Data Loading...

ATERIRA Volume 7 Flipbook PDF

ATERIRA Volume 7


118 Views
120 Downloads
FLIP PDF 767.03KB

DOWNLOAD FLIP

REPORT DMCA

1

የተመረጡ አጫጭር ፅሁፎች ስብስብ ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

2

በዚህኛው ቅፅ

ኮብላዩ

BEZ BROWN

KALKIDAN GETNET

HAYMANOT GIRMA

AMHAGETA YILMA

ABDULKERIM ESSA

POMY HAILU L

LEOUL ZEWELDE

NEBIYU SEYOUM

ዋቅጅራ ከበደ

EL NATTY DAGNAW

MESAY A. DEGUALEM

ህላዊ ተስፋዬ ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

3

አዘጋጆቹ “ቅጠል ቆረጠና መድሃኒት ነው አለኝ ምነው ፈራ ሆዴ ሊቀረ ነው መሰለኝ “አስኒ፡ የክራር ንግስት

ሰላም ሰላም... ይሄው አጤሬራ እናንተን ተማምና ቀጥ ለጥ ብላ ቅፅ ሰባትን ይዛ ከተፍ ብላለች! ከባለቤቱ ያወቀ የኬጂቢ ሰላይ ነው እንዴ እማሆይ ቆፅለገነት እኛ መሃል ሰፋሪ እናንተ ባለቤት ናችሁ እና ይሄን እጠፍ ይሄ አቅና በሉን! እስካሁንም ለምታነቧትም ለምትልኩላትም ሁለት ፎቅ እና አንድ መርከብ... መስጠት ነበር ! እሱ ስለሚከብድ በገንዝብ የማይተመነውን የትዬለሌ ምስጋና እናካችሁ ብለናል። ዛሬም ነገም ከትናት ወዲያም አጤሪራ የእርሶ ናትና ሳይሳቀቁ ስራዎትን ይላኩልን!

አጤሪራን ያንብቡ - ለአጤሪራ ይፃፉ - አጤሪራን ለወዳጆችዎ ያጋሩ! ሁሌ እንደምንለው ያለእናንተ ተሳትፎ አብዮቱ ግቡን እና እስክስታ አይመታም!

Telegram | https://t.me/aterira

Facebook | https://www.facebook.com/aterira ቅፅ-7

Call | +251 925 749 956

ታህሳስ| 2012

4

ኮብላዩ ጠየቁ! እቴሜቴ የሎሚ ሽታ፣ ያ ሰውየ ምይ አለሽ ማታ? መለሰች። “ምንም ምንም አላለኝ ትዳሩን ፈቶ ልውሰድሽ አለኝ”። ጠ የ’ ኩ |’ኔ’|። የት አይቶ ተመኛት? ምን ጎሎት ከሚስቱ ?እንደምንስ ሻታት? ቀልቡ ወዷት ይሆን ?ሚስቱ አናዳው ይሆን?የለም ወይ ጠልቷት ነው ?አይ ደብራው (ማለት ከምድር ተነስቶ ሰውየው ይደብታቸው ይሆናል አንድ አይነት ኑሮ ሲደጋገም ይሰለች የለ?) እና አዲስ ነገር ልሞክር ብለው?። እሷስ የልቧ መሸፈት ! ምን ይባላል? ገና በኮረዳነቷ ? ገና አጎጠጎጤ ነችኮ ! አይኖቿን በፍርሀት ከጉብል አይን የምታሸሽ ፣የቀይ ዳማ፣ በሀፈረት ስስቅ የጉንጮቿ ስርጉዶች (ዲምፕሎች) ብቅ የሚሉላት ፣እንደወሎ ልጃገረድ ፀጉሮቿ ላይ ብዙ ቀለም ያለው መሀረብ ጣል ያረገች፣ ብዙ ሰማያዊ አበባ የተሳለበት ቀሚስ የለበሰች፣ ኮንጎ ጫማ የተጫማች በ፣አንድ እጇ አፏን ሸፍና እየሳቀች በሌላኛው የተደገፈች አይነት ኮረዳ። ወይ ልቧ ሲ’ ሰቀል ፡ ሰውየው (እሳቸው ባለግ’የው) ያሏትን ለጓደኞቿ ልታወራ ስትሮጥ። . ምንም ምንም ምንም አላለኝ፣ ትዳሩን ፈቶ ልውሰድሽ አለኝ ።ስትል! የነሱስ የወሬ ሱስ (አይጣል) ተሰብስበው አንድ አረንጓዴ ሳራም ሜዳ ላይ ተቀምጠው ፤ እሷ ቆማ በጥያቄ ሲያጣድፏት (በጃዝ የሚጨፍር የሚመስል ድንገቴ የክረምት ንፋስ እያፏጨ ሲያልፍ፣ ረጃጅም ፀጉሮቿን በሆነ ቅብጠታዊ ፓተርን ፊቷን ሲያለብሰው፣ በጣቶቿ እየመሰለችና ...የመሳሰሉት) ። እቴሜቴ የሎሚ ሽታ ( ውቢት ደሞ ጠረኗ የሎሚ ሽታ ነችና) ያሰውየ ምን አለሽ ማታ ሲሉ። (ሰውየም ሰውየ ናቸውና ፡ኮፍያ ሚያረጉ ፣ጠይም ሽበት ጣል ጣል ያለበት ፀጉር ያላቸው፣ ወፍራም ጃኬት የሚለብሱ፣ ከዘራ አልፎ አልፎ የሚይዙ ጭምት ሰውየ ፡ ጎልማሳ ናቸውና። ) ደም ወዳጆቿ ምቀኝነታቸው (አይ ‘ሴት ብላ ይሆናል ውቢታችን በልቧ) ። ምንም ምንም ምንም አላለኝ ትዳሩን ፈቶ ልወስድሽ አለኝ ስትላቸው ። አለማመናቸው ። ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

5 እንዲህ ማለታቸው የምቀኛ ጎረቤት በሚመስል ምላሳቸው። አይወስድሽም ትዳሩን ፈቶ ምሎልሻል ጋሻ ጦር ደፍቶ ። (ብለው ልቧን ቀጥ ማረጋቸው፡ “ውይ ማሳዘናቸው ፣ጓደኞቸ ብየ ብቀርባቸው እኚህስ ክፉወች ናቸው “አሁንም በልቧ። ) ተቀየመቻቸው ፡ ጥላቸው ‘ሮጠች፤ ወፈፈች ወደኦናው። ከሚያሸማቅቀው ማህበራቸው ኮበለለች ። አበደች አሏት ።ቀባጠረች ።እንስሳት ሁሉ እያናገረች ነው። “ነካ “ያረጋት ሸይጣን ነው አሉ ሚስጥሩን (‘ የእንስሳቱን ቋንቋ የገለጠላት ‘ (‘በጆሮዋ ሹክ! ቀን እኮ አያሳብድ’))። ከቤቷ በላይ ቁራ ሰፍሮ ፡ ሸጋዋን ፍለጋ እንደወጣች አይቶ ተረድቶ የለችም ብሎ ሄዶ በሮ፣ የዝሆን አሞት ቀምሳ መሯት፣ ቁራውን ያብረኝ ብላው አሳዝኗት(ምፅ፣ ምፅ) ፣የጎበዝ ልብ ተርሮባት አስደንቋት፣ የጅቡ ለአይያው ማልቀስ በቋንቋቸው ገብቷት ፣ ቁንጫ ቆሞ ፍታት(ሆየ ቁንጫ ! መስቀሉን በቀኙ ይዞ ፣በግራው ፀናፅሉን፣ ራሱን በትልቅ ሻሽ እንደቄስ ጠምጥሞ ወገቡ እጥፍ ዝርጋ ሲል። ) እባብ አንገቱን ሲነቀስ ፡ ይህን ሁሉ እያየች ለኦናው (ለእኛ ) ዘመረች አሉ (ከዛማ የገደል ማሚቶ ዜማውን ከዘመን ዘመን እየተቀባበለ በየገደሉ ተሸሽጎ ሲያጣጥም ፣ካሴት ከች ! በሪኮርደር በሽነና አለችብና) ። ከዚያን ቀን በኋላ ተረቷ በትውልድ ሲቀባበል እኛ ድረስ ክሱት(ውይ ጉዳችን ፈላ) !ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ።

