Data Loading...

Issue 7 Flipbook PDF

newfile


115 Views
56 Downloads
FLIP PDF 6.6MB

DOWNLOAD FLIP

REPORT DMCA

ገበያ

ሲራራ

ማይድሪም ሪልእስቴት MY DREAM

REAL ESTATE

G+16 0922 02 2220

ሲራራ 1ኛ ዓመት ቁጥር 007 መጋቢት 12 2012

ዋጋ ው ብር 13.00

በምሥረታ ላይ

‘ለስኬትዎ አዲስ መንገድ’ The new way for your success!

አክሲዮኑ በሁሉም ባንኮች እየተሸጠ ይገኛል

በመድሃኒት ቤቶች

ላይ ምርመራ “በውጭ ዜጎች ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚደርሰው መገለልና ጥቃት የኢትዮጵያን ዕሴት አይመጥንም” ዶ/ር ሊያ ታደሰ

በውጭ ዜጎች ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥቃት እየደረሰ ነው ተባለ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያልተገባ መገለልና ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ እንደገለጹት፣ ኮሮና ቫይረስ ዓለም ዐቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን እና አገር፣ ዘርና የቆዳ ቀለም የማይለይ መሆኑን ገልጸው አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ዜጎችን በበጎ ያለማየት አዝማሚያ እያሳዩ መምጣታቸው ትክክል እንዳልሆነ፣ ይልቁንም እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ዕሴት ፍፁም ተጻራሪ በመሆኑም በፍጥነት ሊታረም እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በአንዳንድ የውጭ አገሮች ዜጎች ላይ ከማግለልም አልፎ የጥቃት እርምጃ መድረሱን

ሪፖርት እንደደረሳቸው ገልጸው፣ እንዲህ ዓይነቱ የአገሪቱን ገጽታ የሚያበላሽና ከሕዝባችን የዘመናት አኩሪ ዕሴት ጋር የሚጋጭ አካሄድ ባስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ቤተልሔም ተካልኝ የተባሉ በአንድ የቻይና ኩባንያ ውስጥ በፋይናንስ ባለሙያነት የሚሠሩ ኢትዮጵያዊ እርሳቸውም ሆኑ እንደ እርሳቸው ከውጭ ዜጎች ጋር የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ሰዎች ድርጊት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸማቀቁ እንደሚገኙ፣ እንዲህ ዓይነቱን የአገሪቱን ገጽታ የሚያበላሽ ድርጊት መንግሥትም ችላ ሊለው እንደማይገባ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡ የሲራራ ጋዜጣ ባልደረቦች ተዘዋውረው ያነጋገሯቸው የውጭ ዜጎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ‹በሽታ ባለቤት የለውም› ያሉት በአዲስ

የምንከተለውን የኢኮኖሚ ፍልስፍና ከስም በላይ እናውቀዋለን ወይ? የብልጽግና ፓርቲ ከልማታዊ መንግሥት ፍልስፍና አፈግፍጎ ወደ ሊብራል ኢኮኖሚ ፍልስፍና አጋድሏል ይባላል:: የተለያዩ ባለሥልጣናት እና ባለሙያዎች ስለ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሲናገሩም በውስጥም በውጭም እስካሁን ያልተሞከረ

አዲስ ዓይነት ለውጥ አስመስለው ያቀርባሉ:: ሆኖም ከሦስቱ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የፖሊሲ ምሶሶዎች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት ማስተካከል መሆኑን ተናግረዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚህ ጉዳይ ላይ አጽንኦት ሰጥተው በሚዲያ አረጋግጠዋል::

ገበያ

ገጽ 15

አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ማቲው፣ በውጭ ዜጎች ላይ የሚታየው የማግለል አዝማሚያ ኢትዮጵያን ባህል ስለማይመጥን መስተካከል ይገባዋል ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና ዶ/ር ኤባ አባተ የዓለም ዐቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም እንዳስገነዘቡት አፍሪካ ለከፋው ዘመን መዘጋጅት እንደሚገባት ተናግረዋል፡፡ በአገራችን ዜጎች የሚስተዋለው ከፍተኛ የሆነ የመዘናጋት ሁኔታም በፍጥነት መታረም እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ኤባ አክለውም በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት በአገርና በሕዝብ ላይ የከፋ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል ስለሆነ ሁሉም ዜጋ ራሱን ከበሽታው ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ ገጽ 3

አንዳንድ ነጥቦች “ስለዘር ፖለቲካ”ገጽ 8

ተጀምሯል ተባለ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ መድሃኒት ቤቶች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አቶ አልቃድር ኢብራሂም ለሲራራ ጋዜጣ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ጓንት፣ የአፍ መሸፈኛ፣ አልኮል፣ ሳኒታይዘር እና መሰል ምርቶች ላይ የተጋነነ ጭማሪ መኖሩን መታየቱ ገልጸዋል፡፡

ገጽ 5

መንግሥት ከአረቄ ምርት ወደ አልኮል ምርት ፊቱን ማዞር አለበት በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት በአገሪቱ የተፈጠረውን የአልኮል ምርት እጥረት ለመፍታት መንግሥት የአረቄ አምራች ድርጅቶች ወደ አልኮል ምርት እንዲያደርጉ ማድረግ አለበት ተባለ፡፡ ከሲራራ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶሎዳ መድሃኒት መደብር ባለቤት አቶ ፀጋዬ ገብረየሱስ አሁን ላይ በመድሃኒት ቤቶች የአልኮል፣ ሳኒታይዘር፣ የአፍ መሸፈኛ አና ጎንት ምርት እጥረት መኖሩን ይገልጻሉ፡፡ የእጥረቱ ምክንያት ቀድሞ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት በብዛት ምርት ካለመግባቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ መሆኑን ያነሳሉ፡፡

ገጽ 5

“መንግሥት የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ

በአግባቡ አልመራውም” አቶ ጌታቸው አስፋው

ከሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር የት ላይገጽነን? 14 ገጽ 22

2 ርእሰ አንቀጽ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ዲሞክራሲ ዲሞክራቶችን ይፈልጋል ‹ደኅንነት ወይስ ነጻነት?› ‹ዴሞክራሲ ወይስ የአገር ህልውና?› የሚሉት ጥያቄዎች የፖለቲካ ፍልስፍና ነባር ጥያቄዎች ናቸው:: በእኛም አገር ብዙ ክርክር ተደርጎባቸዋል፤ እየተደረገባቸውም ነው:: ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን እና የአገር ህልውና መጠበቅ በእኩል ደረጃ እንደሚያስፈልጉን፤ ስለሆነም ከኹለቱ መሠረታዊ አጀንዳዎች አንዱን መምረጥ እንደሌለብን ሊሰመርበት ይገባል:: ለሰላም ሲባል፣ ለአገር ህልውና ሲባል ዴሞክራሲው ይዘግይ የሚሉት ፈሊጥ አውዳሚ ነው:: የአገራችን ህልውና መጠበቅ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: አገር ሳይኖር ሰላምም ዴሞክራሲም ልማትም አይታሰብምና:: አገር ሰላም ሳይሆን ከቦታ ቦታ በነጻነት ተንቀሳቅሶ መኖርና መሥራት አይቻልንምና:: ሰላም ወሳኝ ነገር ነው:: የሕግ የበላይነት መከበር የሁሉም ነገር መጀመሪያ ነው:: ዴሞክራም ለአገር ህልውና መጠበቅ ያለው አስተዋጽዖ የሚያከራክር አይደለም:: የዴሞክራሲ እጦት፣ የዜጎች ሰብአዊ ክብርና መብት አለመጠበቅ በአገር ህልውና ላይ የሚያመጣውን አደጋ ደግሞ ከእኛ በላይ የሚያውቀው የለም:: አንድ የአፈና አገዛዝ በሕዝብ ትግል ተንበርክኮ የፖለቲካ ሽግግር በሚደረግበት ጊዜ፣ በሽግግር ወቅት ግጭቶች እንደሚበረክቱ፣ የሰው ሕይወትም እንደሚጠፋ የታወቀ ጉዳይ ነው:: የቀደመው አገዛዝ ቅሪቶች ለውጡን ለማደናቀፍ፣ ‹የለውጥ ኀይሎች› ለውጡን ከቅልበሳ ለመጠበቅና የራሳቸውን አገዛዝ ለመትከል፣ ልዩ ልዩ የፖለቲካ ተዋናዮች ደግሞ ለውጡን በራሳቸው መንገድ ለመጋለብና የራሳቸውን ዓላማ ለማስፈፀም፣ ሁሉም በየፊናቸው ይታገላሉ:: በዚህ ሒደት አገርና ሕዝብ ከፍ ያለ ያለመረጋጋት ሰለባ ይሆናሉ:: ዜጎች የገደላቸው ሳይታወቅ እንደወጡ ይቀራሉ:: ሁሉም ነጻነቱን ተጠቅሞ እንደፈለገ ስለሚቀሰቅስ በኅብረተሰብ መሀከል ጥርጣሬና ጥላቻ ይፈጠራል፤ ግጭቶችም ይከሰታሉ:: ብዙ ጊዜ የዘር ፍጀት የሚከሰተውም እንዲህ ባለ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ነው:: ግጭት ሲበረክትና አለመረጋጋት ሲሰፍን፣ ብሩህ ነገር እናገኛለን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንመሠርታለን ብሎ የለውጡ አካልና ደጋፊ የነበረው ዜጋ፣ አገዛዙ አገር ወደ ቀውስ ከማምራቷ በፊት ሕግና ሥርዓትን እንዲያሰፍን ወደ መጠየቅ ያተኩራል:: በዚህ ምክንያት መጀመሪያ ሕግና ሥርዓት ይስፈን፣ የአገር ህልውና ይጠበቅ የሚለው ነጥብ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ ይወጣል:: በብዙ አገሮች፣ በተለይም መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ በተካሄባቸው አገሮች ውስጥ ይህ የኅብረተሰብ ጥያቄ ነው አንድ የአፈና አገዛዝ በሌላ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ እንዲተካ ምክንያት የሚሆነው:: ቅድሚያ ለኅብረተሰብ ሰላምና መረጋጋት፣ ቅድሚያ ለአገር ህልውና ይባልና ዴሞክራሲ ኹለተኛ ቦታ እንድትይዝ ይደረጋል:: አገዛዝ ደግሞ ሕግና ሥርዓት በማስከበር ስም አንድ ጊዜ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብት መደፍጠጥ ከጀመረ አይመለስም:: ትልቁ አደጋ ይህ ነው:: በኢትዮጵያችን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ያስፈልጋል፤ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱት ግጭቶች፣ የዜጎች ሞትና መፈናቀል ሊቆም ይገባል፤ የአገራችን ህልውናም ጥያቄ ውስጥ ሊገባ አይገባም::

ሆኖም ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ነጻነቶችና መብቶች ሰለባ ይሁኑ ማለት ትልቅ ውድቀት ነው:: ለኢትዮጵያ ህልውና ትልቁ መድኀኗ ዴሞክራሲ ነው:: የሚበዙት የአፍሪካ አገዛዞች ሕግና ሥርዓትን በማስፈን እና የአገር ህልውናን በማስጠበቅ ስም የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አፍነው ነው የሚኖሩት:: ሆኖም በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሰላምና መረጋጋትም አይሰፍንም፤ የአገር ህልውናም አይጠበቅም፤ ዴሞክራሲም አይታሰብም:: ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ አምባገነናዊ አገዛዝን ልትሸከም የምትችልበት ትከሻ የላትም:: ብዙ ቋንቋና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በጣም በርካታና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ያሉባት ኢትዮጵያ በአንድ የአፈና አገዛዝ ሥር ልትቀጥል አይቻላትም:: ይህ መንገድ ተሞክሮ የከሸፈ የጥፋት መንገድ ነው:: የአፈና አገዛዝን ኮትኩተን ስናበቃ ሁላችንም የጭቆና ሰለባ መሆን፣ ጭቆናውን ለማስወገድ ስንታገል መሞት፣ እንደገና አንዱን የአፈና አገዛዝ ጥለን ሌላ ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ማንገሥ የኖርንበትና እስኪበቃን ያየነው የጥፋት መንገድ ነው:: ከዚህ አዙሪት የሚያወጣን ዴሞክራሲ ብቻ ነው:: ለአገራችን ከዴሞክራሲ ውጪ ምርጫ የለም:: ስለሆነም ኢትዮጵያ አንድነቷን አስከብራ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚወስዳትን ሽግግር (democratization) በሙሉ ልብ መጀመር አለባት፤ አሁንኑ! ለዚህ ደግሞ የኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በጣም ወሳኝ ነው:: ሕዝባችን የራሱን ሰላም ራሱ የሚጠብቅና የዴሞክራሲ ተስፋውን በመረጋጋት ስም ለአገዛዝ የማያስረክብ መሆን ይገባዋል:: መንግሥት በአገራችን ሰላምና መረጋጋትን እንዲያሰፍን መጠየቅና መርዳት፣ እዚያው በዚያው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና መንግሥታቸው ዴሞክራሲን ለመገንባት የገቡትን ቃላቸውን እንዲያከብሩ መጠየቅና ከሥር ከሥር እየተከታተሉ መወትወት፤ ከኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ መግባት እናተርፋለን ብለው በየቦታው እሳት የሚለኩሱ የጥፋት ኀይሎችንም አምርሮ መታገል ይገባል:: ስለ አገራችን ሰላምና ደኅንነት እየሠራን እዚያው በዚያው ሌሎች ለዲሞክራሲ እንቅፋት የሆኑ ኀይሎች ከአፍራሽ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ መታገል ይኖርብናል:: የንቁ ዜጋ መሠረታዊ መርኹ ይህ ነው:: ዴሞክራሲን በሰላምና መረጋጋት ስም መስዋዕት ማድረግ ውድ ዋጋ ያስከፍለናል:: ሕግና ሥርዓት ባልተከበረበት ሁኔታም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊገነባ አይችልም:: ኹለቱም ጎን ለጎን አብረው መሄድ ይገባቸዋል፤ ይቻላልም:: ከሁሉም ነገር በላይ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር ግን፣ ዲሞክራሲ ዲሞክራቶችን የሚፈልግ መሆኑን ነው:: ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚያጎናጽፈውን መብት እንዲሁም የሚያሸክመውን ኀላፊነትና ግዴታ ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል:: የጨዋታው ሕግ በደንብ እንዲሰርጸን ያስፈልጋል:: ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲገነባ እኛው ራሳችን ዲሞክራቶች መሆን ይገባናል::

ሲራራ በሲራራ ሚዲያና ኮምኒኬሽን ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር

እየታተመ በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚወጣ ጋዜጣ ጥር 2012 ተጀመረ የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ፡አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 06፣ ቲ.ኤስ.ቢ.ጂ. ሕንጻ፣ የቢሮ ቁጥር 306 ስልክ ቁጥር፡- +251-922-58-0561 [email protected] www.theblacklionafrica.com

ማኔጂንግ ኤዲተር ሊያ አምደማርያም ዋና አዘጋጅ ይስሐቅ አበበ ክ/ከተማ: የካ ወረዳ: 12 የቤትቁ. 517 [email protected]

አዘጋጆች መስፍን አርአያ ያባትፈንታ ጌታቸው ሁሉናየን ይዘንጋው ሪፖርተሮች ርብቃ ዳንኤል ሳምሶን ዳኛቸው ዲዛይን ሀብ ዲዛይን [email protected]

አታሚ፡ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 17/የቤት ቁ.984

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ዜና 3

ቁጥር 007

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ ባንኩ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለጤና ሚኒስቴር የ10 ሚሊዮን ብር ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል::

ቀለም፣ ብሔር፣ ሃይማኖት ሳይል የሚያጠቃ በመሆኑ ሁሉም በትብብር መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል:: በተያያዘ ዜና የተለያዩ ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በልገሳ ፕሮግራሙ ላይ የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሳህረነ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተገኝተዋል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር በዓለም ብሎም በአገራችን እየተከሰተ ያለውን የኮሮና ቫይረስን መዋጋት የአንድ ተቋም የብቻ ሥራ ባለመሆኑ ባንኩ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚሠራውን ዘመቻ ለማገዝ የ10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ገልጸዋል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በቀጣይ ሁኔታዎችን እየገመገመ የገንዘብ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል:: አገር እንዲህ ችግር ውስጥ በምትገባበት ጊዜ ከመንግሥት ጋር መቆም የተቋማት ኀላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው ያሉት አቶ አቤ የወረርሽኙን ሥርጭት ለመቆጣጠር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል:: ባንኩ አሁን ላይ ከ24 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ከ62 ሺሕ በላይ ሠራተኞችንም በሥራ የያዘ አንጋፋ ተቋም እንደ ሆነ ጠቁመዋል:: በሥሩ ያሉ ሠራተኞቹንም ሆነ ደንበኞቹን ከቫይረሱ ስርጭት ለመታደግ የጥንቃቄ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑ ገልጸዋል:: ወረርሽኙን የመከልክል ሥራውን ሊደግፉ የሚችል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑም አቶ አቤ ተናግረዋል::

የባንኩ በጤናው ዘርፍ ላይ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት አቶ አቤ የባንኩን 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ጤና ጣቢያ እያስገነባ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አቤ፣ ከነዚህም ሦስቱ ተጠናቀው ወደ ሥራ መገባቱን እና ለሥራው 78 ሚሊዮን ብር በጅት መመደቡን ገልጸዋል:: በቀን ከ18 ሺሕ በላይ ደንበኞች የባንኩን ቅርንጫፎች እንደሚጎበኙ የገለጹት አቶ አቤ በቅርንጫፎች በኩል የሚታየውን መጨናነቅ እና መተፋፈግ ለማስቀረት ደንበኞች ወደ ባንክ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በኤሌትሮኒክስ የገንዘብ ልውውጥን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል:: የባንኩን የሞባይል ባንክ፣ ሲ.ቢ.ኢ.ብር፣ ኢንተርኔት ባንክ፣ ካርድ ባንክ መጠቀሙ ሰዎች ወደበዙባቸው አካባቢዎች የምንደርሱበትን መጠን እንደሚቀንሰው የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ

በኤ.ቲ.ኤም. ማሽኖች አካባቢ ያሉ ሥጋትን ለመቀነስ የንጽሕና መጠበቀያ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል:: በኔትዎርክ መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጠረውን ችግር ለማስቀረት ባንኩ የውስጥ ኔትዎርክ መሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን አንስተው ከዐሥር ቀናት በኋላ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንደሚገባም ጠቁመዋል:: ወደ ባንክ ለሚመጡ ደንበኞች በሁሉም ቅርንጫፎች በር ላይ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የተዘጋጁ መሆኑንም ተናግረዋል:: በጤና ሚኒስቴር በኩል የግንዘብ ርክክቡን የፈፀሙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ሳህረነ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: አሁን በዓለማችን የተከሰተው ወረርሽኝ ዘር፣

የከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እና የተለያዩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ ይገኛል ብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አማካኝነት በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የንጽሕና እቃዎችን ማሰባሰቢያ ማዕከል በመስቀል አደባባይ ተቋቁሟል። ኅብረተሰቡም አቅሙ በፈቀደ መጠን ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ማንኛውንም የንጽሕና መጠበቂያ ምርቶች መለገስ እንደሚችል ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ የንጽሕና እቃዎችን መግዛት ለማይችሉ ወገኖች ኅብረተሰቡ አቅሙ በፈቀደው ልክ ድጋፍ በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚሠራው ሥራ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር 5 ሺሕ ሊትር በረኪና፣ 1 ሺሕ 48 የልብስ ሳሙና እንዲሁም 6 ሺሕ 452 የገላ ሳሙና ድጋፍ አድርጓል። ስታር ሳሙና እና ዲተርጀንት ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በበኩሉ 720 ሳሙና በጠቅላላው 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ማበርከቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ስድስት ወራቱ 192 ሚሊዮን በላይ ገቢ አገኘ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በተያዘው የበጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ-አዳማ እና በድሬዳዋ-ደወሌ የክፍያ መንገዶች ከ192 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በተለይ ለሲራራ ጋዜጣ በላከው መረጃ ገልጿል:: በአዲስ-አዳማ እና በድሬዳዋ-ደወሌ የክፍያ መንገዶች በድምሩ 4,532,197 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ብር 181,728,254 መሰብሰቡን የጠቆመው ኢንትርፕራይዙ፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ማለትም ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ፣ ከተሽከርካሪ ማንሻና መጎተቻ 10,284,984 በማግኘት በአጠቃላይ ብር 192,013,240 መሰብሰቡን ገልጿል:: ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አገልግሎት አየሰጠ የሚገኘው የአዲስ አበባአዳማ የፍጥነት መንገድ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎችን

ተጠቅሞ ያሉትን ጠንካራ ጎኖችንም አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ የሚስተዋሉ ድክመቶችን በመቅረፍ፣ ያለውን የሰው ኀይል በዕውቀትና በክህሎት በማሳደግ፣ የአሠራር ስልቶችን በማሻሻል በስፋት ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ለግኝቱ ምክንያቶች መሆናቸውንም ገልጿል:: የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ 78 ኪ.ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ሥራ የገባ መንገድ ነው:: የመንገዱ ግንባታ 11.2 ቢሊዮን ብር የፈጀ ነበር ተብሏል:: ከዚህ ውስጥ 53 በመቶ ወጪው ከቻይናው የኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር የተሠራ ሲሆን ቀሪው በመንግሥት ወጪ ተሸፍኗል:: መንገዱ በፌዴራል መንግሥት በኩል በተገኘ ብድር በመሆኑ የብድር ክፍያ አፈጻጸሙም በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ነው ያሉት የኢንተርፕራይዙ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሮቤል አያሌው ናቸው:: እስካሁንም ያለበትን እዳ ለማቃለል ከወጪ ቀሪ በተገኘ ትርፍ 3.5 ቢሊዮን ብር እዳ መክፈል መቻሉን ገልጸዋል:: በሰኔ ወር 2011 ወደ ሥራ የገባው ድሬዳዋ-ደወሌ የፍጥነት መንገድ ለግንባታው

5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን 85 በመቶ ወጪው ከቻይና የኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር የተሠራ ሲሆን፣ ቀሪው 15 በመቶ ወጪ በመንግሥት የተሸፈነ ነው:: መንገዱ አዲስ ከመሆኑ አንጻር የብድር ክፍያ መፈጸም እንዳልጀመረ የተናገሩት አቶ ሮቤል፣ የመንገዱን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ በተለያዩ ቦታዎች ሰፊ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት፣ በማስተማር እና በመንገዱ ክልል ውስጥ የ24 ሰዓት የመንገድ ላይ ቅኝታዊ ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በትራፊክ አደጋ የሚደርስ ሞትን በ50 በመቶ መቀነስ ተችሏል:: በዚህም አምና በተመሳሳይ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ 12 ሞት ያጋጠመ ሲሆን ዘንድሮ 6 ሆኖ ተመዝግቧል:: በተጨማሪም የጥገና አቅምን በማሳደግ በኹለቱም አቅጣጫ ከ10 ኪ.ሜ በላይ የመንገድ መስመሮችን ቀለም በመቀባት እንዲሁም በአገልግሎት ዕድሜ ማብቃት እና በአደጋ ምክንያት በመንገድ ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን በመጠገን የመንገዱ ምቾት እና ደህንነት እንዳይጓደል ተሠርቷል ተብሏል::

በድሬደዋ-ደወሌ መንገድ ላይ ያለው የክብደት ቁጥጥር ውጤታማነት አስተማማኝ አለመሆኑ እና ከክብደት በላይ ጭነው የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በመንገዱ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑ የገለጸው ኢንተርፕራይዙ፣ ትኩረት የሚሻ ተግባር መሆኑን ጠቁሟል:: በተጨማሪም በመንገዶቹ ላይ የሥርቆት ሥራዎች መኖራቸውን የገለጸው ኢንተርፕራይዙ ከኅብረተሰቡ እና በቦታው ከተሰማሩ የጥበቃ ሥራዎች ጋር በቅንጅት በመሥራት ላይ እንደሚገኙም አቶ ሮቤል ገልጿል::

የ2012 በጀት ዓመት ስድስት ወራት የውጤት ተኮር ሥርዓት ዕቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ ውጤት 93.25 በመቶ ሲሆን የአፈጻጸም ደረጃውም ከፍተኛ ሆኖ መሆኑ ተገልጿል:: በቀጣይ ስድስት ወራት 2ኛው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ማገባደጃ እንደ መሆኑ የታዩ ደካማ ጎኖችን በጥልቀት በመመርመርና ማስተካከያ በማድረግ፣ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማዳበር ከዚህ በተሻለ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ የኢንተርፕራይዙን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ እንደሚሠራም ተጠቅሷል::

