َوٱلرُّ َّك ِع ٱل ُّسجُو ِد ْ وا َم َٰنَفِ َع لَهُمۡ َويَ ۡذ ُكر ْ لِّيَ ۡشهَ ُد٦٢ ُكلِّ فَج َع ِميق َّ ٱس َم ۡ ُوا ت َعلَ َٰى َما ٍ ٱَّللِ فِ ٓي أَيَّام َّم ۡعلُو َٰ َم ْ وا ِم ۡنهَا َوأَ ۡط ِع ُم ْ ُ ِم فَ ُكلٞۖ َرزَ قَهُم ِّم َۢن بَ ِهي َم ِة ۡٱۡلَ ۡن َٰ َع (س ۡٱلفَقِي َر َ ِوا ۡٱلبَآئ (22፡ 26-33. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ ፡፡ ቤቴንም ለሚዘይሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ ፡፡ ኢብራሂም ሆይ ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ ፡፡እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ በከሳዋ ግመሎች ላይ እንኳን ሆነውም ይመጡልሃልና ፡፡ ለእነሱ የሆነ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእኒያ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል፡፡ ) የአላህ መልዕክተኛ () እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ይህን ቤት ካዕባን ሐጅ ያደረገ፤ ሐጅ በሚያደርግበት ጊዜ ከባለቤቱ ጋር ያልተገናኘና የግንኙነት ወሬም ያላ ወራ ፤ መጥፎ ነገርንም ያተናገረ ልክ እንደ ተወለደ ህፃን ወንጀል የሌለበት ሆኖ ይመለሳል››1በማለት ሁጃጆች አያሌ ፋይዳ እነደሚቀስሙ አስተምሮናል፡፡ ከብዙ በጥቂቱ፡-
ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ
1
.
3
1-ሐጅ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል አምስተኛው ነው ፡፡ እናም ሙስሊሞች በየአመቱ በማንም ምርጫ ሳይሆን በአንድ አላህ ምርጫና ጥረ ብቻ ከምስራቅ ፤ ከምእራብ ፤ ከሰሜንና ከደቡብ በመሰብሰብ አንድነታቸዉን ፤ ወንድማማችነታቸዉን ፤ እኩልነታቸዉን ፤ ተዛዛኝነታቸዉን ፤ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር ያሳያሉ ፡፡ ከአለባበሳቸው ጀምረው እስከመሪ ቃላቶቻቸው ገና በመግቢያው ላይ ለበይክ ከሚለው አንስቶ በኋላም አላሁ አክበር እስከሚሉት የፆሎት ቃሎች ይገልጧቸዋል፡፡ 2-ሙስሊሞች በያሉበት ወደ አንድ ቂብላ (ከዕበህ)በመዞር እንደሚሰግዱ ሁሉ ፤ የሶላት አሰጋገድ ፤ የዘካ አሰጣጥ ፤ የፆምም አፈፃፀም ልክ እንደዚሁ የሙስሊሙን አንድነት አብሳሪዎች ናቸው ፡፡ የሐጅም ተግባር ልክ እንዲሁ የሙስሊሙ አንድነት በይፋ የሚታይበት አምልኮታዊ ተግባር ነው፡፡ 3-ሐጅ ሰዎችን ለማስተማር አመች ወቅት ነው ፡፡ ሁሉም በየ ቤቱ የነበረዉን የግል ስራዉን እርግፍ አድረጎ በመተው ስለመጣና በየቤቱ ራሱን ከፍ ከፍ ያድርግ የነበረ ሁሉ ዝቅ ብሎ ሀብታሙ ከድሆች ጋር ፤ ዓሊሙ ከጃሂሎች ጋር ፤ ተደባልቆ የሚያልፍበት ሰዐት በመሆኑ ነበር ነቢዩ በዐረፋ፤በሙዝደሊፋ ፤ በሚናና በጉዟቸው ላይ በነበራቸው ቆይታዎች ላይ ሁሉ ሰፊ ትምህርት ይሰጡ የነበሩት ፡፡ አሁንም እነዚህኑ እድሎች በመጠቀም አዋቂዎች ጥረታቸዉን ቀጥለዋል ፡፡ ለሐጅ የታደልን ሰዎችም በዚሁ እድል በመሳተፍ እውቀታችንን ልናዳብር ይገባናል ፡፡ ምክኒያቱም ብዙ ሁጃጆች ባለማወቅ ወይም በችለተኝነት ስለ ሐጅ ምንም የማያውቁ ከዚህም አልፎ በሽርክና በቢድዓ የተዘፈቁ ሁነው ወደ ሐጅ የሚመጡ አሉ ፡፡ ከዚያም የባሱ ለጂን ፤ ለዛር ፤ ለመቃብር ፤ ለዶሪህ እየተሳሉ ፤ እያረዱ ...ባሉበት ሳይቶብቱ ወደ ቀብር የሚገቡ አሉ ፡፡ ይህንን የማስተማር ሃላፊነት ደግሞ በዋነኝነት የተጣለው በዐሊሞች ላይ ነው ፡፡ 4-ሐጅ በተለይ ተውሂድን ለመማር ሰፊ እድልን ይከፈታል ፡፡ ምክኒያቱም ከመጀመሪያው ከተልቢያው አንስቶ በዉስጡ እንዲወሱ የተደነገጉት ዉዳሴዎች የተውሂድን ዋናዉን ከፍል በተደጋጋሚ ያስታዉሳሉ ፡፡ ለምሰዳሌ የኢህራምን ልብስ ከመልበስ ጀምሮ እስከ ጠጠር ዉርወራው ድረስ ያሉት ተግባሮቹ የአላህን የአምልኮ ብቸኛነት በጉልህ ያስተምራሉ ፡፡
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
الحج والتوحيد
ሐጅና ተውሂድ
ከዚህ በታች የሐጅንና የተውሂድን ጥብቅ ግንኙነት በአጭሩ እጠቅሳለሁ ፡፡ 1-ቁርኣን በአልበቀረህ ምዕራፍ በ196ኛው አንቀፅ ላይ ( اْلَ َّج َوالح ُع حمَرَة لملَّ مه )وأَمِتُّوا ح َ (ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈፅሙ ፡፡....) በማለት ሐጅና ዑምራ ሊፈፀሙ የሚገባቸው ለአላህ ብቻ በፍፁምነት መሆኑን ያዉጃል ፡፡ 2-ተልቢያ ( ለበይክ.....) ምክኒያቱም ትርጉሙ አቤት ጌታየ አቤት....ማለት ከመሆኑም በተጨማሪ በዚህች በአጭር ዚክር ላይ ብቻ አቤቱ የሚለውቃል ሶስት ጊዜ ፤ አጋር የለህም የሚለው ደግሞ ሁለት ጊዜ መደጋገሙ የተውሂድን አሳሳቢነት ይገልፃል ፡፡ 3-ጃቢር በዘገቡት ሐዲስ (አቤት ፤ ጌታየ አቤት ፤ አቤት አንተ አጋር አልባ የሆንከው ጌታ አቤት ፤ ምስጋናም ፀጋም ለለአንተ ብቻ ነው ፡፡ ንግስናም ለአንተ ብቻ ነው ፡፡ ንግስናም እንዲሁ ለአንተ ቢጤ አልባ ለሆንከው ጌታ ተገቢ ነው) በማለት ድምፃቸዉን ከፍ አደረጉ) 2 ብለዋል ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ሱሃቢዩም ይህኑ ጉዳይ እንደተገነዘቡ ያመለክታል፡፡ 4-አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስመረ (አቤት አንተ የዐውነቱ ጌታ አቤት የሚለዉን ጨምረዋል ) 3 ማለታቸው እና 5-አነሰም በዘገቡት ሐዲስ (አላህ ሆይ ይዩልኝና ይስሙልኝ የሌለባት አርግልኝ ) የሚለዉን ይጨምሩ ነበር) ብለዋል ፡፡ 4 ይህን ሁሉ በጥሞና ስንመለከት በሐጅ ተግባር ዉስጥ ተውሂድ የቱን ያህል ትኩረት እንዳገኜ ና ነው፡፡
2
ሙስሊም. 3 ኢብኑ ማጀህ. 4 ኢብኑ ማጀህ. .
5
6- ከጦዋፍ በሃላ በሚሰገዱት ሁለት ረከዓዎች ሁለቱን የኢኽላስ ምዕራፎች (ቁል ያአዩሃል ካፊሩን እና ቁል ሁወ አላሁ አሀድን እንዳነበቡ ተዘግቧል ፡፡5 7-ጃቢር በዘገቡት ሐዲስ በሶፋና በመርዋ ላይ ሶስት ሶስት ጊዜ በነደጋገም ያደረጉት ዱዓ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ስለ ተውሂድ ነው፡፡ 8-ነቢዩ እኔም ሆንኮ ከእኔም በፊት የነበሩት ነቢያት ካልነው ዉስጥ በላጩ ( ከአላህ ዉጭ በእውነት የሚገዙት ብቸኛና ቢጤ የለሽ ጌታ የለም ስልጣንና ምስጋና ለርሱ ብቻ ነው ፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ቻይ ነው የሚለው ነው) ብለዋል ፡፡ 6 ይህም የተውሒድን ክብደት ከሚያስረዱት ዋናው ነው ፡፡ 9-በአረፋ ቀን አብዛኛው የነቢዩ ዱዓ (ከአላህ ዉጭ በእውነት የሚመለክ የለም) የሚለው እንደነበር ተዘግቧል ፡፡ 7 እነዚህና መሰል የሐጅ ተግባራትና ሂደት የሚያጠነጥነው አምልኮ ለአንድ አላህ ብቻ እንጂ ለማንም እንደማይገባ ነው፡፡ ዉድ ሁጃጆች የሐጅንና የዑምራን አፈፃፀም አስመልክቶ አጠር ያለ ፀሑፍ አዘጋጅቻለሁና በጥሞና እንድታነቡት በአክብሮት እጋብዛለሁ ፡፡ ይህ የሐጅ እና የዑምራ ፆሎት አፈፃፀም አጭር ማብራሪያ የሚለዉ መፅሐፉ የሐጅንና የዑምራን አምልኮታዊ ተግባራትን በዝርዝር ፤ የመካ ትሩፋትንና የመዲና መስጂድን ጉብኚትን በዋነኝነት ይዳስሳል ፡፡ እነሆ መፀሐፉ በዘጠኝ ዋና ዋና ርዕሶች ተከፍሏል ፡፡ ስለ ሐጅ እና ስለ ዑምራ አፈፃፀም ሰፋ ባለ መልኩ ከየመዝሀቦች ከማስረጃ አኳያ ጠንከር ያለዉን በበመረጥ፤ የታላቋን ከተማ የመካን ክብር ፤ አያሌ አስደናቂ ፤ አስገራሚ እንዲሁም ገሳጭና አስጠንቃቂ መልዕክቶችን ያዘለዉን በተለይም ከሀገሪ ኢትዮጵያ ወደ መካ ለሚጓዙ ሑጃጆች ፤ ጎብኚዎች ፤ ኗሪዎችና ለጠቅላላ ሙስሊሞች የተሰጡ ጠቃሚ ትምህርቶች ፤ ማብራሪያዎች እና ምክሮችን መፅሐፍ በአጭሩ በማካተት፤ የታላቋንና የሁለተኛዋን ከተማ የመዲናን ክብር ፤ በተለይም ከሀገራችን ወደ መዲና ለሚጓዙ ፤ ጎብኚዎች ፤
5
ቲርሚዚ. ቲርሚዚ. 7 አህመድ. 6
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ኗሪዎችና ለጠቅላላ ሙስሊሞች የተሰጡ ጠቃሚ ትምህርቶች ፤ ማብራሪያዎች እና ምክሮች ተካተዉበታል፡፡ ስለዚህ ሐጃችሁን በአግባቡ ለመፈፀም ይረዳችሁ ዘንድ ይህን መፅሐፍ በቅድሚያ እንድታነቡት እመክራለሁ ፡፡ መፅሐፉ አንድጊዜ ብቻ ተነቦ የሚተው ሳይሆን ሐጅህን/ዑምራህን እስከምትፈፅም ድረስ እንዳይለይህና ለመሰል ተግባር ለተዘጋጁ ወንድሞችህም መልካም ስጦታ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ በጋራ ሁናችሁ ብታነቡት የበለጠ ዉጤታማ ይሆናል ብየም አምናለሁ ፡፡ ሐጃችሁን በትክክለኛው መንገድ ለመፈፀም እንዲያድላችሁ አላህን እለምናለሁ ፡፡ ከዚያም አላህ በሰላም ወደ የሀገራችሁ እንዲመልሳችሁ በመልካም ስሞቹና በምሉዕ ባህሪያቱ እለምነዋለሁ ፡፡ 9-እኛ ሙስሊሞች ልንተገብራቸው ከሚገባን ዋና ዋና አምልኮታዊ ተግባሮች መካከል በመካ እንጂ በሌላ ቦታ የማይፈፀሙት ሁለቱ የሐጅና የዑምራ ፀሎቶች ናቸው ፡፡ ይህ ፁሑፍም በእነዚሁ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ ዉድ ወንድሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የዑምራን ተግባር ለማድረግ ካሰብክ ጥቂት ጊዜ ወስደህ ይህን መልዕክት በጥሞና አንብብ ፡፡ ይህን ያልኩህ ብዙ ግር የሚሉህን ነገሮች ይፈታልሃል ብየ በማሰብ ነው ፡፡ ተስማማን በል ቢስሚላህ በልና ንባብክን ጀምር ፡፡ ቢበዛ ሁለት ቀን ወይም ከዚያ ያነሰ ነው የሚወስድብህ ፡፡ የሚሰጥህ ትምህርት ግን ያንን የጀነት ባለሟል የሚያደርግህን የዑምራንና የሐጅን ፀሎት በትክክል እንድትተገብር የሚያስችልህን እውቀት ነው ፡፡ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ ! ኢስላም የተመሰረተው በአምስት ዋና ዋና ዋልታዎች ላይ ነው ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ የሚያስፈልግ አይመስለኝም ፡፡ ምክኒያቱም አላህ በቁርኣኑ በብዙ አንቀፆች ፤ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺበትክክለኛ አያሌ ሐዲሶቻቸው በሰፊው አስተመረዉታልና ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡፡ ቁርኣን እንዲህ አለ፡اْلرمام الَّ مذي جع حلناه لملنَّا م سوا الحعاكم يم ميه والحبا م مم م َّ م م َّ م ُ َ ََ ُ َين َك َفُروا َوي َ َ ُ َ ََ ا َ إ َّن الذ ََصدُّو َن َع حن َسب ميل الله َوالح َم حسجد ح ) وإم حذ ب َّوأحنَا ممِلب ر ماهيم م َكا َن الحب ي م52( اب أَلمي ٍم ٍ ومن ي مرح يم ميه بممإ حْلا ٍ بمظُحل ٍم نُ مذقحهُ ممن َع َذ ت أَ حن ََل تُ حش مرحك مب َح َ َ َح َ َ ح َ ُ ََ ح شيئا وطَ ِّهر ب ي م م مم مم وك مر َج ااَل َو َعلَى ) َوأَذِّ حن مِف النَّا م بم ح52( الس ُجوم َ ُاْلَ ِّج يَأحت ُّ الرَّك مع ُّ ني َو َ ني َوالح َقائم َ ِت للطَّائف َ َ ح ا َ ح َح ٍ ) لمي حشه ُدوا منَايمع ََلم وي حذ ُكروا اسم اللَّ مه مِف أَيَّ ٍام معلُوم52( ُك ِّل ض مام ٍر يأحتمني ممن ُك ِّل يَ ٍّج ع مم ٍيق ات َعلَى َ َ َح َ َ َ ح َ َ َ َ َ ُح َ َ ُ ح م م م م ما رزقَهم ممن ََبم م م ضوا تَ َفثَ ُه حم َولحيُويُوا نُ ُذوَرُه حم ُ ) ُُثَّ لحيَ حق52( س الح َفق َري َ َ ََ ُ ح ح َ يمة حاْلَنح َعام يَ ُكلُوا محن َها َوأَطحع ُموا الحبَائ .
7
م م م م م م ولحيطََّّويُوا بمالحب ي م ت لَ ُك ُم حاْلَنح َع ُام َ ) ذَل52( ت الح َعتم ميق ك َوَم حن يُ َعظِّ حم ُحُرَمات اللَّه يَ ُه َو َخحي ٌر لَهُ عحن َد َربِّه َوأُحلَّ ح َح ََ الرج م إمََّل ما ي حت لَى علَي ُكم يَ م م )03( الزومر ُّ اجتَنمبُوا قَ حو َل س م َن حاْل حَوثَان َو ح َ ُ َح ح ح َ اجتَنبُوا ِّ ح (እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችን ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት ሰዎች እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ ማንኛውንም ነገር የሚያስብ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን ፡፡ መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ ፡፡ ቤቴንም ለሚዘይሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ ፡፡ ኢብራሂም ሆይ ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ ፡፡ እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ በከሳዋ ግመሎች ላይ እንኳን ሆነው ይመጡልሃልና ፡፡ ለእነሱ የሆነ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእኒያ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል ፡፡ ከእርሷም ብሉ ፡፡ ችግረኛንም አብሉ ፡፡ ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ ፡፡ ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ ፡፡ በጥንታዊውም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ አልን ፡፡ የሐጅ ሥርአት ይህ ነው ፡፡ የአላህን ህግጋት8 የሚያከብር ሰው ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው ፡፡ የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች ፡፡ ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ) አል ሐጅ 25.30 የአላህ መልዕክተኛ () እንዲህ ብለዋል፡- ‹ይህን ቤት ካዕባን ሐጅ ያደረገ ሐጅ በሚያደርግበት ጊዜ ከባለቤቱ ጋር ያልተገናኘና መጥፎ ነገር ያልተናገረ ልክ እንደ ተወለደ ህፃን ወንጀል እንደሌለበት ሆኖ ይመለሳል ›9 8
ምልክት ሊባልም ይቻላል ፡፡ ይህም ማለት ለእሱ መገለጫ ይሆን ዘንድ ለሰዎች ይፋ ያደረጋቸው ትዐዛዛቱና ክልክሎቹ ፤ ለርሱ ፆሎት የሚደረግባቸው ቦታዎች ማለት ነው ፡፡ 9 -ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ. الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
በእነዚህ በተባረኩ ቀናት ብዙ ሰዎች ከየ አካባቢው ያን የነቢዩ ኢብራሂምን ጥሪ በማክበር ወደ ታላቋ ሀገር ወደ መካ ይጓዛሉ ፡፡ ሶላትና ሰላም ለነቢዩ ፤ ለንፁሃን ቤተሰቦቻቸው ፤ ለባል ደረቦቻቸው እንዲሁም በቀናው መንገድ እስከ ዐለም ፍፃሜ ድረስ ለተከተሏቸው ትክክለኛ ሙስሊሞች ሁሉ እንዳይለያቸው አላህን እለምናችኃለሁ ፡፡ ዉድ ሁጃጆች አላህ መንገዱን ቀና አድርጎላችሁ ፤ እንኳን ደህና መጣችሁ ፡፡ ሐጃችሁን እና ዑምራችሁን አላህ ይቀበላችሁ ፡፡ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ !
.
9
ለ-የጉዞ ስነ ስርዐቶች آداب السفر ዉዱ የሐጅ ተጓዡ ወንድሜ ሆይ ! ዉዷ የሐጅ ተጓዡ እህቴ ሆይ ! የጉዞ ስነ ስርዐቶችን በደንብ ታውቃላችሁን ? ካወቃችሁ ክለሳ ይሆናል ካላወቃችሁም በጥሞና እንድትማሩት በር ይከፍትልና ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ነገሮች በጥሞና ተከታተሉ፡፡ 1-ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፡- አልሀመዱ ሊላሂ አለዚ አህያና በዕደ ማ አማተና ወኢለይሂ ኑሹር 2-ከቤትህ ስትወጣ፡-(አላሁመ ኢኒ አኡዙ ቢከ አን አዲለ አው ኡደል አው አዚለ አው ኡዘለ አው አዝሊመ አው ኡዝለም አው አጅሃለ አው ኡጅሃል አው ዩጅሃለ ዐለየ) (ቢስሚላሂ ተወከልቱ አለላህ ወላ ሃውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ) 3-ከዉጭ ወደ ቤትህ ስትመለስ ፡- ቢስሚላሂ ወለጅና ወቢስሚላሂ ኸረጅና ወዐላ ረቢና ተወከልና 4-ምግብ ስትበላ፡-ቢስሚላህ 5-የሚጠጡ ነገሮችን ስትጠጣ፡-ቢስሚላህ 6-ስትተኛ፡-ቢስሚከላሁመ አሙቱ ወአህያ 7-ወደ ሺንትቤት ስትገባ፡-አላሁመ ኢኒ አኡዙ ቢከ ሚነል ኸቢሲ ወል ኸባኢሲ 8-ከሺንት ቤት ስትወጣ፡-ጉፍራነክ 9-ወደ መስጂድ ስትገባ ፡-ቢሰሚላህ ወል ሐምዱ ሊላህ ወሰላቱ ወሰላሙ አላ ረሱሊላህ አላሁመ ግፊር ሊ ዙኑቢ ወፍተህሊ አብዋበ ረህመቲክ 10-ከመስጂድ ስትወጣ ፡-ቢስሚላህ ወል ሐምዱ ሊላህ ወሰላቱ ወሰላሙ አላ ረሱሊላህ አላሁመ ግፊር ሊ ዙኑቢ ወፍተህሊ አብዋበ ፈድሊክ:: 11-ስትቆጣ፡-አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጣኒ ረጂም ፡፡ ኢሰላም ለሁሉም ነገር ሙሉ ስነ ስርዐት አለው ፡፡ ለምሳሌ ከዚህ በታች ያሉትን ጉዳዮችና ሥነሥርዐቶች ብንመለከት የዚህን አባባል አውነታ እናረጋግጣለን ፡፡ ለምሳሌ ሀ-ከጉዞ በፊት መከናዎን የሚገቡ ነገሮች 1-ትክክለኛ ተውበት በማድረግ ለአላህ ፍፁም ታዛዥ መሆን አለባቸው፤ 2-ያስቀመጡት የሰዎች የገንዘብ አማና ካለ መመለስ ፤ 3-በመሀከላቸው ያለን ቅሬታ ማስወገድ፤ 4-ከቤተሰቡ ሙሉ ዐፉታን መጠየቅ ፤ 5-ስለ ሐጅና ዑምራ ጠንቅቆ ማወቅና ለዚህም የሚሆኑ መፅሐፍትን መያዝ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
6-የመካንና የመዲናን ክብር ጠንቅቆ መረዳት፤ 7-ያለበትንም ሆነ በሰው ላይ ያለዉን የሚገልፅ ኑዛዜን መፃፍ ፤ 8-ለሐጁ ሐላል እና ንፁህ ገንዘብ መምረጥ ፤ 9-ለጉዞው መልካም ጓደኞችን መምረጥና፤ 10-በቂ ስንቅ መያዝ ናቸው፤ ለ-በጉዞ ወቅት መከናዎን የሚገቡ ነገሮች፤ 1-በመልካም ስነ ስርዐት መታነፅ ፤ 2-አብዛሃኛዉን ሰዐት ዚክር ፤ ዱዓ ፤ በማድረግ ማሳለፍ፤ 3-ምላስን ጆሮን አይንንና ባጠቃላይ ሙሉ ሰዉነቱን ከሆነ ካልሆነው ሁሉ መጠበቅ ፤ 4-በሌሎች ላይ አዛ/ችግር/ ከሚያደርሱ ነገሮች ሁሉ መጠንቀቅ ፤ 5-አውሮፕላን ወይም መኪና ላይ ሲወጣ ከዚህ በታች ያለውን ዱኣ ያድርግ፤ ከቁርኣን እንዲህ አለ፡م م استَ َويحتُ حم َعلَحي مه َوتَ ُقولُوا ُسحب َحا َن الَّ مذي َس َََّّر لَنَا َه َذا َوَما لتَ حستَ ُووا َعلَى ظُ ُهومرهم ُُثَّ تَ حذ ُكُروا ن حع َمةَ َربِّ ُك حم إمذَا ح م )31( ) َوإمنَّا إم ََل َربِّنَا لَ ُمحن َقلمبُو َن30( ني َ ُكنَّا لَهُ ُم حق مرن (በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ፀጋ እንድታስታውሱ ፤ እንድትሉም ያ ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ የገራልን ጌታ ጥራት ተገባው ፡፡ እኛ በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን እንድትሉ ነው ) አዙኽሩፍ 13-14 -ሙስሊም ፣ አቡዳውድና ነሳኢ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ ሙሐመድ () ፈረሳቸውን ሲጋልቡ ሶስት ጊዜ አሏህ አክበር፤ አሏህ አክበር፤ አሏህ አክበር ካሉ በኋላ (ሱብሃነለዚ ሰኸረ ለና ሃዛ ወማ ኩናለሁ ሙቅርኒን ወኢና ኢላ ረቢና ለሙንቀሊቡን) አላሁመ ኢና ነሰአሉከ ፊሰፈሪና ሀዛ አልቢረ ወትተቅዋ ወሚነልዐመሊ ማተርዷ አላሁመ ሀዊን ዐለይና ሰፈረና ሃዛ ወጥዊ ዐና ቡዕደህ አላሁመ አንተ ሷሂቡ ፊሰፈር ወልኸሊፈቱ ፊልአህል አላሁመ ኢኒአዑዙ ቢከ ሚን ወዕሳኢ ሰፈር ወከኣበቲል መንዞር ወሱኢል ሙንቀለብ ፊልማሊ ወል አህል ›› ይሉ ነበር ፡፡ .
11
(አሏህ አክበር ማለት አላህ የታላቆች ታላቅ ነው! አላህ የታላቆች ታላቅ ነው ! አላህ የታላቆች ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡) ይህን መጓጓዣ ያገራልን ጌታ ፍጹማዊ ነው ፡፡ እኛ ይህን ለመፈፀም የምንችል አልነበርንም ፡፡ የመጨረሻ መዳረሻችንም ወደ ጌታችን ነው ፡፡ አላህ ሆይ! በዚህ ጉዟችን መልካም መሥራትን (ቢር) ከመጥፎ መከልከልን (ተቅዋ) የምትወደውን ነገር እንድንፈጽምም እንጠይቅሃለን ፡፡ አላህ ሆይ ! ይህን ጉዞአችንን አመቻችልን፤ በአጭር ጊዜም የምንቆርጠው አድርገን ፡፡ አላህ ሆይ ! አንተ በጉዞ ላይ ጓደኛ (ባልደረባ) ነህ ፡፡ የቤተሰብም ምትክ (ዋቢ) ነህ ፡፡ አላህ ሆይ ! እኔ ከጉዞ ጣጣ ከአመለካከት ለውጥና በንብረትና በቤተሰብ ላይ መጥፎ ነገር ደርሶ በመመለስ በአንተ እንበቃለሁ ፡፡) ከጉዞ ሲመለሱም የተጠቀሰውን ፀሎት ካነበቡ በኋላ ይህን ይበል :- ኣይቡን ታኢቡን ዓቢዱን ሊረቢና ሃሚዱን› (ተውበት አድርገ ፤ (አላህን) እየተገዛና ጌታችንን አመስጋኞች ሆነን ተመልሰናል) ضى اللَّهُ َّم ه َِّو ْن َعلَ ْينَا َ ْ«اللَّهُ َّم إِنَّا نَسْأَلُكَ فِي َسفَ ِرنَا هَ َذا ْالبِ َّر َوالتَّ ْق َوى َو ِم ْن ْال َع َم ِل َما تَر ْ َسفَ َرنَا هَ َذا َو َّاحبُ فِي ال َّسفَ ِر َو ْالخَ لِيفَةُ فِي اۡلَ ْه ِل اللَّهُ َّم ِ اط ِو َعنَّا بُ ْع َدهُ اللَّهُ َّم أَ ْنتَ الص 10 »ال َواۡلَ ْه ِل ِ َإِنِّي أَ ُعو ُذ بِكَ ِم ْن َو ْعثَا ِء ال َّسفَ ِر َو َكآبَ ِة ْال َم ْنظَ ِر َوسُو ِء ْال ُم ْنقَل ِ ب فِي ْال َم ) َآيِبُونَ تَائِبُونَ عَابِ ُدونَ لِ َربِّنَا َحا ِم ُدون 6-ፈርድ ሶላቶችን በመስጂድ በጀማዓ መሰግድ ላይ መጣጣር ፤ 7-አቅሙ በፈቀደለት መጠን ሁጃጆችን የማያውቁትን ማስተማር ፤ የተሳሳቱትን ማስተካከል፤ ችግራቸዉን ማቃለል ፤ 8-አብረው ከሚሄዱት ሁጃጆች መካከል አንዱን በመምረጥ አሚር ማድረግና በሱ መመራት፤ 9-ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት ሁለት እያረጉ መስገድ ፤ 10-በሚሰፍርበት ቦታ ሲደርስ ለዚህ ቦታ የተደነገገዉን ዱዓ ማድረግ፤ 11-ከሱብሂ ሱና እና ከዊትር ሱናዎች በስተቀር ሱናዎችን አለመስገድ፤ እነዚህን ስርዐቶች በየጉዟችን ሁልጊዜም ልናከብራቸው የሚገቡ ቢሆንም በሐጅ ጊዜ ድግሞ የበለጠ ነው፡፡ 10
ሙስሊም الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
العمرة
ክፍል አንድ ፡ ቅድሚያ ስለ ዑምራ አፈፃፀም በአጭሩ
معنى العمرة
1-1.የዑምራ ትርጉም
ዑምራ የሚለው የጥሬ ቃል ትርጉም የተከበረውን የአላህን ቤት መጎብኘትና የዑምራን የአምልኮ ተግባር በውስጡ ለመፈፀም ማሰብ ማለት ነው ፡፡ حكم العمرة
1-2. የዑምራ ፆሎት ብይን
ሀ-የዑምራ ፆሎት ግዴታ ነው የሚለው የብዙ ዐሊሞች ማለትም የኢማሙ ሻፊዕ ፣ የኢማሙ አህመድ ፣ የኢማሙ ቡኻሪ እና ሌሎችም የመረጡት አቋም ነው ፡ ፡ ለ-ሱና ነው የሚለው ነው ፡፡ ይህ ኢማሙ አቡ ሐኒፋህ ፣ ኢማሙ ማሊክና ኢማሙ ኢብኑ ተይሚያህ የመረጡት አቋም ነው ፡፡ ሆኖም ከማስረጃ አኳያ የመጀመሪያው ጠንካራ ነው፡፡ በመሆኑም በእድሚያችን አንድ ጊዜ መተግበር ግድ ይላል፡፡ أركان العمرة
1-3.የዑምራ ግዴታዎች
የዑምራ ማዕዘናት ሶስት ተግባሮች ብቻ ናቸው ፡፡ እነሱም ፡1) ኢህራም ማድረግ ፤ 2) የዑምራ ጦዋፍና 3) የዑምራ ሰዕይ ናቸው፡፡ 1-4.የዑምራ ዋጂቦች واجبات العمرة የዑምራ ዋጂቦቹ 11 ደግሞ ሁለት ተግባሮች ብቻ ናቸው ፡፡ እነርሱም ፡1) ከቦታው ኢህራም ማድረግና፤ 2) ፀጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር የሚሉት ናቸው፡፡ سنن العمرة
1-5. የዑምራ ሱናዎች 1-የጉዞ ስርዓቶችን በቻለው አቅም መጠበቅ 2-በኢህራም ግዜ ገላዉን መታጠብ ፤ መፀዳዳትና ሽቶ መቀባት፤
11-ዋጂቦችና ግዴታዎች የሚሉ ተግባራት በዚህ ረዕስ ላይ በሁሉም መዝሀቦች ዘንድ ልዩነት አላቸውና በደንብ ለይቶ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ .
13
3-ነጫጭና ንፁህ የሆኑ የኢህራም ልብሶችን መልበስ፤ 4-ዑምራውን በቃሉ ለበይክ አላሁመ ዑምረተን ማለቱ፤ 5-እንቅፋት ሊኖር ይችላል ብሎ ከሰጋ የምፈታው እንቅፋቱ ባጋጠመኝ ቦታ ላይ ነው ብሎ ማሰብ፤ 6-ወዲያው እንደሃረመ ተልቢያ ማብዛት፤ 7-ወንዶች በተልቢያ ግዜ ድምፃቸውን ከፍ ማድረግ ሲሆን ሴቶች ድምፃቸውን ዝቅ ማደረግ፤ 8-ተልቢያውን በተለይም ወደ ኮረብታ ሲወጣ ወደ ዝቅተኛ ቦታ ሲወርድ ወይም ሌላ ሰው ተልቢያ ሲል ቢሰማ ፤ ከሰላቶች በኋላ ፤ በስሁር ሰዓት፤ ጠዋትና ማታ ማብዛት፤ 9-ጠዋፍ እስከሚጀምር ድረስ ተልቢያን አለማቋረጥ፤ 10-መንገዱ ዚጡዋ በተባለው ቦታ አጠገብ ከሆነ በዚያው ማደርና ሰውነቱን መታጠብ በዚያ አጠገብ ካልሆነ ግን የተመቸው ቦታ አድሮ ሰውነቱን ታጥቦ በቀን መግባት፤ 11-ወደ መካ ሲገባ በከዳእ በኩል ፤ ሲወጣ ደግሞ በኩደይ በኩል መሆኑ፤ 12-ወደ መስጂደል ሐረም ሲገባ ከተቻለ በበኒ ሸይባ በር መግባት፤ 13-ወደ መስጂዱ ሲገባም ቀኝ እግርን በማስቀደም ወደ ማንኛውም መስጂድ ሲገባ የሚባለውን ዱዓ ማድረግ ሲወጣም ግራ እግሩን በማስቀደም ማንኛውም መስጂድ ሲወጣ የሚባለውን ዱዓ ማድረግ ፤ 14-ዑምራ የሚሰራ ሰው መስጂደል ሐረም ገና እንደገባ በጠዋፍ መጀመር፤ 15-ጠዋፍ ጀምሮ እስከሚጨርስ ድረስ ቀኝ እጁን ማውጣት፤ 16-ሐጀረል አስወድን በሙሉ ሰውነቱ መቅጣጨት፤ 17-ጠዋፍ ሲጀምር ቢስሚላህ አላሁ አክበር ብሎ መጀመርና አላሁመ ኢማነን ቢከ…የሚለውን ዱዓ ማንበብ በሌሎቹ ዙሮች ግን አላሁ አክበር ብቻ እያሉ መጠወፍ ፤ 18-በየዙሩ ሀጀረል አስወድን ከቻለ ራሱ ላይ እየተደፉ መሳም ካልቻለ በእጅ መንካትና እጁን መሳም ከልሆነም በዝንግ ነገር ነክቶ ዘንጉን መሳም ይህ ካልተቻለ ግን በእጅ በማመልከት ብቻ ነው፤ በዚህ ጊዜ እጅን መሳም ክልክል ነው፡፡ 19-ከመካ ውጪ የመጣ ሁሉ በዑምራ እና በጠዋፈል ቁዱም የመጀመሪያውን ሶስት ዙሮች በሶምሶማ ከዞረ በሁዋላ ቀሪ አራት ዙሮችን በተለመደ ጉዞ ማደረግ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
20-በሩክነል የማኒ አጠገብ ባለፍ ቁጥር ከቻለ በእጁ መንካት ካልቻለ ግን ማመልከትም ፤ መሳመም ሆነ አላሁ አክበር ማለት ተገቢ አይደለም፤ 21-በሩክነል የማኒ እና በሀጀረል አስወድ መካከል ረበና አቲና ፊዱንያ ሀሰነተን ወፊል አሂረቲ ሃሰነተን ወቂና አዛበናር ማለት፤ 22-በጠዋፍም ሆነ በሰዒ ወቅት ቁርኣን መቅራት፤ 23-ዚክር መዝከር ዱዓ ማድረግ፤ 24-ወሬን እና አላስፈላጊ ምልከታዎችን መተው ፤ 25-ከነጃሳ ፀድቶ በዉዱእ ጠዋፍንም ሆነ ሰዕዬን ማድረግ፤ 26-ጠዋፉንም ሆነ ሰዕይን በእግር ጉዞ ማድረግ፤ 27-ከጠዋፍ በኋላ ከኢብራሂም መቆሚያ ጀርባ አካባቢ ሁለት ረከዓን መስገድ፤ 28-ይህን ሰላት ጠዋፍ እንደጨረሱ ወዲያውኑ ማደረግ፤ 29-ይህን ሰላት ሊሰግድ ሲል ወተኺዙ ሚን መቃሚ ኢብራሂመ ሙሰላ የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ማንበብ፤ እነዚሁኑ ረከዓዎች የመጀመሪያውን በፋቲሃና በቁልያ አዩሃል ካፊሩን የሁለተኛውን ደግሞ በፋቲሃና በቁል ሁወላሁ አሃድ መስገድ፤ 30-ጠዋፍ እንደጨረሰ ወደ ሰዕዬ መሄድ የፈለገ ሰው ከቻለ ሃጀረል አስወድን ሂዶ በእጁ ሰላም ማለት ፤ እሱን መሳሙና ወደ እሱ ማመልከቱ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ 31-ጠዋፍንና ሰዕይን ማከታተል፤ 32-ወደ ሶፋ ኮረብታ ሲሄድ ኢነ ሰፋ ወል መርወተ ሚን ሸዓኢሪላህ የሚለውን በመጀመሪያው ግዜ ብቻ ማንበብ፤ 33-መስጅዱ እስከሚታየው ድረስ ወጥቶ ወደ እሱ በመዞር እጆቹን በማንሳት ሶስት ግዜ አላሁ አክበር ! ብሎ ‹‹ላኢሃ ኢለላሁ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሃምድ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለውን ማንበብ፤ 34-ከዛም ዱዓ ማድረግ እና ይህንኑ ተግባር በየዙሩ ሶስት ሶስት ግዜ መደጋገም ፤ 35-በሁለት አረንጉዋዴ ምልክቶች መካከል ጉዞን ፈጠን ፈጠን ማድረግ፤ 36-ፀጉር መላጨትና ፤ 37-ጠዋፈል ወዳዕ ማድረግ የሚሉት ናቸው፡፡ ሌሎችን ጉዳዩች በሐጅ ትምህርት ስር ስለሚጠቃለሉ አብረን እንከታተል፡፡
.
15
ክፍል ሁለት ፡-አል ሐጁ ልመብሩር معنى الحج
2-1.የሃጅ ትርጉም
ሐጅ :-የሚለው የዐረበኛ ጥሬ ቃል ትርጉሙ የተከበረውን የአላህን ቤት መጎብኘትና የሐጅን የአምልኮ ተግባር በውስጡ ለመፈፀም ማሰብ ማለት ነው ፡፡ የሸሪዓ ት ርጉሙ ደግሞ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች የተሟሉለት ሰው ወደ መካ ተጉዞ የሐጅን ሥርዓተ ፀሎት አከናውኖ ለመመለስ ማሰብ ነው ፡፡ ይህም ማለት ወደ መካ ተጉዞ የሐጅን ሥርዓተ ፆሎት አከናውኖ ለመመለስ አስፈላጊ ሁኔታዎች የተሟሉለት ሰው ሁሉ በሕይወት ዘመኑ ውስጥ አንድ ጊዜ ሐጅ የማድረግ ግዴታ አለበት ማለት ነው ፡፡ በስለት ምክኒያት ከአንድ ጊዜ በላይ መጓዝም ግዴታ ነው፡፡ حكم الحج
2-2.የሐጅ ፆሎት ብይን
ሐጅ ፡-ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ የሐጅ ፆሎት መፈፀም በእድሜ አንድ ጊዜ ግዴታ ነው፡፡ የሀጅ ተግባር ከታላላቅ የአምልኮ ስርዐቶች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ትክክለኛው ሀጅ ፈፃሚዉን ከወንጀል አፅድቶ ልክ ከእናቱ ሆድ እንደወጣ እንደሚያደርገው እና ምንዳውም ጀነት መሆኑን ረሱል ( )ﷺአውስተዋል ፡፡ በተጨማሪም ሀጅ የአለም አቀፍ ኢስላማዊ አንድነት ፡፡ ወንድማማችነትና እኩልነት ይፋዊ መገለጫ ነው፡፡ 2-3. የሐጅና የዑምራ ፆሎቶች ትሩፋት በቁርኣን እና በሐዲስ فضل الحج والعمرة في القرآن الكريم ዉድ ወንድሜ/ እህቴ/ ከዚህ በመቀጠል ያሰፈርኳቸዉን የቁርኣን አንቀፆች በጥሞና በማንበብ ያልገባችሁን አዋቂዎችን በመጠየቅ የሐጅንና የዑምራን ዋና ዐላማዎች በመረዳት ዉጤታማ ሐጅና ዑምራ እንድታደርጉ በቅድሚያ አደራ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
አደራ… እላለሁ ፡፡ ምክኒያቱም ብዙ ሐጃጆች ላ! ለበይክ ማለትም ለፍተው መና የሚሆኑ ሑጃጆች ስላሉ ነው ፡፡ አንደኛ ቁርኣን አል በቀራህ ምዕራፍ 197-203 ያሉት አናቅፅ እንዲህ ይነበባሉ፡፡ اْلَ ِّج َوَما تَ حف َعلُوا مم حن وق َوََل مج َد َال مِف ح ض يمي مه َّن ح ح ث َوََل يُ ُس َ اْلَ َّج يَ ََل َريَ َ وم ٌ ات يَ َم حن يَ َر َ اْلَ ُّج أَ حش ُهٌر َم حعلُ َ خ ٍري ي علَمه اللَّه وتَزَّو وا يَإم َّن خي ر َّ م م م م اح أَ حن َح َح ح ُ ُ َ َ ُ س َعلَحي ُك حم ُجنَ ٌ َحَ الزا التَّ حق َوى َواتَّ ُقون يَا أُوِل حاْلَلحبَاب ( )322لَحي َ ضتم ممن عريَ ٍ تَبت غُوا يَ ح م م اْلََرمام َواذح ُكُروهُ َك َما َه َدا ُك حم ات يَاذح ُكُروا اللَّهَ معحن َد الح َم حش َع مر ح حَ ض اَل م حن َربِّ ُك حم يَإذَا أَيَ ح ُ ح ح ََ وإم حن ُكحنتم ممن قَبلم مه لَ ممن الضَّالِّني (ُُ )322ثَّ أَيميضوا ممن حيث أَيَاض النَّا و م ُ ح َح ُ َ استَ حغفُروا اللَّهَ إم َّن اللَّهَ َ ُ َح َ ُح ح ح َ م َغ ُفور رمحيم ( )322يَإم َذا قَضيتم منَ م َش َّد مذ حكارا يَ مم َن النَّا م َم حن اس َك ُك حم يَاذح ُكُروا اللَّهَ َكذ حك مرُك حم آَبَا َ ُك حم أ حَو أ َ َ حُ ح َ ٌَ ٌ ول َربَّنَا آَتمنَا مِف الدُّنحيَا ول َربَّنَا آَتمنَا مِف الدُّنحيَا َوَما لَهُ مِف حاْلَ مخَرةم مم حن َخ ََل ٍق (َ )533وممحن ُه حم َم حن يَ ُق ُ يَ ُق ُ ص م م م م اْلمس م اب اب النَّا مر ( )533أُولَئم َ َح َسنَةا َومِف حاْلَخَرةم َح َسنَةا َوقنَا َع َذ َ يب ِمَّا َك َسبُوا َواللَّهُ َس مر ُ ك ََلُ حم نَ ٌ يع ح َ ٍ م ٍ ات يَم حن تَ َع َّجل مِف يَوَم ح م َخَر يَ ََل إم حُثَ َعلَحي مه لم َم من ني يَ ََل إم حُثَ َعلَحي مه َوَم حن تَأ َّ َ ح (َ )535واذح ُكُروا اللَّهَ ِف أَيَّام َم حع ُدوَ َ اتَّ َقى َواتَّ ُقوا اللَّهَ َو حاعلَ ُموا أَنَّ ُك حم إملَحي مه ُحُت َشُرو َن ()530 ‹‹ሙስሊሞች ሆይ ! ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈፅሙ ፡፡ ከጀመራችሁ በኋላ ብትታገዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ ፡፡ ሀድዩ /የመስዋዐት እንሰሳት/ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ ፡፡ ከእናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ራሱን ቢላጭ መፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት ፡፡ ፀጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈፀሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈፀም የተገላገለ ሰው ከሀድይ የተጋራውን መሰዋት አለበት ፡፡ ሀድይን ያላገኘም ሰው ሶስት ቀናት በሐጅ ወራት ፤ ሰባትንም ቀናት ደግሞ ወደ መኗሪያችሁ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት ፡፡ እነዚህ ሙሉ አስር ቀናት ናቸው ፡፡ ይህም ህግ የሚያገለግለው ቤተሰቦቹ በቅዱስ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ሰዎች ብቻ ነው ፡፡ አላህንም ፍሩ ፡፡ ሐጅ የሚፈፀመው በተወሰነለት ወራት ነው ፡፡ እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው ሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት ፤ በአላህ ላይ ማመጽና ከጓደኛው ጋር ክርክር አያደርግም /አያድርግ/ ፡፡ የምትሰሩትን በጎ ስራ ሁሉ አላህ በትክክል .
17
ያውቀዋል ፡፡ ሙስሊሞች ሆይ ! ስንቅ ያዙ ፡፡ ከስንቅም ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ ! እኔን ብቻ ፍሩኝ ፡፡ በሐጅ ጊዜ በንግድ ስራ ከጌታችሁ ትርፍን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም ፡፡ ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁ ጊዜ መሸአረል ሀረም ዘንድ ስትደርሱ አላህን በብዛት አውሱ ፡፡ ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም ዝከሩት ፡፡ ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ ፡፡ ቁረይሾች ሆይ ! ከዚያም ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ አብራችሁ ተንቀሳቀሱ ፡፡ አላህንም ምህረት ለምኑት ፡፡ አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና ፡፡ የሐጅ ስራዎቻችሁን በፈፀማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከእሱ ይበልጥ የበረታን አላህን አውሱ ፡፡ ከሰዎችም ውስጥ ፡- ጌታችን ሆይ ! በምድረ ዓለም መልካም እድልን ስጠን የሚል ሰው አለ ፡፡ ለእርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለውም ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ‹ጌታችን ሆይ ! በምድር ዓለም ደግን ነገር ፀጋን በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር ገነትን ስጠን ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን› የሚሉ ሰዎች አሉ ፡፡ እነዚያ ከሰሩት በጎ ስራ ደጎስ ያለ ድርሻ አላቸው ፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው ፡፡ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ በሚና ጠጠሮችን ስትወረውሩ አላህንም አውሱ ፡፡ በሁለት ቀናት ውስጥ ከሚና ወጥቶ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለበትም ፡፡ እስከ ሶስት ቀን ድረስ የቆየም ሰው እንዲሁ ምንም ኃጢአት የለበትም ፡፡ ይህ ምህረት አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው ፡፡ አላህንም ፍሩ ፡፡ እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም በትክክል እወቁ ›› -አልበቀረህ 196-203. አንቀፆች እንዲህ ይነበባሉ م م م ٍ م م مم م م يم ٌ َات بَيِّ ن ٌ َ) ييه آَي69( ني َ إم َّن أ ََّو َل بَحيت ُوض َع للنَّا م لَلَّذي بمبَ َّكةَ ُمبَ َاراكا َوُه ادى للح َعالَم َ ات َم َق ُام إبح َراه م م مم م اع إملَحي مه َسبم ايَل َوَم حن َك َفَر يَإم َّن اللَّهَ َغ مِ ٌّ َع من َ َاستَط َوَم حن َ َخلَهُ َكا َن آَمناا َوللَّه َعلَى النَّا م ح ُّج الحبَ حيت َم من ح م )69( ني َ الح َعالَم
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
‹‹ለሰዎች ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው ፡፡ በውስጡ ግልፅ የሆኑ ተዐምራት አሉበት ፡፡ የኢብራሂምም መቆሚያ የነበረው በዉስጡ አለ ፡፡ ወደ እርሱ የገባ ሰው ሁሉ ሰላም ይሆናል ፡፡ ለአላህ ከሰዎች መካከል ወደ እርሱ የመሄድን ጣጣ በቻለ ሰው ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኜት ግዴታ አለበት ፡፡ በአላህ የካደ ሰው ግን እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም ፡፡ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነውና››-ኣሊ ዒምራን 96-97 3ኛ በአል ሐጅ ምዕራፍ ከ 25-30 ያሉትም አንቀፆች እንዲሁ ይነበባሉ اْلرمام الَّ مذي جع حلناه لملنَّا م سوا الحعاكم يم ميه والحبا م مم م َّ م م َّ م ُ َ ََ ُ َين َك َفُروا َوي َ َ ُ َ ََ ا َ إ َّن الذ ََصدُّو َن َع حن َسب ميل الله َوالح َم حسجد ح ) وإم حذ ب َّوأحنَا ممِلب ر ماهيم م َكا َن الحب ي م52( اب أَلمي ٍم ٍ ومن ي مرح يم ميه بممإ حْلا ٍ بمظُحل ٍم نُ مذقحهُ ممن َع َذ ت أَ حن ََل تُ حش مرحك مب َح َ َ َح َ َ ح َ ُ ََ ح شيئا وطَ ِّهر ب ي م م مم مم وك مر َج ااَل َو َعلَى ) َوأَذِّ حن مِف النَّا م بم ح52( الس ُجوم َ ُاْلَ ِّج يَأحت ُّ الرَّك مع ُّ ني َو َ ني َوالح َقائم َ ِت للطَّائف َ َ ح ا َ ح َح ٍ ) لمي حشه ُدوا منَايمع ََلم وي حذ ُكروا اسم اللَّ مه مِف أَيَّ ٍام معلُوم52( ُك ِّل ض مام ٍر يأحتمني ممن ُك ِّل يَ ٍّج ع مم ٍيق ات َعلَى َ َ َح َ َ َ ح َ َ َ َ َ ُح َ َ ُ ح م م م م ما رزقَهم ممن ََبم م م ضوا تَ َفثَ ُه حم َولحيُويُوا نُ ُذوَرُه حم ُ ) ُُثَّ لحيَ حق52( س الح َفق َري َ َ ََ ُ ح ح َ يمة حاْلَنح َعام يَ ُكلُوا محن َها َوأَطحع ُموا الحبَائ م م م م م م ولحيطََّّويُوا بمالحب ي م ت لَ ُك ُم حاْلَنح َع ُام َ ) ذَل52( ت الح َعتم ميق ك َوَم حن يُ َعظِّ حم ُحُرَمات اللَّه يَ ُه َو َخحي ٌر لَهُ عحن َد َربِّه َوأُحلَّ ح َح ََ الرج م إمََّل ما ي حت لَى علَي ُكم يَ م م )03( الزومر ُّ اجتَنمبُوا قَ حو َل س م َن حاْل حَوثَان َو ح َ ُ َح ح ح َ اجتَنبُوا ِّ ح ‹‹እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችን ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት ሰዎች እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ ማንኛውንም ነገር የሚያስብ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን ፡፡ መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ ፡፡ ቤቴንም ለሚዘይሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ ፡፡ ኢብራሂም ሆይ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ ፡፡ እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ በከሳዋ ግመሎች ላይ እንኳን ሆነውም ይመጡልሃልና ፡፡ ለእነሱ የሆነ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእኒያ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች .