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

6

KALKIDAN GETNET “what’s your name?” They asked him He then told them the name of the old lady who had helped his mother through labor He then told them the name of the priest who was reciting a prayer to our holy mother of God. He then told them the n ame of the angel he was baptized by He then told them the name of the dog he played with growing up He then told them the name of the church he had to bury his dad He then told them the names of the sheep he had to look after He then told them the name of the school he had a dream of joining but couldn’t he then told them the names of his brother and sister he had to sacrifice his dreams for He then told them the name of the girl he ever loved And the name of the old man who paid her parents a great deal for hand in marriage “What’s your name?” He was asked He then told them the name of a town he wished to runaway he then told them the name of a girl he impregnated and stay He then told them the name of her mother who begged him to marry He then told them the names of the children she gave him He then told them the name of the school he sent his children to He then told them the name of the tree he wants to be buried six feet under He then told them a name After all that At last He told them a name he wished he had. ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

7

UNCHAIN MY WORDS AMHAGETA YILMA

You got me naked You got me cold Have mercy on me As I am your only prisoner. I tell you Now that my life is dull I don’t have the words to cut through your thick skull. Unchain my mind Unchain my soul Let my thoughts fly Up in the free sky. Twilight The beauty of the day It’s never the day light Nor the blackness in the night It’s about that time when The darkness mingles With sunlight Spiking colors like a ray Escaping the dark in the sky.

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

8

#ColorizingHistory

Tojo’ the lion guarding the Jubilee Palace in Addis Ababa, 1965.

Source: https://www.facebook.com/colorizinghistory ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

9

BEZ BROWN ጥፍር ቀለም ያን ያህል አልወድም የምቾት ግዜው ትንሽ ነው:: ከዛ የሚቀረፋፈተው የሚላላጠው ነገር ያስጠላኛል:: አምሮበት ከሚቆየው ይልቅ የሚያስጠላበት ግዜ ይበልጣል:: ግን ያን ለት ጥፍሬን ቀለም መርጬ ተቀባሁ..ያሉኝ የውስጥ ልብሶች አረጁብኝ ... አላረጁም ግን ገላዬን ሲዳብሰኝ ጡት መያዣዬን ሊከፍት ምናምን እጁን ሲሰድ የተፋተጉ ጨርቆች የወለዷት ድብሉቡል ንጭጪት እንድታጋጥመው አልፈልግም ... አንዲትም ብትሆን እንኳ... አዲስ ጡት መያዣ አዲስ እሙሙ ማፈኛ ገዛሁና ለብሻቸው መስታወቴ ፊት ዞር ዞር አልኩ:: ጡቴ ፍንጯ ሲቀር አጋልጧታል ከግማሽ በላይ የሚሆን ቂጤ ውጪ ነው:: እነዛ ፊልም ላይ ሳይጠየቁ የልብስ ቁልፋቸውን ተረረም አድርገው ከጉልበታቸው በታች እንደሚነሰንሱት ሴቶች አስመስሎኛል:: እኔ ታግለው የሚያወልቁት ጠባቅ ሱሪ ነው ያለኝ:: ሌላው ቢቀር ብዬ ፀጉሬን ፈታሁ እና ጀርባዬ ላይ ጣልኩት ...ነስነስ ነገር ... ከትከሻዬ ወደሁዋላ መታ ... እዚች ደረቴ አጥንት ስር ምንድናት? ኦኦ ምንስ ብትሆን አሁን እሱ ይሄን ማያ ሰአት ይኖረዋል? እንዳገኘኝ ልብሴን ቡትርፍርፍ ውልቅልቅ አድርጎ ወደስራው ይግባ እንጂ... የሆነ በሩ ላይ ደርሼ ሳንኳኳ ደረጃውን ለወጣሁበት ትንፋሼ ሰአት ሳይሰጠኝ ጠልጠል አድርጎ በሩን በእግሩ ዘግቶ ሶፋ ላይ እንዲጥለኝ እንጂ ይቺ ደረቴ ስር ስላለች ነገር እንዲጠበብማ ባልፈቀድኩለት ...አንገቴን ሰበር እሽኩርምም ..ደሞ ደረቴን ነፋ ..ሆዴን አንጀቴን ሳብ አድርጌ በጎኔ ጋደም ..እንዴት ልሁን? ተነስቼ በሌላ ጎኔ መልሼ ጋደም .. በየቱ ጋር እንደሚመች ... እያሰብኩ... ደሞ እጋብዝሻለሁ ያለኝን ሙዚቃ ጫፉን ይዤ እያንጎራጎርኩ ...”ደረስኩ ውጪ” እስኪለኝ የምጠብቀው ልጅ በሆነ መንፈስ አብሮኝ እንዲሆን ተመኘሁ... ለምን አይሆንም? ለምን አልፈቅድለትም? መንፈሱን እንደምቦቃቅላ እጁን ይዤ ዳዴ እያስባልኩ ወደተቃጠለ ሰውነቴ እንዲወጣ ስፈቅድለት.... ማንም በሌለበት ቀላል መንፈሱ ላዬ ላይ ሲሰፍር ትንሽ በጣም ትንሽ “እህህህ” አስባለኝ ...ትናንሽ ትንፋሾቼ ተጠራቀመው የእሱን ስም አስቃተቱኝ ... የምንገናኝበት ሰአት ራቀኝ... አልጋዬ ጫፍ ላይ በጀርባዬ ጋለል... እሱ እንዳለ ሁሉ... ይሄን ሁሉ የምሆንለት ....ጥፍር ቀለም የተቀባሁለት ልጅ አጠገቤ እንዳለ አስቤ አይኔን ስልምልም ጭፍንፍን ... ከየት መጣ ሳይባል ከነወደድኩለት ሽቶው ጭምር ህሊናዬ ውስጥ እንደ ድንገተኛ ጎርፍ ሿ ብሎ ሙልት.....አቅበጠበጠኝ.... ቀስ ብዬ እጆቼን ወደጡቶቼ ላኩ... መጀመሪያ ከላይ በጡት መያዣው ላይ ዳሰስኳቸው ምንም የተነጨ የተነጫጨ ነገር የለም ይሄ ራሱ ሴክሲነት ይኖረዋል.. አልጠራጠርም ...ቀስ ብዬ ፈታሁት ወደመሬት ጣልኩት... ፍንጭ ፍንጫ ቸውን ቆንጥጬ ያዝኳቸው ... ቁንጥጥ ሳብ ..እሽት ለቀቅ.. በመዳፌ ጨመቅ ለቀቅ አደረኳቸው ትንፋሼ እየጋለ መጣ.... በገዛ ሆዴ ላይ በጣቶቼ ተራመድኩ.. ልክ እሱ እንሰሚያረገኝ ሁሉ እየነዘረኝ ....ዝቅ ዝቅ ወደታች ፓንቴ ጠርዝ ላይ ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

10 ደርሼ ስሻገር ልቤ ንጥር ንጥር ስትል.. ከአይምሮዬ ጋር የነበረኝን ትግል ትውት yes ...yes... yasss የእሙሙዬ የላይኛው ክፍል እና የውስጠኛው ክፍል መጋጠሚያ ወሰን የሆነችው ያች ቦታ ላይ ትንሽ ቆም ..(ይቺ ቦታ ለኔ ብቻ ነው ልስልስ ብላ ደስ የምትለኝ ወይስ ወንዶችም ይወዷታል? )እርግጠኛ አይደለሁም ..ልብ ይሏታል ለመሆኑ ? ... አዎ አሁን ብቻዬን እንደሆንኩ አይደለም ሁኔታዬ ..ማቃሰት ሳያስፈቅደኝ አፌን ፈልቅቆ በጥርሶቼ መሀል እንደፉጨት እያመለጠ እህ እህ እህህህ ..... ሸርተት አልኩ ... ወደ ውስጥ ....ስልኬ ጠራ ደነበርኩ... ፍርግጥ ብዬ ተነሳሁ... እሱ ነው:: የምሰራውን ሲያይብኝ እንደቆየ ሁሉ እፍር ብዬ ተነሳሁ ... ደሞ “ቆዪ እሱ ጋራ እኔ አለሁልሽ ሊለኝ የደወለ መሰለኝ “ ተንገብግቤ አነሳሁት... “ወዬ” በፍስሀ ... “ብታይ መንገዱ ዝግትግት ብሏል..ገና ... ያለሁት ....” አይኔ ፈጠጠ ክዛ በሁዋላ ያለውን አልሰማሁትም! ሰውነቴ ላይ የሆነ ጥግ ቆሞ እቺን ሰአት በስላቅ ሲጠብቃት የነበረ ዱካክ ውሀ ችልስ አደረገበት... ኩምሽሽሽ ... ስልኬን ዘጋሁ:: እርቃኔ ላይ የቀረችኝን አንዲት ብጣሽ ፓንት አወለኩ የማታ ሰፊ ቢጃማዬን ለበስኩ... አልጋዬ ውስጥ ገባሁ.. ከምናምኔ መውጣት የነበረበት ፈሳሽ ከአይኔ ተዥጎደጎደ በብሽቀት ጥፍር ቀለሜን በጥርሴ ፈቀፈኩት::