4

ማስታወቂያ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

አ ል ፎ ዝ ፕላ ዛ • አልፎዝ ፕላዛ የከተማችን ባለ ብዙ አገልግሎት ሕንጻ • ከሶስት በላይ ባንኮች • የህፃናት እና የአዋቂ አልባሳት መሸጫ በርካታ ሱቆች • ሱፐር ማርኬት • የቤትና የቢሮ ዕቃ መሸጫ ሱቆች

የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል።

• ሬስቶራንቶችና ካፌዎች • ሐኪም ቤትና ፋርማሲ • የተለያዩ ቢሮዎች እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን የያዘ ውብ ሕንፃ

አድራሻ:- ገርጂ፤ ከኢፔሪያል ትራፊክ መብራት ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ላይ

ቁጥር 007

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ዜና 5

ቁጥር 007

በመድሃኒት ቤቶች ላይ ምርመራ ተጀምሯል ተባለ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ መድሃኒት ቤቶች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ያረጋግጣል ያሉት አቶ አልቃድር የገበያውነ የበላይነት በመጠቀም ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ የንግድ ተቋማት ካሉ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል፡፡

የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አቶ አልቃድር ኢብራሂም ለሲራራ ጋዜጣ እንደገለጹት አሁን ላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ጓንት፣ የአፍ መሸፈኛ፣ አልኮል፣ ሳኒታይዘር እና መሰል ምርቶች ላይ የተጋነነ ጭማሪ መኖሩን መታየቱ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ የገበያ ሥርዓት ምርት በዚህ ዋጋ ይሸጣል አይሸጥም በሚል የተቀመጠ ግልፅ የዋጋ ተመን የሌለ በመሆኑ የቁጥጥር ሥራውን አዳጋች እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡ ይህም ያለ አግባብ ዋጋ ጨምረው የተገኙ የንግድ ማኅበረሰብ አካላትንም በሕግ ለመጠየቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አዳጋች እንደሚያደርገው አቶ አልቃድር ተናግረዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በገበያ ላይ ነጋዴዎች ያልተገባ ትርፍን ለማግኘት በማሰብ ገበያው ላይ የምርት እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ እና የገበያ የበላይነትን ለመያዝ የሚፈፀሙ ድርጊቶች ካሉ ተከታትሎ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድም አቶ አልቃድር ተናግረዋል፡፡ አሁን በከተማዋ መድሃኒት ቤቶች ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከያነት የሚውሉ እቃዎች በውድ እየሸጡ በመሆኑ ባለሥልጣኑ በመድሃኒት ቤቶቹ ላይ ምርመራ መድረግ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ምርመራው ከመድሃኒት ቤቶች በተጨማሪ መድሃኒት አስመጪዎችን፣ አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን እንደሚያካትት ተናግረዋል፡ ፡ ባለሥልጣኑ በሚያከናውነው ምርመራ ገበያው በበላይነት መያዙን እና አለመያዙን

በተጨማሪም ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በደረጊ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ እያደረገ መሆኑንም አቶ አልቃድር ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአዲስ አበባ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 767 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ በከተማዋ መታዩቱን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር ግብረ ኀይል በማቋቋም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።

ባለፉት ቀናት በተዋቀረው ግብረ ኀይል ውጤታማ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ድረስ ከ14 ሺሕ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። በቁጥጥሩም 11 የምርት ዓይነቶች እና 12 ፋርማሲዎችን ጨምሮ በ767 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኀላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል። ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ ለማድረግ፣ በጋራ ዋጋ የመወሰን፣ ምርት የማከማቸት እና የመደበቅ እንዲሁም በተለያዩ ምርቶች የዋጋ ንረትና ሰው ሠራሽ እጥረት በሚያስከትሉ ሥራዎች በተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ኀላፊው ገልጸዋል። እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል ወፍጮ ቤቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ተቋማት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ተቋማት፣ ፋርማሲዎች እና ችግር በፈጠሩ ነጋዴዎች ላይ እንደጥፋታቸው ዓይነት ከአስተዳደራዊ ጀምሮ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም ነው የቢሮ ኀላፊው የተናበበርበሬ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የሚፈጠረውን ኢኮኖሚያው ገዳት ለማቃለል መንግሥት እየሠራ ነው የኮሮና ወረርሽኝ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን ያሉት የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ያለው ጥረት ባደነቁበት መልዕክታቸው ነው፡፡ ዐቢይ አህመድ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡ “ጀግኖቹ የጤና ባለሙያዎቻችን ሕዝብን ከስቃይ ለመታደግ አያሌ መሥዋዕትነት ከፍለዋል፤ በሁሉም የጦር

ግንባሮች ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ተሰልፈው ለድንበራችን መከበርና ለሉዓላዊነታችን መረጋገጥ ሕይወታቸውን ሰጥተዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ

የመከላከል ዘመቻ፣ የጤና ባለሙያዎቻችን ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን እስከ አሁን ላከናወኑት አኩሪ ገድል በኢፌዴሪ መንግሥትና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።

“እኛ ጤና እንድንሆን ሁሉም ጤና ይሁን'' በሚለው መርሕ መሠረት፣ ሀገርን እና ሕዝብን ወክለው በኢቦላ ወረርሽኝ ወቅት፣ ከ150 በላይ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎቻችን ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመጓዝ አፍሪካውያን ወንድሞቻችንን አገልግለው በድል መመለሳቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ መሆኑንም አንስታውሰዋል። ̎ተደምረን የማንሻገረው ፈተና፣ ተባብረን የማናልፈው መከራ አይኖርም̎ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአገር ዐቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን

“ፈተናውን በድል መወጣት እስከሚቻል ድረስ መንግሥት ሁሉንም ኀይሎች አስተባብሮ ከእናንተና ከቤተሰቦቻችሁ ጎን እስከ መጨረሻው የሚሰለፍ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ” ያሉ ሲሆን ወረርሽኙ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።

ጋስት ሶላር በሲኤምሲ ሚካኤል ያለውን ሞል ዘጋ ሞሉ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማስታወቂያ ከመጋቢት 9 ቀን እስከ መጋቢት 21 ቀን በኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሞሉን መዘጋቱን አስታውቋል፡፡ መንግሥት ሰው የሚበዛባቸው እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ተቋሙ ከመንግሥት ጎን ለመቆም እና የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን የጋስት ሞል ጂም ማናጀር አቶ ይማሙ ሞላ ለሲራራ ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት መከላከል ለመንግሥት ብቻ አልያም ለጤና ሚኒስቴር የሚተው ሥራ

አይደለም ያሉት ኀላፊው ሁሉም ተቋም እና ዜጋ ሊተባበር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የጋስት ሞሉ በቀን በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች የሚጠቀሙበት በመሆኑና የሰዎች መቀራረብ እና መነካካትን ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ከወረርሽኙ ጉዳት ደንበኞቹን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ መወሰኑን አቶ ይማሙ አንስተዋል፡፡ ሞሉ በውስጡ ጂም ናዚየም፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ካፍቴርያዎች፣ የልጆች መጫወቻ፣ እስፓ እንዲሁም የውበት መጠበቂያ ቤቶች እንደሚገኙበትም የተናገሩት አቶ ይማሙ፣ ጋስት ሞሉ ሙሉ በሙሉ ሲዘጋ በውስጡ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት እንደሚቋረጥም ገልጸዋል፡፡

ሞሉ ለተከታታይ ቀናት በመዘጋቱ በጥቂቱ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሊታጣ እንደሚችል ማናጀሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በሞሉ መዘጋት ቀድሞ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ከኹለት መቶ በላይ ሠረተኞች ደሞዝ ሳይቋረጥ እንደሚከፈልም ጨምረው አንስተዋል፡፡ ጋስት ከሞል በተጨማሪ ለግንባታው ዘርፉ ጥቅም ላይ የሚውሉ የኬሚካል ምርቶች፣የግድግዳ ቀለም፣ ኳርትዝ፣ ሲልከን እንዲሁም ኦክስጅን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን የፋብሪካዎቹ ሥራ ግን እንዳልተቋረጠ አቶ ይማሙ ነግራናል፡፡

"መንግሥት ከአረቄ ምርት ወደ አልኮል ምርት ፊቱን ማዞር አለበት” በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት በአገሪቱ የተፈጠረውን የአልኮል ምርት እጥረት ለመፍታት መንግሥት የአረቄ አምራች ድርጅቶች ወደ አልኮል ምርት እንዲያደርጉ ማድረግ አለበት ተባለ፡፡ ከሲራራ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶሎዳ መድሃኒት መደብር ባለቤት አቶ ፀጋዬ ገብረየሱስ አሁን ላይ በመድሃኒት ቤቶች የአልኮል፣ ሳኒታይዘር፣ የአፍ መሸፈኛ አና ጎንት ምርት እጥረት መኖሩን ይገልጻሉ፡፡ የእጥረቱ ምክንያት ቀድሞ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት በብዛት ምርት ካለመግባቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ቀድሞ በነበረው ጊዜ ምርቶቹ ያን ያህል ተፈላጊ ባለመሆናቸው መድሃኒት ቤቶች በብዛት እንደማይዞቸው ይናገራሉ፡፡ “በቀን አንድ ጎንት በማይሸጥበት ሁኔታ ነበር የነበረው አሁን በቀን 500 እና 400 ገዥ ሲመጣ እጥረት መፈጠሩ የማይቀር ነው፤” ይላሉ አቶ ፀጋዬ፡፡ ቀድሞ በምርቶቹ ላይ ዝግጅት ባለመደረጉ እና ይህ ይመጣል ተብሎ ባለመታሰቡ በነጋዴው እጅ ያለው ምርት በአንድ ቀን ውስጥ ማለቁን ጠቁመዋል፡ ፡ መድሃኒት ቤቶች ምርቱን አከማችተው ነው እጥረት የተፈጠረው በሚባለው ነገር ብዙም እንዳማይስማሙ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ዋናው መንስኤ የምርት እጥረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተጋነነ ዋጋ ጨምረው ሲሸጡ የነበሩ መዳኒቶች ቤቶች ሊኖሩ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡ አሁን የተፈጠረውን የምርት እጥረት መንግሥት በቆራጥነት ከሠራ ሊፈታው እንደሚችል አቶ ፀጋዬ ይገልጻሉ፡፡ “በአገሪቱ ያሉ የአረቄ ፋብሪካዎች የኹለት ቀን ምራታቸውን አልኮል ላይ ቢያደረጉ እጥረቱን በእርግጠይነት መፍታት ይቻላል” ይላሉ፡፡ በአረቄ ፋብሪካዎች ምርት ላይ መንግሥት ጣልቃ መግባት እንዳለበት የሚያነሱት አቶ ፀጋዩ አሁን ላይ ትኩረቱ ከአረቄ ምርት ይልቅ ወደ አልኮል መሆን እንዳለበት ያነሳሉ፡፡ የአፍ መሸፋኛ ምርት እጥረትም አገር ውስጥ ባሉ የጨርቃ ጨርቅ አምራቾች የሚፈታ መሆኑን አቶ ፀጋዬ ያነሳሉ፡፡ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያሉ የጨርቃ ጨርቅ ድርጅቶች ለአንድ ሳምንት መምረት ቢችሉ የምርት እጥረቱን መፍታት እንደሚችሉ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ቁርጠኛ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት መኖር እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ 20 ሚሊዮን ብር መደበ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ በሰጡት መግለጫ፣ ማኅበሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል 20 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቀዋል። በዚህም 5 ሺህ የፊት መሸፈኛ ማስኮች፣ 6ሺህ የሰርጅካል ጓንቶች፣1 ሺህ 500 የሕክምና ጫማዎች፣ 1 ሺህ የፕላስቲክ የፊት መከላከያ እና 5 ሺህ የመለያ ጓንቶችን ለመግዛት መታቀዱን ዶክተር መሸሻ ተናግረዋል። በተጨማሪም ከ500 በላይ አምቡላንሶች አስፈላጊው የሕክምና ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው ዝግጁ መሆናቸውን ተገልጿል። ማኅበሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከዓለም ዐቀፍ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን እንዲሁም ከእኅት ማኅበራት ጋር በመሆን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑም ተነግሯል። ከዚህ ባለፈም ማኅበሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በፌደራል እና በክልል ያሉትን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶችን በማስተባበር እየሠራ መሆኑንም አንስተዋል። የማህበሩ በጎ ፈቃደኞች ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በአውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአጎራባች አገራት ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ኬላዎች ለሚገቡ ሰዎች የሙቀት ልየታ ሥራዎችን እየሠሩ መሆናቸውን አውስተዋል። ማኅበሩ ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል፡፡

6 እንግዳ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

“መንግሥት የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ በአግባቡ አልመራውም” አቶ ጌታቸው አስፋው አቶ ጌታቸው አስፋው የብሔራዊ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ ናቸው:: ለበርካታ ዓመታት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በከፍተኛ ባለሙያነት እንዲሁም በአስመራ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት አገልግለዋል:: በአገራችን ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ በርካታ ጽሑፎችን በሪፖርተር ጋዜጣ እና ውይይት መጽሔት ላይ አውጥተዋል:: በአማርኛ ቋንቋ የታተሙ አራት መጻሕፍትም ለአንባቢያን አድርሰዋል:: ከባልደረባችን ይስሐቅ አበበ ጋር ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወቅታዊ ሁኔታዎች ቆይታ አድርገዋል:: ውይይቱን እነሆ፡-

ሲራራ፡- የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ዓመታት አገሪቱን በልማታዊ መንግሥት የዕድገት ፈለግ ሲመራ መቆየቱን ይገልጻል:: አንዳንድ ምሁራን የልማታዊ መንግሥት ፈለግ ለእኛ አይጠቅመንም ሲሉ፣ ሌሎች ምሁራንና ፖለቲከኞች ደግሞ የዕድገት ፈለጉ አስፈላጊ ቢሆንም አገሪቱ በልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ እየተመራች እንዳልሆነ ይናገራሉ:: የእርስዎ እይታ ምንድን ነው? አቶ ጌታቸው፡- እንግዲህ መጀመሪያ ማየት ያለብን ነገር በምርት አስተዳደር ውስጥ ኹለት መሠረታዊ ባለድርሻዎች አሉ:: እነሱም የግል ክፍለ ኢኮኖሚ እና መንግሥት ናቸው:: የመንግሥትን ሥራ ካየን ታሪካዊ ቅደም

ተከተል አለው:: በመጀመሪያ የፍትሕ ሥርዓትን የማስጠበቅ፣ ሕግን የማስከበር እና አስተዳደራዊ ሥራዎችን ብቻ ይሠራ ነበር:: ከዚያም አለፍ ብሎ የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፍ ጀመረ:: ትምህርት ቤት ማስፋፋት፣ ጤና ተቋም መገንባት፣ መሠረተ ልማት የማሟላት የመሳሰሉትን ሥራዎች መሥራት ጀመረ:: የኢኮኖሚ ተንታኞች መንግሥት የሚሰበስበው የግብር መጠን ሊሠራው ባሰበው ሥራ ልክ መሆን እንዳለበት ይገልጻሉ:: ይህም ማለት የፍትሕና አስተዳደራዊ ሥራ ብቻ የሚሠራ መንግሥት መሰብሰብ ያለበት ግብር ለዚህ ሥራው የሚበቃውን ያህል ብቻ መሆን አለበት:: ትምህርት ቤት የሚገነባ፣ ጤና ጣቢያ የሚሠራ መሠረተልማት የሚያስፋፋ መንግሥት የሚሰበስበው ግብርም በሚሠራው ሥራ ልክ

ማደግ አለበት:: እነዚህ ያነሳናቸው ቆየት ያሉ በሊብራል ኢኮኖሚ ፍልስፍና ውስጥ ያሉ አገሮችም የሚቀበሉት የመንግሥትን ታሪካዊ ኀላፊነቶች ተንተርሰው የነበሩ እሳቤዎች ናቸው:: ሥራው እየሰፋ ስለመጣ ዛሬ ዛሬ በምዕራባውያን አገሮች የልማት ሥራዎቹ በመንግሥትና በግሉ ትብብር በጋራ የሚሠሩ ሆነዋል:: ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ነጻ ገበያውን የሚያክም የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አስተዳደር የሚባለው ሳይንስ ተጀመረ:: ከዚያ ጊዜ በኋላ መንግሥት የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚና ገበያውን በፖሊሲ የመግራት ሥራ መሥራት ጀመረ:: በተለየ መልኩ ‹ሞነተሪ ፖሊሲ› እና ‹ፊስካል ፖሊሲ› እንዲሁም የገቢ መጠን እና የገቢ ክፍፍል ፖሊሲ በማዘጋጀት፣ በተለይም በገቢ ፖሊሲው ሸማቹ አምራቹን በሸመታ ምርጫው እንዲያዘው በማድረግ የገበያውን እንቅስቃሴ ይገራል:: መንግሥት የዓለም ባንክም፣ የዓለም ጥሬ ገንዘብ ድርጅትም የተወሰነ የቁጥር ቡራኬ እየሰጡት 11 በመቶ 10 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስመዝገብኩ ሲለን ከርሟል:: ይህ ዕድገት የመጣው በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ ነው ወይስ በመንግሥት የብሔራዊ ኢኮኖሚ?

መረጃዎችን ወስዶ መመርመር ያስፈልጋል:: እውነት ለመነጋገር ባለፉት ዓመታት መንግሥት የራሱን በኢኮኖሚው ተሳትፎ ከፍ ያደረገ ቢሆንም፣ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚና ገበያውን በዕቅድ በመምራት እና በመግራት ረገድ ፈፅሞ የሠራው ሥራ የለም:: ገበያን በፖሊሲ አለመግራትና አለመቆጣጠር ሊብራል (ልቅ ነጻ ገበያ) ሊያሰኝ ይችል ይሆናል:: ሆኖም ግን መንግሥት መሬትን እና ካፒታልን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ በሬሽን ያከፋፍልና በሞኖፖል ገበያ በሊዝ ይሸጥ ስለነበር ውድድራዊ የነጻ ገበያ ሥርዓት ነበር ለማለት የሚያስችል ሁኔታ የለም:: ነጻ ገበያ የሚሆነው የምርትንም የግብዓተ ምርቶችንም ዋጋ ገበያው መወሰን ቢችል ነበር:: ያ ነበር እንዳትል የውድድር ሜዳው ለሁሉም በእኩል መጠን ክፍት አልነበረም:: የልማታዊ መንግሥት አስተዳደር ፍልስፍና ከምሥራቅ እና የደቡብ ምሥራቅ ኤስያ አገሮች የተጀመረ ነው:: መንግሥት ኢኮኖሚው በፍጥነት እንዲያድግ የሚያደርጉ ዘርፎች ላይ የግል ባለሀብቱ እንዲሳተፍ በማድረግ ወይም ራሱ መንግሥት በመሳተፍ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራበት ስልት ነው:: በርካታ የኤስያ አገሮች የዕቅድ መሥሪያ ቤታቸውን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ስምሪት እና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ሚቀጥለው ገፅ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

አስተባብረው ብሔራዊ አጀንዳ ቀርጸው በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚውን ሊያሳድጉ በሚችሉ ዘርፎች ላይ ዕቅድ ይነድፋሉ፤ ፖሊሲዎችን ያዘጋጃሉ፤ በዚያ ይመራሉ:: ከነጻ ገበያ ኢኮኖሚ በፊት እንደነበረው የመርካንታሊስት ኢኮኖሚ ሥርዓት መንግሥትና የግሉ ኢኮኖሚ ባለሀብቶች እጅና ጓንት ሆነው ከውጭ ኢምፖርት ከሚያደርጉት በላይ ወደ ውጭ ኤክስፖርት አድርገው አገራቸው በፍጥነት እንድታድግ በብሔራዊ ስሜት የሚነሳሱበት የኢኮኖሚ አስተዳደር ነው:: ኢትዮጵያ በልማታዊ መንግሥት አስተዳደር እመራለሁ ካለች ጊዜ ጀምሮ የልማት ስትራቴጂዎችን እና ዕቅዶችን አዘጋጅታለች:: ግብርና መር፣ ኢንዱስትሪን ማፋጠን፣ “agriculture lead industrialization” የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች (Micro and Small Scale Industries) ልማት፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች (Medium & Large Scale Industries) ልማት ወዘተ… ያልተባለ ነገር የለም ተግባሩ ላይ ግን የለችበትም:: ለስኬቱ ማጣት በርካታ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል:: ሙስና የመጀመሪያው ነው፤ ሌላው የወጡት ዕቅዶች ተስፋ ላይ እንጂ በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመረኮዙ አልነበሩም፤ በኢኮኖሚው ላይ የፖለቲካው እጅ የበዛም ነበር:: ከሁሉም በላይ ደግሞ በብሔር የተከፋፈለች አገር ብሔራዊ አጀንዳ መቅረጽ አትችልም:: እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተደማምረው የአገሪቱን ዕቅድ መና አስቀርተውታል:: በእኛ አገር አብዛኛው ሥራ በግለሰብ ምኞት ላይ የተንጠለጠለ ነበር:: ‹ዓባይን የደፈረ ጀግና›፣ ‹ስኳሩን የደፈራ ጀግና› እየተባለ ነበር ባለፉት ዓመታት ሲፎከር የቆየው:: ለምሳሌ የስኳር ፕሮጀክቶችን እንመልከት 10 የስኳር ፕሮጀክቶችን በአንድ ጊዜ ለማስጀመር ዕቅድ መያዝ ማለት ምን የሚሉት ነው:: አንዲት ደሃ አገር 10 የስኳር ፋብሪካ በአንድ ጊዜ ትገነባለች ብሎ ማሰብ የፖለቲካ ጫና ለማሳደር ካልሆነ በቀር ምን ሊሆን ይችላል? አእምሮ ያለው የዕቅድ ባለሙያ ያን ያደርጋል ብዬ አላስብም:: የአገሪቱ ኢኮኖሚ የግለሰቦች የተጽዕኖ እጅ የበዛበት ነበር:: ባለሙያውም ኅብረተሰቡም ድምፅ አልነበራቸውም:: ስለዚህ የልማታዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ውጤታማ አልነበረም ብሎ መያዝ ይቻላል:: ነገር ግን እንዲሁ ኢኮኖሚው ሲገመገም በነበሩ ታሪካዊ የመንግሥት የመሠረተ ልማትን ጤናን፣ ትምህርትን፣ መንገድ የማስፋፈት ኀላፊነት ረገድ ብዙ ሥራዎች ተሠርተዋል:: የገንዘብ ምንጩ ብድርና እርዳታ ኅብረተሰቡም አንጀቱን አስሮ ከፍጆታ ይልቅ በመቆጠቡ ቢሆንም ይህ የሚካድ አይደለም:: የልማታዊ መንግሥት ዋና ዓላማው ሀብት ማፍሪያ የመንግሥት ይሁን የግል ይሁን ሳይሆን፣ ኢኮኖሚውን ሊያሳድግ የሚችለውን ዘርፍ መርጦ በዚያ ላይ ትኩረት አድርጎ ተባብሮ መሥራት መቻል ነው:: እኛ አገር ብዙ ጊዜ ልማታዊ መንግሥት የሚተረጎመው ከይዞታ ጋር ተገናኝቶ ነው:: ይህ ዘርፍ የመንግሥት ነበር የግል ነበር እየተባለ:: አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደርም ያተኮረው በይዞታው ላይ ነው:: መንግሥት ከልማታዊ ሥራ ወጥቶ የግል ዘርፉ የኢኮኖሚው አንቀሳቃሽ ሞተርነት ሚናውን እንዲጫወት ይደረጋል የሚል ነው ሐሳቡ:: ቁም ነገሩ በመንግሥት መያዙ ወይም በግል መሆኑ አይደለም:: ዋናው ነገር ሥራው በትክክል ተለይቶ ተሠርቷል ወይ ነው? የሚለው ነው:: እስካሁን ትኩረት የተሰጠው ግብርና በድጋፉ ልክ አላደገም፤ ያደገው የኢ-መደበኛው ክፍለ ኢኮኖሚ (informal sector) ነው:: ትናንሽ የሚባሉት በየጥጋጥጉ እንደ አሸን የፈሉት የቡና ንግድ፣ ምግብ ንግድ፣ በኮንትሮባንድ የሚገቡ የልባሽ ጨርቅና መጫሚያዎች ንግድ፣ በኮንትሮባንድ የሚገቡ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ንግድ፣ የጉልት ንግድ ነው:: የነዚህ ስብስብ ምናልባት የአገሪቱን ጥቅል ምርት ሊያሳድገው