19
በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል ፡፡ ከእርሷም ብሉ ፡፡ ችግረኛንም አብሉ ፡፡ ከዚያም እንደ ፀጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ ፡፡ ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ ፡፡ በጥንታዊውም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ አልን ፡፡ የሐጅ ሥርአት ይህ ነው ፡፡ የአላህን ህግጋት የሚያከብር ሰው ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው ፡፡ የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች ፡፡ ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ ፡፡ ለአላህ በእርሱ የማታጋሩ ሆናችሁ ወደ ቀጥተኞች መንገድ የተዘነበላችሁ (ታዛዦች) ሁኑ ፡፡ በአላህ የሚያጋራ ሰው ሁሉ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ንፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ነው ፡፡ ነገሩ ይህ ነው ፡፡ የአላህን ሃይማኖታዊ ምልክቶች የሚያከብር ሰው ሁሉ ድርጊቱ አላህን ከሚፈሩ ልቦች የሚፈፀም ጥንቃቄ ነው ፡፡ ለእናንተ በእርሷ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ ፡፡ ከዚያም የማረጃ (የኡሁዱህያ) ስፍራ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው ፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ ለህዝቦች ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ሀይማኖታዊ ሥርአቶችን ደነገግን ፡፡ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ፡፡ እርሱንም ብቻ ታዘዙ ፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም በመልካም ነገር አብስራቸው ፡፡ እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን (የሚፈሩትን) በደረሰባቸውም መከራ ላይ ታጋሾችን ፤ ሰላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን በጀነት አብስር ፡፡ ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው ፤ በነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ ፤ በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮችዋ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ ፡፡ ጎኖቻቸውም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ ፡፡ በግልፅ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ ፡፡ ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት ፡፡ አላህን ስጋዎቿም ሆኑ ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም ፡፡ ለእናንተ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ብቻ ይደርሰዋል ፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት በጎ ሰሪዎችንም አብስር ፡፡ አላህ ከእነዚያ በሱ ካመኑት ሰዎች ላይ የከሓዲያንን ተንኮል ይከላከልላቸዋል፡፡ አላህ ከዳተኛንና ውለታ ቢስን ሁሉ አይወድም› አል ሐጅ 25-30 እነዚህ አንቀፆች የሐጅንና የመካን ታላቅነት ነው በግልፅ የሚያስተምሩት፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ሐዲስንም በተመለከተ ያ ! ታላቁና እውቁ የጂብሪል ሐዲስ ብቻ በቂ ይመስለኛል ፡፡ ሆኖም ብዛት ካላቸው ሐጅን ከሚመለከቱ ሐዲሶች መካከል ከዚህ በታች ያሉትን በጥሞና እንመልከት ፡፡ 1ኛ ሐዲስ አቡ ሁረየራ ከነቢዩ ﷺየዘገቡት م م ) ُاْلَنَّة س لَهُ َجَزا ٌ إمََّل ح َّارةٌ لم َما بَحي نَ ُه َما َو ح ُ اْلَ ُّج الح َمحب ُر َ (الح ُع حمَرةُ إ ََل الح ُع حمَرة َكف َ ور لَحي (ከዑምራ እስከ ዑምራ ድረስ የለውን ወነወጀል ያስምራል ፡፡ የትክክለኛ /ተቀባይነት ያለው/ ሐጅ ምንዳው ጀነት ብቻ ነው) 12 2ኛ ሐዲስ ኢብኑ መስዑድ ከነቢዩ ﷺየዘገቡት (تابعوا بين الحج والعمرة فإنهما ينفيان الفقر والذنوب كما ينفى الكير خبث الحديد 13 )والذهب والفضة وليس للحجة المبرورة ثواب إَل الجنة (በሐጅና በዑምራ መካከል አከታትሉ ፡፡ የእሳት ወናፍ የብረትን ፤ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግድ ሁሉ ድህነትን ወንጀልን ያሰወግዳሉ ፡፡ ለትክክለኛ ሐጅ ምንዳ መሆን የሚችለው ጀነት ብቻ ነው) 14 3ኛሐዲስ እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ አንሃ) ከነቢዩ ﷺየዘገቡት عن عائشة أم المؤمنين أنها قالت لرسول هللا صلى هللا عليه وسلم ( أرى الجهاد )15 أفضل العمل أفال نجاهد قال لكن أفضل الجهاد حج مبرور
12
ቡኻሪና ሙስሊም. አህመድ ፤ ቲርሚዚ ፤ ነሳኢ እና አቡ ኑዐይም. 14 ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ. 15 አቡ የዕላ. 13
.
21
(የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ጂሃድ የስረዎች ሁሉ አውራ ሁኖ ተመልከተነዋል ፡፡ ታዲያ እኛ አንዋጋምን ? በማለት ሲጠይቋቸው በፍፁም የእናንተ ትልቁ ጂሃድ ትክክለኛ ሐጅ ማድረግ ነው) 16 በሌላ ዘገባው በእነሱላይ ጦርነት የሌለበት ጂሃድ አለባቸው እሱም ሐጅና ዑምራ ነው) ብለዋል፡፡ 4ኛ ሐዲስ አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ አንሁ) ከነቢዩ ﷺየዘገቡት 17
) هللا ثم َح ٌّج َمبْرُ و ٌر ِ يل ه ِ (أفضل األعمال إِي َمانٌ ِب ه ِ اَّلل َو َرسُولِ ِه ثم ِج َها ٌد فِى َس ِب
(የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ከስራው ሁሉ የበለጠው ምድን ነው ተብለው ሲጠየቁ በአላህ በመልዕክተኛው ማመን ነው ከዚያስ ተብለው ሲጠየቁ ጂሃድ ነው አሉ ፡ ፡ ከዚያስ ተብለው ሲጠየቀቁ ትክክለኛ ሐጅ ማድረግ ነው) 18 ብለዋል፡፡ 5ኛ ሐዲስ አቡ ሁረይራ(ረዲየላሁ አንሁ) ከነቢዩ ﷺየዘገቡት ) (من حج َّلل فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه (ለአላህ ብሎ ሐጅ ያደረገ ሰው ከዚያም የግብረ ስጋ ግንኙነትን ጉዳይ ያላወሳ ሌሎችንም ታላላቅ ወንጀሎችን ያልፈፀመ እናቱ እንደወለደችው ሁኖ ይመለሳል) 19 ብለዋል፡፡ 6ኛ ሐዲስ 16
ቡኻሪ. ቡኻሪ ፤ ሙስሊምና አህመድ. 18 ቡኻሪና ሙስሊም. 19 ቡኻሪና ሙስሊም. 17
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
)(أما علمت أن اِلسَلم يهدم ما كان قبله وأن اَلجرة هتدم ما كان قبلها وأن اْلج يهدم ما كان قبله 20
(ነቢዩ ﷺለዐምር ብን ዓሲ ኢስላም ከእሱ በፊት የነበረዉን እንደሚሰርዝ ፤ ስደት ከሱ በፊት የነበረዉን እንደሚሰርዝ ፤ ሐጅም ከሱ በፊት የነበረዉን እንደሚሰርዝ አላወክምን ) ያሉት ነው ፡፡ 21 ስለሆነም ትክክለኛ ሐጅ ማለት በአጭሩ የነቢዩን ﷺየአፈፃፀም ፈለግ ተከትሎ የተደረገ ሐጅ ማለት ነው ፡፡ የቦታዎች መበላለጥና ከሱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ዉድ አንባቢያን አላህ በጥበቡ በህዝቦች ፤ በወቅቶችና በቦታዎች መካከል በልዩ ልዩ ብልጫዎች አበላልጧል ፡፡ በዚሁም ልዩነት ላይ የተመሰረተ ልዩ ልዩ ህግጋትን አስቀምጧል ፡፡ ከዚህ ልዩ እድል ከፍተኛዉን ከታደሉት መካከል፡1ኛ ከሰዎች መካከል ምርጥ ነቢያት ሲሆኑ ከእነሱም ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ የምርጥ ምርጥ በመሆን ዋናው ናቸው፡፡ 2ኛ ከህዝቦች መካከል ሙስሊሞች በተለይም እኛ የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ተከታዮች ነን ፡፡ 3ኛ ከቦታዎች መካከል ደግሞ መካ ፤ መዲና በይተል መቅዲስ ና መስጂዶች ዋና ዋና ተብለው የሚጠቀሱት ናቸው ፡፡ በመካ ሀገር ያ ! ለመጀመሪያ ጊዜ ለዒባዳ የተሰራው ታላቅ የፀሎት ቤት ካዕባ ፤ ያ ! የመጀመሪያው የተውሂድ መዐከል ፤ የሙስሊሞች ሁሉ በህይወታቸዉም ሆነ ሞተው ቂብላቸው የሆነው ቤት ፤ ያ ! የወህይ ምንጭ ፤ የነቢይነት መነሻ ፤ የኢስላም መፍለቂያ ማዕከል የሆነው ታላቅ ቤት ካዕባ አለ ፡፡ በመሆኑም ሙስሊሞች ዘንድ የተቀደሰው ቦታ ማለት ዋናው መካ ነው ፡፡ ለአላህ ምስጋና ይገባዉና ከሙስሊሞች ዉስጥ ከሞላ ጎደል የዚህን ቤት ክብር የማያውቅ አንድም የለም ማለት ይቻል ይሆናል ፡፡ የሀገራችን ሙስሊሞች ትንሹም ትልቁም ስለ መካ ሲዘከር እንባው በአይኑ የሚንቆራዘዝ ብዙ ነው ፡፡
20 21
ሙስሊም. ሙስሊም. .
23
ታላላቅ ዐሊሞች ስለ መካ የገጠሙት ቁጥር ስፍር የለዉም ፡፡ ገና አፋችንን ስንፈታ የምንማረው የሀገር ስም የመካን ነው ፡፡ እኔ ራሴ የሀገሬን ዋና ከተማ ሳላውቅ በፊት መካን የእምነት መሰረቶችን ስማር አምስተኛው መካን መጎብኜት ነው እያልኩ ነው የተማርኩት ፡፡ በመሆኑም የሀገራችን ሙስሊሞችም ቢሆኑ ለመካ ያላቸው ክብርና ዉዴታ ወደር የለዉም ፡፡ ምክኒያቱም ኢስላም ከሀገራችን ጋር ያለው ግንኙነት ከዐለም ህዝቦች ሁሉ በፊት ከመካ በመቀጠል በሁለተኛ ቁጥር ላይ የገባ በመሆኑ ነው ፡፡ ስለዚህ የዚህ ታላቅ ቤት ጉዳይ በእኛ በሐበሻ ሙስሊሞች ዘንድም ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም ፡፡ መካ በደል ፤ እንግልት ፤ መከራና ስቃይ ፤ የትናንቱ የጃሂሊያ ሥርዓት እርም ተደርጎበት በአንፃሩ ክብር ፤ ፍቅርና ሰላም ፤ ጌጥና ብርሃን በመሆን ለዓለም ተምሳሌት ሆኖ የአላህ ትዕዛዝና የረሱል ﷺመልዕክት ደማቅ ታሪክና ገድል እየተዘከረበት በፅናት የሚቆይበት ቦታ ነው ፡፡ የአላህን ትዕዛዝና የረሱልን ሱና መተግበር ከእስላማዊ ጥቅም እስከ መጨረሻው የሰው ልጅ ናፍቆት የሆነው ‹ጀነትን›› የመውረስ እድልን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ፡፡ በተውሂድና በሱና መታነፅ ከአዱንያ የባርነት ቀንበር ሙሉ በሙሉ ነፃ ያደርጋል ፡፡ ታላቁ ቁርኣንና የነቢዩ ሐዲስም ይህን ጉዳይ በሰፊው ዘርዝረዋል ፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ይህን ሀገር የመጎብኘቱን እድል ለማግኘት ከፍተኛ ልፋትና ጥረት አድርገው ስለ ነበር የሚያገኙት በጣም ይጠቀሙበት ነበር ፡፡ የአላህ ፍቃድ ከሆነ በዚህ መፅሐፍ ዉስጥ ለዚህ አባባል ዋቢ የሚሆኑ ብዙ ዘገባዎችን ታነባላችሁ ፡ ፡ አሁን አሁን ግን አንዳንድ የዚህን መስጂድና ሀገር ክብር ጠንቅቀው የማያውቁ ትውልዶች መጥተዋል ፡፡ ከመካ ክብር ይልቅ የግላቸዉን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ክፍሎችም አሉ ፡፡ ምድባችን ከእነዚህ መሰሎች እንዳይሆን አደራ እላለሁ ፡፡ የመካን ክብር እና የዚያራዉን ሥነ ሥርዐት በደንብ ሳይረዱ ለሐጅም ሆነ ለዑምራ ፀሎት የሚመጡ ሰዎች ይህን መፅሐፍም ሆነ መሰሉን አስቀድመው ማንበብ ወይም ካሴቱን/ሲዲዉን ማዳመጥ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ብየ አምናለሁ ፤ የማይናቅ እውቀትም ይገበያል ፤ የዉስጥ እርካታም ያገኛል ፡፡ ለሐጅ የሚወጡ ወጪዎች ልክ ለጂሃድ እንደሚወጡ መሆናቸዉን ነቢዩ አህምድ፤ጦበራኒ በይሐቂ በዘገቡት ሐዲስ (ለሐጅ የሚ ከፈሉ ሀብቶች ሁሉ ልክ ለጂሃድ እንሚከፈሉ ሀብቶች አንድ ብር በሰባት መቶ ነው ክፍያው ብለዋል)፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ኢብኑ ዐባስም ለሐጅ የሚወጡ ወጮች ለሐጅ እንደወጡ ነው ምክኒያቱም ሁሉም ፊ ሰቢሊላህ ነዎና ) ብለዋል፡፡ 2-4.የሐጅ ፆሎት ፋይዳዎችና ዋና ዋና አላማዎቹ فوائد الحج ዉዶች በመጀመሪያ ኸይር ስራ ሁሉ ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ካላሟላ በስተቀር በአላህ ዘንድ በጭራሽ ተቀባይነት የለዉም ፡፡ እነሱም ፡1ኛ-የሚያድረገዉን ነገር ሁሉ ለአላህ በኢኽላስ ብሎ መፈፀምና 2ኛ-በተግባሩ ላይም ነቢዩ ሙሐመድን ﷺበመከተል እሳቸው ባስተማሩት መሰረት መፈፀም የሚሉት ናቸው ፡፡ እናም ሁልህም ሐጅህን ስታስብ ከይዩልኝ ና ከይስሙልኝ ነፃ የሆነ ትክክለኛ ኒያ ሊኖርህ ግድ ይላል ፡፡ አላህ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጸሙ ዒባዳዎችን የኢማን ስንቅ እንዲሆኑ ደንግጓል ፡፡ ለምሳሌ የአምስትን ወቅት ሰላቶችን አጅር ስንመለከት ፡- የዙሁር ሰላት እስከ አስር ሶላት ወቅት ላለው ክፍት ጊዜ የኢማን ስንቅ በመሆን ፤ የዐስር ሰላት እስከ መግሪብ ሶላት ወቅት ላለው ክፍት ጊዜ የኢማን ስንቅ በመሆን ፤ የመግሪብ ሶላት እስከ ዒሻ ሶላት ወቅት ላለው ክፍት ጊዜ የኢማን ስንቅ በመሆን ፤ የዒሻ ሶላት እስከ ሱብሒ ሶላት ወቅት ላለው ክፍት ጊዜ የኢማን ስንቅ በመሆን ፤ የሱብሒ ሰላት እስከ ዙህር ሶላት ወቅት ላለው ክፍት ጊዜ የኢማን ስንቅ በመሆን ያገለግላል ፡፡ የጁምአ ሰላትም እንዲሁ እስከ ቀጣዩ ጁምዓ ድረስ ጠንከር ያለ የኢማን ስንቅና በረከት ይሆናል ፡፡ ረመዷንን ወር ፆም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዓመቱን በሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል የሚለውን ፋይዳ እናገኛለን፡፡ ይህም የዓመት የኢማን ስንቅ ነው ማለት ነው ፡፡ የሐጅ መንፈሳዊ ፤ ማህበራዊመ ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች ብዙ ናቸው ፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች የቀረቡት ናቸው ፡፡ 1-ትክክለኛን ሐጅ ማድረግ ከዚያ በፊት የተሠራን ወንጀልን ሙሉ በሙሉ አስምሮ ሐጅ ያደረገውን ሙዕሚን ልክ ዛሬ እንደተወለደ ህፃን ከወንጀል ነፃ ያደርገዋል ፡፡ 2- ሰዎች በአላህ ዘንድ እኩል መሆናቸውን ያስተምራል ፤ ምክንያቱም በሐጅ ወቅት ሙስሊም ነጭ ሽርጥና ነጭ ኩታ መሰል ይለብሳል ፡፡ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የመጡ ሙስሊሞች ሁሉ በአንድ ቦታ ላይ ይሰበሰባሉ ፡፡ በገዥና ተገዥ ፤ በሀብታምና በድሃ ፤ በነጭና በጥቁር መካከል የሚታይ ምንም አይነት ልዩነት .
25
የለም ፡፡ ሁሉም የአላህ ፍጡራንና ባሪያዎች ናቸው ፡፡ አንዱ ከሌላው የሚበልጠው አላህን በመፍራትና በበጎ ስራው ብቻ ነው ፡፡ 3- የሁሉም ነብያት እምነት አንድ መሆኑን በግልፅ ያስገነዝባል ፤ 4-የሰዎች ወንድማማችነትን በግሃድ እንድናስታውስ ያደርጋል ፡፡ አንዱ ከሌላው የሚበልጠው አላህን በመፍራትና በበጎ ስራው ብቻ ነው ፡፡ 5- ሙስሊሞች በሐጅ አማካኝነት ይታዋወቃሉ ፡፡ ይተጋገዛሉ፡፡ 6- ከሞት ተቀስቅሰው ለምርመራ በአንድ ምደር ላይ የሚቆሙበትን ጊዜም ያስታውሳሉ ፡፡ እናም ከሞት በኃላ ላለው ሕይወታቸው ስኬት በዚች ዓለም አላህን ለመታዘዝ የበለጠ ዝግጁዎች ይሆናሉ ፡፡ እናም የሐጅ ጉዞን ለቻለ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ እንዲፈፅመው ግዴታ የተደረገ የኢባዳ ክፍል እንደመሆኑ ለአንድ ሙእሚን እስከ ህይወት ፍፃሜው ድረስ የኢማን ብርታት የሚሰጠው የኢማን ስንቅ ነው ማለት ነው ፡፡ ስለዚህ የሐጅን ፀሎት ስንተገብር በትክክል ከአላህ የታዘዘ መሆኑን ከዉስጣችን አምነን መተግበር ይኖርብናል ፡፡ ለምሳሌ ፡- በከዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ጦዋፉ / ዙሪያ ማድረግ ፤ ሐጀረል አስወድን / ድንጋዩን መሳሙ ፤ በእሱ ላይ ሱጁድ ማድረጉ ፤ በሶፋና በመርዋ መካከል ሰባት ጊዜ ጎዞ ማድረጉ ፤ የራስ ፀጉርን መላጨቱ/ማሳጠሩ ፤ በሶስቱም የጠጠር መወርሪያ ቦታዎች ላይ በተለየ ስርዐት መወርወሩ ፤ እንሳሰዎችን ማረዱ ፤... ከአላህ የታዘዙ ናቸው ብለህ ከዉስጥህ አምነህበት ካልተገበርከው በስተቀር ምንም ፋይዳ የለዉም ፡፡ ክፍል ሶስት ፡-የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም انواع الحج
3-1.የሃጅ አይነቶች
የሐጅ አይነቶች ሶስት ናቸው ፡፡ እናም ሐጅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ከሶስት የሐጅ ፀሎት አሰራር ሥርዓቶች መካከል አንዱን መምረጥ መብቱ ነው ፡፡ እነሱም ፡ሀ-ኢፍራድ ፡-ኢፍራድ ማለት ደግሞ በቀጥታ ሐጅ ለማድረግ ኢህራም ማድረግ ነው ፡፡
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ለ-ተመቱዕ ፡- ተመቱዕ ማለት የዑምራን ፀሎት ለመፈፀም በማሰብ በሐጅ ወራቶች ኢህራም ማድረግና ከሱ ተፈቶ ከሰነበተ በኋላ በዚያው አመት ሐጅን ለመፈፀም ኢህራም ማድረግ ነው ፡፡ ሐ ቂራን ፡- ቂራን ማለት ደግሞ ሁለቱንም ለማድረግ ወይም ዑምራን አስቦ ከገባ በኋላ ጠዋፍ ከማድረጉ በፊት ሐጁን በዚያው ውስጥ ማስገባቱ ነው ፡፡ ሆኖም ከሁሉም የሚመረጠው በተመቱዕ ሐጅ ማድረጉ ነው ፡፡ 22 የነቢዩ ሙሐመድ ሐጅ የትኛው አይነት ነበር በሚለው ጉዳይ ላይ የዐሊሞች ልዩነት አለ ፡፡ አንዳንድ ዐሊሞች ኢፍራድ ነበር ሲሉ ሌላው ተመቱዕ ነበር ብሏል ፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ቂራን ነበር የሚለው ነው ፡፡ እንደኔ ተቀባይነት ያለው አባባል ተመቱዕ ነበር የሚለው ነው ፡፡ شروط الحج
3-2.የሐጅ ቅድመ ሁኔታዎች
3.3 የሐጅን/የዑምራን/ ፀሎት ማድረግ የሚወጅብባቸው ሰዎች የሐጅን ፆሎት የጉዞ ጣጣውን በሚችል ፣ ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ ሐጅም ሆነ ዑምራ መፈፀም ግዴታ የሚሆነው በዕድሜው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡ ከዚያ የተጨመረው ትርፍ ነው ፡፡ በስለት ምክኒያት ግን ግዴታ ይሆናል ፡፡ ግዴታ የሚሆነውም ከዚህ በታች ያሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ካሟሉ ብቻ ነው ፡፡ 1) ሙስሊም መሆን ሲሆን ፤ ከሃዲ የሆነ ሰው ሐጅ ቢያደርግ ተቀባይነት የለውም ፡፡ እናም አንድ ሰው ሶላት ሳይሰግድ ሐጅ ቢያደርግ ሐጁ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው ፡፡ ምክንያቱም ሶላት በመተው ከኢስላም ስለሚወጣ ሐጁም ሆነ ሌላው ተግባሩ ተቀባይነት የለውም ፡፡ ስለዚህ ሶላት መስገድ ሲጀምር እንደገና ሐጅ ማድረግ አለበት የሚሉ ብዛት ያላቸው ዐሊሞች ሲኖሩ ፤ ሶላት በመተው ከእምነቱ አይወጣም እና ወንጀለኛ ቢሆንም ሐጁ ፈርዱን ያሰቅጥለታል ብለው የሚከራከሩም ዓሊሞች አይጠፉም ፡፡ 23 2) የአዕምሮውም ሆነ የሌላው አካል ጤናማ መሆን፤ 22
ይህ አባባል የብዙሃን ዐሊሞች አቋም ቢሆንም ከዚህ የተለየ አቋምም ያለው ዐሊምም አለ ፡፡ 23 -የዚህ ክርክር መነሻው ሶላት የማይሰግድ ሰውን በተመለከተ ካለዉ ከፍተኛ ልዩነት ጋር የተያያዘ ነው ፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሶስተኛ መፅሐፍ ላይ ሰፊ ነገር አለ ፡፡ .
27
3) ለአቅመ አዳም /ለአቅመ ሂዋን መድረስ/፤ 4) ከባርነት ነፃ መሆን ፤ 5) የገንዘብም ሆነ የጉልበት አቅም ያለው፤ ማንኛውም ሙስሊም ፤ ወደ ተቀደሰው ሀገር መካ መሄድ የሚችልበት መጓጓዣ/ መሄጃና መምጫ / የሚሆነው ገንዘብ ፤ ቀለብ ለቤተሰቦቹም ደርሶ እስኪመለስ ድረስ ቀለብ ካለው ፤ 6) መንገዱም ሰላም ከሆነና ቤተሰቦቹንም ጥሎ በመሄዱ በነርሱ ላይ ምንም አደጋ የማያስከትልበት ከሆነ ሐጅ ማድረግ ግዴታ ይሆንበታል፡፡ 7) ለሴቶች ብቻ ከላይ ከተጠቀሱት ስድስት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ ዘመድ/መህረም/ አብሮ መኖር አለበት ፡፡ የዚህን አብሮ ተጓዥ ወጭ መሸፈን ያለባት እሷው ናት ፡፡ የዚህም መሰረት የሆነው ከሴቶች ሰላም ጋር የተያያዘ መሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም ፡፡ የመህረሙን ወጭ መቻል ያለባት እሷው ናት የሚሉ ሲሆኑ ኢማሙ አጡሃዊ ግዴታ የለባትም ፡፡ المحرم للنساء
3-4. ስለ ሴቶች ሙህረም ባጭሩ
ሙህሪም ማለት ፡-ሴት ልጅ በሐጅ ለመገደድ ስድስተኛ ቅድመ ሁኔታ ትጨምራለች ማለት ነው ፡፡ እሱም አብሮ የሚሄድ ወንድ ዘመድ መኖር ነው ፡ ፡ የሴት ልጅ የወንድ ዘመድ በሁለት ይከፈላል፡፡ 1ኛው ዘመድ ከሷ ጋር በስጋ የሚገናኙ ሰዎች ሲሆኑ እነሱም ፡1-አባትና አያቶች ፤ 2-ልጅና የልጅልጆች ፤ 3-ወንድም፤ የወንድም ልጆችና የልጅልጆቻቸው ፤ 4-የእህትልጅ እና የልጅልጆቻቸው ፤ 5-በሁለቱም በኩል ያሉት አጎቶች ማለት ነው ፡፡ እነዚህ ለሁልጊዜም እሷን ማግባት ክልክል የሚሆኑባት ወንዶች ዘመዶች ናቸው ፡፡ 2ኛው ከሷ ጋር በጡት መጥባት ምክኒያት የሚገናኙ ሲሆኑ እነሱም ፡1 -የጡት አባትና አያት ፤ 2-የጡትልጅና የልጅልጅ ፤ 3-የጡት ወንድም ፤ 4-የጡት ወንድም ልጅ ፤ የጡት እህትልጅ እና የልጅልጆቻቸው ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
6-በሁለቱም በኩል ያሉት የጡት አጎቶች ማለት ነው ፡፡ 3ኛው ከሷ ጋር በጋብቻ ምክኒያት የሚገናኙ ሲሆኑ እነሱም ፡1-ባል ፤ 2-የባል ልጆች ፤ 3-የባል አባትና አያቶች ፤ 4-የእናት ባል ፤ 5-የልጆች ባል ናቸው፡፡ እነዚህ መህረሞችም ሶስት መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለባቸው ፡፡ ሆኖም ሴት ያለ ዘመድ ሐጅ ብታደርግ ግን ወንጀለኛ ብትሆንም ሐጇ ትክክል ይሆናል ፡፡ መህረም ብቻ የጎደላት ሴት ከአስተማማኝ24 ቡድን ጋር ሐጅ እንደታደርግ የፈቀዱ ዐሊሞችም አሉ ፡፡ ኢማሙ ማሊክና ኢማሙ አሻፊዒ በዚህ ጉዳይ ከሚጠቀሱት እውቅ ዐሊሞች ናቸው ፡፡ ኢብኑ ተይሚያህ ደግሞ መንገዱ ሰላም መሆኑ ከተረጋገጠ ሴት ልጅ ያለምንም መህረምም ብቻዋን እንኳን ቢሆን ሐጅ ይወጅባባታል ይላሉ ፡፡ እናም በተለይም በሳዑዲ የሚኖሩ ሴት እህቶቻችን መህረም የለንም በማለት ግዴታ ሐጃቸዉን ሳይተገብሩ ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ አበክሬ እየመከርኩ ይህንን ለሚቃወሙ አስተማሪወችም አላህን እንደፈሩ ማስተወሴን አልተዉም ፡፡ ብዙ የሀገራችን ሰዎች በሀሰት ሴቶችን እህቴ ፤ ሚስቴ …እያሉ ሚስት ወይም እህት ያልሆነችውን ሴት ይዘው ይጓዙና ሐጅ ያደርጋሉ ፡፡ የነዚህ አይነት ሰዎች ሐጅ ጭራሽ ተቀባይነት የለዉም ባይባልም በሀሰት ምስክር በወሰዷቸው ሴቶች ጥፋት ግን ይጠየቃሉ ፡፡ 25 ህፃንና ባሪያ ለጊዜው ሐጅ ባይወጅብባቸዉም ሐጅ ቢያደርጉ ግን ሐጁ ትክክል ነው ፡፡ ሆኖም ግዴታቸውን አይሸፍንላቸውም ፡፡ እናም ባሪያው ከነፃነት በኋላ ፤ ህፃኑም ለአቅም አዳም ከደረሰ በኋላ እንደገና ሐጅ ማድረግ አለባቸው ፡፡ እብድ 24
አስተማማኝ ጓደኞች ማለት እነማንን እንደሆኑ አንዳንድ ዐሊሞች ምሳሌ ሲጠቅሱ በዛ ያሉ ሴቶች ፤ ታማኝ ወንዶች ፤ መህረም የያዙ ሴቶችን ይመስላሉ ፡፡ እናም ከዚህ በመነሳት አንዲት መህረም የሌላት ሴት ከእነዚህ መሰሎች ጋር ሐጅ ማድጓ ችግር የለዉም ማለት ነው ፡፡ 25 -እዚህ ላይ ችላ ተብሎ ሊታለፍ የማይገባው ነገር አለ ፡፡ እሱም የየሀገሪትን ህገ-ደንብ ሳያሟሉ ወደ ሐጅ የመሄድ ጉዳይ ነው ፡፡ ምክኒያቱም ለምሳሌ ወደ መካ ለመግባት ፍቃድ የሌላቸው ሰዎች ሐጅም ሆነ ዑምራ የማይወጀብባቸው መሆኑን ማወቅ ግድ ነው ፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ እሄዳለሁ ብሎ ራስን በችግር ላይ መጣሉ ስህተት ነው ፡ ፡ ይንህም የፊቅህ ምሁራን በአስተምህሮታቸው ላይ መንገዱ ሰላም መሆን አለበት የሚሉት ነው፡፡ .
29
ሐጅ ቢያደርግ ሐጁ በፍፁም ተቀባይነት የለውም ፡፡ አቅም የሌለው ድሃ ሰው ተበድሮ/ ወይም በሰዎች እርዳታ ሐጅ ቢያደርግ ተግባሩ ተገቢ ባይሆንም ሐጁ ግን ምንም ችግር የለበትም ፡፡ 3-5. ከሌላ ሰው ተወክሎ ሐጅ ማድረግን በተመለከተ الحج عن الغير የግዴታ ሐጅን ወይም ዑምራን በተለያዩ ምክንያቶች እሱ የማይችል መሆኑ በትክክል ካልተረጋገጠ በስተቀር በእሱ ፈንታ ሌላን መተካት አይቻልም ፡፡ ይህ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን በዐሊሞች መካከል ያለምንም ልዩነት ይቻላል ፡፡ ይኸውም የመዳን ተስፋ የሌለው በሽታ እና ሽምግልናን ይመስል ነው ፡፡ መተካቱ ለትርፍ ሐጅ ከሆነ ደግሞ በዐሊሞች መካከል ብዙ ክርክር ያስነሳል ፡፡ ቢሆንም መከልከሉን ብዙ ዓሊሞች ይመርጣሉ፡፡ ለሞቱ ሰዎች ሐጅን ወይም ዑምራን ማድረግ ፤ ሌላም ኸይር ሥራ ሰርቶ ምንዳውን ለሟች እንዲደርስ ከአላህ መለመን ግን ይቻላል፡፡ የራሱን የግዴታ ሐጅ ሳይወጣ ለሌላ ሰው ተወክሎ ሐጅ ያደረገ ሰው ሐጁ ለራሱ ነው የሚሆነው፡፡ በቂ ገንዘብ እያለው ችላ ብሎ ሐጅንና ዑምራን ሳያደርግ የሞተ ሰው ከተወው ገንዘብ ሐጅና ዑምራ የሚያስደርግ ገንዘብ ያክል ከውርስ በፊት ይቀነሳል ፡፡ ይህ አባባል የአብዛኞቹ ዐሊሞች አባባል ነው ፡፡ ኢብኑ ልቀይም የተባሉ ዐሊም ግን የተገደዱበትን ጉዳይ መፈፀም እየቻሉ ችላ ብለው ያስመለጡ ሰዎች ሁሉ ሌላ ሰው ቢሰራላቸውም ከተጠያቂነት ነፃ ስለማይሆኑ ፋይዳ የለዉም ይላሉ ፡፡ أركان الحج
3- 6.የሐጅ ማዕዘናት የሐጅ ማዕዘናት አራት ናቸው ፡፡ እነሱም ፡1) ኢህራም ማድረግ፤ 2) በዐረፋ ላይ መገኘት፤ 3) የዚያራ /ኢፋዷ/ የሚባለውን ጦዋፍ መጦወፍና 4) የሐጁ ሰዕይ ናቸው፡፡
واجبات الحج
3-7.የሐጅ ዋጂባቶች የሐጅ ዋጂባቶች ደግሞ ስምንት ናቸው ፡፡እነሱም:الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
1) ከኢህራም ማድረጊያ ቦታው ላይ ኢህራም ማድረግ፤ 2) እስከ ማታ ድረስ በዐረፋ ክልል ዉስጥ መቆየት፤ 3) ግማሽ ሌሊት እስከሚያልፍ ድረስ በሙዝደሊፋ ክልል ውስጥ ማደር፤ 4) የተሸሪቅ ቀናት ማለትም የዙልሒጃ ወር 11ኛ፤12ኛ እና 13ኛ ቀኖች ሌሊቶችን በሚና ክልል ውስጥ ማደር ፤ ችግር ያለባቸው እንደበሺተኛ ፖሊስ ቦታ ያጣ እና መሰሎቹ ግን ከሚና ዉጭ ማደር ይችላሉ ፡፡ 5) በእነዚህ ቀናት ዉስጥ ጠጠሮችን መወርወር፤ 6) ፀጉርን መላጨት ወይንም ማሳጠርና፤ 7) የወር አበባ ካለባት ሴት በስተቀር የመሰናበቻው ጦዋፍ፤ 8) በተመቱዕ/ በቂራን ሐጅን ለሰራ ሰው ስጦታን ማረድ ናቸው፡፡
3-8.የሐጅ ሱናዎች
سنن الحج
የጉዞ ስርዓቶችን መጠበቅ፤ ነጫጭና ንፁህ የሆኑ የኢህራም ልብሶችን መልበስ፤ በኢህራም ግዜ ገላን መታጠብ መፀዳዳትና ሽቶ መቀባት፤ ሐጀረል አስወድን በሙሉ ሰውነቱ መቅጣጨት፤ ጠዋፍ ሲጀምር ቢስሚላ አላሁ አክበር ብሎ መጀመርና አላሁመ ኢማነን ቢከ… የሚለውን ዱዓ ማንበብ በሌሎቹ ዙሮች ግን አላሁ አክበር ብቻ እያሉ መጠወፍ፤ በየ ዙሩ ሀጀረል አስወድን ከቻለ ራሱ ላይ እየተደፉ መሳም ካልቻለ በእጁ መንካትና እጁን መሳም ከልሆነም በዝንግ ነገር ነክቶ ዘንጉን መሳም ይህም ካልተቻለ ግን በእጅ በማመልከት እንጂ እጅን መሳም ክልክል ነው ፡፡ እንቅፋት ሊኖር ይችላል ብሎ ከሰጋ የምፈታው እንቅፋቱ ባጋጠመኝ ቦታ ነው ብሎ ማሰብ፤ወዲያው እንደሃረመ ተልቢያ ማብዛት፤ ወንዶች በተልቢያ ግዜ ድምፃቸውን ከፍ ማድረግ ሲሆን ሴቶች ድምፃቸውን ዝቅ ማደረግ፤ተልቢያውን በተለይም ኮረብታ ላይ ሲወጡ፤ ወደ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ሲወርዱ፤ ሌላ ሰው ተልቢያ ሲል ሲሰማ ፤ ከሰላቶች በኋላ ፤ በስሁር ሰዓት፤ ጠዋትና ማታ ማብዛት፤ ጠዋፍ እስከሚጀምር ድረስ ተልቢያን አለማቋረጥ፤ .
31
መንገዱ በዚጡዋ በተባለው ቦታ ከሆነ በዚያው ማደርና ሰውነቱን መታጠብ ካልሆነ ግን የትም ቦታ አድሮ ሰውነቱን ታጥቦ በቀን መግባት፤ ወደ መካ ሲገቡ በከዳእ በኩልመግባተ፤ ከመካ ሲወጣ ደግሞ በኩደይ በኩል መውጣት፤ ወደ መስጂደል ሐረም ሲገባ ከተቻለ በበኒ ሸይባ በር በኩል መግባት፤ ወደ መስጂዱ ሲገባም ቀኝ እግርን ማስቀደም ፤ ወደ ማንኛውም መስጂድ ሲገባ የሚባለውን ዱዓ ማድረግ ፤ ሲወጣም ግራ እግሩን ማስቀደም ፤ ከማንኛውም መስጂድ ሲወጣ የሚባለውን ዱዓ ማድረግ ፤ ጠዋፍ ጀምሮ እስከሚጨርስ ድረስ ቀኝ እጁን ማውጣት ፤ ከመካ ውጪ የመጣ ሁሉ በዑምራ እና በጠዋፈል ቁዱም የመጀመሪያውን ሶስት ዙሮች በሶምሶማ ከዞረ በኋላ ቀሪ አራት ዙሮችን በተለመደ ጉዞ ማድረግ ፤ በሩክነል የማኒ አጠገብ ባለፈ ቁጥር ከቻለ በእጁ መንካት ፤ ካልቻለ ግን ማመልከትም ፤ መሳመም ሆነ አላሁ አክበር ማለት ተገቢ አይደለም በሩክነል የማኒ እና በሀጀረል አስወድ መካከል ረበና አቲና ፊዱንያ ሀሰነተን ወፊል ኣኺረቲ ሃሰነተን ወቂና አዛበናር ማለት በጠዋፍም ሆነ በሰዕይ ወቅት ቁርኣን መቅራት ዚክር መዝከር ዱዓ ማድረግ ፤ ወሬ እና አላስፈላጊ ምልከታዎችን መተው፤ ከነጃሳ ፀድቶ በዉዱእ ጠዋፍም ሆነ ሰዕዬ ማድረግ ፤ ጠዋፉንም ሆነ ሰዕይን በእግር ጉዞ ማድረግ፤ ከጠዋፍ በኋላ ከኢብራሂም መቆሚያ ጀርባ አካባቢ ሁለት ረከዓን መስገድ፤ ይህን ሰላት ጠዋፍ እንደጨረሱ ወዲያውኑ ማደረግ፤ ይህን ሰላት ሊሰግድ ሲል ወተኺዙ ሚን መቃሚ ኢብራሂመ ሙሰላ የሚለውን የቁርዓን አንቀፅ ማነበብ ፤ እነዚሁኑ ረከዓዎች የመጀመሪያውን ረከዓ በፋቲሃና በቁልያ አዩሃል ካፊሩን ፤ የሁለተኛውን ረከዓ በፋቲሃና በቁል ሁወላሁ አሐድ መስጀድ ፤ ጠዋፍ እንደጨረሰ ወደ ሰዕይ መሄድ የፈለገ ሰው ከቻለ ሃጀረል አስወድን ሂዶ በእጁ ሰላም ማለት ይወደዳል ፡፡ መሳሙና ወደ እሱ ማመልከቱ ተገቢ አይደለም ፡፡ ከዚያም ጠዋፍና ሰዕዬን ማከታተል፤ እናም ወደ ሶፋ ኮረብታ ሲሄድ ኢነ ሰፋ ወል መርወተ ሚን ሸዓኢሪላህ የሚለውን በመጀመሪያው ግዜ ብቻ ማንበብን ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
መስጅዱ እስከሚታየው ድረስ ወጥቶ ወደ እሱ በመዞር እጆቹን በማንሳት ሶስት ግዜ አላሁ አክበር! ብሎ ‹ላኢሃ ኢለላሁ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሃምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለውን በማንበብ ከዛም ዱዓ ማድረግ እና ይህንኑ ተግባር በየዙሩ ሶስት ሶስት ግዜ መደጋገም ፤ በሁለት አረንጓዴ ምልክቶች መካከል ጉዞን ፈጠን ፈጠን ማድረግ ፤ ጸጉር መላጨትና ጠዋፈል ወዳዕ የሚሉት ናቸው፡፡
3-9.የጠዋፍ ዓይነቶች
أنواع الطواف
1. ጠዋፍ አል ቁዱም /የመግቢያ ጠዋፍ/፣ 26 ይህ ወዲያው እንደ ደረሰ የሚያከናዉነው ጠዋፍ ነው ፡፡ በዚህ ጠዋፍ በሶስት ዙሩ ብቻ የሶምሶማ ጉዞ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ 2. ጠዋፍ አል ኢፋዳ ፣ ይህ ጠዋፍ ከዐረፋ ዉሎ እና ከሙዝደሊፋ አዳር በኋላ መሆኑ ግዴታ ቢሆንም ከነህር ቀን ሌሊት ግማሽ በኋላ አንስቶ እስከ ፈለገው ቀን ማዘግየት ችግር የለውም ፡፡ 3-ጠዋፍ አል ወዳዕ ፣ /የመሰናበቻ ጠዋፍ ፤/ ይህ ጦዋፍ ሑጃጆች ሁሉ ሀጃቸዉን ጨርሰው መካን ሲለቁ የሚያደርጉት ነው ፡፡ በሀጅም ሆነ በዑምራ ጊዜ መደረግ ያበት ጠዋፍ ነው ፡፡ በወር አበባ ደምና በወሊድ ደም ላይ ያለች ካልሆነ በሰተቀር ሁሉም ሊፈፅሙት ግድ ይላል ፡፡ እየቻለ ያልፈፀመው ደም አለበት፡፡ 4-ትርፍ ጦዋፍ ነው፡፡
3-10. የጦዋፍ ቅድመ መስፈርቶች
شروط الطواف
1) ሙስሊም መሆን ፤ 2) አዕምሮ ጤነኛ መሆን፤ 3) ቁርጥ ያለ ኒያ፤ 4) የጠዋፍ ጊዜው መግባቱ፤ 5) ለሚችል ሰው ሀፍረተ ገላን መሸፈን፤
26
ጠዋፍ ማለት ሰባት ጊዜ በካዕባ ዙሪያ መዞር ማለት ሲሆን እሱም የሚጀመረው ከሀጀረል አስወድ በመነሳት ነው ፡፡ የሚያበቃዉም በሱው ፡፡ .
33
6) ህፃን ካልሆነ በስተቀር ውዱዕ መኖር ፤27 7) በትክክል ሰባት ዙር መሙላቱን ማረጋገጥ፤ 8) ከዕባውን በስተግራው በኩል አድርጎ መዞር፤ ከተሳሳተ ይመልሳል፤ 9) ወደ ኋላ አለመሄድ፤ 10) ለሚችል ሰው በእግሩ መሄድ፤ 11) የጦዋፍ ዙሮችን ማከታተል፤ 12) በተከበረው መስጊድ ግቢ ውስጥ መሆን፤ 13) ከተከበረው ድንጋይ/ሀጀረል-አስወድ/ መጀመር 14)ሰዎነቱም ሆነ ልብሱ ንፁህ መሆን ናቸው፡፡ 3-11.የጦዋፍ ሱናዎችسنن الطواف 1) የተከበረውን ድንጋይ በእጅ ሰላም ማለት ፤ እና ከተቻለ እሱን መሳም ካልተቻለ ደግሞ በርቀትም ቢሆን ሰላም ማለት ፤ ይህን የተከበረ ዲንጋይ በመሳሙ ላይ ብዙ የመንፈስ ቀውሰኞች የተለያዩ ነገሮችን ለማስወራት ሞክረዋል ፡፡ ጉዳዩ ግን የፈጣሪን ትዕዛዝ ከማክበር አኳያ ከታየ ምንም ማለት አይደለም ፡፡ ተግባሩ መደረግ ስላለበት ይፈፀም እንጂ በእርሱ ላይ መንፈሳዊ እምነት ማለትም ይጠቅመኛል ይጎዳኛል ተብሎ ታምኖበት አይደለም ፡፡ ዑመር ይህኑ እውነታ ለማስታወስ ይመስላል እዚሁ ዲንጋይ አጠገብ ሆነው ነብዩ ሲስሙህ ስላየኋቸው እንጂ አልስምህም ነበር ፡፡ የማትጎዳ የማትጠቅም ዲንጋይ ነህ ብለው አስተምረዋል፡፡ 2) እሱ ዘንድ አላሁ አክበር ማለት፤ 3) የመናዊውን ማዕዘን ከተቻለ በእጅ ሰላም ማለት፤ 4) በጦዋፈል ቁዱም ብቻ ጊዜ ቀኝ እጅን ማውጣት፤ 5) ማረትረትና በቀስታ መሄድ፤ 6) በጦዋፉ መካከል ዱዓ ማድረግ፤ 7) ዚክር ማውሳት፤ 27
-በጦዋፍ ጊዜ የተሟላ ንፅህና ቢኖረው ጥሩ ቢሆንም እነ አቡ ሀኒፋና ኢብኑ ተይሚያ የመረጡት በጦዋፍ ጊዜ ውዱዕ ግዴታ አይደለም የሚለዉን ነው፡፡እኔም እንዲሁ፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
8) ከተቻለ ወደ ቤቱ-ከዕባው መቅረብ፤ 9) ከነብዩ ኢብራሂም መቋሚያ አጠገብ ሁለት ረከዐዎችን መስገድ ናቸው፡፡ 10)ጦዋፍን በፍርሃት በመተነናስ፤ 11)በጣም ካላስፈለገ በስተቀር ንግግር አለማብዛት፤ 12)ዚክር ማብዛት፤ 13)በንግግርም ሆነ በተግባር ሙስሊምን አዛ አለማድረግ ናቸው፡፡ 20) ጠዋፍን በተመለከተ ለሴቶች ብቻ የሚሆኑ ጠቃሚ ምክሮች የመመለሻውን ጠዋፍ (ጠዋፈል ኢፋዷ) ስትፈፅም የወር አበባ የመጣባትን ሴት የሚመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎች እነሆ፡የወር አበባዋ እስኪቆምና እስክትጸዳ ድረስ ጠብቃ የመመለሻ (ኢፋዷ) ጠዋፍ ትፈፅም ፡፡ ቀደም ብላ ሰዕይ ያላደረገች ከሆነ ሰዕይ ታድርግ ሆኖም እነዚህን ሁሉ የሐጅ ሥራዎች መሥራት የሚኖርባት ባልንጀሮቿ ይህን እስከምታደርግ ድረስ የሚጠብቋትና ጥለዋት ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ከሆነ ነው ፡፡ -አብረዋት ለሐጅ ሥራ ወደ መካ የሔዱት ባልንጀሮቿ ጥለዋት የሚመለሱና የማይጠብቋት ከሆነ ደግሞ ሌሎች አማራጮች ይኖሯታል፡፡ -እነዚህ አማራጮችም ወደ ሀገሯ ተመልሳ ትሄድና ከወር አበባዋ ከፀዳች በኋላ ከሙህሪሟ ጋር ተመልሳ መጥታ የመሰናበቻ ጠዋፋ መፈጸም የምትችል ከሆነ እንደገና በመመለስ የመሰናበቻ ጠዋፍ ማድረግ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ከሐጅ መሠረቶ እንዱ የሆነው ይህ ጠዋፍ የሚቀራት በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ከኢህራም እንደተፈታ ሰው የማትቆጠር መሆኑን ማወቅ ይኖርባታል፡፡ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ከኢህራም ለመፈታት ይህንን ጠዋፍ ማድረግ ይኖርባታል ፡፡ -ቀለል ያለውን የሀነፍይ መዝሀብ ስርዓት በመከተልም የወር አበባዋ ሳይቆም ተከናንባና ተጠንቅቃ ጠዋፍ ማድረግ ትችላለች ፡፡ ሆኖም ለማካካሻ ለድሃ የሚመፀወት እርድ መስዋዕት ታደርጋለች ፡፡ ወይም የማሊኪይን መዝሀብ በመከተል አንድ ቀን ሙሉ የወር አበባዋን የሚቆም መድኃኒት ትውሰድና ታጥባ ጠዋፍ ታድርግ ምክንያቱም በማሊኪይ መዝሀብ መሰረት ለአንድ ቀን የወር አበባ ከተቋረጠ እንደ መጽዳት ይቆጠራልና ነው ፡፡ በዚህ ዓይነት መልኩ ጠዋፍ የምታደርግ ሴት ምንም ማካካሻ አይጠበቅባትም፡፡ ሐጅን የሚፈፅም ሁሉ ወደ ሀገሩ መመለስ ሲፈልግ የመሰናበቻውን ጦዋፍ ሳያደርግ ሊመለስ አይገባም ፡፡ በንግድ ከተንቀሳቀሰ ይህን ጦዋፍ እንደገና .
35
ይመልስ ፡፡ ይህን ጦዋፍ ሳያደርግ ወደ ሀገሩ የወጣ ሰው ቅርብ ከሆነ ይመለስ ከራቀ ግን ደም ማፍሰስ አለበት ይላሉ፡፡ 4.ጠዋፍ አተጠውዕ ናቸው ፡፡ ከሩቅ ሀገር ከመጡ ሑጃጆች ይህ ጦዋፍ ከትርፍ ሶላት ይበልጣል፡፡ 3-12.በጦዋፍ ጊዜ የሚታዩ ስህተቶች أخطاء الطواف ተ. 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15
ስህተት ነወይቱ ጠዋፍ በማለት ኒያን በድምፀ ማውጣት፤ ከ ሃጀረል አስወድ በፊት ጠዋፍ መጀመር፤ ለየ ዙሩ የተለየ ዱዓ ማድረግ፤ በሂጅር ኢስማኤል ግቢ መጠወፍ፤ በሁሎችም የጠዋፍ ዙሮች ሶምሶማ ማድረግ፤ በግፊ ግዜ ሐጀረል አስወድን እስማለሁ በማለት ሰዎችን ማስቸገር፤ የካዕባ ማእዘናትን ሁሉንም በእጅ መንካት፤ የኢበራሂም መቆሚያን መንካትም ሆነ መሳም ለዚሁመ ጉዳይ መጋፋት፤ ኢብራሂም መቆሚያ አጠገብ እሰግዳለሁ በማለት ችግር መፍጠር፤ ሀጀረል አስወድን ሰላም ለማለት ሲባል ከአጅ ነብይ ጋር መጋፋት፤ ሃጀረል አስወድንም ሆነ ሩክነል የማኒን ሰላም ሲል በግራ እጁ መንካት፤ ለዱዓ ድምፅን ከፍ ማድረግ፤ በአንድ አቀንቃኝ መሪነት ዱዓ ማድረግ፤ በካዕባ መተሻሸት፤ የካዕባ መጋረጃዎችን መሳም፤
3-13.የመሰዋዐት አይነቶች
أنواع الفدية
ሀ. ሱንና የሆነ የዕርድ መስዋዕት፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ለ. የስለት የሆነ መስዋዕት፤ ሐ. የማካካሻ (ከፋራህ)የሆነ መስዋዕት ፤ መ. ምስጋና ለማድረስ የሚፈፀም የግዴታ መስዋዕት፤ሰ-ፀጉርን መላጨት/ማሳጠር ረ-ጦዋፈል ኢፋዷን መጦዎፍ ናቸው፡፡
3- 14.የሰዕይ 28 ቅድመ ሁኔታዎች ዘጠኝ ናቸው፡፡
شروط السعي
1) ሙስሊም መሆን፤ 2) አዕምሮ ጤናማ መሆን፤ 3) ኒያ መኖር ፤ 4) ማከታተል፤ 5) ለሚችል በእግሩ መሄድ፤ 6) በትክክል ሰባት መሙላቱን ማረጋገጥ፤ 7) በሶፋና በመርዋ ጋራዎች መካከል ማዳረስ፤ 8) ይህን ጉዞ ከትክክለኛ ጦዋፍ በኋላ መደረጉ፤ 9) ነጠላ ቁጥር ከሶፋ፤ ሙሉ ቁጥርን ደግሞ ከመርዋ መጀመር ናቸው፡፡ የሰዕይ ሱናዎች ከጠዋፍ ጋር የተያያዘ መሆን፣ በሶፋና በመርዋ ላይ መውጣት ፣ ተክቢራና (አላሁ አክበር) ተህሊል (ላኢላሀ ኢለሏህ) በማለት በፍትነት መሮጥ ናቸው፡፡ سنن السعي
3-15.የሰዕይ ሱናዎች
1-ከጠዋፍ ጋር የተያያዘ መሆን፣ 2-በሶፋና በመርዋ ላይ መውጣት፣ 3-ተክቢራና (አላሁ አክበር) ተህሊል (ላኢላሀ ኢለሏህ) ማለት ፤ 4. ውዱዕ ከሚያስፈቱ ነገሮችም ሆነ ከቆሻሻዎች መፅዳት፤ ሀፍረተ ገላን መሸፈን፤ 28
-ሰዕይ ማለት ሶፋና መርዋ በተባሉት ጉረብታ ቦታዎች መካከል ሰባት ጊዜ መጓዝ ሲሆን ለወንዶች ብቻ በሁለቱ አረንጓዴ መብራቶች መካከል ላይ ፍጥነትን ጨምሮ መጓዝ ይገባል፡፡ .