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

11

ይድረስ ባለህበት

HAYMANOT GIRMA 2 years ago today I watched you take your last breath. Your two sisters, your mom and I stayed up all night, whispering to you that it was ok to go. Your son was there too. He was just a little nugget then, still growing in my womb. When that moment finally came, you took a shallow inhale, but the air did not find it’s way back out. You were so still, and I knew you were gone. I did not cry, for I had shed them all hours before. I was filled with relief that you were no longer in pain. I was devastated that I would never hear your voice again. I was angry at you for hiding your illness from me, because you didn’t want to be a burden. I was angry with myself too, for not seeing how much you were suffering. For not being more insistent in helping you to tell you that it was ok to ask for help. I remember the first time you came and spoke to me at work. You shook my hand and introduced yourself, “Nice to meet you Haymi, I’m your team leader. And my name is Danny” Hahaha, this still makes me laugh to this day. You took your job so seriously and not going to lie, you were the most irritating guy to work with ever. Our very first shift together even got people talking, I remember everyone being like “oh look at Haymi and Danny” “There will be new couple soon, just you wait and see” I absolutely loved the attention especially when you didn’t deny any of it. I knew from the start that there was something special about you. የደስታ ጊዜያቶቹ አለፉ። የማላውቀው አንተ መጣህ... I remember you as a man with many flaws. A man who made unwise choices that tore us apart. Your addiction cost you everything. Your relationship, Your son, Your family, Your freedom and Your soul. Each day you told me it would be different. Yet, it was the same. Down 2 pills with your morning coffee. 2 more in the afternoon. 2 in the evening. No matter how many you took, it was never enough. ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

12 And I was unfamiliar with drug addiction. I didn’t understand how addiction rewires the brain to do anything to get a fix; I didn’t understand that addiction possesses people like a demon, leaving the beautiful person that was once there to succumb to his sickness. Had I known how evil addiction was when we met, I would have stayed very far away from you. Although you are gone I have many days where I feel you are still here. It’s ridiculous but I find myself talking to you all the time and I know you listen. You were a man of many flaws. But in the end, despite it all, we made amends. I see now how I am so much like you. a fool with a tender heart, who would never give up on love, no matter how much it hurt. I will always admire you for that so this is what I’ve been waiting to tell you, and that I miss you.

Your Love Lives On By Shawna Erback ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

13

ABDULKERIM ESSA የድሮ ሰው ስም ሲያወጣልህ እንደ አሁኑ በዘፈቀደ አልነበረም። በስሙ ውስጥ ሊያስተላልፍልህ የሚፈልገው መልዕክት አለ። ከጀርባው የሆነ wisdom አታጣበትም። ብሶቱን፣ደስታውን፣ምኞቱን፣ጉራውን በሚያወጣቸው ስሞች ታያለህ። ያ በሰው በሬ እያረሰ ሲሰቃይ የነበረው ጭሰኛ ገበሬ በመጨረሻም የራሱን በሬ ሲገዛ ያለፈበትን ውጣ ውረድ ሊገልፅ ሲፈልግ በሬውን “መቻል” ብሎ ስም ይሰጠዋል። እነዛ ልጅ መውለድ እምቢ ብሏቸው ከብዙ ሙከራ በኃላ የወለዱ ባለትዳሮች ልጃቸውን “ቦጋለ” ይሉታል። አይ ሰው፣ገርባቸው፣አነባብራቸው፣ሰጥአርጋቸው፣ደባልቄ ብሎ ወይ ለበደሉት መልእክት ያስተላልፍበታል ወይ ጀግንነቱንና ጉረኛነቱን ሊነግርህ ይሞክራል( አስቡት ይሄ ሰውየ አራት ኪሎ ቢገባ ጨርሶን ነበር......ሃሃ)። ያች ልጅ ስትወልድ ጤናዋ የተመለሰላት እናት “መድሀኒት፣ፈውስ” ብላ ስም ታወጣለች። “ጀንበሬ” ብላ ደስታዋን ትገልፅበታለች። አንድ ዘመዶቿ ሁሉ በድለዋት ብቻየን ከድመቴ ጋር ነው የምኖረው ያለች ሴት ድመቷን “ዘመዴን ተውኩት” ብላ ትጠራት ነበር። በነገራችን ላይ ለሰው ወይም ለ እንስሳ ብቻ አልነበረም ለ ሰፈር፣ለ እቃ፣ ለከተማም.... ትርጉም ያለው ስም ነበር የሚያወጡት። ለምሳሌ ለልብስ የሚወጡ ስሞች ነበሩ። በጣም ውድ የሆነውን ቀሚስ የባልን ኪስ የሚያራቁተውን “እሪ በል ወንዱ” ብለው ስም ይሰጡት ነበር። shine የሚያደርገውን ቀሚስ “ብቅ በይ ተጓዳ፣አማቴ አይስሙ” ፣ ጥለቱ በውሀ የማይለቀውን ቀሚስ “ወንዝ አይፈሬ” ይሉታል። እንደውም አንዷ ኮረዳ እንደዚህ ብላ ገጥማ ነበር “ እምወድህዋ ወንዝ አይፈሬ ቀሚስ ተገዛህልኝ የገረዶ ወስደህ አሻቦ ጫነኝ ተዚያ መልስና በጥጥ ቀንጥበኝ” ሌላኛዋ ደግሞ “ ፈሰስ በገላየ ብቅ በይ ተጓዳን ተገዛህልኝ እንኳን በጀርባየ ባፍጢሜ ድፋኝ”

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

14

#ColorizingHistory

እንኳን ለፍቅር ለጥልያንም አለተንበረከኩ

Source: https://www.facebook.com/colorizinghistory ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