እንግዳ 7

ቁጥር 007

ይችል ይሆናል:: ኢኮኖሚውን ግን ጤናማና ምርታማ እንዲሁም እያደገ ለመጣው የሰው ኀይል የሥራ ዕድል የሚፈጥር አያደርገውም:: ምክንያቱም በትንንሽ የአገልሎት ዘርፍ ዕድገት አዲስ ምርት አይገኝም:: ቡና ማፍላት ምግብ ማብሰል ቀድሞ ባለቤቱ እቤት ውስጥ ለራሱ ይሠራ በነበረበት ጊዜ እንደ ምርት ተቆጥሮ በብሔራዊ ኢኮኖሚ ልኬት ውስጥ አይካተትም ነበር፤ ዛሬ ግን ንግድ ነውና ተለክቶ በብሔራዊ ኢኮኖሚ ውስጥ ይካተታል:: ይህ ነው ኢኮኖሚውን በፍጥነት ያደገ ያስመሰለው:: አቶ ጌታቸው፡- በትክክል:: መንግሥት የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ በአግባቡ አለመግራቱ ጉዳቱ አሁን የሚታየው ነው:: በእኔ ዕድሜ ቀድሞ ምግብ ቤት ገብተን ዋጋ ሳንጠይቅ ነበር ምግብ አዘን እንበላ የነበረው:: ምክንያቱም ዋጋው የሚታወቅና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነበር:: ዛሬ ምግብ ቤት ተገብቶ ዋጋውን ከምግቡ ዓይነት ለማስቀደም የምግብ ዝርዝሩ እንደ ዐረብኛ ጽሑፍ ከቀኝ ወደ ግራ ነው የሚነበበው:: ዋጋ በጥንቃቄ ታይቶና ተመርምሮ ነው ምግብ የሚታዘዘው:: ነፍስ የፈለገውን ምግብ ዛሬ መብላት ከባድ ነው:: በቀናትና በቦታ ልዩነት ዋጋው አይገናኝም:: ይህ በድሮው ዘመን አይታወቅም:: አንድ ምርት ዋጋው ለዓመታት ተመሳሳይ ሆኖ ነበር የሚቆየው:: አሁን የተፈጠረው የገበያ ውጥንቅጥ መንግሥት በአግባቡ ሊመራው ባለመቻሉ ምክንያት የተፈጠረ ነው:: ያልተገራው ገበያ የዋጋ ግሽበትን አመጥቷል፤ ሥራ አጥነትን አባብሷል:: ይህ ሁሉ ነገር የመጣው መንግሥት ገበያውን በአግባቡ ባለመግራቱ ነው:: ገበያው ዛሬ ላይ ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጥር አልተቻለውም:: ቡና ማፍላት ከአንድ ሰው በላይ የሚያስፈልገው ሥራ አይደለም:: እሱ ነው ዛሬ እያደገ ያለው:: ከመንግሥት ሥራ አንስቶ እስከ ግል ሠራተኞች ድረስ በምንሠራው ልክ እኮ አይደለም እየተከፈለን ያለው:: የአንድ ሰዓት ሥራ ነው ስምንት ሰዓት ሙሉ ስናባክንበት የምንውለው:: ገበያው በነጻነት በፍላጎትና አቅርቦት መስተጋብር ዋጋን እንዲወስን አልተደረገም:: ምርት እና ምርታማነት ከጊዜ ጊዜ እየወረደ ነው:: ምርት በነጻ ገበያ መመራት የሚችለው ለምርት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ነጻ ማድረግ ሲቻል ነው:: የመሬት፣ የካፒታል፣ የሰው ኀይል ዋጋዎች ነጻ ካልሆኑ ምርት እና የምርት ዋጋ ነጻ ሊሆን አይችልም:: በእኛ አገር መሬት ነጻ አይደለም:: መንግሥት ለፈለገው ይሰጣል ላልፈለገው አይሰጥም:: በመሬት ላይ መንግሥት የሞኖፖል ገበያ ሥርዓት አካሄድ ነው እየተከተለ ያለው:: መሬት ነጻ ሆኖ ካልተሸጠ እና ካልተገዛ በመሬት ላይ የሚመረተው ምርትን በነጻ ገበያ መገበያየት አትችልም:: ካፒታልን እንውሰድ:: የባንክ ብድር እሳካሁን የመንግሥት ባንኮች ለማን ነበር ብድር የሚሰጡት? በማን ትዕዛዝ ነበር ብድር የሚሰጡት? ገበያውን ተመርኩዘው አልነበረም ብድር የሚሰጡት:: ስለዚህ ከምርት ግብዓት የቱ ነው ነጻ የሆነው? አንድ ነጻ ነው ሊባል የሚችለው የሠራተኛው ጉልበትና ዕውቀት ወይም የሰው ኀይል ብቻ ነው:: እርሱም ቢሆን በዘመድ አዝማድ ቅጥር የተተበተበ ስለሆነ አፍን ሞልቶ ነጻ ነው ለማለት ይከብዳል:: ስለዚህም ግብአቶች በሙሉ ነጻ አይደሉም:: ግብዓቶች ነጻ ባልሆኑበት ነጻ የምርት ገበያን መጠበቅ የዋህነት ነው:: ይህ ሁሉ ነገር ተደማምሮ ነው ዛሬ አገሪቱ ላለችበት ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጥ የተጋለጠችው:: ሲራራ፡- የኢትዮጵያ መንግሥት ‹ነጭ ካፒታሊዝም› የሚለውን ወይም የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲን እንደሚከተል ሲገልጽ ቆይቷል:: በእርስዎ አስተያየት መንግሥት ሲመራበት የቆየው የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዴት ይገለጻል? እውን የምንመራበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ የገበያ ኢኮኖሚ ነው ማለት እንችላለን?

አቶ ጌታቸው፡- አንችልም:: ኹለት ዓይነት ነጻ ገበያ ነው ያለው:: አንደኛው ሊብራል ነጻ ገበያ ነው:: ሌላኛው ማክሮ ኢኮኖሚ የሚቃኘው ነጻ ገበያ ነው:: ሊብራል ገበያ ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት የነበረው ሁኔታ ነው:: ፍፁም የነጻ ገበያ የነበረበት ነው:: የሊብራል ኢኮኖሚ ቅጣይ የሆነው ኒዮ-ሊብራሊዝም እንደገና ከ1970ዎቹ ጀምሮ ብቅ በማለት ዛሬ የምዕራብ አገሮች በኒዮሊብራሊዝም እና በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚገራ ኢኮኖሚ የሚከተሉ በመባል በጥግግት ይመደባሉ:: የጥግግቱ ደረጃ የተለያየ ነው ለምሳሌ የጀርመንና የጃፓን ነጻ ገበያ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ ነጻ ገበያ ይለያል:: የስካንዲኔቪያን አገሮች ደግሞ ከሌሎች ይለያል:: አሁን የኛ አገር የነጻ ገበያ ከኹለቱም ወገን ያልሆነ ነው:: የሊብራል ነጻ ገበያ ነው እንዳይባል የምርት ግብዓቶች ነጻ አይደሉም:: በማክሮ ኢኮኖሚ የሚቃኝ ነጻ ገበያ ነው እንዳይባል የማክሮ ኢኮኖሚው ገበያውን አልገራውም:: ስለዚህ በዚህ አገር ይህን ዓይነት ገበያ ነው ያለው ማለት ከባድ ነው:: ምስቅልቅሉ የወጣ የሶሻሊዝም እና የካፒታሊዝም ድብልቅ ነው ማለት ይቀላል:: ሲራራ፡- መንግሥት ባለፉት ዓመታት የዕድገት እና ትራንፎርሜሽን 1 እና 2 እያለ ዕቅድ ሲያዘጋጅና በዚያ መሠረት ለመሥራት ሲሞክር ቆይቷል:: ሆኖም በእነዚህ የመንግሥት ዕቅዶች እና በአፈጻጸማቸው ላይ እርስዎን ጨምሮ በርካታ ምሁራን ጥያቄ ሲያነሱ ይደመጣል:: የእርስዎ ምክንያት ምንድን ነው? አቶ ጌታቸው፡- ስለ ዕቅድ ስናነሳ ኹለት ዓይነት ዕቅድ አለ:: አንደኛው ብዙውን ጊዜ ሶሻሊስት አገሮች የሚከተሉት ዕቅድ ነው:: በመንግሥት ‹ይህን አምርት ያን አታምርት› እየተባለ በትዕዛዝ የሚሠራበት የዕቅድ ዓይነት ነው:: ሌላኛው ኢኮኖሚያዊ የልማት ዕቅድ ነው:: ሕንድን ለአብነት ማንሳት ይቻላል:: ኢትዮጵያም የአምስት ዓመት የዐሥር ዓመት እያለች አቅዳ እንቅስቃሴዎችን ስታደረግ ይስተዋላል:: በአገራችን ያለው የዕቅድ አወጣጥ መሠረታዊ ችግሮች አሉበት:: ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ:: ኢትዮጵያ ስትመራበት በቆየችው ዕቅድ በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ ሥራዎች ረገድ ስኬቶች ቢያስመዘግቡም፣ የገበያውን ሥርዓት መግራት ላይ ግን ክፍተቶች ነበሩበት:: በአንደኛውም ሆነ ኹለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (‹ጂ.ቲ.ፒ-1› እና ‹ጂ.ቲ.ፒ-2›) ምርትን ለማሳደግ የተሄደበት መንገድ ገበያው በውድድር ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ድጋፍ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አድርጎታል:: ለምሳሌ የአበባ ምርትን እንውሰድ::

ምን ያህል ጊዜ የውጭ ንግድ ገበያው ላይ ቆየ? ባለ ሀብቶቹ ድጋፋቸውን ሲበሉ፣ መሬታቸውን ሲወስዱ፣ ከባንክ ብድር በትዕዛዝ ሲቀበሉ ነው የቆዩት:: ዛሬ ምን ያህል አበባ ኤክስፖርት እናደርጋለን? መመለስ አለበት:: የጋምቤላ የእርሻ ልማትን ብንመለከት 4 ቢሊዮን ብር ከልማት ባንክ ተበድሮ ተከስሯል:: ባለፉት ዓመታት ምርት እና ምርታማነትን ያሳድጋሉ የተባሉ ዘርፎች በሙሉ ውጤት አላመጡም:: ምርት ማደግ የሚችለው ውድድርን ማምጣት ሲቻል ነው:: ለሁሉም እኩል ሜዳ መፍጠር ይገባል፤ ያሸነፈው ተወዳድሮ ያሸንፍ ቀጣይነትም ይኑረው:: የመንግሥትን ድጋፍ በልቶ የሚሄድ ካምፓኒ አይደለም መኖር ያለበት:: የምርት አቅርቦቱ በነዚህ ችግሮች ተተብትቦ ማደግ አልቻለም:: ሌላው ለዕቅዱ ውጤት ማጣት በተገቢው ቦታ ተገቢው ሰው አለመቀመጡም ትልቁ ድክመት ነበር:: ተቋማት በሚፈልጉት ባለሙያ አለመመራታቸው ትልቅ ኪሳራ አምጥቷል:: ዕቅድ በዘፈቀደ አይሠራም ኢኮኖሚስት ሁሉ ዕቅድ መሥራት አይችልም:: አኮኖሚክስ በውስጡ በርካታ ዘርፎች አሉት ግብርና ላይ ስፔሻላይዝ ያደረገ ይኖራል፤ በፋይናንስ አለ፤ በኢንዱስትሪ አለ፤ ዕቅድም ራሱን የቻለ ‹ስፔሻላይዜሽን› ነው:: በእኛ አገር ሁሉም ነገር በጅምላ ነው እንዲቀመጥ የተደረገው:: ባለሙያው በቦታው አልተቀመጠም:: እዚህ አገር ዕቅድም የሚያዘጋጀው በስመ ኢኮኖሚስት ነው:: በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ነው የአገሪቱ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶቹ ለውጤት ሳይበቁ የቀሩት:: ሲራራ፡- በአገራችን በአንድ በኩል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉ:: በሌላ በኩል የኢንዶውመንት ድርጅቶች የሚባሉት የፓርቲዎች ወይም ከፓርቲዎች ጋር ከፍተኛ ትስስር ያላቸው ድርጅቶች አሉ:: የግሉ ዘርፍም አለ:: ገበያ በእንዲህ ዓይነት ተዋናዮች መያዙ ያለው አንድምታና ያስከተላቸው አሉታዊም ይሁን አወንታዊ አስተዋጽዖዎች ምንድን ናቸው? አቶ ጌታቸው፡- ሌላውን የፖለቲካ ሥራ ትተነው የአገሪቱ የፌዴራሊዝም አወቃቀር በራሱ ለኢኮኖሚው እንቅፋት ሆኗል:: አወቃቀሩ በራሱ ማንነትን መሠረት ያደረገ መሆኑ ለኢኮኖሚው ችግር ነው:: የሕዝብ አስተዳደሩን እና የኢኮኖሚ አስተዳደሩን ለብቻ ወስደን ብናየው አሁን ያለው ማንነትን መሠረት ያደረገው አከላለል የሕዝብ አስተዳደርን ጥያቄ ሊመልስ ይችል ይሆናል እንጂ የኢኮኖሚ አስተዳደርን ጥያቄ ሊፈታ ወደ ገፅ 20 ዞሯል

8

ሲራራ

መጋቢት 12 2012 ገጽ 8-11

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

እንወያይ

አንዳንድ ነጥቦች “ስለዘር ፖለቲካ” አንድ ብቻ እንደሆነ እንረዳለን:: በዘረመል ረገድ የተደረጉ ጥናቶች የሚያመለክቱት የሰው ልጆች እስከ 99.90 በመቶ አንድ ናቸው የሚል ነው::

በቀለ ጉተማ (ፕሮፌሰር)

ኢትዮጵያ ላለፉት ሐምሳ ዓመታት ገደማ በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ ትገኛለች:: እንደምናውቀው አብዮቱ በ1966 ዓ.ም. ከተጀመረ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊትም የተወሰኑ ዓመታትን ወደኋላ ሄዶ የነበረውን የለውጥ ፍላጎት ማየት ይቻላል:: የ1953ቱ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት፤ እሱን ተከትለው የመጡ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴዎች፤ በባሌና በሌሎችም ቦታዎች የተቀሰቀሱ አመፆች፤ የመጫና ቱለማ ማኅበር እንቅስቃሴ በተለይም ደግሞ የዩኒቨርሲቲና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ወደ አብዮቱ ያመሩ ክስተቶች ሲሆኑ, በነዚህ ሁሉ ውስጥ የሚታዩት የለውጥ ፍላጎቶች የመሬት ጥያቄን፣ የሕዝቦች የመብት ጥያቄን፣ የእኩልነትንና ሌሎች መብቶችን የተመለከቱ ነበሩ:: የእነዚህን ዓመታት ትግሎች በምናይበት ጊዜ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያማከሉት ጎላ ብለው ይታያሉ:: እነርሱም የመሬት ጥያቄና የሕዝቦች መብቶችን የተመለከቱት የሚጎሉባቸው ሲሆን በእርግጥ ከዚያው ሥር ሊታቀፉ የሚችሉ የማደግና የመልማት፤ እንዲሁም የማኅበራዊ ፍትሕ ጥያቄዎችና የመሳሰሉት ናቸው:: የ1966 አብዮት በተወሰነ ደረጃ በተለይም የመሬት ጥያቄን ለመመለስ ሞክሯል:: በዚሁ መሠረት ጭሰኝነትን ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለማስወገድ ችሏል:: ደርግ አሮጌውን ሥርዓት አሰወግዶ፤ መሬትን ለአራሹ አድርጎ በሶሻሊስታዊ አብዮት ኢትዮጵያን እለውጣለሁ ብሎ በሚታትርበት ወቅት ከፍተኛ ተግዳሮት የገጠመው ከብሔራዊ ንቅናቄዎች መሆኑ የሚካድ አይመስለኝም:: በዋነኛነት የኤርትራ የአርነት ንቅናቄ፤ ሕወሓትና ኦነግ በዚህ ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው:: በእነርሱ የተነሱት ጥያቄዎች ያለፉትን በርካታ ዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ የወሰኑ መሆናቸው የማይካድ ከመሆኑም በሻገር እነኚህ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ ሁኔታ ለሚቀጥሉት በርካታ ዓመታትም ቁልፍ ጥያቄዎች ሆነው የሚቆዩ ይመስላል:: እነዚህ ጥያቄዎች በቀላሉ ልንተዋቸው ወይንም ልንገላገላቸው የማንችላቸው ናቸው:: በኢሕአዴግ አገላለጽ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመባል የሚታወቀው ጉዳይ ስለ ሕዝቦች የራሳቸውን መብት በራሳቸው የመወሰን መብት በተለይም እራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደርን የተመለከተ ነው:: ይህ ጉዳይ በቀላሉ ልንገላገለው እንደማንችል የተገነዘቡ በርካቶች ቢኖሩም ተገቢውን መፍትሔ መስጠት ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ ካለመፈለግ ግማሹ ጉዳዩን የሌለ ጉዳይና ወያኔ ወይም ኦነግ የፈጠረው የሌለ ነገር ሊያስመስለው ይሞክራል:: ሌላው ላይ ላዩን በመቀባት ጉዳዩ እንዲፈታ ይመኛል:: ችግር በምኞት የሚፈታ ቢሆንማ ዛሬ የት በደረስን ነበር! በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ እንደ ኢሕአዴግ የደከመበት ያለ አይመስለኝም:: የችግሩን መኖር ከመገንዘብ ጀምሮ የችገሩ መፍትሔም ሕዝቦች የእራሳቸውን መብት በራሳቸው እንዲወስኑ ማድረግን የተመለከቱት ናቸው:: ባለፉት የኢሕአዴግ ዘመናት ያየናቸው አከላለሎችና እነሱን ተከትለው

ይህ ከሆነ ታድያ የቆዳና ሌሎች ልዩነቶችን እንዴት ነው መረዳት ያለብን? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው:: የቆዳ ቀለምና ሌሎች የቅርጽ ሁኔታዎች የሚያሳዩት በሰው ልጆች መካከል ያለውን መሠረታዊ ልዩነት ሳይሆን (መሠረታዊ የሆነ ልዩነትም የለም) ከምንኖርበት አካባቢ ከባህላችንና ከመሳሰለው ጋር የተያየዘና በረጅም የሰው ልጆች አዝጋሚ ለውጥ የመጡ ልዩነቶች፤ እነሱም መሠረታዊ ሳይሆኑ በሁኔታዎች ውስጥ የተፈጠሩ መሠረታዊ ያልሆኑ (contingent) ገጽታዎች መሆናቸውን ነው::

የመጡት ለውጦች እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ቢሆኑም፣ ኢሕአዴግም እንደቀደምት የኢትዮጵያ ገዥዎች ከተለመደው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል መውጣት ባለመቻሉ እውነተኛው የአገዛዝ ወራሽ ሆኖ ቀጥሏል:: ጆን ማርካኪስ እንደሚሉት ከረጅም ጊዜ ልፋት በኋላ ኢሕአዴግ ሁለት ድንበሮችን ማለፍ/ማቋረጥ ባለመቻሉ ከአባቶቹ ብዙም አልተለየም:: ሁለቱ ድንበሮች ማርካኪስ የደጋና የቆላ ድንበሮች የሚሏቸው ሲሆኑ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ገዥዎች ወራሾች የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል እንዴት ሥልጣንን ከታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ውጭ ላሉ ወገኖች ለማካፈል ዝግጁነት እንደሌላቸው ለማሳየት የተጠቀሙበት አገላለጽ ነው:: በዚህ ረገድ ኢሕአዴግ ያመጣው የፌዴራል ሥርዓት ተጠቃሽና ተገቢው መፍትሔ ቢሆንም ሥርዓቱ የይስሙላ ሆኖ ከማዕከል የሚዘወር በመሆኑና በዚህም የተነሳ የሕዝቦች መብቶች እየተረገጡ በመሄዳቸው፤ ማኅበራዊ ፍትሕ በመጥፋቱ እና በመሳሰለው ሁኔታ ከ2008 ዓ.ም.፣ ጀምሮ ያየናቸው ከፍተኛ የሕዝብ ዓመጾች በተለይም በወጣቱ በመካሄዳቸው ከ2010 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ያየናቸው ለውጦች ሊከሰቱ ችለዋል:: ለውጡ ገና በጅምሩ ላይ ያለ ከመሆኑ የተነሳ በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙት ይገኛል:: ለውጡ ብዙ ድጋፍ ያለው ቢሆንም ሊያደናቅፉት የሚፈልጉ እንዳሉም አይካድም:: ዋናዎቹ ጥያቄዎች እራስን በራስ የማስተዳደር፤ የብዝኃነት፤ የመሬት ጥያቄና በነዚሁ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ማንነትን፤ የማኅረበራዊ ፍትሕንና ሌሎችንም ጉዳዮች የሚያካትቱ ናቸው:: በዚህ ረገድ አሁን የምንከተለውን ሥርዓት ከማይፈልጉ ሰዎች ሥርዓቱን “የዘር ፖለቲካ” እና የመሳሰሉትን ብለው ለማጥላላት ስለሚፈልጉና እየሰሩም ስለሚገኙ ስለነዚህ ነገሮች የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ጠቃሚ ስለመሰለኝ ይህንን አጭር ፅሑፍ ለመጻፍ አሰብኩ:: ያለው ፌዴራሊዝም በክልሎች ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ መጠንና ክልሎቹም የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ፣ ኦሮሚያ ወዘተ. የሚል ስም ስላላቸው ይህ “የዘር ፖለቲካ” ነው የሚሉ የተወሰኑ በከፍተኛ ደረጃ የተማሩትን ጨምሮ ይገኛሉ:: “የዘር ፖለቲካ” ማለት ምን ማለት ነው? “የዘር ፖለቲካ” የሚባል ነገር አለ ወይ”? “ዘር” ማለት ምን ማለት ነው? የሚሉትን

ጥያቄዎች በማንሳት እሞክራለሁ::

ሐሳቤን

ለማቅረብ

“ዘር” የሚለው ቃል ‘race’ በሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ይተረጎማል:: ይህ ከሆነ ዘር ወይም race ምን ማለት እንደሆነ በመመለስ መጀመር ተገቢ ይመስለኛል:: ዘር የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ጎልቶ ለፈላስፎች፤ ለአንትሮፖሎጂስቶችና ለሌሎችም የመወያያ ርዕስ የሆነው በዘመናዊት አውሮፓ ውስጥ ነበር:: የተወሰኑ ልሂቃን በዚህ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ጽፈዋል፤ ተጠበዋል:: በመሆኑም ዘርን ከቆዳ ቀለምና ከመሳሰሉት ወጭያዊ ምልክቶች በማንተራስ የተለያዩ የሰው ዘሮች እንዳሉ፤ እነዚህም ዘሮች መሠረታዊ የሆነ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ መረዳት ነው:: ዘሮች በተዋረድ (hierarchically) እንደሚገኙ ይናገራሉ:: ይህም ማለት ከፍተኛና ዝቅተኛ ዘሮች እንዳሉ፤ በዚህም የተነሳ ከፍተኛው ዘር ዝቅተኞቹን ዘሮች መግዛትና ማሰልጠን እንደሚገባቸው ጽፈዋል:: በእርግጥ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን መሠረት የሚሰጡት እንደዚህ ዓይነት የዘር ክፍፍሎች እንደሆኑ መገንዘብ ተገቢ ነው:: ከታወቁት የአውሮፓ ፈላስፎች አንዱ የሆነው ኢማኑኤል ካንት የሰው ዘርን በአራት ከፍሎ፤ የነጭ፣ የቢጫ (ኤዥያ)፣ የጥቁርና የቀይ ዘሮች እንዳሉ አሳይቶ ማንነታቸውም በዚያው ልክ በተዋረድ የተቀመጠ፣ ከፍተኛ የተባለው ዘር ዝቅተኛውን ማሠልጠን/መግዛት እንዳለበት አድርጎ ጽፏል:: ባጭሩ ዘር ማለት ይህንን ይመስላል:: ዘሮች በመሠረቱ የተለያዩ ናቸው ይላል:: የመለያየታቸውን ሁኔታ የሚያስረዳውም የቆዳ ቀለማቸውንና ተመሳሳይ ውጭያዊ ገጽታዎችን በመጠቀም ነው:: ዘርን ሥነ-ሕይወታዊ (bilological) መሠረት ያለው ክስተት አድርጎ ይገልጻል:: ይሁንና ይህንን ከመቀበላችን በፊት ዘር የሚለውን ሐሳብ ከሳይንስ አንጻር ምንድነው የሚለውን መመለስ መቻል አለብን:: በሳይንስ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን የሚችለው በሥነ-ሕይወት መስክ ‹ጄኔቲክስ› የሚባለው ዘርፍ ሲሆን፣ ፓሊዎ አንትሮፖሎጂና የመሳሰሉትን ብናይ ዘር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልንረዳ እንችላለን:: በነዚህ የሳይንስ መስኮች ላይ ተመሥርተን ዘር ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ብንሞክር፣ በቀለምም ይሁን በዘረመል (DNA) ወይም በሌላ በሰው ልጆች መካከል መሠረታዊ ልዩነት እንደሌለና የሰው ዘር በሙሉ