37
5. በእሱ ላይ እያሉ ዚክርና ዱዓን ማብዛት፤ 6. እንዳስፈላጊነቱ በየቦታው መፍጠንና ቀስ ማለት፤ 7. ሁለቱም ሶፋና መርዋ ጋራዎች ላይ መውጣት፤ 8. ጦዋፍንና እሱን ማከታተል ናቸው፡፡ أخطاء السعي
3-16.በሰዕይ ላይ የሚታዩ ስህተቶች ተ 1 2 3 4 5 6 7 8 9
ስህተት ሶፍዋ ወይም መርዋ ጫፍ ካልወጣን ሰዕይ አይሆንም ብሎ ማመን፤ 14 ግዜ ሰዕይ ማድረግ በመሮጫ ምልክቶች መካከል እንደ ጠዋፍ ሶምሶማ ሶስቱን ዙር ላይ ብቻ ማቆም ፤ ከመሮጫ ምልክቶች ውጪ ባሉ ቦታዎች መሮጥ፤ በሶፋም ሆነ መርዋ ላይ ወደ ካዕባ ዙሮ ልክ እንደ ሰላት ተክቢራእጅን ማንሳት፤ ሰዒይ ላይ ልክ እንደጠዋፍ ሁለት ረከዓ መስገድ፤ ሰዕይ እያረገ ባለበት ኢቃም ሲደረግ ያንን ዙር ልሙላ በማለት መቀጠል፤ ያለ ውዱዕ ሰዕይ እማይደረግ መስሎት መጨናነቅ፤ በየ ዙሩ ኢነ ሰፈ…. የሚለውን መቅራት፤
3-17. የሐጅ ስነ-ስርአት ቅደም ተከተል ልክ
كيفية الحج مرتبة
ኢህራም ፡ኢህራም ማለት ማሰብ ፤ መነየት ፤ ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡ የኢህራም ልብስ ማለት ደግሞ ለወንድ ያልተሰፋ ብትን ጨርቅ ሆኖ ሽርጥና ከወገብ በላይ የሚለበስ ጨርቅ ሲሆን ፤ ለሴት ልጅ ደግሞ ፊቷን የማይሸፍንና ጌጣጌጥ የሌለው ልብስ ማለት ነው ፡፡ በአጠቃላይ ኢህራም ሲባል የሐጅ ወይም ኡምራ ፀሎት ማድረግ ፈልጎ የሚመጣ ሰው በየአቅጣጫው በተወሰኑት የኢህራም ቦታዎች ሲደርስ የሐጅ ወይም የኡምራ ፀሎት ለመፈጸም ከልቡ ወስኖ ልብስ በመቀየር የሐጅና የኡምራን ፀሎት ወይም ከሐጅና ከዑምራ አንዱን ለመፈፀም ማሰብ ማለት ነው ፡፡ እናም ይህን ማድረግ የፈለገ ሰው ፡- ገላውን መታጠብ ፤ መፀዳዳት ፤ ልብሱ ሳይሆን ሰዉነቱን الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
መሻተት ፤ ለወንዶች የተሰፉ ልብሶችን አውልቆ ንፁህና ነጫጭ የሆኑ ሽርጥና ኩታ መልበሱ ሱና ነው ፡፡ እናም ሐጅን ማድረግ የሚፈልግ ሰው በፈረሱ /መኪናው/ ላይ ሆኖ (ለበይክ አላሁመ ለበይከ ፤ለበይክ ላሸሪከ ለከ ለበይክ ፤ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላሸሪከ ለከ) በማለት ኢህራሙን ይጀምር ፡፡ ይህንንም ቃል መደጋገሙና ማብዛቱ ፤ እሱንም በማለት ከሴቶች በስተቀር ድምፅን ከፍ ማድረጉ ይወደዳል ፡፡ ከዚያም ለበይከ አላሁመ ዑምረተን ወይም ሐጀን ወዑምረተን በማለት በውስጡ ያሰበውን በአንደበቱ መናገሩ ይወደዳል፡፡ ወደ ሐጅ ሥርዓት ከገባ በኃላ በሆነ ችግር ምክንያት ኢህራሜን እፈታ ይሆናል የሚል ስጋት ከገባው ‹ከኢህራሜ የምፈታው ባገድከኝ ቦታ ላይ ነው› በማለት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ይቻላል ፡፡ ከቶዉንም ተገቢ ነው ብለው ያስተማሩ ብዙ ናቸው ፡፡ በተለይ በልዩ ልዩ ምክኒያት ስጋት ያደረባችሁ ሁሉ ይህን ስርአት ብትከተሉ ለእናንተም መፍቲሄ ነው ፡፡ ከላይ የተጠቀሰዉን ዚክር ሴቶች ሲቀሩ ለወንዶች ድምፅን ከፍ በማድረግ በብዛት ማለቱ ይወደዳል ፡፡ በኢህራም ጊዜ ከሚደረጉ ጥንቃቄዎች መካከል ኢህራም አድራጊው ሰው ስጋት ካለበት የምፈታው ባገድከኝ ቦታ ነው ብሎ መናገር ይገባል፡፡ ኢህራም ሳያደርግ የኢህራም ቦታዎችን ያለፈና መካ የገባ ሰው ተመልሶ ከቦታው ኢህራም ማድረግ አለበት ፡፡ ካልቻለ ደግሞ ለመካ ድሃዎች የሚከፈል በግ ማረድ አለበት ፡፡ الميقات
3-18.የኢህራም ማድረጊያ ቦታዎች
የኢህራም ማድረጊያ ቦታዎች ማለት ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ ወደ መካ የሚሄድ ሰው ኒያ ወይም ሀሳብ ሳያደርግ የማይታለፍ ቦታማለት ሲሆን ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ የሐጁ ፀሎተኞች ታላቁ ነብዩ መሐመድ የት የት ቦታ ኢህራም ማድረግ እንዳለባቸው በግል ያስቀመጧቸው ናቸው ፡፡ እነሱም ፡ስም የአሁን ስሙ ተጠቃሚ ህዝቦች ርቀት በኪ .ሜ ጁህፋህ ራበግ በሻምና በቱርኪያ፣ ለሞሮኮና መሰሎቹ 200 ቀርኑን መናዚል - ከነጅድ የአረብ ኤምሬትና የመሳሰሉት ሀገሮች 94 የለምለም
ከየመን እናከሀገራችን ኢትዮጵያና ከመሳሰሉት 54 .
39
ዙልሁለይፋ ዛቱ ኢርቅ
አባር አሊይ ከመዲና ከአካባቢዋ ለሚመጡ ከመካ 45 ከኢራቅ በኩል ለመሚጡ 49
6-በመካ ዉስጥ የሚኖሩ ሁሉ ለሐጅ ከየቤታቸው ነው ኢህራም ማድረግ ያለባቸው ፡፡ 7--በመካ ዉስጥ የሚኖሩ ሁሉ ለዑምራ ግን ከሐረሙ ክልል ዉጭ ወጥተው ነው ኢህራም ማድረግ ያለበት ፡፡ 8-ከእነዚህ ኬላዎች ዉጭ ወደ መካ የሚገቡ ሁሉ ለእነሱ ቅርብ በሆነ የኢህራም ቦታ ሲደርሱ ያህርሙ ፡፡ 9-ከኢህራም ቦታዎች በፊት ኢህራም ቢያደርግ ብዙም ችግር የለበትም ፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሑጃጆች ኢህራም ቦታችን ጋር መቸ ልንስተካክል ስለማናውቀው ከዚያው ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ኢህራም እንዲያደርጉ እመክራለሁ ፡፡ ምክኒያቱም ብዙ ሰዎች እንቅልፍ ስለሚጥላቸው/ ወይም አስተናጋጆች ስለሚረሱት /ወይም እነሱ ቢናገሩም ብዙ ሰው ስለማይሰማው ሳያህረሙ ጂዳ የደረሱ አጋጥሙኛልና ነው ፡፡ 10-አስቀድሞ ወደ መዲና ለመሄድና ከዙልሁለይፋ ኢህራም ማድረግ አስቦ የኢህራም ቦታዉን ያለፈ ሰው ምንም የለበትም ፡፡ 11-ወደ መዲና እንዳይሄድ ከተከለከለም በዚያው ባለበት ቦታ ኢህራም ያድረግ ፡ ፡ በዚህም የተነሳ ምንም ቅጣት የለበትም ፡፡ 12-ኢህራም አድርጎ መጥቶ ጂዳ ሲደርስ ወደ መዲና እንዲሄድ የታዘዘ ሰው ኢህራሙን መፍታት የለበትም ፡፡ أشهر الحج
3-19.የሐጅ ኢህራም ማድረጊያ ወራቶች
የሐጅ ኢህራም ማድረጊያ ወራቶች ደግሞ ሰባ ቀኖች/ሁለት ወር ከአስር ቀናት/ ገደማ ናቸው ፡፡ እነሱም ከሸዋል ወር አንደኛ ሌሊት ጀምሮ እስከ የዙል ሂጃ ወር አስረኛው ቀን ንጋት ድረስ ነው፡፡
3-20.በኢህራም ወቅት ከሚታዩ ስህተቶች ተ.ቁ ስህተት الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
أخطاء اإلحرام
1 2 3 4 5
ያለ ኢህራመ ቦታዉን ማለፍ፤ የኢህራም ልብስን መልበስን ብቻ እንደ ንያ መቁጠር፤ ለሴቶች ልዩ የኢህራም ልብስ እንዳለ ማሰበ፤ ሐይድ ያለባት ሴት ያለ ኢሀራመ ቦታዉን ማለፍ፤ ኢህራም ካደረገ ጀምሮ ቀኝ እጅን ማውጣት፤
3-21.የሐጅ ወር የ8ኛው ቀን ተግባራት
أعمال يوم التروية
በመካ ውስጥ የሚኖር እና ከኢህራም የተፈታ ከሆነ የዙልሒጃህ ስምንተኛው ቀን ሲሆን ካለበት ቦታ (ከቤቱ) ኢህራም አድርጎ የዘጠነኛውን ቀን ሌሊት በሚና ለማደር አስቦ ወደ ሚና ጉዞውን ይጀምር ፡፡ 1. የኢህራም ልብስ ይለብሳል፣ 2. ለሐጅ ይነይታል ፣ የኢህራም ሁለት ረከአ መስገድ፤ 3. ከዚያም (አላህ ሆይ ! ሐጅ እፈልጋለሁና ስራውን አግራልኝ ኢባዳንም ተቀበለኝ አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና የሚለውን ፀሎት ያደርጋል) በመቀጠልም ፀሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ሚና ጉዞ ማድረግ ፡፡ 4. ዝሁርን ፣ አስርን ፣ መግሪብንና ዒሻን እዚያው መስገድ፤ 5. እዚያው በማደር ሱብሂንም ሚና ላይ መስገድ፡፡ 3-22.የሐጅ ወር የ9ኛው ቀን ተግባራት أعمال يوم عرفة የዘጠነኛው ቀን ፀሐይ ስትወጣ ረፋዱ ላይ ወደ ዐረፋ ጉዞውን ይቀጥል፤ ወደ አረፋ ምድር ሲሄድ ሊከተላቸው የሚገቡ ሱናዎች፡1. ንጋት ላይ ፀሐይ ከወጣች በኋላ ወደ አረፋ ምድር ጉዞ መጀመር ፤ 2. ከተቻለም ወደ ‹ነሚራህ››መስጊድ ተጉዞ ኹጥባ ማዳመጥ ፤ 3. የዙህርና የአስርን ሰላት እዚያው አሳጥሮና በአንድ ላይ መስገድ ፣ 4. ከዚያም ከቀኑ አጋማሽ በኋላ አረፋ ወደ ሚቆምበት ስፍራ መሄድ፤ ዑርናህ የተባለው ቦታ ሲቀር ሁሉም የአረፋ ቦታዎች ለውቁፍ የተፈቀዱ ናቸው፡ ፡ 5. ዚክርና ዱዓ ማብዛት ፤ -እዚህ ላይ የሚከተሉትን ዱዓዎች ማድረግ የተመረጠ ነው ፡፡ ‹ከዱዓዎች ሁሉ መልካም ዱዓ በአረፋ ቀን የተደረገ ዱዓ ነው ፡፡ (ላኢላህ ኢለሏህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለዉን .
41
ዱዓ ማለት ያብዛ ፤ ለኔና ከኔም በፊት ለነበሩት ነብያት ከተላለፈልን መልዕክቶች ሁሉ በላጩ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም አንድ ነው አጋር የለውም ፡፡ ንግስና የእርሱ ብቻ ነው ፤ ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው ፤ እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነው የሚለው ነው›› ሲሉ ተርሚዚይ በዘገቡት ሐዲስ ላይ ተናግረዋል፡፡ በሌላም ሐዲስ ነቢዩ ሙሐመድ ‹ ﷺአላህ ሆይ ! ልቦናዬ ውስጥ ብርሃን ጆሮዬም ውስጥ ዓይኔም ውስጥ ብርሃን አድርግልኝ ፡፡ አላህ ሆይ ! ልቤን አስፋልኝ ነገሬን ሁሉ አድርግልኝ› የሚለው ፀሎትም የተመረጠ መሆኑን ረሱል በይሐቂ በዘገቡት ሐዲስ ተናግረዋል ፡፡ م م م )اب النَّا مر َ ( َربَّنَا آتنَا مِف الدُّنحيَا َح َسنَةا َومِف اْلخَرةم َح َسنَةا َوقنَا َع َذ ‹ጌታችን ሆይ ! በዚህ የቅርቢቱ ዓለም መልካሙን ነገር ፤ በመጪውም ዓለም መልካሙን ነገር ስጠን ፤ ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን› እንዲሁም ፡ُّ وَلَ يَغح مفر، ت نَ حف مسى ظُلحما َكثمريا يَا حغ مف حر مَل َمغح مفَرةا مم حن معحن مد َك، ت َ وب إمَلَّ أَنح ُ « قُ مل اللَّ ُه َّم إم ِِّّن ظَلَ حم َ ُالذن َ ا ا ُ َّك أَنحت الحغَ ُفور َّ م ‹ يم َ َ َو حارَحَحمن إمن، ُ ُ الرح አላህ ሆይ ! ራሴን በብዛት በድያለሁ ኃጢአቴን ከአንተ ሌላ የሚምር የለም ከአንተ የሆነ ምህረትን ለግሰኝ እዘንልኝም አንተ መሐሪ አዛኝ ነህና አላህ ሆይ ! ከኃጢአት ውርደት ወደ ታዛዥነት ክብር አዝልቀኝ በሀላልህም ከሀራምህ ጠብቀኝ በችሮታህ ከአንተ ውጭ ያለን ፍጡር ከመከጀል አድነኝ መልካም ነገሮችን ሁሉ ሰብስብልኝ አላህ ሆይ መብቃቃትን እጠይቅሀለሁ ፍርሀትንም (ተቅዋ) ጥብቅ ሀብትንም እማፀንሀለሁ› 6. ፀሐይ እስከምትጠልቅም ድረስ አረፋ ላይ መቆየት፣ 7. በዐረፋ ቆይታ ወቅት በተመስጦ ወደ አላህ ፀሎት ማድረግና መተናነስ እንዲሁም አላህን በብዛት ማውሳት ፤ 8. በዚሁ እለት ለነብዩ ሙሐመድ ﷺበብዛት ሰለዋት መለመን፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
9. እንዲሁም ቁርኣንን ማንበብ በተለይም ሱረቱል ሐሸርን መቅራት 10. በዱዕ ወቅት እጅን ወደ ላይ ዘርግቶ ፊትን ወደ ቂብላ ማዞር፤ 11. ንፁህ መሆን (ጡሀራ መሆን) ናቸው፡፡ 12.በተጨማሪም ለወንድና ለሴት አማኞች በሙሉ ፀሎት ማድረግም ይወደዳል፡ ፡ በአዐረፋ መቆም የሐጂ ቁንጮ ዋናው ማዕዘን እንደሆነ ምንም ልዮነት የለበትም፡ ፡ ሆኖም ይህን ግዴታ ለመወጣት ለሴኮንድ ቢሆንም በዐረፋ ምድር ከተገኘ እንደፈፀመው ይቆጠራል ፡፡ አንዳንድ ዓሊሞች ‹በአየር ቢያልፍ እንኳን ኒያው እስካለው ድረስ አረፋ እንደደረሰ ይቆጠራል› ብለዋል ፡፡ ጊዜውም ቢሆን ከአረፋ ግማሽ ቀን ጀምሮ እስከ ነህር ቀን ንጋት ድረስ ነው ፡፡ ከፀሀይ መጥለቅ በፊት ወደ ሙዝደሊፋ መውጣት ከባድ ችግር ነው ፡፡ እናም ይህን የፈፀመ ሰው ደም ግዴታው ነው፡፡ سنن يوم عرفة
3-23.የዘጠነኛው ቀን ሱናዎች
1. መግሪብንና ዒሻን አዳብሎ በኢሻ ወቅት መስገድ፣ 2. በሙዝደሊፋ ሜዳ ክልል ዉስጥ ማደር ፤ 29 3. የፈጅርን ሰላት በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እዚያው መስገድ ፣ 4. መሸአረል ሀራም ላይ ንጋቱ እስኪጎላና ፀሐይ ለመውጣት እስከምትቀርብ ድረስ ተክቢራና ተህሊል (አላሁ አክበርና ላኢላሀ ኢለላህ) እያሉ መቆየት፣ 5. ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ወደ ሚና ጉዞ መጀመር፣ 6. ለመጨረሻው የጠጠር ውርወራ ሥርዓት ሰባት ጠጠሮችን መልቀም ናቸው ፡፡ 3-24.በአረፋ ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች أخطاء يوم عرفة ተ. ስህተት 1 ከአረፋ ክልል ውጪ መስፈር፤ 29- እዚህ ላይ ሴት አብሮ የያዘ ሐጅ አድራጊ ለጠጠር ውርወራ ሥርዓት ለመፈፀምና ለጠዋፍ ሴቷ ከወንዶች ጋር እንዳትጋፋና እንዳትጎዳበት ከሌሊቱ አጋማሽ በኋላ ከሙዝደሊፋ መንቀሳቀሱ ይመረጣል፡፡ .
43
2 3 4 5 6 7 8 9
አረፋ ጸሀይ ከመጥለቁዋ በፊት መመለስ፤ በዱዓ ግዜ የአረፋን ተራራ መቅጣጨት፤ ከአረፋ ወደ ሙዝደሊፋ ሲመለሱ መጋፋት፤ ጋራው ላይ ለመውጣት መጋፋት፤ የአረፋን ቀን በአልባሌ ወሬዎች ማሳለፍ፤ በፎቶገራፍና በቪዲዮ ቀረጻ እራስን መወጠር፤ የአረፋ ቀን መፆም፤ ተልቢያ ማቋረጥ፤
3-25.የሙዝደሊፋ አዳር ተግባራት أعمال ليلة مزدلفة ከዚያም በኋላ ወደ ሙዝደሊፋ በሙዝደሊፋ ቆይታ ወቅት የሚፈፀሙ የሐጅ ሥራዎች ብዙ ሲሆኑ በሙዝደሊፋ ላይ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ እዚያው መቆየት በሁሉም ሐጃጆች ላይ ግዴታ ነው ፡፡
3-26.በሙዝደሊፋ ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች
أخطاء ليلة مزدلفة
ተ. ስህተት 1 ከአረፋ ወደ ሙዝደሊፋ ሲሄዱ መጋፋት፤ 2 በመጀመሪያ እንደደረሱ መግሪብና ኢሻ ሰግደው ማረፍ ሲገባቸው ወደ ጠጠር ውርወራ መግባት፤ 3 ከሙዝደሊፋ ከግማሽ ሌሊት በፊት መውጣት፤ 4 ሙዝደሊፋ ሳይደርሱ መስፈር፤ 5 መግሪብና ኢሻን በመንገድ ላይ መስገድ፤ 6 ዒሻና መግሪብን ሙዝደሊፋ ካልደረስኩ በሚል ወቅቱም ቢያልፍ ዝም ብሎ ማሳለፍ፤ 7 ሱበሂን ከመንጋቱ በፊት መስገድ፤ 8 የሙዝደሊፋን ሌሊት በኢባዳም ቢሆን ሳይተኙ መደር፤ 9 በሙዝደሊፋ ጸሃይ እስክትወጣ መጠበቅ ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
3-27.የሐጅ ወር የ10ኛው ቀን ተግባራት በአጭሩ أعمال يوم النحر 1-የሱብሂን ሶላት ቀደም ብሎ በሙዝደሊፋ ሰግዶ ዱዓ እያደረገ እዚያው ቆይቶ በጣም ሲነጋ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት በሙሐሲር ሸለቆ /ቦታ/ሲደርስ የአቅሙን ያህል ፈጠን ፈጠን እያለ ወደ ሚና መሄድ፤ 2- ጀምረተል ዐቀበህ ላይ ጠጠር መወርወር ፤ 3-በየጠጠሩ አላሁ አክበር እያለ ሲወረውር እጆቹን ያንሳ፡፡ ጠጠሮች ቋሚውን ባይመቱም በገንዳው ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4-ጠጠር መወርወር ሲጀምር ለበይክ የሚለውን ያቋርጥና አላሁ አክበር ይበል፡ ፡ 5-ከዚያም ስጦታውን ይረድ፡፡
3-28.በጠጠር ውርወራ ላይ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል أخطاء الرمي
ተ. ስህተት 1 ከመጠን በላይ ግፊ፤ .
45
2 3 4 5
ሰባቱን ጠጠሮች በአንድ ግዜ መወርወር፤ ሸይጡዋንን እንደሚመቱ ሁሉ መበሳጨት፤ በትላልቅ ድንጋዮች በጫማዎች በዣንጥላዎች መወርወር፤ በአንደኛውና በሁለተኛው ውርወራ በሁዋላ ሊደረግ የሚገባውን ዱዓ አለማድረግ ፤ 6 ያለ በቂ ምክንያት ሌሎችን መወከል፤ 7 ግፊያውን በመፍራት ከመደበኛ መወርወሬያ ሰዓቱ በፊት ወይም በሁዋላ ማደረግ፤ 8 ቅደም ተከተላቸውን አለመጠበቅ፤ 9 የተወረወረው ጠጠር ገንዳው ውስጥ መግባቱን አለማረጋጥ፤ 10 በጠጠር ውርወራ ሰዓት የተለያዩ ዱዓዎችን ማለት፤ 11 ጠጠሮችን ማጠብ፤ 12 ጠጠር መወርወሪያ ቦታዎችን እንደ ሸይጧን መቁጠር፤
3-29.የሐጅ አራተኛው ቀን የሆነው የ 11ኛው ቀን ተግባራት أعمال الحادي عشر በየቀኑም ከግማሽ ቀን/ፀሃይ ካዘነበለች በኋላ/ በሶስት የመወርወሪያቦታዎች ሰባት ሰባት ጠጠሮችን ይወረውራል፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
በመጀመሪያው ጠጠር ውርወራ /ጀምረተል ኡላ/ ጀምሮ ሰባት ጠጠሮችን ከወረወረ በኋላ ትንሽ ወደፊት ቀደም ብሎ ቆም ካለ በኋላ የፈለገዉን ዱዓዕ ያድርግ ፡፡ ከዚያም ወደ መካከለኛዋ/ ጀምረተል ውስጣ/ሂዶ ልክ እንደዚሁ ይወረውርና ያሻዉን ዱዓ ያደርጋል ፡፡ ከዚያም የመጨረሻዋን ይወረውርና ለዱዓ ሳይቆም ወደ ቦታው ይመለስ፡፡ የሐጅ ወር የ12ኛው ቀን ተግባራት اعمال اليوم الثاني عشر 1-ከዚያም በአስራ አንደኛው ቀን እንደወረወረው ሁሉ በሶስቱም ቦታዎች ላይ መወር ወር ነው ፡፡ 2-ከፈለገም በዚያው ቀን ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ከሚና መውጣት፡፡ 3-30.የሐጅ ወር የ13ኛው ቀን ተግባራትاعمال اليوم الثاني عشر 1-አስራ ሶስተኛዉን ቀን መቆየት ከፈለገ በአሥራ ሁለተኛው ቀን እዚያው ሚና እያለ ፀሐይ ከገባችበት ሚና ማደርና 2-በነጋታው በሶስቱም የጠጠር መወርወሪያ ቦታዎች ላይ መወርወር ይጠበቅበታል፡፡
3-31.ማሳሰቢያ 1-በአስራ ሁለተኛው ቀን ለመውጣት ቆርጦ ግን ግፊያው አላስኬደው ብሎ የተቸገረ ሰው ፀሐይ ከገባች በኋላም ቢወጣ ችግር የለውም ፡፡ 2-ቃሪን የሆነ ሐጃጅ ልክ እንደ ሙፍሪድ ነው ፡፡ ባይሆን እንደ ሙተመቲዕ ሁሉ ሀድይ/ስጦታ/ማረድ አለበት፡፡ 3-ወደ ሀገሩ መመለስ ሲፈልግ ከአላህ ቤት የመሰናበቻ ጦዋፍ ሳያደርግ ሊመለስ አይገባም፡፡ 4-የወር አበባና የወሊድ ደም ያለባቸው ሴቶች የመሰነበቻ ጠዋፍ የለባቸውም፡፡ 5-የመሰናበቻ ጠዋፍ ካደረገ በኋላ ለንግድ ከተንቀሳቀሰ ይህን ጦዋፍ እንደገና ይድገም ፡፡ 6-ይህን ጦዋፍ ሳያደርግ ወደ ሀገሩ የወጣ ሰው ቅርብ ከሆነ ይመለስና ጠዋፍ ያድርግ ከራቀ ግን ደም ማፍሰስ/ማረድ/ ይኖርበታል፡፡
.
47
7-የሚመረጠው በዕለቱ ጠጠሩን መወርወር ነው ፡፡ ሆኖም ለሁለተኛው ቀን ቢያሳልፈው ወይም የሁሉንም ቀን ጠጠር ውርወራ ወደ መጨረሻው ቀን ቢያዘገየው ምንም ችግር የለውም 30፡፡ 3-32. የሐጅ ወር የ12ኛው ቀን ከሚስተዋሉ ስህተቶች أخطاء اليوم الثالث عشر ተ. 1 2 3
4
ስህተት ጠጠር ውርወራ ሳይጨርሱ የመሰናበቻ ጠዋፍ ማድረግ፤ ከመሰናበቻ ጠዋፍ በሁዋላ መካ መሰንበት፤ አንዳንድ ሁጃጆች የመሰናበቻ ጦዋፉን መስጂደል ሐራምን ለቀው ሲወጡ ጀርባቸውን ለካዕባ ላለመስጠት ፊታቸውን ወደ ካዕባ አዙረው ወደ ኋላ መሄዳ በዲን የማይታወቅ ፈጠራ ነው፡፡ እንዳንድ ሁጃጆች ሚና የጠጠር ውርወራን ከጨረሱ በኋላ ከዚያው ከሚና ተነስተው ወደ ሀገራቸው መሄዳቸው ስህተት ነው ፡፡ ምክኒያቱም ነቢዩ (የመጨረሻ የሐጅ ስራችሁን ጠዋፍ አድርጉት) ብለዋልና ፡፡ ሆኖም ከመሰናበቻ ጠዋፈል ወዳዕ በኋላ ወድያውኑ መካን ለቆ መውጣት ተገቢ ነው፡ ፡
3-33.በኢህራም ምክኒያት የሚከለከሉ ነገሮች እና ማካካሻዎች محظورات اإلحرام وكفارتها በሐጅ ወይም በዑምራ ኢህራም ምክንያት የሚከለከሉት ዘጠኝ ነገሮች ናቸው ፤ እነሱም፡1ኛ. ፀጉርን መላጨት ነው ፡፡ ይህም ማለት የራስንም ሆነ በሌላ የሰዎነት አካሎች ላይ ያሉ ፀጉሮችን ያጠቃልላል፡፡ 2ኛ. ጥፍርን መቁረጥ ፡፡
30-ይህ ጉዳይ በዚያ ግፊቱ ብዙ እልቂቶችን እያስከተለ ባለበት ዘመን ነበር፡፡ አሁን ግን በጣም ተግራርቶ ባለበት በዚያው ቀን ማድረግ ይገባል፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
3ኛ.ለወንዶች የተሰፋ ሙሉ ልብስ ወይም በግማሽ ወይም በትንሹ የተሰፋን መልበስ የተከለከለ ፡፡ ሆኖም ሸርጥ በማጣቱ ሱሪ ቢለብስ ወይም ነጠላ ጫማ አጥቶ ሙሉ ጫማ ከቁርጭምጭሚት በታች አሣጥሮ ቢለብስ ምንም የጥፋት ማካካሻ የለበትም፡፡ 4ኛ. ለወንድ እራሱንም ሆነ ፊቱን መሸፈን ነው፡፡ 5ኛ. ለልብሰም ሆነ ለሰውነት ሸቶ መጠቀምነው ፡፡ ከኢህራም በፊት የተጠቀመው ሸቶ ቅሬቱ ቢታይ ምንም ችግር የለዉም፡፡ 6ኛ.አውሬ ማደንነው ፡፡ ይህም ማለትም የዱር አውሬ ሆኖ መብላቱ የተፈቀደውን ማለት ነውነው ፡፡ 7ኛ.ጋብቻን መፈፀም፤ይህን ማድረግ ክልክል ቢሆንም ቢፈፅም ግን ምንም ማካካሻ የለበትም፡፡ 8ኛ. ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ በስሜት መተሻሸት ሲሆን ፤ የዚህም ማካካሻው አንዲት ፍየል ወይም ሶስት ቀን መፆም ወይም ስድስት ድሆችን ማብላት ነው፡፡ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ፤ ይህ ተግባር የተፈፀማ ከመጀመሪያው መፈታት በፊት ከሆነ ሐጁ ይበላሻል ፡፡ ሆኖም ሐጁን ጨርሶ በሚቀጥለው አመት ቀዷ ማውጣት የኖርበታል ፡፡ ይህም የሚሆነው ለመካ ድሆች የሚከፋፈል አንድ ግመል ከማረድ ጋር ነው ፡፡ ከመጀመሪያው መፈታት በኋላ ከሆነ ግን ሐጁ አይበላሽም ፡፡ አንድ ግመል ግን ማረድ አለበት፡፡ በዑምራ ፆሎት ላይ እያለ የግብረ ስጋ ግንኙነት ቢፈፅም ዑምራው ይበላሻል ፡፡ እናም አንዲት ፍየል ማረድ አለበት ፡፡ ዑምራንም በሌላ ጊዜ ቀዷ ማውጣት አለበት ፡፡ ከግብረ-ስጋ ግንኙነት ውጭ በሆነ ነገር ሐጅ ወይም ዑምራ አይበላሽም ፡፡ ሴት ልጅ በዚህ ሁሉ ልክ እንደ ወንድ ናት ፡፡ ሆኖም የተሰፋ ልብስ መልበስ ትችላለች ፡፡ ጓንትና የአይን እርግብ ወይም ኒቃብ መልበስ ግን አትችልም ፡፡ በሐጅ ላይ እያለን የምንፈፅማቸው ስህተቶች ማካካሻን በተመለከተ ከዚህ በታች ያሉትን ተመልከቱ 1. አዛ በመሆን፤ ሽቶ በመቀባት ፤ በልብስ አለባበስ ላይ ለሚከሰቱት ስህተቶች ማካካሻው ፊድያ መክፈል ነው ፡፡ እሱም ሶስት ቀን መፆም ወይም ስድስት ድሆችን በማሸቁና ገብስ፤ ስንዴ መስጠት ወይም አንዲት በግ/ፍየል ማረድ ነው ፡፡ .
49
م صرُُت يَما است يسر ممن ا حَل حد مي وََل َحُتلم ُقوا ر وس ُكم ح َّىَّت ي ب لُ ََ ا حَل حد م اْل َّج والحعمرةَ لملَّ مه يَمإ حن أ م ي ََلَّهُ ح ُح ح ح َ ح َ ح َ َ َ َ َ ُ ُ َ ح َ َح َ ُ َوأَِتُّوا حَ َ ُ ح َ ٍ م م ٍ مم م م مم م م م ٍ َّع يَ َم حن َكا َن محن ُك حم َم مر ا يضا أ حَو به أَذاى م حن َرأحسه يَف حديَةٌ م حن صيَام أ حَو َ ص َدقَة أ حَو نُ ُسك يَإذَا أَمحنتُ حم يَ َم حن ِتََت َ اْل ِّج يَما استَ يسر ممن ا حَل حد مي يَمن ََل َمَي حد يَ م م ك صيَ ُام ثَََلثَمة أَيَّ ٍام مِف ح اْلَ ِّج َو َسحب َع ٍة إمذَا َر َج حعتُ حم تملح َ بالح ُع حمَرةم إم ََل حَ َ ح ح َ َ َ َ َ ح ح م م م ك لممن ََل ي ُكن أَهلُه ح م يد الحعم َق م اض مري الح َم حس مج مد ا حْلََرمام َواتَّ ُقوا اللَّهَ َو حاعلَ ُموا أ َّ اب َن اللَّهَ َشد ُ َع َشَرةٌ َكاملَةٌ ذَل َ َ ح ح َ ح ح ُ َ ()669
‹ሐጂንና ዑምራን ለአላህ ሙሉ ፡፡ መብት ብትታጉዱም ከሀድይ ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ፡፡ሀድዩ አስፈራው እስኪደርስ ድረስ ራሶቻችሁን አትላጩ ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከፆም ወይም ከመስዋዕት ቤዛ አለበት ፀጥታም ባገናችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈፀሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈፀም የተገላገለ ሰው ከሀድይ የተጋራውን መሰዋት አለበት ፡፡ ያላገኘም ሰው ሶስቱን ቀናት በሐጅ ወራት ሰባትንም በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት ፡፡ ይህ ሙሉ አስር ቀናት ናት ፡፡ ይህም ህግ ቤተሰቦቹ ከቅዱስ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው፤ አላህንም ፍሩ )አላህም ቅጣቱ ብርቱ መሆኑን እወቁ›› (አል-በቀረህ 196 ث أَيَاض النَّا واست حغ مفروا اللَّه إم َّن اللَّه َغ ُف م ُُثَّ أَيم م يم ()322 ُ يضوا م حن َححي ُ َ ُ َ ح َ ُ َ َ ٌ ور َرح ٌ ‹‹ከዚያም ቁረይሾች ሆይ ! ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ ተንቀሳቀሱ አላህንም )ምህረት ለምኑ ፡፡ አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና›› (አል-በቀረህ 199 م م لمي حشه ُدوا منَايمع ََلم وي حذ ُكروا اسم اللَّ مه مِف أَيَّ ٍام معلُ ٍ يم مة حاْلَنح َع مام يَ ُكلُوا ممحن َها َح َ ومات َعلَى َما َرَزقَ ُه حم م حن ََب َ َ َ َ َ ُح َ َ ُ ح َ وأَطحعمموا الحبائمس الح َف مقري (ُُ )52ثَّ لحي حقضوا تَ َفثَهم ولحيويُوا نُ ُذورهم ولحيطََّّويُوا بمالحب ي م ت الح َعتمي مق ()52 َ ُ َح َُ ح َ َ ُح َُ َ َ ُ َ َ
ትክክለኛው ሕጅ
الحج المبرور
‹‹ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይምሉ ፡፡ በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ አልን ›› (ሐጅ 29) م م م ف َبمم َما َوَم حن َّ (إم َّن َ اح َعلَحي مه أَ حن يَطََّّو َ الص َفا َوالح َم حرَوَة م حن َش َعائ مر اللَّه يَ َم حن َح َّج الحبَ حي َ َت أَ مو حاعتَ َمَر يَ ََل ُجن م م م )322( يم َ تَطََّو ٌ ع َخحي ارا يَإ َّن اللَّهَ َشاكٌر َعل ‹የሶፋና የመርዋ ጋራዎች የአላህን ትዕዛዝ ከመፈፀሚ ጉልህ ቦታዎች ናቸው፡፡ ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ የጎበኘ ሰው ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ኃጢአት የለበትም ፡፡ መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ ሰው ሁሉ አላህ ይመነዳዋል ፡፡ አላህ አመሰጋኝ፤ አዋቂ ነውና› (አል-በቀረህ 158) አንድ ፀጉር ሁለት ፀጉር ማርገፍ ወይም አንዲት ጥፍር ሁለት ጥፍር የለበትም በያንዳንዳቸው አንድ ድሃ መስጠት ነው ያለባቸው በኢህራም ምክንያት የተከለከለውን ነገር ረስቶ ቢፈፅም ከማውደም ጋር የተያያዘ ከሆነ ለምሳሌ አውሬን ማደን ፁጉርን መላጨት የመሰለ ጥፋት ከሆነ አውቄ እንደፈፀመው ነው የሚቆጠረው ፡፡ ከማውደም ጋር ግንኙነት የሌለው ከሆነ የተሰፋን ልብስን መልበስ፤ ሽቶ መቀባት ፀጉርን መሸፈን ከሆነ ምንም የለበትም ፡፡ 2. የግብረስጋ ግንኙነትን መፈፀም ማካካሻን በተመለከተ ከመጀመሪያ መፈታት በፊት ከሆነ ግመል ማረድ አለበት ሐጁም ይበላሻል ፡፡ እንደዚሁም በማቀፍ ወይም ሰውነትን በማነካካት ወይም በመሳም አትኩሮ በመመልከት ያፈሰሰ ሰው እንዲሁ ግመል ማረድ አለበት ፡፡ ግመል ባይችል አስር ቀን ሶስቱን በሐጅ ሰባቱን ወደ ቤቱ ሲመለስ መፈፀም አለበት፡፡ 3. ከመጀመሪያው መፈታት በኋላ ግንኙነት ማድረግ ሐጅን በጭራሽ አያበላሽም፡ ፡ በግ/ፍየል ማረድ ግን አለበት ፡፡ ከዚያም በሐረሙ ክልክል በመውጣት አዲስ ኢህራም አድርጎ ጠዋፍ ማድረግ አለበት፡፡ የዑምራ ተግባርን በሶፋና በመርዋ መካከል ቢያፈርስ በግ/ፍየል/ ማረድ አለበት፡ ፡ ከማሳጠሩም በፊት ከተከሰተም..... መተዉን በተመለከተ ከሀጅ ማዕዘናት/ግዴታዎች አንዱን የተወ ሰው ሐጁ ይበላሽበታል፡፡ ከሐጅ ዋጂባቶች አንዱን የተወ ሰው ደግሞ በደም/ በእርድ/ይጠገናል:: ሱናን የተወ ደግሞ ምንም የለበትም ፡፡
.
51
1) በምርጫ የሚደረግ ነገር ሲሆን እሱም ፡- ፀጉሩን የተላጨ ፤ ሽቶ የተቀባ ጥፍሩን የተቆረጠ ፤ ለወንድ ራሱን የሸፈነ የተሰፋ ልብስ የለበሰ -ይህን የፈፀመ ሰው ከዚህ በታች ያሉትን ማካካሻዎች ይተግብር ፡፡ ሶስት ቀን መፆም ወይም ለአንድ ድሃ በአንድ ኪሎ ተኩል ሂሳብ ስድስት ድሆችን ማብላት፤ወይም አንዲት ፍየል ማረድ ነው ፡፡ በሐጅ ላይ እያለ አውሬ ያደነ ሰው የተገደለውን አውሬ ተመሳሳዩን ከቤት እንሰሳ ማረድ ያለበት ሲሆን፤ መሰል ከሌለው ደግሞ ዋጋውን ይከፍላል፡፡ 2) ተራውን ጠብቆ መተግበር ያለበት ማካካሻ ሲሆን፤ ይህም የሙተመቲዕና የቃሪን መካካሻ /በግ ፤ፍየል ነው ፡፡ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማካካሻው ግመል ሲሆን፤ ይህን ካላገኘ ሶስት ቀን በሐጅ ላይ እያለ፤ ሰባት ቀን ደግሞ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የሚፆመው ነው፡፡ ለእርድ የሚደርሰው እንሰሳም ሆነ ማብላቱ ለሐረም ድሆች ብቻ የተወሰነ ነው፡ ፡ ወደ መካ መግባት፡-ሐጅ የሚያደርግ ሰው መካ ሲገባ ፤ ወደ ሌሎች መስጊዶች ሲገባ የሚያነባቸውን ዚክሮች ያንብብ፡፡ ከዚያም ሙተመቲዕ ከሆነ የዑምራ ጦዋፍ ይጀምር ቃሪንና ሙፍሪድ ከሆነ ደግሞ ጦዋፈልቁዱም/ መካ የመድረስ/ ጠዋፍ ያድርግ፡፡ በዚህ ጦዋፍ ቀኝ እጁን ያውጣና ሐጀረተል-አስወድ ሰላምታ ያቅርብ ፡፡ ከቻለም ስሞ አለበለዚያም ወደ እሱ አመልክቶ ቢስሚላህ ወላሁ አክበር ብሎ ይጀምር ፡፡ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ ሁሉ ያድርግ ፡፡ ከዚያም ካዕባን በግራው አድርጎ ሰባት ጊዜ ይዙር ፡፡ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ዙሮች እያረተረተ 31 ይዞርና በቀሩት ደግሞ እንደ አቅሙ እየሄደ ይጨርሳል፡፡ ሩክነል-የማኒ በሚባለው ማዕዘን አጠገብ ባለፈ ቁጥር በእጁ በመንካት ሰላምታ ማድረግ ከቻለ ሰላም ይበለው ፡፡ ወደ እሱ በማመልከት ግን አይደረግም፡፡ በሁለቱ ማለትም በሩክነል-የማኒና በሐጀረል አስወድ መካከል (ረበና ኣቲና ፊዱንያ ሀሰነተን ወፊል-ኣኪረቲ ሀሰነተን ወቂና አዛብ-አልናር) ይበል ፡፡ በሌላው ቦታ ላይ የፈለገውን ዱዓ ያድርግ፡፡ 31 እርምጃን በማቀራረብ መፍጠን ማለት ነው፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ከዚያም ከተቻለው ከኢብራሂም መቆሚያ በኋላ ሱረቱል ካፊሩንንና ሱረቱል ኢኽላስን በማንበብ ሁለት ረከዓ ይስገድ ፡፡ ከዚያም ከዘምዘም ውሃ በብዛት ይጠጣ ፡፡ ከቻለ ተመልሶ ሀጀረል-አስወድን ይሰላመት ፡፡ ከዚያም በሀጀረል አስወድና በበሩ መካከል ባለው ሙልተዘም በሚባለው ቦታ ላይ የቻለውን ያህል ዱዓ ያድርግ ፡፡ ከዚያም ሶፋ ጋራ ላይ ወጥቶ አላህ በጀመረበት እጀምራለሁ ካለ በኋላ م م م ف َبمم َما َوَم حن َّ (إم َّن َ اح َعلَحي مه أَ حن يَطََّّو َ الص َفا َوالح َم حرَوَة م حن َش َعائ مر اللَّه يَ َم حن َح َّج الحبَ حي َ َت أَ مو حاعتَ َمَر يَ ََل ُجن م م م )322( يم َ تَطََّو ٌ ع َخحي ارا يَإ َّن اللَّهَ َشاكٌر َعل የሶፋና የመርዋ ጋራዎች የአላህን ትዕዛዝ ከመፈፀምባቸው ጉልህ ቦታዎች ናቸው ፡፡ ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ ሰው ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም ፤ መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ ሰው ሁሉ አላህ ይመነዳዋል ፡፡ አላህ አመሰጋኝ ፤ አዋቂ ነውና) አል በቀረህ 158. የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አንብቦ አላሁ አክበር ላኢላሀ ኢለሏህ በማለት ወደ ከዕባ ዙሮ እጆቹን አንስቶ ዱዓ ያድርግ ፡፡ ከዚያም ወደ ቅጠላማው አረንጓዴ ምልክት ይሂድና እስከመሰሉ ምልክት ድረስ በፍጥነት ይራመድ ፡፡ ከዚያም መርዋ እስከሚደርስ ድረስ በቀስታ ሂዶ በሶፋ ላይ እንዳደረገው በመርዋም ላይ ይስራ ፡፡ ከዚያም ወርዶ በመጀመሪያው ዙር ላይ እንደሰራው ይስራ ፡፡ ልክ እንደዚሁ እያደረገ ሰባት ዙሪያ ይሙላ ፡፡ ከሶፋ እስከመርዋ አንድ ዙር ሲሆን ከመርዋ እስከ ሶፋ ደግሞ ሌላ ዙር ነው ፡፡ ከዚያም ፀጉሩን ያሳጥር ወይም ይላጭ ፡፡ ሆኖም መላጨቱ ይመረጣል ፡፡ይህም በሙተመቲዕ ዑምራ ላይ ብቻ ሲቀር:: ምክኒያቱም ከኋላው ሐጅ ስለሚያደርግ ነው ፡፡ ቃሪንና ሐጅን ብቻ የሚያደርግ ሰው የዒድ ቀን ጀምረተል- ዐቀበህን እስከሚወረውር ድረስ ከኢህራሙ አይፈታም ፡፡
.
53
1- ከዚያም የራሱን ፀጉር ይላጭ ወይም ያሳጥር መላጨቱ ይመረጣል ፡፡ ጠጠር በመወርወሩ ከሴት በስተቀር ሁሉ ነገር ይፈቀድለታል ፡፡ ይህም የመጀመሪያው መፈታት ተብሎ ይታወቃል፡፡ 2- ከዜያም ወደ መካ ይጓዝና ኢፋዷ የሚባለውን ጦዋፍ ያድርግ ፡፡ ይህ ጦዋፍ ዋናውና ያለሱ ሐጁ አይበቃም የሚባለው ጦዋፍ ነው፡፡ 3- ከዚያም ተመቱዕ የሚደርግ ወይም ከጦፈልቁዱም ጋር ሰዕይ ያላደረገ ከሆነ በሶፋና በመርዋ መካከል የሚደረገዉን ሰዕይ ይሂድ፡፡ 4-ይህን ካደረገ ሁሉም ነገር ማለትም በኢህራም ምክኒያት ተከልክሎ የነበረው ሁሉ ሴትም ሳይቀር ይፈቀድለታል ፡፡ ይህም ሁለተኛው መፈታት ይበላል ፡፡ 5- ከዚያም ወደሚና ይመለስና ሌሊቶችን በዚያው ማሳለፍ ግዴታ ነው፡፡ በዙልሂጃ ከ11ኛው -13ኛው ባሉት ቀናት ሐጅ አድራጊ በነዚህ ቀናት ዋነኛው የሐጅ አድራጊ ሥራ የጠጠር መወርወር ስራ ብቻ ነው፡፡ የጠጠር ውርወራ ሥርዓት 3 ቦታ ላይ ሲሆን ይኸውም ትንሹ ፣ መሀከለኛውና ትልቁ (የመጨረሻው) በመባል ይታወቃል፡፡ በሶስቱም የጠጠር መውርወሬያ ላይ ሰባት ሰባት ጠጠሮች ይወወረወራሉ ፡፡ በጠጠር ውርወራው ወቅት የሚከተሉትን ስርዓቶች መከተልም ያስፈልጋል፡፡ ሀ. በያንዳንዱ ጠጠር ውርወራ ወቅት ተክቢራ ማድረግ ፣ ለ. ሰባቱንም ጠጠሮች አከታትሎ መወርወር፣ ሐ.የውርወራውን ስርዓት ቅደም ተከተል መፈፀም ሱና ነው ማለት በትንሹ መጀመርና በትልቁ ማጠናቀቅ፣ መ. ጠጠሮችን የሚወረውሩባት ገንዳና በውርወራው መሀከል የሶስት ክንድና ከዚያም በላይ ርቀት መኖሩ ሱንና ነው ፡፡ ምክንያቱም ከሶስት ክንድ ባነሰ ርቀት ላይ ቆሞ መወርወር/ መጣል እንጂ ውርወራ አይባልምና ፡፡ ስለሆነም የሚፈቀድ ቢሆንም ከሶስት ክንድ በላይ ርቀት ላይ ቆሞ መወርወር ይገባል፡፡ ሠ. በትንሹ /በመጀመሪያው/ እና በመሀከለኛው ውርወራ በኋላ በፈለጉት ዱዓ ማድረግ ፤ ዱዓውንም ረዘም ማድረግ የነብዩ ፈለግ ነው፡፡ ከሶስተኛው በኋላ ግን ዱዓ ማድረግ ሱና አይደለም፡፡ ረ. የጠጠር ውርወራው ስርዓት የሚጀምረው ከኢዱ ሌሊት አጋማሽ በኋላ ሲሆን የውርወራውን ስርዓት እስከ አያመ ተሸሪቅ የመጨረሻ ቀን ፀሐይ ከመጥለቁ በፊት ድረስ ማከናወን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ታላቁን የውርወራ ስርዓት ለመፈፀም ተመራጩ ጊዜ ከኢዱ ሌሊት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ቀን አጋማሽ ድረስ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ይሆናል፡፡ የአያመ ተሸሪቅ ውርወራን ደግሞ ተመራጩ ጊዜ ከቀኑ አጋማሽ እስከ ፀሐይ መጥለቂያ ድረስ ያለው ወቅት ነው፡፡ 3-34. የሴት ልጅና ጦዋፍ ሴት ልጅ በጦዋፍ ጊዜ ሶምሶማ፤ በሰዕይ ጊዜ አታረተርትም እንጂ በሌላው የሐጅና የዑምራ ተግባራት ሁሉ ልክ እንደ ወንድ ናት ፡፡ እንደዚሁም ሴት ልጅ ሽቶ የነካው ልብስ ፤ የፊት ሽፋንና የእጅ ጓንት ካልሆነ በስተቀር ሌላ የተሰፋን ልብስ መልበስ ትችላለች ፡፡ የእጅ ጓንትና የአይን እርገብ ወይም ኒቃብ መልበስ ግን አትችልም ፡፡ ሆኖም ከበዐድ ወንድ እራሷን ለመጠበቅ በጉፍታዋ ትጠቀማለች ፡፡ 3-36.የማካካሻ አይነቶች ማካካሻ ሁለት አይነት ነው ፡፡ 1. በምርጫ የሚደረግ ነገር ሲሆን እሱም ፡- ፀጉርን በማሳጠር ፤ ወይም ጥፍርን በመቁረጥ፤ ወይም ራስን መሸፈን ወይም ወንዶች የተሰፋን ልብስን በመልበስ ምክኒያት መከፈል ያለባቸው መካካሻዎች ናቸው ፡፡ ከእነዚህ አንዱን የፈፀመ ሰው ከዚህ በታች ካሉት ማካካሻዎች አንዱን ይተግበር ፡፡ 1-ሶስት ቀን መፆም፤ 2-ወይም ለአንድ ድሃ በአንድ ኪሎ ተኩል ስንዴ/ቴምር/ገብስ ሂሳብ ስድስት ደሆችን ማብላት 32፤ 3-ወይም አንዲት ፍየልን /በግን/ ማረድ ነው ፡፡ ቁርኣን ይህን አስመልክቶ م م م اْل َّج والحعمرةَ لملَّ مه يَإم حن أ م ي ُحص حرُحُت يَ َما ح ح َ ُاستَ حي َسَر م َن ا حَلَحد مي َوََل َحُتل ُقوا ُر ُ وس ُك حم َح َّىَّت يَحب لُ ََ ا حَلَحد َ ) َوأَِتُّوا حَ َ ُ ح مم م م م مم م م م ٍ صي ٍام أَو ص َدقَ ٍة أَو نُس ك يَمإذَا أ مَمنحتُ حم يَ َم حن ََلَّهُ يَ َم حن َكا َن محن ُك حم َم مر ا ُ يضا أ حَو به أَذاى م حن َرأحسه يَف حديَةٌ م حن َ ح َ ح 32
ሷዕ የሚለው ቃል ሶስት ኪሎ ነው በሚሉት ዐሊሞች ዘንድ ነው ፡፡ ኢብኑ ዑሰይሚን ሁለት ኪሎ ከአርባ ይሆናል ይላሉ ፡፡ ሆኖም የተሻለው የፊተኛው ነው ልዩነቱም ከእህሎቹ አይነቶች ና ልዩነት የተነሳ ይመስለኛል ፡፡ .