15

ትናንሽ ኑዛዜዎች POMY HAILU L

(ክፍል 1) ሃያ አምስት አመቴ ነው፡፡ አልጋዬ ውስጥ ሆኜ ያለማቋረጥ በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው ደግሞ በነዛ አመታት ውስጥ ያሳለፍኳቸው ትውስታዎች ናቸው፡፡ እንዳሉ እንኳን የዘነጋኋቸው የመሰለኝ ትዝታዎች ልገምት ከምችለው በላይ የበዙ ሃሳቦች፡፡ ተደምረው ህይወቴን የሞሉ አጋጣሚዎች፡፡ ለኔ ግን ከዛም በላይ ናቸው፡፡ እነዚህ እኔንና እሱን ያያዙ ገመዶች ናቸው፡፡ ለምንድነው ይህን እያሰብኩ ያለሁት? ሃያአምስት አመቴ ነው እናም ለሞት ከምንም ጊዜ በላይ ቀርቤያለሁ፡፡ ውጪው ሞቃት እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ሁሉም መስኮቶች ተከፍተው አልፎ አልፎ ውልብ ሚል ንፋስ ክንዴን ሲነካኝ ይሰማኛል፡፡ እጆቼን አየኋቸው እንደሁሉም የሰውነቴ ክፍል ቀጥነዋል፡፡ አልጋዬ ምቹ ነው ይሞቃል የትም መሄድ እንዳልፈልግ የሚያደርግ አይነት ምቾት እንዳልፈራ የሚያደርግ አይነት ምቾት ምናልባትም ላዩ ላይ ከመቆየቴ ብዛት ተላምጄው ይሆናል፡፡ ይህ ግን ከሰላሳ ደቂቃዎች በፊት ነበር፡፡ ከግማሽ ሰአት በፊት ዳግም ክፍሌ ውስጥ ገብቶ ከቆመ በኋላ ግን ምቾቴን ነስቶኛል፡፡ መጣብኝ እንዳልል መምጣቱን ወድጄዋለሁ ፡፡ ድንጋጤዬን ነው መቋቋም ያልቻልኩት፡፡ የደበዘዘ ፈገግታ ፊቱ ላይ አለ፡፡ ከተናገረኝ ነገር በኋላ ግን ምመልስለት መልስ አልነበረኝም መልሼ ለመሳቅም አልሞክርም፡ ፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ጊዜዎች ትውስታ አእምሮዬ እየተበጠበጠ በመሆኑ ሌላ ነገር ማሰብ አልችልም፡፡ አስቤ ከመናገሬ በፊት አፌ ቀድሞኝ ልቤ ውስጥ ያለውን መናገሩ አይቀርም ከዛም ሁሉም ነገር ይታወቅብኛል ስሜቴን ያውቅብኛል ፍቅሬን ያውቅብኛል፡፡ ችግሩ ዝምታዬ ራሱ መልስ መሆኑ ነው፡፡ ዝም ብዬው ስቆይ ‹ችግር የለውም› አለ፡፡ አየሁት፡፡ ከዛም ወደእጮኛው ቤቲ ዞርኩ፡፡ አጠገቡ ቆማለች፡፡ ፊቷ ላይ ምንም አይነበብም፡ ፡ በጥንቃቄ እያየችኝ ነው፡፡ ለሷ ምን ማለት እንዳለብኝም ሆነ ምን እያሰበች እንዳለች ማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግራ የተጋባ ፈገግታ ፈገግ አለችልኝ፡፡ በቀስታ ወደአልጋዬ ተጠጋች፡ ፡ ፈራኋት፡፡ ፈገግታዋ ግን አያስፈራም ምታባብለኝ ትመስላለች ወይም ያዘነችልኝ፡፡ ጎንበስ ብላ አቀፈችኝ፡፡ ክንዶቼን በቀስታ አንስቼ መልሼ ላቅፋት ሞከርኩ አቅም አልነበረኝም፡ ፡ ወደጆሮዬ ተጠግታ ‹እናንተ አውሩ እሺ እኔ ውጭ እሆናለሁ› አለችና ወደኋላ ፈቀቅ ብላ አየችኝ፡፡ የተናደደችብኝ አትመስልም ትንሽ ሰላም ተሰማኝ፡፡ አሁንም ቢሆን ጓደኛዬ ነች ከሄድኩ በኋላ ከሚናፍቁኝ ሰዎች አንዷ መሆኗ የማይካድ ነው፡፡ መቼም ላሳዝናት አልፈልግም፡፡ እኔና ዳግም ብቻ ቀረን፡፡ እያየኝ ነው እንደሁልጊዜው አምሮበታል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ መቼ እንዳየሁት ለማስታወስ ሞከርኩ፡፡ አራት ወራት…. እንደቀልድ ያለፉ አራት ወራት፡ ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

16 ፡ በየቀኑ ስለአንድ ሰው ማሰብ የጊዜን ትርጉም ሳይቀይረው አልቀረም፡፡ ምናልባትም ጊዜ ማለት እሱ ይሆናል፡፡ ዝም ብሎ የሚፈስ ወንዝ …. ቀስ ብሎ እንዲሄድልን ያገኘነውን ሁሉ ምንጨምርበት ወንዝ፡፡ ሰዎችን፤ ትውስታዎችን፤ ቦታዎችን ምንሞላበት ወንዝ፡፡ ጸጉሩን ተቆርጧል፡፡ ቤቲ አስገድዳው ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ፡፡ አይኖቹ ከበፊቱ የተለቁም መሰለኝ፡፡ ከሚታየው ነገር አልፈው ውስጤን የሚያነቡ ሚመስሉኝ አይኖቹ፡ ፡ ለራሴ ደግሜ ደጋግሜ እውነት እንዳልሆነ ተናግሬያለሁ ማንም እንዲያውቅብኝ ማልፈልገውን ማንነቴን እንዲያውቅብኝ አልፈለኩም ግን አልተሳካልኝም፡፡ ዳግም ረዘም ያለ ከቁመቱ ጋር የሚመጣጠን ሰውነት ያለው ቀላ ያለ ልጅ ነው፡፡ እስኪስቅ ድረስ ለሰው ብዙም የሚያምር ላይመስል ይችላል፡፡ ፈገግታው ግን ያ ነው የሱ ውበት ምናልባትም ለዛ ይሆናል ሁሌም የሚስቀው፡፡ ከሳቀ በዙሪያው ያለውን ነገር ሁሉ ወደሌላ አለም መውሰድ የሚችል ሀይል አለው፡፡ ሲስቅ በፊት ከነበረው እሱነቱ ሚጨምረው ነገር አለ፡፡ ትክክለኛ ማንነቱን እንዳወጣ አይነት፡፡ ‹ለምን አልነገርሽኝም› በቀዘቀዘ ድምጽ ጠየቀኝ፡፡ ፊቱ ላይ ፈገግታ የለም፡፡ ‹ሁሉንም ነገር ሊቀይር ይችል ስለነበር› መለስኩለት፡፡ ‹እሱን አታውቂም› ‹አውቃለሁ› ተናገርኩ፡፡ እውነታው ግን ምን ታውቂያለሽ ብሎ ቢጠይቀኝ መልስ አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም ለሰባት አመታት ያፈቀርኩት ሰው ሆኖ ሳለ ራሱ አሁንም ምንም ነገር አላውቅም አሁንም እንደአዲስ ያስደነግጠኛል፡፡ ‹ምንም አታውቂም› ውስጤን እያነበበ የተናገረ መሰለኝ፡፡ ጎንበስ ብዬ የተጨበጠ እጄን አየሁት፡፡ ብችል የሆነ ነገር ብመታበት ደስ ባለኝ፡፡ ጣቶቼን ዘርግቻቸው እንዳዲስ አየኋቸው፡፡ ቀጥነዋል በጣም ቀጥነዋል ይገርማል ሁሌም መክሳት ምኞቴ ነበር አሁን ግን ከምንም በላይ መወፈር ፈለኩ......

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

17

TEARDROP EARRING LEOUL ZEWELDE If you ask me, it was the most amusing yet craziest night I remember. Every single one of my friends was drunk and I, I was a little on the tipsy side. The concert we were attending was filled with people that were twirling with a psychotic dance in the streets. Every move they make was too antic.

In all of that craziness though, I was bent half searching in the darkness for a tiny earring. One of the dancers next to me, a girl I haven’t met before had dropped it. I don’t even understand why she wouldn’t let it go. I mean, she wore many stylish jewels, and in my eyes, she already had enough bling on her. Inadvertently, my eyes were pulled to her left hand. No wedding ring. That was the only finger on both her hands that wasn’t adorned by some kind of rings. “ታገኘዋለህ ብለህ ነው? She shouted to surpass the sound of band music. I found myself saying “ልሞክር cutie pie” . I have never been this witty. Nor this forward. I looked up into her face and I froze. Her features had some sort of memory in me spiking. “ምን አልከኝ?” ... she said. I hesitated to reply again. It must be a trick in my mind. Where would I know her? Why did my heart beat this fast ? I forced myself to look back down to the ground again and started searching for that tiny eardrop earing, all the while asking myself “What the hell am I doing?”. Because I know these days people mistaken kindness for flirting. Me, I was being both kind and amorous at the same time. It was an unexplainable adventure and battle to find a tiny earring while being drunk. The search was not that easy. Exploring for a time time that felt like a decade, I finally spotted it blinking in the random concert lights under a filthy use and throw solo cup. ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

18 Getting up from where I was kneeling on the dirty ground with the music exploding in my ears, I looked into her bewitching eyes and saw her beautiful yet confused smile directed at me. “You know; you didn’t have to do that” she said. 9 ... 8 ... 7 ... The crowd started to chant, impatient to leave the old year behind. 6 ... 5 ... 4. Yet she didn’t thank me. She looked like a person I used to know in my past life so I pretended like I don’t want any compliment from her. The crowd continues to count. 3 … 2 … 1. And then Something explodes. On spur of the moment, I kissed her. It was my “ምንም አይደል” rejoinder to the ‘thanks’ that I am pretty sure she uttered in silence. With the syrupy kiss lasting for minutes, I transcended time. It’s been Seven years now and መስከረም አንድ is coming again with full of vivid memories. I love the New Year, I love her, love earrings.