እንደ ናኦሚ ዛክና (Naomi Zak) ክዋሜ አንቶኒ አፒያህ (Kwame Anthony Appiah) ግንዛቤ የዘርን ምንነት የሚያሳዩ ምንም ባዮሎጂያዊ ምክንያቶች የሉም:: የዘርን ዕውነታነት መግለጽ የሚችል ነባራዊ ነገር የለም:: ጂኦገራፊ፤ ውጭያዊ ቅርጽ (phynotype)፣ ውስጣዊ ይዘት (genotype)፤ የሰው ልጅ አመጣጥ (genealogy) የዘርን ምንነት እንደሚያሳዩ ተደርጎ ይወሰዳል:: ይሁን እንጂ እነዚህ የሚያሳዩት በሰው ልጆች መካከል ምንም መሠረታዊ ልዩነት እንደሌለ ነው:: Phenotype ውጭያዊና ድንገተኛ ነው፤ genotype በአብዛኛው (99.90 በመቶ) የሰው ዘር ልዩነት የለውም ይላል:: በዚህም የተነሳ ዘር የሚያሳየው ምንም ነባራዊ ባሕርይ የለም ይባላል:: ይህ ከሆነ ዘንዳ ዘረኝነት የሚባለው ክፉ አባዜ ከዬት መጣ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው:: እንደምናውቀው ዘረኝነት በዓለም ላይ በሰፋት ከመኖሩም በላይ ለብዙ ጥፋቶች ምክንያት እንደሆነ የታወቀ ጉዳይ ነው:: ዘረኝነት መኖሩ እርግጥ ከሆነና ሥነ-ሕይወታዊ የሆነ የዘር መሠረት ከሌለ ዘረኝነት ከዬት መጣ? የዘረኝነት መሠረቱ ምንድነው? የዘረኝነት መሠረቱ ደም ወይም ዘረመል አይደለም:: ምክንያቱም በዚያ ረገድ የሰው ልጆች ሁሉ እስከ 99.90 በመቶ አንድ ስለሆኑ:: ስለዚህ ዘረኝነት የሚመሠረተው በሌላ ነገር ላይ ነው ማለት ይቻላል:: ዘረኝነት የቆዳ ቀለምንና ሌሎች የቅርጽነት ባሕርይ ባላቸው እንደቁመና፤ ፀጉርና በመሳሰለው ላይ የተመሠረተ ነገር ነው:: ስለዚህ ዘረኝነት በማኅበረሰብ የሚፈጠር ነገር ግን ምንም የባዮሎጂም ወይም የሌላም ነገር መሠረት የሌለው ነገር መሆኑ ነው:: በእንግሊዝኛ “racism is a social construct” እንደሚሉት ማለቴ ነው:: ለዚህም መነሻው እላይ እንደተባለው የቆዳ ቀለም፤ፀጉር፤ ቅርጽ ባጠቃላይ phenotype በስው ልጆች መሃል ያለን ምንም መሠረታዊ ልዩነት አያሳዩም:: ዘረኝነት ግን በነዚህ ላይ ተመሥርቶ እንደራስ ያልሆነን መጨቆን፤ ማግለል፤ ማንኳሰስ ነው:: ዘረኝነት በአንዱ የበላይነትና በሌላው የበታችነት የተመሠረተ ነው:: ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ የነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት በነጭ የበላይነት ላይ የተመሠረተና ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሕጎችን አውጥቶ ሥራ ላይ ያውል ነበር:: በዚህም የተነሳ ነጭ ያልሆኑ ሰዎች የመኖሪያ ቦታቸው፤ ትምህርት ቤታቸው፤ የሚገለገሉበት የሕክምና ተቋማት፤ ሬስቶራንቶች ከነጮቹ የተለዩ ነበሩ:: እንደ አሜሪካ ባሉ አገሮችም በሕግ ላይ የተመሠረተ ባይሆንም ነጭ ያልሆኑ የአሜሪካ ዜጎች ላይ በርካታ መድሎዎች ይካሄዳሉ:: ከሀብት ክፍፍል ጀምሮ በሌሎች የማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወደ ሚቀጥለው ገፅ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ላይ ነጭ ያልሆኑ ዜጎች ያላቸው ቦታ ዝቀ ያለ ነው:: በተለይ ደግሞ በነጭ ፖሊሶች አማካይነት በጥቁሮች ላይ የሚደርሰው ጭቆናና ግድያ የዘረኝነት ማሳያ ሆነው፤ ነጭ ያልሆኑ የአሜሪካ ዜጎች ባልተጻፉ የዘረኝነት ሕጎች እንደሚጨቆኑ የሚያሳዩ ናቸው:: ስለዚህ ዘርንና ዘረኝነትን ለያይቶ መረዳት ያስፈልጋል:: እላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የሰው ዘር አንድ ነው:: ሳይንስም ሆነ ሃይማኖቶች የሚያስተምሩን የሰው ዘር አንድ መሆኑን ነው:: ዘረኝነት ግን ሳይንሳዊም ሆነ ሃይማኖታዊ መሠረት በሌላቸው መሥፈርቶች ላይ በመመሥረት የሰው ልጆችን ለክፉ ዓላማ የሚከፋፍል ነው:: በዘረኝነት ውስጥ ያለው ዋና ሐሳብ አንዱ የበላይ ሌላኛው የበታች ስለሆነ የበታቹ መገዛት አለበት የሚል ነው:: እነኚህን ነገሮች በመረዳትም ሆነ ባለመረዳት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያሉ ሰዎች በማንነት ላይ የተመሠረተውን የአሁኑን ፌዴራሊዝም “የዘር ፖለቲካ” ይሉታል:: እውን አሁን በኢትዮጵያ የሚካሄደው “የዘር ፖለቲካ” ነው? “የዘር ፖለቲካ” ማለትስ ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ሕዝቦች ማንነታቸው፤ ባህላቸው፤ ታሪካቸውና የመሳሰለው እንዲከበርላቸው ረጅም ትግል አካሂደዋል፤ ከፍተኛ መሰዋዕትነትም ከፍለዋል:: ማንነት የሚመሠረተው በተለያዩ መሥፈርቶች ላይ ሲሆን በዘር ላይ አለመመሥረቱ ግን ሊሠመርበት ይገባል፤ ምክንያቱም ዘር የሚባል ነገር ስለሌለ:: የብሔር ማንነት እንደሚታወቀው የሚመሠረተው በቋንቋ፣ በታሪከ፣ በሥነ-ልቦና፣ በመኖሪያ አካባቢና በመሳሰለው ላይ ነው:: ከሁሉም በላይ አጽንዖት ሊሰጠው የሚገባው የብሔር ማንነት በደም ላይ የተመሠረተ አለመሆኑ ነወ:: የአንድ ብሔር አባላት የጋራ መሠረት አለን ብለው ሊያምኑ ይችላሉ:: ይህም ከአንድ መሰረት የመሆን እሳቤ (myth of origin) የሚባለው ነገር በደም ወይም በDNA ላይ የተመሠረተ አይደለም:: ማንነት እንደሚታወቀው ከላይ በተዘረዘሩት ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው:: ማንነት ብዙ መብቶችን የያዘ ሆኖ የራስን መብት በራስ የመወሰን መብት የሚያካትት ነው:: እንደ ሕዝብ የራስን መብት በራስ መወሰን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሰብዓዊ መብት ነው:: በኢትዮጵያ ከሩብ ምዕተ ዓመታት ላለፈ ጊዜ “የዘር ፖለቲካ”፣ “የጎሳ ፖለቲካ” እና የመሳሰሉት ሐሳቦች በተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለይም በተማሩት ሲንጸባረቅ ይታያል:: ዘር የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ምንም ሳይንሳም ሆነ ሃይማኖታዊ መሠረት የለውም:: የብሔርን ማንነት ለማስከበር የሚታገሉ ወገኖችን “የዘር ፖለቲካ” የሚያራምዱ ሰዎች ናቸው ብሎ መክሰስ ተገቢ አይመስለኝም:: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉና ለመብታቸው መከበር (ከሌሎች በላይ ለመሆን ሳይሆን ለእኩልነት) ለረጅም ዓመታት ሲታገሉ የኖሩ እንደ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ በቅርቡ ደግሞ አማራ እና ሌሎች በርካታ ብሔረሰቦ አሉ:: እነኚህ የተጠቀሱት በምንም መለኪያ ዘሮች ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም:: ምክንያቱም እላይ እንደተጠቀሰው ዘር የሚባል ነገር ባለመኖሩ:: ጎሳ የሚለው ጽንሰ ሐሳብ እነዚህን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕዝቦችን መግለጽ አይችልም:: በመሠረቱ ጎሳ ከቤተሰብ ከፍ ብሎ የሚገኝ ምናልባትም በደም መተሳሰርን የሚያመለክት ጽንሰ ሐሳብ ነው:: ጎሳ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የተወሰኑ ትውልዶችን የሚመለከት ሆኖ በጎሳው አባላት መካክል የስጋ ዝምድና ከመኖሩ የተነሳ ጋብቻ እንኳን በጎሳ አባላት መካከል አይፈጸምም:: ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ ቢያንስ አርባ ሚሊዮን ሕዝብ ገደማ ላለው የኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና መብት መከበር የሚደረገውን ትግል የጎሳ ፖለቲካ ማለት ይቻላል? ይህ ደግሞ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለብሔራቸው

እንወያይ 9

ቁጥር 007

መብት የሚታገሉትን ሁሉ ይመለከታል:: ለእኩልነት፣ ለማነነትና ለማኅበራዊ ፍትሕ የሚደረግን ትግል “የጎሳ” ወይም “የዘር ፖለቲካ” ማለትና በዚህ ዓይነት የብሔሩን አባላት ወይም መሪዎቹን “የጎሳ ፖለቲካ” አራማጆች ማድረግ የጋራ አገርን ለመገንባትና አንዱ ሌላውን ለመረዳት ፋይዳ አለው? ዘር፣ ጎሳ፣ ነገድ፣ ወዘተ. የመሳሰሉ በግልጽ ምን ማለት እንደሆኑ የማንረዳቸውን ጽንሰ ሐሳቦች በፖለቲካ ሐቲት (discourse) ውስጥ ማስገባት ጥቅሙ ምንድነው? እኛ ራሳችን በቅጡ ያልተረዳነውን ጽንሰ ሐሳብ በመጠቀም ሌሎችን ለማሸማቀቅ መሞከር ከጋራ ግብና ዓላማ አንፃር ፋይዳው ምንድነው? “የዘር ፖለቲካ”፣ “የጎሳ ፖለቲካ” እና ሌሎችም ኅብረተሰባችንን በትክክል የማይገልፁ ጽንሰ ሐሳቦችን የማንነት ፖለቲካ የሚያካሄዱ ሰዎችን ለማሸማቀቅ ሆን ተብለው በጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላት ሕዝቦችን ለማቀራረበም ሆነ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ምንም የማይፈይዱ በተቃራኒም የሚያራርቁ ናቸው:: የማንነት ፖለቲካን በቀላሉ የምንገላገለው ነገር አይደለም:: የማንነት ፖለቲካም “የዘር ፖለቲካ” አይደለም:: የማንነት ፖለቲካ የዕውቅና ጉዳይ ነው:: ‹እኛ ማን ነን?› የሚለውን እራስን በራስ ማን እንደሆንን የመግለፅ መብት የሚመለከትና እንዳለን እኛን ከማወቅ ይልቅ እኛን ለመግለጽ ለምን ትሞክራላችሁ የሚል ነው:: በኅብረተሰብ ሳይንስ ውስጥ የተናጋሪው ማንነት ወሳኝ እንደሆነ የሚጠፋን አይመስለኝም:: ማን እንደሆንኩ የማውቀው እኔ ነኝ ወይስ ጎረቤቴ ነው የሚወስንልኝ? የሚል መሠረታዊ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው:: ማንነት የሚመሠረተው ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው በዘረመል ላይ ሳይሆን በቋንቋ፣ በጋራ ታሪክ፣ በሥነ-ልቦናና በመሳሰሉት ላይ ነው:: የማንነትን ፖለቲካ ማራመድም አገርን የማፍረስ ጉዳይ አይደለም:: የማንነት ፖለቲካ ልዩነትን ለመደፍጠጥ የሚደረጉ አካሄዶችን የሚገዳደር፣ ነገር ግን በልዩነት ላይ ተመሥርቶ አንድነትን መመሥረትና ማፅናት የሚቻል መሆኑን የሚያሳይ ነው:: የማንነት ፖለቲካን ማካሄድ አደጋ የለውም ማለት አይደለም:: አደጋውን ማስቀረት የሚቻለው ግን ለልዩነት ተገቢውን ዕውቅና መስጠት፣ የጋራ ነገሮችን በጋራ ማሳደግ፣ አንዱ ሌላውን እንዲረዳ ማድረግ፣ ከዚያም ባለፈ ልዩነትን ለማጥፋት ከመጣር ይልቅ መቻቻልን መምረጥ ተገቢ ነው:: በእርግጥ ለማንነት ፖለቲካ የተደራጁ ወገኖች/ቡድኖች ጥፋት አይሠሩም፤ ሁሉም ለመብታቸው ብቻ በሐቅ ይታገላሉ፤ መድልዎ የለም ማለት አይቻልም:: እንዲያውም እንዲህ ዓይነት አደረጃጀት ለመድልዎ፤ በዝምድናና በቡድን ለመሥራትና ለሙስና የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም:: ያም ሆኖ ግን ይህንን ስላደረጉ ተግባራቸውን ዘረኝነት አድርጎ መፈረጅ አስቸጋሪ ይመስለኛል:: መቀራረባቸውን፤ ዝምድናቸውን፤ አንድ ቋንቋ መናገራቸውን ወዘተ. ይጠቀሙበታል:: ይህ እንዳይሆን ተቋማዊ መፍትሔዎችን ማበጀት እንጂ ነገሩን ያልሆነውን ስም መስጠት ችግሩን አባብሶ ያራርቅ እንደሆነ ነው እንጂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም የኛና የነሱ የሚባሉ ነገሮች ብዙ ጊዜ አሉ:: ችግር የሚፈጠረው የኛ የምንላችው ነገሮች ብቻ ተቀባይነት ይኑራቸው፤ የነሱ ከፋፋይ ወይም ኢትዮጵያዊ ስላልሆኑ የነሱን ትተን አንድ ዓይነት ብቻ እንሁን ስንል ነው:: ይህ በቋንቋም፣ በእምነትም፣ በባህልም በሌላውም ሊንጸባረቅ ይችላል:: ይህ ዓይነት አካሄድ ግን ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ረጅም መንገድ እንዳላስኬደ ለበርካታ ዐሥርተ ዓመታት ያየናቸው ክስተቶች አስረጅ ናቸው:: አንዱና ዋነኛው የማንነት ፖለቲካ መገለጫ እራሳችንን እንሁን፤ እራሳችን ማን እንደሆንን እንግለጽ ስንል በሌላ በኩል ሌሎች እኛ እናውቅላችኋለን፤ እኛ የምንለውን ተቀበሉ

ሲሉ ችግር ይፈጠራል:: እኛ አናውቅላችኋለን፤ እኛ እንዳልናችሁ ብቻ ሁኑ የሚለው አስተሳሰብ ዘመኑም ከደረሰበት ሁኔታና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከዘመናት ትግል በኋላ ከደረሱበት ደረጃ አኳያ ብዙ የሚያስኬድ ባለመሆኑ ወደ መከባበርና መቻቻል፣ ብሎም ዕውቅና መስጠት ደረጃ ከፍ ብንል ችግሮቻችንን ለመፍታት የጋራ ቀና መንገድ ይሆናል:: በዚህ አጋጣሚ ሁለት ነጥቦችን ባጭሩ አንስቼ ይህችን አጭር ጽሑፍ ላጠቃልል:: የግልና የጋራ መብቶች የተሰኙት ጽንሰ ሐሳቦች በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ ብዙ የሚያከራክሩ ናቸው:: የግለሰብ መብቶች ቢከበሩ ችግሮቻችን ይፈታሉ የሚሉ ሰዎች ብዙ ሐሳቦችን ከተለያዩ ምንጮች በመጥቀስ የግል መብቶች መከበር ለሁሉም ችግሮች ፍቱን መድኃኒት (panacea) መሆናቸውን ያስረዳሉ:: ምሳሌ ለመስጠትም ሳይቸገሩ የአውሮፓና ሌሎች በዲሞክራሲ አስተሳሰብ የሚመሩ አገሮችን ሁኔታ ይጠቅሳሉ:: ዲሞክራሲን ለማስፈን ዓይነተኛው መፍትሔ ይህ ብቻ መሆኑን ለማስረዳት ጥረት ያደርጋሉ:: በሌላ በኩል የጋራ መብቶች ወሳኝ መሆናቸውን የሚከራከሩ ሰዎች፣ ኅብረተሰቦች በራሳቸው ሁኔታ ላይ ተመሥርተው ለውጥ ማካሄድ እንዳለባቸው ለማስረዳት ይሞክራሉ:: ከሌላ ኅብረተሰብ የምንማረው ነገር የመኖሩን ያህል የራሳችንን ተጨባጭ ሁኔታ ማገናዘብ እንዳለብን ይከራከራሉ:: በአውሮፓ የተተገበሩት ሊበራል ዲሞክራሲም ይሁን ሶሻሊዝም ለአፍሪካና ለሌሎች አገሮች ምን ያህል አመቺ ናቸው? የሚል ጥያቄ በማንሳት ማንኛውንም የኅብረተሰብ ንድፈ ሐሳብ እንዳለ መገልበጥ እንደማያዋጣ ይከራከራሉ:: እሩቅ ካለ ሊብራል አስተሳሰብ ይልቅ የጋራ መብቶችን የሚያማክለው አስተሳሰብ የበለጠ ወደእኛ በአኗኗራቸን ሁኔታ፣ በባህላችንና በታሪካችን የተነሳ ለኛ ይቀርባል ይላሉ:: Individualism vs Communitarianism በሚለው ክርክር ውስጥ ግለሰብን ከኅብረተሰብ ውጭ ማሰብ እንደማይቻል ከማሳየት በተጨማሪ የረጅም ጊዜ አኗኗራችንም የበለጠ ወደ ሁለተኛው ያዘነበለ መሆኑን ለማሳየት ጥረት ያደርጋሉ:: የእያንዳንዱ ሰው ማንነት የሚቀረጸው በኅብረተሰቡ ውስጥና አማካይነት እንደመሆኑ መጠን፣ ሊብራሊዝም የሚነግረን ዓይነት ግለሰብና ግለሰበኝነት ከእውነት ይልቅ ወደ ልበወለድነት ያደላ ነው የሚል ክርክር ያነሳሉ:: በዚህ ረገድ በታወቁ የፖለቲካ ፈላስፎች ያለውን ክርክር ማስታወስ ተገቢ ነው:: በአውሮፓ በርካታ የግል መብትን የሚያጎሉ ያሉትን ያህል በሌላ በኩል ደግሞ እዚያው በአውሮፓና ሌሎች በርካቶች ደግሞ ከኤዥያና አፍሪካ የጋራ መብቶችን የሚደግፉ እናገኛለን:: እንግዲህ ያለው ክርክር በግለሰብና በኅብረተሰብ ዲያሌክቲክ፣ በባህላችንና በታሪካችን ላይ ተመሥርተን በምናይበት ጊዜ የጋራ መብቶች ከግል መብቶች ይልቅ ወደኛ ይቀርባሉ የሚል ነው:: ዞሮ ዞሮ ከሁለቱ ከመምረጥ ሁለቱን የሚያስተናግድ ነገር መሥራት አንችልም ወይ? የሚለው ሐሳብ የሚሻል ይመስለኛል:: ለዚህ ፎርሙላ ባይኖረኝም የግለሰብ መብትን ለማስከበር ብለን የጋራ መብቶችን መርገጥ የለብንም፤ የጋራ መብቶችን ለማስከበር ብለንም የግል መብቶችን መደፍጠጥ የለብንም:: ሁለቱን እንደተጻራሪ ከማየት ይልቅ እንደተደጋጋፊ ማየት እኛ ባለንበት ሁኔታ አስፈላጊ ይመስለኛል:: ሁለቱንም ከማጦዝ ለሁለቱም ማዕከላዊ የሆነ ነገር ማግኘት የሚቻል ይመስለኛል:: እዚህ ላይ ያለው ክርክር እውነቱ የትኛው ነው? የሚለው ይመስለኛል:: በሁለቱም ረገድ ፍፁም እውነት የሆነ ነገር የለም:: ፍፁም የሆነው ነገር ይህ ብቻ ነው፤ የኔ ብቻ ነው ካልን የትኛውንም ችግር መፍታት አንችልም:: የኛ ብቻ የሆኑ ፍፁም እውነቶች አሉ ብለን እንኳን ብናምን የራሳችንን ፍፁም እውነቶች ሌሎች ላይ መጫን አንችልም፤ ምክንያቱም የእኛ እውነቶች

የነሱ እውነቶች መሆን ስለማይችሉ:: በዚህ ረገድ እውነትንና ዕውቀትን ከፍላጎት/ጥቅም ለይተን ማየት እንችላለን የሚል መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል:: እውን እውነት ከፍላጎትና ከሥልጣን ተለይቶ ታይቶ ያውቃል? ይቻላልስ ወይ? በመሆኑም አማካይ ቦታ የመፈለጉ ጉዳይ ተገቢ ነው:: እላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በኅብረተሰብ አስተሳሰብ ውስጥ ብዙ ወገናዊ ያልሆነ (neutral) ነገር ለማግኘት አዳጋች ስለሆነ፣ የኛን ፍፁም እውነቶች በሌሎች ላይ መጫን ባንሞክር፤ አንዱ አንዱን ለመረዳት፣ ነገር ግን መሠረታዊ መግባባቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ብንረዳ፤ የግድ እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ የሚለው አስተሳሰብ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል በመገንዘብ እንደኛ ሊያስብ ከማይፈልገው ሰው ጋር ላለመግባባት ብንግባባና በመቻቻል መንፈስ ብንሠራ ሕመሞቻችንን ቀንሰን የጋራ አገር መገንባት እንችላለን:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ትክክለኛው ኢትዮጵያን የምናዋቀርበት የፖለቲካ ሥርዓት የቱ ነው የሚለው ጉዳይ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ ቢሆን ብዙ ቅራኔዎችን ለማስወገድ ይረዳናል:: ኢትዮጵያ አሜሪካ ወይንም ጀርመን ወይንም ሌላ አገር ሳትሆን ኢትዮጵያ ነች:: በርግጥ ከሌሎች የምትማረው ብዙ ነገር ቢኖርም እራሷን ካልሆነች ግን የትም ልትደርስ አትችልም:: ይህንን የምልበት ምክንያት በአንዳንድ አገሮች (በተለይም በምዕራቡ ዓለም) ሁኔታ ላይ በመመሥረት በዜግነት ብቻ ላይ የተመሠረተ፣ የግለሰብ መብት የተከበረበት ኅብረተሰብ አማራጭ የሌለው ነው የሚሉ አሉ:: ይህ አካሄድ ለዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝቦች የታገሉለትን ጥያቄ ይመልሳል ወይ? ብለን መጠየቅ አለብን:: ኅብረተሰብን በሞዴል ላይ ተመሥርቶ መገንባት ይቻላል ወይስ የራስን ሁኔታ አጢኖ ለራስ የሚሆን ይዘት ያለው ኅብረተሰብ ለመገንባት መጣር ይሻለል? የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ነው:: የላይኛውን ሐሳብ የሚደግፉ ሰዎች ያሉትን ያህል በሌላ ወገን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት አካሄድ የአገሪቱን ሁኔታ አያገናዝብም በማለት ብዝኃነታችንን ያማከለ ከውጭ ልምድም ጠቃሚ ሐሳቦችን የወሰደ ነገር ግን ለዐሥርተ ዓመታት ትግል የተካሄደበትን የማንነት ጉዳይ የማይሽር አካሄድ ተከትለን ኅብረተሰባችንን ብናዋቅር ይሻላል የሚሉ አሉ:: ይህ ጉዳይ በዚህ ምክንያት ከአካዳሚ ክርክር በላይ ነው:: ለበርካታ ዐሥርተ ዓመታት ከተካሄደው የትጥቅ ትግል በተጨማሪ ባለፉት ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ገደማ የተካሄው ለውጥ መሠረታዊ ከመሆኑም በላይ ይህንን ለመቀልበስ መሞከር ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል:: ዜግነት ላይ ብቻ የተመሠረተ መዋቅር ይሥራ ማለት እስካሁን የተካሄደው ትግል ምንም አስፈላጊ አልነበረም ማለት ነው:: የኅብረተሰብ መዋቅርን የሚወስነው በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ መሆን አለበት እንጂ የልሂቃን ምኞት መሆን የለበትም:: ተጨባጭ ሁኔታው የሚፈቅደውና የሚወስነው ነገር ነው ተግባራዊ የሚሆነው:: በአሁኑ ሁኔታ የልሂቃንን እናውቅላችኋለን አስተሳሰብ ለመቀበል ዝግጁ የሆነ ብዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለመኖሩም በላይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ፣ በሶማሌ ክልል፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክልሎች ሕዝቦች አሁን ስላለው ፌዴራሊዝም ያላቸውን ግንዛቤ ማጤን ለወደፊት እርምጃችን ጠቃሚ ይሆናል:: ቢያንስ ሰሞኑን በደቡብ ክልል የሰገን ዞን ሕዝቦች የሚጠይቁትን፣ የሲዳማን ሕዝብ ጥያቄ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች ራያን፣ ወልቃይትን፣ ጠገዴን አስመልክቶ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችን በጥሞና ያጤነ የጉዳዩን ክብደትና ሂደት ለመገንዘብ አይቸገርም:: ይህንን መገንዘብ ደግሞ ስለ መፍትሔው በጥልቀት እንድናስብ ያስገድደናል::