55
اْل ِّج يَما استَ يسر ممن ا حَل حد مي يَمن ََل َمَي حد يَ م ِتََت م اْلَ ِّج َو َسحب َع ٍة إم َذا َر َج حعتُ حم صيَ ُام ثَََلثَمة أَيَّ ٍام مِف ح َّع بالح ُع حمَرةم إم ََل حَ َ ح ح َ َ َ َ َ ح ح َ م م م م م م ك لمن ََل ي ُكن أَهلُه ح م يد اض مري الح َم حسجد ح ُ اْلََرمام َواتَّ ُقوا اللَّهَ َو حاعلَ ُموا أَ َّن اللَّهَ َشد َ تمحل َ ُ ك َع َشَرةٌ َكاملَةٌ َذل َ َ ح ح َ ح ح الحعم َق م ]322 :) [البقرة322( اب (‹ሐጂንና ዑምራን ለአላህ ሙሉ ፡፡ መብት ብትታጉዱም ከሀድይ ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ፡፡ሀድዩ አስፈራው እስኪደርስ ድረስ ራሶቻችሁን አትላጩ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከፆም ወይም ከመስዋዕት ቤዛ አለበት ፀጥታም ባገናችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈፀሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈፀም የተገላገለ ሰው ከሀድይ የተጋራውን መሰዋት አለበት ፡፡ ያላገኘም ሰው ሶስቱን ቀናት በሐጅ ወራት ሰባትንም በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት ፡፡ ይህ ሙሉ አስር ቀናት ናት ፡፡ ይህም ህግ ቤተሰቦቹ ከቅዱስ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው፤ አላህንም ፍሩ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መሆኑን እወቁ›› (አል-በቀረህ 196)) የአውሬዎቹን መግደል ጉዳይ በተመለከተ መሰል ካላቸው ተመሳሳዩን ማረድ ሲሆን፡ መሰል ከሌለው ደግሞ ዋጋውን አስገምቶ መክፈል ነው ፡፡ 2. ተራውን ጠብቆ መተግበር ያለበት ማካካሻ ሲሆን፤ ይህም የሙተመቲዕና የቃሪን መካካሻ /በግ ፤ ፍየል ነው ፡፡ ይህን ካላገኜ ሶስት ቀን በሐጅ ላይ ሳለ ሰባት ቀን ደግሞ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የሚፆመው ነው ፡፡ እርድም ሆነ ማብላቱ ለሐረም ድሆች ብቻ የተወሰነ ነው ፡፡ እነዚህን ከላይ የተወሱትን ስህተቶች የፈጸመ ሰው -እኒህን ስህተቶች የፈጸመው በመርሳት ወይም ባለማወቅ ከሆነ ከአላህ ምህረትን ከመጠየቅ በስተቀር ምንም የለበትም የሚሉ ዐሊሞች ማስረጃቸው ጠንካራ በመሆኑ እኔም ይህኑ አስፍሪያለሁ ፡፡ በኢህራም ላይ እያለ ግብር ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ብይን
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
በኢህራም ላይ እያለ ግብር ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ሐጁ የተበላሸበት በመሆኑ ሥርዓተ ሐጁን በሌላ ዓመት በአዲስ መክፈል ያለበት ቢሆንም ለስህተቱ እርድ ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ከመጀመሪያው መፈታት በፊት ከሆነ ሐጁ ይበላሻል ፡፡ ሆኖም ይህንም መሙላት ግዴታው ነው ፡፡ በሚቀጥለው አመትም ቀዷ ማውጣት አለበት ፡፡ ይህም የሚሆነው ለመካ ድሆች የሚከፋፈል አንድ ግመል ከማረድ ጋር ነው ፡፡ ከመጀመሪያው መፈታት በኋላ ከሆነ ግን ሐጁ አይበላሽም ፡፡ አንድ ግመል ማረድ ግን አለበት ፡፡ በዑምራ ስራ ላይ እያለ የግብረ ስጋ ግንኙነት ቢፈፅም ዑምራው ይበላሻል ፡፡ በተጨማሪም አንድ ፍየል ማረድ አለበት ፡፡ ዑምራውንም በሌላ ጊዜ ቀዷ ማውጣት አለበት ፡፡ ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ በሆነ ስህተት ሐጅ አይበላሽም ፡፡
.
57
ሐጅ ያመለጠው ሰው من فاته الحج በተለያየ ምክኒያት ሐጅ ያመለጠው ሐጃጅ ከዚህ በታች ያሉትን ይፈፅም 1-በዑምራ ይፈታ 2-እርድም ይረድ 3-ካልቻለም ልክ እንደ ሙተመቲዕወይምቃሪን የአስር ቀኑን ፆም ይፁም፡፡
የስጦታ አይነቶች أنواع الهدي የእርድ መስዋዕት (ነህር) ማቅረብ ስርዓት በተመለከተ ሐጅንና ዑምራን በአንድ የሚፈፅም (ቃሪን) እና በሁለቱ መሀከል ኢህራም የሚፈታ (ሙተመቲዕ) ለአላህ የዕርድ መስዋዕት ማድረግ አለባቸው፡፡ መስዋዕቶቹ ደግሞ ሶስት ዓይነት ናቸው ፡፡ እነርሱም፡ሀ. ሱንና የሆነ መስዋዕት፡ሐጅና ዑምራ የሚፈፅም ሐጅ አድራጊ በሙሉ የነብዩን ፈለግ በመከተል የዕርድ መስዋዕት ማቅረቡ ሱንና ነው ፡፡ ነብዩ ሙሐመድ በመሰናበቻው ሐጅ ወቅት መቶ ግመሎችን አርደዋል፡፡ መስዋዕቱን ያቀረበው ሐጅ አድራጊ ልክ እንደ ኡድሂያ ስጋ ከእርዱ ላይ ትንሽ ሥጋ ቢመገብ ይወደዳል፡፡ ለ. የስለት መስዋዕት ፡- ሐጅ አድራጊ ለአላህ ቤት የተሳለው መስዋዕት ካለ ማረዱ ግዴታ ነው፡፡ ሐጅ አድራጊ ድሀ ቢሆን እንኳ ይሄ ግዴታ አይነሳለትም ፡፡ በተጨማሪም ሐጅ አድራጊ ለስለት ብሎ ካረደው እርድ ሊመገብ እንደማይፈቀድና ሙሉ በሙሉ ለድሃ መስጠት አንዳለበትም የፊቅህ ጠቢባን አጠቃላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡ ፡ ሐ. የማካካሻ (ከፋራህ) መስዋዕት ነው፡፡ ይህ የመስዋዕት እርድ ደግሞ ሐጅ አድራጊው በተለያዩ ምክንያቶች ያልፈፀማቸውና በማካካሻ እርድ የሚጠገኑ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
የሐጅ ስራዎችን ለመጠገን የሚፈጸም የእርድ አይነት ነው እንደ ግዴታነትም ይታያል፡፡ 4-የነብዩ ሙሐመድ ﷺሐጅ አፈፃፀም እንዲህ ነበር حج النبي ዉድ ሁጃጆች አላህ በቁርኣን እንዲህ አለ قُل إم حن ُكحنتم ُمُتبُّو َن اللَّه يَاتَّبمع موِن ُُيبمب ُكم اللَّه وي غح مفر لَ ُكم ذُنُوب ُكم واللَّه َغ ُف م :) عمران03( يم ٌ ُ َ َ ُ ح ح ُ ُ ََ ح ح َ ح ٌ ور َرح ُح ح
31
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ፡- ህዝቦች ሆይ ! አላህን በትክክል የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ ፡፡ አላህ ይወዳችኋል ፡፡ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና) ብሏል) (ኣሊ ዒምራን31) ከሐጅ /ከዑምራ/ አፈፃፀም ሁሉ የሚበልጠው ነቢዩ ሙሐመድ ﷺባደረጉት መልኩ ማከናዎን ነው ፡፡ በዚህም የአላህንና የነቢዩን ዉዴታ ያገኛል ፡፡ ነብዩ ሙሐመድ ሐጅ ሳያደርጉ ዘጠኝ አመት መዲና ከቆዩ በኋላ በአስረኛው ዓመተ ሂጅሪያ ላይ ሐጅ የሚያደርጉ መሆናቸው ለሕዝቡ በይፋ ተነገረ ፡፡ የነብዩ ሙሐመድን ﷺፈለግ ተከትሎ ሐጃቸዉን አብረዋቸው ለመፈፀም በማሰብ ብዙ ሕዝብ በመዲና ተሰባሰበ ፡፡ ጉዞውም ተጀምሮ ዙል-ሑለይፋህ ከተባለው ሥፍራ ሲደርሱ የአቡበክር ባለቤት ወለደችና ምን ማድረግ እንዳለባት በመጠየቅ ወደ ነብዩ መልዕክተኛ ላከች ፡፡ ነብዩም ‹ ﷺገላሽን ታጠቢ ወገብሽን በመቀነት አስረሽ ሰፋ ያለ ጨርቅ በሁለት እግሮችሽ መሀል አሳልፈሽ ጫፎቹን ከፊትና ከኋላ ከመቀነቱ ጋር እሰሪና ኢሕራም አድርጊ› አሏት›› ፡፡ ነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ ውስጥ ሁለት ረከኣ ሰግደው ግመላቸው ላይ ከተቀመጡ በኋላ ከፊት፤ ከኋላ ፤ ከቀኝና ከግራቸው ብዙ ሺህ ሕዝብ እያጀባቸው ጉዟቸዉን ቀጠሉ ፡፡ ተከታዩቹ ነብዩ የሚያደርጉትን ሁሉ በርሳቸው እየተመሩ አደረጉ ፡፡ መካ ሲገቡም የካዕባን ማዕዘን (ሩክኑል የማኒ) በእጃቸው ነክተው ሳሙ፡፡ በካዕባ ዙሪያ ሶስቱን በፈጣን እርምጃ (በሶምሶማ) አራቱን .
59
በመደበኛ አካሂድ በአጠቃላይ ሰባት ዙር ዞሩ ፡፡ ከዚያም ወደ ኢብራሂም መቆሚያ (መቃሙ- ኢብራሂም) ሄደው ፡مم اعيل أَ حن طَ ِّهرا ب ي م م مم اَّت ُذوا ممن م َق مام إمب ر ماهيم مصلًّى وع مه حدنَا إم ََل إمب ر ماه م م ) و َّم. ني َ َ َ ُ َ َح َ ح َ ني َوالح َعاكف َ ِت للطَّائف َ َ َح َ َيم َوإ حْس َ َ َح م )352( الس ُجو ُّ الرَّك مع ُّ َو ‹‹ከኢብራሂምም መቆሚያ፤ መስገጃን አድርጉ ፤......) (አል በቀረህ 125) የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡና መቆሚያውን እፊት ለፊታቸው በራሳቸውና በካዕባ መሐከል አስቀርተው ሁለት ረከዓ ሶላት ሰገዱ ፡፡በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሐ በኋላ ‹አል- ካፊሩን› የተባለውን የቁርኣን ምዕራፍ፤ በሁለተኛ ምዕራፍ ደግሞ ‹ቁልሁወልሏሁ አሐድ›ን አነበቡ፡፡ ከዚያም ወደ ከዕባ ተመልሰው ማዕዘኑን በእጃቸው ነክተው ከሳሙ በኋላ ወደ ሶፋና መርዋ ኮረብታዎች በመሄድ ሰዕይ አደረጉ ፡፡ የተቀሩትን ስነ ሥርዓቶችም በዚያው መሰረት አከናወኑ ፡፡ በምድረ ዐረፋ ተገኝተውም ለሕዝቡ ከፍተኛ ዲስኩር አደረጉ ፡፡ በዚህ ዲስኩር የሙስሊሞች ደምና ንብረታቸው የተከበረ በማንም የማይደፈር መሆኑን ፤ በቅድመ እስላም በዘመነ ማሀይምነት የነበሩት የጃሂሊያ ተግበራት ነገሮች በሙሉ ውድቅ መሆናቸውን ፤ የደም መበቀሉም ሆነ አራጣው ከዚያ ቀን ጀምሮ የማይጠየቁ ውድቅ መሆናቸውን አበክረው ለሕዝቡ ገለፁ ፡፡ ሕዝብ የሴቶችን ጉዳይ በትኩረት እንዲመለከትና የአላህን ሕግ እንዲጠብቅ አጥብቀው አሳሰቡ ፡፡ ተከታዩቻቸው የአላህን መፅሐፍ- ቁርኣን- የነብያቸውን ፈለግ -ሱና አጥብቀው ከያዙና ተግባራዊ ካደረጉ ምንጊዜም የማይሳሳቱና የማይጠሙ መሆናቸውን ተንትነው ገለፁ ፡፡ በዚህ ዲስኩራቸው ተልዕኮዋቸውን በሚገባ አድርሰው ኃላፊነታቸውን ተውጥተው የአላህን መልዕክት በታማኝነትና በፍፁምነት ማድረሰቸውን ሕዝቡ በአንድ ቃል መሰከረ ፡፡
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
5-ሐጅና ቀደምት ሙስሊሞች الحج والسلف الصالح ብዙ ሰዎች ሐጅ አድርገን ምንም ለውጥ አላገኜንም ፡፡ አባቶች ከሐጅ በኋላና ከሀጅ በፊት ብዙ ልዩነት ይታይባቸው ነበር ፡፡ ምስጥሩ ምንድን ነው ? በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ሐጅና ቀደምት ሙስሊሞች ስለ ስለፎች ሐጅ መናገር ታሪኩ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ተግባሩ ከእና አካቴው የጠፋ ይመስላል ፡፡ ሐጅ በእነሱ ጊዜ ከፍተኛ ክብር ነበረው ፡፡ በህይወት ላይ ከፍተኛ ለውት በማምጣት ላይም ብዙ ሚና ነበረው ፡፡ ለዚህም ዋናው ምክኒያት የዉስጥ ልዩነታችን ይመስለኛል ፡፡ ለምሳሌ፡እነሱ ለሐጅ ብዙ ለፍተው ከፍተኛ ወጪ አውጥተው በዚያው ላይ ተቀባይነት ካልኖረውስ በሚል ስጋት ላይ ብዙ ሲጨነቁ ነበር ፡፡ በአሁኑ ዘመን ያለን ሰዎች ግን እንኳንስ በኋላ ይቅርና በተግባሩ ላይ እያለን የቱን ያህል እንጨነቃለን ሁሉንም አላህ ያውቃል፡፡ 5-1.የቀደምት ሙስሊሞችና ሐጅ ሐጅ በቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የነበረውና ተግባሩ ቀርቶ ወሬው እንኳንን ብዙ ትምህርት ይገኝበት የነበረ እና የደረቁ ልቦችን የሚያረጥብ ፤ የተሳሳቱ ዓዕምሮዎችን የሚስተካክል፤ ከተጓዦችም አልፎ በሸኚዎችና በተቀባዩች ላይ እንኳን ከፍተኛ የድባብ ጥላ ያጠል የነበረ ኢስላማዊ ተግባር ነበር ፡፡ ያም ሆኖ አንዳንዶቹ ለሐጅ ተጓዋዡ ብዙ ነው ትክክለኛ ሁጃጆች ግን ጥቂቶች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ታዲያ በኛ ግዜስ ትክክለኛ ሑጃጆቹ ስንት ፐርሰንት ይሆኑ ? ሓጅ በእምነትም ፤ በአምልኮትም በስነ ምግባርም ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል እና ብዙ ገንዘብ ጉልበትና የውስጥ ንያ ወይም ሐሳብ የሚጠይቅ ተግባር ነው ፡፡ ብዙ ሰዎች ሀጅ አደረግን ፤ ያውም በተደጋጋሚ፡፡ ነገር ግን ለውጥ አላገኘንም ሲሉ ይደመጣሉ ፡፡ እነዚህና መሰል ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚከተሉትን እውነታዎች ማየት ይበጃል ብየ አምናለሁ፡ ፡
.
61
5-2.የቀደምት ሙስሊሞችና የሐጅ ጉዞ ስነ ስርዓት
سفر الحج لدى السلف
ሰለፎች የጓደኛን ሀቅ በትክክል ያውቁ ነበር ፤ በአግባቡም ለመወጣት ይጥራሉ፤ የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር ያለ ገደብ ይቸራሉ ፡፡ ሁሉም ጓደኞቻቸውን ሲያገለግሉ በደስታና በፍቅር ነበር፤ ዘርም ሆነ ስልጣን አይከለክላቸውም ነበር ፡ ፡ ሙጃሂድ የተባለ አሊም (ከአብደላህ ኢብኑ ኡመር ጋር ለማገልገል ብዬ አብሬ ተጉዤ ሳይሳካልኝ ቀረ ፡፡ ምክንያቱም የሚንከባከቡኝ እሳቸው ነበሩና) ብሏል፡ ፡ ቡሃየም አል አጀሊ የሚባሉ ታላቅ አሊምም (ከአንድ ሃብታም ነጋዴ ጋር ሐጅ ለማድረግ ጉዞ ሲጀምር እንባው በደረቱ ላይ እስኪፈስ ድረስ አለቀሰና ሲጠየቅ ይህ ጉዞ ወደ አላህ ያለውን ጉዞ አስታወሰኝ እና ነው አለ፡፡ ነጋዴው ይህ ሰውዬ ሲያለቅስ ሊከርም ነው በማለት ጓደኝነቱ እየከበደው ጉዞዋቸውን ቀጠሉ፤ ሐጅ አድርገው ሲመለሱ ያ መጀመሪያ ያገናኘቸው ሰው ነጋዴውን ሲጠየቀው ወላሂ በዘመናችን ይህን ሰውዬ የሚመስል ሰው ያለ አይመስለኝም በማለት መለሰለት ፤ ምክንያቱም እሱ ድሃ ሆኖ እኔ ሀብታም ሁኜ ወጪያችንን በሙሉ እሱ ይሸፍን ነበር ፡፡ ደካማ ሽማግሌም ሆኖ እኔ ደግሞ እንደምታየኝ ወጣት ሆኜ ያገለግለኝ ነበር ፡፡ እኔ ሳልፆም እርሱ ግን እየፆመ ምግብ ይሰራልኝ ነበር ) አለው ሰውየውም በጣም ገርሞት ከርሱ ተለይቶ ቡሃይም ዘንድ ሄዶ ጓደኛህ እንዴት ነበር በማለት ሲጠይቀው ጥሩ ጓደኛ በብዛተ አላህን የሚዘክር ቁርኣን በብዛት የሚቀራ እንባው ፈጣንና የሰዎችን ስህተት የሚያልፍ ጎበዝ እና ጠንካራ ሰው ነበር ፡፡ እንዲህ አይነት ጓደኛ በማገናኘትህ አላህ ጀዛህን ይክፈልህ አለው) ይባላል፡፡ ብዙ ሰለፎች አብረዋቸው ለሚጉዋዙ ሰዎች የሚያሰቀምጡት አንድ ቅድመ ሁኔታ ነበር፡፡ እርሱም ጉዟችንን አጠናቀን እስከምንመለስ ድረስ እኔ ላገልግልህ የሚል ነበር ፤ አሚር ኢብኑ ቀይስ እና አምር ኢብኑ ዑትበት ኢብኑ ፈርቀድ የተባሉ ሁለት ታላላቅ አሊሞች እንዲህ አይነት ቅድመ ሁኔታ ከሚያስቀምጡ ሰለፎች መካከል ቀዳሚዎች ነበሩ፡፡ አብደላህ ኢብኑ ሙባረክ የሚባል አንድ ታላቅ አሊም የጉዞ ጓደኞቻቸውን እየፆሙ ምግብ ሰርተው ያበሉዋቸው እንደነበረ ይነገራል፤ ወደ ሐጅ መሄድ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ሲፈልጉም ጓደኞቻቸውን በመሰብሰብ ሐጅ መሄድ የሚፈልግ ሁሉ ስንቁን ወደ እኔ ያምጣ ይሉና በሳጥን ውስጥ አስቀምጠው ይዘጉበታል ከዚያም ደርሰው እስኪመለሱ ድረስ የመጓጓዣም ሆነ የምግብ ወጪን ሳይጠየቁ ሐጁን አድርገው ሲጨርሱ ለያንዳነዳቸው የሚፈልጉትን ስጦታ ከመካ ገዝተውላቸው ወደ አገራቸው ይመልሱዋቸዋል ፡፡ ከዚያም አገራቸው ሲደርሱ ድግስ ይደግሱና ሳጥናቸውን በማምጣት ፊት ለፊታቸው ከፍተው የያንዳንዳቸውን ስንቅ ምንም ሳይነካ ይመልሱላቸው እንደነበር ፡፡ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ 51-የቀደምት ሙስሊሞችና ኢህራም ይህን ይመስሉ ነበር ውድ ሑጃጆች ሰለፎች ኢህራምን የሚረዱት ከምድራዊ ስሜቶች ሁሉ ተላቆ ወደ ሓያሉና የአለማት ፈጣሪ ወደሆነው ጌታ በዓካለም ሆነ በመንፈስ መጓዝ አድርገው ነው ፡፡ ለዚህም ነበር ኢህራም በሚያደርጉበት ግዜ አካላቸው ይንዘፈዘፍ የነበረው ፤ አንዳንዶችማ ልባቸው በፍርሃት እየተናፀ መልካቸው ሁሉ ይቀየር ነበር፡፡ 1-አነስ ኢበኑ ማሊክ ኢህራም ካደረጉበት ግዜ ጀምረው እስከሚፈቱ ድረስ በዱንያ ጉዳይ ትንፍሽ አይሉም ነበር፡፡ 2-አሊይ ኢበኑ ሑሰይን (ኢህራም አድርገው ግመላቸው ላይ ሲወጡ መልካቸው ወደ ቢጫነት ተቀይሮ እየተንቀጠቀጡ ለበይክ ማለት አልችል ሲሉ ምን ሆኑ ተብለው ተጠየቁ ና ላ ለበይክ ወላ ሰዓደይክ እባላለሁ ብዬ ፈርቼ ነው አሉ፡፡ 3-ጃዕፈሩ ሳዲቅ ሐጅ ሲያደርጉ ለበይክ ማለት ሲያቅታቸውና ፊታቸው ሲቀየር የአላህ መልእክተኛ ልጅ ምን ሆኑ ? ተብለው ሲጠየቁ ለበይክ ማለት ፈልጌ ያልሆነ መልስ እንዳልሰማ ነዋ! አሉ፡፡ 4-አቡ ሃዚም የነብዩ ሰሃባዎች ኢህራም ሲያደርጉ ረውሃ ወደሚባለው ቦታ ሳይደርሱ ድምፃቸው ይዘጋባቸው ነበር፤ ምክንያቱም ከሐጅ ስራዎች መካከል ትልቁ ድምፅን ከፍ አርጎ “ለበይክ” ማለትና የስጦታዎችን እንስሳት ደም ማፍሰስ/በብዛት ማረድ ነውና ፡፡ 5-4.የቀደምት ሙስሊሞችና ኢባዳ በሐጅ ላይ እያሉ እንዲህ ነበር 1-ኢብኑ ረጀብ የተባለ ታላቅ አሊም በሐጅ ላይ ከሚሰሩ ታላላቅ ተግባሮች አንዱ ሰላትን በአግባቡ መስገድ ነው….. ብለዋል ፡፡ 2-አብደላሀ ኢብኑ ዑመር ነብዩ በጉዞ ላይ እያሉ ግመላቸው ላይ ሱና ሰላት ሲሰግዱ አይቻለሁ ብለዋል፤
.
63
3-ሙሃመድ ኢብኑ ዋሲዕ የተባለ ታላቅ አሊም በመካ መንገዶች ሌቱን ሙሉ በግመሉ ላይ ሁኖ እየጠቀሰ ይሰግድ ነበር ሰዎቹ እንዳያቋርጡት ግመል መሪውን ከሁዋላቸው ሁኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲያቀነቅን ያዙት ነበር፤ 4-መስሩቅ የተባሉ ታላቅ አሊም ሐጅ አድርገው በስጁድ ላይ ሁነው እንጂ ሳይተኙ እንደተመለሱ ይነገራል፤ 5-ሙጊራ ኢበኑ ሹዕበህ አሰንዓኒ ከየመን በእግራቸው ሐጅ ያደርጉ ነበር ፡፡ በየ ሌሊቱ የቁርኣንን አንድ ሶስተኛ የመቅራት ልምድ ነበራቸውና በጉዟቸውም ላይ ሌሊት ቆም ብለው ይህንኑ ውርዳቸውን ቀርተው ከጓደኞቻቸው ጋር ለመድረስ ጉዞ ይቀጥሉ ነበር ፤ አንድ አንድ ግዜም ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ሲሄዱ ውለው የማታ ማታ ይደርሱባቸው ነበር፡፡ 5-5.Ømƒጠቃሚ ምክሮች ለሑጃጆች نصائح نافعة
በሽተኞች የውርወራውን ስርዓት የሚፈጽምላቸው ሰው መወከል ይችላሉ ፡፡ ግን የተወከለው ሰው የውርወራውን ስርዓት ለወካዩ መፈፀም የሚችለው የራሱን ውርወር ከጨረሰ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም ሴት ሐጅ አድራጊ ግፍያውና መጨናነቁ በራሷ ላይ ጉዳትን ሁከትን እንደሚፈጥር ካልፈራች በስተቀር ሌላ ሰው ውርወራውን እንዲፈጽምላት መወከል አትችልም፡፡ ሴቶች በግፊያ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከፈሩ የጠጠር ውርወራውን በአያመ ተሸሪቅ ቀናት በየትኛውም ወቅት ከፀሐይ መጥለቂያ በኋላ እንኳን ቢሆን ራሳቸው እንዲፈጽሙት ማድረግ መልካም አማራጭ ነው ፡፡ ግን የአያመ ተሸሪቅ የመጨረሻው ቀን (ከኢዱ በአራተኛው ቀን ማት ነው) ፀሐይ ከመጥለቅ በፊት ውርወራውን ማጠናቀቅ አለባቸው ፡፡ እንዲህ አይነት ችግር ላይ ያሉ ሁሉ ውርወራውን በሙሉ አዘግይተው በአንድ ላይ ቢፈፅሙም ይበቃላቸዋል፡፡ ሐጅ አድራጊ ወንድ አማኝ በዚሁ እለት ፀጉሩን ያሳጥራል ፡፡ አልያም ይላጫል ፡ ፡ ሆኖም መላጨቱ በላጭነት አለው ፡፡ ሴት ሐጅ አድራጊዎች ግን ከፀጉራቸው ጫፉን ማሳጠሩ ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው ፤ ከዚያም በኋላ የመሰናበቻ ጠዋፍ ማድረግ ፤ በዚህ ወቅት الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ከኢህራም መፍታት በኋላ ለጠዋፍ መታጠብ ልብሶችን መልበስ ሽቶ ማድረግ የሚችል ከሆነ ነብዩ ያደረጉት ተግባር በመሆኑ በላጭነት አለው፡፡ اسماء مكة وفضلها
6-የመካ ስሞች እና ትሩፋቶች
6.1 ከመካ ስሞች መካከል 1ኛ-መካህ ፡- መካህ የሚለው ዋናዉ ስሙ ሲሆን ፡- የዚህን ያክል ባይጎላም ሌሎች ስሞች አሉት ፡፡ አላህ በቁርኣን እንዲህ አለ ‹‹አላህ ያ ! በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻላችሁ በኋላ እጆቻችሁንም ከእናንተ ላይ እጃችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው›› አል ፈትህ 24. በማለትና በሌሎች በተለያዩ ቦታዎችም ላይ አዉስቶታል፡፡ 2ኛው- በካህ ይህ ስሙ በቁርኣን እንዲህ አለ ፣ ‹‹... ›› ... ለሰዎች ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው› ኣሊ ዒምራን 95.97. 3ኛው-ኡሙልቁራ /የመንደሮች እናት/ አላህ እንዲህ አለ መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ልታስፈራ› አሽ -ሹራ 7) (ይህ ያወረድነው ብሩክና ያንንም በፊት የነበረውን መጽሐፍ አረጋጋጭ ነው ፡፡ የከተሞችንም እናት መካንና በዙሪያቸው ያሉትንም ሰዎች ልታስጠነቅቅበት አወረድነው) አል አንዓም 92 4ኛው- አልበለዱል አሚን /የሰላሙ ሀገር/ አላህ እንዲህ አለ) ‹‹…በዚህ በፀጥተኛው (ፀጥታ በነገሰበት) አገርም እምላለሁ…›› አትቲን1 5ኛው-አልበለድ /ሀገር/ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! በዚህ አገር በመካ እምላለሁ) 6ኛው-አል በይት/ቤት/(…ሰራ ፤ስለዚህ የዚህን ቤት የካዕባን ጌታ ያምልኩ) አንነምል 91. 7ኛው- አልመስጂዱል ሐራም/ የተከበረው መስጂድ/ ይህ ስሙ በአስራ አምስት ቦታ ላይ በቁርኣን ተጠቕሷል፡፡ ከነዚህም መካከል፡8ኛው ፡- መንደር /አልቀርየህ / (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ከዚያች አንተን ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በሀይል ጠንካራ የሆኑ ባለቤቶቻቸዉን ያጠፋናቸው ብዙ ናቸው) ሙሐመድ 13. .
65
9ኛው፡-አልበልደህ/ሀገሪቱ ‹‹ መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!የታዘዝኩት የዚህችን አገር የመካን ጌታ ያንን ክልክል ያደረጋትን አላህን እንድገዛ ብቻ ነው› አነምል 91. 10ኛው ፡- መመለሻው/ መዓድ/ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ያ ! ቁርኣንን የተከፋፈለ ሆኖ በአንተ ላይ ያወረደው አምላክ ወደ መመለሻ ወደ መካ በእርግጥ መላሽህ ነው ) አልቀሶስ 85. 11ኛው ፡-አልዋዲ (ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ) ኢብራሂም 37. 12ኛው ፡- አልበይቱል ዐቲቅ /ጥንታዊው ቤት ካዕባ/ ‹‹ከዚያም የማረጃ (የኡዱህያ) ስፍራ ጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው ›› አልሐጅ 33. 13ኛው፡-አል ሐረም ‹ሰዎቹ ከየዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ አገራቸውን ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን?››አል ዐንከቡት 67. 6.2.የመካ ክልሎች حدود الحرم المكي ኢማሙ ነወዊ የተባሉት ታላቅ ዐሊም ተህዚብ በተባለው መፀሐፍ ላይ ‹የመካን/ የሐረሙን ድንበሮች ማወቅ ብዙ ህግጋትን ስለሚመለከት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ እናም ማወቁ በጣም አስፈላጊ ነው› ብለዋል፡፡ ኢማሙ ኢብኑ ሐጀር ‹ኢሷባ› በተባለው መፀሐፍ 1/183 ትክክለኛ ሐዲስ በማለት በዘገቡት ሐዲስ ‹‹መላኩ ጂብሪል ወደ ነቢዩ ኢብራሂም መጥቶ የመካን ክልሎች በየ አቅጣጫው አሳወቃቸው›› ብለዋል፡፡ በነቢዩ ዘመንም አሰድ አልኹዛዒ የተባለን ሰው ልከው የመካ ክልል ከየት እስከየት እንደሆነ ተከልሏል ፡፡ ሁል ጊዜም እንደ ሁኔታው በየጊዜው ይህ ክለላ እየታደሰ ቆይቷል፡፡ አሁን በቅርብ ጊዜም ክቡር ሸኽ ሙሐመድ አሱበይል የታላቁ መስጂድ ዋና ኢማምና የሁለቱም መስጂዶች አስተዳዳሪ በነበሩበት ዘመን አንድ በሳቸው የተመራ ታላቅ ኮሚቴ ክልሉን በአዲስ ምልክት አድርጎበታል ፡፡ እኔ ከመጣሁኝ በኋላም ባቡል ሂንድ እየተባለ የሚታወቀው የጂዳው መግቢያ በአዲስ ‹‹ወአዚን ፊናሲ…›› ሲገባ ፤‹‹ወሊላሂ ዐለናሰ…›› የሚለው ደግሞ ሲወጣ የተፃፈበት ኬላ በትልቁ ተስርቷል ፡፡
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
6.3.የመካን ትልቅነትና ክብር በተመለከተ የተዘገቡ ሐዲሶች አላህ በጥበቡ በህዝቦች ፤ በወቅቶችና በቦታዎች መካከል አበላለጠ ፤ በዚሁም ልዩነት ላይ የተመሰረተ ልዩ ልዩ ህግጋትን አስቀምጧል ፡፡ ከዚህ እድል ከፍተኛዉን ከታደሉት ቦታዎች መካከል መካ ዋናው ነው ፡፡ በመካ ሀገር ያ ! የመጀመሪያው ለዒባዳ የተሰራው ቤት ከዕባ፤ የመጀመሪያው የተውሂድ እኒስቲትዩት የሙስሊሞች ሁሉ በህይወታቸዉም ሆነ ሞተው ቂብላቸው የሆነው ቤት፤ የወህይ ምንጭ ፤ የነቢይነት መነሻ ፤ የኢስላም መፍለቂያ ማዕከል የሆነው ታላቅ ቤትከዕባ አለ ፡፡ ለአላህ ምስጋና ይገባዉና ከሙስሊሞች ዉስጥ የዚህን ቤት ክብር የማያውቅ አንድም የለም ፡፡ ቁርኣንና ሐዲስም ይህን ጉዳይ በሰፊው ዘርዝረዋል፡፡ በሳዑዲ በድርጅት መልክ ስለዚህ ታላቅ ቤት ክብር ልዩ እንክብካቤ መደረግ ሲጀመር ከተወሱ ትክክለኛ የነቢዩ ሐዲሶች መካከል አርባ ሐዲሶችን በመምረጥ በመፀሐፍ መልክ አንድ ዓሊም ዶ/ር ጦላል ሙሐመድ አቡኑር ሰብስበዋል፡፡ ከዚያም 1-ጠቅለል ያለ የሐዲሱን መግቢያ፤ 2-ጠቅለል ያለ የሐዲሱን መልዕክት፤ 3-የሐዲሱን አስተምህሮት፤ 4-ከሰለፎች መካከል ሐዲሱን ከተገበሩት ሰዎች መካከል አንድን ወይም ሁለትን ታሪኮች እንደናሙና የሚጠቅስ እና ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ ፋይዳዎችን ያጠቃለለ አጠር ያለ ማብራሪያ ተጨምሮበታል፡፡ የበለጠ ያሳመረው ማብራሪያ የተሰጠው በደራሲው መሆኑ ነው፡፡ የሀገራችን የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችም ቢሆኑ ለመካ ያለቸው ክብርና ዉዴታ ወደር የለዉም ፡፡ ምክኒያቱም ኢስላም ከሀገራችን ጋር ያለው ግንኙነት ከዐለም ህዝቦች ሁሉ ከመካ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የገባ በመሆኑ ነው ፡፡ ስለዚህ የዚህ ታላቅ ቤት ጉዳይ በእኛ በሐበሻ ሙስሊሞች ዘንድም ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም፡፡ በድል ፤እንግልት፤መከራና ስቃይ፤የትናንቱ የጃሂሊያ ሥርዓት እርም ተደርጎባት በአንፃሩ ክብር፤ፍቅርና ሰላምጌጥናብርሃን በመሆን ለዓለም ተምሳሌት ሁና የአላህ ትዕዛዝና የረሱልመልዕክት ደማቅ ታሪክና ገድል እየተዘከረባት እየተወደሰችበፅናት የሚቆይባት ቦታ ናት ፡፡ የአላህን ትዕዛዝና የረሱልን ሱና መተግበር ከእስላማ ጥቅም እስከ መጨረሻው የሰው ልጅ ናፍቆት የሆነው .
67
‹‹ጀነትን›› የመውረስ እድልን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በተውሂድና በሱና ከአዱንያ የባርነት ቀንበር ነፃ ያደርጋል፡፡ እነሆ አርባ ሐዲሶችን ያካተተና በዶ/ር ጦላል ተፅፎ በአላህ ፍቃድ ለመተርጎም የበቃው መፅሐፍ የመካን ክብርና አያሌ አስደናቂና አስገራሚ እንዲሁም ገሳጭና አስጠንቃቂ መልዕክቶችን አዝሏል ፡፡ ታዲያ ዐረበኛዉን አንብባችሁ ለመረዳት ለማትችሉ ሙስሊሞች ሁሉ ሥራዎች ሁሉ በእጥፍ በሚመዘገቡበት ቦታ ላይ እንዲሁም የሰራነው ብቻ ሳይሆን ያሰብነው ሁሉ በሚፃፍበት በመካ ላይ ሁነን ቢያንስ መልካም ነገር መስራት ቢዳዳን ከተንኮል ራሳችንን ማቀብ የግድ ይላናል፡ ፡ ቀደምት አባቶቻችን ይህን እድል ለማግኘት ከፍተኛ ልፋትና ጥረት አድርገው ስለነበር በጣም ነው፡፡ አሁን አሁን ግን አንዳንድ የዚህን መስጂድና ሀገር ክብር ጠንቅቀው የማያውቁ ትውልዶች መጥተዋል፡፡ የመካን ክብርየዚያራዉን ሥነ ሥርዐት በደንብ ሳይረዱ ለሐጅም ሆነ ለዑምራ ፆሎት የሚመጡ ሰዎች ይህን መፅሐፍ አስቀድመው ማንበብ ወይም ካሴቱን /ሲዲዉን ማዳመጥ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ፡፡ የማይናቅ እውቀትም ይገበያል ፡፡ የዉስጥ እርካታም ያገኛል ፡፡ ከመካ ክብር ይልቅ የግላቸዉን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ አሉ ፡፡ ምድባችን ከእነዚህ መሰሎች እንዳይሆን አደራ እላለሁ፡፡ እናም በዚህ አጋጣሚ እኔም ወደ እዚህ ሀገር ለመምጣትና ለመኖር የቻልኩት በ1433 ሂጅሪያ ላይ በሀገራችን በተከሰተውና በተለይም በእኔና በመሰሎች ላይ በተደረገው ልዩ ጭቆና ምክኒያት ሲሆን ይህንን ችግር እያደረሱብን ያሉ ሙስሊም ተብየዎች ለመካ ያለቸው ንቀሽ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የእምነቱ ተከታይ ያልሆኑን ሰዎች እንኳን ወደ ዚሁ ሀገር ከማምጣቸዉም አልፎ እራሳቸውም በመካ ኢማሞች ተከትለን እንሰግድም እስከማለት ደርሰዋል ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መነሳት ካለበት የእነዚህ አይነቶች ሊፍሩ ሲገባቸው ይህን ፀያፍ ተግባራቸዉን በይፋ እስከሚያወጡት ድረስ ሙስሊሙ ዝም ብል ማየቱ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ 1ኛበመካ የሚገኘው ከዕባ በምድር ከተሰሩት መስጊዶች/የአምልኮ ቦታዎች/ሁሉ የመጀመሪያው መሰጊድ ነው ፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም ሃጀር የተባሉትን ሚስታቸዉንና ኢስማዒል የተባለዉን ልጃቸዉን በዚያ ምንም አዝርእት በሌለበት ዋሻ አስቀምጠው በሄዱበት እና ወደ እነሱ ሲመላለሱ በነበሩበት ጊዜ ፤ በአንደኛው ጉብኚታቸው ለልጃቸው ለኢስማዒል ‹ልጄ ሆይ!አላህ በዚህ ቦታ የዒባዳ ቤት እንድሰራ አዞኛል እና እርዳኝ አሉት › ከዚያም ኢስማዒል ድንጋይ እያቀበሉ ፤ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ኢብራሂም ገነቡ ፡፡ ግንባታው በሰላም አለቀ ፡፡ በዚህም ምክኒያት የመጀመሪያው ቤት የሆነው አልመስጂዱል ሐራም ተመሰረተ ፡፡ 33 ይህን እውነታ በተመለከተ አቡ ዘር የተባሉ ሱሃቢ ከነቢዩ ጋር የሚከተለዉን ያማረ ዉይይት አድርገዋል ፡፡ እስቲ አብረን እንከታተለው፡፡ አቡ ዘር፡-‹የአላህ መልዕከተኛ ሆይ ! በምድር ላይ በመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው መስጊድ የትኛው መስጊድ ነው›› ነቢዩ ‹‹የመካው መስጂድ ነው››፡፡ አቡ ዘር ‹ከዚያስ ›› የአቅሷ መስጂድ ነው›› አቡ ዘር ‹‹ በመሀከላቸው ስንት አመት ነበር›› ነቢዩ ‹አርባ አመት ፡፡ ከዚያም የትም ቦታ ላይ ሶላት ከደረሰብህ ስገድ ፡፡ ምክኒያቱም ቱሩፋት ያለው እዚህ ላይ ነዉና›› ብለዋል፡፡34 በብዙ ነገሮች ላይ መጀመሪያ መሆን ራሱን የቻለ ክብር አለው ፡፡ ለዚህም ነበር በምድር ላይ ለዒባዳ የተሰራ መስጂድ በሚል ጥያቄ የተነሳው ፡፡ ነቢዩም የመጀመሪያው አልመስጂደል ሐራም መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ቀጥሎ በመሰራት እንጂ በክብር ሳይሆን የበይተል መቅዲስ መስጂድ ነው አሉ ፡፡ ምክኒያቱም በመሰራት እንጂ ከመካ መስጂድ ቀጥሉ በክብርማ የመዲና መሰጂድ ነዉና ነው ፡ ፡ ከመልሱ በመቀጠል የሶላትን ጉዳይ ማንሳታቸው መስጂዶች የተሰሩበት ዋና ምክኒያት ለሶላት መሆኑን ነው ፡፡ ነቢዩ ‹‹ከዚያም የትም ቦታ ላይ ሶላት ከደረሰብህ ስገድ ፡፡ ምክኒያቱም ቱሩፋት ያለው እዚህ ላይ ነዉና›› በማለት ሁሉም ሊያውቀው የሚገባን ነገር አስታውሰዋል፡፡ ይኸዉም የጊዜ ዐባዳ የሚሉትን ነገር ነው ፡፡ ማለትም ከእነዚህ ሶስት መሰጊዶች በስተቀር በቦታ ሳይሆን በጊዜ በመስገድ ብቻ መሆኑን ነው ፡፡ 35 1-የመጀመሪያው መስጊድ የመካ መስጊድ መሆኑንና ከዚያም የበይተል መቅዲስ መሆኑን፤ 2-በማስረጃ ከተከለከሉት ቦታዎች በስተቀር በየትኛዉም መሬት ሶላት መፈቀዱን፤ 33
የታሪኩን መነሻ በአጭሩ ቡኻሪ ዘግቦታል፡፡ የሐዲሱ ደረጃው፡- ቡኻሪ በ 3366 እና ሙስሊምም 520 ዘግበዉታል፡፡ 35 ኢብኑ ልቀይም አል ፈዋኢድ በተባለው መፀሐፋቸው 193 ገፅ.ላይ አዉስተዉታል፡፡ 34
.
69
3-የነቢዩ ኡማህ ክብር ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ፤ 4-ሶላትን በጊዜው ጠብቆ መስገድ በአላህ ዘንድ ምን ያህል ክብርናከፍተኛ ምንዳ እንዳለው ነው ፡፡36 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ይህ ቤት ከተፈጠረ ጀምሮ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ይንከባከቡታል ፡፡ ያከብሩታል ፡፡ የተበላሸዉን ያድሳሉ ፡፡ ሁሉንም ህንፃ በአዲስ የሚሰሩ ሌሎች ደግሞ ማስፋፋት የሰሩ ነበሩ ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዑመር ብንልኸጣብ ፤ ዑስማን ብን ዐፋን፤ ይገኙበታል ፡፡ ልክ በዚህ መልኩ ሰዎች ለዚህ ቤት የነበራቸው እንክብካቤና ክብር አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ ቀጥሏል ፡፡ 37 አሁን ባለው በሳዑዲ ቤተሰቦች መንግስት ታሪክ ዉስጥም ሶስት ጊዜ በከፍተኛ እድሳት ታድሷል ፡፡ 38 አንደኛው በንጉስ ሱዑድ ብን ዐብዱል ዐዚዝ ጊዜ. ሁለተኛው በንጉስ ፈህድ ብን ዐብዱል ዐዚዝ ዘመን.. ሶስተኛው በንጉስ ዐብደላህ ብን ዐብዱል ዐዚዝ ዘመን ናቸው፡፡ 2ኛው መካ የሁሉም ነቢያት የሐጅ ቦታ ነው ነቢዩ ኢብራሂም መስጊዱን ገንብተው በጨረሱበት ወቅት ‹‹ሰዎች ሆይ! ኑ! ይህንቤት ጎብኙ ›› የሚል ጥሪ አስተላለፉ ፡፡ በዚህሰዐትም ብዙ ህዝብ ጥሪዉን ተቀበለ ፡፡ ከነዚህ መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሱት ነቢያት ነበሩ ፡፡ እናም ነቢዩ ኢብራሂም ራሳቸው ፤ ነቢዩ ኢስማዒል ፤ ነቢዩ ሙሳ ነቢዩ ዩኑስ እና ሌሎችም ነቢያት ወደ ዚሁ ቤት ሐጅ አድርገዋል ፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ሁሉ የጉብኚቱ ሂደት በትክክል የተመዘገበው የታላቁ ነቢይ የነቢዩ ሙሐመድ የመሰናበቻ ሐጅ እየተባለ የሚታወቀው ሐጅ ብቻ ነው ፡፡ ይህም ሐጅ ማንም ሙስሊም ሐጁን በሱ አስመስሎ ሊተገብር የሚጓጓው ሐጅ ነው፡፡ ኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ዋዲ ል አዝረቅ በተባለ ቦታ ሲያልፉ ከሙስሊሞች ጋር የሚከተለዉን ዉይይት አደረጉ፡፡ ነቢዩ ‹‹ ይህ ወንዝ ምን ይባላል›› ሙስሊሞች ‹‹ዋዲል አዝረቅ ይባላል፡፡
36
ፈትሁል ባሪ 6/408-409 ሸርሁ አና አንነወዊ 5/2፡፡ አኽባሩ መካ አዝረቂ ፤2/65-69እና አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ2/1፡፡ 38 ኢናረቱ ል መስጂዲልሐራም ወልመስጂዲ ነበዊ ኢብኑ ዱሀይሽ ከ87 ገፅ…..፡፡ 37
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ነቢዩ ‹ልክ ሙሳ ከአቀበቱ ወደ አላህ ለበይክ በማለት እያለቀሰ በቁልቁለቱ ሲወርድ የማየው ይመስለኛል› ኢብኑ ዐባስ ‹‹ከዚያም ሐርሻ የተባለ ቦታ ደረስን ከዚያም›› ነቢዩ ሙሐመድ ‹‹ይህ ቁልቁለት ማን ይባላል›› ሙስሊሞች ‹‹ሐርሻ የተባለ ቁልቁለት ነው› ፡፡ ነቢዩ ‹‹ልክ ዩኑስ ኢብኑ መታን የሱፍ ካቦርት ለብሶ በደለበች ቀይ ግመል ላይ ሁኖ ለበይክ እያሉ በቁልቁለቱ ሲወረድ የማየው ይመስለኛል ፡ ፡ ብለዋል ፡፡ 39 ይህ ታሪክ ከነቢዩ ገድሎች መካከል አንዱ ነው ፡፡ መካን ማክበር ፤ አላህን አንድ ማድርግ ዲንን ፍፁም ማድረግ ፤ ነቢያትን ማክበር ፤ እና መውደድ በአላህ ዘንድ ያላቸዉን ደረጃ ማውሳት ና የነቢዩ ኢብራሂምን ጥሪ ማክበራቸዉን ያስታዉሰናል ፡፡ ሰዎችን ክስተቶች የተፈፀሙበትን ቦታ ላይ በመሆን ማስተማር ተገቢ መሆኑን የመለክታል፡፡ 1-የሐጅ ስራ የቀድሞ ነቢያትም ተግባር እንደሆነ፤ 40 2-የሐጅን አስፈላጊነት በመጥቀስ ሰዉን ወደ ሐጅ ማግባባት ፤ በእሱም ዉስጥ ነቢያትን በመከተል ራስን ዝቅዝቅ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ፤ 41 3-ለበይክ በሚለዉ ቃል ድምፁን ከፍ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ፤ 42 4-ጉዳዮች የተከሰቱበትን ቦታ በመጠቀም ማስተማር ተገቢ መሆኑን፤ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ስለ ነቢያት ሐጅ ሲወራ መጠቀስ ካለባቸው ጉዳዮች መካከል 1-ወደ ዐለም ፍፃሜ መዳረሻ አካባቢ ነቢዩ ዒሳ የሚያደርጉት ሐጅ ነው ፡፡ አቡ ሁረይራ ነቢዩ ‹‹ሕይወቴ በእጁ በሆነ ጌታ በአላህ ይሁንብኝ ኢብኑ መርየም ለሐጅ ወይም ለዑምራ ወይም--ከፈጀረውሓእ ኢህራም ያደርጋል››43
39
ሙስሊም 241. ሚርቃት አል መፋቲህ10/394. 41 ሚርቃት አል መፋቲህ 10/394. 42 ሱነኑል ኩብራ5/41-42፡፡ 43 ሙስሊም 1252. 40
.