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

19

NEBIYU SEYOUM ለማስታወስ ያህል ካንቺ በፊት ህይወት ነበረኝ። ፀሃይ ለአመታት ሳትጠልቅ እንደፈጀችው ረግረግ ንቃቃት ወርሶት ነበር እንጂ፡፡ በዛ ንዳድ ውስጥ ክንፉን ለዘላለም እኩሌታ አንደረሳ ፈዛዛ መልአክ ቆሜ ነበር፡፡ ቅጠሎቿ ረግፎ መለመላዋን የቆመች እፀ-በለስ ተደግፌ ሳናውዝ አንቺ ተከሰትሽ፡፡ አድማሴን ሞላሽው። መናወዜ ውስጥ ተሰገሰግሽ። የህልሜን ዳርቻ በስውር ክርሽ ዘመዘምሽው፡፡ በዛ ሐሩር ባገኝሽ ጊዜና ... የሽክናዬን ወለል እንዳረጠበችው እፍኝ ውሃ ተስገብግቤ ጭልጥ፡ ፡ ሽክናዋ ከናፍርቴን ከነካች በኋላ ሽክናዋ ባዶ እስክትሆን የጊዜ ክፍተት ነበርን? ጠጪውም አያውቀው። ጠብታዋም አታውቀው፡፡ ጠጪው አሁንም ይጠማል፡፡ በእፍኝዋ ትዝታ አምሮት ይጋያል፡፡ ቀይ-ባህርን በአንኮላ እየቀዱ በገፍ ወደ ጉሮሮው ቢከለበሱት ለእሱ ምንተዳው?! ጥምም እርካታም የሆነች፤ ህይወትም ሞትም የሚወልዱዋት፤ ሙላትም ጉድለትም ያደላትን ጭላጭ ይመኛል፡፡ አብረን ስንሆን ጊዜ ይቀራል፡፡ አብሮነታችን መች በጊዜ ይለካል? በአብሮ መቆየታችን እንጂ፡ ፡ ራስ ወዳድነቴ ይስበኛል እንጂ አንቺን ለሁሉ ባለሙርጢያም ባጋራሽ ምንኛ በወደድኩ ነበር፡፡ እንዲህ ከንፈርሽ ከከንፈሬ እንደተጋጠመ ዘላለም መሽቶ በነጋ ፣ ገነት አርጅቶ በታደሰ … እንዲሁ እንደወደድኩሽ ትኩረትሽ ሳይዛነፍ ቀልብሽ ሳይሰለቸኝ፡፡ ፍቅር አጉርሼ ስጨረስ ከሃጥያቴ ጋር ፈስሼ አንቺን ብቀላቀል ምንኛ ደስ ባለኝ። ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከቃላት በላይ ሆኖ ይሃፀችተየንሯዋህም (ይህን ሃረግ ከቀኝ ወደ ግራ አንብቢው) አድርጎኛል፡፡ በህልውናዬ ገፀ-ምስል (ስክሪን) ላይ የትየለሌ ጊዜ ተከስቶ(ዲስፕሌይ) በሶስት ነጥብ ይቀጥላል፡፡ወደ ጎረቤት ኢንፊኒቲ እሱ ደሞ በተራው እስኪሞላ፡፡ በህልውና መስክ ላይ ችካሎቹ ተራርቀው የተተከሉ የተወጠረ ገመድ አለ፡፡ የእንጀራ ገመዴ ወጥነት እንዴት ያሰለቻል መሰለሽ! አንድም መቋጠር የለበትም፡፡ አንቺ ስትመጪ ገመዴን እንደምትበጥሽውም-እንደምትቀጥይውም አውቅ ነበር፡፡ ፈዛዛ ኑረቴን በጥፊ ብለሽ አነቃሽው፡፡ አምላክ ፡- ጊዎን ዳርቻ ተቀምጠህ የስጋዬን ቋንጣ እየበላህ በፅዋህ ፈለጉን ሞልቶ ከሚፈሰው ወይን ተጎንጭ ከሚለኝ፤ መብረሬን እንደረሳው መቆሜን እንደዘነጋው፣ መንደዴን ችላ እንዳልኩ መኖርን እመርጣለው፡፡ እናም ትዝታሽን እየማግኩ ፣ እፍኝነትሽን እየተጠማው ወደ ቀደመ መናወዜ ብመለስ እመርጣለው፡፡

P.s መጋቢት 20/2004 ለሊት 9:30 የሳይንስ ፋካልቲ ቤተ-መፅሃፍ ውስጥ የተፃፈ። ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

20

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

21

መታቀፍ

ዋቅጅራ ከበደ በስንት አመቴ ከፍላጎቴ ሸሽቼ ይሉኝታ ውስጥ መደበቅ እንደ ጀመርኩ አላውቅም። የወሰደኝን ቦታ ግን አልወደውም። በራስ ጥላቻ መሰረት ላይ የተገነባ የማስመሰል ህይወት ነው። መቆጣጠር ከምችለው በላይ ካልተናደድኩ ፣ ካላዘንኩ ወይም ካልተደሰትኩ ትክክለኛ ማንነቴን ለማንም አላሳይም። ገና ለተዋወቁት ፣ ለማያውቁት ወይም በደንብ ለሚያውቁት ሰው ትክክለኛ ማንነትን በተመሳሳይ መልኩ ማሳየት ትክክል ነው አይደለም የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው። ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። እኔ ግን የማወራው ስለ እሱ አይደለም። እያወራሁ ያለሁት ለመስጠት ቀላል የሆኑ ነገሮችን ለመጠየቅ ሲከብድ የሚፈጥረውን ስሜት ነው። ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ። “የመጀመሪያ” የሚለውን ቃል ለመጠቀም የደፈርኩት አንድ ታናሽ እህት ስላለችኝ ነው እንጂ ቤት ውስጥ በቁጥር በዝተን አይደለም። እናት እና አባቴ በማህበረሰባችን ውስጥ በብዛት የተለመዱ አይነት ወላጆች ናቸው። ማለትም አንድ ሰው በህይወት ለመኖር ሟሟላት ያለበትን ነገሮች የሚያሟሉ እሱንም “ወላጅነት” ብለው የሚጠሩ ወላጆች ናቸው። እንደዛ ማለት ግን ያደረጉልኝን ሁሉ ችላ ብያለሁ ማለት አይደለም። የሚወዱኝ ያህል እወዳቸዋለሁ። መጠኑ ምንም ያህል ቢሆን። በ1989 ማገባደጃ ላይ ስለተወለድኩ አሁን ከደረቀው የኢትዮጵያዊነት ፈለግ ጠብታም ቢሆን እየጠጣሁ ነው ያደኩት። እጆቼ እና እግሮቼ በአቧራ እስኪነጡ ተጫውቼ ፣ የቦኖ ውሃ ጠጥቼ ፣ የአባባ ተስፋዬን ተረት ሰምቼ ፣ እያለቀስኩ አጥንቼ ፣ የሰራተኛ ጡት አሽቼ ነው ያደኩት። ልጅነቴን እወደዋለሁ። የምወደው ግን ላሳመሩልኝ ነገሮች ብዬ ብቻ አይደለም። ልጅነቴን የምወደው ትልቅ ሰው መሆንን ስለምጠላ ጭምር ነው። “ ትልቅ “ ወይም “ ሰው “ የሚሉት ቃላት አሁን ያለሁበትን የእድሜ ደረጃ እንደሚገልጹ እርግጠኛ ባልሆንም። ብቻ በተወለድኩበትና ባደኩበት ዓመተ ምህረትና ባህል ተወልጄ እና አድጌ አሁን እዚህ የህይወት ወር አበባ ላይ ደርሻለሁ (ስለ ወር አበባ ከስሙ እና በየሽንት ቤቱ ጥጋጥግ ተጥሎ ካየሁት መልኩ በስተቀር ምንም ነገር እንደማላውቅ ልብ በሉልኝ . . . “ያማል” ሲባል ስለ ሰማሁ ነው)። የማደግ አንድ አካል ይሁን አይሁን ባላውቅም ይህ የማያቋርጥ (የሚመስል) ራስ እርማት እና ይሉኝታ ህይወቴን ግን አበላሽቶታል (“ አበላሽቶታል “ ትርጉም - እንዲኖረኝ ከምፈልገው ህይወት አግዶኛል)። ከራሴ ጋር በማንነት ብቻ ሳይሆን በመልክም ተሸዋውጃለሁ። ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ማውራት ስለምንወደውና ስለምንፈልገው ነገር እያወራን (ስለ ፊልም ፣ ስለ ሴት (ይኽኛው መቅደም ነበረበት መሰለኝ) ፣ ስለ ራሺያ ስነ ጽሁፍ (ይኼኛውን እሱ ሲያወራ እኔ እየሰማሁ) ስለመሳሰሉት . . . ) በዝናብ መጣል ምክንያት የሞላ ቆይቶም በዝናቡ ማባራት ምክንያት የተራቆተ ካፌ ውስጥ ተቀመጠን አመሸን። ድንገት ከመመላለሱ ብዛት ለምን መጣ ብዬ እንኳን የማልጠይቀው ድብርት ጎበኘኝ። ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