10 እንወያይ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሥርዓት ይበጃታል? ውስጥ ለኢትዮጵያዊነት ባላቸው የመረረ ጥላቻ ግንባር ቀደምቱን ሦስት እንጥቀስ ቢባል በተዋረድ መለስ ዜናዊን፣ ሚካኤል ስሁልንና ሱስንዮስን ማንሳት ይቻላል:: ምናልባት ልዩነቱ የሚካኤል ስሁልና የሱስንዮስ ጥላቻ በኢትዮጵያዊነት እሳቤ ላይ የተወሰነ ሲሆን፣ የመለስ ጠላትነት ግን አገሪቱ ከምትመራበት ሥርዓት አልፎ ከህልውናዋ ጋር ጭምር መሆኑ ይመስለኛል:: ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚመኙ ኀይሎች በሙሉ ዋነኛው የጥቃት ዒላማቸው ኢትዮጵያዊነት ነው:: በዚህ ረገድ አገር በቀል ጽንፈኛ ዘውገኞችን እንደ ጣልያን ካሉ ባዕዳን ወራሪዎች የሚያመሳስላቸው ከኢትዮጵያ ጋር የቋጠሩት ዘላለማዊ ደመኝነት ነው:: አገሪቱን በእጃቸው ማስገባት አይበቃቸውም:: መንግሥቱን በማፍረስ ወይም በመውረስ አይመለሱም:: አጋጣሚ እየጠበቁ ኢትዮጵያዊነትንም ከምድረ ገፅ ጠራርገው ለማጥፋት መገለጫ ርዕዮቱን፣ ባህሉን፣ ተቋማቱን፣ ትዕምርቶቹን፣ እምነቶቹን፣ እሴቶቹን ለማውደም ይዘምታሉ::

ቴዎድሮስ ኀይሌ

ይህ ጥያቄ ገና ከ1928 ዓ.ም የጣልያን ወረራ ቀድሞ ባለው ዘመን ባቆጠቆጠው የለውጥ ሐዋሪያ ልሂቃን በተለያየ መልኩ የተነካካ ቢሆንም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ በማንሳት የተሟላ መልስ ለማቅረብ የሞከሩት እውቁ ሊቅ ሀዲስ ዓለማየሁ ነበሩ:: ከዚያ ወዲህ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ሀዲስ ካቀረቡት አማራጭ ሌላ ሁለት ፍፁም የተራራቁ የአገር አስተዳደር ርዕዮት ዓለሞች የተከተሉ ሁለት አገዛዞች በተግባር ተሞክረዋል:: የወታደራዊው ደርግ አብዮታዊ መንግሥት ለ17 ዓመታት፤ ኢሕአዴግ ዘውጋዊ መንግሥት ለ28 ዓመታት በተቃራኒ አቅጣጫ አገሪቱን ሲያንገላቱ ከርመዋል:: ሆኖም ዛሬም እንዳዲስ ለአገራችን ምን ዓይነት ብሔራዊ ሥርዓት እንደሚበጃት መነጋገሪያ ሰዓት ላይ ነን:: “ዞሮ ዞሮ ዜሮ” እንደሚባለው ዓይነት:: ጥያቄውን ያስታወሰኝ ላለፉት 27 ዓመታት “ሞቶ ተቀበረ” እየተባለ ሲሟረትበት የከረመው ኢትዮጵያዊነት ካልተጠበቀ አቅጣጫ ባልተጠበቀ ሰዓት በለውጥ ፍልስፍናነት አንገቱን ቀና ማድረጉ ነው:: ይህ በአስደናቂነቱ ልክ በአግባቡ ያልተወያየንበትን ክስተት አብዛኞቻችን የተቀበልነው በሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ነው:: አንደኛው “ጠርጥር ከገንፎ አይጠፋም ስንጥር!” ነው:: ለውጡንም ሆነ የለውጡን ኀይል የኢትዮጵያዊነት ትርክት እስካሁንም በጥርጣሬ የሚመለከቱ አሉ:: ጥርጣሬ መዳረሻው ወደ ሴራ ንድፈ-ሐሳብ ነውና ባለፉት ስምንት ወራት ገደማ የተግተለተለውን ሁሉ ነገር እንደ ታላቅ የሕወሓት ድራማ አለበለዚያም እንደ ኦሕዴድና ኦነግ የጣምራ ተውኔት የሚቆጥሩ አሉ:: መጠራጠር በልኩ ሲሆን ጤናማነት ነው:: እንደዚህ ለከት ያጣ ጥርጣሬ ግን በሽታ ነው:: ናፖሊዮንና ሂትለር አልሞቱም ብለው የሚያምኑና ምድር ጠፍጣፋ ናት ብለው ማኅበር ያቋቋሙም ሁሉ መኖራቸውንም መዘንጋት የለብንም:: ኹለተኛው የለውጡን ኢትዮጵያዊነት የተቀበልንበት መንፈስ ደግሞ በሙሉ ልብ ማመን ነው:: በዚህም ወገን ከተንጸባረቁት የተለያዩ ዝንባሌዎች ዋነኛው ክስተቱን ከተአምራት መቁጠር ነው:: ኢትዮጵያ የፈጣሪ ተራዳኢነት

የማይለያት ቅድስት አገር ናት:: ስለዚህ ለውጡ አይቀሬ ነው:: ቲም ለማም ሆነ ዐቢይን በግል የኢትዮጵያ አምላክ የላካቸው ተአምራት አስፈፃሚዎች ናቸው:: ይኼ ነገር ብሔራዊ እምነት እንጂ ሃይማኖት አይደለም:: በተለምዶ በአንድ ሃይማኖት አለመገደቡ ብቻ ሳይሆን እምብዛም በሃይማኖት ጥብቅነት የማይታወቁ “ሳይንቲስቶችን” ጭምር የማረከ እምነት ነው:: “ይኼ ልጅ አግዚአብሔር ለኢትዮጵያ የላከላት ነው!” እውነትም ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን አገር ናት! እነዚህ ኹለት ዝንባሌዎች አግባብ ናቸው ወይም አይደሉም ማለት ጉንጭ አልፋ ነው:: ጥርጣሬው በብሔራዊ ፖለቲካችንና ፖለቲከኞቻችን ሥነ-ምግባር ላይ ካሳደርነው ተጨባጭ ትዝብት የሚነሳ ነው:: እምነቱም ጭፍን ሳይሆን በአገሪቱ ብሔራዊ ትውፊተ ታሪክ የተደገፈና ኢትዮጵያዊነት ለብዙ ሺሕ ዘመናት በታሪክ ውጣ ውረድ ካለፈበት የጽናት ተመክሮ ላይ የተመሠረተ ነው:: ነገር ግን ኹለቱንም አመለካከቶች የሚያማክለውን የኢትዮጵያዊነት ማንሰራራት ምሥጢር የሚገልፁት በምክንያትና ውጤት ላይ ተመስርተው አይደለም ለማለት ነው:: ባለፈው ግማሽ ምዕት የአገር ግንባታ መንግሥታዊና ብሔራዊ አማራጮች ላይ ለመደማመጥ ትዕግሥት አጥተናል:: ምን ዓይነት ፖለቲካዊ ሥርዓትና መንግሥታዊ አወቃቀር ይበጀናል? የብሔራዊ አቋማችን ቅርፅና ይዘት ምን ይምሰል? የሚለው በጡንቻና በሁካታ የሚወሰን ነበር:: በተለይ ስለ ኢትዮጵያዊነት በወጉ ተነጋግረን አናውቅም:: በየራሳችን የኢትዮጵያዊነት ትርጉም ተቧድነን ተፋለምን እንጂ:: በዘመነ ደርግ ኢትዮጵያዊነት ለጥቃት ባይጋለጥም እምብዛም ከመፎክር ያለፈ ትኩረት አላገኘም:: በዘመነ ኢሕአዴግ ደግሞ ከናካቴው በይፋ የተወገዘ ርዕሰ ጉዳይ ነበር:: ኢትዮጵያዊነት በደረሰበት ዙሪያ ገብ ጥቃት ከፖለቲካው ብቻ ሳይሆን ከምሁራዊውም ዓለም ወደ ጥጋጥግ ተገፍቶ ቆይቷል:: ስለዚህም እንደ ሕዝብ በአንገብጋቢ የብሔራዊ ማንነትና የአገር ግንባታ ርዕሶች ላይ ለማሰላሰልና ለመምከር የምንችልበት ዕድል ተዘግቷል:: በአንድ ጥግ “ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት!” በሌላው ደግሞ “የፌዴራል ሥርዓቱ

የሚፈርሰው በመቃብራችን ላይ ነው፤” የሚል ፈሊጥ አለ:: ይህ ቀና ያልሆነ መንፈስ ደግሞ ሙግታችን፣ ጥላቻችንና ውዴታችን ከፊደሉ ያለፈ እንዳይሆን እግር ተወርች አስሮታል:: ይህን የጭፍንነት ገረገራ ሰብረን በጭብጡ ላይ መነጋገር ከጀመርን ስለአገር ግንባታ አማራጮች ለመተማመን ረዥም መንገድ እንጓዛለን:: በዚህ መንፈስ ለውይይት መቀስቀሻ እንዲሆን ያሳለፍናቸውን ሁለት የአገር ግንባታ ሙከራዎች አጠር አጠር አድርጌ አቀርብና አሁንስ ምን ይበጀናል ለሚለው በአማራጭ ሐሳብ እደመድማለሁ:: ከዚያ በፊት ግን ስለ አገር ግንባታ ምንነት ጥቂት ልበል:: አገር ግንባታ በአጭሩ መንታ ዘርፎች ያሉት ብሔራዊ መንግሥት ግንባታ ነው:: አንደኛው መንግሥት ግንባታ ሲሆን፣ ይህም ለአገር አስተዳደር የሚያገለግሉ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊና ሥርዓታዊ መዋቅሮች ላይ ያተኩራል:: በተለይም ወታደራዊና ኤኮኖሚያዊ ሀብቶችን የማማከል፤ የመሬት ስሪትና የግብር ሥርዓት የመዘርጋትና የመቆጣጠር፤ የፍትሕና ሕግ ሥርዓት የማቆምና የማስከበር ተግባራትን ያጠቃልላል:: ሁለተኛው ብሔር ግንባታ ደግሞ አገራዊ ማንነትና ሥነ-ልቡናዊ አንድነት ላይ የሚያተኩር ሂደት ነው:: ይህም የጋራ ርዕዮተ ዓለም መንደፍ፣ የጋራ ሥርዓተ ትምህርት፣ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶችንና ትዕምርቶችን ማደራጀት፣ ማበልፀግና መጠበቅን ያካትታል:: በዚህ መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን እስከ ዘመነ ደርግ የዘለቀው ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትና በዘመነ ኢሕአዴግ ሥራ ላይ የዋለው አዲስ የዘውጌ ብሔርተኝነት የአገር ግንባታ ሂደቶች የምንገመግማቸው ልዩና ግልፅ የብሔራዊ ማንነት ንቃተ ኅሊና ፈጥረዋል ወይ? ጠንካራ የብሔራዊ አንድነት መሠረት ተጥሏል ወይ? የአገሪቱን ህልውና ቀጣይነትስ አረጋግጠዋል ወይ? እያልን ነው::

1.ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያዊነት በአጭሩ ኢትዮጵያ የምትባል አገር፣ ሕዝብና መንግሥት አሃዳዊ ዜግነታዊ ብሔርተኝነት ነው:: ብሔራዊ ታሪካችን እንደሚመሰክረው ኢትዮጵያዊነት በተደጋጋሚ ፈተና ላይ ሲወድቅና ሲነሳ እዚህ ደርሷል:: የኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ባለጋራዎች ደግሞ ባሕር ተሻግረው ድንበር ሰብረው የሚመጡ ብቻ አልነበሩም:: ሌላው ቢቀር ከአገሪቱ መሪዎች

በተቃራኒው ኢትዮጵያ ደረታቸውን ለጦር ግንባራቸውን ለጥይት ያለማቅማማት የሚሰጡላት በሀገር ፍቅር የነደዱ ልጆችን አላጣችም:: የኢትዮጵያን መንግሥት ተቆጣጥሮ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ መሪ የኢትዮጵያ ጠላት ሊሆን አይችልም:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ ሲናገሩ ከአንጀት እንደሆነ ያስታውቃል:: ኢትዮጵያዊነትን በሕይወታቸው የቋጠሩ መሆናቸውን መጠራጠር አይቻልም:: ነገር ግን ፍልሚያው የግል ሳይሆን የለውጡ ኀይሎች ርዕዮት በሆነው በኢትዮጵያዊነትና በአልሞት ባይ ተጋዳዩ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት መካከል ነው:: የአዲሱ ሥርዓት ጠላቶች የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ደመኞች ናቸው:: ዋነኛው ፍልሚያ በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የሚደረግ ነው:: የለውጡ ኀይሎች ለ27 ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን ቀመር ገልብጠው “ኢትዮጵያዊነት ውስጤ ነው” ማለታቸው የአገሪቱን ፖለቲካ መልክዐምድር ክፉኛ ገለባብጦታል:: ዘውጌ ሥርዓቱ ባመቻቸላቸው መሠረት እንደ አሸን የፈሉት ጥቃቅን ‹ጨርቦሌ› ፓርቲዎች ክፉኛ ሚዛናቸውን አስቷቸዋል:: በኢትዮጵያዊነት ተስፋ አንቆርጥም ብለው በረሃ ድረስ የወረዱት ጥቂት የፖለቲካ ቡድኖች ደግሞ አጀንዳቸውን ተነጥቀዋል:: ራሱ ኢሕአዴግ ዘረመሉ ዘውጋዊ ስለሆነ ከአዲሱ ኢትዮጵያዊ ማንነቱ ጋር እንዴት እንደሚላመድ የቸገረው ይመስላል:: ዞሮ ዞሮ በሚቀጥሉት ዓመታት የፖለቲካ ሥልጣን ፉክክሩ ምሕዋር ኢትዮጵያዊነት መሆኑ አያጠራጥርም:: በአጠቃላይ የአገራችን ብሔራዊ ታሪክ ሂደት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኀይል ኢትዮጵያዊነት በውስጣዊም ውጫዊም ኀይሎች እየተፈተነ የሚያልፍበት ዲያሌክቲክ ነው:: ለብዙ ሺሕ ዓመታት የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ህልውና አስጠብቆ በመኖር ፍቱንነቱን ያረጋገጠ ርዕዮተ ዓለም ነው:: በዚህ ታሪካዊ ማዕቀፍ ካየነው ዛሬም እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያዊነት መንምኖ ለህልውናው በሚፋለምበት ወቅት እንደገና የማንሰራራቱ ምሥጢር ያለው በተፈጥሯዊ ባሕርያቱ ላይ ነው:: አንደኛ ኢትዮጵያዊነት በዜግነት ላይ የተመሠረተ አዎንታዊ የአገር ግንባታ ርዕዮተ ዓለም ነው:: በትናንትና በዛሬ ላይ ብቻ ሳይተከል ነገንም በቀና መንፈስ የሚያልም ራዕይ ነው:: በጋራ ታሪክ፣ ባህል፣ እሴቶች፣ ተቋማትና ሥርዓታት ላይ የቆመ ነው:: ወደ ሚቀጥለው ገፅ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

11

እንወያይ

ማስታወቂያ ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነት የሃርነት ርዕዮት ነው:: በመላው ዓለም ራሳቸውን ከጥንታዊም ሆነ ዘመናዊ ቅኝ አገዛዝ ተከላክለው፣ ብሔራዊ ነፃነታቸውን አስከብረው እስከዛሬ የኖሩ ሕዝቦች ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው:: የአይበገሬነታቸው ምሥጢርም የነጻ ሕዝብነታቸው ምልክት የሆነው ኢትዮጵያዊነት ነው:: ኢትዮጵያ የፈጣሪዋ ተራዳኢነት የማይለያት፣ ብትወድቅ ወድቃ የማትቀር፣ በትሸነፍ በድል መውጣቷ አይቀሬነቱን የሚሰብከው ኢትዮጵያዊነት ነው:: ስለዚህም ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት የሆነ የሃርነት ርዕዮተ ዓለም ነው:: ሰው በላውን የወያኔን ሥርዓት የገረሰሱት የለውጥ ኀይሎች በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር የተሰባሰቡት ኢትዮጵያዊነት የማታ ማታ አሸናፊ ርዕዮት በመሆኑ ነው:: ኢትዮጵያዊነት በተጨባጭም ራሳቸውን ከሕወሓት ጋሻ ጃግሬነት፣ ሕዝባቸውንና አገራቸውን ከጭቆና ቀንበር ነፃ ለማውጣት የሚያስችል የሃርነት መሳሪያ ስለሆነ ነው:: ‹ቲም ለማ› ከወደቀበት ያነሳው የኢትዮጵያዊነት ዓርማ ካራማራ ላይ ኢትዮጵያውያን በጋራ የወደቁለት ነው:: ሦስተኛ ኢትዮጵያዊነት የመቻቻልና አብሮ የመኖር አስተምህሮ ነው:: በታሪክ ሂደት ማኅበራዊ ልዩነቶችን በጋራ ፈትል እያሰናሰለ፣ ድንበሮች እየተሻገረ የሚዘልቅ፤ ፅናትን ከልዝብነት፣ ታጋሽነትን ከቆራጥነት፣ መስጠትን ከመቀበል ያጣመረ ርዕዮት ነው:: ክፍትና አካታች በመሆኑ መስፈርቶቹ ሚኒመም/ገራገር ናቸው:: በዚህም ባሕሪው በየጊዜው ማኅበራዊ ድንበሩን እያሰፋ ያመነበትን ኀይል ያለልዩነት ያቅፋል ይቀበላል:: በአንድ ቡድን ወይም ማኅበረሰብ ያልተገደበ የበርካታ ማኅበረሰቦች የጋራ ርዕዮት ለመሆን ችሏል:: በቅርብ ዓመታት በአገሪቱ ህልውና ላይ አንዣብቦ የነበረውን ማዕበል ገስፆ ፀጥ የማድረግ ኀይሉ ምክንያት መሠረተ ሰፊነቱ ነው:: ኢትዮጵያዊነት በተግባርና በሂደት ለመሻሻልና ለመለወጥ ቀና ነው:: በዚህም ምክንያት ከጊዜው ጋር ለመራመድ፣ አዳዲስ እሳቤዎችንና ኀይሎችን ለማስተናገድ አይቸገርም:: ኢትዮጵያዊነት ከአገዛዝ አገዛዝ እንኳን ልዩነቶችን ሊያስተናግድ የሚችልበት ክፍትነት አለው:: ለዚህ ሁነኛ ምሳሌ የሚሆነው የወታደራዊው ደርግ ሶሻሊስት ኢትዮጵያዊነትን ለመገንባት ያደረገው ጥረት ነው:: ከደርግ ብሔርተኝነት ሕጋዊ መሠረቶች የመጀመሪያው አገር በቀል ብሔርተኛ አቋሙ “ኢትዮጵያ ትቅደም” የተባለው ነው:: ሁለተኛው በታኅሣሥ 11 ቀን 1967 ዓ.ም ባወጣው “ኅብረተሰባዊነት” የተባለውና ኢትዮጵያዊነትን ከሶሻሊዝም መርሆች ለማዳቀል የሞከረበት የፖለቲካና ኤኮኖሚ መርሐ ግብሩ ነው:: ኅብረተሰባዊነት ከኢትዮጵያ አፈር፣ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖቶች የመነጨ ፍልስፍና ነው:: ከታላላቅ ሃይማኖቶቻችን የሰብአዊ እኩልነት አስተምህሮ፣ ከአብሮና ተካፍሎ መኖር ባህላችን፣ እንዲሁም በብሔራዊ መስዋዕትነት ካሸበረቀው ታሪካችን የሚመነጭ የፖለቲካ ፍልስፍና ነው:: የኅብረተሰባዊነት አምስት ቁልፍ መርሆች ብሔራዊ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነት፣ ብሔራዊ በራስ መተማመን፣ የሥራ ክቡርነት እና የሕዝብ ጥቅም ቀዳሚነት ናቸው:: በአጠቃላይ ከባህል አኳያ ዘውዳዊውና ወታደራዊው አገዛዞች የተከተሉት ብሔራዊ ፖሊሲ ባህላዊ ይዘት የሌለው ፖለቲካዊ አንድነት ፋይዳ ቢስ ነው የሚል ነበር:: የሁለቱ የባህል ግንባታ አቅጣጫና ይዘት እንደ ርዕዮተ ዓለማቸው የተራራቀ ቢሆንም ቅሉ ፣ የባህል ውሕደት ስልታቸው ግን ኢትዮጵያን በአንድ ቡድን ባህል ሥር የሚጨፈልቅ (assimilationist) አልነበረም:: የባህላዊ ማኅበረሰቦች መሠረታዊ ልዩነቶች እንደተጠበቁ በቁልፍ ብሔራዊ ምልክቶች የተዋሃደና ከዘውጎች የላቀ አገራዊ ባህል የመገንባት (integrationist) እንጂ::

2.ዘውጋዊ ብሔርተኝነት ዘውጋዊ ብሔርተኝነት በትውልዳዊ ማኅበረሰቦች ሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ ድምር ማንነታዊ ኢትዮጵያዊነት ነው:: በኢትዮጵያ ታሪክ ዘውገኝነት በአውራጃዊነት የተበታተነ ስለነበር በማዕከላዊ መንግሥቱ ላይ የሚያሳድረው ጫና በዘላቂነት የህልውና አደጋ አልሆነም:: ነገር ግን አልፎ አልፎ እንደ ጉዲት፣ ግራኝ የመሳሰሉ ጠንካራ የጦር አበጋዞች የየአውራጃቸውን ህዝብ ቀስቅሰው ሲነሱ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተላቸው አልቀረም:: ዘውጋዊነት ዘለግ ያለ ጉልበት ያገኘው ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚታወቀው የአገራችን ታሪክ (ከ1760 ዓ.ም እስከ 1848 ዓ.ም) ባለው የአንድ ምዕት ገደማ ወቅት ነው:: ይህም ቢሆን ዛሬ እንደሚታየው ያለ መላውን ዘውግ ያቀፈ ሳይሆን በአንድ ዘውግ የበላይነት የሚመራ አውራጃዊ ክስተት ነበር:: ስለዚህም ዘውጋዊነት ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ የአገር ግንባታ ርዕዮትነት እውን የሆነው በዘመነ ኢሕአዴግ ነው:: በዚህ እሳቤ መሠረት ኢትዮጵያ አሃዳዊ ብሔር ሳትሆን ብዝሃዊ ወይም የብሔሮች ብሔር ናት:: ብሔራዊ መሰረቷም ሕዝባዊ ሉዓላዊነት ሳይሆን ዘውጋዊ ሉዓላዊነት ነው:: ስለሆነም ዜግነታዊ ብሔርተኝነት በዘውጋዊ ብሔርተኝነት ተተክቷል:: ኢሕአዴግ ለ“ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” ፖለቲካዊ ነፃነት በማጎናፀፍ የመንግሥቱ አስተዳደራዊ መዋቅር መሠረት አድርጓቸዋል::