71
ኢማሙ ነወውይ እንደሚሉት ‹‹ይህ ሊሆን የሚችለው ነቢዩ ዒሳ ካረጉበት ከወረዱ በኋላ ነው›› ብለዋል ፡፡44 2-ያ ! ታሪካዊውዉና አያሌ ተዐምር የታየበት የነቢዩ ሙሐመድ የመሰናበቻው ሐጅ…….45 አላህ በዐረፋ ቀን ኒዕማዉን ሞላላቸው ፡፡ አላህ እንዲህ አለ ‹ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ ፡፡ ፀጋየንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ ›› አልማኢዳህ 3. ነቢዩ በአስረኛውቀን ኹጥባቸው ላይ ዐሊሞች እንደሚሉት ነቢዩ በዚህ ኹጥባቸው ላይ ዋናው ትኩረታቸው የአስረኛዉን ቀን ክብርና የዙልሒጃ ወርን ትልቅነትን ማሳወቅ ነው ይላሉ ፡፡ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ዘንድ አንድ አይሁድ መጥቶ በእናንተ መፅሐፈ ዉስጥ አንድ አንቀፅ አለ በእኛ በአይሁዶች ላይ ወረዶ ቢሆን ኖሮ ያን የወረደበትን ቀን በዕል አድርገን እንይዘው ነበር አላቸው ፡፡ ዑመር የትኛው ነው አሉት ‹……………………….› የሚለው ነዋ አላቸው ፡፡ ቀኑንም እናውቃዋለን ቦታዉንም በትክከል የት እንደወረደ እናውዋለን ቀኑ ጁሙዓ ቀን ሲሆን ነቢዩ በዐረፋ ላይ ቁመው ባሉበት ነው የወረደው አሉት ፡፡ 46 3ኛው ወደ ተከበሩ ቦታዎች የሚደረጉ ጉዞዎች
ተፈላጊ ነገሮችን ለማግኘት ወደ ዉድ ቦታዎች ለመድረስ የሚከፈሉ ምስዋዕትነቶች ከፍተኛ ቢሆኑም ምንም አይመስሉም ፡፡ ሙጊራ ብን ሐኪም የተባሉ ሰው ወደ መካ ሀምሳ ጊዜ ፆመኛ ሁነው ኢህራም አድርገው በባዶ እግራቸው ተጉዞው እንደነበርና ከዚያም ጋር የሌሊት ሶላት አንድ ቀንም አልፏቸው አያውቅም ነበር የሚል ዘገባ በታሪካቸው ዉስጥ እናገኛለን 47 ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺአቡ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ‹ወደ ሶስቱ መስጂዶች እንጂ ወደ ሌላ ቦታ ለዒባዳ ተብሎ ጉዞ አይደረግም ፡፡ ይህ የመዲናው መስጂድ
44
የሙስሊም 8/234 ሙስሊም1218. 46 ቡኻሪ 45. 47 አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ 2/323 45
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
፤ የመካው መስጂድ ‹‹አልመስጂደል ሐራም ፤ እና የአል አቅሷ መስጂድ ናቸው 48 › ብለዋል፡፡ ወደ ተከበሩ ቦታዎች መጓዝ በአላህ ፍቃድ ከፊትና ይጠብቃል፡፡ ከአኺራ ቅጣትም ያድናል ፡፡ የተሳሳተ አመላካከትም እንዳያሳስት ይከለክላል፡፡ በዱንያም ሆነ በአኺራ ክፍያን እጥፍ ድርብ በማድረግ ፤ ሪዝቅን (ሲሳይን) በማብዛት ፤ ጥቅሞችን በማበርከትደስታን ይፈጥራል ፡፡ ከዚህም በመነሳት ወደ ተከበሩ ቦታዎች መሄድ ከነቢዩ ኢብራሂም ዘመን አንስቶ ለአላህ ፈሪዎች ሁሉ መመላለሻ ፤ ለዓቢዶችም መደበቂያ ስፍራ ሆነ ፡፡ መህሙዱ አዘመኽሸሪ የተባሉት ዐሊም ‹‹እናንተ በአላህ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት ፡፡ ብትቸገሩ ተሰደዱ ፡፡ እኔንም ብቻ ተገዙኝ›› -አል ዐንከቡት 56 የሚለዉን አንቀፅ ሲያብራሩ ማንኛዉም አማኝ ባለበት ቦታ ሁኖ የአምልኮ ተግባር ሲከብደው ዲኑን እንደሚመኘው መተግበር ሲያቅተው ከዚያ በተሻለ ጌታዉን ሊገዛ በሚችልበት ሀገር መሄድ ይኖርበታል ፡፡ በጌታየ ይሁንብኝ ስፍራዎች ብዙ ይለዋወጣሉ ፡፡ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት ሰዎች ሞክረን ራስን በማሸነፍ ስሜትን ለመቆጣጠር አዕምሮን ለመሰብሰብ ባገኘው ለመብቃቃት ሰይጣንን ከላይ ላይ ለማስወገድ ና በአጠቃላይ የተለያዩ ፈተናዎችን ለመቋቋም ሐረም ከመኖር ና የአላህን ቤት ከመጎራበት የተሸለ አላገኘንም›› ብሏል፡፡ 49 1-የእነዚህን የሶስቱ መስጂዶችን ክብርና ማዕረግ በግልፅ መረዳት፤ 50 2- ወደ እነዚህ ሶስት መስጂዶች ጉዞ ማድረግ ያለዉን ታላቅ ምንዳ መረዳት፤51 3- በእነዚህ ሶስት ሀገሮች የሚኖሩ ህዝቦች ምን ያህል ትልቅ እድል እንደተሰጡ፤ 4- ከእነዚህ መስጂዶች ሌላ የትኛዉም መስጊድ ለዒባዳ ጉዞ ማድረግ መከልከሉን ፤52 5-ለንግድ ፤ ለትምህርት እና ለመሳሰሉት ነገሮች ወደ የትም አካባቢ ቢኬድ ክልከል እንዳልሆነ ፤ 53 6-በመዲና መስጊድ ለመስገድ የተሳለ ስው በመካ ቢሰግድ እንደሚተካለት ፤ 48
ቡኻሪ189 እና ሙስሊም2475 . አልካሻፍ 3/465 50 የሙስሊም ሸርህ አነወዊ 9/168 ዛዱል መዓድ1/48. 51 የሙስሊም ሸርህ አነወዊ 9/168.52 ፈትሁል ባሪ3/65 53 ፈትሁል ባሪ3/65 . 49
.
73
7-ከእነዚህ መስጊዶች ሌላ ለየትኛዉም መስጊድ የተሳለ ሰው ወደ ተሳለበት መስጊድ መሄድ እንደማይገደድ ፤54 8- እነዚህ ሶስት መስጊዶች የተለዩበት ዋናው ምክኒያት የነቢያት መስጊድ ስለ ሆኑ እንደሆነና እነሱንም በአርአያነት መከተል አላህ‹…..ስለሆነም ፈለጋቸውን ተከተል›› አንዓም 90 ላይ እንዳዘዘን ፤55 ወደ እነዚህ መስጊዶች ጉዞ በማድረግ ከታወቁ ሰዎች መካከል 1-አቡ ሙሐመድ አጦበሪ በመባል የሚታወቁት የሻፊዒይ መዝሐብ ተከታይ የነበሩ በመካ ከዚያም በመዲና መስጊድ ኢማም ሁነው ያሰገዱት ታላቅ ሸኽ በስተርጅና እድሜያቸው በይተል መቅዲስ ኢማም ሁነው እንዳሰገዱ የተዘገበው ነው ፡፡ ዘሀቢ የተባሉ ዐሊም ስለ እኒህ ሰው ሲናገሩ በእኒህ በታላላቅ ሶስት መስጊዶች ማሰገድ የቻሉ ታላቅ ሰው ናቸው ብለዋቸዋል ፡፡ 56 2-ዐብዱሶመድ የተባለው የደማስቆው ተወላጅ የዚያ እውቅ የደማስቆ ታሪክ የሚለው መፅሐፍ ፀሐፊ የኢብነ ዓሳኪር የልጅልጅ ወደ መካ ሂዶ አርባ አመት ከቆየ በኋላ ወደ መዲና በመሄድ በ686 አመት ላይ ሞተ፡፡ 57 3-የምስራቁ ሀገር ሙፍቲ የተባለው የሐዲስ ባለሞያ ዐላኡዲን ነህረዋሊ የተባሉት የሐነፊ መዝሀብ ተከታይ የነበሩ ሁርሙዝ በተባለው ሀገራቸው የራፊዷዎች መስፋፋትን ተከትሎ በተፈጠረው ችግር ምክኒያት ወደ መካ በመምጣት ባቡል ዑምራ በተባለው ልዩ ቦታ በመኖር በሐረሙ መስጊድ እያስተማሩ ኖሩ 58 ፡፡ 59 4ኛ አንድ ሶላት በመቶ ሺህ ሶላት የሚቆጠርበት ቦታ አንዲትሴት ታማ ከዳንኩኝ አቅሷ መስጂድ ሂጄ ሶላት እሰግዳለሁ ብላ ተሳለችና ከበሽታዋ ስትድን ወደዚያው ለመሄድ ተዘጋጅታ ወደ እናታችን መይሙና ቤት መጥታ ሰላም ብላ ሁኔታዉን ነገረቻት ፡፡ እናታችን መይሙናም ‹‹እዚሁ መስጂድ ተቀመጪ እዚሁ በነቢዩ መስጂድ የተሳልሺዉን ሶላት ስገጂ በማለት አስቀረቻት
54
ኢክማሉል ሙዐሊም 4/267. ገሪቡል ሐዲስ አልኸጣቢ1/133. 56 ታሪኹል ኢስላም 52/122. 57 ለሐዙ ል አልሓዝ ኢብኑ ፈህድ 81-82. 58 ቡሉጉልቂራ 3/1956. 59 እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ይህ ሁኔታ አሁን በሀገራችን ከተፈጠረው ጋር ይመሳሰላል፡፡ 55
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
60
›› ይህም የሆነው በነቢዩ መስጂድ የሚሰገደው ሶላት በበይተል መቅዲስ ከሚሰገደው ስለሚ በልጥ ፤ በመስጂደልሐራም የሚሰገደው ሶላት ደግሞ በሁለቱም ከሚሰገደው ሶላት ስለሚበልጥ በመሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺጃቢር ብን ዐብዲላህ በዘገቡት ሐዲስ ‹በዚህ መስጊዴ የሚሰገድ ሶላት በሌላ መስጊዶች ከሚሰገዱ ሶላቶች በሺ ይበልጣል ፡፡ በመካ መስጊድ መስገድ ደግሞ በሌላ መስጊድ ከሚሰገደው በመቶ ሺህ ይበልጣል61› ብለዋል፡፡ በዚህ ሐዲስ የሁለቱን መስጂዶች ትልቅነት በጉልህ እናያለን ፡፡ መካም ከመዲና የበለጠ መሆኑን እንዲሁ ፡፡ በሐረሙ ክልል ዉስጥ የሚሰሩ መልካም ነገሮች ሁሉ የሚባዙት በመቶ ሺህ ነው ፡፡ ይኸዉም አላህ እንዲህ ሲል ‹‹ለሰዎች ማምለኪያ ይሆን ዘንድ መሬት ላይ በመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በመካህ (በመካ) ያለው ቤት ካዕባ ነው › 96 ኣሊ ዒምራን. ላይ በረካ ያለው እሱው ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺበዛር በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ‹‹በመስጂደል ሐራም የሚሰገድ ሶላት በሌላው ከሚሰገደው ሶላት የሚ በልጠው በመቶ ሺህ ሶላት ነው ፡፡ በዚህ መስጂዴ የሚሰገደው ደግሞ በአንድ ሺህ ሶላት ነው ፡፡ በበይተል መቅዲስ መስጂድ የሚሰገደው ደግሞ በአምስት መቶ ሶላት ነው 62›› ብለዋል፡፡ 1-በሁለቱ በመካና በመዲና መስጊዶች መስገድ ያለው ከፍተኛ ቱሩፋት፤ 63 2-በመካ መስጊድ ዉስጥ መስገድ በሌላው ከሚሰገደው በመቶ ሺ እንደሚበልጥ፤ በመዲና መስጊድ የሚሰገደው ደግሞ ከመካ መስጊድ በስተቀር ከሆኑት መስጊዶች በአንድ ሺህ እንደሚበልጥ፤ 64 3-ይህ ቱሩፋትም በሐንበሊና በሻፊዒ መዝሀቦች ፈርዶቹንም ሆነ ትርፍ ሶላቶችን እንደሚያጠቃልል፤ሐነፊዎችና ማሊኪዩች ደግሞ ከፈርዱ ዉጭ አያጠቃልልም ብለዋል ፡፡ 65
60
ታሪኩን ሙስሊመ በአጭሩ ተር ኮታል1396. አህመድ፤ ኢብኑ ማጀህና ነሳኢ; አልባኒም ትክክል ነው ብለዋል፡፡ 62 አለ-በዛር ዘግበዉታል ሀይሰሚ ትክከለኛ ነው ብለዋል፡፡ 63 ሱቡሉ አሰላም 2/216 64 ተምሂድ 6/32. 65 አነወዊ መጅሙዕ…… 61
.
75
4-ይህ ቱሩፋት በምንዳ እንጂ ሌላ ሶላቶችን ከመስገድ ይሸፍናል ማለት እንዳልሆነ፤ 66 5-በመካ የሚሰገድ አንድ ሶላት የሀያ አምስት አመት ከስድስተ ወር ከሀያ ቀን ያለን እድሜ እንደሚወክል፤ በመካ በአንድ ቀን የሚሰገደው አምስት ወቅት ሶላት ደግሞ የሁለት መቶ ሰባ አመት ከሰባት ወር ከአስር ቀን እድሜ ጋር እንደሚወዳደር ፤ 67 6-ይህ ቱሩፋት በአብዛሓኛው ዐሊሞች ዘንድ በመካም ሆነ በመዲና መስጊድና በበይተል መቅዲስ መስጊዶች የተቀጠሉትን ማስፋፊያዎችንም ሆነ በመካ ክልል ዉስጥ ያሉ ልዩልዩ መስጊዶችን ሁሉ እንደሚያጠቃልል ፤ 68 7-ቦታዎች ከሚሰሩባቸው የአምልኮ ተግባሮች ትልቅነት ጋር እንደሚያያዝ እና ከዚህም በመነሳት መካ ከመዲና እንደሚበልጥ ከአንዳንድ የማሊኪ መዝሀብ ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ዐሊሞች መስማማታቸውን ፤ 69 8-እነዚህ መስጂዶች ባሉበት ቦታ የሚኖሩ ህዝቦች ሁሉ በተለይም በመካ ለመኖር የታደሉ ሁሉ የአላህ ቱሩፋት ምን ያክል ታላቅ እንደሆነ ማስታወስ እንደሚገባቸው ፤ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ነቢዩ የቦታዎችንም ሆነ የጊዜያትን ምንዳዎች በመጠቀም ዋና አርአያ ነበሩ ፡፡ ለምሳሌ በሁደይቢያ ስምምነት ጊዜ ወደ መካ እንዳይገቡ ሲከለከሉ የሶላት ወቅት ሲገባ ወደ ሐረሙ ክልል ግቢ ገባ ብለው ሰግደው ይመለሱ ነበር ፡፡ 70 ሱሃቦችም ቢሆኑ የእሳቸዉን አርአያ ተከተሉ ፡፡ ዐብዱላህ ብን ዐምር ብን ዓሲ ሁለት ቤት ነበራቸው አንዱ ሐረም ክልል ሁለተኛው ከሐረሙ ክልል ዉጭ የነበሩ ፡፡ ሊሰግዱ ሲሉ በክልሉ ዉስጥ ወዳለው ገብተው ይሰግዱና ሲጨርሱ ከክልሉ ይወጣሉ ፡፡ 71
66
ዙርቃኒ2/4….. ሙሲሩልአዝሚ ሳኪን1/359፣ ሺፋኡል ገራም 1/171፣ፈትሁል ባሪ3/82… 68 ቱህፈቱል አህወዚ2/238፣ ሸኽ ኢብኑ ባዝም በዚሁ ላይ ፈትዋ ብለዋል፡፡ 69 ፈትሁል ባሪ 3/68፣ፈይዱል ቀዲር4/299. 70 ሙስነዱ አህመድ አርናዖጥ በ18930 ትክክለኛ ነው ብሏል፡፡ 71 አዝረቂ የመካ ታሪክ 2/131፣ተፍሲሩ ኢብኑ ጀሪር 9/132.67
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
5ኛ በመካ መኖርን አትተው የሚለው ሐዲስ
ሙሐመድ ብን ሐሰን አል አጁሪ የተባሉ ዐሊም አንድ አመት ሐጅ ሲያደርጉ የከዕባን ቅዱስነትና ክበሩን ሲያጤኑ አላህ ቢያንስ አንድ አመት በዚያው እንዲያኖራቸው ሲለምኑት አንድ በቸካል የማያዩት ሰላሳ አመት በል የሚል ተናጋሪን ሲናገር ሰሙ፡፡ ከዚያም አላህ ያ! ከተናጋሪው የሰሙትን ነገር አረጋገጠላቸውና በመካ ሰላሳ አመት ኖሩ፡፡ በዚያው ሙተው በዚያው ተቀበሩ ፡፡ 72 ነቢዩ ﷺኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹መካ ከሀገሮች ሁሉ ምን ታምሪ ፤ እኔም ዘንድ ተወዳጅ ነሽ ህዝቦችሽ ባያስወጡኝ ኑሮ በሌላ ሀገር ባልኖርኩኝ ነበር 73› ብለዋል ፡፡ አላህ መካን አከበረው አላህም ሆነ ምልዕክተኛው ከሁሉ ሀገሮች የበለጠ ወደዱት ፡፡ ነቢዩ ከመካ መውጣት በጣም ከባድ ሆኖባቸው ነበር ፡፡ ታዲያ በዚህ ሀገር ለመኖር የታደለ ሁሉ‹‹ከሀገሮች ሁሉ ምን ታምሪ › ያሉትን ቃል በደንብ ማጤን ያስፈልጋል ፡፡ በመሆኑም ያመረን ነገር እንጂ በዉስጡ መስራት የለበትም ፡፡ መካ ያመረ ሀገር በመሆኑም ጣኦት አምላኪዎች ወደ እሱ ሊገቡ አይፈቀድም ፡፡ ሙሐመድ አህመድ አዲያእ74 የተባለው የሐነፊ ዐሊም ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር ‹በመካ የሚኖሩ ፤ ጉረቤቶችም ሆኑ ጎብኚዎች የመካን ክብር ጠንቅቀው ሊረዱ ይገባል ፡፡ ሚስጥሯን ሊጠብቁ ፤ ክበሯን ሊያውቁ ፤ አላህ የቸራቸዉን የጉርብትና እድል በማመስገን ቀጣይነቱን ሊለምኑት ይገባል ፡፡ እንኳንስ የተከለከሉትን አይደለም ለመካ ክብር ሲሉ ከተፈቀዱ ነገሮችም ቢሆን ብዙም ጥቅም የሌላቸዉን ነገሮች ሊተው ይገባል ፡፡ ይህንንም የምንለው መካ የዒባዳ ቦታ እንጂ የመዝናኛ የእረፍት ቦታ ባለመሆኑነው› 75 1-መዲናም ታላቅ ክብር ያላት ብትሆንም ብዙዎች ዐሊሞች እንደሚሉት መካ ከመዲና የሚበልጥ መሆኑን ፤
72
ዒቅዱ ሰሚን 2/3-5. ቲርሚዚና ኢብኑ ሒባን የዘገቡት ሲሆን አል ባኒ ትክክለኛ ብለዉታል፡፡ 74 አል አዕላም 3/332. 75 አል በህሩል ዐሚቅ. 73
.
77
2-በመካ ዉስጥ የሚኖር ሰው ሊያጋጥመው የሚችለዉን ችግር ለአላህ ብሎ መታገስ እንዳለበት ፤ 76 ኢብኑ ዐባስ የዛፍ ቅጠል እየበላህም ቢሆን በመካ ኑር ብለዋል፡፡ 77 3-ነቢዩ ያጋጠሟቸው ችግሮች ምን ያክል የከፉ እንደነበሩ ፤ 4-መካ ንፁህ ጥሩ ሀገር ካፊር ደግሞ ቆሻሻ መጥፎ ሰው በመሆኑ ካፊር ወደ መካ መግባት እንደተከለከለ፤ 5-ሙባረክ ፉሪ የተባሉ ዐሊም እንደሚሉት በመካ ለመኖር የታደለ ሰው ከአቅም በላይ የሆነ ሃይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ ችግር ምክኒያት ካልሆነ በስተቀር መልቀቅ እንደሌለበት፤78 6-አላህ ለመካ ኗሪዎች ሁሉ ምን ያማረ ፀጋ እንደዋለላቸው ማስታወስ፤ የመካ ናፍቆት በሙሃጂሮች ዘንድ ምን እንደሚመስል፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሀ-እናታችን ዓኢሻህ‹‹የስደት አጅር ባልነበረ ኖሮ በመካ እኖር ነበር ፡፡ ምክኒያቱም ሰማይ ወደ ምድር ቅርብ የሆነበት እና ጨረቃም በይበልጥ የሚያምረበት ቦታ እንደመካ አላየሁም ›› ብለዋል ፡፡ 79 ለ-አል ሓሪስ ብን ሒሻም በዑመር ብን ኸጧብ ኸሊፋነት ዘመን ለኢስላማዊ ጉዳይ ከነቤተሰባቸው ወደ ሻም ሲሄዱና የመካ ሰዎች እየተላቀሱ ሲገላግሏቸው በጣም አዝነው ሀገር ለመቀየር ወይም ጉረቤት ለመምረጥ በነበረ ኖሮ ከናንተ ሌላን ባል መረጥኩኝ ነበር ፡፡ ነገር ግን ጉዞው ወደ አላህ ስለሆነ ነው ፡፡ በማለት መለሱላቸው ፡፡ ከዚያም ራሳቸዉን በጂሃድ ጠምደው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በዚያው ኖሩ ፡፡ 80 6ኛ መካ የመንደሮች ሁሉ ዋናና ከሁሉም በይበልጥ የተከበረች መንደር ናት ፡፡ በምድር ላይ እንደ መካ ክብር ያለው ቦታ የትም የለም ፡፡ ቱሩፋቱ ትልቅ ነው ፡ ፡ በመካ መኖር የሚያስገኘው ምንዳም ከባድ ነው ፡፡ ለዚህም ነበር ሰለፎች አንዱ ሌላዉን በመካ እንዲኖር አቅሙ ከቻለ ችላ እንዳይል አደራ ይባባሉ የነበረው ፡ ፡ 76
አህወዚ 10/295. ሺፋኡል ገራም1/176-177. 78 አህወዚ10/294. 79 የመካ ታሪኮች 2/153. 80 ዒቅዱ ሰሚን 4/34 77
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ነቢዩ ሙሐመድ ﷺዐብዱላህ ብን ዐዲይ ብን ሀምራእ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ አንድ ኮረብታ ላይ ቁመው ‹በጌታየ እምላለሁ አንቺ ከምድሮች ሁሉ በላጭ ነሽ ፡፡ አላህ ዘንድም ተወዳጅ ነሽ ብየ እመላለሁ ፡፡ ህዝቦችሽ በግድ ባያስወጡኝ ኑሮ ከአንቺ አልወጣም ነበር 81› ብለዋል፡፡ ናፍቆት ከመካ ጋር ሲገናኝ በጣም የከበደ ነው ፡፡ ሐዲሱም መካ ለምን እንደምትወደድ አስተምሯል፡፡ ከምድሮች ሁሉ የበለጠ ነው ፡፡ ሙስሊሞች መካን የሚወዱት ከሌሎች ሀገሮች በበለጠ ነው ፡፡ በይበልጥ በዚህ ሀገር መኖርን የሚያስወድደው ለሌላ ዐላማ ሳይሆን ለዒባዳ ብቻ ታስቦ በዚያ ቦታ ዘለግ ያለ ጊዜን ማሳለፍ ነው ፡፡ አቡ ዑመር አዘጃጂ የተባለ ዐሊም ከአላህ ሌላን እያሰበ በመካ የተቀመጠ ሰው ከሳራዉን በይፋ አውጥቷል፡፡ 82 1-መካ የመንደሮች ሁሉ እናት አላህና ነቢዩ ዘንድ ከመሬቶች ሁሉ የተወደደ፤ 2-መካ ከመዲና የተሻለ መሆኑን፤ 3-አላህ የሚወደዉን መውደድ፤የጠላዉን መጥላት ፤ 83 4-አላህ የመውደድ ባህሪ እንዳለው፤ 5-ሐዲሱ አላህ የሚወድ መሆኑን እና የመውደድ ባህሪ ለእሱ በሚገባው መልኩ እንዳለው እንማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ቀደምት ሰለፎች ወደ ዚህ ሀገር ለመምጣት የማይከፍሉት መስዋዐትነት የለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ከተወሩ ዘገባዎች መካከል፡ሀ-ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህና አቡ ሱፍያን በመካ ለመኖር እንደመጡ ፤ አቡ ሱፍያን ከጃቢር ጋር በመካ ስድሰት ወር ቆይተናል ብለዋል84›› ለ-ዐጣእ ብን አቢ ረባህ በመካ አርባ አመት ሙሉ እያስተማሩ፤ እየተማሩ ፤ ጦዋፍ እያደረጉ ፤ አሳልፈዋል85 ፡፡
81
አህመድ ፤ ቲርሚዚ፤ኢብኑ ማጀህ የዘገ ቡት አልባኒ ትክክለኛ ነው ያሉት፡፡ አብኑ ል ጀውዚ ሙሲሩል ዐዝሚ ሳኪን ላይ 2/210. 83 ኢብኑ ዐብዲል በር በተምሂድ 2/288 ዐራቂ በጦርሁ ተስሪብ 6/46. 84 አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ 2/287. 85 አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ 2/32182
.
79
ሐ-ሀሩኑ ረሺድ የተባለው ኸሊፋህ በመካ ሲኖሩ ከየሶላቱ በኋላ ጦዋፍ ያደርጉ ነበር ፤ በተለይም ዐስር ሶላት ከሰገዱ በኋላ እስከ መግሪብ ድረስ ሲጦዉፉ ነበር 86 ፡፡ 7ኛ በሐረም ዉስጥ ወንጀልን/ከእውነት መዘንበልን/ ማሰብ
በብዙዎች ዘንድ በሐረም ዉስጥ ወንጀል መስራት ቀርቶ ማሰብ ማለት ብዙ አይነት እንደሆነ የሚረዱት ጉዳይ ነው ፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚገርመው እኒያ እሳቸው እያሉ በመካ ስለ ሐጅ ማንም አይጠየቅም የተባላላቸው ዐጣእ ብን አቢ ረባህ የተባሉት የመካ ዐሊምና እውቅ የሐዲስ አስተማሪ ‹አንድ ቀን ከተማሪዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ባሉበት አንዱ ወደ እሳቸው ጠጋ ብሎ ሸኽ ብርዎን ሰጥተሁን እህል ለእኛ እንደምን ገዛ ሁሉ ለእርሰዎም ገዝተን ብናስቀምጥስ ሲላቸው ምንድን ነው የምትገዙት በማለት ጠየቋቸው እነሱም ስንዴ በረከሰ ጊዜ እንገዛና ሲወደድ እንሸጣለን አሏቸው ፡፡ ይህን አልፈልግም ፡፡ አላህ በቁርኣን ላይ አእንዲ ይላል‹‹በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል በዳይ ሆኖ ማንኛውንም ነገር የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን› አል ሐጅ 25 ያሉት ነው ፡፡ 87 ነቢዩ ሙሐመድ ﷺኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹ከሰዎች ሁሉ በአላህ ዘንደ የተጠሉ ሶስት ሰዎች ናቸው ፡፡ በሀረም ዉስጥ ወንወጀል ያሰበ ፤ በኢስላም ዉስት የጃሂሊያን ተግባር የሚመኝ ፤ ያለ አግባብ የሰዎችን ደም ለማፍሰስ ግድ ብሎ የሚጠይቅ ነው 88›ብለዋል፡፡ ሰዎች በአላህሚዛን ሲታዩ በወንጀላቸው ብዛትና አይነት ይበላለጣሉ ፡፡ በዚህ ሐዲስም የተማርነው ወንጀሎች ከተሰሩበት ቦታ ጋር በተገናኘም እንደሚ በላለጡ ነው ፡፡ በዚህ በተከበረው መስጂድ ዉስጥ ወንጀል መፈፀም ኢልሃድ ነው ፡፡ ዐሊሞች ‹‹የሰው ልጅ ከሐረም ክልል ዉጭ ሁኖ እንኳን በሐረም ዉስጥ ወንጀል ለመስራት ካሰበ ከባድ ቅጣት ይቀጣበታል›› ብለዋል ፡፡ አላህ እንዲህ አለ ‹በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል በዳይ ሆኖ ማንኛውንም ነገር የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን› አል ሐጅ 25. ኢብኑ 86
አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ 2/303-304. አኽባሩ መካ ፋኪሃኒ 3/5288 ቡኻሪ 6882. 87
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
መስዑድ ስለዚህ አንቀፅ ሲናገሩ ‹በሐረም ዉስጥ ወንጀል ለመስራት ዐደን አብየን ሀገር ላይ ሁኖ እንኳን ቢሆን አላህ ክፉን ቅጣት ያቀምሰዋል›89 ብለዋል፡፡ እዚህ ላይ ማስታወስ የም ፈልገው ነገር ቢኖር በመካ ለመኖር አላህ ያደላችሁ ሁሉ ከመለማመዳችሁ የተነሳ ይህን አደገኛ ነገር እነዳትረሱትና ችግር ዉስጥ እንዳትገቡ ነው፡፡ 1-በሐረም ዉስጥ ክህደትን ወይም ወንጀልን መመኘት አደጋ መሆኑን፤በሐረም ክልል ዉስጥ የሚሰራ ወንጀል በሌላ ሀገር ከሚሰራወንጀል የበለጠ መሆኑን ፤ የአላህን ቁጣና ቅጣት የሚያስከትል መሆኑን፤ 2-በመካ ዉስጥ መልካም ምንዳ እንደሚደራረብ ሁሉ የመጥፎ ተግባራትም ቅጣት እንዲሁ ይደራረባል፤ 3-ኢስላም የሰዎችን መብት የጠበቀና የፍትህ መሰረቶችን ያወጀ ፤ አውቆ ዘመዱ የተገደለበት ሰው እንኳን ከገዳዩ ሌላን ማንንም ግደሉልኝ ብሎ መጠየቅ እንደሌለበት ፤ 4-ጃሂሊያን ና አድናቂዎቿን ከኢስላም በሚለዩበት ነገር ሁሉ መለየት፤ 5-በመካ የሚኖሩ ከመኖር ብዛት የተነሳ ለመካ ያላቸው ክብር እንዳይዳከም በከፍተኛ ሁኔታ ማስጠንቀቅ፤ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ በሐረም ዉስጥ የሚሰራ ወንጀል ያለውን ክብደት በማየት ቀደምት ሙስሊሞች ይህን ጉዳይ ማስጠንቀቅና መከልከል ያበዙ ነበር ፡፡ ዑመር በመካ የሚኖሩ ሰዎችን ጠርተው በመካ ዉስጥ መወንጀልን በሀይለኛ ያስጠነቅቋቸው ነበር ፡፡ እንዲህ ይሉ ነበር‹‹በአላህ ሐረም ዉስጥ አላህን ፍሩ ፡፡ በዚህ ሀገር ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦች ታውቃላችሁን የእነገሌ ዘሮች ይኖሩ ነበር ክብሩን ሲደፍሩ ጠፉ ፤ የእነገሌ ዘሮች ይኖሩ ነበር ክብሩን ሲደፍሩ ጠፉ፤ በማለት የቻሉትን በሄሮች ካወሱ በኋላ በሌላ ቦታ አስር ወንጀል መስራት በሐረም ዉስጥ አንዲት ወንጀል ከመስራት ይሻለኛል› 90 ብለዋል ፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር በኢስማዒል ሒጅር ዉስጥ ሲቀመጡና ሰዎች ሲከቡት ከዕባን በዘንጋቸው እያሳዩ ይህ ስለናንተ ሲጠየቅ እናንተም ስለ እሱ ስትጠየቁ ምን ትላላችሁ/ በሱ የሚኖር ሰው
89
አህመድ ፤ አቡ የዕላ ፤ ኢብኑ አቢ ሸይበህ ፤ ዳሩ ቁጥኒ ፤ ኢብኑ ሐጀር ፈትህ ላይ 12/210 ዘግበዉታል፡፡ ትክክለኛው ግን የኢብኑ መስዑድ አባባል ነው የሚለው ነው፡፡ 90 ኢብኑ አቢ ሸይበህ ሙሰነፍ 4/352. .
81
በወለድ አይነግድም ፤ደም አያፈስም ፤ በሐሜት የማይንቀሳቀሱበት ሀገር ነው›91 ነው አሉ፡፡ 8ኛ የተከበረው የእሙኑ ሀገር የመካ ህብረተሰብ /ማህበረሰብመለያዎች ለተከበሩ ነገሮች ሁሉ ተገቢ መለያዎች አላቸው ፡፡ እናም መካም ልዩ ለአላህ የሚደረጉት የአመልኮ መፈፀሚያ ቦታ በመሆኑ ልዩ ክብርና ተገቢ ስርዐት አድርጎለታል ፡፡ ነቢዩም ይህን ስርዐት በሰፊው ተንትነው አስረድተዋል ፡፡ ይህም የሆነው በዚያ መካን ከተቆጣጠሩ በኋላ ባደረጉት ሐጅ ሰፊ ኹጥባ ላይ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹መካ በተከፈተ ዕለት ከዛሬ በኋላ ከመካ ወደ መዲና ስደት የለም ፡፡ ነገር ግን ጂሃድና በፍፁምነት መስራት ነው ፡፡ ወደ ጂሃድ ስትቀሰቀሱ ተነሱ ፡፡ ይህ ሀገር አላህ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ያከበረው እስከዐለም ፍፃሜም ድረስ በዚሁ ክብሩ ላይ የሚቀጥል ነው ፡፡ ከእኔ በፊት ለማንም በዚህ ቤት ዉስጥ ጦርነት አልተፈቀደም ፡፡ ለእኔም ቢሆን ትንሽ ሰዐት እንጂ አልተፈቀደልኝም 92 › ብለዋል፡፡ ከመካ ወደሌላ ሀገር መሰደድ በመካ መከፈት አብቅቷል ፡፡ ምክኒያቱም መካ የሙስሊሞች ሀገር ሁኗል ፡፡ ከዚህ በኋላ የክህደት ሀገር ምንጊዜም አይሆንም ፡ ፡ ጂሃድ ግን የሙስሊሞች መሪ ከጠራ ሁልጊዜም ግድ ሁኖ ይቀጥላል፡፡ መካ ሰማይና ምድር ከተፈጠሩ ጊዜ አንስቶ የተከበረ ሀገር ነው ፡፡ ገና ከዕባ እንኳን ሳይገነባበት በፊት ፡፡ ይኸው ክብር እሰከ ዐለም ፍፃሜ ድረስ ይቀጥላል፡ ፡ በዉስጧ ጦርነት የተፈቀደው ከአንድቀን የተወሰነ ሰዐት ነው፡፡ ያዉም ከጣኦት አምልኮና አምላኪዎች ነፃ ለማውጣት ሲባል ብቻ ነው፡፡ 1-የሐረም ዛፍን እሾህማ እንኳን ቢሆን መቁረጥ ክልክል መሆኑን፤93 2-በሐረም ዉስጥ አውሬዎችን መግደል ይቅርና ማስደንገጥ እንኳን ክልክል መሆኑን፤94 3-ባለቤቱን ለማፈላለግ ያሰበ ሰው ካልሆነ በስተቀር የወደቁ ነገሮችን ማንሳት ክልክል መሆኑን፤ 95 91
-የመካ ታሪክ አዝረቂ 2/137. -ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት በመሆኑ ምንመ ችግር የለበትም.፡፡ 93 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ ላይ 9/126. 94 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ ላይ 9/126. 95 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ ላይ 9/126. 92
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
4-ጠጄ ሳር የተባል ሳር ካልሆነ በስተቀር እርጥብ ሳርን መቁረጥ ክልክል መሆኑን፤96 5-የደረቁ ሳሮችን መቁረጥ የሚፈቀድ መሆኑን ፤97 6-በራሱ የተከላቸዉን ዛፍም ሆነ ሳር መቁረጥ የሚፈቀድ መሆኑን፤ 98 7-እነዚህ በመካ የተከለከሉትን ነገሮች ሁሉ መዘርዘር ሳይሆን ከሌሎች ሀገሮች መካ የተለየበትን ማውሳት መሆኑን ፤ 8-መካ ለአማኞች ሁሉ የበለጠ ሀገር መሆኑን፤ 9-በመካ ዉስጥ የሚካሄዱ ጦርነቶች እና የሚፈሱ ደሞች ምን ያክል ከባድ መሆኑን፤ 10-ልክ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺእንዳደረጉት ሁሉ ሁላችንም የዚህን ታላቅ ቤት ትልቅነትና ክብር ማሰራጨት ተገቢ መሆኑን ፤ 11-የነቢዩ ሙሐመድ ﷺአጎት የሆኑት የዐባስ ትልቅነትን እንማራለን፡፡ 99 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ይህ ሐዲስ ሙስሊም የተባለ ሁሉ ከመካ ማህበረሰብ ጋራ ሊኖራቸው የሚገባዉን ስነ ስርዐትን በሰፊው ያስተምራል ፡፡ ከእነዚህም መካከል ከሙጃሂድ ‹‹ኢብኑ ዑመር ጦዋፍ ሲያደርጉ አልወሰዷትም ፡፡ ›› የተባለው ታሪክ አንዱ ነው፡ ፡ ዑመር አንድን ሰው-----ሲያደርግ አይተው ተቆጡትና ‹ይህን ነቢዩ የከለከሉ መሆናቸዉን አላወቅክምን›› ብለዋል ፡፡ ከዚያም እንዳስፈለገው ሲነግራቸው አሳዝኗቸው እንዳዘዙለት ተዘግቧል100 ፡፡ ቀደምት ዐሊሞችም የመካን ማህበረሰብ ክብርን መንካትና አውሬዎቿን ማደንን በጣም ይጠሉት ነበር ፡፡ ይህ ተግባር ለአቅመ አዳም ባልደረሰ ህፃን ቢፈፀም እንኳን 101 ፡፡ ኢብኑ ዐባስ በመካ እያሉ አንድ ህፃን ልጅ ከመካ እርግቦች አንዷን ገሎ ሲጠየቁ በአባቱ ላይ አንዲት ፍየል እንዲያርድ አስገድደዋል 102፡፡ 96
ፈትሁል ባሪ4/59. ፈትሁል ባሪ4/59. 98 ፈትሁል ባሪ4/59. 99 ፈትሁል ባሪ4/59. 100 የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ.3/48 101 የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ.3/370 . 102 የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ.3/382. 97
.
83
በዚሁ መልክ ነበር የመካ ሰዎች የኖሩት ፡፡ ሙጃሂድ እርግቦች በመካ ሲኖሩ ከሰዎች ጋር በጣም ይቀራረቡ ነበር ፡፡ ተሳስቶ አንድ ሰው እንኳን ከያዛት ይህን ያደረገ ማን ነው ፤ ይህን ያደረገ ማን ነው ይህን አይነት ተግባር ካልተዋችሁ ከሰማይ ዝናብ እንከለከላለን››በማለት ሰው ያዋክበው ነበር›103 ብለዋል ፡፡ 9ኛ ደምን ስለ ማክበር…… ኢስላም ከሌላው የሰዎች ህግጋት ከሚለዩት ሰፊ እንክብካቤ ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ደምን መጠበቅ ነው ፡፡ የማንም ሙስሊም ደም ልክ እንደ ፀሐይ ቁልጭ ባለ መረጃና በጥፋት ካልሆነ በስተቀር ያለ አግባብ አይፈስም ፡፡ በተለይ ወደዚህ ሀገር የገባ ሁሉ የበለጠ የተከበረ ነው፡፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ሐጅ ላይ እያሉ የጦር ጫፍ ዉስጥ እግራቸዉን መታቸውና ሐጃጅ ሊያቸው መጥቶ ያቆሰለህን ብናውቀው ኖሮ ሲላቸው አንተ እኮነህ የመተሀኝ አሉት ፡፡ እሱም ደንገጥ ብሎ እንዴት ሁኖ አላቸው ፡፡ እሳቸውም አንተነህ እኮ የጦር መሳሪያ በማይያዝበት ቀን እንዲያዝ የፈቀድከው ወደ ሐረም ጭራሽ ማስገባት የማይፈቀደዉን የጦር መሳሪያ አስገባህ አሉት 104፡ ፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺጃቢር ብን ዐብዲላህ በዘገቡት ሐዲስ ‹ለማንኛችሁም ሰው በመካ የጦር መሳሪያ ማስገባት አይፈቀድለትም 105›ብለዋል፡፡ አላህ ይጠብቀዉና የመካ ፀጥታን በተመለከተ ከሚደረጉት ጥረቶች መካከል የሸሪዓ ጉዳዮችን የተመለከተው ነው ፡፡ ይኸዉም የመካ ኗሪዎች እና ጎብኚዎቿ ሊያከብሩት የሚገባው ነገር ነው፡፡ ይህም ሐዲስ የሚያስተምረው ይህንኑ ነው ፡ ፡ ይህ ሐዲስና ነቢዩ የሑደይቢያ ስምምነት ዕለት በተሰረዘችው ዑምራ ፈንታ በተደረገችው የቀዷዋ ዑምራ ዕለትና መካን የተቆጣጠሩ ቀን መሳሪያ ይዘው መግባታቸዉን በተመለከተ ይጋጫል ተብሎ ሊታሰብ ይችል ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ይህ አይነቱን መልዕክት ለማሰማማት በማያስፈልግበት ጊዜ የተከለከለ ነው ካስፈለገ ግን ይፈቀዳል በማለት ነው106፡፡ 1-በአላህ ዘንድ የመካን ትልቅነት ፤107 103
የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ.3/384. ቡኻሪ966. 105 ሙስሊም1365. በመሆኑ ምንም የለበትም፡፡ 106 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ. 9/130. 107 የሰዕዲ ተፍሲር 138. 104
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
2-የመካን ክብር ለመጠበቅ ሲባል የትኛዉንም የጦር መሳሪያን ማስገባት የተከለከለ መሆኑን 108 ፤ 3- ከመሳሪያም ሌላ ሰዎችን ሊያስቸግሩ የሚችሉ ነገሮች መከልከሉን ፤ 4-ሆኖም ለችግር ሰዐት መሳሪያ መያዝ የሚፈቀድ መሆኑን ፤ 109 5-በመካ ጦርነት ማካሄድ በፍፁም የተከለከለ ፀያፍ ተግባር መሆኑን እንማርበታለን፡፡ 110 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ይህን ክብር መጠበቃቸዉን ከሚያመለክቱ ተግባሮች መካከል በድሩዲን ሐሰን የተባለው በአንድ ወቅት የመካ አስተዳዳሪ የነበረ የመካን ክብር ለመጠበቅ ሲባል በመካ የሚኖር ሁሉ መሳሪያ መያዝ ክክል መሆኑን አዉጆ ነበር ተብሏል ፡፡111 በየዘመኑ የነበሩ የመካ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ያለ ፍቃድ በግልፅ መሳሪያ ይዞ በመካ የሚታይን ሰው ሁሉ በተለያየ ቅጣት ይቀጡ ነበር ፡፡ 112 አሁንም ያለው የሳዑዲ መንግስት ይህን ህግ በሚተላለፉ ላይ የሚያደርገው ይህንኑ አይነት እርምጃ ነው ፡፡ በተለይም ለሐጅና ለዑምራ የሚመጡትን ለማስቸገር የሚፈለጉትን ሁሉ ለመከላከል በማሰብ ነው፡፡ 10ኛ ሁለቱ ቅዱሳን ከተሞች ከደጃል ወረራ እንኳን ስለ መጠበቃቸው፡፡ በዚህ ዐለም ላይ ከሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ መጥፎው የዚያ ከዐለም ፍፃሜ ቀደም ብሎ የሚከሰተው የደጃል ፈተና ነው ፡፡ ለዚህም ነው የትኛዉም ነቢይ ስለ እሱ ህዝቡን በትኩረት እያስጠነቀቀ ያልፍ የነበረው ፡፡ ይህ ሰው በሚመጣበት ጊዜ ዐለምን ይዞራል፡፡ መካና መዲና ግን መግባት አይችልም ፡፡ ወደ መዲና ለመግባት ሲሞክር ያቅተዋል ፡፡ እንዲያዉም ከመዲና አንድ የተሸላ ሰው ይነሳና አንተ ያ ! ነቢዩ ያስጠነቀቁን ደጃል ነህ ይለዋል ፡፡ ደጃልም በዚህ ጊዜ ይህን ገድዬ እንደገና ባስነሳው አሁንም በኔ ጉዳይ ትጠራጠራላችሁን ይላል፡ ፡ ህዝቦችም በፍፁም እነጠራጠርም ይላሉ ፡፡ ከዚያም ይገለዉና እንደገና ይቀሰቅሰዋል ፡፡ የተቀሰቀሰው ሰው እንዴዉም አሁን ነው በትክከል ደጃል 108
ነወዊ በሙስሊም ሸርህ9/130. ነወዊ በሙስሊም ሸርህ. 9/131. 110 ኢብኑል ጀውዚ ከስፉል ሙሽኪለ 3/108. 111 ዒቅዱ ሰሚን4/86. እና 4/98 112 አኑጁሙ ዛሂረህ 13/177. 109
.
85
መሆንህን ያረጋገጥኩት ሲለው እንደገና ለመግደል ሲሞክር ሳይችል ይቀራል ፡፡ 113 ነቢዩ ﷺአነስ ብን ማሊክ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ከመካና ከመዲና በስተቀር ደጃል የማይወረው ሀገር የለም ፡፡ እነሱማ በየኬላዎቻቸው ላይ የመላይካ ዘበኞች አሉ ፡፡ ከዚያም መዲና ሶስት ጊዜ ትርገፈገፋለች ፡፡ ከዚያም በአላህ ሀይል ከሃዲያንና ምናፍቃን ከመዲና ጥርግ ብለው ይወጣሉ114››ብለዋል፡፡ ሐዲሱ የመካንና የመዲናን ትልቅነት እና ሁለቱም በአላህ ጥበቃ ስር መሆናቸዉን ከደጃል ፈተና እንኳን በመላይኮች የሚጠብቃቸው መሆኑን በግልፅ ያስተምራል፡ ፡ ከዚያም መዲና በዉስጧ የሚኖሩትን ምናፍቃን ወደ ደጃል የምታባርር መሆኗንም እንዲሁ በግልፅ ያስረዳል፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ሀገሮች የሚኖሩ ሰዎችም እንደዚሁ በአላህ ጥበቃ ስር ለመሆን የሚያስፈልጋቸው ትክክለኛ አማኞች ከሆኑ ብቻ ነው ፡፡ ሁለቱም ከተሞች ለወደ ፊት የትክክለኛ እምነት ባለቤቶች ሁሉ የሚጠጉባቸው ናቸው ፡፡ እምነቱን ጠንክሮ ለመጠበቅ ያሰበ ሰው ሁሉ በሰላም የሚኖርባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡ 1-ሁለቱም ከተሞች ከሌላ ሀገራት ላይ ያላቸዉን ብላጫ ፤ 115 2-ወደ ፊት የሚሆንን ነገር በግልፅ በማውሳት ተዐምር. ፤ 116 3-በመካና በመዲና የሚኖሩ ትክክለኛ አማኞች ሁሉ በአላህ ዘንድ ያላቸው ክብር፤117 4-በመካና በመዲና መኖር ተፈላጊ መሆኑንና በተለይም በችግር ዘመን፤ 5-መካን አላህ ከደጃል እንድጠበቀው ሁሉ እኛም የተከለከሉ ነገሮችን በማክበር ራሳችንን መጠበቅ እነዳለብን፤ 6-መካና መዲና ኗሪዎቻቸዉን ከደጃል የሚጠብቁት በትክክል እምነት ላይ ያሉትን ብቻ መሆኑን ነው ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
113
ቡኻሪና ሙስሊም. ቡኻሪና ሙስሊም. 115 የቡኻሪ ሸርህ ኢብኑ በጣል 4/551. 116 ዑምደቱል ቃሪ10/244. 117 ዑምደቱል ቃሪ10/244 114
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ሁለቱም ሀገሮች ከደጃል ስለጠበቁ ብዙ ሰዎች በመኗሪያነት በጣም ይፈልጓቸዋል ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዐብዱላህ ብን ዐባስ ‹‹በመካ ለመኖር ተጣጣሩ ፡፡ ሌላ ነገር ጠፍቶ ቅጠል እየበላችሁ እንኳን ቢሆን በመካ ኑሩ ይሉ ነበር 118 ፡፡ አል ሙጊራህ ብን ሐኪም የተባለ የሶንኣ ሀገር ሰው ወደ መካ ሀምሳ ጊዜ ፆመኛ ሁነው በእግራቸው ተጉዘዋል፡፡ በብዛትም በመካ ይኖሩ ነበር ፡፡ የሞቱትም በዚያው ነው ፡፡ ጀሪር የተባለ ሰው የከዕባን ዙሪያ አል ሙጊራህ ብን ሐኪም የሞተ ዕለት ብቻ እንጂ ያለ አንድም ጦዋፍ አድራጊ አይቸው አላውቅም ብሏል ፡፡119 11ኛ ለመካ ብቻ የተቸረው የሁል ጊዜ አስተማማኝ ሰላም ነው፡፡ አላህ መካ የዚህ የተከበረው ቤት የመጀመሪያ የአምልኮ ቤት የሆነው መስሪያ እንዲሆን ፈለገ ፡፡ ከመጥፎ ነገሮችም ሁሉ ጠበቀው ፡፡ የዝሆኑ ታሪክም ለዚሁ ጥበቃ ታላቅ ማስረጃ ነው ፡፡ አል-ሓሪስ ብን ማሊክ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ‹‹ﷺይህ ሀገር ከዛሬ በኋላ እስከ ዐለም ፍፃሜ ድረስ አይዘመትበትም 120 ›› ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፡፡ በመካ ዉስጥ በሙስሊሞች መካከል የእርስ በእርስ ጦርነት በተደጋጋሚተካሂዷል ፡፡ ከዚህ ሁሉ በጣም የታወቀው ሐጃጅ ብን ዩሱፍ ኢብኑ ዙበይርን በከበበበት ጊዜ የነበረው ነው ፡፡ በቃራሚጧዎችም ጊዜ እንዲሁ ተካሂዷል፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ የሐዲሱ መልዕክት ከዚህ ጊዜ በኋላ መካ መቸም ቢሆን በካሃዲያን አይወረርም ፡፡ የከሃዲያን ሀገርም ሁኖ ሙስሊሞች እሱን ነፃ ለማውጣት አይዘምቱበትም ማለት ነው ፡፡ 1-የመካ ኗሪዎች ምን ጊዜም ወደ ክህደት ይሄዳሉ ተብሎ አያሰጉም እናም ወደ ክህደት ገብተው አይዘመትባቸዉም ፤ 121 2-መካ ከሙስሊም ሀገሮች ሁሉ ሰላም ሀገር መሆኗን፤ 3-ለትክከለኛ አማኞች አስተማማኝ ሀገር መሆኑን፤ 4-ለማካ ኗሪዎችም ሆነ ለጉብኚት ለሚ መጡ ሁሉ ቀጥ እንዲሉ ማስታወስ፤ 5-መካ ኗሪዎች አላህ የሰጣቸዉን ፀጋ እንዲያመሰግኑ ማስታወስ፤ 118
ሺፋኡልገራም 1/176-177. ዒቅዱ ሰሚን 7/254-255 120 አህመድና ቲርሚዚ አልባኒም ትክከለኛ ሐዲስ ነው ብለዋል፡፡…… 121 ሸርሁ መዓኒ ል አሳር 3/326. 119
.