22 ከራሴ ጋር በማንነት ብቻ ሳይሆን በመልክም ተሸዋውጃለሁ። ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ማውራት ስለምንወደውና ስለምንፈልገው ነገር እያወራን (ስለ ፊልም ፣ ስለ ሴት (ይኽኛው መቅደም ነበረበት መሰለኝ) ፣ ስለ ራሺያ ስነ ጽሁፍ (ይኼኛውን እሱ ሲያወራ እኔ እየሰማሁ) ስለመሳሰሉት . . . ) በዝናብ መጣል ምክንያት የሞላ ቆይቶም በዝናቡ ማባራት ምክንያት የተራቆተ ካፌ ውስጥ ተቀመጠን አመሸን። ድንገት ከመመላለሱ ብዛት ለምን መጣ ብዬ እንኳን የማልጠይቀው ድብርት ጎበኘኝ። ከዚህ በፊት በዚህ ስሜት ስጎበኝ እንደማደርገው ስለ ህልሜ (አለመሳካት) ፣ ስለ እሷ (መቼም እንደማልነግራት) እና ስለ እራሴ (ስለ መልኬ ፣ ስለ ፀባዬ እና ስለ ክብደቴ) አሰብኩ። ጓደኛዬ ስለ Terrance Malick ፊልሞች ባህሪ እያወራኝ እኔም ፍላጎቱ ስላለኝ እየሰማሁ ግን ህመሜን እያዳመጥኩ ከተቀመጥንበት ካፌ ወጥተን እስከ ጎሮ ድረስ ሸኘሁት (ጎሮ እስክንደርስ ድረስ ስለ ሌላ ብዙ ነገሮች አውርተናል)። እሱን ተሰናብቼ እኔ ወደ ገርጂ መብራት ሀይል የሚመለስ ታክሲ ተሳፈርኩ። ታክሲው እስከ መገናኛ ድረስ ስለሚጭን ስወርድ በሰዎች ላይ እንዳልረማመድ በማለት ከኋላ ባዶ ወንበር ቢኖርም ሶስተኛው ረድፍ ላይ ሶስተኛ ሆኜ በግማሽ ቂጤ ተቀመጥኩ። ታክሲው ሞላና(?) መንገድ ጀመረ። ረዳቱ ሂሳብ እየሰበሰበ መብራት ሀይል በገባው ተሳፋሪ ብዛት ሀዘኑን እየተናገረ የረር በር ደረስን። ታክሲው ካልሞላ (“ካልሞላ” ትርጉም - ጥቅጥቅ ካላለ) እዚህ ሲደርስ ልማዱ ነውና ቆሞ። አንድ ማርጀት የጀመረች ሴት እና ሁለት አንዳንድ ህጻን ልጅ ያቀፉ ወንድ እና ሴት ታክሲው የቆመበት ቦታ በሰጣቸው ቅደም ተከተል መሰረት ተሳፈሩ። ማርጀት የጀመረችው ሴት ከኔ እግር ስር የታክሲው ሰሪዎች ሳይሆኑ የታክሲው ሹፌር እና ረዳት የፈበረኩት በጣሳ እና ለታክሲው የኋላ ጎማ ተብሎ ታክሲው ውስጥ በተፈጠረው ጉብታ ላይ ሚዛን የያዘ የጣውላ አግድም ወንበር ላይ ተቀመጠች። አንዱን ህጻን ያቀፈችው ሴት ከገቢናው ጀርባ ልጁን ጭኗ መሀል አኑራ ስትቀመጥ ወንዱ ደግሞ የታክሲው የመጀመሪያ የወንበር ረድፍ ላይ ቀይ የአራስ ካፖርት የለበሰች እንደ ባልቴት ሻሽ ያሰረች ህጻን አቅፎ በረዳቱ በኩል ወደ ውጪ እያየ ተቀመጠ። ትንሽ ከሄድን በኋላ በሰውየው እቅፍ ውስጥ ያለችውን ህጻን ልብ አልኩ። ህጻኗም ልብ አለችኝ። ህጻን ልጅ ሲያዩ እንደ ጅል መሆን የማህበረሰባችን ባህል ነውና የድርሻዬ ያልተሳካለት ሙከራ አደረኩ። ፊቴን ባጨማድድ ባላቅቅ ፣ ከንፈሬን ባሾል ብመልስ ፣ አይኔ ባሰፋ ባጠብ ደንታ አልሰጣት አለ። ፈገግ እንኳን አላለችም። እንቅልፏ እንደ መጣ አይኗን በዝግታ እየጨፈነችና እየከፈተች ተመለከተችኝ። የአባቷ(?) ደረት ላይ የተለጠፈችበት መንገድ አስቀናኝ። ጅልነቴን ገትቼ በቅናት አይን አየኋት። እሷም በድካም አይን አየችኝ። ምን ያህል መታቀፍ እንደምፈልግ ተራዳሁ። መረዳቴ ይሉኝታ ይዞ መጣ። ግን እንደሌላው ግዜ ይሉኝታው ከፍላጎቴ በልጦ አልተሰማኝም። የታክሲው ኮርኒስ ላይ ከጭንቅላታችን በላይ ባለው ትንሽ አምፖል እና አልፎ አልፎ ከመንገድ ዳር ፓውዛዎች ተርፎ በረዳቱ ብብት ስር አልፎ በሚገባው ብርሃን ይቺን እድለኛ ልጅ በአባቷ እቅፍ ውስጥ ስትተኛ እና ስትባንን ተመለከትኩ። ደጋግሜ ቀናሁ። ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

23 ሙቀቷ በሚሰማ ሳይሆን በሚታይ መልኩ ሞቀኝ። እራሴን ከኳስ ሜዳ ቦክቼ ስመለስ አስታወስኩ። አባቴ ዱካ ላይ ቁጭ ብሎ ቴሌቪዥን ሲደበድብ ደረስኩ። ዘልዬ ጀርባው ላይ ወጣሁ። እጆቹን የኋሊት ሰዶ እንደ ትንሽነቴ አቅልሎ እንደ ከበድኩት ሁሉ ዝሎ በጭንቅላቱ ላይ አሳልፎ እንደ አራስ ደረቱን አስደግፎ አቀፈኝ። አርማታ ያጨቀየው ሸሚዙ ላይ የእግሬን አቧራ ጠረኩ። ውሎዬን እየኮረኮረኝ እየሳቅኩ ነገርኩት። ከዛም ግንባሬ ላይ ሳመኝ። ከዛም አጥብቆ አቀፈኝ። መብራት ሀይል ደርሼ ወረድኩ። ታክሲው ውስጥ ስገባ የነበረኝ ስሜት ስወርድ ተራብቷል። ስለ ደረስኩበት የህይወት ክፍል እያሰብኩ በቅስታ ወደ ቤቴ አመራሁ። በር አንኳኳው። ተከፈተልኝ። የታናሽ እህቴን ጉንጭ ስሜ የሳሎን በር ላይ ጫማዬን አውልቄ ወደ ውስጥ ገባሁ። አባቴ ትልቁ ሶፋ ላይ አንድ እጁን ሱሪው ውስጥ ከቶ ሌላኛውን ተንተርሶ ተኝቶ እህቴ የከፈተችውን አሸንጉሊት ፊልም እያየ ነው። ሰላም ሳይለኝ ሰላም ሳልለው ወደ ክፍሌ ገባሁ።