ማይድሪም ሪልእስቴት MY DREAM

REAL ESTATE

0922 02 2220

የዚህ ዘመናዊ ዘውጋዊነት ለዘብተኛ መነሻዎች በራስ ማንነት የመኩራት፣ ቋንቋንና ባህልን የመጠበቅና የማበልፀግና በደምሳሳው የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄዎች ናቸው:: ነገር ግን ዘውጋዊነት በተፈጥሮው በነዚህ አዎንታዊ ባሕርያት ላይ አይቆምም:: ከራስ በላይ የሚል የግለኝነት ስሜትና ተቀናቃኝነት የገነነበት የመለያየት፣ የመቃቃር፣ የማፍረስ ርዕዮት ነው:: እንዲህ ያለው ጽንፈኛ ዘውጋዊነት ጎሰኝነት ይባላል:: ዘውጋዊነት ማኅበራዊ ድንበሮቹ የተዘጋና በሐሳይ ሥነ-ሕይወታዊ ወይም ተፈጥሯዊ ጠባይ ባላቸው እንደ ደምና ዘር ያሉ የማያፈናፍኑ መስፈርቶች ላይ የተመሠረተ ነው:: የሰውን ልጅ ወደ ደመነፍሳዊነት የሚያወርድ እሳቤ ነው:: በዘመነ ኢሕአዴግ እንደታየው ዘውጋዊነት ጽንፈኛ ሲሆን ከናካቴው የሰው ልጅን ተፈጥሯዊ አንድነትና ሰብአዊ እኩልነት ይክዳል:: ከጠባብ ቅጥሩ የዘለለ ምንም ዓይነት የዴሞክራሲና የፍትሕ መንፈስ የለውም:: በአገሪቱ የተዘረጋው ዘውጋዊ ፌዴራል ሥርዓት በዚህ እሳቤ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ፣ ብዙውን ጊዜ ደጋፊዎቹ እንደሚሉት ችግሩ አተገባበሩ ነው የሚለው የጠነዛ ሙግት ነው:: አንድን ፖለቲካዊ ሥርዓት የምንመዝነው ቢያንስ ለአብዛኛው ዜጋ በሚያስገኘው ዘላቂ ጥቅሙ ከሆነ፣ ፌዴራል ሥርዓቱ ከጥንስሱ ጀምሮ ያስከተለውን ሰቆቃና በአገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ አስተባብሎ ማለፍ አይቻልም:: ካለፉት 28 ዓመታት ተመክሯችን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ በእጅጉ ያመዘነ መሆኑን ዓይን ያለው ሁሉ የሚያየው ነው:: የኢሕአዴግ ዘውጌ ብሔርተኝነት መሠረቶች አንደኛው በ1975 ዓ.ም. ማሌሊት ሲመሠረት አንስቶ የሕወሓት መሪ የፖለቲካ አስተምህሮ የነበረው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ነው:: ኹለተኛው የሽግግር ቻርተሩ (ከሐምሌ 15 ቀን 1983 እስከ ነሐሴ 15 ቀን፣ 1987 ዓ.ም) እና ሦስተኛው በታኅሣሥ 2 ቀን 1984 ዓ.ም. የታወጀው “የብሔራዊ ክልላዊ ራስ-ገዝ አዋጅ ቁ.7/1984” ነው:: ይህ አዋጅ “ብሔር ወይም ብሔረሰብ ማለት በአንድ ኩታ ገጠም መልክዐ ምድር የሚኖር፣ አንድ የሚያግባባ ቋንቋና የአንድነት ሥነ-ልቦና ያለው ሕዝብ ነው” ይላል:: አራተኛው በነሐሴ 1987 ዓ.ም. የታወጀው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወደ ገፅ 20 ዞሯል

በከተማችን እምብርት ከአፍሪካ ሕብረት ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ ግንባታው በመፋጠን ላይ ያለው G+16 ሕንፃ

12 ሐሳብ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

የልኂቃን ውድቀት ወደ ከፋ መከራ ከመግባታቸው በፊት ሁላችንም መፍትሔ የምንለውን ምክረ-ሐሳብ እንድንሰነዝር ለማሳሰብ ነው::

ብርሃኑ አበጋዝ

ለመሆኑ በእንዲህ ዓይነት ምስቅልቅል ውስጥ የጨመረን ምንድን ነው? ይህን አደጋ ኮትኩቶ በማሳደግ ረገደ የልኂቃኑ ሚና ምን ያህል ነው? መፍትሔውስ ምንድን ነው? በእነዚህና እነዚህን በመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ ጊዜ ሳናባከን ልንወያይባቸው ይገባል:: ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች በእነኝህ መሠረታዊ አጀንዳዎች ላይ ልንመክር ልንዘክር ይገባናል::

አስተኔ ምሁራን



ልኂቃን ውድቀት አገራችንን ውድ ዋጋ እያስከፈላት ነው:: በዚህች አጭር ጽሑፍ ስለ ኢትዮጵያ ልኂቃን በተለይም ስለ አማራና ትግራይ ልኂቃን አንዳንድ ጉዳዮችን አነሳለሁ:: ስለ አማራና ትግራይ ወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ስለሁለቱ ሕዝቦች ኅብረትና አንድነት መናገር አልፈልግም፤ በደንብ የሚታወቅ ስለሆነ:: እነኝህ አንድም ሁለትም የሆኑ ሕዝቦች በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በፊደል፣ በሥነ-ልቦና አንድና ያው መሆናቸው የማያጠራጥር ሐቅ ስለሆነ:: የእኔ አጀንዳ በእነኝህ የኢትዮጵያ ምሰሶዎች ላይ ልኂቃኑ ምን ያህል በደል እንዳደረሱባቸውና እያደረሱባቸው እንደሆነ የተወሰኑ ነጥቦችን መፈንጠቅ፣ ይልቁንም ወደለየለት ዝቅጠት እየወረደ የመጣው ልኂቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁለቱን ወንድምና እህት ሕዝቦች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ሊማግዳቸው እየሠራ መሆኑን ለመግለጽ እና አገርና ሕዝብ

ተማርን የምንለው ኢትዮጵያዊያን “ምሁር” የሚለውን ትልቅ ማዕረግ የመሸከም አቅሙም የሞራል ልዕልናውም የለንም:: የበቀለበትን ኅብረተሰብ ዕሴት በሚገባ በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ ያልመረመረ፣ የውጭውንም ዓለም አቀፍ ሁኔታ በሚገባ ፈትሾ ከአገራዊ ሁኔታው ጋር በማስታረቅ ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ዕውቀት ማመንጨት ያልቻለ አካል “ምሁር” የሚለውን መጠሪያ መሸከም ከቶም አይችልም:: ተማርን የምንል ኢትዮጵያዊያን ትልቁ ችግር ይህ ነው:: በአንድ በኩል የበቀልንበትን ኅብረተሰብ ዕሴት በዕውቀት ላይ ተመሥርተን አልመረመርነውም፤ አናውቀውም:: ስለኢትዮጵያ እያወራን ነገር ግን ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ያለን ዕውቀት እጅግ ደካማ ነው:: የአገራችን ባህልና ዕሴት በመናቅ መንፈስ ወደ ውጭ ብናማትርም በአንድ በኩል የውጭውንም መጠንቀቅ አልተቻለንም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ የቃረምነውን ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንጻር አስማምተን መጠቀም አልቻልንም:: በዚህ ምክንያት ተማረ የሚባለው የኅብረተሰብ ክፍል አብሪ ኮከብ ሆኖ አገርና ሕዝብን ወደፊት ከማራመድና አቅጣጫ

ከማሳየት ይልቅ በአውዳሚ አጀንዳዎች ላይ መሰለፍን ግብሩ አድርጓል:: ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ደጋግመው እንዳስገነዘቡት የራሱን ጥሎ የሌላውን የሚያንጠለጥል፣ የራሴን ያዝኩ በሚልበት ጊዜም የእኔ ብቻ ይበቃኛል ወደሚል መታበይ የሚወርድ ቅጥ-አምባሩ የጠፋበት የኅብረተሰብ ክፍል ነው፤ “ምሁሩ”:: ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑት የትግራይና አማራ “ምሁራን” ናቸው:: እነኝህ የድሃ ድሃ ከሆኑ ማኅበረሰቦች የወጡ “ምሁራን” ሕዝባቸው ከገባበት የብሉይ ዘመን ድህነት እንዴት መውጣት እንዳለበት የመፍትሔ ሐሳብ ሲያቀርቡ አይታይም፤ ሕዝብ ሊጠቅሙ የሚችሉ የፈጠራ ውጤቶችን ሲያቀርቡ አይሰማም፤ የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነት ስለሚጠናከርበት፣ ሺሕ ዓመታት ያስቆጠሩ የጋራ እሴቶቻቸው ከዘመኑ ጋር ስለሚዘምኑበትና ስለሚጎለምሱበት ሁኔታ አይመክሩም፤ አይዘክሩም:: ከዚህ ይልቅ በሚያሳፍር መልኩ ተማርኩ የሚለው ኀይል ነገሮችን ይበልጥ በማጋጋል ላይ ተጠምዷል፤ ጥላቻና ግጭት የሚፈጥሩ የጥፋት አጀንዳዎችን በማምረት ላይ ተሰማርቷል:: ዛሬ በሚያሳፍር ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ሳይቀሩ የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ወጣቱን አክራሪ በሆነ ዘውጌ ብሔርተኝነት ኮትኩተው እያሳደጉት ይገኛሉ:: ገለልተኛ ሆነው ሁሉንም የኢትዮጵያ ልጆች በእኩል ደረጃ በዕውቀት መኮትኮት የሚገባቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን አክራሪና አውዳሚ በሆነ የዘውግ ፖለቲካ ተጠምደው ይውላሉ:: መምህራኑ ለደቀ-መዝሙሮቻቸው አርአያ መሆን ሲገባቸው ፌስቡክ ላይ ወጥተው ጥላቻን ይሰብካሉ፤ ግጭት ቀስቃሽ በሆኑ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፤ በሕዝብ መካከል ጠባሳ የሚጥል ተግባር ይፈጽማሉ:: ስለውይይትና አብሮ ስለማደግ አይጽፉም፤ ስለጋራ ዕሴቶቻችን አይናገሩም:: ሥራቸው ሁሉ ከተማረ ሰው ፈጽሞ የማይጠበቅ ነው::

ሥራ ፈጠራ ወይስ ጦርነት? አደጋውና ዝቅጠቱ በ”ምሁራኑ” ብቻ የተወሰነ አይደለም:: ኹለቱን ክልሎች የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅቶችም በሁሉም ረገድ ወድቀዋል:: እነኝህ በትግራይና አማራ ሕዝቦች ስም የተቋቋሙ ድርጅቶች በሁለቱ ሕዝቦች ዘላቂ ግንኙነት ላይ የፈፀሙት ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በሚገባ ሊጋለጥ ይገባዋል:: ሕወሓት ገና ከፅንሱ ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ድህነትና ቁስቁልና ውስጥ የሚገኘውን የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ በመሳል፣ ሰነድ አዘጋጅቶ የትግራይን ልጆች ሲያስተምር ኖሯል:: በኹለቱ ወንድምና እህት ሕዝቦች መካከል ለሺሕ ዘመናት የተገነባውን የአብሮነት እሴት ለመናድና ትግራይ ከአማራ ጋር የሚያገናኘው የታሪክም የባህልም ክር የለም የሚለውን በሬ-ወለደ በሕዝብ ላይ ለመጫን ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም:: ሕወሓት ሰፊው የትግራይ ሕዝብ በሁለንተናዊ መልኩ ወንድሙ የሆነውን የአማራን ሕዝብ እንዲጠላ ማድረግ ባይቻለውም ብዙሃኑ የትግራይ ልኂቅ ግን የሕወሓት አውዳሚ ትርክት ሰለባ ሆኗል ማለት ይቻላል:: በዚህም ምክንያት ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ሦስት ዐሥርት ለሚጠጉ ዓመታት መጠነ-ሰፊ ውርጅብኝ ሲያወርድ “ተው አይሆንም፤ ትክክል አይደለም፤” ያለ አካል አልታየም:: ሕወሓት የእጅ ሥራው በሆነው ብአዴን (የአሁኑ የአማራ ብልጽግና) አማካይነት በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈፅሟል:: ሆኖም ለጊዜው ካልሆነ በስተቀር ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልምና የአማራ ሕዝብ የሚደርስበትን የግፍ ቀንበር ከላዩ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል ቆርጦ ከተነሳ ማግስት ጀምሮ የብአዴን አመራሮችም ዐይናቸውን በጨው አጥበው የለውጥ ሐዋሪያ ሆነው ቀርበዋል:: ሳያፍሩ ሳይፈሩ የትግሉ ዋና ተዋናዮች እኛ ነን እስከማለትም ሄደዋል:: ትናንትና ከሕወሓት ጋር በመሆን ሕዝብ ሲያሸብሩ የነበሩ ግለሰቦች ኮታቸውን ቀይረው “የለውጥ ኀይል” የሚል ማዕረግ ተሰጥቷቸው እንደ ጀግና እየተወደሱ ይገኛሉ:: በጥቅም ኔትዎርክ ተሳስረው ሕዝብ ሲያማርሩ የኖሩ ግፈኞች የመደመር ፊታውራሪዎች ለመሆን በቅተዋል:: የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ደም ያቃባው ግፈኛው የሕወሓት ቡድንም እየተወደሰ ነው:: ከአማራ ወንድሙ ጋር ሊያፋጀው ቆርጦ የተነሳውን ግፈኛ ቡድን የትግራይ ልኂቅ አቅፎ ደግፎ ይዞታል:: በአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ በደል ያደረሰውን ብአዴንንም የአማራ ልኂቅ እንደ ለውጥ ኀይል ቆጥሮ እየተንከባከበው ነው:: ብአዴንና ሕወሓት በበኩላቸው የልኂቃኑን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ስሜት ቀስቃሽና ኮርኳሪ የሆኑ የማንነት አጀንዳዎችን በማጦዝ ላይ ይገኛሉ:: ወጣቱ የሚፈልገው ሥራ ነው፤ ጥራት ያለው ትምህርት ነው:: ሕዝቡ የሚፈልገው ከገባበት የብሉይ ዘመን የድህነት አረንቋ መውጣት፣ ንጹሕ የመጠጥ ውኃና የጤና ተቋማትን በአቅራቢያው ማግኘት ነው:: ሕዝብ መሠረተ-ልማት ነው እየጠየቀ ያለው:: በሰላም ወጥቼ የምገባበት ሰላማዊ ሁኔታ ይኑር እያለ ነው ያለው ሕዝባችን:: ችግሩ፣ ሕዝብ የሚጠይቀው ሌላ ሕወሓትና ብአዴን የሚሰጡት መፍትሔ ሌላ መሆኑ ነው:: እነኝህ ያረጡ የፖለቲካ ድርጅቶች ለስሙ “ጥልቅ ተሐድሶ” አድርገናል እያሉ ለማደናገር ቢሞክሩም በምንም ዓይነት መልኩ የመታደስ ምልክት አይታይባቸውም:: ስለሆነም ወደ ሚቀጥለው ገፅ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ሐሳብ 13

ቁጥር 007

ኢትዮጵያ እና የቦትስዋና ፈለግ



ሹር ጉፕታ ስለ ቦትስዋና ተናግሮ አይጠግብም:: አገሩ ደቡብ አፍሪካ “የቦትስዋና ፈለግ” ብሎ የሚጠራውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንድትከተል አጥብቆ የሚከራከረው ጉፕታ፣ ቦትስዋና ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች እየተገኘ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርቧል:: በርዕሰ-ጉዳዩ ላይ መጽሐፍም እያዘጋጀ ነው:: ግን ለምን ቦትስዋና? የቦትስዋና ፈለግስ እንደምን ያለ ነው? የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ (SADC) መቀመጫ የሆነቸው ቦትስዋና በአህጉራችን ከሚገኙት በጣት የሚቆጠሩ ዲሞክራሲያዊ አገሮች ውስጥ አንዷ ናት:: እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1966 ከብሪታኒያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣች ወዲህ [በቅርቡ ወደ ሥልጣን የመጡትን ጨምሮ] አምስት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ ፕሬዚዳንቶችን አይታለች:: ቦትስዋና አነስተኛ የቆዳ ስፋት ያላት፣ ወደብ አልባ የሆነችና እዚህ ግባ የሚባል ወታደራዊ አቅም የሌላት አገር ብትሆንም፣ በቀጠናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የምታራምደው አቋምና የምታሳርፈው ተጽዕኖ ከብዙዎቹ ትልልቅ የሚባሉ የአፍሪካ አገሮች በእጅጉ የላቀ ነው:: የአገሪቱ “ገር ኀይል” (soft-power) ከውስጣዊ ሰላሟና ከገነባችው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይመነጫል:: የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ መርሆዎች መከባበርና ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች መከበርና የሕግ የበላይነት፣ እንዲሁም ቀጠናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ሰላም ሲሆኑ፣ ያዳበረችው የዲሞክራሲ ዕሴትና የገነባችው ኢኮኖሚ በቀጠናው የምትጫወተውን ሚና ከፍ አድርጎላታል:: እነዚህን መርሆዎች መሠረት በማድረግ የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያካሂዱ፣ የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያ መብቶች እንዲያክሩ እና ለሕግ የበላይነት እንዲገዙ ግፊት ታደርጋለች:: የአካባቢው አገሮች ኢዲሞክራሲያዊ እርምጃዎችን ሲወስዱና የዜጎቻቸውን ሰብአዊ መብቶች ሲጥሱ የቦትስዋና መሪዎች እርምጃውን በድፍረት በአደባባይ በመተቸትና በማውገዝ ይታወቃሉ:: የቦትስዋና መሪዎች አካሄድ እንደ ሮበርት ሙጋቤ ላሉ የአካባቢው ፈለጫ ቆራጭ መሪዎች የማይመች ቢሆንም ዲሞክራሲ በቀጠናው ስር እንዲሰድ ግን ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ነው:: ጉፕታ “የቦትስዋና ፈለግ” የሚለው ይህንን የደቡብ አፍሪካዊቷን አገር የውጭ ግንኙነት ዘይቤ ነው:: ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት እና ይህን ውስጣዊ አቅም ተጠቅሞ በቀጠናው አገሮች ላይ በጎ ተጽዕኖ ማሳረፍ::

“ድንበር አያስፈልግም” ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ፣ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መሀከል ሰላምና ትብብር ሊኖር እንደሚገባ ብቻ ሳይሆን፣ የቀጠናው አገሮች በመሀከላቸው ያለውን ድንበር አስወግደው በሒደት ሊዋሐዱ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምቷል:: በእርግጥ ከዚህ ቀደምም እንደ ተስፋ ጽዮን መድኀኔና ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ ያሉ ምሁራን የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በኮንፌደሬሽን ወይም በፌደሬሽን መልክ ስለሚተሳሰሩበት መንገድ አበክረው ሲናገሩና ሲጽፉ ቆይተዋል:: በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተያየት

እንደማይስማሙ የሚገልጹት ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ በበኩላቸው “በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መሀከል ድንበር አያስፈልግም የሚለው ሐሳባዊነት (idealism) የሚጫነው አስተያየት ነው፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መነሻ በጎ ቢሆንም አስተያየታቸውና ፍላጎታቸው ከነባራዊው የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ በእጅጉ የራቀ ነው፤” በማለት ይከራከራሉ:: “እንዲያውም፣ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መሀከል ሰላም እንዲሰፍን ካስፈለገ፣ ሊወሰድ የሚገባው ተቀዳሚ እርምጃ ተጎራባች አገሮች የሚቀበሉትና የሚያከብሩት ድንበር እንዲኖር ማድረግ ነው:: እንኳን ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት በሌላቸው የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ይቅርና በአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች መሀከልም ጠንካራ ድንበር አለ:: ስለሆነም የድንበር አጥር አያስፈልገንም፣ መዋሐድ አለብን ወዘተ. እየተባለ የሚቀርበው አስተያየት የቀጠናውንም ሆነ የዓለምን ሁኔታ ያላገናዘበ ሐሳባዊነት የሚጫነው አስተያየት በመሆኑ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ቀማሪዎች በደንብ ሊፈትሹት ይገባል፤” ይላሉ ዶ//ር ብርሃኑ::

ተቋማዊ ባሕርይ የለውም፤ በግለሰቦች ስሜና ይሁንታ ላይ የተንጠለጠለ ነው::

ድንበር አያስፈልግም ከመባሉና የቀጠናው አገሮች በኮንፌደሬሽን ወይም በፌደሬሽን መልክ ይተሳሰሩ የሚል አስተያየት ከመቅረቡ በፊት ሊከወኑ የሚገባቸው በርካታ ተግባራት አሉ:: ከሁሉ አስቀድሞ እያንዳንዱ የአፍሪካ ቀንድ አገር ዘመናዊ አገረ-መንግሥት (modern state) እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይጠበቅበታል:: ጉራማይሌ የሆነ የአገረ-መንግሥት ቁመና ባላቸው አገሮች መሀከል የሚደረግ ኅብረት ከንቱ ነው፤ የጋራ ዲሞክራሲያዊ ዕሴት በሌላቸው አገሮች መሀከል የሚደረግ ትስስርም የእምቧይ ካብ ነው::

“የአፍሪካ ቀንድ አገሮች መጀመሪያ ውስጣቸውን ያጽዱ፣ ዘመናዊ አገረ-መንግሥትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገንቡ፣ ቅድሚያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያቸው ከመሪዎችና መሪ ድርጅቶች ጠባብ ፍላጎት ወጥቶ ተቋማዊ መሠረት ይኑረው፤” ሲል ይከራከራል የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ጉፕታ::

ለመተባበር መከባበር በአፈና ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ አገሮች የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሚቀመረው በመስኩ የትምህርት ዝግጅትና ተሞክሮ ባላቸው ባለሙያዎች ሳይሆን በገዥዎች በመሆኑ፣

በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መሀከል ትልቅ እንቅፋት ፈጥረው ከቆዩት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ችግር ይህ ነው:: ቀጠናው ከትናንት እስከዛሬ የፈላጭ ቆራጮች መፈንጫ በመሆኑ የአገሮች ግንኙነትም ከመሪዎች ስሜትና ፍላጎት ጋር የሚለዋወጥ ሆኖ ቆይቷል:: የየአገራቱ መሪዎችና ገዥ ፓርቲዎች ናቸው ግንኙነቱን በፈለጉት መልኩ የሚዘውሩት:: የመሪዎችና የገዥ ፓርቲዎች ግንኙነት ነው የየአገራቱ ግንኙነት ተደርጎ የሚቆጠር:: በቀጠናው አንዱ በሌላው የውስጥ ጉዳይ እየገባ ማሴር፣ አንዱ የሌላውን ተቃዋሚ አቅፎ ደግፎ ሌላውን ማድማት የተለመደ ነው:: መከባበር ብሎ ነገር የለም፤ በአገሮች መሀከል የጋራ እሴት መገንባትና ስትራቴጂክ ወዳጅነት መመሥረት እንደ ቁም-ነገር ተወስዶ አልተሠራበትም:: በመሠረታዊነት መቀየርና መሻሻል ያለበት ይህ ነው::

የኢትዮጵያ ውለታ በመዲናችን አዲስ አበባ፣ በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ነን:: ጉፕታ ስለቦትስዋና ፈለግ በስሜት እየተወራጨ ያወራል፤ ምሳሌ እየጠቀሰ ያስረዳል:: ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ቦትስዋና ልትሆን እንደምትችልና እንደሚገባ ይሞግታል:: “ኢትዮጵያ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት ካላት፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ከቻለች ለቀጠናው ትልቅ ብስራት

ነው፤ የአፍሪካ ቀንድ ብቻ ሳይሆን የምሥራቅ አፍሪካም የስበት ማዕከል መሆን ትችላለችና፤” ይላል ጉፕታ:: በእርግጥም፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ትልቅ ውለታ ልተውል የምትችለው የሰላምና መረጋጋት ደሴትና ዲሞክራሲያዊት አገር የሆነች እንደሆነ ነው:: ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ብዙ የቤት ሥራ ይጠብቃታል:: ያለ ጥርጥር ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ቁመና በምንም ዓይነት መልኩ ምሳሌ ልትሆን አትችልም:: ለሌሎች የቀጠናው አገሮች አብነት ልትሆን ትችላለች የምንላት ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ ችግር ላይ መሆኗን መገንዘብና በውስጣዊ ጉዳያችን ላይ ማተኮር ያስፈልጋል:: በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኀይሎች መሀከል የሚታየው የተካረረ (አንዳንዴም የማይታረቅ የሚመስል) ልዩነት መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል:: አሁንም በአገራችን በየአካባቢው ዘውጋዊ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች እየተከሰቱ በርካታ ዜጎች እየተፈናቀሉና እየተገደሉ ይገኛሉ:: ኢትዮጵያ ለቀጠናው አገሮች ምሳሌ መሆን ካለባት ይህን አደገኛ ሁኔታ መሻገር ይኖርባታል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩና የመንግሥታቸው ተግባር መሆን ያለበት ይህ ነው:: ቅድሚያ ቤታቸውን ማጽዳት፤ ዘመናዊ አገረ-መንግሥት መገንባት፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያሳትፍ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት:: ያኔ ነው የኢትዮጵያ ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ከፍ እያለ ሊመጣ የሚችለው:: እንዲያ ሲሆን ነው ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽዖ ማድረግ የምትችለው:: ብሔራዊ መግባባት ሲፈጠር፣ ዲሞክራሲ ሥር እየሰደደ ሲሄድ እና የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ሲከበሩ የአገሪቱ “ገር-ኀይል” እየጨመረ በአካባቢው የምታሳድረው በጎ ተጽዕኖም ከፍ እያለ ይመጣል::

14 ሐሳብ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ኢትዮጵያን እንሥራት፤ እንኑርባትም! ሰዒድ ኑሩ