87
6-በመካ መኖር መልካም መሆኑን ማስታዎስ፤ 7-የነቢዩ ነቢይነትን የሚያመለክት ﷺግልፅ ተዐምር፤ 8- መካ በአላህ ዘንድ ያለው ክብር መጠቆም ናቸው ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ዐሊሞች መካ አላህ ይጠብቀዉና በሺፍቶች ፤በጠላቶች ቢወረር እና እነሱን ለማስወጣት ሲባል ጦርነት ማድረግ ቢያስፈልግ አስፈላጊዉን ሀይል መጠቀም ይቻላል ብለዋል122 ፡፡ የነቢዩ ሙሐመድ ﷺየልጅልጅ የሆኑት ሁሰይን ብን ዐሊይም ከመካ ወጥተው ወደ ዒራቅ ሀገር የሄዱበት ዋናው ምክኒያት በሳቸው ሰበብ መካ በጥጋበኞች እንዳይወረር ብለው ነው፡፡ ኢብኑ ዐባስም ስለዚሁ ክስተት ሲናገሩ ‹አልሑሰይን ብነ ዐሊ ወደ ዒራቅ ለመሄድ አማከረኝና ለእኔም ሆነ ለአንተም ሆነ ለእኔ ዉርደት ባልሆነ ኖሮ አናትክን ባልኩህ ነበር› አልኩት ፡፡ እሱም በእገሌ ቦታ መገደሌ መካ በእኔ ምክኒያት ከሚደፈር ይሻለኛል አለኝ ፡፡ ይኸው ሁኔታው ነበር እኔም ችላ እንድለው ያደረገኝ›› 123 ብዋል፡፡ 12ኛው አክብሮት ዉስጥን ሲቆጣጠር በሰዎች ዘንድ በተለይም በመካ ኗሪዎች ዘንድ በጣም ሊጠናከር ና ሊበረታታ የሚገባው ነገር ቢኖር የመካ ክብርንና ትልቅነትን በዉስጣቸው ማሳደርን ነው ፡ ፡ በግልፅ የሸሪዓ መመሪያዎችን የማይፃረር እሰከሆነ ድረስ ከቀደምት ዐረቦችም ሆነ ከሌሎች ህዝቦች መልካም ነገሮችን መውሰድና ማዳበር ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ዐበዱላህ ኢብኑ ዑመር የመካ እርግቦች ምግባቸዉንና ልብሳቸዉን ሲረጋግጡት እንኳን ምንም አይሏቸዉም ነበር 124፡፡ አንዳንዶች በመኪና ላይ ሁነው ቆሻሻ ሶፍትን እንኳን በእግራቸው ስር እንጂ ፊትለፊት መጣል እስከሚፈሩ ድረስ ይጠነቀቃሉ፡፡ አልሚስወር ብን መኽረመህ እና መርዋን ብንል ሐከም በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ነቢዩ ﷺየሁደይቢያው ስምምነት ዕለት ወደ መካ ገስግሰው በመንገድ ላይ እያሉ ኻሊድ ኢበኑ ልወሊድ ገሚም በተባለ ቦታ ላይ ተዘጋጅቶ ነው ያለዉና 122
አል ሙሓላ ኢብኑ ሐዝም 11/96. የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ 2/265. 124 ትክክለኛ ታሪክ 2/112... 123
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ቀኝያችሁን ያዙ አሉ ፡፡ ኻሊድም ምንም ሳይሰማ ነቢዩ ከባል ደረቦቻቸው ጋርአጠገቡ ደረሱ ፡፡ በዚህ ጊዜ ደንግጦ ለቁረይሾች ነገረ ፡፡ ነቢዩም ጉዟቸዉን ቀጥለው በቁልቁለቱ ላይ ሲደርሱ ግመላቸው በረከች ፡፡ ሰዎች ተነሽ ተነሽ አሏት እንቢ ስትል ግመሏለገመች አሉ፡፡ ነቢዩ አለገመችም ግን ዝሆኑን ያሰረው ጌታ አስሯት ነው አሉ ፡፡ በጌታየ ይሁንብኝ የአላህን ህግጋት የሚያስጠብቅ የሆነ ነገር ከጠየቁን እቀበላቸዋለሁ ፡፡ ከዚያም ቀሰቀሷትና…125›› ብለዋል፡፡ ነቢዩ በስድስተኛው አመት ላይ ዑምራ ለማድረግ ወደ መካ ለመግባት ዝግጂታቸዉን አጠናቀቁ ፡፡ ከዚያም አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰዎችን ይዘው ጉዞ ጀመሩ ፡፡ ወደ መካ ሲቀርቡ መኮች ማውቃቸዉን ሰሙ ፡፡ በድንገት ሊገቡባቸው አስበው ሲሞክሩ ግመላቸው እንቢ አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ነቢዩ ያ የአብረሃን ዝሆን ከመካ የከለከለው አላህ እሷንም እንደከለከላት ተረዱ ፡፡ ሰዎች ግመሏ ለገመች ፤ ለገመች ፤ ሲሉ ‹ ነቢዩ ተዋት አለገመችም ፡፡ ግና ያ የአብረሃን ዝሆን ከመካ የከለከለው አላህ እሷንም እንደከለከላት › አሉ ፡፡ 1-የግማሏ እንቢ ማለት የዚህን ቤት ወደር የለሽ ክብር እንደሚያመለክት፤ 2-ነቢዩ ‹‹ﷺየአላህ ህግጋት የሚያስከብር እቅድ ካመጡ የትኛዉም ቢሆን እስማማለሁ›› በማለት ለአላህ ህግጋት የነበራቸው ክብርና ዉዴታ እንደሚያመለክት፤126 3-መካ በአላህና በነቢዩ ዘንድ ምን ያክል የተከበረ እንደሆነ፤ 4-የግመሏን እንቢታ ከዝሆኑ ታሪክ ጋር ማመሳሰላቸው ሶሃቦች ገብተው በነበረ ጦርነት ይካሃድ ነበር ይህ ደግሞ ምን አይነት ጥፋት እንደሆነ የሚያውቀው አላህ በዚያን ቀን ሳይገቡ መቅረታቸው የነበረው ከፍተኛ ጠቀሜታ ምን እንደሆነ ፤ 127 5-ጥሩ ተግባር ሁሉ ይህንን ታላቅ ነገር የሚያረጋግጥ መሆኑን፤ ለምሳሌ ሀገርን ማክበር ‹የአላህ ህግጋት የሚያስከብር እቅድ ካመጡ የትኛዉም ቢሆን እስማማለሁ› በማለት ያስተማሩት እንኳንስ ሙስሊም አይደለም ጣኦት አምላኪዎች፤ ሺፍቶች ም ቢሆኑ የአላህ ህግጋት የሚያስከብር እቅድ ካመጡ
125
ቡኻሪ 2731. ኢብኑ በጣል የቡኻሪ ሸርህ8/127. 127 ዑምደቱ ልቃሪ14/7. 126
.
89
የትኛዉም ቢሆን ልንቀበላቸው ፤ ልን ደግፋቸው ፤ ልን ተባበራቸው እንደሚገባ እንማራለን ፡፡128 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ስለዚህ ቤት ክብር ከሚያመለክቱ ታሪካዊ ተግባራት መካከል……. -የከዕባ ልብስ ባለ ስልጣኖችና ባለ ሀብቶች ከዕባን ማልበስ ከጀመሩበት ዘመን እስካሁን በተከታታይ ቀጥለዉበታል፡፡ የዚህን እድል ካገኙት ሰዎች መካከል ሙዓዊያህ አንዱ ነው ፡፡ እንዲያዉም ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕባን የሐር ልብስ ያለበሰው እሱ ነው ይባላል ፡፡ ሸይበህ ብን ዑስማን ዘንድ ከዕባን አጥበህና ሺቶ ቀብተህ ይህን አልበሰው በማለት ላከበት ፡፡129 ከዚያም በኋላ በየ አመቱ ሺቶ ማጨሻ፤ይልክ ነበር፡፡ ብዛት ያላቸው የመካ አገልጋዮችም ይልክ ነበር ፡፡ ከሱም በኋላ የመጡ ገዢዎች እንደዚሁ ያደርጉ ነበር፡፡ ለከዕባ አገልግሎት የሚዉል ዘይትና ሻማ ከቤተ መንግስት በጀት እንዲደረግለት አስደርጓል130፡፡ ይህ ሁሉ ሸሪዓ የማይቀዋወመውና ብሎም የሚያበረታታው ነው ፡፡ ይህን ተግባር ከሚያበረታቱት መካከል ነቢዩ ራሳቸው ወደ መካ የሚወሰዱ በጎችንና ገመሎችን ልዩ ምልክት/በላያቸው ላይ ገመድ ማሰር፤ወይም የሆነ ቦታቸው ላይ ወጋ አድርጎ ሰዉነታቸዉን በደም መቀባት/ ማድረግን ቀደም ሲል በጃሂሊያ ዘመን ይደረግ እንደነበረ ሁሉ ከኢስላም በኋላም መተዋቸው አንዱ ነው፡፡ ለዚህም ነበር ያ የቁረይሾችን ሃይል በሁለት እጅ ያጥፋል የተባለው የአሃቢሽስብስብ ሃላፊ የነበረው ሁለይሱል ኪናኒ የተባለው ሰው ከነቢዩ ጋር ሊወያይ በመጣበት ጊዜ የገመሎች ሻኛ ምልክት ተደርጎበት ሲያይ በጣም ተሰምቶት ሱብሃነ ሏህ እኒህ ሰዎች ከአላህ ቤት ሊከለከሉ አይገባም ያለው.131 13ኛ አክብሮትና ትልቅነት/ሰላምና ፀጥታ
128
ዛዱል መዓድ 3/303. መናኢሁል ከረም 2/7. 130 -መናኢሁል ከረም 2/7. 131 -ሲረቱ ኢብኑ ሒሻም.4/280. 129
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ይህን ቤት ከዕባን ማክበርና ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ መጠበቅ በሁሉም ሙስሊም ትክሻ ላይ የተጣለ ታላቅ ሀላፊነት ነው ፡፡ የበለጠ የሚመለከተው ደግሞ ህዝቦቹን እንዲመራ ፤ ሀገር እንዲያስተዳድር የተደረገ ሰው ላይ ደግሞ የባሰ ነው ፡፡ ይህን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት ዲንን መጠበቅ ነው ፡፡ ለሙስሊሞችም ስኬታማነት ከጌታ ቃል የተገባ ነው ፡፡ ነቢዩ ﷺዐያሽ ኢብኒ አቢ ረቢዓህ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹የእኔ ኡመቶች የዚህን ቤት ክብር በተገቢው እስከጠበቁት ድረስ ኸይረኞች ናቸው ፡፡ ከተዉትና ችላ ካሉት ግን ይጠፋሉ132› ብለዋል ፡፡ ሙስሊሞች የዚህ ታላቅ ቤት ክብር በልባቸው እስካለ ድረስ ክብራቸዉም አለ ፡፡ ችላ ማለት ሲጀምሩ ግን የመጥፊያቸው መጀመሪያ ነው ፡፡ ኢብኑ ልቀይም የዚህን ታላቅ ቤት መለያዎች እያወሳ ባለበት ቦታ ላይ አንዱ የእነሱን ፈለግ ለዐለም መቀጠል ዋስትና አደርጎታል፤ የእነሱ ፈለግ እስካለ ድረስ ዐለምም ይኖራል ፡፡ ፈለጋቸው ከምድር ገፅ ከጠፋ የዐለም መጨረሻ መድረሱን ያመለክታል ፡፡ ‹‹አላህ የተከበረውን ቤት ካዕባን ፤ ክልክል የሆነውን ወር፤ መስዕዋቱንና ባለ ምልክቶቹን መንጋዎች ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ›› አል አልማኢዳህ 97. ኢብኑ ዐባስ ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ 1-ሁሉም ሰዎች ሐጅ ማድረግን በአንድ ቢተዉት ሰማይ በምድር ላይ ትደፋለች ፡፡ 2- ‹ሰዎች ሁሉም ሐጅ ማድረግ ቢተዉ በምድር ላይ አይኖሩም 133 ብለዋል ፡፡ 1-ሙስሊሞች ይህን ቤት ማክበራቸው ዋና ከፊትና መጠበቂያቸው መሆኑን ፤ 134 2-ይህን ቤት ሲያዋርዱ አላህ እንደሚያዋርዳቸው፤ 3-ይህን ቤት ማክበር ማለት በቁርኣንና በሐዲስ በተነገረው ማለት እንደሆነ፤ 4-ነቢዩ ለህዝቦቻቸው የሚጠቅሙ ነገሮችን ባጋጣሚው ሁሉ ማውሳታቸው፤ 5-ይህን ቤት ማክበር በኢስላም መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን፤ 6- አዲሱን ትውለድም በዚሁ አደብማሳደግ ግዴታ መሆኑን፤ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
132
-አህመድ፤ ኢብኑ ማጀህ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ደካማ ነው ብለዋል፡፡ ጂላኡል አፍሃም 313-314. 134 ፈትሁልባሪ3/449. 133
.
91
የነገስታትና የመሪዎች ለመካ የነበረበራቸው እንክብካቤ በሌሎች ሰዎች ዘንድም ክብሩ እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋፆእ አድርጓል ፡፡ በየጊዜው የነገሱ የሙስሊም መሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ሺቶዎች ፤ ማጨሻ ጋቻዎች፤ ቅባት ነክ የሆኑ ሺቶዎች ን ወደ ከዕባ በይጊዜው ይልኩ ነበር ፡፡ ባሪያዎች ሰራተኞችም እንዲሁ በገፍ ይላኩ ነበር፡፡135 በሌላ በኩልም ዐሊሞች የመካን ትልቅነት በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ እንዲሰርፅ አድረገዋል ፡፡ ወሊድ ብን ሰዕድ የተባለ ሰው ከኢብኑ ዑመርም ግር መካ ዉስጥ ነበርኩኝ አንዲት ዲርሃም ወድቃ አያት ፡፡ እኔ ለአነሳት ወደ እሷስሄድ አጄን መትተው አስጣሉኝና ጭራሽ እድተዋት መከሩኝ›› ብሏል ፡፡136 ኢብኑ ዑመርም ጠማሪዎችንና በአካባቢያቸው ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች የመካን ትልቅነት ጠንክረው ያስተምሩ ነበር ፡፡ አንድቀን ከሙጃሂድ ጋር ሁነው ጦዋፍ እያደረጉ ባሉበት ገንዘብ የያዘ ከረጢት አዩና ሳያነሱት አለፉ ፡፡137 መህዲ የተባለው ኸሊፋ ሙስሊሙን መምራት ሲጀምር የመካ አስተዳዳሪ ያደረገዉን ከመካ ዘፋኝ የተባለን ሁሉ ፤ ሴታሴት የወንድ አገሮችን ፤ ወንዳወንድ ሴቶችን ጠርጎ ከመካ እንዲያወጣና የቁማር ጨዋታና ሌሎችንም ወደ ሐራም የሚስቡትን ነገሮች በማጥፋት መካን እንዲጠበቅ አዘዘው ፡፡ ሴቶች ሺቶ ተቀብተው በአካባቢው እነዳይዘዋወሩም እንዲከለከሉ ዘበኞች ተገቢዉን ክብር እንዲሰጡት አዘዘ ፡፡ 138 14ኛ በተከበረው ቤት በመካ የምግብ ረድኤታመነት ነቢዩ ኢብሂም ሀጀር የተባሉትን ሚስታቸዉንና ኢስማዒል የተባለዉን ልጃቸዉን ወደዚህ አምጥተው ምንም አዝርእት በሌለበት ዋሻ አስቀምጠው በሄዱበት ጊዜ ብዙ ዱዓ አደረጉ ፡፡ ያ ! ዱዓ ለመካ እድሜልኩን ጠቀመ ፡፡ ‹ጌታችን ሆይ ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ደንቡን ጠብቀው ይሰግዱ ዘንድ
135
መናኢሁል ከረም2/7. የመካ ታሪከረ ፋኪሃኒ3/47. 137 የመካ ታሪከረ ፋኪሃኒ3/47 138 ተህሲሉል መራም .3/606-607. 136
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
አስቀመጥኳቸው ፡፡ ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነሱ የሚናፍቁ አድርግ ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው › ኢብራሂም37 ነቢዩ ﷺዐበዱላህ ብን ዘይድ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ነቢዩ ኢብራሂም ለመካ ክልል እንደከለሉለትና ዱዓ እንዳ አደረጉለት ሁሉ እኔም ለመዲና ዱዓ አድርጊያለሁ፡፡ ለመዲና ቁናና ቁሊጥ ኢብራሂም ባደረጉት ሁለት እጥፍ ዱዓ አድርጊያለሁ139፡፡›› ነቢዩ ሙሐመድ ﷺነቢዩ ኢብራሂም መካን በአላህ ፍቃድ የከለሏትመሆናቸዉንና ለኗሪዎቿም ዱዓ ያደረጉ መሆናቸዉን ከተናገሩ በኋላ የመዲናን ክልል ደግሞ እርሳቸው አወጁ ፡፡ በሁለት ጋራዎች መካከል ያሉ አውሬዎች አይታደኑም ፡፡ ለኗሪዎቿም ኢብራሂም ለመኮች ያደረጉትን እጥፍ ደርብ ዱዓ አድርገዋል ፡፡ እናም መዲና በበረካነቷና አውሬ ባለመታደኑ በኩል ልክ እንደመካ መሆኑንና መካም ከመዲና የበለጠ መሆኑን ያመለክታል፡፡ 1-የመካን ክብርና ትልቅነት ማመለከት ሲሆን ይህ ክበር ቀድሞኑ ሰማያት ምድር ሲፈጠሩ ጀምሮ ነው ፡፡ የኢብራሂም ሚና ግን ለህዝቡ በይፋ ማወጅ ነበር ፤140 2-መዲናም ልክ እንደመካ ሁሉ ተገቢ ክብር እነድተሰጠው እንዲያዉም የመካን እጥፍ ዱዓ እንዳደረጁለት፤141 3-በተለይ ለመካ ሰዎች ስጋንና ዉሃን አላህ እንዲባርክላቸው ነቢዩ ኢብራሂም ዱዓ ማድረጋቸው ከዚህም የተነሳ ማንም ሰው በመካ ሲኖር ዉሃና ስጋ ብቻ ቢጠቀም በሌላ ሀገር እነደሚያም ሁሉ በመካ እንደማ ያመው፤ 4-ነቢያት በህዝቦቻቸው ላይ የነበራቸው የዱንያም ሆነ የአኺራ ረድኤት፤ 5-ነቢዩ ኢብራሂም ለመካም ሆነ ለኗሪዋ ህዝቦች ያደረጉት ዱዓና የታየው ረድኤት፤ 6-አሁን በመካ የሚታየው የሲሳይ መብዛት ነቢዩ ኢብራሂምን እና ያደረጉት ዱዓ እንደሚያስታዉሰን፤ 7-የመካ ሰዎችን ይህን ፀጋ እንዲያመሰግኑ ማስተወሱን እንማራለን፡፡
139
ሙስሊም. ፈትሁል ባሪ3/440 141 ነወዊ በመሙስሊም ሸርህ ላይ 9/134. 140
.
93
15ኛ የመካ ጎረቤት ሁኖ መኖር የሚያስገኘው ልዩ ዒባዳ በመካ የሚኖርም ሆነ ጎብኚዎች ሁሉ ከሌሎች የሚለዩት ቀንም ሆነ ማታ በፈለጉበት ሰዐት ጦዋፍ ማድረግ መቻሉ ነው ፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ዐሊሞችና ታላላቅ ሰዎች መካን መኖሪያ ሀገራቸው ያደረጉት፡፡ አቡበክር ዐብዱረዛቅ አዱካሊ የተባሉ የማሊኪ መዝሀብ ተከታይ ዐሊም ‹‹ በመካ ከ23 አመት በላይ ሲኖሩ አብዛኛውን ወቅት የሚያሳልፉት በሶላት፤ በጦዋፍና በፆም ነበር ተብሏል142 ፡፡ ነቢዩ ﷺዐብዱላህ ብን ዑመር በዘገቡት ሐዲስ ‹‹በዚህ ቤት ተገልገሉበት ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ፈርሷል፡፡ ከሶስተኛው መፍረስ በኋላ ግን ላንደኛው ይነሳል143›› ብለዋል ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺጠቅላላ ሙስሊሞችን በተለይ ለመካ ሰዎችና ለጎረቤቶቿ በዚህ መስጊድ ስትኖሩ ትንፋሻችሁን በሶላትና በጦዋፍ አሳልፉ››በማለት መክረዋል ፡፡ ይህ ቤት ሁለት ጊዜ ፈርሷል ፡፡ በሶስተኛው ጊዜ ሊነሳ ይቀርባል ፡፡ እናም ማንም ለሶላትም ሆነ ለጦዋፍ ወይም ዲንጋዩን ሰላም በማለትና በመሳም ማንም አይመጣም ፡፡ ይነሳል ማለት ባለ ቀጫጭን እግሮች ሐበሻዎች ሲያፈርሱት በረካው ይነሳል ማለት ነውም ተብሏል ፡፡ ባለፉት ሁለት ጊዜ ፈርሶ ነበር የተባለው በኑህ ዘመንና ቁረይሾች መልሰው ለመገንባት ያፈረሱትን ነው ብለዋል፡፡ 1-በዚህ ሀገር የሚኖሩም ሆኑ ጎብኚዎች ጊዜያቸዉን መጠቀም፤ 144 2-የዚህ ቤት ዋና አላማው አላህ በፈቀደዉና በደነገገው የአምልኮ አይነቶች ሁሉ ዒባዳ እንዲደረግበት ነው ፡፡ ከዚህም ዋናው ጦዋፍ ማድረግ ነው ፡፡ ዐሊይ ‹‹ ሳትከለከሉ በፊት አቅማችሁ በፈቀደ ያክል በዚህ ቤት ጦዋፍ ማድረግን አብዙ›› ብለዋል ፡፡145 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሰለፎች በዚህ ጉረቤት ሁነው ሲያሳልፉ በጣም ነበር የሚጨነቁት ለምሳሌ፡-
142
ዒቅዱ ሰሚን 8/14. የሐዲሱ ደረጃው ኢብኑኹዘይመህ 4/129፤ኢብኑ ሒባን 15/153. 144 ፈይዱልቀዲር1/639. 145 ዐብዱረዛቅ ሙሶነፍ በተባለው 5/137.ኢብኑ አቢ ሸይበህም ሙሶነፍ በተባለው መፅሐፉ3/269. 143
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
-የመካው ሙፍቲና ታላቁ ዐሊም ዐጣእ ኢብኑ አቢ ረባህ በዚህ መስጊድ አርባ አመት እየሰገዱና እየጦዎፉ አሳልፈዋል146 ፡፡ ብዙ ህዝቦች ሌላ ስራዎችን አቁመው በዒባዳ ብቻ አሳልፈዋል ፡፡ በመካ ብዙ ሰዎች ጊዚያቸዉን ያሳልፉ ነበር ፡፡ ከእነዚሁም መካከል ሙሐመድብን ዐብደላህ አልበዕዳኒ የተባለ ዐሊም በሁለቱ መስጊዶች ሰላሳ አመት አካባቢ እየተማሩ ፤ ዒባዳቸዉን እያደረጉ አሳልፈዋል147፡፡ -ኢብኑል ቀይም በመካ ብዙ አመታት አሳልፈዋል ፡፡ በዚህም ጊዜ ብዙ የሚገርሙ ታሪኮች ታይተዉባቸዋል ፡፡ ለምሳሌ በዘምዘም ዉሃ መዳን፤ በዒባዳ ላይ፤በድረሰት ላይ፤ሰፊ ጊዜ መስጠታቸዉን ይመስል ነው 148፡፡ -ኢብኑ ረጀብ ስለ ኢብኑል ቀይም ሲናገሩ ብዙ ጊዜ ሐጅ አድረገዋል ፡፡ በመካም ኑረዋል ፡፡ የመካ ሰዎች ስለዚህ ታላቅ ሰው ዒባዳና ጥንካሬ ብዙ ያወሳሉ ፡፡ 149 -ሙሀና ብኑ አቢ በክር አልሚስሪ የተባለዉም ዐሊም አንዱ ነበር ፡፡ ይህ ሰው አርባ አመት ወይም ከአርባ አመት በላይ በመካ ኑሯል ፡፡ ከዚሁም ጋር ለድሆች መልካም ተግባርን አድራጊ ኸይረኛ ሰው ነበርም ተብሏል 150 16ኛ ለቂብላችን ሊሰጠው የሚገባው ክብር ቂብላ በአላህም ዘንድ ሆነ በሙስሊሞች ዘንድከፍተኛ ክበር አለው ፡፡ ከዚህም በመነሳት በኢስላም ዉሰጥ ልንጠብቃቸው የሚገቡና ልናከብራቸው ዋጂብ የሆነብን ስነ ስርአቶች እና ህግጋት አሉ፡፡ ኢብኑልቀይም መካን ከሌሎች ለየት ከሚያደርጓት ነገሮች መካከል በምንፀዳዳበት ጊዜ ፊትለፊት መቅጣጨትም ሆን ከኋላው ማድረግ የተከለከለ ነው ፡፡ በዚህ ጉዳይ የተመረጠው ና ማስረጃው ጠንካራ የሆነው በቤትም ዉስጥ ይሁን በሜዳ ላይ ሁሉም እኩል ነው ፡፡ ስለዚህ ዱዳይ በሌላ ቦታ በሰፊው የተጠቀሱ ከአስር በላይ የሆኑ ማስረጃዎች ስላሉት ነው ይህን አባባል የመረጥኩት
146
የመካ ታሪክ 2/321. ዒቅዱ ሰሚን 2/52. 148 ዳሩ ሰዓደህ 1/246፣250 ዛዱል መዓድ 4/393.መዳሪጁ ሳሊኪን1/58. 149 ዘይሉ ጦበቃቲል ሀናቢለህ2/448. 150 ዒቅዱ ሰሚን 7/315. 147
.
95
፡፡ በሁለቱ ሁኔታ ላይ ልዩነት አለ ለሚሉ ዐሊሞች ሁሉ ምንም ማስረጃ የላቸዉም ፡፡ የሁለቱንም ማስረጃ በሰፊው ማቅረቢያ አጋጣሚ አይደለም ፡፡ 151 ነቢዩ ሙሐመድ ﷺአቡ አዩብ አል አንሷሪ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ማንም ሊፀዳዳ ሲፈልግ ቂብላን በመቀመጫው አይቅጣጫት ፡፡ ጀርባዉንም እንዳይሰጣት ፡፡ ይልቁንም ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ምዕራብ ይዙር 152›ብለዋል፡፡ ስንፀዳዳ በቤት ዉስጥም ሆነንም ሆነ ከቤት ዉጭ ሁነን ቂብላን ፊትለፈት ማድረግም ሆነ ጀርባን መስጠት አይፈቀድም ፡፡ የዚህን ክልክለነት ከሚያመለከቱት ጉዳዮች መካከል በየትኛዉም ቦታ ላይ ሁነን ወደ ቂብላ መትፋት መከልከሉ አንዱ ነው ፡፡ ምክኒያቱም ሺንትና ሰገራ ከዚህ የባሰ ነዉና፡ ፡ ‹‹ይልቁንም ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ምዕራብ ይዙር … ›› ያሉት ደግሞ በቲኒሹ ሸንደል ማለቱ ብቻ በቂ እንዳልሆነ በግልፅ ያመለክታል ፡፡ እናም ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ምዕራብ መዞር ግድ ይላል ማለት ነው ፡፡ ይህም አባባል የሚመለከተው ቂብላቸው ወደ ምስራቅ ፤ ወይም ወደ ምዕራብ ያልሆነዉን ለምሳሌ በሻም ፤ በየመን እና በእነሱ አቅጣጫ የሚኖሩትን ህዝቦች ብቻ ነው ፡፡ እነዚያ አቅጣጫቸው ወደ ምዕራብ የሆነዉማ እንደግብፅ ፤ ሪያድ ፤ ያሉት ሀገራት ወደ ሰሜን ወይም ወደ ደቡብ ነው መዞር ያለባቸው ፡፡ 1-ለማንም ሰው በየትኛዉም ቦታ ቢሆን ቂብላን ማክበር ተገቢ መሆኑን ፤153 2-ስለ ቆሻሻ ነገሮች ሰወር ባለ ቃል መናገር ተገቢ መሆኑን እንማራለን ፡፡ 154 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ይህንን ሐዲስ የዘገቡልን ሱሃቢ ወደ ሻም በሄዱ ጊዜ ሺንት ቤቶች ፊታቸው ወደ ቂብላ ተስርተው ስለ አገኟቸዉ ሲቀመጡ አቅጣጫቸዉን ቀየር አድርገው ይጠቀሙ እንደነበር እና ከአላህ ምህረትን ይለምኑ ነበር ፡፡155
151
ዛዱል መዓድ1/49 ቡኻሪና ሙስሊም. 153 አል ኢዕላም 154 ፈትሁል ባሪ 10177 155 ቡኻረና ሙስሊም. 152
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
17ኛ ከቂብላ ጋር ሊኖረን የሚገባን ስነ ስርአት ጣዉስ የተባሉ ዐሊም ‹‹ሙስሊም የሆነ ሰው ሁሉ ቂብላን ማክበር ይጠበቅበታል፡፡ እናም እሱን ሊቅጣጭ አይገባም ››ብለዋል ፡፡ 156 ሙስሊሞች ይህንን ነቢያዊ ስነ ስርአት በየትኛዉም ቦታ ላይ ሁነው ሁለው ጊዜ ሊያከብሩት ይገባል ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺአቡ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ‹በተፀዳዳ ጊዜ ቂብላን በፊት ለፊቱ ያልተቅጣጨ ወይም በጀርባው ያለ ደረገ ሰው አንድ ሐሰናህ ይፃፍለታል ፡፡ አንድ ወንጀልም ይተበስለታል 157› ብለዋል፡፡ መካንና በአካባቢዋ የሚኖሩ የአምልኮ ቦታዎችን ማክበር የሚመለከተው በዉስጧ ለሚኖሩ ብቻ ህዝቦች አይደለም ፡፡ ሃላፊነቱ በዐለም የሚኖሩ ሙስሊሞችን ሁሉ በጠቅላላ ይመለከታል ፡፡ ከእነዚህም መካከል ሲፀዳዱ ፊትንም ሆነ ጀርባዉን ወደ እሱ ከማዞር መጠንቀቅ የሚለው አንዱ ነው፡፡ 1-በመፀዳዳት ሰዐት ወደ ፊትንም ሆነ ጀርባዉን ወደ ቂብላ ያላ ዞረ ሰው አንደ ሐሰነህ ይፃፍለታል ፡፡ አንዲት ወንጀል ትታበስለታለች ፤ 2-መፀዳዳት የፈለገ ሰው ቂብላው ወዴት እንደሆነ መፈለግ እንዳለበት፤ 3-ይህ አጅር የሚገኘው ይህንን አዳብ አስቦ ለሰራ ሰው ሁሉ መሆኑን፤ 4-ሐዲሱ መፀዳጃን ስንሰራም ይህኑ አዳብ ጠብቀን መገንባት እንዳለብን፤ 5-ሐዲሱ አምልኮ ሁሉን ነገር የሚያጠቃልል መሆኑን ያመለክታል፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ዑመር ብን ዐብዱልዐዚዝ ‹‹በምፀዳዳ ጊዜ ከ-ዚህ ዘመን ጀምሮ አንድም ቀን ተቅጣጭቸ አላውቅም› ብለዋል፡፡ 158 ኢብራሂሙ አነኸዒይ ቀደምተ ሰለፎችን የነበሩበትን ሲጠቅሱ ‹መካን በምፀዳዳት ጊዜ ከ-ዚህ ዘመን ጀምሮ አንድም ቀን ተቅጣጭተው አያውቁም› 159. 18ኛ የቂብላን ጉዳይ ማክበርን በተመለከተ ይህን ሙስሊሞች በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ወደ እሱ ፊታቸዉን የሚያዞርበትን ቦታ ማክበር በሶላት ብቻ የተወሰነ አይደለም ፡፡ በቦታም የተወሰነ ሳይሆን ሁልጊዜም በየትኛዉም ቦታ ሊኖር የሚገባ ጉዳይ ነው ፡፡ ማንም ሰው ይህን
156
ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይበህ 1/151. ጦበራኒ አልባኒ ትክክለኛ ነው ብለዋል፡ 158 ሱነኑል ኩብራ በይሀቂ 1/92159 ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይበህ 1/150. 157
.
97
ክብር በመንፈሱ ዉስጥ ማስታወስ ሁልጊዜም ይህን መልካም ስርዐት ምራቅ መትፋትን በመሰለ ተራ ነገር እንኳን ሳይቀር እንዲጠነቀቅ ያደርገዋል፡፡ ነቢዩ ሁዘይፈቱል የማኒ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ምራቁን ወደ ቂብላ የተፋ ሰው በትንሳኤ ዕለት የተፋው ምራቅ በሁለት አይኖቹ መካከል ሁኖ ይቀሰቀሳል160›› ብለዋል፡፡ ምራቅ ለራሱ ንፁህ ቢሆንም መትፋት የመናቅ ምልክት ነዉና ነው፡፡ ቂብላ ደግሞ የተከበረ ነው ፡፡ በመሆኑም እያወቀ ወደ እሱ መትፋት በፍፁም የተከለከለ ነው፡፡161 ይህ ህግ በመስጂድም ሆነ ከመስጂድ ዉጭ የተጠላ ነው ፡፡ ሆኖም በመስጂድ ዉስጥ ሲሆን የበለጠ የተጠላ ለመሆኑ አከራካሪ አይደለም ፡፡ ከዚህ በበለጠ ደግሞ የሚያስከፋው በሶላት ዉስጥ ሲሆን ነው ፡፡162 1-ቂብላ በአላህ ዘንድ ያለው ከፍተኛ ቦታና ልዩ ማዕረግ፤ 163 2-የሙስሊሞችን ቂብላ በምንም ምክኒያት ማዋረድ የተከለከለ መሆኑን፤164 3-ወደ ቂብላ ሆን ብሎ ለተፋ ሁሉ የተለየ ቅጣት መኖሩን፤ 4-የስራው ዉጤት ነው ፡፡ ቂብላን ያዋረደ ሁሉ በህዝብ ፊት ይዋረዳል፤ 5-ወደ ቂብላ መቅጣጨት ይህን ያህል ከተከለከለ ከዕባን ራሷን በተለይ መቅጣጨት ከዚህ የባሰ ክልክል መሆኑን፤ 6- ይህ ህግ የሚመለከተው በትክክል አቅጣጫዉን አውቆ በማን አለብኝነት ለሰራው ሰው ብቻ መሆኑንም እንማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ለከዕባ ይህን ያክል ታላቅ ክብር እንዳው የሚያመለክተው ብዙ ማስረጃ አለው ፡፡ ከእነዚህም አንዱ ነቢዩ ﷺራሳቸው ወደ በይተል መቅዲስ እየሰገዱ በነበሩበት ዘመን ወደ እሱ ለመዞር በጣም መናፈቃቸው ብቻ በቂ ነው፡፡ አላህ እንዲህ አለ ‹የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ ተመልክተናል ፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርልሀለን ፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር › አል-በቀራህ 144
160
አቡዳዉድ የዘገበው አልባኒ ትክክለኛ ነው ያለው ነው፡፡…… ዙርቃኒ 1/556. 162 ፈትሁልባሪ 1/606.፣ዑምደቱልቃሪ4/150. 163 ፈትሁልባሪ 1/508. 164 ፈትሁልባሪ 1/508. 161
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ቀታዳህ ይህን አንቀፅ ሲያብራራ ‹ነቢዩ ﷺወደ በይተል መቅዲስ እየሰገዱ በነበረበት ወቅት ወደ መካ መዞርን ይመኙ ነበር ፡፡ ከዚያም አላህ ወደ እዝያው ወደ ተመኙት አዞራቸው› ብለዋል ፡፡ 165 19ኛ የሙስሊሞች በህይወትም ሆኑ ሙተው የሁል ጊዜ ቂብላቸው የሆነው አላህ በሙስሊሞች ላይ በቀንና በሌሊት አምስት ወቅት ሶላቶችን ደንግጓል፡፡ በዚህች ዐለም ላይ አንዲት ሰከንድ እንኳን ሰዉነቱንም ሆነ አዕምሮዉን ወደ ዚህ መስጂድ አዙሮ ለአላህ ሰጁድ ወይም ሩኩዕ የማይደረግባት ሰከንድ የለችም፡፡ ኢብኑ ዐብዱል በር የተባለ ዐሊም ‹‹ መካ ሌላው ቀርቶ ያ ! ለህዝቦች ወንጀል ማራገፊያና ማስማሪያ እንዲሆን በእድሜያቸው አንድ ጊዜ እንዲጎበኙት ያዘዛቸው፤ ከማንም ሶላትን ወደ እሱ ካል ዞራችሁ በስተቀር ፈፅሞ አል ቀበላችሁም ያለው የአላህ ቤት በሱ ዉስጥ መኖሩ ብቻ በቂ ነው166››ብሏል፡፡ ይህ ቤት ለሙስሊሞች በህይወትም ሆኑ ሙተው የሁል ጊዜ ቂብላቸው ነው›› ብሏል፡፡ ነቢዩ ኡሳመት ብን ዘይድ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ከነቢዩ ጋር ወደ ከዕባ ገብቸ ነበር እናም እንደገቡተቀመጡ አላህን አመሰገኑ አወደሱት አላህ አክበር ላኢላሃ ኢለሏህ አሉ ከዚያም ወደ ቤቱ ልባቸዉን አስጠግተው እጃቸዉንና ጉንጫቸዉን እሱ ላይ አስቀምጠው አላህ አክበር ላኢላሃ ለሏህ አሉ ፡፡ ዱዓም አደረጉ፤ ይህን አይነት ተግባር በአራቱም አቅጣጫ ካደረጉ በኋላ ወጥተው እበሩ ላይ ወደ ቂብላ ዙረው ቆሙና ይህ ነው ቂብላ ፡፡ ይህ ነው ቂብላ አሉ 167›› ብለዋል፡፡ ኡሳማህ ስለ መካ ማክበር እንዴት እንደሆነ ከፍተኛ ትምህርተ ዘግቦልናል፡፡ ነቢዩ በከዕባ ዉስጥ በገቡበት ሰዐት ምንምን እንደሰሩ አትኩሮ በመመልከት ወዲያው እነደገቡ አላህን ማውደሳቸወን ፤ ከዚያም የቤቱን ግርግዳ በአራቱም አቅጣጫ በመያዝ አላህ እያመሰገኑ ዱዓ እንዳደረጉ ፤ ከዚያም ወጥተው ወደ አሱው በመዞር ቆሙና ‹ይህ ነው ቂብላ ፡፡ ይህ ነው ቂብላ አሉ › ብሎናል ፡፡168 1-ሱሃቦች ነቢዩን ለመከተል የነበራቸው ጉጉት ምን ያክል እንደነበር፤ 165
ተፍሲሩ ጦበሪ3/172. ኢስቲዝካር2/465. 167 አህመድ ፤ነሳኢ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ትክክል ነው ብለዋል፡፡ 168 የሙስሊም ሸርህ 9/87. 166
.
99
2-ወደ ከዕባ መግባት የሚፈቀድ መሆኑን፤ 3-የከዕባዉን ዉስጡን ይዞ አላህን መለመን ተገቢ መሆኑን፤ 4-መስጂደል ሐራም ላይ ያለ ሁሉ የከዕባን መቅጣጨት ተገቢ መሆኑን እንማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ሰለፎች ሁልጊዜም ቢሆን የአላህን ፍራቻ ያስታዉሱ እንደነበር በተለይም በዚህ ቤት ዉስጥ ሁነው፡፡ በአላህ ላይ ያለቸው ተስፋ ይጠነክራል ዱንያን ይንቋታል፡ ፡ ከአላህ ዉጭ ያለን ግንኙነት ሁሉ ያቋርጣሉ፡፡ በዚህ አይነቱ ከተወሩ ጠቃሚ ነገሮች መካከል ሒሻም ብን ዐብዱል መሊክ ወደ ከዕባ ገብቶ ሳሊም ብን ዐብደላህን አጠገቡ አገኘውና ሳሊም ጉዳይ ካለህ ጠይቀኝ አለው ሳሊም ግን በአላህ ቤት ዉስጥ ሁኜ ሌላን መጠየቅ እፈራለሁ አለው ፡፡ ሲወጣ ተከትሎት ወጣና እሺ አሁን ወጥተሃልና የምትፈልገዉን ጠይቀኝ አለው፡ ፡ ሳሊምም የዱንያ ጉዳይ ነው ወይስ የአኺራ አለው; የዱንያ ነው እንጂ አለው ፡ ፡ ሳሊምም ዱንያ ከባለ ንብረቱ ከአላህ እንኳን ጠየቄ አላውቅም እንዴት ከማያዝዝባት እጠይቃለሁ አለው ፡፡ 169 20ኛ መካ ምንጊዜም ጎብኚ አታጣም ከማክበር ምልክቶች መካከል የሚከበረዉን ነገር በሆኑ መለያዎች መለየት ነው ፡፡ መካም ከምድሮች ሁሉ ምርጥ በመሆኑ ብዙ መለያዎች አደረገለት ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዋናው ይህን የተከበረዉን ቤት በዉስጡ ማድረጉ እና በየትኛዉም ጊዜና በተፈለገ ሰዐት እንዲጦዎፍ መፍቀዱ፤ ከዚያም ሶላት በተከለከለበት ሰዐትም ቢሆን መጦዎፍ መቻሉ ነው ፡፡ ስለዚህ ማንም ሙስሊም በፈለገው ሰዐት መጦዎፍና የጦዋፉን ሁለት ረከዓ መስገድ ይችላል ፡፡ ኢብኑ ዑመርና ኢብኑ ዐባስ ከዐስር በኋላ ጦዉፈው የጦዋፉን ሁለት ረከዓ ሰግደዋል170 ፡፡ ነቢዩ ﷺጁበይር ብን ሙጥዒም በዘገቡት ሐዲስ ‹የዐብዱ
169 170
አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂሩል ዒልሚ.1/384. ሙሰነፍ ብን አቡ ሸይበህ 3/563. الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
መናፍ ልጆች ሆይ ! በዚህ ቤት ዙሪያ የጦዎፈን ሰው በየትኛዉም ሰዐት-ማለትምሌትም ሆነ ቀን ቢሰግድ እንዳትከለክሉ 171›› ብለዋል፡፡ የመካ ኗሪዎችና ጎብኚዎች ሁልጊዜም የጦዋፍ ፤ የሶላት፤ እድላቸዉን መጠቀም ተፈቀዶላቸዋል ፡፡ ማንም ከጦዋፍ በመቃሙ ኢብራሂም አጠገብ መስገድ አይከለከልም ፤ ይህ በቤቱ በረካ እንጂ በሌላ ምኪኒያት አይደለም፡፡ ሶላትን በተመለከተ የጦዋፍ ረከዓዎችን ብቻ ነው እንጂ ሌሎች ምንም ምክኒያት የሌላቸዉን ትርፍ ሶላቶችን መስገድ የተከለከለ ነው የሚለዉን ነው ፡፡ 172 1-በከዕባ ዙሪያ በየትኛዉም ሰዐት ቢሆን ጦዋፍ መፈቀዱን ፤173 አንደ ዐብዱል ሐይ ለክነዊ የተባለ የሐነፊ መዝሀብ ተከታይ የሆነ ዐሊም‹‹የመሰናበቻ ጦዋፍ አድርጌ በመቃሙ ኢብራሂም አጠገብ ለሰግድ ስል አስጦዋፊዎች ክልክለ ነው አሉኝ ፡፡ እኔ ግን ትክክለኛው ና ማስረጃ ያለው ይቻላልየሚለው ነው ፡፡ ይህንኑ አባባል ሸይኹ ጡሃዊም ደግፈዉታል ለእኛ ደግሞ ይህ በቂ ነው በማለት ሳስታዉሳቸው በጣም ጠቃሚ ነገር ነው ያስተማርከን እስከ ዛሪ ይህን መኖሩን አናውቅም ነበር ብለዉኛል››ይላል ፡፡174 2-የጦዋፍ ሁለት ረከዓዎችን ሶላት መስገድ በተከለከለበት ሰዐትም ቢሆን መሰገድ የሚፈቀድ መሆኑን እንማራለን ፡፡ ይህን አባባል ኢብኑ ዐባስ ፤ ኢብኑዑመር ፤ ኢብኑ ዙበይር ፤ ሻፊዒ፤ አህመድና ሌሎችም የተቀበሉት ነዉና ፡፡175 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ሳቢት ብን ዐብደላህ ብን ዙበይር ከሱብሂ በኋላ ጦዋፍ አድርጎ ሳይሰግድ ሲቀመጥ አባቱ ‹ልጄ ሆይ!ጦዋፍ ካደረክ ስገድ የማትሰግድ ከሆንክ ግን አትጦዉፍ›› በማለት ሶላት በተከለከለበትም ሰዐት ቢሆን እንኳን መተው የሌለበት መሆኑን እንዳስተማሩ ተዘግቧል፡፡176
171
አቡዳዉድ ፤ቲርሚዚ፤ ነሳኢና ኢብኑ ማጀህ የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ነው፡፡ ሚርቃቱል መፋቲህ. 173 ሚርቃቱል መፋቲህ. 174 ሚርቃቱል መፋቲህ. 175 ተምሂድ 176 ሙሰነፍ ብን አቡ ሸይበህ 3/563. 172
.
101
21ኛ ጦዋፍ ማድረግና ሁለቱን ማዕዘናት በእጅ መንካትበመካ የሚፈፀሙ አምልኮታዊ ተግባር ናቸው ፡፡ ወንጀልን ማስማር ሃጢኣት ማሰረዝ የአላህን ዉዴታና የአኺራ ዐለም ከሚመኙ ሁሉ ሰዎች የሚታሰብ ዋና አላማ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ሊጨነቅበት ይገባዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በቤቱ ዙሪያ ላይ መዞር ጦዋፍ ማድረግ፤ሁለቱን ማዕዘናት በእሱ ላይ ዉጥረትና ግፊ ቢኖሩበትም በሌላ ሰዎች ላይ የሚያደርሰው ምንም ችግር ከሌለው በእጅ መንካት የሚሉት ጥቂቶች ናቸው ፡፡ ጦልሓህ ብን ኢስሓቅ ቃሲም ብን ሙሐመድን በእነዚህ ቦታዎች ላይ መጋፋት እንዴት ታየዋለህ ብየ ጠይቄው ‹‹የወንድሜ ልጅ ተጋፋ ዐብደላህ ብን ዑመርን እስከሚነስራቸው ድረስ ሲጋፉ አይቻለሁና›› ብሏል ፡፡ 177 ነቢዩ ኢብኑ ዑበይድ ብን ዑመይር ከአባታቸው ወስደው በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ዐብዱላህ ብን ዑመር በሁለቱም ማዕዘኖች ላይ ይጋፉ ነበር ፡፡ እናም የዐብዱረህማን አባት በሁለቱም ማዕዘናት ላይ ማንንም ከነቢዩ ሱሃቦች ያላየሁትን ግፊ ስትጋፋ አየሁህ አልኳቸውና እሳቸዉም አዎ እጋፋለሁ ምክኒያቱም ነቢዩ ሁለቱን መንካት ወንጀል ያሰርዛል ሲሉና›› በዚህ ቤት ዙሪያ ሰባት ጊዜ የጦወፈ ሰው ባሪያን ነፃ እንደማውጣት ይቆጠራል ፡፡ እና ‹አንድ እግሩን አስቀምጦ ሌላዉን አያነሳም አላህ አንዲት ወንጀልን የሰረዘለትና አንድን መልካም ነገር የፃፈለት ቢሆን እንጂ ሲሉ ሰምቻለሁ178›› ብለዋል ፡፡ ኢብኑ ዑመር የነቢዩን ሱና በመከታተል ይታወቃሉ ፡፡ ለዚህም ነበር በሁለቱ ቦታዎች ላይ ሌላ ሰው የማያድርገውን አንተ ለምን ታደርጋለህ በሚል ሲጠይቁት እሳቸዉም በትክክል መለሱ ፡፡ ይህ አይነት ምክኒያት ያለው ሁሉም የአላህን ዉዴታ የሚመኝ ሁሉ ይጓጓለታል ፡፡ ለዚህ ነው ነቢዩ ሁለቱን ማዕዘናት ለመንካት በጣም ይጓጉ የነበሩት ፡፡ ኢብኑ ዑመር ነቢዩ በየጦዋፋቸው ሁሉ ሁለቱንም
177
-ሙሶነፍ ብን አብዱ ረዛቅ5/35……… ቲርሚዚ፤ኢብኑ ማጀህ ፤ኢብኑኹዘይመህና ሓኪም ዘግበዉታል፡፡ አልባኒም ትክከል ነው ብለዋል፡፡ 178
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ማዕዘናትን ሰላም ማለትንአይተዉም ነበር›› ናፊዕም አብዱላህ ኢብኑ ዑመርም እንዲሁ ይሰሩ ነበር›› ብሏል179፡፡ 1-ሁለቱን ማዕዘናት መሳለምና ከተቻለ በእጅ መንካት ያለዉን አጅር፤180 2-በከዕባ ዙሪያ ጦዋፍ ማድርግ ያለዉን ከፍተኛ አጅር መጠቆም፤181 3-ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ ሁለቱም ማዕዘናት ላይ ግፊ የተፈቀደ መሆኑን፤ 4-ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ሱናን በመከታተል የነበራቸዉን ጥንካሬ፤ 5-ለመካ ኗሪዎች ሁሉ ዐብዱላህ ብን ዑመር አርአያሊሆኗቸው እንደሚገባ፤ 6-በመካ ሲኖሩ ጊዜን በዒባዳ ላይ ለማሳለፍ መሞከር የታላላቅ ሰዎች ተግባር መሆኑን ነው ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ከእንቁየ ሞዲሎቻችን ነቢዩ በሀጀተ-ልወዳዕ ጊዜ በሚና ቀናት ሁሉ በየሌሊቱ ወደ መካ እየሄዱ ጦዋፍ ያደርጉ እንደነበር የተዘገበው ዋናው ነው182፡፡ -ሱሃቦችም ቢሆኑ በመካ እስካሉ ድረስ ጦዋፍ ያበዙ ነበር ፡፡ ‹ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ሌሊት ብቻ ሰባት ቀን አምስት ጦዋፍ ያደርጉ ነበር› ተብሏል፡፡183 -እናታችን ዓኢሻህ ሶስት ጦዋፍ በተከታታይ ያደርጉና ለእያንዳድዱ ጦዋፍ ሁለት ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር፡፡ -ከሱሃቦች መካከል በመካ ዒባዳን በማብዛት የታወቀው ዐብዱላህ ብን ዙበይር ነበር በዚህ ጉዳይ ወደር የለዉም እስከሚባል ድረስ ፡፡ አዎ እሱ እንደተባለው ነው ፡፡ ማንም ሰው በዋና ከዕባን የጦወፈ እሱብቻ ነው ፡፡ ይኸዉም አንድጊዜ ከፍተኛ ጎርፍ መጥቶ ሰዉን ሁሉ ጦዋፍ ከልከሎት እሱ ብቻ ጦዋፍ አደረገ ፡፡ ዐጣእ ኢብኑ አቢ ረባህ ‹በመካ አርባ አመት ሲቀመጥ በለሊት ከሶላትና ከጦዋፍ በስተቀር ምንም አይሰሩም ነበር ፡፡
179
ሱነኑ አቢ ዳዉድ 1876. ዑምቱልቃሪ9/240. 181 አሕወዚ3/513. 182 ቡኻሪ. 183 የመካ ታሪክ አዝረቂ1/44. 180
.