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

24

አስገድዶ ከመድፈር ራስህን ለመግታት የሚረዱህ አስር ነጥቦች ወፍዘራሽ መቼም አለም ጨረቃላይ ወጥቶ ምድርን ቁልቁል በሚያበት ዘመን ስለፈቃደኝነት ማውራት አልነበረብንም። ግን ደረቅ ነህ፣ አልገባህም’ እንበል። “እኔ እኮ አይደለሁም… ሰይጣኑ ነው… ድሮስ ‘እሸት እና ቆንጆ አይታለፍም’ አይደል ብሂሉ?! ምናባቴ ላድርግ? ቆንጂትን ሳይ በሽታዬ ይነሳብኛል። አቅሌን ያስተኛል።” አይነት ተልካሻ ምክንያት እደረድራለሁ ካልክ፣ ለሱም መፍትሄ አለን። እንደ መድሃኒት በአንገትህ አስረህ፣ እንደ ዳዊት ልደጋግመው የሚገባ አስር የምክር ነጥብ እነሆ! ከነጥቡ በፊት ‘እሸት እና ቆንጆ አይታለፍም’ ላልከን ቆንጂትንም መብቷን ገፍተህ ከምታስጨንቃት፣ ስሜትህን ገትተህ ብታልፋት አለም አይጠፋምና ብሂሉን እርሳው። እሸት ዕድሜህን በነውረኛነት አትለፈው። ክብርህን ጠብቅ። ገባህ አቶ እሸቱ?! ራስን ከመድፈር ለመግታት የሚረዱህ እነዚህን አስር አስር ነጥቦች አስታውስ፦ 1. ድግስም ላይ ሆነ ሌላ ቦታ ብታገኛት፣ የምትጠጣው ነገር ውስጥ ራሷን የሚያስት መድኃኒት አታድርግባት! 2. መንገድ ላይ ስለየሃት ብቻ መናገርም ሆነ መላከፍ አለብህ ብሎ ያስማለህ ማንም የለምና ዝም ብለህ እለፍ! ጎንበስ ብለህ አረጋግጥ፣ ይህን በማድረግህ ወንድነትህን አልተነጠክም። 3. አውቶብስ አምልጧት፣ ታክሲ አጥታ አልያም ከሄደችበት ስትመለስ መሽቶባት መንገድ ዳር ቆማ ስታገኛት፣ እና ለመርዳት ስትቀርብ ዝም ብለህ እርዳት! እርዳታህ የመድፈሪያ የፈቃድ ካርድ አይምሰለህ! 4. ልብሷን ልታለቀለቅ አንተም ከብት ልታግድ ወንዝ ወርዳችሁ ብቻችሁን ብትሆኑም እንኳን አትድፈራት! ሌላ ቦታም ብቻችሁን ብትሆኑ አትድፈራት! 5.

ብቻዋን ከመደብ ተኝታ ብታገኛት አትድፈራት!

6. እንደሙት መንፈስ ስትገባ ስትወጣ ተደብቀህ አትከታተላት! ተዋት! እና አትድፈራትም! 7. አስታውስ! ጫካ የምትወርደው እንጨት ልትለቅም ነው! ካፌ የምትገባው ቡና ልትጠጣ ነው! ቢሮ የምትቀመጠው ስራዋን ልትሰራ ነው! ታክሲ ውስጥ የምትገባው ከጉዳይዋ ለመድረስ ነው! ፈፅሞ ትንኮሳም ሆነ ጥቃት ፈልጋ ነው ብለህ አታስብ! አትድፈራትም! ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

25 8. ካየኋት ያቅበጠብጠኛል ካልክ፣ አሪፍ ወዳጅህን ፈልግ እና ሲነሳብህ እጅና አፍህን ጥፍር አርጎ እንዲይዝህ አስምለው። የልብ ወዳጅህን ትብብር ጠይቅ! 9. ብታገኝ ፊሽካ ብታጣ ጡሩምባ እና ነጋሪት ይዘህ ተንቀሳቀስ! አየኋት ሊያቅበጠብጠኝ ነው ስትል ፊሽካውን ቅልጥ አርገህ እርዳታ ጥራ። እነሱንም አላገኝም ካልክ ደግሞ ገና ሲጀማምርህ እሪታህን ልቀቀው። ሰው ደርሶ ከነውረኛነት ያድንሃል። 10. እንዳትረሳ! “እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር” እንዲሉ ፈቅዳልህ እንኳን ሽርሽር አብራህ ለመሄድ፣ አብራህ ሻይ ቡና ለማለት ብትስማማ እንኳን፥ በንጹህ ወዳጅነት ስለማንነቷ እንደወደድካት አታስመስል። ልብህ ውስጥ ድብቅ አላማ ካለ፥ በጊዜ፣ “ወጡ ሳይወጠወጥ” እውነቱን ንገራት። እውነቱን ካልነገርካት፣ ልትደፈር መሆኑን አትጠረጥርምና ከረፈደ በኋላ ራሷን መከላከል አትችልም። *adapted from Sara Silverman’s the ten rape prevention tips*

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

26

#ColorizingHistory

አንበሳን በጡጫ እለው የነበረ...

Source: https://www.facebook.com/colorizinghistory ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

ስለዜንና እኛ

27

EL NATTY DAGNAW ዜን ይመስላል።...የአኗኗር ዝንባሌየ ወደዛ ያደላ ነዉ። ፀጥታና ንቃት....የአእምሮ ልቡና ና መንፈስ ዉህደት ያለበት።...በሰዉ ልጅ ያለመሞት ትግል ዉስጥ ትርጉማቼዉ የተዛነቀዉን ሁሉ በታቸለ መጠን ልክነታቸዉን ወደ ሚመጥን የእዉነት ፍቻቼዉ የማስጠጋት አካሄድ.....Redefine ማድረግ አለበት። ፈታኙ ነገር ይሄ ዓይነቱ መሻት በራሱ የንስሃ ጉዞ መሆኑ ነዉ።....የሰዉ ልጅ ከንፁህና ወሰን አልባዉ ጨቅላነቱ ወጥቶ በቋንቋና ባህል define ተደርጎ meaning ከያዘ በኋላ(psychosociality of being) ከተፈጥሮዉ የማፈንገጥ ትግል ዉስጥ ይገባል። ((ቀለም....ዘር...ምናምን መርጦ መቧደን is instinctual thing. እኔ ደግሞ ሰዉ ነኝ።...So never say me ከኔ ወገን ነህ።)) ሰዉ በአካል አደኩ ሲል ከንፁህ ተፈጥሮ ይጎድላል ስለዚህም Instinctual ወደ ሆነዉ የመቧደን ዝንባሌ ማድላት ይጀምራል። ዜን ይሄን የጎደለ ንፅህና የመመለስ ሂደት...ወደ ሰዉ’ነት ተፈጥሮ የመመለስ ጉዞ ነዉ። ህይወት መንገድ ናት.... በመንገዱ ምን እንደሚገጥመዉ የሚያዉቅ ደግሞ የለም።... መኖር እነዚህን ነገሮች ተለማምዶ አሻጋሪ ማድረግን ይጨምራል። ...ሚዛን እየሳቱ ወደ አንዱ (ምቹ ወደሆነዉ) ብቻ መጠጋት ሙሉ ንቁ አያደርግም።... መኖር ሚዛንን ጠብቆ የመጓዝ ሂደት:ሰዉ ሆኖ የመቆየት ትግል ማለት ነዉ። ሰነፍና ዝንጉ ለመሆን እንዳልተፈጠርኩ አዉቃለሁ።...አኗኗር ግን ከዝንጋኤ የተጣመደ... መኖር ደግሞ ከስንፍና የተዋረሰ ነዉ።...ዝንጋኤ ወደ ፊት ቀጥሎ የመኖር ምክንያታችን ይመስለኛል። ዝንጋኤ ሲረታ ትዝታ ይፈጠራል።....ሁሉም ነገሮች ሲያልፉ የሚዘነጉ ሆነዉ እያለ አንዳንዱ ክስተት ጉልበታም ሆኖ ራሱን ከዝንጋኤ ይሰዉራል...ትዝታ ይለዋል ቋንቋ ደግሞ። ዝንጉ ለመሆን አልተፈጠርኩም ብልም ለመኖር ስል ሰንፌ ከዝንጋኤ ተጋብቻለሁ።...ይህን ስፅፍ እንኳ ካሰብኩት ላይ ስንት ሃሳብ ዘነጋሁ? ወደ ዜን መሳዩ አኗኗር ስመጣ አካልን ረፍት አጠር አድርገዉ እየሰሩ የሚሰሩትን ጠንቅቆ ማወቅ: አብረዉ የሚሰሩትን በስሜት ብልህነት መያዝ እና አየሩን ሁሉ ከሞላዉ የማቴሪያሊዝም ስብከት ተላቀዉ መንፈሳዊ ለመሆን መጣር ረጅም: መንገዱም አድካሚ ነዉ። የዜን ዋና ግቡ ግን ሰላም ነዉና....የአእምሮ....የስሜት ና የመንፈስ ሰላም ማግኜት ነዉና ሁሉን ያስችላል።....በሰላም ዉስጥ ሁሉም አለና ዜን ሰላምን ይሰጣል...።