ትዮጵያችን ከዚህ በኋላ የአንድ ቡድንም ይሁን የአንድ ሕዝብ የበላይነት የነገሠበት የአፈና አገዛዝ የመሸከም አቅሙ የላትም:: መድኀናችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ ከዴሞክራሲም ሁሉንም ሕዝቦች አካታችና አሳታፊ የሆነው (consociational democracy) ዓይነት ዴሞክራሲ ነው:: በዘውጋዊ ማንነታቸው የተደራጁትም ይሁን በዜግነት ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊነትን እንከተላለን የሚሉት የፖለቲካ ኀይሎች ሁሉ በነጻነት የሚሳተፉበትና ሁሉም እንደየአቅማቸው የሚሳተፉበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሲገነባ ብቻ ነው በአገራችን ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው:: አንዳንድ በኦሮሞ ሕዝብ የተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች ከሰሞኑ የሚያራምዱት “የእኛ ተራ ነው” የሚል ከዴሞክራሲ ጋር የሚጋጭ አዝማሚያ ለአገርና ሕዝብ በምንም ዓይነት መንገድ አይበጅም::

ታሪክ፡- የጦርነት አውድማ

አልፎ የግል ባንኮችና ዩኒቨርሲቲዎች በእነኝህ ስያሜዎች ቅርንጫዎቻቸውን እንዲሰይሙ በመደረግ ላይ ነው::

ታሪክ የዘውጌ ብሔርተኞች ዋና የጦርነት አውድማ ነው:: የትኛውም ዘውጌ ብሔርተኛ ታሪክን እሱን በሚያገለግል መልኩ መጻፍ ዓይነተኛ መለያ ባሕርይው ነው ማለት ይቻላል:: ለዚህ ደግሞ በተለይ የውጭ አገራት የሥነ-ሰብዕ፣ ታሪክና ቋንቋ ምሁራን እንዲሁም ሚሲዮናዊያን አስተዋጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው:: ዊሊያም ሀስቲንግስ የተባለው ብሪታኒያዊና ‹ኢስት ኢንዲያ ካምፓኒ› ውስጥ በኀላፊነት ቦታ ላይ ይሠሩ የነበሩ ባልደረቦቹ የቤንጋል ቋንቋን በማሳደግ ለሕንድ ብሔርተኝነት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አድርገዋል:: የኦሮሞ ዘውጌ ብሔርተኝነትም በአውሮፓ ወንጌላዊ ሚሲዮናዊያን እና እንደ ባርቴልስ (Bartels, L.)፣ ሃበርላንድ (Haberlaned Von, E.)፣ ባክስተር (Baxter, P.T.W.)፣ ሆሎኮምብ፣ (Holocomb,B.K.)፣ አስምሮም ለገሠ ወዘተ... ባሉ የሥነ-ሰብዕና የቋንቋ ምሁራን አማካይነት የተፈጠረ ነው::

በየትኛውም አገር ውስጥ በብሔራዊ ታሪክ ላይ አለመግባባቶችና ክርክሮች አሉ:: በየትኛውም አገር ከዋናው ብሔራዊ/አገራዊ የታሪክ አተያይ (interpretation) የሚለዩ የታሪክ ድርሳናትና አተያዮች ይኖራሉ:: ሆኖም አንድ ሁሉም ሕዝቦች የእኛ ታሪክ ነው ብለው የሚቀበሉት ብሔራዊ ታሪክ ከሌለ ጠንካራ አገረ-መንግሥት ሊኖር አይችልም:: ታሪክ የዘውጌ ብሔርተኞች የፖለቲካ መሣሪያ ሲሆን ደግሞ መዘዙ ከሁሉም የከፋ ነው:: አዲስ አበባ የኦሮሞ ርስት ናት የሚለው የአክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች ትርክት የሚያሳየው ዘውግተኮር ታሪክ ምን ያህል አገር እንደሚያጠፋ ነው:: የሕወሓት የበላይነት የሰፈነበትን አገዛዝ ያንኮታኮተው ቄሮ ነው እያሉ ለ27 ዓመታት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያስገኙትን ፍሬ ለአንድ ቡድን አሳልፎ መስጠት ዘውግ-ተኮር እይታ ምን ያህል አእምሮን እንደሚሸብብ ምስክር ነው::

በዚህ የታሪክ አውድ ውስጥ ተወለደው የኦሮሞ ዘውጌ ብሔርተኛ የኢትዮጵያ ታሪክ የሁሉንም ሕዝቦች ታሪክ ያካተተ ብሔራዊ ታሪክ አይደለም ብሎ ሲያበቃ እዚያው በዚያው ራሱን በሚጠቅም መልኩ ልዩ ልዩ ድርሳናትን እያዘጋጀ ታሪክን የፖለቲካ መሣሪያነት ሲገለገልባት ከርሟል:: የትናንቱን ኹነት በዛሬ መነጽር በማየት ተመልሶ ከ1983 ዓ.ም. በፊት በታሪክ ውስጥ ስላልነበረችው “ኦሮሚያ” የተባለች አገር የፈጠራ ታሪክ ያስነብበናል፤ የኦሮሞን የገዳ ሥርዓት የገደሉት አባ ጅፋርን ጨምሮ ከራሱ ከኦሮሞ ሕዝብ የወጡት ባህላዊ መሪዎች (አባ ሞቲዎች) መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ፣ አክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች የሐበሻ ወረራ የፍትሕ ሥርዓታችንን አወደመ ብለው ሳያፍሩ መጻሕፍት ያሳትማሉ፤ የኦሮሞ ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙት አብያተክርስቲያናት የተሠሩት በአባ ገዳዎች መሰብሰቢያ ላይ ስለመሆኑ ይተርኩልናል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮምኛ ስያሜ ያላቸው አካባቢዎች የኦሮሞ እንደነበሩ ይገልጹልናል:: አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን ሰፈሮቿም የኦሮምኛ ስያሜ የነበራቸው ስለመሆኑ የሚያብራራ መጽሐፍ ከመጻፍም

ማነው ኢትዮጵያዊ? የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኀይለማርያም A History Of Nationalism in Ethiopia፡ 1941-2012 በሚል ርዕስ በጻፈው የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ሥራው እንደገለጸው በማርክሳዊ አስተሳሰብ የተቃኘው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ የሚመራበት ርዕዮተዓለም በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አመለካከት ውስጥ በመደባዊና አውራጃዊ ወይም በአውራጃዊና ብሔራዊ ጭቆናዎች፤ በጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰቦች፣ በደቡብና በሰሜን ንፍቀ አገራት፣ በባህላዊ ራስ-ገዝነትና በፖለቲካዊ መገንጠል ወዘተ. የተፈረጁ ተቃርኖዎችን ያለቅጥ በማጋነን ትልቅ ጥፋት አድርሷል:: ማነው ኢትዮጵያዊው? የሚለው ውስጠ ወይራ ጥያቄ የአፍለኛው ምሁር የትግል አጀንዳ ሆኖ ብቅ ያለውም በዚህ ግርግር ውስጥ ነበር:: ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳብራራው ይህንን ብዥታና ወላዋይነት ተጣብተው የተፈለፈሉት ጥገኛ አስተሳሰቦች ቀስ በቀስ የብሔረሰቦችን ጥያቄ በማጉላት ገዥ መርህ ሆኖ እንዲወጣ ለማድረግ ቻሉ:: ገና የኢትዮጵያ አብዮት ከመፈንዳቱ ቀደም

ብሎ በየአውራጃው በሕዝብ ስም የተቋቋሙ ልዩ ልዩ የባህልና የመረዳጃ ማኅበሮችን በመጠለል ሲንቀሳቀሱ የቆዩት የብሔረሰብ ፖለቲካ አቀንቃኝ ኀይሎች የአብዮቱን ሒደት መቆጣጠር እንዳልቻሉ በተገነዘቡ ጊዜ ወዲያውኑ እውነተኛ ማንነታቸውን በማጋለጥና እነኘህን ማኅበራት በብሔረሰብ ስም ወደተደራጁ አማጺ ቡድኖች በመቀየር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መዋጋት ቀጠሉ:: ከእነዚህ ውስጥ እንደ አብነት የሚጠቀሰው “ሜጫና ቱለማ” (1955 ዓ.ም.) በኋላ ለተመሠረተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መቀፍቀፊያ በመሆን አገልግሏል:: የኦነግና ሌሎች ዘውጌ ብሔርተኛ ታሪከኞች የዓለም ሁሉ ክፋትና ጥፋት ምንጭ ምኒልክ ነው የሚሉ ትርክቶችን በማድራት፤ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቋንቋና የባህል ማኅበረሰቦች መካከል ያሉ የአብሮነት ታሪኮችን፣ የጋራ ዕሴቶችንና ባህሎችን በመካድ፤ ከብዙ ዐሥርት ዓመታት በፊት የተደረጉ ጦርነቶችን እየተቀሱ በአዲስ መልክ የጭቆናና የሰቆቃ ገድሎችን በመፍጠርና በማጉላት፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኙ ድልድዮችን ሁሉ ለማፍረስ ያልተጓዙበት ርቀት የለም:: ኢትዮጵያ የሁላችንም እንድትሆን የጋራ ዕሴቶችን ከመፍጠርና ከማጉላት ይልቅ በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ግጭትን በሚፈጥሩ አጀንዳዎች ላይ ብዙ ሀብት ፈሰሰ፤ ብዙ ጉልበት ባከነ::

“የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል” በአንዳንድ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን አካባቢ ስለ “ሐበሻ ወረራ” እና ከዚህ ወረራ ነጻ ስለመውጣት ብዙ ተጽፏል፤ ለረዥም ዘመናት ብዙ ተብሏል:: የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና በገዳ አባ ጃራ ይመራ የነበረው የኦሮሞ እስላማዊ ግንባር ዋና ዓላማ “ፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል” ማካሄድና ነጻ የኦሮሚያ ሪፐብሊክን መመሥረት እንደነበርም የሚታወቅ ነው:: እንደነ አሰፋ ጃለተና ሲሳይ ኢብሳ ያሉ የኦሮሞ ምሁራን ኢትዮጵያን “ብቸኛዋ የጥቁር ቅኝ ገዥ” ይሏታል:: መፍትሔው ከኢትዮጵያ የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ መውጣት ነው የሚል ትርክት ለበርካታ ዓመታት ሲራመድ ቆይቷል:: በብዙ አንጃዎች የተከፋፈለው ኦነግ ይህን ነባር ትርክቱን ይቀይር አይቀይር በግልጽ የሚታወቅ

ነገር የለም:: ኦነግ ምንም ይበል ምን የነዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን መያዝ ለረዥም ዘመናት ሲያራምደው የነበረው አጀንዳ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ይበልጥ ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ጥርጥር የለውም:: እንደ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያሉ የኦሮሞ ልጆች በበላይነት የሚመሯት ኢትዮጵያ የኦሮሞ ቅኝ ገዥ ናት ቢሉ የሚሰማቸው የለም:: ስለሆነም አክራሪው ጎራ ኦሮሚያን እገነጥላለሁ (በእነሱ አነጋገር ነጻ እናወጣለን) ነባሩን አቋሙን ቀይሮ ተራው የእኛ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል አጀንዳ ማራመድ የጀመረ ይመስላል::

ዴሞክራሲ ብቻ! በመግቢያዬ እንደገለጽኩት ለኢትዮጵያዊያን መድኅናችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ብቻ ነው:: ከዚህ በኋላ በዚህች አገር የአንድ የፖለቲካ ቡድንም ይሁን የአንድ ሕዝብ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት የሚኖርበት የፖለቲካ ሁኔታ የለም:: ሁሉም አገራችን የፖለቲካ ኀይሎች ይህን መሠረታዊ ሐቅ በሚገባ ተገንዝበው ሁላችንም በእኩልነት የምታስተናገድ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል:: በሚያሳዝን መልኩ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚታየው አካሄድ ከዴሞክራሲ በተጻራሪ ቆመ ነው:: የክልሉ መንግሥት ሁኔታዎችን ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ቢሆንም በክልሉ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ ፈርተውና ተሸማቅቀው እንዲኖሩ ሆኗል ማለት ይቻላል:: እነ ዶ/ር ዐቢይ ይህን አሳፋሪ ሁኔታ እንደሚያስተካክሉት ተስፋችን የሰፋ ነው:: አክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች በሚረጩት የጥላቻ አዋጅ ምክንያት ዜጎች ትልቅ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ:: የአገሬና የሕዝቤ ጉዳይ ይመለከተኛል የምንል ኢትዮጵያዊያን ጠንከር ብለን ለሁላችንም የሚበጀውን ስንናገርና በአክራሪ ዘውጌ ብሔርተኞች ላይ ሂስ ስናቀርብ “የኦሮሞ ጥላቻ” (Oromo phobia) አለብህ ወይም አለብሽ እያሉ ዜጎችን ለማሸማቀቅና ዝም ለማሰኘት ከመሞከር ተቆጥበን፣ ለሁላችንም የምትሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመገንባቱ ላይ እናተኩር:: ብቸኛው መዳኛችን ዴሞክራሲ ብቻ ነው!

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቢዝነስ ኢኮኖሚ 15

ቁጥር 007

የምንከተለውን የኢኮኖሚ ፍልስፍና ከስም በላይ እናውቀዋለን ወይ? ጋር የግል መዋዕለንዋይ ከወለድ መጣኝ ጋር የመንግሥት መዋዕለንዋይ ከመልማት ፍላጎት ጋር ኤክስፖርትና ኢምፖርት ከውጭ ምንዛሪ ግኝት ጋር ተዛምደው የሚጠኑበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዘርፍ ነው:: ድጋፍ በመስጠት የግሉን ታሳትፎ ለማሳደግ የመንግሥትን ተሳትፎ እቀንሳለሁ ከሚል የአቅርቦት ጎን ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለየት ያለና ጥልቅ የባለሙያ ትንታኔ የሚጠይቅ ነው::

ጌታቸው አስፋው የብሔራዊ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ ([email protected])



ከወለድ መጣኝ ጋር አያይዘን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለኢንቬስትመንት የሚበቃ ገንዘብ አልተገኘም በማለት የነጋዴዎች እሮሮና በየመድረኩ ስለሚነሳው ንትርክ ጽንሰ ሐሳባዊ ተንታኔዎች ላይ ተመርኩዞ ለመናገር ኹለቱን የኢኮኖሚ አስተዳደር ፍልስፍናዎች ማለትም የሊበራል ኢኮኖሚን እና በማክሮ ፖሊሲ የተገራ ኢኮኖሚን እናነጻጽር::

ብልጽግና ፓርቲ ከልማታዊ መንግሥት ፍልስፍና አፈግፍጎ ወደ ሊበራል ኢኮኖሚ ፍልስፍና አጋድሏል ይባላል:: የተለያዩ ባለሥልጣናት እና ባለሙያዎች ስለ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሲናገሩም በውስጥም በውጭም እስካሁን ያልተሞከረ አዲስ ዓይነት ለውጥ አስመስለው ያቀርባሉ:: ሆኖም ከሦስቱ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የፖሊሲ ምሶሶዎች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት ማስተካከል መሆኑን ተናግረዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚህ ጉዳይ ላይ አጽንኦት ሰጥተው በሚዲያ አረጋግጠዋል:: ይሁንና ግን የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ሥራ አጥነቱ እንዲሁም የዋጋ ግሽበቱ እየባሰባቸው እንጂ እየተሻሻሉ አለመምጣታቸው በቂ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ አለመደረጉን የሚያመለክቱ ናቸው:: የፕላን ኮሚሽነሯ መጋቢት አምስት ቀን በኑሮና ቢዝነስ ፕሮግራም ላይ ቀርበውም የዐሥር ዓመቱ ዕቅዳችን መሠረት የአቅርቦት ጎን ኢኮኖሚክስ እንጂ የፍላጎት አስተዳደር (Demand Management) ኢኮኖሚክስ አይደለም ብለው ተናገሩ:: ምክንያቱን ሲያስረዱም የኑሮ ደረጃ ዝቅተኛ ስለሆነ ከዚህ በላይ ፍላጎትን ተጭኖ መግታት ትክክል አይደለም አሉ:: ሁልጊዜም በምጽፋቸው ጽሑፎች ለአንባቢ ምን ያህል ግልጽ ነኝ? ቴክኒካዊ የሙያ ዕውቀት አበዛበታለሁ ወይ? ባለሙያ ያልሆነ ሰው እንዴት ይረዳኛል? ምንስ ያደርግለታል? ጽሑፌ በትምህርት ቤት የሚሰጠውን የሙያ ዕውቀት ያህል ረቂቅ ይሆንን? እያልኩ አስባለሁ:: የሙያው ባሕሪይ ሆኖ ከመሠረታዊ ጽንሰ ሐሳቡ ካልተነሱ ተጨባጭ ሁኔታን ለማብራራት ስለሚቸግር ሆኖብኝ ነው:: የፍላጎት አስተዳደር ፖሊሲ ከታላቁ የኢኮኖሚ ጠቢብ ኬንስ አስተምሮ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ የፍላጎት አስተዳደር ፖሊሲ ማለት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማለት ነው:: የጥሬ ገንዘብም (Monetary) ሆነ የበጀት (Fiscal) ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የፍላጎት አስተዳደር ፖሊሲዎች ናቸው:: ዕውቀታችን ጎደሎ የሚሆነው ፍላጎት ፍጆታ ብቻ ሲመስለን ነው:: ለመሆኑ የፍላጎት አስተዳደር ማለት ምን ማለት ነው:: የሊበራል ኢኮኖሚስቶች የገበያ ኢኮኖሚ አመለካከት ምንም እንኳ ለጥቂት ጊዜ ፍላጎትና አቅርቦት እኩል ሳይሆኑ ቀርተው ዋጋዎች በመዋዠቅ የተመረተው ምርትና ለገበያ የቀረበው ሁሉ እንዲሸጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ የገበያ ማጣሪያ ዋጋ (Market Clearing Price) ባይፈጠርም በረጅም ጊዜ ውስጥ ግን ፍላጎትም ሆነ አቅርቦት ከዋጋ ውጣ ውረድ ጋር በመጨመርና በመቀነስ

ተለዋውጠው እኩል በመሆን የረጋ ቋሚ የገበያ ማጣሪያ ዋጋ ይፈጥራሉ ይላሉ:: ይህንን የገበያ ማጣሪያ ዋጋ እንዲፈጠር መሬትና ካፒታል ግብዓተ ምርቶች በነጻ ገበያ በውድድር ሥርዓት መሸጥ አለባቸው የሊበራል ኢኮኖሚክስ ተሟጋቾች እምነት የማይከተለውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስተዳደር ወደ ሊበራል ኢኮኖሚ ያጋደለ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይከብዳል:: ከልማታዊ መንግሥት እለያለሁ የሚልበት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም ከመንግሥት ድርሻ ቆርሼ ለግሉ ኢኮኖሚ እንዲበቃው አደርጋለሁ የሚልበትን ተስፋ ብቻ ነው:: በማክሮ ኢኮኖሚክስ ጥናት የፍላጎት አስተዳደር ማለት በብሔራዊ ኢኮኖሚ ሒሳብ መዝገብ ውስጥ የሚመዘገቡትን ሦስት የወጪ ዓይነቶች፡- የቤተሰቦች የፍጆታ ፍላጎት ወጪዎች፣ የመንግሥታዊና የግል ድርጅቶች የመዋዕለንዋይ ፍላጎት ወጪዎች፣ የመንግሥት መደበኛ ወጪዎች ፍላጎት ድምር አስተዳደር ጥናት ነው የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነትን ካካተትንም ኤክስፖርትና ኢምፖርት አብረው ይተነተናሉ:: ይህም እስከዛሬ ከተጓዝንበት በመንግሥት ድጋፍ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና አገልግሎትን ከማሳደግ ልማታዊ የአቅርቦት ጎን ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች የተለየ ነው:: የፍላጎት አስተዳደር ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በጽንሰ ሐሳብ ትንታኔ ደረጃም “አቅርቦት የራሱን ፍላጎት ይፈጥራል” ከሚለው የክላሲካል ሊበራል ኢኮኖሚስቶች የአቅርቦት ጎን ፍልስፍና የተለየና የማክሮ ኢኮኖሚክስ አባት በሆነው ኬንስ “ወጪ የራሱን ገቢ ይፈጥራል” በሚል የፍላጎት ጎን ፍልስፍና የተገለበጠበት አስተምህሮ ነው:: የኹለቱን ልዩነት በዝርዝር መተንተን ለባለሙያዎች ትቼ ለሕዝብ በሚቀርበው ላይ ላትኩር::

ፍጆታን በመግራት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በኅብረተሰቡ ዘንድ የገቢ መመጣጠን እና አለመመጣጠን በምርት ፍላጎት ላይ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ አውቆ ገቢን ማሳደግ ወይም የገቢ ክፍፍልን ፍትሐዊ ማድረግ ዋናው የሸማቾችን ወጪ መግሪያ መንገድ ነው:: በኢትዮጵያ ከልክ በላይ የሆነ የሀብት ክፍፍል ስላለ የሀብታሙን ገቢ ማሳደግ የውጭ ሸቀጦችን ማበረታታት ሲሆን፣ የድሃውን ገቢ ማሳደግ ግን የውስጥ ሸቀጦች አምራቾችን እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ማበረታታት ነው:: የመንግሥት መዋዕለንዋይ ፍላጎት የሚወሰነው በመሠረተልማት ግንባታና መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፖሊሲው ላይ ተመርኩዞ ሲሆን የመንግሥት መደበኛ ወጪ የሚወሰነው በየመንግሥት አገልግሎት ለሕዝብ ተፈላጊነት መጠን ነው:: የመንግሥት አገልግሎት ለሕዝብ ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መንግሥት ብዙ ሠራተኞችን ይቀጥራል:: ይህ ሲባል ግን መንግሥት የሥራ አጥነትን ለማስወገድ መዋቅሩን አስፍቶ ምርታማ ባልሆነ የሥራ መደብ ሠራተኞችን መቅጠር አለበት ማለት አይደለም::

በወለድ መጣኝ አወሳሰን ላይ ሊበራል ኢኮኖሚስቶች እና ማክሮ ኢኮኖሚስቶች ይለያያሉ:: ሊበራል ኢኮኖሚስቶች ከቁጠባ ጋር በማያያዝ የባንክ ተቀማጭ እንዲያድግ መንግሥት የወለድ መጣኝ ጣሪያን ከመወሰን አንስቶ ማንኛውንም ቁጥጥሩን መተው አለበት ሲሉ፣ ኬንሳውያን ማክሮ ኢኮኖሚስቶች ግን የወለድ መጣኝን ከመዋዕለንዋይ ዕድገት ጋር አዛምደው ይተነትናሉ:: የወለድ መጣኝ ለቆጣቢዎች እና የወለድ መጣኝ ለመዋዕለንዋይ አፍሳሾች ተቃራኒ ጥቅምና ጉዳት አለው ማንንም እንዳይጎዳ ወይም ቆጣቢዎችንም መዋዕለንዋይ አፍሳሾችንም እንዲጠቅም ወይም የገንዘብ ፍላጎትን እና አቅርቦትን እንዲያመጣጥን ተደርጎ እንዴት ሊወሰን ይችላል:: የሊበራሎቹንም ሆነ የማክሮኢኮኖሚስቶቹን ሙግት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አገናዝቦ መተንተንን ይጠይቃል:: በኢትዮጵያ የተቀማጭ ወለድ ቆጣቢዎችን የሚያበረታታ ነውን የብድር ወለድስ መዋዕለንዋይ አፍሳሾችን የሚያበረታታ ነውን? አወሳሰኑስ በፍላጎትና አቅርቦት የዋጋ ሥርዓት ነው ወይስ በመንግሥት ጣሪያና ወለልን በመገደብ? የመንግሥት አካላት ግን የብልጽግና ፓርቲ ከልማታዊ መንግሥት መርህ ወደ ሊበራል ኢኮኖሚ ያጋድላል ከሚሉት ፍልስፍና አንጻርም ሆነ ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው አንድ ምሶሶ ነው ካሉት ጋርም አያይዘው ያሉት ነገር የለም:: ለዚህ ነው የዚህን ጽሑፍ ርዕስ የምንከተለውን የኢኮኖሚ ፍልስፍና ከስም በላይ እናውቀዋለን ወይ ብዬ የሰየምኩት::

የግል ድርጅቶች መዋዕለንዋይ ፍላጎት ግን የሚወሰነው በወለድ መጣኝ ላይ ተመርኩዞ ነው:: ስለዚህም ጠለቅ ያለ የገበያ ትንተና የሚያስፈልገው ነው:: በገበያ ኢኮኖሚ የወለድ መጣኝ የሚወሰነውም በገበያ ውስጥ በተሰራጨው የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ነው:: የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱ ከፍተኛ ሆኖ የወለድ መጣኙ ዝቅተኛ ሲሆን፣ መዋዕለንዋይ ስለሚበረታታ ድርጅቶች በብዛት ለማምረት ተጨማሪ ሠራተኞችን ይቀጥራሉ::

የብልጽግና ፓርቲ ወደ ሊበራል ኢኮኖሚ በማጋደሉ በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የገበያ ኢኮኖሚ ዳብሮ የገበያ ኢኮኖሚ ሰው ባሕሪይን ተላብሰን ፍላጎትና አቅርቦት በራሳቸው ውስጣዊ ሂደት ተመጣጥነው ትክክለኛው የሸቀጦች የገያ ማጣሪያ ዋጋ (Market Clearing Price) በገበያ ውስጥ ተተምኖ ገበያዎቻችን ይስተካከሉ የሚለውን የሊበራል ኢኮኖሚስቶች አመለካከት የሩቅ ጊዜ ውጥን ወደ ጎን ትተን መንግሥት መቼ ነው ገበያውን በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው ገርቶና መርቶ ገበያዎቻችን የሚያስተካክለው ብለን የምንጠይቅበት ጊዜ ላይ ነን::

የፍላጎት አስተዳደር ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ስለዚህም በአብዛኛው ፍጆታ ከገቢ

የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ፍልስፍናም ከአጠቃላዩ ሶስዮ-ፖለቲካል ኢኮኖሚ ወይም ወደ ገፅ 20 ዞሯል

16 ቢዝነስ ኢኮኖሚ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ዴሞክራሲን የማስፈን ንቅናቄ የደቡብ ኮሪያ ተሞክሮ በመንግሥት ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ፀረ ኮሚኒስት ድርጅቶች አደራጀ:: ይህም ቀኝ አክራሪ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓትን ወለደ:: ሌላኛው ወሳኝ ነጥብ፣ በኮሪያ ጦርነት ምክንያት የደቡብ ኮሪያ ኀይሎች ቁጥር ወደ 600,000 መመንደጉ እና በዚህም ምክንያት፣ የመንግሥት አስገዳጅ ኀይል በአሰቃቂ ሁኔታ ማደጉ ነበር:: ከዚህም ባሻገር፣ በኮሪያ ጦርነት አማካይነት በተገኘው ልምድ ሰበብ ፀረ ኮሚኒስትነት በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሰርጿል:: ወዲያውም፣ የኮሪያ ጦርነት ፀረ ኮሚኒስትነትን የአገረ መንግሥቱ ገዢ ርዕዮተ ዓለም አደረገው::

ዳንኤል ክንዴ (ዶ/ር)

(፩) የደቡብ ኮሪያ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የልማት ጎዳና ለአገራችን ከፍተኛ አብነት ያለው ነው:: ለመሆኑ የደቡብ ኮሪያ የዝመና ጎዳና እንደምን ያለ ነው? እኛስ ከዚያች አገር ተሞክሮ ምን እንማራለን? በሚቀጥሉት የሲራራ ጋዜጣ ተከታታይ እትሞች ስለዚያች አገር ያለኝን ግንዛቤ ለማካፈል እሞክራለሁ:: 1.