103
22ኛ በጦዋፍ ዉስጥ መነጋገር በጦዋፍ ዉስጥ መናገር ቢፈቀድም ተራ ወሬን ማብዛቱ ግን ተገቢ አይደለም 184፡ ፡ ሙስሊሞች በጦዋፍ ዉስጥ ሊናገሩት የሚገባው ዱዓና ዚክር ነው ፡፡ ሻፊዒ ‹‹በጦዋፍ ዉስጥ ደስ የሚለኝ ቁርኣን መቅራት ነው ፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች ከተናገሩት ሁሉ የተመረጠው ተግባር ነው›185 ብለዋል ፡፡ ነቢዩ ኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹በከዕባ ዙሪያ መጦወፍ ልክ እንደ ሶላት ነው ፡፡ ባይሆን በጦወፍ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ እንጂ ፡፡ እናም በጦወፍ ወቅት የተናገረ ሰው መልካም ንግግርን እንጂ ሌላ እንዳይናገር 186› ብለዋል፡፡ በንጉስ ቤት የሚዞር በጣም አስፈልጎት እነደሚሆን ምንም ጥርጥር የለበትም፡፡ ታዲያ ልክ እንደ ሶላት ሁሉ በዚህ ሰዐት ከእሱ ሌላ በሆነ ነገር መወጠርና ጊዜን ማሳለፍ ተገቢ አይሆንም ፡፡ ሆኖም በአላህ ችሮታ ከሌላ ጋር ማውራቱ ተፈቀደ ፡፡ ስለዚህ ይህንን ኒዕማ በማስወታወስ ልናመሰግነው ይገባል ባልሆነ ጋጠ ወጥ ንግገርም ልናሳልፈው አይገባም፡፡ 1-የጦዋፍን ትልቅነት በሶላት በመመሰል ማሳየት፤ 2-በጦዋፍ ዉስጥ ዱዓ ማድረግ ዚክር ማብዛት ተገቢ መሆኑን 3-በኸይር ከሆነ በጦዋፍ ዉስጥ መነጋገር መፈቀዱን፤187 4-ብዙ ዐሊሞች ዘንድ ይህን ሐዲስ ማስረጃነት በመጥቀስ ዉዱእ ለጦዋፍ ግድ ነው ማለታቸውን እንማራለን፡፡188 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሰለፎች በጦዋፍ ላይ ከመነጋገግር ምንጊዜም አላቆሙም፡፡ ኢብራሂም ብን ናፊዕ የተባለ ‹‹ጧዉስን በጦዋፍ ላይ እያለ አናግሬው መልሶልኛል ››ብሏል፡፡189 184
በተለይም በሞባይል ከሐረም ዉጭ ከሆነ ሰው ጋር ማራቱ በጣም አስቀያሚ ነው
፡፡ 185
ዑምደቱልቃሪ9/263. የሐዲሱ ደረጃው ቲርሚዚ፤ ነሳኢ፤ ኢብኑኹዘይማህና ሓኪም ዘግበዉታል ፡፡ አልባኒም ኢርዋእ ላይ ዘግቦታል፡፡ 187 -ዑምደቱልቃሪ 9/263. 188 -የኢብኑ ማጀህ ሸርህ1/209. 189 ዑምደቱልቃሪ 9/263. 186
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
እዚህ ላይ ከሚነገሩ ምርጥ ታሪኮች መካከል ፈዷለት ብን ዑበይድ የሰለመበትን ምክኒያት ሲናገር ያወራው ነው፡፡ ፈዷለት፡- መካ የተከፈተ ቀን ነቢዩን በጦዋፍ ላይ እያሉ ለመግደል አስቤ አጠገባቸው ስደርስ ነቢዩ ፡- ፈዷለት፡ ነህ አሉኝ ፈዷለት፡- አዎ ያ አላህ መልዕክተኛ ነቢዩ ፡- ምን ነበር የምታወራው ፈዷለት፡- ምንም አልነበረም አላህን አወሳ ነበር፡ ፡ ነቢዩ ሳቅ አሉና አላህን ምህረት ጠይቀው አሉኝና እጃቸዉን ደረቴ ላይ አድርገው ገና ሳያነሱት አላህ ከፈጠራቸው ሁሉ ይበልጥ ወደደኳቸው› ያለው ፡፡ 190
190
ኢብኑ ሐሻም5/80. .
105
23ኛው ባሪያን ነፃ እንደማውጣት ይቆጠራል በአላህ ዘንድ ታላላቅ ስራዎች ከሚባሉት ነገሮች መካከል ባሪያን ነፃ ማውጣት ነው ፡፡ ምክኒያቱም ይህ ተግባር የሰዉን ልጅ ከባርነት ቀንበር ወደ ነፃነት ሜዳ ማውጣት ነዉና፡፡ ይህን ተግባር ደግሞ የሚችለው ባለ ሀብት ብቻ ነው፡፡ በመካ የሚሰሩ መልካም ተግባሮች ግን ሰባት ጊዜ ከዕባን መዞር ልክ ባሪያን ነፃ እንደማውጣት ይቆጠራል፡፡ ለዚህ ሲሉ ነበር ሰለፎች በጦዋፍ ላይ ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ከተዘገቡት አስገራሚ ታሪኮች መካከል ‹‹ነስር አልሐምዳኒ የተባለው ሰው ‹በየቀኑ ሰባ ጊዜ ጦዋፍ ያደርግ ነበር › ፡፡ 191 ነቢዩ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑበይድ ብን ዑመይር በዘገቡት ሐዲስ ‹‹አንድ ሰው ለዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ሁለቱን ማዕዘናት እንጂ ሌላዉን ሰላም አትሉምሳ ሲሏቸው ነቢዩ ሁለቱን ማበስ ወንጀል ያራግፋል ›› ‹‹ሰባት ጊዜ ጦዋፍ ያደረገ ሰው ባሪያን ነፃ እንዳወጣ ነው የሚቆጠረው ሲሉም ሰምቻለሁ192›› ብለዋል፡፡ በቸሩ ጌታ በአላህ ዘንድ ሽልማቶች አሉ ፡፡ ሰባት ጊዜ በመዞር ብቻ ባሪያን ነፃ እንደማውጣት ይቆጠራል ፡፡ ሁለቱን ማዕዘናት በመንካት ወንጀሎች ይታበሳሉ፡ ፡ 1-ሁለቱን ማዕዘናት በመንካት ያለው አጅር፤ 193 2-ሁለቱ ማዕዘናት ብቻ በመንካት የተለዩ ሐጀረል አስወድ ብቻ በመሳም የተለየ መሆኑን፤194 3-ከሁለቱ ሌላ ያሉትን ማዕዘናት መንካት ተገቢ አለመሆኑን፤195 4-መካ የብዙ ኸይር ነገር ሀገር መሆኗን፤ 5-የአላህ ረህመት ሰፊ መሆኑን፤ 6-የመካ ሰዎች አላህ ያደላቸዉን እድልማስታወስ እንዳለባቸው ነው፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ 191
ዒቅድ ሰሚን7/333. የሐዲሱ ደረጃው ቲርሚዚ…… 193 ዑምደቱልቃሪ 9/240. 194 ፈትሁ ል ባሪ3/475. 195 ተም ሂድ፤ፈትሁ ል ባሪ3/474፤ዑምደቱልቃሪ 3/27. 192
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ሰለፎች በተለይም በየጊዜው ለመምጣት ወቅት የሌላቸው ሰዎች በመካ እስካሉ ድረስ ጊዚያቸዉን ማሳለፍ ያለባቸው በጦዋፍ ላይ መሆኑ እንደሚገባ፤ ለምሳሌ ሃሮኑ ረሺድ መካ ሲሄድ አስርን ሰግዶ እስከ መግሪብ ድረስ ጦዋፍ ላይ ነበር ፡ ፡ ኢብኑ ሸቢብ የተባለ ሰው ሃሮኑ ረሺድን ከአስር ሶላት እስከመግሪብ ሶላት ድረስ አስራ ስድስት ጦዋፍ ቁጥሬለታለሁ ፡፡ ያዉም በየሁለቱ ጦዋፍ ሁለት ፤ ሁለት ረከዓ እየሰገደ ነበር 196) ብሏል ፡፡ ኢብኑ ዐባስ ከሙዓዊያህ ጋር ጦዋፍ አድርገው ሙዓዊያህ በአራቱም ማዕዘናት ላይ ሰላም ሲል ኢብኑ ዐባስ ይሕ አይሆንም አሉት ፡፡ ምክኒያቱም ነቢዩ ከሁለቱ በስተቀር ሰላም አላሉምና ነው አሉት ፡፡ ሙዓዊያህ ከዚህ ቤት የሚተው ነገር ምንም የለም አለ ፡፡ ኢብኑ ዐባስ ቁርኣን ‹ለእናንተ በነቢዩ መልካም አርአያ አለላችሁ› ብሏል› ሲሉት እውነትህን ነው አላቸውና ከዚያ ተግባሩ ተመለሰ፡፡197 ሰለፎችም የተጓዙት በዚሁ መንገድ ላይ ነው ፡፡ ዐጣእ ሼኾቻችንን ማለትም ኢብነ ዐባስን ጃቢርን፤ አቡሁረይራን ፤ ዑበይድ ብን ዐመይርን፤ ያገኘነው ሁለቱን ማዕዘናት ብቻ ሰላም ሲሉ ብቻ ነው198›ብለዋል፡፡ 24ኛ በሐጀረል አስወድ ላይ የታየው ልዩ ተአምር ቤቱ እየተገነባ ሲያድግ ቁመቱና ሐጀረል አስወድ ያለበት ቦታላይ ሲደርስ ኢብራሂም ለልጃቸው ለኢስማዒል እንዲህ አሉት ‹አንድ ዲንጋይ ፈልግልኝ ለሰዎች በጦዋፍ ጊዜ ለመጀመሪያ ምልክት እንዲሆናቸው ፡፡ ኢስማዒል በመፈለግ ላይ እያለ በቤቱ ዙሪያ ካሉት ከአላህ ተዐምራት አንዱ ይሆን ዘንድ መላኩ ጂብሪል ከጀነት ይዞት ዱብ አለ199 ‹ለሰዎች ማምለኪያ ይሆን ዘንድ መሬት ላይ በመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በመካህ (በመካ) ያለው ቤት ካዕባ ነው ፡፡ በውስጡ ግልፅ የሆኑ ተዐምራቶች አሉበት › -ኣሊ ዒምራን 96-97. ነቢዩ ኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹ሀጀረል አስወድ ከጀነት ሲወርድ- የሰዎች ወንጀል አጠቆረው እንጂ -ከወተት የነፃ ነበር200›› ብለዋል፡፡ 196
የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ2-/303-304.-ጦበራኒ3/17. 198 ሙሰነፍ ብን አቢሸይበህ. 199 ዋናዉን ሐዲስ ሓኪም 2/293 ላይ ዘግቦታል፡፡ዘሀቢም እንዲሁ፡፡ 200 የሐዲሱ ደረጃው አህመድ …… 197
.
107
የአደም ልጆች ወንጀል አጠቆረው ማለት የአደም ወንጀል ለመጥቆሩ ምክኒያት ሆነ ማለት ነው ፡፡ ይህም ማለት እውነታ ነው ፡፡ 201 አነስ ብን ማሊክ ‹‹ ድንጋዩ ከጀነት ድንጋዮች አንዱ ነው፡፡ ብለዋል፡፡202 ዐብዱላህ ብን ዐምር ‹‹ድንጋዩ ከጀነት ነው የወረደው ሲወርድ ከበረዶ የነጣ ነበር ፡፡ ያጠቆረው የሰዎች ወንጀል ነው›› ብለዋል ፡፡203 የሰዎች ወንጀል ድንጋዩ ላይተፅዕኖ ማሳደር መቻሉ ተዐምር ነው ፡፡ አልመሒቡ አጦበሪ የተባሉት ዐሊም ‹‹ እስካሁን ድረስ ጥቁር ሁኖ መቅረቱ አይን ላለው ሰው ሁሉ ተዐምር ነው፡፡ ምክኒያቱም ወንጀል በድንጋይ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ከቻለ በሰዎች ልብ ላይማ ይበልጥ ነው አቅም ያለው ማለት ነው ›› ብለዋል ፡፡204 ይህ ጥቁረት ላይኛዉን ክፍል እንጂ ዉስጡ አሁንም ነጭ ነው ፡፡ ሐዲሱም የሚያሳየው ይህንኑ ነው ፡፡ ሙጃሂድ ብን ጀብርም ‹‹ዐብዱላህ ብን ዙበይር ባፈረሱት ጊዜ ተመልክቻለሁ በቤቱ ዉስጥ ያለው የድንጋዩ ክፍል ነጭ ነው ብሏል›› 205 ሙሐመድ ብን ናፊዕ አል ኹዛዒ‹‹ ድንጋዩ ተነቅሎ በነበረበት ጊዜ ሳየው ጫፉ ብቻ እንጂ ሌላው ነጭ ነበር ፡፡ እርዘመቱም አንደ ክነድ ያክል ነው ፡፡206 1-ከጀነት የመጣን ድጋይ በዉስጡ በማድረግ ስለ መካ ትልቅነት መግለፁን፤ 2-ሐጀረል አስወድ ከጀነት የመጣ መሆኑን ማመን አስፈላጊነቱ፤ 207 3-ወንጀል በዲንጋይ ላይ እንኳን ምን ያክል መለወጥ እንደቻለ፤208 4-ዲንጋዩን ጥቁር ድንጋይ ማለት የሚቻል መሆኑን፤ 5-ዲንጋዩን የወንጀለኞች ጥፋት እንዳጠቆረው ሁሉ የዐቢዶቹ እጅ እሱን ማንጣት ግዴታ እንዳልሆነ እና ምን አልባትም ጠቁሮ የመቆየቱ ፋይዳ የተንሳኤ ዕለት በከሃዲያን ላይ ሊመሰክር ሊሆንም እንደሚችል እንማራለን ፡፡209 201
አህወዚ 3/525. ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይበህ3/706. 203 ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይበህ3/706. 204 ፈትሁል ባሪ 3/463. 205 የነካ ታሪክ ፋኪሃኒ1/92. 206 ታሪኹል ለፋእ ሱዩጢ345. 207 አህወዚ3/525. 208 ፈትሁልባሪ3/541. 209 ፈይዱል ቀዲር4/713. 202
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
25ኛ ዲንጋዩ ሲመሰክር በዚያ የጭንቅ ቀን ይህን ታላቅ የምስክርነት ቃል ለማገኘት ሲባል ሰለፎች ዲንጋዩን ለመሳለምና በእጃቸው ለመንካት ከተቻለም በአፋቸው ለመሳም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህም ነቢዩን ለመከተል የሚያድረጉት ጥረት ነው፡ ፡ ነቢዩ ኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ‹ይህ ዲንጋይ የተሳለሙትን የሚያይባቸው ሁለት አይኖች፤ የሚናገርበት ምላስ አሉት፡፡ በትክክል ለተሳለመው ሰው ሁሉ ይመሰክራል210› ብለዋል፡፡ ይህ ዲንጋይ በዚህች ዐለም ዉስጥ ሳለ በትክክል ከጀነት የመጣ ነው ፤ እሱን መንካትም ሆነ መሳሙ ለአላህ ከሚደረጉት ዒባዳዎች አንዱ ነው ብሎ አምኖ ለተሳለመው ሰው ሁሉ የቂያማ ዕለት ይመሰክራል ፡፡ ‹ይህ ድንጋይ የተሳለሙትን የሚያይባቸው ሁለት አይኖች፤ የሚናገርበት ምላስ አሉት ፡፡ በትክክል ለተሳለመው ሁሉ ትክክለኛ አማኝነታቸዉን ይመሰክራል፡፡ 1-የዚህን ዲንጋይ ትልቅነትና የዘያሪው ሰውን ትልቅነት፤ 2-አላህ ለዲንጋዩም ቢሆን አይንም ሆነ ምላስ መሰጠት የሚችል መሆኑን፤211 3-በዚህ ሐዲስ ዉስጥ የተወሱትን ሁሉ በሀቂቃነታቸው ማመን፤212 4-የዚህ ቤት ጉዳይ በጣም የከበደ መሆኑን ማወቅ እንዳለብን ነው ፡፡213 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ዑመር ኢብኑልኸጣብ ይህን ዲንጋይ ሳሙትና ‹‹ምንም የማጥጠቅም ና የማትጎዳ ዲንጋይ መሆንክን አውቃለሁ፡፡ ነቢዩ ሲስሙህ ባላየሁኝ ኖሮ አልስምህም ነበር214››አሉ፡፡ ዐሊይ ዲንጋዩን ሲሳለሙ‹ጌታየ በአንተ አምኜ በኪታብህ ሲድቅ ብየ፤የነቢዩን ሱና ተከትየ› ይሉ ነበር215፡፡
210
የሐዲሱ ደረጃው አህመድ…… ሚርዓቱል መፋቲህ9/111.212 ፈይዱል ቀዲር5/439. 213 አህወዚ4/31 . 214 ቡኻሪ 1597. 215 ኢትሃፉ ል ኺብረቲ 3/189. 211
.
109
26ኛ ዲንጋዩን በእጅ መንካትና በአፍ መሳም ነቢዩ ዲንጋዩን ለመሳለም በጣም ጉጉት ነበራቸው ፡፡ ወደ እሱ መድረስ ካልቻሉ በእንጨትም ቢሆን ይሳለሙት ነበር ፡፡ አቡ ጡፈይል ‹‹ነቢዩ በከዕባ ሲዞሩ ዲጋዩን በዘንጋቸው ነክተው ያን የነኩበትን ዘንግ ሲስሙት አይቻለሁ፡፡››216 ነቢዩ ዙበይር ብንዐረቢ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹አንድሰው ዐብዱላህ ብን ዑመርን ዲንጋዩን መሳለም እንዴት ነው ብሎ ጠየቀ ነቢዩ ሲሰልሙትና ሲስሙተ አይቻለሁአሉ ግፊ ቢኖርስ ተብለው ሲጠየቁ ቢሆንስ የሚለዉን የመን ላይ ተወው እኔ የምልህ ነቢዩ ሲሰልሙትና ሲስሙት አይቻለሁ ነው የምልህ አሉ217›› ብለዋል፡፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ሱናን ለመከተል የተለያዩ ምክኒያቶችን እየደረደሩ ማመካኜት እንደማይቻል ፡፡ ግልፅ ትምህርት ሰጥተዋል ፡፡ ሆኖም ግፊ ካለ መተዉ አማራጭ እንደሌለው ጥያቄ የለዉም ፡፡ 1-ዲንጋዩን ሰላም ማለትና መሳሙ ተገቢ መሆኑን ፤ 218 2-ሁላችን ሸሪዓዊ ማስረጃዎች ሲነገሩን አሚን ብለን መቀበል እንዳለብን፤ 219 3-የነቢዩ ተግባራት በቂ ማስረጃ መሆኑን፤ 4-ዲንጋዩን ስንስም ድምፅ እንደማያስፈልግ፤ 5-አቅሙ ለቻለ ሰው ሁሉ በሀጅ ጊዜ መሳሙ ካልቻለም መንካቱ ከሐጅ ሱናዎች አንዱ እንደሆነ እንማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ
ዐብዱ ረህማን ብን ዐውፍ ወደ ዲንጋዩ አጠገብ ሲደርሰ ግፊት ሲያይ በትክከሉ ቆም ብሎ አላሁ አክበር ብሎ ዱዓ አድርጎ ነበር የሚጓዘው 220 ፡፡ ታዲያ ነቢዩ እንዴት ነው የምታድርገው ብለዉት ሲነግራቸው ጥሩ ነው ያደረከው ብለዉታል221፡፡ 216
ሙስሊም›1275. የሐዲሱ ደረጃው ቡኻሪና ሙስሊም…… 218 የሙስሊም ሸርህ ነወዊ9/15. 219 ዑምደቱ ል ቃሪ9/256. 220 የመካ ታሪክ -አዝረቂ. 221 የመካ ታሪክ - ፋኪሂ1/126. 217
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
27ኛ ዲንጋዩን በመሳም ላይ ከፍተኛ ጉጉት ማሳደር የነቢዩ ባልደረቦች በጣም የነቢዩን ሱና በህይወታቸው ላይ ለመተግባር ግንባር ቀደም ነበሩ ፡፡ ሌላው ህዝብም ከእነሱ ነው የወረሰው ፡፡ የዚህን አውቀትና ትምህርትም ከእነሱ ነው የወሰዱት ፡፡ ነቢዩ ናፊዕ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ኢብኑ ዑመር ዲንጋዩን በእጃቸው ሰላም ብለዉት እጃቸዉን ሲስሙት አየሁ ፡፡ ከዚያም ይህን ተግባር ነቢዩን ካየሁኝ በኋላ ሁልጊዜም ትቸው አላውቅም 222›› ብለዋል፡፡ ሐዲሱ ድንጋዩን በተመለከተ በጣም ክብር እንዲስጠው ማግባባት ዋናው መልዕክት ሲሆን ኢብኑ ዑመር ነቢዩ በጣም እሱን በመሳለም ከፍተኛ ጉጉት ስላየሁባቸው እኔም ከዚያን ቀን ጀምሬ አልተውኩም፡፡ 1-የዲንጋዩ ትልቅነትና እሱን በእጅ ሰላም ማለትም ከተቻለ እጅን መሳም ተገቢ መሆኑን፤ 2-አቅም በፈቀደ ያክል ማንኛዉም ሙስሊም ይህን ሱና ችላ ሊለው እንደማይገባ፤ 3-የኢብኑ ዑመር ሱናን በቲኒሽ በትልቁ መከተል መውደዳቸዉን እማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ የሐዲስ መፅሐፍት ሰለፎች ይህን ዲንጋይ በመሳም፤ በመንካት ዙሪያ ከፍተኛ ዘገባዎችን ዘግበዉልናል ፡፡ ከእነዚህም መካከል ኢብኑ ጁረይጅ ለዐጣእ ከነቢዩ ሱሃቦች ዲንጋዩን በእጃቸው ነክተው እጃቸዉን ይሰሙ ነበርን በማለት ጠየኩት ፡፡ አዎ ጃቢርን ፤ ኢብኑ ዑመርን፤አቡ ሰዒድን ፤ አቡሁረየራን በእጃቸው ሰላምታ ብለው እጃቸዉን ሲስሙ አይቻለሁ አለ ፡፡ ኢብኑ ዐባስስ ብየ ስጠይቀው አዎ እሱም አለኝ›› ብሏል223፡፡ ሒሻም ብን ዑርወት አባቴን በእጁ ሰላም ብሉ እጁን ሳይስም አላየሁም 224›› መዕመር‹‹ማንንም ሰው እጁን ሲስም ነው ያየሁት ፡፡ ሰዎችንም በዚሁ ላይ ነው ያገኘናቸው ›‹‹ አዩበሰኽቲያኒን በእጃቸው ሰላም ካሉ በኋላ እጃቸዉን ሲያብሱ ተመልክቻለሁ››ብለዋል ፡፡ 225
222
ሙስሊም1268. ሙሶነፍ ብን አቢ ሸይበህ3/768. 224 ሙሶነፍ ብን አቢ ሸይበህ3/768. 225 ሙሶነፍ ዐብዱረዛቅ5/42. 223
.
111
28ኛ ዲንጋዩን በመንከባከብ ላይ ሊጠበቅ የሚገባው ጉዳይ ዲንጋዩን መሳለምና በየጦዋፉ ጊዜ ማስታውስ ከመልካም ስራዎች አንዱ ነው ፡፡ ሙጃሂድና ጣዉስ ሁለቱንም ማዕዘናት በየ ነጠላ ቁጥሩ ሰላም ማለትን ይወዱ ነበር፡፡ ዐሊሞችም ዘንድ የሚተገበረው በዚሁ አይነት ነው ፡፡ ማለትም በየጦዋፉ ከቻሉ ዲንጋዩን መሳም፤ ካልቻለ በእጁ መንካትና እጁን መሳም፤ በየጦዋፉ ካልቻለ በየነጠላ ቁጥሩ ላይ እጁ መድረስ ካልቻለ እንኳን በአቅጣጫው ላይ ሁኖ አላሁ አክበር በማለት ሰላም ማለት ተገቢ ነው ፡፡ ሱወይድ ብን ገፈለህ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ኢብኑ ዑመር ዲንጋዩን ሰላም ብለው ሲያቅፉትና ነቢዩ በጣም ስለ አንተ ሲጨነቁ አይቻለሁ አሉ 226›› ብለዋል፡፡ ሱሃቦች ምንንም ነገር የሚያከብሩት ነቢዩን ብቻ ተከትለው መሆኑን ነው፡፡ 1-የዲንጋዉን ትልቅነት፤ 2-ዲንጋዩን መሳምና ማቀፍ ተገቢነቱን፤ 3-ዲንጋዩን ማክበርና መንከባከብ ተገቢ መሆኑን፤ 4-ዲንጋዩን መሳም ነቢዩን መከተል እንጂ እንደ ጣዖት አምላኪዎች ዲንጋዩን ለብቻው አክብረነው አለመሆኑን እንማራለን፡፡ 29ኛ በሒጅር ኢስማዒል ዉስጥ መስገድ
በከዕባ ዉስጥ መስገድ የብዙ ሰዎች ወደ በካ ሲሄዱ የሚመኙት ህልም ነው፡፡ ከህዝብ ብዛት አኳያ ይህ ህልም ለሁሉም በተግባር የመዋሉ ጉዳይ አይታሰብም፡ ፡ በተለይም እኒያ በሐጀረል አስወድ ላይ እንኳን እግፊ ዉስጥ መግባት እንደሌለባቸው ልዩ ምክር የተቸራቸው ሴት ልጆች፡፡ ነቢዩ እናታችን ዓኢሻ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹በከዕባ ዉስጥ ገብቶ መስገድ በጣም እመኝ ነበር ፡፡ አንድቀን ነቢዩ እጀን ያዙና ሒጅር ኢስማዒል የተባለው ቦታ ወሰዱኝና በከዕባ ዉስጥ ገብቶ መስገድካማረሽ እዚህ ስገጂ ምክኒያቱም ይህ ስፍራ የቤቱ አካል ነዉና ፡፡ ዘመዶችሽ ቤቱን ሲያድሱ በጀት ስላነሳቸው ቀንሰዉት ነው ፡፡ አሉኝ….. 227 ›› ብለዋል፡፡
226
-የሐዲሱ ደረጃው ተምሂድ…… አህመድ አቡዳዉድ….አልባኒም ትክክል ነው ብለዉታል፡፡
227
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ይህ ሐዲስ በከዕባ ዉስጥ ገብቶ መስገድ ለሚፈልግ ሰው ሁሉ ምኞቶችን በአጭሩ የሚያሳካ መልዕክት ይዟል ፡፡ ምክኒያቱም ታሪኩ ከሴት ጋር ስለተያያዘ ለወንዶች አይሆንም አይባልምና፡፡ 1-ይህ ተቋርጦ የቀረው ጅምር ቤት የቤቱ አካል መሆኑን ፤228 እና እሱም ሰባት ክንድ አካባቢ ሊሆን እንደሚችል፤ 229 2-በዚህ ቦታ የሚሰገድ ሶላት በከዕባ ዉስጥ እንደተሰገደ መቆጠሩ ፤ 230 3-ጦዋፍ ሲደረግ ከዚሁ ጅምር ቤት ዉጭ መሆን እንዳለበት ፤ 231 4-በጊዜው የዚህ ቤት ተጀምሮ የመቅረቱ ጉዳይ ዋናው ምክኒያት መኮች ይህን ቤት ለመገንባት ያስቀመጡት ቅድሚያ ሁኔታ በንፁህ ገንዘባቸው መሆን አለበት ብለው ስለነበር ይህን ያሟላ የገንዘብ እጦት እንደነበር ፤ 232 5-ወንድ ልጅ ሚስቱን በዒባዳ ላይ መርዳትና ማበረታታት ተገቢ መሆኑን እንማራለን ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሰለፎች በዚህ ቦታ መሰገድን በከፍተኛ ደረጃ ይመለከቱታል ፡፡ በዚህም ጋር የተያያዘ አያሌ አስገራሚ ታሪኮች ተከስተዋል ፡፡ ለምሳሌ፤1-ዐምር ብን ዲናር አብኑ ዘበይር ሒጅር ዉስጥ አይናቸዉን ደፍተው እየሰገዱ በፊት ለፈታቸው ድንጋይ ተወርዉሮ የለበሱትን ልብስ ግማሹን ይዞት ሲሄድ እንኳን ዘዎርም አላሉም ነበር፡፡ 233 2-ሰዒድ ብን ጁበይር ጦዋፍ በጨረሱ ቁጥር ወደ እዚህ ቦታ ይሄዱና ሶላት ይሰግዳሉ፡፡ 234 -ዐሊይ ብንል ሁሰይንም አንዲሁ ነበሩ፡፡ 3-ሙስሊሞች ይህን ተከትለው ነው እየሄዱ ያሉት፡፡ አንዳንድ የታሪክ መፅሐፍት አልሚስወረብመኽረመህ የተባለው ሱሃቢ በዚያ ኢብኑ ዙበይር ተከበዉበት
228
በገዊ ሸርሁ ሱና ላይ 7/110. ተምሂድ10/50. ፈትሁል ባሪ3/443230 ኢብኑ ዐብዲል በር ኢስቲዝካር ላይ 4/189. 231 በገዊ ሸርሁ ሱና ላይ 7/112. ተምሂድ10/50. 232 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ9/89. 233 አህመድ ብን ሐንበል አዙህድ በተባው መፅሐፍ3/162. 234 ሙሶነፍ ብን አቢ ሸይበህ2/496. 229
.
113
በነበረው የሐጃጅ ጦርነት ላይ በዚሁ ቦታ ላይ እየሰገደ ባለበት በተወረወረ ዲንጋይ ነው ተመቶ የሞተው ይላሉ ፡፡235 ኢብኑ ዐባስ ሰዎች በዚህ ቦታ ላይ መስገድ እንዳለባቸው ‹በምርጦች መሰገጃ ላይ ስገዱ ፤ ከአብራሮች መጠጥ ጠጡ እያሉ ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር፡፡ የምርጦች መሰገጃ የትኛው ነው ተብለው ሲጠየቁም በሚዛቡ ስር ያለው ቦታ ነው፤ የአብራሮች መጠጥስ ምንድነው ሲባሉ የዘምዘም ዉሃ ነው ብለዋል፡፡236 30ኛው ሐዲስ በዲንጋዩ ላይ መደፋት/ሱጁድ ማድረግ ተገቢ ስለ መሆኑ በዲንጋዩ ላይ ሱጁድ ስለማድረግ ነቢዩ የመሰናበቻው ሐጅ ዕለት ወደ መካ ገብተው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሩት ነገር ዲንጋዩን ሰላም ማለትና ከዚያ ጦዋፍ ማድረግ ነው ፡፡ ይህ የዲንጋዩ ሰላምታ በመካ ብቻ ከሚደረጉ የአምልኮ ተግባራት አንዱ ነው ፡፡ ነቢዩ ጀዕፈር ብን ዐብዱላህ በዘገቡት ሐዲስ ‹ሙሐመድ ብን ዐባድ ብን ጀዕፈር ዲንጋዩን ስመው በእሱ ላይ ሱጁድ አደረጉ ፡፡ ከዚያም አጎቴን ኢብኑ ዐባስን ስመው ሱጁድ ሲያደርጉ አይቻለሁ ኢብኑ ዐባስም ዑመር ኢብኑልኸጣብንም እንደዚሁ ስመው ሱጁድ ሲያደርጉ አይቻለሁ ከዚያም ነቢዩ እንዲህ ሲያደርጉ ስላየሁ እኔም አድርጊያለሁ ››237 ብለዋል ፡፡ ይህን ሐዲስ ስናነብ ‹‹ አየሁ ›› የሚለዉን ተደጋጋሚ ቃል ልናተኩርበት ይገባል ፡፡ አራት ጊዜ ሙሉ ተደጋግሞ እናገኘዋለን ፡፡ ማለትም ፡1-ጀዕፈር‹‹ አየሁ›› 2-ሙሐመድ ብን ዐባድ 3-ኢብኑ ዐባስ ‹‹ አየሁ›› 4-ዑመር ኢብኑልኸጣብ ‹‹ አየሁ›› በዚህ ባማረ የሰነድ ሰንሰለት ነቢዩ በዲንጋዩ ላይ ሱጁድ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ 1-ዒባዳ በግል ጥረት ሳይሆን ነቢዩን በመከተል መሆኑን፤ 2-ዲንጋዩን መሳለም፤በሱ ላይ ሱጁድ ማድረግ ማለትም እሱን ሰላም ብሎ በእሱው ላይ ግንባሩን ማስቀመጡ አስፈላጌ መሆኑን ፤ 238 235
አል ኢሷበህ 6/119. አዝረቂ የመካ ታሪክ1/318. 237 የሐዲሱ ደረጃው ሙስሊም…… 238 ነወዊ በሙስሊም ሸርህ ላይ 9/16. 236
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
3-ሰለፎች የነቢዩን ፈለግ በመከተል በኩል የነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት እንደነበራቸዉና ይህም ስሜት 239ስላለ መሆኑን፤ 4-ዲንጋዩን መሳም መሳለም በሱ ላይ ሱጁድ ማድረግ የዚህ የተባረከ ሀገር ልዩ አምልኮታዊ ስርአት መሆኑን ፤ እውቀት ግዴታው ማስተማር መሆኑን እንማራለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሙሐመድ ብን ጀዕፈር ‹ኢብኑ ዐባስን ዲንጋዩን ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ ፤ ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ ፤ ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ ፤ ሶስት ጊዜ አይቻለሁ 240 ብሏል›› ሐንዞለህ ኢብኑ አቢሱፍያንም ‹‹ዲንጋዩን ብቻዉን ሲያገኙት ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ፤ ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ፤ስመው በላዩ ላይ ሱጁድ ሲያደርጉ፤ ሶስት ጊዜ ብሏል241› ኢብኑል ሙንዚር የተባሉ ዐሊም ‹‹በዚህ ዲንጋይ ላይ ሱጁድ ማድረግ የተፈቀደ ነው ብለዋል242፡፡ 31ኛ በመዕምናን በሶፋና በመርዋ ላይ የሚደረጉት ተክቢራዎች በመካ ዉስጥ ሁለት ታላላቅ ጋራዎች አሉ ፡፡ ትልቅነታቸው በአካል ግዝፈት ሳይሆን በሙስሊሞች ዘንድ ባላቸው ክብር ነው ፡፡ እኒህ ሁለት ጋራዎች ከኢብራሂም ወደ ዚህ ቦታ መምጣት ጀምሮ ከከዕባ ታሪክ ጋር ብዙ ሁኔታዎችን አሳልፈዋል፡፡ አላህም ስለ እነሱ ጉዳይ በቁርኣን እንዲህ ሲል ‹‹የሶፋና የመርዋ ጋራዎች የአላህን ትዕዛዝ ከመፈፀሜያ ጉልህ ቦታዎች ናቸው››አል በቀራህ 158 አዉስቷል ፡፡ ነቢዩ ጃቢር ብን ዐብዱላህ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ነቢዩ ከዲንጋይ እስከ ዲንጋይ ድረስ በሶስቱ ዙር ብቻ ፈጠን፤ ፈጠን እያሉ ይሄዱ ነበር ፡፡ ጦዋፍ ሲጨርሱም ሁለት ረከዓ ይሰግዱና ዱዓ ያደርጉ ነበር ፡፡ ከዚያም ወደ ዲንጋዩ ይሄዱና ከሳሙት በኋላ ወደ ዘምዘም ዉሃ በመሄድ ከሱ ጠጥተው በራሳቸዉም ላይ ያፈሱ ነበር፡፡ ከዚያም እንደገና ወደ ዲንጋዩ በመሄድ ሰላም ካሉት በኋላ ወደ ሶፋ ጋራ ይሄዳሉ
239
አህዛብ 21 240 ሙሶነፍ ዐብዱረዛቅ 5/37፣ አሻፊዒ አል ኡም ላይ 2/171፤ አልኢስቲዝካር 4/201241 ፋኪሃኒ የመካ ታሪክ1/116. 242 አል ኢጅማዕ 61. .
115
፡፡ ሶፋ ላይ እንደደረሱም ‹‹አላህ በጀመረበት እጀምራለሁ›› በማለት ሰዕዩን በሶፋ ይጀምራሉ 243› ብለዋል፡፡ የሐዲሱ መልዕክት ሐዲሱ ነቢዩ በመሰናበቻው ሐዲስ የሰሩትን የሐጅ ተግባር ዘርዘር አድርጎ ይዘግባል ፡፡ በዚህ ቦታ ማውሳት የተፈለገው ግን ‹‹አላህ በጀመረበት እጀምራለሁ›› ያሉትን ጉዳይ ሰፋ አድረጎ ማየት ሲሆን ይኸዉም ‹‹የሶፋና የመርዋ ጋራዎች የአላህን ትዕዛዝ ከመፈፀሜያ ጉልህ ቦታዎች ናቸው › አል በቀራህ 158 ፡፡ በማለት ያወሳዉን ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሶፋ ስለ ጀመረ ነቢዩም እሱኑ በመከተል በሶፋ ጀምሩ፡፡ ሶፋ በመካ ከሚገኙ የአምልኮ ቦታዎች ነው ፡፡ ከአባታችን ኢብራሂም ዉርሶችም አንዱ ነው ፡፡ በዚያ ከመካ ምስረታ ታሪክ ጋር በተያያዘው ጉዳይ ላይ ሃጀር በእሱና በመርዋ መካከል ሰባት ጊዜ ተመላልሳለች፡፡ ነቢዩ የአላህን ብቸኛ አምላክነት የጣኦት ዉድቀት በይፋ ያወጁትም በዚሁ ጋራ ላይ ነው ፡፡ በመሰናበቻው ሐጃቸውም ጊዜ በእሱው ላየ ሁነው ፊታቸዉን ወደ ከዕባ አዙረው የአላህን አንድነትና ታላቅነት በይፋ አውጀዋል ፡፡ እዚያው ላይ ቁመዉም ‹‹ለኢላሀ ኢለሏህ ወሀደህ ላሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ …›ብለዋል ፡፡ ይህንኑ ተመሳሳይ በመርዋም ላይ ፈፅመዋል ፡፡ ስለዚህ ሁለቱም ቦታዎች ከአላህ ግልፅ ተአምራት ናቸው ፡፡ 1-የተከበረው ዲንጋይ የጦዋፍ መጀመሪያው መሆኑን፤244 2-ከጦወፍ በኋላ ሁለትረከዓ መስገድ ተገቢ መሆኑን፤ 245 3-በመግቢያ ጦዋፍ ላይ በሶስቶቹ ዙሮች ላይ እርምጃን አሳጥሮ ፈጠን ፤ ፈጠን ማለቱ ተገቢ መሆኑን ፤ 246 4- ከሁለቱ ረከዓ ሶላቶች ካበቁ በኋላ ፤ የዘምዘም ዉሃም ከጠጡ በኋላ ዲጋዩን መሳለም ተገቢ መሆኑን፤ 247 5-ከሁለቱ ረከዓ ሶላቶች ካበቁ በኋላ፤ የዘምዘም ዉሃን መጠጣት ተገቢ መሆኑን፤ 243
የሐዲሱ ደረጃው አህመድ ቲርሚዚ ነሳኢ አልባኒም ትክከለኛ ሐዲስ ነው ብለዉታል፡፡ 244 ኢብኑ በጧል በቡኻሪ ሸርህ4/285. 245 ሚዓቱል መፋቲህ9/8. 246 ኢብኑ ዐብዲል በር በተምሂድ ላይ 2/76. 247 ሚርዓቱል መፋቲህ. الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
6-በሶፋና በመርዋ መካከል ያለው ሰዕይ መጀመር ያለበት አላህ እና ነቢዩ ከጀመሩበት ከሶፋ መሆኑን እንረዳለን ፡፡248 32ኛ ቋሚ የሆነው ግልፅ ተዐምር አላህ ነቢያት ለእውነተኝነታቸው ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ በተለያዩ ተአምራት አጠናክሯቸዋል ፡፡ የነቢዩ ኑህ መርከብ ፤ የነቢዩ ሷሊህ ግመል ነቢዩ ሙሳ ዘንግ ነቢዩ ሱልይማን ሰራዊት እናሌሌችም በግልፅ ከታዩት ተአምራት ጥቂቶቹ ናቸው፡ ፡ ከእነዚህ መካከል በጣም ትንሾቹ ብቻ ሲቀሩ ሁሉም ጠፍተዋል ፡፡ ከእኒሁ ከጥቂቶች መካከል በመካ የታዩት እኒህ የኢብራሂም ቅሬቶች ናቸው ፡፡ እሱም ነቢዩ ኢብራሂም የመስጊዱን መሰረት ሲያሳድጉ የቆሙበት ዲንጋይ ነው ፡፡ ነቢዩ ዐብዱላህ ኢብን ዐምር በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ዲንጋዩና የኢብራሂም መቋሚያ ከጀነት የመጡ ያቁቶች ናቸው ፡፡ አላህ ብርሃናቸዉን አብሶት ነው እንጂ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያበሩ ነበር ፡፡ ሲሉ ሰምቻለሁ››249 ብለዋል ፡፡ ሐዲሱ -ሁለቱም ዲንጋዮች ከተከበሩ የጀነት ዲንጋዮች መሆናቸዉን፤-አላህ ብርሃናቸዉን ማጥፋቱ ሰዎች በገይብ እንጂ በማየት እንዲያምኑ አለመፈለጉ ወደ ምድርም መመጣት የሚችሉት በዚሁ መልክ ሲሆን ብቻ መሆኑን ፤ ይህ ባይሆን ነሮ በእነሱ ብርሃን ቀንና ሌሊት ይዋጡ እንደነበር፤ ከዚያም ሁሉም አመፀኛዉም ሆነ ከሃዲው በእኩለነት ያምኑ እንደነበር፤ ሁለቱም ከጀነት የመጡት ዲንጋዮች መኖራቸው በመካ ካሉ ተአምራት ናችው ፡፡ አላህ እንዲህ አለ ‹‹ ለሰዎች ማምለኪያ ይሆን ዘንድ መሬት ላይ በመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በመካህ (በመካ) ያለው ቤት ካዕባ ነው :: በውስጡ ግልፅ የሆኑ ተዐምራቶች አሉበት ፡፡ የኢብራሂምም መቆሚያ የነበረው በዉስጡ አለ›› ኣሊ ዒምራን 96-97. በዚህ አንቀፅ የኢብራሂምን መቋሚያ ብቻዉን ግልፅ ተአምሮች ብሏል ፡፡ ምክኒያቱም በእሱ ብቻ ብዛት ያላቸው ተአምሮች አሉበት ና፡፡ 1-በለንጣ ዲንጋዩ ላይ የቆሙበት ምልክት መኖሩ፤ 2-እስከ ቁርጭምጭምት ድረስ መጥለቁ፤ 3-ከዲንጋዎች መካከል አንዳደንዱን ማለዘቡ፤
248
ኢበኑ ሐጀር በፈትሁል ባሪ 3/503. የሐዲሱ ደረጃው አህመድ…… -
249
.
117
4-ስንትና ስንት ጠላቶች እያሉበት ይህን ያክል በሺዎች የሚቆጠሩ አመታትን አልፎ ሁሉም ሲጠፋ እሱ እስካሁን መቆየቱናቸው ፡፡ ይህ መቋሚያ ኢብራሂም ሰዎችን ለሐጅ የጠሩበት ቦታ ነበር ፡፡ አላህም የዚህኑ ዲንጋይ ክብር ከፍ አድርጎ እንዲህ በማለት ‹‹መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ቤቱን ለሰዎች መሰባሰቢያና ቅዱስ ማዕከል ባደረግን ጊዜ የነበረውን ታሪክ አሰታውስ ። አማኞች ሆይ ! ከኢብራሂም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ›› አልበቀራህ 125 በማለት መስገጃ ቦታ ሁኖ እንዲያገለግል አድርጎታል ፡፡ ይህ ነው በእሱ ዘንድ ሊሰራ የሚገባው ፡፡ ከዚህ ያለፈ ነገርን ግን መስራት ክልክል ነው ፡ ፡ ለዚህ ነበር ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር አንዳንድ ነገሮችን ባዩ ጊዜ በሃይል ያወገዙት ፡፡ ሰዎች በእጃቸው ዲጋዩን ሲያብሱት አይተው በፍፁም ይህ ተግባር ክልከልል ነው በማለት ካወገዙ በኋላ ‹‹በማበስ ሳይሆን የታዘዛችሁት በመስገድ ነው አሏቸው››250 1-ሁለቱም ዲንጋዮች ከተከበሩ የጀነት ዲንጋዮች መሆናቸዉን፤ 2-አላህ ብርሃናቸዉን ማጥፋቱ ሰዎች በገይብ እንደጂ በማየት እንዲያምኑ አለመፈለጉን ያመለክታል፡፡ 251. 3-ይህ ሀገር ያለዉን ትልቅነትና ክብር ሁለቱም ከጀነት የመጡት ዲንጋዮች መኖራቸው፤ 4-የመካ ሰዎች በቀላሉ ከጀነት የመጡ ዲንጋዎችን ለማየት በመቻላቸው ትልቅ እድል መታደላቸውን እንማራለን፡፡ 33ኛ ለዝንተ ዐለሙ ጉዞ መዘጋጀት ሰዎች ወደ ሆነ ጉዳይ ለመሄድ ሲል የተሸለ ልብስና ሁኔታ አመቻችቶ ያማረ ሆኖ ንፁህ ሁኖ መሄድ ይፈልጋል ፡፡ ለአላህም ከፍተኛ ምሳሌዎች አለው ፡፡ ነቢዩን ወደ እሱ ለመውሰድ ሲፈልግ በዘምዘም ዉሃ አጥቦ ወሰዳቸው፡፡ የሰው ልጅ ለትልቅ ስብሰባ ሲዘጋጅ ባማረና በተሸለ ሁኔታ ለመሆን ይዘጋጃል፡፡ እናም ነቢዩ ወደ እሱ ሊወስዳቸው በፈለገ ጊዜ በዘምዘም ዉሃ አጥቦ ነው፡፡
250 251
-ዐብዱረዛቅ 5/49. -አሕወዚ3/526. الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ነቢዩ አቡ ዘር በዘገቡት ሐዲስ ‹በመካ ሳለሁ 252 ጣራየ ተከፈተና ጂብሪል ወርዶ ልቢን ከፈተው ና በዘመዘም ዉሃ አጠበው ፡፡ ከዚያም በእምነትና በጥበብ የተሞላ የወርቅ ሰሀን አምጥቶ በልቤ ዉስጥ አፈሰሰው፡፡ ከዚያም ዘጋው ከዚያም እጀን ይዞኝ ወደ ሰማይ ወሰደኝ253› ብለዋል፡፡ ይህ ሐዲስ የዘምዘም ትልቅነት ከተነገረባቸው ሐዲሶች አንዱ ነው ፡፡ ምክኒያቱም ለዚያ ከጌታቸው ጋር በሲድረቱል ሙንተሃ ላደረጉት ታላቅ የመገናኘት የሶላትን ግዴታ ከምንዳ ሀምሳ በተግባር አምስት የመደረግ የተገኘበት እድልና ከነቢያቱም ጋር በእሳቸው ኢማምነት በበይተል መቅዲስ ለመስገድ የቻሉበት ቀን በእሱ እንዲታ ጠቡ በሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ በዘምዘም ዉሃ የታጠቡት አራት ጊዜ ነው በያንዳንዱ ጊዜ ልባቸው እይተቀደደ በዘምዘም ዉሃ እየታጠበ ነበር ይህም የሆነበት የራሱ ምክኒያት አለው የሚሉ አሉ ፡፡ ቀጥለዉም ምክኒያቱን ሲዘረዝሩ በመጀመሪያው ጊዜ ህፃን ሁነው ሐሊማህ ዘንድ በነበሩበት ዘመን ነበር ይህም የተደረገው ከልባቸው ዉስጥ የሰይጣንን ድርሻ ለማጥ ነበር ፤ ሁለተኛ ጊዜ ደግሞ የአስር አመት እያሉ ሲሆን ፤ ሶስተኛው ደግሞበሒራእ ዋሻ ዉስጥ እያሉ ወህይን ለመቀበል ለማዘጋጀት ሲባል፤አራተኛው ወደ ሲድረቲል ሙንተሃ በመሄድ ከጌታቸው ጋር ለመገናኘት በተዘጋጁበት.254 1-የዘምዘምን ዉሃ ትልቅነት ፤255 2-ለነቢይነታቸው ከሚያመለክቱ አንዱ የነቢዩ……….፤256 3-የነቢዩ ልብ የመታጠቡ ምክኒያት ምን ምን እነ ደሆነ ፤….እንማራለን፡፡257 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ አስማእ ቢንት አቢ በክር ሲዲቅ ዐብዱላህ ብን ዙበይርን ካጠበች በኋላ የመጨረሻው ትጥበት ዘምዘም አድርገዋል ፡፡ 258 ፋኪሃኒ የተባለ ዐሊም ይህን
252
- እዚህ ላይ ………. -የሐዲሱ ደረጃው ቡኻሪና ሙስሊም፡፡… 254 ኢብኑ ሐጀር 1/460. 255 -የቡኻሪ ሸርህ ኢርሻዱ ሳሪ1/382. 256 ቁርጡቢ አል ሙፍሂም ላይ 1/382. 257 -ሺፋኡል ገራም 1/247. 258 -ፋኪሃኒ -የመካ ታሪክ በሚለው2/48. 253
.