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

28

MESAY A. DEGUALEM “ምክር እና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው” በሚለው ሽሙጥ አልስማማም! ምንም ነገር ለማያውቅበት ሰው ከባድ ነው። ቡጢውም ቢሆን በተሳሳተ አጨባበጥ ከሆነ ለመሰበር ነው። መሳሙ እራሱ የማያውቅበትን “ፍቅራም” አስትቶ “ንፍጣም” ነው ሚያስብል... የምክሩም እንደዛው ነው... አንድ ትልቅ ሰውዬ በጠዋቱ ልቤን ጠብቶት ነው ... የሀገሬ ሰው በተሞገሰ ቁጥር የመምከር መብት እራሱን ያጎናፅፋል... በርሱ አቅጣጫ የሮጠው እርቀት በተከበረለት መጠን በሌላው አቅጣጫ የሚተጉት አክባሪዎቹ እሩጫ ላይ ትንተናና ማብራሪያ የመስጠት ሀላፊነት ከራሱ ይቀበላል... “ውይ በሱስ ጉዳይ ከእውቀት ነፃ ነኝ!” ብሎ ማመን ሞቱ ነው... ለነገሩ ምን ያድርግ... ትምህርት ቤት እየቀሩ በቀበሌ ኪነት ድምፃቸውን ሲሞርዱ የጎለመሱ ዘፋኞች በአደባባይ የማህበራዊ ህይወት ፍልስፍናቸውን እና የፖለቲካ አቋማቸውን ሲደሰኩሩ በሚውሉበት ሀገር ትንሽ መማር ብዙ አዋቂ እንደመሆን እንደሆነ የሚያምን ያናድዳል እንጂ አይፈረድበትም። የጠዋቱ ሰውዬም ያው ነው... እመክር ብሎ ተጋጋጠ ተጋለጠ እንጂ... “ትርጉም መስጠት እንወዳለን እንጂ ብዙ ትርጉም የሌለው ነገር ያጣላናል።” ሲል ሞገተኝ... እኔን “ከፍትፍቱ ፊቱ!” እየተባልኩ ያደኩትን ተርጓሚ! “ምናባክ ፣ የታባክ... እንደው ያደባድቡናል እንጂ ትርጉም የላቸውም። ስድብም አይደሉም!” ብሎ አብራራልኝ ይሄ ምሁር ‘ዲያስፖራ’... ደሞ በነሱ ይብሳል...🤔 በተለይ በአሜሪኬዎቹ...😏 በቃ ዲግሪያቸው ላይ ቁጭ ብለው ታክሲ በነዱበት እውቀት ሀገር ለመቀየር ያላቸው ትጋት ግርም ይላል... አስር አመት ነዳጅ ሲቀዱ ቢኖሩም በቃ ዴፖው የተተከለበት ምድር የተባረከ ነውና ከመፍትሄነት የሚያግዳቸው አንዳች ንኳ ከዚህ ድሀ ምድር አይገኝም... “ምን አባክ” እንዴት አባቱ ነው ስድብ የማይሆነው? “አንተ ቀርቶ ያመነክ ሰውዬም ምንም አያመጣም!” አይደለም? አባትየው የሌለው “እኔው እበቃለው!” ብሎ የሚመልሰው ከባድ ጥያቄስ አይደለም? ምን አለበት የቄሳር ለቄሳር ቢተው? ምናለበት ታክሲ በአንክሮት ቀርቶ በአትኩሮት ብቻ ቢነዳ? ኧረ በመድሀኒዓለም ጎድሎ ያጎደለንን ክብር ለመሙላት ሰው መራገጥ እናቁም! ሁላችንም ያለንን ይዘን ጎን ለጎን ብንቆም ነበር ሙሉ የምንሆን... ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

29

ህላዊ ተስፋዬ ድሮ ልጅ ሆነን ሾላ ገበያ አካባቢ ከግጥሞቹ ጋር የማይገናኝ የህንድ አክተርና ሞዴሎች የተለጠፉበትን ጥቅሶች ጮክ ብሎ እያነበበ 25 እና 50 ሳንቲ የሚሸጥ ሰውዬ ነበር። . . ሚገርመው ሰውየው አሁንም ድረስ አለ። አሁን ነጭ ሉክ ላይ በሰማያዊ ማርከር የተፃፉ ግጥሞችን በ3 ብር ይሸጣል። . . እሮብና ቅዳሜ ሰውየው በሰዎች ተከብቦ ግጥሞቹን እንዲህ እያለ ጮክ ብሎ ሲያነብ ግጥሙ ከኛ ህይወት ጋር ይሄዳል የሚሉ ሰዎች ‘አምጣው’ ብለው ተቀብለው ይገዙታል። . . . “የሰው ልጅ አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል: ቁንጫ እንኳን ባቅሙ ሱሪ ያስወልቃል።” ሲል (ቀጭን አጭር አቅመቢስ ሰውዬ ከሰው መሀል ዘሎ ‘አምጣው’ ይላል) . . “ምን ይመጣል ብሎ አይፈራም ገላዬ ፐረሰኛው ጊዮርጊስ አለ ከሁዋላዬ” (አንገቱ ላይ ግብዳ መስቀል ያሰረ ልጅ ‘አምጣው’) . . “ትክትክ ብሎ መሳቅ ጥርስ ያነቃንቃል፣ ድሀ አንዴ ካገኘ ማስቀመጥ የት ያውቃል።” (‘አምጣው’) . . “ስትሄድ እሄዳለሁ ቆሜ አልጠብቅህም፣ በባል ባል ይተካል አባቴ አይደለህም።” (ነጠላ ለብሳ ንፍር ያለች ሴትዮ ‘አምጣው’) . . . ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

30 አሁን ላይ ሰዉ ቤቱን በጋዜጣና ጥቅስ መለጠፍ ሲተው ጊዜ ጥቅስና ግጥሞቹ ወደ ታክሲ ላይ ተዘዋውረዋል። . . ያው እኛ ሀገር አብዛኛው ሰው ላይ እንደምናየው በስሌት ስህተት ወይም የዕድል ነገር ይሆንና ሲዳክር ቆይቶ ሳይሳካለት ሲቀር የሚሰጠው ምክንያት “ሰዎች ምናምን አዙረውብኝ ነው።” የሚል ነገር ነው። ለእነዚህ አይነት ሰዎች ትላንት ታክሲ ላይ እንዲህ የምትል ጥቅስ አየሁ.. “ስትዞር ዋልና አዞሩብኝ በል”

ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012

31

Order Now:

0925 74 99 56 ቅፅ-7

ታህሳስ| 2012