119
ታሪክ ‹ የመካ ሰዎች እስካሁን ድረስ ጀናዛቸዉን በዘምዘም ዉሃ ነው የሚያጥቡት ማንንም ሬሳ ካጠቡት በኋላ በመጨረሻ የዘምዘም ዉሃ ያደርጌበታል› 259 34ኛው ሐዲስ ቤተሰብ አጥጋቢው የዘምዘም ዉሃ በዚያ ምንም አዝርዕት በሊለበት ዋሻ ቦታ የህፃኑ ልቅሶ በረታ ፡፡ ምግብ የለም ዉሃም አልቋል ፡፡ የእናቱ ጡትም ደርቋል ፡፡ እናቲቱ በሁለት ጋራዎች መካከል መላ ባገኝ ብላ መሯሯጥ ጀመረች በዚሁ ላይ እያለች የተከበረው መላይካ በልጇ አጠገብ በተረከዙ መሬቱን ቆፈር ቆፈር ሲያድርግ አየቸው ወዲያው የዘምዘም ዉሃ ብቅ አለ ፡፡ ከእሱም ስትጠጣ ጡቷወዲያዉኑ ሞላና ልጇን አጠባች ፡፡ ይህ የዘምዘም ዉሃ ቤተሰብ አጥጋቢ ከፈለቀበት ሰዐት ጀምሮ ለሀጀርና ለልጇበምግብነት አገለገለ ፡፡ እስከዐለም ፍፃሜ ድረስ ለሰዎች ሁሉ በቂ ምግብ ነው ፡፡ ነቢዩ አቡ ዘር በዘገቡት ሐዲስ ወደ ኢስላም የገቡበትን ታሪክ ሲያወሱ ነቢዩ ከመቸጀምረህ እዚህ ነበርክ አቡ ዘር ፡ ከሰላሳቀንና ሌሊት ጀምሬ፤ ነቢዩ ማን እየቀለበህ ፤ አቡ ዘር ፡-ከዘምዘም በስተቀር ምንም ምግብ አልነበረኝም ፤ ቦርጬ እስከሚሰበር ድረስ ወፈርኩ፤ በአንጀቴ ዉስጥ ምንም የረሀብ ስሜት የለኝም፡፡ ነቢዩ የተባረከ እኮነው ለምግብነትም የሚያገለግልነው ‹…………..260› ቁረይሾች ወደ ነቢዩ የሚመጣን ሁሉ እያሰቃዩ በነበሩበት ዘመንአቡ ዘር ነቢዩን ለማግኘት ወደ ነቢዩ መጥቶ ሰላሳ ቀን ሲያፈላልግ ሰነበተ ፡፡ በዚያ ጊዜም ከዘምዘም ዉሃ በስተቀር ምንም ምግብ አልነበረዉም ፡፡ 1-የዘምዘም በረካነት፤ 2-የዘምዘም በረካነት በተጨበጭ እንደተሞከረ፤ 3-የአቡ ዘርን ፅናት እንማራለን ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ኢብኑልቀይም ብዛት ያለቸው ሰዎች ዘምዘመን ቀለብ አድረገው ከግማሽ ወር በላይ የሆኑ ቀናት ሲያሳልፉና እንደማንም ጦዋፍ እያደረጉ አይቻለሁ እንዲዉም አንዳዶቹ እስከ አርባቀን ድረስ ይቆዩ ነበር ብለዋል፡፡ 259 260
-የመካ ታሪክ 2/48. -የሐዲሱ ደረጃው ሙስሊም…… الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
35ኛ ልዩ የመካ ስጦታ ሰዎች ወደ ሆነ ሀገር ደርሰው ሲመጡ ከዚያሀገር ምርጥ ነገሮች ለቤተሰቦቻቸው ይዘው መምጣት የተለመደ ነው ፡፡ በመካ ደግሞ ከዘምዘም ዉሃ የተሻለ ምርጥ ነገር የለም፡፡ ነቢዩ እናታችን ዓኢሻ ‹የዘምዘም ዉሃ ይዘው ይሄዱነበር ለምንድነው ተብለው ሲጠየቁ ነቢዩም ይህን ያደርጉ ነበር ብለዋል 261› የመካ ሰዎች ለሌሎች ከሚያበረክቱት ስጦታ ሁሉ የዘምዘም ዉሃ መሆኑንነው፡ ፡ 1-ነቢዩ የዘምዘም ዉሃ ወደ ሌላ ሀገር ይዘው በመሄድ የሰጡት ክብር፤ 2-የዘምዘም ዉሃ የመካ ሰዎች ስጦታ መሆኑን፤ 3-የዘምዘምን ዉሃወደ ዉጭ ሀገር ይዞ መሄዱ ችግር እንደሌለበት፤ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ኢብኑ ዐባስ እንግዳ ሲመጣ የሚያበረክቱለት የዘምዘም ዉሃ ነበር፡፡ ዐጣእ ኢብኑ አቢ ረባህ ከዕብ ሀጅ ባደረገ ጊዜ አስራሁለት ወይም አስራስድስት ---የዘምዘም ዉሃ ይዘው ወደ ሻም ሂደዋል›› ብለዋል፡፡ አንዳደንድ የኢንዱኑሲያ ሀጀኞች ለመካ ወጣቶች እንደተናገሩት የዘምዘም ዉሃ ወደ ሀገራቸው ወስደው በቡና ሲኒ እንደሚያቀምሷቸው ነግረዋቸዋል ፡፡ ይህንም ተግባር በጣም እንደሚደነቅ ነግርዋቸዋል፡፡ 262 36ኛው ሐዲስ የተውሳኮች ሁሉ ፍቱን መድሐኒት የሆነው የዘምዘም ዉሃ ከአመት እሰከ አመት ብዙ ቁጥር ያለቸው ሰዎች ለሐጅ ወይም ለዑምራ ወይም ለጉብኚት ወደ መካ በገፍ ይጓዛሉ ፡፡ በተለይም በሐጅ ወራትና በረመዷን ወር ላይ ፡፡ ይህ አይነቱ ስብስብ ደግሞ የተለያዩ በሺተዎችን ሊያስከትል እንሚችል ያሰጋል ፡፡ ግን በአላህ ቤት አጠገብ ና በዚያ ለሁሉም በሺታ መድህን የሆነው ተዐምረኛው የዘምዘም ዉሃ አጠገብ በመሆናቸው በአላህ ጥበቃ ስር ስላሉ በምንም በሺታ ሲጠቁ አይታዩም፡፡ 261
-የሐዲሱ ደረጃው ኢማሙ አህመድ ዘግበዉታል አልባኒም ትክክል ነው ብለዋል፡፡ -በእኛም ሀገር እስካሁን ድረስ እንደዚሁ ነው የሚደረገው ፡፡ ከህዝቡ ፍላጎትና ከዘምዘም ዉሃ እጥረት የተነሳ በስኒ ነው የሚዳረሰው ፡፡ ስለሆነም የሚቻል ከሆነ ምንግስታት እያመቻቹ የዘምዘም ዉሃ በነፃ ለሙስሊሙ የሚደርስበት መንገድ ቢታሰብ መልካም ነው እላለሁ፡፡ 262
.
121
ነቢዩ ሙሐመድ ﷺኢብኑ ዐባስ በዘገቡት ሐዲስ ‹በምድርዉስጥ ካሉ ዉሃዎች ሁሉ ምርጡ የዘምዘም ዉሃ ነው ፡፡ ለምግብነት ለሚፈልጉት ሁሉ ምግብ ነው ፡፡ ለመድሃኒትነት ለሚፈልጉትም እንዲሁ መድሀኒት ነው 263 ›ብለዋል፡፡ ምግብ ዉሃ ጤና የሰው ልጆች ያለነሱ ሊቆሙ የማይችሉት ነገር ነው ፡፡ እናም የሰው ልጅ እነዚህን ሶሰት ነገሮች ለማሟላት ብዙ ይጥራል ፡፡ ለመካ ሰዎች ግን አላህ ራሱ ሼፈነ ላቸው ፡፡ ዘምዘምን በመስጠት ምግብና ዉሃ እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪጤናም ለሚፈልግ ሰው ሁሉ ፍቱን መድሀኒት አደረገው ፡፡ የመካ ኗሪዎች ይህን እውነታ በገሃድ ያስተዉሉታል ፡፡ ይህ ረድኤት የመጀመሪየው ‹‹ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው› ኢብራሂም 37 ያለው ነው ፡፡ 1-የዘምዘም ዉሃ ለጠጪው እንደምግብ የሚያገለግል ፤ ለበሺተኛም እንደመድሐኒት የሚያድን ፤ መሆኑን ፤ 264 2-የዘምዘም ዉሃ ያለዉን ረድኤትና በረከት ፤265 3-ይህን ትሩፋት የሰጣቸው የመካ ሰዎች ማመመስገን እንደሚገባቸው፤ 4-ማንኛዉም ሙስሊም ከዘምዘም መጠጣት ከቻለ መጠጣቱ እንደሚወደድ ፤ 266
ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ኢብኑ ዐባስ ሲጠጡት ‹‹ አንተን ብቻ እገዛለሁ ከአንተ ብቻ እርዳታ እጠይቃለሁ…›› አልፋቲሐሕ. በማለት ይጠጡት ነበር 267፡፡ ኢብኑልቀይም የዘምዘምን መድሃኒትነት በራሴ ሞክሪዋለሁ ፡፡ ብዙ ተዐምራት አይቸበታለሁ ፡፡ ከብዙ በሺታዎችም በአላህ ድንኜበታለሁ268 ብለዋል፡፡ እንደዚሁም በመካ ሳለሁ ታምሜነበር ሐኪምም መደሀኒትም አጥቼ ባለው እያታከምኩኝ ነበር ፡፡ ከዘንዘም ዉሃ እጨልፍና በሷላይ ቀርቼ እጠጣው ነበር ይህን በተደጋጋሚ አደርጌ ብዙ ፈውሶችን አግኚቻለሁ ፡፡ ይህኑ ተግባር በሌላ 263
-የሐዲሱ ደረጃው ቡኻሪ በታሪክ መፅሐፉና ሙስሊም. ፈይዱል ቀዲር 4/85. 265 -ፈታዋ ኢብኑ ባዝ 25/278. 266 -ፈታዋ ኢብኑ ባዝ 25/279. 267 -ዳረቀጥኒ2/288. 268 - ዛዱል መዓድ 4/178. 264
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ጊዜም በብዛት ተጠቅሚያለሁ ፡፡ ኢማሙል ዐራቂም ለነበረባቸው የዉስጥ ደዊ በዚሁ እነድተፈወሱ ተናግረዋል፡፡ ዐብዱረሺድ ተታሪ የተባለም ዐሊም ለብዙ በሸታዎች ሞክሬው በተለይም ለፍኛና ለዉስጥደዊዎች ለአይን በሺታዎች ወሳኝ ሁኖ አገኚቸዋለሁ፡፡ ብሏል፡፡ 37ኛ የድሆች ሐጅ ሙስሊሞች ከእላህ ረህመትን በመከጀል የኢብራሂምን ጥሪ በማክበር መካን ለመጎብኜት ከያሉበት በተለያዩ መጓጓዣዎች ይሄዳሉ ፡፡ ከዚያም በዚሁ ቤት አጠገብ ጓዛቸዉን ያስቀምጣሉ ፡፡ ዛዱል መዓድ ዙረያዉን አካላቸው ብቻ ሳይሆን መንፈሳቸዉም ይሽከረከራል ፡፡ በዘምዘም ዉሃ በመታጠብ ወንጀላቸዉን ያራግፋሉ ፡፡ ወደ እየሀገራቸው ሲመለሱም እናታቸው ስትወልዳቸው እንነበሩ ንፁህ ሁነው ይመለሳሉ ፡፡ 269 ሙስሊሞች ሁሉ ይህን ቤት ለመጎብኘት ሲያስቡ ሁሉን ነገር ወደ ኋላ ትተው ይህ ጉዳይ ብቻ ነው ምኞታቸው ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺአቡ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ይህን ቤት ለሐጅ የጎበኜና ስለ ስሜት ያላወራ ወንጀልም ያልፈፀመ ሰው እናቱ ስትወልደው እንደነበረ ሁኖ ይመለሳል270› ብለዋል፡፡ ይህ ሐዲስ ያን ታላቅ ሐዲስ እሱን የመሰለ ሐጅ ያደረገ ሰው ዋጋው ጀነት ብቻ ነው የሚለዉን ሐዲስ ያብራራል፡፡ 1-አላህ ለወፈቀወ ሰው መካን ለሐጅ መጎብኘት ምን ያክል ክብር እንዳለው፤ 2-ወንጀሎችን ባጠቃላይ ከመፈፀም ማስጠንቀቅ፤ 3-የትኛዉንም ወንጀል መስራት ከሐጅ ዉጭም ክልከል ቢሆንም በሐጅ ላይ ሁኖ መስራቱ ግን በይበልጥ የተከለከለ መሆኑን፤ 4-ወንጀሎች በየ አይነታቸው የመልካም ስራን ምንዳ እንደሚያጎሉ፤ 5- ሐጅን መልካም የሚያስብለው ከተለያዩ ወንጀሎች ነፃ መሆኑ እንደሆነ፤271 6-የትክክለኛ ሐጅ ጥቅሙ እናቱ እንደወለደችው ሁኖ መመለሱ መሆኑን እንማራለን፡፡272 ሰለፎችና ይህ ሐዲስ 269
4/178. -የሐዲሱ ደረጃው ቡኻሪና ሙስሊም…… 271 -ነወዊ በሙስሊም ሸርህ ላይ 9/118. 272 -ኢብኑ በጧል በቡኻሪ ሸርህ ላይ 4/190. 270
.
123
ከዚህ ሐዲስ ጋር ከተያያዘ አርአያ ሊሆኑ ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል 1-ኢብራሂም ብን ዐብደላህ አልኹራሳኒ ከአባቴ ጋር አረሺድ ሐጅ የሰራ አመት ሐጅ አደረኩኝ ፡፡ እናም ረሺድ በባዶ እግሩ አሻዋው ላይ ቁሞ ፤ ራሱን ገልጦ ፤ እጆቹን ወደ ላይ አንስቶ ፤ እያለቀሰ ጌታየ ሆይ! እኔም ያው ወንጀለኛው ነኝ ፡፡ አንተም ያው መሃሪው ነህና ማረን እያለ ዱዓ ሲያደርግ አየሁት ይላል፡፡ 273 2-ዐሊይ ብን ሳቢት ሱፍያን አሰውሪ ወደ መካ እየሄዱ ባሉበት ላያቸው ላይ ያለዉን ንብረት ስገምት አንድ ዲረሃምና አራት ዳኒቅ ብቻ ነበር ፡፡274 3-ዧሂር በብሪስ የተባለ ታዋቂ ንጉስ እንደ ተራ ሰው ብቻዉን ህዝብ ጋር እየተጋፋ የሐጅ ተግባራትን ጦዋፍ ፤ ሰዕይ ፤ ብቻዉን ከማድረጉም በተጨማሪ ከዕባን አጥቦ በህዝብ ዉስጥ ብቻዉን ተቀላቅሎ ኢሃራሙን ለሰጠው ሁሉ አጥቦለት ይሰጠዋል ፡፡ በከዕባ በር ላይ ተቀምጦ ሰዎችን እጃቸዉን እየያዘ ቤቱን የሳዋል ፡፡ አንድ ተራሰው በኢህራሙ ተንጠልጥሎ ሊወጣ ብሎ ኢህራሙ ከመበጠሱ አልፎ ንጉሱም ሊወድቅ ነበር ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ንጉሱ በፍፁም ደስተኛ ነበር ፡፡ የቤቱን መጋረጃ በእጁ ከመስራቱም ሌላ በመካና በመዲና የነበሩትን ታላላቅ ሰዎች በመዘየር ተዋወቃቸው፡፡ 275 38ኛ ልቦች ሁሉ ወደ መካ ይናፍቃሉ ሱፍያን ብን ዑየይነህ በሙዝደሊፋላይ ተኚተው ለአንድ ጓደኛቸው እዚህ ቦታ ሰባ ጊዜ መጥቻለሁ በየአመቱ መጨረሻ አታድርግብኝ እላለሁ ፡፡ አሁን በየ ጊዜው ይህኑ ጉዳይ መጠየቁ አሳፈረኝ አሉ ፡፡ ከዚያም ተመልሰው በዚያው አመት ሞቱ፡፡ ነቢዩ ﷺዐብዱላህ ብን መስዑድ በዘገቡት ሐዲስ ‹ሐጅንና ዑምራን አከታትሉ ፡፡ ምክኒያቱም እሳት በብረት፤ በወርቅና በብር ላይ ያለን ቆሻሻ እንደሚያስወግድ ሁሉ ሁለቱም ዒባዳዎች ድህነትንና ወንጀሎችን ያስወግዳሉና ትክክለኛ ሐጅ ክፍያው ጀነት ብቻ ነው፡፡276› ብለዋል፡፡
273
-ኢትሓፉልወራ2/222. ሒልየቱል አውሊያእ 6/378. 275 አሱሉክ ለመዕሪፈቲ ዶሊ ልሙሉከ 1/196. 276 አህመድ፤ ቲርሚዚ፤ነሳኢ ኢብኑ ሒባን አልባኒም ትክክለኛ ነው ብለዋል፡፡ 274
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ታላቁ ነቢዩ ሙስሊሞች ሐጅና ዑምራን በማከታተል ግፊት አሳድረው በዱን ያ ሪዝቅን በማስፋት በአኺራ ደግሞ ወንጀልን በማስማር ከፍተኛ አስተዋፆእ ያለው መሆኑን ያስተምሩናል፡፡ 1-ሁለቱን ማለትም ሐጅንና ዑምራን ማከታታል ተገቢ መሆኑን 277፤ 2-ሁለቱን ማከታተል ለድህነት ማስወገጃ ምክኒያት መሆኑን፤ 278 3--ሁለቱን ማከታተል ለወንጀል ማስወገጃ ምክኒያት መሆኑን፤279 4-የትክክለኛ ሐጅ ምንዳው ጀነት መሆኑን፤ 280 5-የአምልኮ ተግባሮች ለዱንያም ሆነ ለአኺራ ከፍተኛ ጠቀ፣ሜታ እንዳላቸው እንገነዘባለን፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ሰለፎች በዚህ ሐዲስ በጣም ነው የተደሰቱት አቡ ጋሊብ ኢብኑ ዐባስ ‹‹ ወደዚህ ቤት በብዛት ተመላለስ ወደ ዚህ ቤት ከተመላለስክ ከጌታህ ጋር ስትገናኝ ሼክምህ ቀላል ሁኖ ነው››281 ዐጣእ ብን አቢ ረባህ ሰባ ሐጅ አድርገዋል፡፡282 አል አወድ ብን የዚድ አነኸዒ ለዑምራነወይም ለሐጅ ሰማኒያ ጊዜ ጎብኚተዋል፡ ፡283 ጣዉስ በሞቱ ጊዜ ሰዎች አላህ ይማረው አርባ ጂዜ ሐጅ አደርጓል›› ይሉነበር ፡፡ 284
ሙሐመድ ኢብኑ በአቢ ዑመር አልዐደኒ የተባሉት ታላቅ ዐሊም ሰባሰባት ጊዜ ሐጅ አድርገዋል ፡፡ 285
277
አልሙጅተባ ሸህ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም 23/324 አልሙጅተባ ሸህ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም 23/324 279 አልሙጅተባ ሸህ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም 23/324 280 አልሙጅተባ ሸህ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም 23/324 281 የመካ ታሪክ ፈኪሃኒ 1/41 1 282 ሲፈቱ ሶፍዋህ 2/214 283 ሴር አዕላሚ ኑበላእ4/50 284 ሴር አዕላሚ ኑበላእ4/51 285 ሴር አዕላሚ ኑበላእ4/97 278
.
125
39ኛ ሐጅ የተከበረው እንግዳ/ልዑክ ዑመር ብን ዐብዱል ዐዚዝ ለየመን አስተዳዳሪው ለዑርወህ እንዲህ ብሎ ላከለት ፡፡ ‹ይህ መልዕክቴ ሲድርስህ ከየመን ገንዘብ መቶ ሺህ ዲናር አውጣና ወደ መልካም እሳቤ ላላቸው ሰዎች ስጥና ወደ መካ የሚወስዱ መንገዶች ዳር ላይ እየተቀመጡ ልብስ የቸገረዉን ያልብሱ ፤ መጓጓዧ ያጣዉን ያጓጓዙ ፡፡ ምክኒያቱም ከሐጅ የበለጠ መልካም ተግባር አላየሁምና ››ብለዋል፡፡286 ነቢዩ ሙሐመድ ﷺዐብዱላህ ብን ዑመር በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ለአላህ ሲል የዘመተ፤ለሀጅ የወጣ ፤ ለዑምራ የወጣ ሰው የአላህ ልዑክ ነው ፡፡ ጠርቷቸው አቤት ያሉ፤ለምነዉት የሰጣቸው ናቸው 287›› ብለዋል፡፡ ይህ በአላህ ዘንድ የተከበረው እንግዳ ከአላህ ቢጠይቅ የሰጠዋል፡፡ የለመነዉን ያደርግለታል ፡፡ በአጠቃላይ በአላህ ዘንድ ያለው ከበሪታ ከፍተኛ ነው ፡፡ የሐጅና የዑምራ ተጓዦች በአላህ ዘንድ ከፍተኛ ማዕረግ ያለቸው መሆኑን በግልፅ ያመለክተናል ፡፡ እዚህ ላይ ሊጠቀስ የሚገባ ነገር ቢኖር ይህ የተከበረ እንግዳ ወደ መካ በየጊዜው መጓዙ የሚያስከትለው በመካና በሌሎችም የዒባዳ ቦታዎች ላይ ግፊ እንደሚያስከትል ነው ፡፡ ይህ ደግሞ በአካባቢው ለሚኖሩ ሁሉ መጨናነቅን ስለሚ ፈጥር የዚህ አካባቢ ሰዎች እኒህ እንግዶች የአላህን ጥሪ ተቀብለው ከሩቅ ሀገር የመጡ አላማቸው የአላህ ዉዴታ የሆነበዐረፋ ላይ በእነሱ አላህ መላይኮችን የሚወዳደርበት መሆኑን አውቀው እነሱን ለማስተናገድ በመብቃታቸው ለዚህ ታላቅ እድል በመታደላቸው ሊደስቱ እንጂ ሊከፋቸው እንደማይገባ ያመለክታል ፡፡ 288 1-የዲን ዘማች ፤ ሐጅ ፤ ዑምራ የሚሰራ ሁሉ የአላህ ልዑክ መሆኑንና ዱዓቸዉም ተቀባይነት ያለው መሆኑን፤ 2- ሐዲሱ እኒህን ሶሰቶችን ብቻ በዚህ ማዕረግ መለየቱ በከፈሉት ከፍተኛ የገንዘብ የአካል ብሎም የህይወት ምስዋዕት መሆኑን ፤ 289
286
የመካ ታሪክ ፋኪሃኒ 1/414 ኢብኑ ማጀህ ጦበራኒ ኢብኑ ሒባን አልባኒም ትክክለኛ ሐዲስ ነው፡፡ 288 አህመድ 2/244 289 ሚርቃቱል መፋቲህ 8/419 287
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
3-የመካ ሰዎች ለሐጅ ወይም ለዑምራ የሚመጡ ሰዎችን ሲረዱ የአኺራን ምንዳ መፈለግ እንደሚገባቸው፤ 4-መካን የአላህ እንግዶች መቀበያ በማድረግ ምን ያክል እንዳከበራት፤ 5-ለሐጅ ወይም ለዑምራ ወደ መካ የሚመጡ ሰዎች ሁሉ የአላህ እንግዶች በመባል መጠራታቸው ከሌሎች የተለየ እክብካቤ እንዲያገኙ ታስቦ መሆኑን እንማራለን ፡፡ ሰለፎችና ይህ ሐዲስ ይህ ሐዲስ- በእኒያ የመካን እግዶች ተቀብለው ማክበር ኢስላም በፊት እንኳን ስራቸው ያደረጉት ሁሉ በተለይ እኒያ ከጃሂሊያ ዘመን ጀምረው ይህን ተግባር ይተገብሩ የነበሩት ሰዎች ዘንድ -ከፍተኛ ከበሪታን ተችሮታል ፡፡ ሐሺም ብን ዐብዱ መናፍ ሐጅ በደረሰ ጊዜ ለቁረይሽ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ቀረይሾች ሆይ ! እናንተ የአላህ ጉረቤቶችናየቤቱ ጠባቂዎች ናችሁ ፡፡ አላህ እናነተን በዚህ ለያችሁ ፡፡ መረጣችሁ ፡፡ ከዚያም ጉረቤት ከጉረቤቱ የሚ ጠብቀዉን ጠበቀላችሁ ፡፡ እናም እንግዶቹን አክብሩለት ጉብኞቹን ተንከባከቡለት ከየ ሀገሩ ተበሳቁለው ፀጉራቸው ተንጨፋሮ ፤ ልባሰቸው አድፎ ይመጣሉ ፡፡ እናም ቁረይሾች ተረዳድተው ይህን ሀላፊነት ለመወጣት ሁሉም ያቅሙን ያበረክት ነበር 290›› ቁሶይ ብን ኪላብም ‹ቁረይሾች ሆይ ! እናንተ የአላህ ጉረቤቶችና የሐረሙ ባለቤቶች ናችሁ ፡፡ ሐጀኞችም የአላህ እንግዶችና የሐረሙ ጎብኚዎች ናቸው ፡፡ እነሱም ከእንግዶች ሁሉ በበለጠ ሊከበሩ የሚገባቸው ናቸው ፡፡ እናም ወደየ ሀገራቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሚበሉትና የሚጠጡት አዘጋጁላቸው አላቸው›› እነሱም ይህንኑ ሰምተው ተገበሩት ፡፡ ለዚሁ ዝግጂት በያመቱ የተወሰነ ገንዘብ በየራሳቸው ላይ ግዴታ አድርገው ለቁሶይ እያዋጡ ይሰጡ ነበር ፡፡ እሱም በዚህ ገንዘብ ምግብ ሰርቶ በመካም ሆነ በሚና እየደገሰ ሐጀኞችን ያበላ ነበር ፡፡ ይህንኑ ተግባር ኢስላምም ሲመጣ በመቀበል መካን የሚያስተዳደሩ ሁሉ በመካና በሚና እያስተናገዱ ይገኛሉ ፡፡ ሙዓዊያህ ለዚህ ጉዳይ የተለየ የምግብ ቤት ሰርተው ለሐጀኞችና ለረመዷን ዑምራ አድራጊዎች የተዘጋጀ ነበራቸው፡፡ ዐብዱሏህ ብን ዑመር ‹አንደ ሰው ሲሞት ገንዘቤን በአላህ ንገድ ላይአዉሉልኝ በማለት ተናዞ ነበር እና እምን ላይ እናዉልለት ተብለው ሲጠየቁ ለሷሊሆችና ለሐጀኞች አብሉት የአላህ እንግዶች ማለት እነሱ ናቸው› ብለዋል 291 ፡፡ 290
አኽባሩ መካህ አዝረቂ1/194-195 አኽባሩ መካህ አዝረቂ1/194-195
291
.
127
40ኛ መካ የእምነት/መደበቂያው/ መሰበሰቢያው ቦታ በመጀመሪያ ጊዜ የነበረው የኢስላም እንገድነት በተከታዮቹ ማነስ የነበረ ሲሆን ፤ በመጨረሻው ዘመን የሚከሰተው እንግድነት ግን ዲናቸዉን ጠንቅቀው ባለማወቃቸዉና ባወቁትም ባለ መተግበራቸው ነው ፡፡ ምክኒያቱም በዚያ ጊዜ ሙስሊሞች በቁጥር በጣም ብዙ ናቸው ልክ እንደ ገለባ ክብደት የሌላቸው ናቸው›› 292 ፡፡ ነቢዩ ﷺዐብዱላህ ብን ዑመር በዘገቡት ሐዲስ ‹‹ኢስላም ሲጀምርም እንግዳ ነበር በመጨረሻው ዘመንም ልክ እንዲሁ እንግዳ ይሆናል ፡፡ እባብ በዋሻዋ እንደምትሰበሰብ ሁሉ ኢስላምም በሁለቱ መስጂዶች መካከል ብቻ ይወሰናል293› ብለዋል፡፡ ኢስላም ይሰበሰባል ማለት ሙስሊሞች ይሰበሰባሉ ማለት ነው ፡፡ ይህም ማለት ልክ የኢስላም የመጀመሪያዉን ሕይወት ያስታዉሰናል ፡፡ ምክኒያቱም ሙስሊም በመጀመሪያ ጊዜ ለዲናቸው ሲሉና ነቢዩን አገኚተው በትክከል ኢስላምን ለመረዳት ሲሉ ወደ መዲና እንተሰደዱ ሁሉ በመጨረሻዉም ዘመን እንደዚሁ ለዲናቸው ሲሉ በሁለቱ መስጂዶች መካከል ከፊትና ለመራቅ ሲሉ ይሰባሰባሉ ፡ ፡ 294 1-ኢስላም ሲጀምርም ወደመጨ ረሻም አካባቢ ላይ እንግዳ እንደሚሆን፤ 2-የመካ ክብር ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ፤ 3-የመዲናም ክብር እንዲሁ ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ፤ 4-ወደ ሁለቱ ከተሞች መግባት የሚፈቀደው ለሙስሊሞች ብቻ መሆኑን 295፤ 5-ኢስላም የተጀመረው በመካ ሲሆን ያበበው ደግሞ በመዲና እንደነበረ እንማራለን 296 ፡፡
292
አህመድና አቡ ዳዉድ አልባኒም ትክክለኛ ሐዲስ ነው፡፡ ሙስሊም የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ነው፡፡ 294 አል አሕወዚ 7/319 295 ሸርሁ ል ቡኻሪ ኢብኑ በጣል 4/548. 296 አል ሙልሂም ቁርጡቢ2/128. 293
الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
የመዲና መስጊድ በኢስላም ታላቁ የመዲና መስጂድ ከፍተኛ ቦታ ካላቸው አንዱ መስጊድ መሆኑንና ከመካ በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ አጅር የሚገኝበት መስጊድ በመሆኑ ሐጅ ለማድረግ ወደ መካ የተጓዘ ሰው በአጋጣሚው ይህንን አጅር ይዞ ወደ ሀገሩ መመለስ በጣም የሚወደድ በመሆኑ እንጅ የመዲናን መስጊድ መጎብኘት ከሐጅ ክፍሎች አንዱ አይደለም ፡፡ ከሀገራት በሐጅ ምክንያት ወደ ሳዑዲ የተጓዘ ሰው ወደ ሀገሩ ሲመለስ ሊጠቅሙት የሚችሉ ዕቃዎችን ይዞ መመለሱ የሐጁን አጅር የማይቀንስ ከመሆኑም ባሻገር ምንም ዓይነት ወንጀል የለበትም ፡፡ ሐጅንና ዑምራን ለመፈጸም ወደ ሳዑዲ የሄደ ሰው ሐጅና ዑምራን ከፈፀመ በኋላ ምድራዊ ጥቅም የሚያስገኝለትን ሥራ መስራትም ሆነ እዚያው መክረሙ ወንጀል የሌለውም ሆኖም በሳዑዲ ቆይታው ወንጀል መስራቱና የተጓዘበትን ዓላማ ሳይፈጽም መክረሙ ወንጀለኛ ያደርገዋል ፡፡ አንድ ሰው አላህ ግዴታ ያደረገበትን ነገር በመፈፀሙ ምክንያት ምንም ዓይነት ምድራዊ ጥቅሞችና ድግሶችን መጠበቅ የለበትም ፡፡ ሐጅ ደግሞ እንደ ሰላት ዘካና ፆም ሁሉ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ የተጣለባቸው የኢባዳ ዓይነት በመሆኑ ይህን ግዴታ የፈፀመ ሰው ከአላህ ምንዳ መጠበቅ ይኖርበታል እንጂ ለክብሩ ተብሎ የሚደረጉ ግብዣዎች በኢስላም ቦታ የለውም ፡፡ የሐጅ ተግባር የፈፀመ ሰው ሐጂ የሚባል የማዕረግ ስም ሲሰጥ ይስተዋላል፡፡ የሐጅ ተግባር በሚፈጸምበትና በክንውኑ ወቅት ሐጅ የሚባል ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ሐጅን በማድረጉ ብቻ የማዕረግ ስም እንደሆነ መቀጠሉ ግን ይዩልኝና ይስሙልኝ በማምጣት ተግባሩን ሊያበላሽበት ስለሚችል መቅረት ያለበት አጠራር ነው፡፡ 6.1.ከመዲና ከተማ ስሞች የመዲና ከተማ ብዙ ስሞች አሏት አንዳንድ ዐሊሞች ወደ መቶ ያደርሱታል፡፡ 1ኛው-የስሪብ ፤ 2ኛው-አልመዲነህ፤ 3ኛው-አዳሩ ወል ኢማን፤ 4ኛው-ጦይባህ፤ 5ኛው-ጣበህ ፤ 6ኛው-ዳሩ ልሂጅረህ፤ 7ኛው-መዐሪዙ ል ኢማን፤ 8ኛው-አርዱ ላህ፤ 9ኛው-አል ኢማን፤ 10ኛው-አል በሂረህ፤ 11ኛውበለዱ ረሱሊ ላህ፤ 12ኛው-አል ጀነቱ ል ሐሲነህ፤13ኛው-ቁበቱል ኢስላም፤ .
129
14ኛው-አዲርዑል ሐሲነህ፤ 15ኛው-አል ሐረም ፤16ኛው-ኛውዳሩ ል አብራር፤ 17ኛውዳሩ ል አኽያር ፤ 18ኛው ዳሩ ሱነህ፤ 19ኛውዳሩ ሰላመህ፤ 20ኛውዛቱ አነኽል፤ 21ኛው አል መዲነቱ ል ሙነወረህ ፤ 22ኛው አል መዲነቱ ል ሙሸረፈህ፤ 23ኛው አሳሪብ ፤ 24ኛው አስረብ ፤ 25ኛው አርዱ ል ሂጅራህ፤ 26ኛው አካለቱ ል ቡልዳን፤27ኛው አካለቱል ቁራ፤ 28ኛው አል ባረህ፤ 29ኛው አል በረህ፤ 30ኛው አል በህር፤ 31ኛው አል በህረህ፤ 32ኛው አል ቡሀይረህ፤33ኛው ሰይደቱ ል ቡልዳን 34ኛው አል በላጥ፤35ኛው አል በለድ፤ 37ኛው አል ጁነህ፤ 38ኛው አል ጁነህ አል ሐሲነህ፤39ኛውአል ሑባብ፤ 40ኛው አል ሐቢበህ፤ 41ኛው ሐረሙ ረሱሊላህ፤ 42ኛው አዳሩ፤ 43ኛው ዳሩ ሰላም፤ 44ኛው ዳሩ ልፈትህ ፤45ኛው ዳሩል ሒጅረህ፤ 46ኛው አዲርዑ ልሐሲነህ፤ 47ኛው አል ሑባብ፤49ኛውአልኸይር ፤ 48ኛው ጣኢብ፤49ኛው አሻፊያህ፤ 50ኛው በይቱ ረሱሊላህ፤ 51ኛው ተብሂረህ ፤ 52ኛው አል ጃቢረህ፤ 53ኛው ጀባር፤ 54ኛው ጀባረህ፤55ኛው ጀዚረቱል ዐረብ እና ሌሎችም ስሞች አሏት፡፡ 6.2.ስለ መዲና ክልሎች በስተደቡብ በኩልዒር የተባለው ጋራ በስተሰሜን በኩል ሰውር የተባለውጋራ በስተ ምስራቅ ናበስተ ምዕራብ በሁለቱ ጋራዎች መካከል ነው፡፡ 6.3. የነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድን ጉብኝት ይህ ሀገር ከኢስላም በፊት1500 አመት ገደማ እንደተመሰረተ ይገራል ፡፡ ስሙም የስሪብ ይባል ነበር ፡፡ ሆኖም በነቢዩ ዘመን ወዲህ በዚህ እንዳይሰየም ተከለክሏል፡፡ (وإم حذ قَالَت طَائمَفةٌ ممحن هم يا أَهل ي ثح مرب ََل م َقام لَ ُكم يَارمجعوا ويستأح مذ ُن يَ مر م َّب يَ ُقولُو َن إم َّن َُ ح َ ح َ َ َ ُ َ ح ح ُ ََ ح ح َّ يق محن ُه ُم النم ٌ َ م )٣١ :) ( األحزاب30( يدو َن إمََّل يمَر اارا ُ بُيُوتَنَا َع حوَرةٌ َوَما ه َي بم َع حوَرةٍ إم حن يُمر መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ከእነሱም የሆነ ቡድን ጭፍሮች የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ ፡፡ الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
...من قال للمدينة" يثرب "فليستغفر هللا መዲናን የስሪብ ብሎ የሰየመ ሰው ከአላህ ምህረትን ይለምን 297፡፡ 3.4 የመዲና ከተማና መስጊድ በኢስላም መከበር ሐጅን እና ዑምራን ከጨረሱ በኋላም ሆነ በማንኛውም ጊዜ መዲና ወደ ተባለው ከተማ በመሄድ የሚከተሉትን ተግባሮች ማከናወን ተፈላጊና ተወዳጅም ነው ፡፡ ይህ ሀገር ልክ እንደመካ ሁሉ ሙስሊም ያል ሆ ነሰው መግባት የተከለከለ ነው ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድﷺ اللهم بارك في مدهم،(اللهم إني أحرم ما بين َلبتيها مثل ما حرم إبراهيم مكة )وَٰاعهم ሆኖም መዲናን መጎብኜት ራሱን ችሎ አጅር ያለው ስለሆነ መጎብኜቱ ተገቢ ነው ፡፡ በመዲና ከተማ ሶስት ቀደምት መስጂዶች አሉ ፡፡ እነሱም ፡1-ትልቁ መስጂድ ፤ 2-የቁባ መስጂድ ፤ 3-እና የሁለቱ ቂብላ መስጂድ ናቸው ፡፡ 1. መዲና እንደደረሱ ወዲያው ወደ ታላቁ ነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ በመሄድና በመስጊዱ ውስጥ በመግባት ተህየተል መስጊድ (ሁለት ረከዓ ሶላት) ከሰገዱ በኋላ በመቀጠል ወደ ወደ ተከበረው የነብዩ ሙሐመድ ﷺበአላህ ዘንድ ያላቸውን ክብርና ደረጃ በልቡ በማስታወስ ከቆመ በኋላ ድምፁን ዝቅ በማድረግ ‹አሰላሙ ዓለይኩም ያነቢየላህ› ማለትም ‹የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ስም በርሶ ላይ ላይ ይሁን ›› በማለት ሰላምታ በነብዩ ላይ እንዲወርድላቸው አላህን መለመን በጣም ተፈላጊና ተወዳጅም የሆነ ድርጊት ነው ፡፡ እንዲሁም 297
አህመድ .
131
ትንሽ ወደ ቀኝ በኩል በመሄድ በሰይድና አቡበክር መቃብር አጠገብ በመቆምና ድምፅን ዝቅ በማድረግ ‹አሰላዓለይኩም ያኸሊፈተ ነብዩላ› ማለት ‹የነብዩ ምትክ የአላህ ሰላም በርሶ ላይ ይሁን› በማለት ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ በመቀጠል አሁንም ትንሽ ወደ ቀኝ በኩል በመሄድ በሰይድ ዑመር ቀብር አጠገብ በመቆም ለርሳቸው ሰላምታ ማቅረብ በጣም ተፈላጊና ተወዳጅ ነው ፡፡ 1. የነብዩ ሙሐመድ ﷺየአቡበከርንና የዑመርን መቃብር ከዘየሩ በኋላ ከዚያ በመመለስ የሚቻል ከሆነ ነብዩ ሙሐመድ ﷺምክር ይሰጡበት በነበረው መድረክ አጠገብ ወይም በረንዳው ላይ በመሆን ሶላትን መስገድ ፤ ቁርኣን መቅራት ፤ የነብዩ ሙሐመድን ﷺሶላት ማድረግ ከምንጊዜም በተለየ ሁኔታ ወደ አላህ ዱዓ ማድረግ በጣም ተፈላጊ ነው ፡፡ 6.4.የቁባን መስጊድ መጎብኘት ያለው ምንዳ ለማንም ሙስሊም በመዲና ወደ ሚገኜው ‹ቁባ›› ወደ ተባለው መስጊድ በመሄድ ሁለት ረከዓ መስገድና መዘየር በጣም ተወዳጅ ነው ፡፡ በመስጂዱ ዋና በር ላይ ተፅፎ እንዳለው ሐዲስ . (. (صَلة ِف مسجد قبا كعمرة (ዉዱኡን አደርጎ መጥቶ በዚህ መስጂድ ሁለት ረከዓ የሰሀደ ሁሉ የዑምራን ፆሎት እንደፈፀመ ይቆጠርለታል)298 ማሳሰቢያ ፡- ማንኛውም ሰው ከዚህ በላይ የተገለፁትን ተግባሮች በሚፈፅምበት ጊዜ ተገቢ ያልሆኑና ከእስልምና ሕግ ውጭ የሆኑ እንዲሁም ነብዩ ሙሐመድ ﷺበሕይወት ዘመናቸው በነበሩበት ጊዜ እንዳይፈፀሙ የከለከሉትን ድርጊቶች መፈፀም አጥብቆ የተከለከለ ነው ፡፡ 6.5. የነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ ጉብኚት የዚያራ ሥርዐተ ደንቦች ስለ ነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ ጉብኚት አንዳንድ የዚያራ ሥርዐተ ደንቦች ፡፡ 1. ወደ መስጊድ ስትገባ ቀኝ እግርህን አስቀድም ‹ቢስሚላህ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ ፡፡ አሏሁምመ እፍተሕሊ አብዋበ ረህመቲከ› በል›› ትርጉም ፡- በአላህ 298
ቲርሚዚ. الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ስም ፡፡ ሰላም ለአላህ መልዕክተኛ ይሁን ፡፡ አላህ ሆይ ! የችሮታህን በሮች ክፈትልኝ› ማለት ነው፡፡ 2. እንደሌሎቹ መስጂዶች ሁሉ ሁለት ረከዓ ሱና (ተሕይየተል መስጊድ) ስገድ ፡፡ ‹አሠላሙ ዓለይከ ያ ረሱለልሏህ ፤ አሠላሙዓለይከ ያአቡበክር አሠላሙ ዓለይከ ያ ዑመር›› በማለት ለአላህ መልዕክተኛ ﷺና ለሁለቱ ኸሊፋዎች ሰላምታ አቅርብ ፡፡ ከዚያም ፀሎት ስታደርግ ፊትህን ወደ ቂብላ አዙር ፡፡ አደራህን እዚህ ላይ የቱንም ያክል ነቢዩን ብትወድ ‹‹ከለመንክ አላህን ብቻ ለምን ፡፡ ረድኤት ስትጠይቅም አላህን ብቻ ጠይቅ ›የሚለውን የነብዩ ሙሐመድ ﷺ ቃል አስታውስ ፡፡ 3. የነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ መጉብኘትና ነብዩን መሰለም የተወደደ ተግባር ሲሆን የሐጁ ትክክለኛነት ግን በርሱ ላይ አይመረኮዝም ፡፡ የተወሰነ የመሳለሚያ ጊዜም የለውም ፡፡ ማንም ሰው በፈለገው ሰዐትና ቀን መዘየር ይችላልና ፡፡ 4. መስኮቱን ወይም ግድግዳውንና የመሳሰሉትን ከመሳምም ሆነ ለመባረክ ከመነካካት ተጠንቀቅ ፡፡ እንዲህ ማድረግ በሃይማኖቱ የሌለ የፈጠራ ነገር ማምጣት (ቢድዓ) ነውና ፡፡ 5. መስጊዱን ለቆ ሲወጡ የኋልዩሽ እየሄዱ መውጣት መሰረት የሌለው በኢስላም ከተፈፀሙት ግፎች አንዱ የሆነ ፈጠራ ነው ፡፡ 6. አክብሮትን ያጣመረ የአላህ እዝነትና ሰላም ለነብዩ ﷺእንዲሆን ፀልይ፡፡ ለነብዩ ሙሐመድ ﷺሰለዋት መለመንን አብዛ ፡፡ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋልና ፡من صلى علي صالة صلى اهلل عليه بها عش ار ‹የአላህ አክብሮት እዝነትና ሰላም ለኔ እንዲደርስ አንድ ጊዜ የፀለየ (ሰለዋት ያለ) ሰው ፤ አላህ አስር ጊዜ ተመሳሳይ ሶለዋት ያደርስለታል›› 299 7. የበቂዕን መካነ መቃብር ፤ የኡሑድ ሰማእታት መቃብርን መገብኘት የተወደደ ሲሆን መዲናና አካባቢው የሚገኙ ሰባት መስጊዶችን መዘየር ግን በዚህ ስር አይጠቃለሉም ፡፡ ማስረጃ ስለሌለው ነው፡፡ 299
ሙስሊም. .
133
8. ወደ መዲና የሚደረገው ጉዞ የነብዩን መስጊድ ለመጎብኘት ዓላማውና እዚያ ከደረሱ በኋላ ደግሞ ነብዩን ለመሰለም የታቀደ ይሆናል ፡፡ በነብዩ ሙሐመድ ﷺመስጊድ የሚሰገደው አንድ ሶላት ከመካ ሌላ በተቀሩት ሌሎች መስጊዶች ከሚሰገደው አንድ ሺህ ሶላት ይበልጣል ፡፡ ይህንኑ የጉዞ ዓለማ አስመልክቶ ነብዩ ሙሐመድ ﷺእንዲህ ብለዋል ْج ِد َ ْج ِد ِ الح َرام َو َمس ِْج ِدي هَ َذا َوال َمس ِ ال َمس:اجد ِ (َل تُ َش ُّد الرِّ َحا ُل إَِلَّ إِلَى ثَلثَ ِة َم َس )صى َ اۡلَ ْق ፡-‹አላህን ለመገዛት ዓለማ በማድረግ ወደ ሶስት መስጊዶች ብቻ እንጂ ወደ ሌላ ጉዞ አይደረግም ፡፡ እነሱም ፡1-የተከበረው የመካ መስጊድ (መስጁዱል-ሀራም) ፤ 2-የአል አቅሷ መስጊድና ፤ 3-ይህ መስጊድ (የመዲና መስጊድ) ናቸው› ብለዋል ፡፡ ሆኖም የመስጊዱ ጉብኝትና ሐጅ ምንም ግንኙት የላቸው ፡፡ በዚሁ እንደመጣ ሊጎበኝ ከፈለገ እንጂ ፡፡ መዲናን ያልጎበኜ ሐጁ ጎደሎ ነው የሚሉ ሐሰተኞች ናቸው ፡፡ የነብዩ ሙሐመድን ﷺቀብር መጎብኘት زيارة قبر النبي ለወንዶች የነብዩ ሙሐመድ ﷺቀብር መዘየር እንደሌላው ቀብር ሁሉ ሱና ነው ፡፡ ሆኖም የሳቸዉን ቀብር በሚዘየርበት ጊዜ ድምፅን ከፍ አድርጎ በመጮህ ማልቀስ ይቅርና ፀሎት በማድረግም ቢሆን የተከለከለ ነው ፡፡ ይህም እንዳይደረግ አላህ በቁርኣን ላይ ‹ድምፃችሁን በነብዩ ላይ ከፍ አድርጋችሁ አትናገሩ› አል ሐጁራት በማለት አስጠንቅቆናል ፡፡ ስለዚህ ነብዩ ሙሐመድ ﷺምንም እንኳ በአካላቸው በሞት ቢለዩንም በመቃብራቸው ውስጥ ህያው እንደሆኑ ስለሚኖሩ ከእሳቸው መቃብር አጠገብ መጮህ አጥብቆ የተከለከለ ነው ፡፡ ከዚህም ሌላ በነብዩ ሙሐመድም ሆነ በሌሎች አስሃቦች (ባልደረቦች) መቃብር ጠዋፍ ማድረግ ፍፁም ክልክል የሆነ ተግባር ነው ፡፡ ምክንያቱም በእስልምና ሕግ መሰረት ጠዋፍ የሚቻለው በካዕባ ዙሪያ ብቻ ስለሆነ ነው ፡፡ ስለሆነም الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ማንኛውም ሐቅን ተቀባይ የሆነ ሙስሊም ሁሉ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ይዘውልን የመጡትን ትክክለኛውን የኢስላም ሕግ በመቀበልና በማክበር በሥራ መተርጎም እንጂ በልብ ወለድ እና በመሰለኝ ተገቢ ያልሆኑና ከእስልምና ሕግ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን መፈፀም ኪሳራ ብቻ እንደሆነ የሃይማኖታችን መሪ ነብዩ ሙሐመድ ﷺበትክክለኛ ሓዲሳቸው ላይ ((من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ‹መን አህደሰ ፊአምሪና ሀዛ ማለይሰ ሚንሁ ፈሁወ ረዱን› ማለትም ‹ከእስልምና ሕጋችን ውጭ የሆነን ሌላን ነገር በመጨመር የሰራ ሰው ሥራው በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ተመላሽ ነው› በማለት አስረድተውናል፡፡ በመዲና ከእነዚህ ሌላ የሚጎበኙና አጅር የሚያስገኙ አሉን በፍፁም ምንም ነገር የለም ፡፡ እናም ሙስሊሞች በዒባዳቸው ላይ ማንም እንዳያታልላቸው መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል ፡፡ ወደ ሀገር ቤት መመለስና የሚታዩት ከሸሪዐ ጋር የሚፃረሩ ስርዐቶች አላህ ከቢድዓ ጠንቅና የቢድዓ ሰዎች ከሚያመጡት አደጋ ሁሉ ሁልጊዜም ይጠብቀን ፡፡ 6.6.የመዲና ትልቅነትና ክብር የመዲናን ትልቅነትና ክብር በተመለከተ የተዘገቡ ሃዲሶች ናቸው ፡፡ ከነዚህም መካከል በዚህ ጉዳይ ላይ 1-አስራ ስድስት ሃዲሶች በቡኻሪና በሙስሊም ፤ 2-አስራ ዘጠኝ ሃዲሶች በሙስሊም ብቻ ፤ 3-ሁለት ሃዲሶች በቡኻሪ ብቻ ፤ እና ሶስት ሃዲሶች ደግሞ በሌላ የሃዲስ ዘጋቢዎች የተዘገቡ ትክክለኛ ሃዲሶች እንዳሉ ደራሲ ሼህ ሙሃመድ አሀመድ ሙሃመድ አል አማሪ ስለ መዲና አርባ ሃዲሶች በተባለው መፅሃፋቸው ላይ አውስተዋል ፡፡ እኔም ከነዚህ ሐዲሶች መካከል የተወሰኑትን በማቅረብ መፅሐፉን እገታለሁ ፡፡ 1ኛ አላህ መዲናን የተከበረች ማድረጉን በተመለከተ የተወራው ሐዲስ ነቢዩ እንዲህ አሉ (ጌታዬ ኢብራሂም መካን የከበረች ጥብቅ እንዳረጋት ሁሉ እኔም መዲናን በሁለት ማእዘኖቿ መካከል ያለውን ቦታዋን የተከበረ እና ጥብቅ .
135
አደርጌ የዋለሁ ፡፡ እሱም ደም ላይፈሰስ ፤ የጦር መሳሪያ ላይያዝ ፤ ለእንሰሳዎች ቀለብ ካልሆነ በስተቀር ዛፍ ላይቆረጥ ነው) 300 2ኛ መዲና ከዐይርና ከሰውር ጋራዎች መካከል ያለው ምድሯ ልክ እንደ መካ ሐረም የተጠበቀ መሆኑን የሚያመለክተው ሐዲስ ነው ፡፡ 3ኛ ነቢዩ ሙሐመድ (ዕባብ ወደ ዋሻው እንደሚመሺግ ሁሉ ኢማንም ወደ መዲና ይመሽጋል) ያሉት ሐዲስ ፡፡ የሐጅ ተግባር በሚፈጸምበትና በክንውኑ ወቅት ተግባሪው ሐጅ የሚባል ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ሐጅን በማድረጉ ብቻ የማዕረግ ስም እንደሆነ መቀጠሉ ይዩልኝና ይስሙልኝ በማምጣት ተግባሩን ሊያበላሽበት ስለሚችል መቅረት ያለበት አጠራር ነው ፡፡ ሁሉን ነገር አላህ ያውቃል ፡፡ በመጨረሻም የሀገራችን ሙስሊሞች በሰላም እምነታቸዉን መተግበር እንዲችሉ የሁሉም ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክቡር ጠ/ር ዶክቶር አብይ አህመድ አመራር የተጀመረው የሰላም ፤ የእርቅ፤ የልማት ሂደት ጠንክሮ እንዲቀጥል ሁላችሁም ዱዓ እንዳትረሱ አሳስባለሁ ፡፡ ሁጃጆች በሰላም ወደ ሀገራችሁ ይመልሳችሁ ፡፡ ስለ ሐጅና ዑምራ የታሰበው ትምህርት እዚህ ላይ አበቃ ፡፡ ሸይኸ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን ኸሊል 23/11/1439
300
ሙስሊም الحج المبرور
ትክክለኛው ሕጅ
ዋቢ መፅሐፍት ተ.ቁ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20
የመፅሐፍት ስም የደራሴው ስም ዘመኑ አል ሙምቲዕ ሸይኽ ዑሰይሚን አልፊቅሁ ኢስላሚይ ዙሐይለ ሶሂሁ ፊቅሁ ሱና አቡ ማሊክ ፊቅሁል ኪታቢ ወሶሂሂ ሱና ዐዛዚ ፊቅሁ ሱና ሰይድ ሳቢቅ አል ፊቅህ ዐለል መዛሂቢ ል አርበዐህ አል ጀዚሪ ሲፈቱል ሐጅ ወል ዑምረህ አል ኢብሃጅ ሱደይስ አልሚንሃጅ ኢፍዐል ወላ ሐረጅ ሰልማን አልዐውደህ ደሊሉ ዛኢር ሊል መስጂድ አል ሐራም ተብሲሩ ናሲክ ዐብዱል ሙሕሲን በድር ከይፍ የሁጁል ሙስሊም ከይፍ ዩአዲል ሙስሊሙ መናሲከል ሐጅ ወል ዑምራህ ሚን አስራሪል ሐጅ ወመናፊዒሂ ሓሉ ሰለፍ ፊ ል ሐጅ ሃከዛ ሐጀ አረሱል ደሊሉል ሐጅ ወል ሙዕተሚር ወዛኢሪ መስጂዲ አረሱል ማ የፍዐሉሁ ልሓጁ ወልሙዕተሚር ነሑጁ ወላ ነተገየር
.