ለደቡብ ኮሪያ የዴሞክራሲ ዕድገት ያገዙ ታሪካዊ ሁኔታዎች

የአሁኗ ደቡብ ኮሪያ ታሪክ፣ አገሪቱ በ1945 ከጃፓን ቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2008 ድረስ ከስድሳ ዓመት ትንሽ አለፍ ያለ ነው:: በዚህ አጭር ጊዜ ደቡብ ኮሪያ ድኅረ ቅኝ አገዛዝ ነጻ መንግሥት መመሥረት፣ ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት ማምጣትንና ጨቋኝ ሥርዓተ መንግሥትን ወደ ዴሞክራሲያዊ መንግሥትነት መለወጥን የመሳሰሉ ዐበይት ግቦችን አሳክታለች:: እነዚህን ስኬቶች ስናገናዝብ፣ ይህ ዘመን የዘመናዊነት ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተተገበሩበት የእምቅ ዘመናዊነት (compressed modernisation) ዘመን ነው:: የዚህ እምቅ ዘመናዊነት ውጤቶች በጣም ፍሬያማ ነበሩ:: ሆኖም፣ በቀዝቃዛው ጦርነት መነሻ ላይ በተካሄደው የሥርዓተ መንግሥት ምሥረታው ሂደት ኮሪያ ተከፋፍላለች፤ እስካሁንም መልሳ አልተዋሐደችም:: የበይነ-ኮሪያ ዳግም ውሕደት አሁንም ቢሆን በደቡብ ኮሪያ የዘመናዊነት ሂደቱ አንድ ተግባር ሆኖ ቀርቷል:: ዘመናዊነትን ዘግይተው ከጀመሩ አያሌ የሦስተኛው ዓለም አገሮች አንጻር የደቡብ ኮሪያ ስኬት ብርቅ ነው:: የዚህ ጽሑፍ ርእሰ ጉዳይ የሆነው፣ የደቡብ ኮሪያዊያን ዴሞክራሲ ታሪክ፣ ከእምቅ ዘመናዊነት ታሪክ ጋር አቻነት አለው:: ምክንያቱም የደቡብ ኮሪያ ዴሞክራሲ የተጀመረው፣ አገሪቱ ከጃፓን ቅኝ አገዛዝ በ9145 ነጻ ስትወጣ ቢሆንም፣ ጉልህ ዕድገት ግን አላሳየም ነበር:: ዛሬ፣ ዴሞክራሲ የትኛውም የሦስተኛው ዓለም አገር ውስጥ ከሚሠራው በላይ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ስኬታማ ሆኖ ይሠራል:: የደቡብ ኮሪያ ዴሞክራሲ ታላላቅ ስኬቶች ቢኖሩትም፣ ታሪካዊ ሁኔታዎቹ ሲታዩ ግን መነሻው ላይ የተደላደሉ አልነበሩም:: ይልቁንም፣ በዘመናዊት ኮሪያ ታሪክ ውስጥ ተመሥርቶ በነበረው “ጠንካራ መንግሥት” መኖር ምክንያት ሁኔታዎቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነበሩ:: በመጀመሪያ፣ ብርቱ አስገዳጅ ኀይል ከነበረውና በድኅረ ቅኝ አገዛዝ ኮሪያ በጠንካራው ቅኝ አገዛዛዊ ሥርዓት መሠረት ላይ ከተቋቋመው የፀረ ኮሚኒስት መንግሥት ውስጥ የፈለቀ ነበር:: በብሔራዊ ነጻነታቸው ማግሥት ቀዝቃዛው ጦርነት ሲካረር፣ በድኅረ ነጻነት ዘመናቸውና በተከተለው የኮሪያ ጦርነት ወቅት ኮሪያዊያን በግራ እና በቀኝ ዘመምነት መሃል ርዕዮተ ዓለማዊና ፖለቲካዊ ግጭቶች ውስጥ ገብተው ነበር:: እነዚህ አጋጣሚዎች ጠንካራ ፀረ ኮሚኒስት መንግሥት ደቡብ ኮሪያ ውስጥ በቀላሉ ሥር የሚይዝበትን ሁኔታ ፈጥረዋል:: ጠንካራውን መንግሥት ይበልጥ ያጠናከረው ደግሞ ፀረ ኮሚኒስቱ መንግሥት በአምባገነን ሥርዓቶች ሥር በዋለው ልማታዊ መንግሥት መተካቱ ነው:: ይህም የታመቀ ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስተዋወቅ ወደ የከፋ ጉልበተኝነትና መንግሥታዊ ፉክክር አመራ:: ከኮሪያ ጦርነት በኋላ በአምባገነን መንግሥታት ሥር የነበረው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የተገነባው በጠንካራ ሥርዓተ መንግሥት መሠረት ላይ በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ ይችል ነበር:: ይኹንና ፈላጭ ቆራጩ ሥርዓት ተቃዋሚዎች ዴሞክራሲን የማስፈኑን ሂደት እንዲቀላቀሉ አድርጓቸዋል:: አገዛዛቸው በበረታ እና በተራዘመ መጠን ዴሞክራሲን የማስፈን ንቅናቄውም እኩል ይስፋፋ ነበር:: በተጨማሪም፣ ከስኬታማው ‹ኢንዱስትሪያላይዜሽን› የመነጩት ጉልህ ማኅበራዊ ለውጦች የዴሞክራሲን ጥያቄዎች

አጠናከሩ:: በውጤቱም፣ በአምባገነኖቹ ሥርዓቶች ጨቋኝ አገዛዝና በ‹ዴሞክራታይዜሽን› ንቅናቄው ተቃውሞ መሃል የነበሩ ቅራኔዎች ቀጥለው፣ ቅራኔዎቹ በኹለቱም ወገኖች መሃል ተደጋጋሚ፣ ሰፋፊ ግጭቶችን አስከተሉ:: የ1960ው “የሚያዚያ አብዮት”፣ የ1980ው “የግዋንጁ ሕዝባዊ አመጽ” እና የ1987ቱ “የሰኔ ዴሞክራሲያዊ አመጽ” በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ አጋጣሚዎች ናቸው:: በስተመጨረሻ፣ የሰኔው ዴሞክራሲያዊ አመጽ አምባገነኑን ሥርዓት ቋጭቶ፣ ለ‹ዴሞክራታይዜሽን› መንገድ ጠረገ:: በዚህ ምክንያት፣ የደቡብ ኮሪያ ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ በንቅናቄ (በንቅናቄ የተገኘ ዴሞክራሲ) ተብሎ ሊጠራ ይችላል:: ቢያንስ ወደ 1987ቱ የዴሞክራሲ ሽግግር መዳረሻ የነበረውን ጊዜ ከግምት በማስገባት:: 2.

በአምባገነን አገዛዝ ሥር የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

የደቡብ ኮሪያ ዴሞክራሲ ከ1987 ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ቀድሞ “ዴሞክራሲ በንቅናቄ” ከነበረ፣ ዴሞክራሲን የማስፈን ንቅናቄው (ከዚህ በኋላ ንቅናቄ) እንዴት በተጨባጭ ተገለጠ? እንደሚከተለው በሦስት ሥፍረ ዘመናት ሊከፈል ይችላል፡የመጀመሪያው ሥፍረ ዘመን ከብሔራዊው መከፋፈል እና ከኮሪያ ጦርነት እስከ የ1960ው 19ኛው አብዮት ድረስ ሲሆን፣ ይኸውም ‹ኢ ሲንግ ማን› ፀረ ኮሚኒስት አምባገነን ሥርዓት ላይ የተካሄደው ንቅናቄ በይፋ መታየት የጀመረበት ጊዜ ነው:: ኹለተኛው ሥፍረ ዘመን በ1961 ከተካሄደው የግንቦት 16 መፈንቅለ መንግሥት እስከ 1980ው የሴዑል ጸደይ ድረስ ያለው ሲሆን፣ ይህም ንቅናቄው የ‹ፓርክ ቹንግ ሂን› ልማታዊ አምባገነናዊ ሥርዓት በመቃወም፣ ይበልጥ የጎለበተበት እና የተስፋፋበት ጊዜ ነው:: ሦስተኛው ሥፍረ ጊዜ በቹን ዱ ህዋን አዲሶቹ ወታደራዊ ኀይሎች በታኅሣሥ 12 እና በግንቦት 17 ከታወጀው መፈንቅለ መንግሥት በ1987 እስከተካሄደው የሰኔ ዴሞክራሲያዊ አመጽ ድረስ ያለው ሲሆን፣ ይኸውም ንቅናቄው እጅግ ከማየሉ የተነሳ ጨቋኙ ሥርዓት በሰኔው ዴሞክራሲያዊ አመጽ አማካይነት ዴሞክራሲያዊ የሆነበት ጊዜ ነው:: 2.1 ንቅናቄ በ‹ኢ ሲንግ ማን› ዘመነ መንግሥት በ‹ኢ ሲንግ ማን› ዘመነ መንግሥት ንቅናቄው ጭቆናን በመቃወም እንዴት እንዳቆጠቆጠ ለመረዳት፣ በድኅረ ነጻነት (ነሐሴ 1945-ነሐሴ 1948) እና በኮሪያ ጦርነት ጊዜ (ሰኔ 1950 - ሐምሌ 1953) የነበሩትን ርዕዮተ ዓለማዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች መመርመር ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም እነዚያ ነባር ታሪካዊ ሁኔታዎች በደቡብ ኮሪያ ጽንፈኛ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓት እንዲመሠረት አስተዋጽዖ አድርገዋል:: ጃፓኖች በነሐሴ 1945 እጅ ከሰጡ በኋላ፣ ነጻ የወጣችው ኮሪያ አዲስ ነጻ አገረ መንግሥት በመገንባት ሕልም ተነቃቅታ ነበር:: በመሆኑም፣ በድኅረ ነጻነቱ ዘመን፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች አዲሲቱን አገር በመገንባቱ ንቅናቄ ውስጥ ተሳትፈዋል:: በዚያው

ጊዜ ግን፣ የአገር ግንባታው በአገር በቀል የፖለቲካ ቡድኖች መሃል ኀይለኛ ግጭቶችን አስነስቶም ነበር:: (በገበሬዎች እና በወዛደሮች የሚደገፉት) ግራ ክንፈኞቹም ሆኑ፣ (በአፍቃሬ ጃፓን ኮሪያዊያን የሚደገፉት) ፀረ ኮሚኒስት ቀኝ ክንፈኞች አዲሷን ኮሪያ በየራሳቸው መንገድ መመሥረት ነበር የሚያስቡት:: በደቡቡ የአሜሪካ ወታደራዊ መንግሥት፣ በሰሜን ደግሞ የሩሲያ ወታደራዊ መንግሥት መኖራቸው ይህንን ግጭት አባብሶታል:: በድኅረ ነጻነት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ውስጥ ግራ ዘመሞቹ ፋና ወጊ የአገረ መንግሥት ግንባታ ጥረቶች ማድረግ ጀመሩ:: በመጀመሪያ፣ የኮሪያዊያን ነጻነት የዝግጅት ኮሚቴ አቋቋሙ፤ ከዚያ ቀጥለው በችኮላ የኮሪያ ሕዝባዊ ሪፐብሊክን መሠረቱ:: በውጤቱም ሕዝባዊ ኮሚቴዎቹ ከነጻነት በኋላ ባሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በደቡብ ኮሪያ ባሉ ከተሞችና አገር ግዛቶች ሁሉ ተደራጁ:: ያም ሆኖ፣ ግራ ክንፈኞቹ ገና በለጋው የጥንቃቄ ተግባራትን ቢፈፅሙም፣ የአሜሪካ ወራሪዎች በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ቅልበሳ አካሂደው፣ በመጨረሻ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ፀረ ኮሚኒስት መንግሥት አቆሙ:: የአሜሪካ ወራሪ መንግሥት፣ ከወግ አጥባቂዎቹ ጋር በማበር፣ የፖሊስ ኀይሎችን ጨምሮ የአገሪቱን አስገዳጅ ኀይል በመጠቀም የግራ ክንፈኞቹን የአገረ መንግሥት ግንባታ ዕቅድ ማፈራረስ ችሎ ነበር:: በዚህ አኳኋን፣ የኮሪያ ሪፐብሊክ በነሐሴ 1948 ተመሠረተ:: ከዚህ አንጻር፣ በደቡብ ኮሪያ በ1948 ያቆጠቆጠው ፀረ ኮሚኒስት መንግሥት፣ የአሜሪካ የቀዝቃዛው ጦርነት የፀረ ኮሚኒዝም ፍላጎቶች የተሟሉበት ድቅል መንግሥት ነው:: ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ፣ ቀዝቃዛው ጦርነት በፍጥነት እየተፋፋመ ሲመጣ፣ አሜሪካ በምሥራቅ እስያው የቀዝቃዛው ጦርነት ግንባር ላይ በሚገኘው በኮሪያ ልሳነ ምድር ጠንካራ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓት ለመዘርጋት ፈለገች:: ጥረቶቿም በአሜሪካ ወራሪ ኀይሎች ዕቅድ መሠረት ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ጠንካራ ፀረ ኮሚኒስት መንግሥት ለማቋቋም አበቃት:: ሆኖም፣ አሜሪካ በጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶች የተነሳ በዚያው ደቡቡ ኮሪያ ውስጥ የሊብራል ዴሞክራሲ ተቋማትን የመመሥረት ፍላጎት ነበራት:: የኮሪያ ልሳነ ምድር፣ በምሥራቅ እስያ የነበሩ የቀዝቃዛው ጦርነት ፍጥጫዎችን የሚወክል ሥፍራ በመሆኑ፣ ደቡቧ ቢያንስ ከሰሜኗ ኮሚኒስት ሥርዓት የሚቃረኑ አንዳንድ የሊብራል ዴሞክራሲ መገለጫዎችን ማሳየት ነበረባት:: በድምሩ፣ አሜሪካ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ጠንካራ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓትና የሊብራል ዴሞክራሲ ተቋማትን የመገንባት ሐሳብ ነበራት:: እርግጥ ነው፣ የመጀመሪያው ዓላማ፣ ከኹለተኛው ይልቅ በጣም ወሳኝ ነበር:: ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓት ደቡብ ኮሪያ ውስጥ በደንብ መልክ የያዘው በኮሪያ ጦርነት ወቅት አካባቢ ነበር:: በመጀመሪያ ከደቡብ ኮሪያ መንግሥት በዓለ ሲመት በኋላ፣ የኢ ሲንግ ማን መንግሥት መሃል ሰፋሪ ብሔርተኞችንና የግራ ክንፍ ኀይሎችን ጭምር አስወግዶ፣ በተለያዩ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ውስጥ

በጥቅሉ፣ በደቡብ ኮሪያ ከድኅረ ነጻነት ግጭቶች እና ግጭቶቹን ተከትሎ ከመጣው የኮሪያ ጦርነት የመነጨ ጽንፈኛ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓት ሰፍኖ ነበር:: በዚህ ሥርዓት ፀረ ኮሚኒስቱ መንግሥት ግዙፍ አስገዳጅ ኀይል ሲገነባ፣ ሲቪል ማኅበረሰቡ ግን በመንግሥት ወድሟል፣ ተዳክሟል፣ ከዚያም አልፎ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ወድቋል:: በሁሉም የማኅበረሰቡ መስኮች ዘንድ ፀረ ኮሚኒዝም “አስተኔ የጋራ መግባባት” (pseudo-consensus) በፈጠረበት ሁኔታ ውስጥ፣ ማኅበረሰቡም “መንግሥት ያደራጀው ፀረ ኮሚኒስት ማኅበረሰብ” ሆኗል:: በእርግጥም፣ ደቡብ ኮሪያ በሊብራል ዴሞክራሲያዊ ተቋማት የተደራጀች ብትሆንም፣ ተቋማቱ ግን ገና በተግባር ያልታዩና በፀረ ኮሚኒስቱ ሥርዓት ገደቦች ሥር የሚሠሩ ነበሩ:: በአጭሩ፣ በ1950ዎቹ የታየው የኢ ሲንግ ማን አምባገነንነት በጽንፈኛ ፀረ ኮሚኒስት ሥርዓት እና መንግሥት ባደራጀው ፀረ ኮሚኒስት ማኅበረሰብ ላይ የተመሠረተ ነበር:: ፀረ ኮሚኒስት አምባገነንነት ተብሎ ሊጠራ ይችላል:: ይኸው ኮሚኒስት አምባገነንነት ኀይሉን ማጣት የጀመረው “የተመረጠ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አዋጅ” (1952) እና “የማሟያ ማሻሻያ” (1954) ተብዬዎቹን አዋጆቹን የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ሊጠቀምባቸው ሲሞክር ነበር:: ምክንያቱም የ‹ኢ› አምባገነንነትና የተራዘመ አገዛዝ ፍላጎቱ በሊብራል ዴሞክራሲ እሴቶችና ተቋማት ላይ የተመሠረተ ትችትና ተቃውሞ ከበታቾች ስለገጠመው ነው:: በ1950ዎቹ አጋማሽ፣ ይህን የአምባገነንነት አካሄድ ለመግታት አዳዲስ ዴሞክራሲያዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተመሠረቱ:: በመጀመሪያ፣ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መስከረም 1955 ተቋቋመ:: ፓርቲው ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ድርጅት ቢሆንም፣ በአምባገነኑ አገዛዝ ላይ ያለውን ተቃውሞ ግን በማያሻማ መንገድ ይገልፅ ነበር:: ከዴሞክራቲክ ፓርቲው በተጨማሪ፣ ተራማጅ ቡድኖች ተራማጅ ፓርቲ ለመመሥረት ጥረት አደረጉ:: በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ ከታዩት ከእነዚህ ለውጦች ጎን ለጎን፣ ሕዝቡም በኢ የረጅም ዘመን አገዛዝ መንገፍገፍ ጀምሮ ነበር፤ ይህም በግንቦት 1956 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ በግልጽ ታይቷል:: በዚህ ምርጫ፣ የ‹ኢ ሲንግ ማን› ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው እጩ (‹ቦንግ አም›) ከተጠበቀው እጅግ የላቀ የምርጫ ድምፅ አሸንፏል:: ይኹን እንጂ የ‹ኢ ሲንግ ማን›ን መንግሥት ከሥልጣን ያስወገዱት የምርጫውን መጭበርበር በመቃወም ደቡብ ኮሪያዊያን ያደረጓቸው ሰላማዊ ሰልፎች እንጂ ዴሞክራሲያዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አልነበሩም:: መጋቢት 1960 በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ፣ በመላው አገሪቱ ሁሉም ዓይነት የምርጫ ማጭበርበር በመፈፀሙ፤ በኮሌጅ ተማሪዎች አነሳሽነት የተጀመሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ወደ መላ አገሪቱ ተስፋፍተው ፕሬዚዳንቱ ሥልጣኑን እንዲለቅ አስገድደውታል:: እነዚህ ንቅናቄዎች የፈጠሩት አመጽ የሚያዝያ 19 አብዮት በመባል ይታወቃል:: ለአምባገነናዊው አገዛዝ መንኮታኮት መንሥኤዎች ከዴሞክራሲያዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ይልቅ፣ በዘመኑ ሲቪል ማኅበረሰቦች ላይ የተከሰቱት ለውጦች ነበሩ:: በ1950ዎቹ አካባቢ በደቡብ ኮሪያ ሲቪል ማኅበረሰብ ላይ ምን ዓይነት ለውጦች ተከሰቱ? እነዚህስ ለውጦች እንዴት የሚያዝያ 19 አብዮትን አስከተሉ? ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ ጦርነት ማግሥት ባጋጠማት ድንገተኛ ከተሜነት ምክንያት ጥልቅ ማኅበራዊ ለውጦችን አካሂዳለች:: በጦርነቱ ጊዜ ቤቶቻቸውንና ሥራዎቻቸውን ያጡ አያሌ ሰዎች ወደ ከተሞች፣ በተለይም ወደ ሴዑል መጥተዋል:: ወደ ገፅ 20 ዞሯል

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቢዝነስ ኢኮኖሚ 17

ቁጥር 007

ጃኖ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጅ ባንክ 1.ጃኖ ባንክ በምሥረታ ላይ ያለ የኢንቨስትመንት ባንክ ጃኖ ባንክ አክሲን ማኅበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪና ደንብን በማሟላት የአክሲዮን ሽያጭ የጀመረ ሲሆን፤ በምሁራን፣ በንግድ ሥራ በተሰማሩ ታዋቂ ነጋዴዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ኢኮኖሚስቶች፣ በኢኮኖሚ ልማት አማካሪዎች እና ረጅም ልምድ ባላቸው የባንክና የቴክኖሎጅ ባለሙያዎች አስተባባሪነት በመቋቋም ላይ የሚገኝ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጅ ባንክ ነው:: ጃኖ ባንክ በ1960 በወጣው የንግድ ሕግ፣ የባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2008 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SB-B/56/2013 መሠረት በምሥረታ ላይ የሚገኝ ባንክ ነው::

2. ባንኩን ለመመሥረት ያስፈለገበት ምክንያት የተለያዩ የሴክተሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአገራችን የሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ማኅበረሰቡ በቂ የባንክ አገልግሎት እንደማያገኝ ያመለክታሉ:: በ2012 ዓ.ም. በአገራችን የሚገኙ የባንኮች መጠን 17 ሲሆን፣ ጠቅላላ የቅርንጫፎቻቸው ብዛት ከ6000 በላይ ነው:: በመሆኑም እነዚህ ባንኮች እና 6000 ቅርንጫፎች ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ለሆነ ሕዝብ በቂ አይደሉም:: ምክንያቱም የባንኮቹ ቁጥር እና የሕዝቡ ብዛት የተመጣጠነ አይደለም:: ምጥጥኑም አንድ ቅርንጫፍ በአማካይ ለ18,308 ሰው ያስተናግዳል ማለት ነው:: ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዋና ከተማው አዲስ አበባ እና በታላለቅ የአገሪቱ ከተሞች አንድ ቅርንጫፍ ከኹለት ሺሕ ሰው በላይ ያስተናግዳል:: በአሁኑ ወቅት በሳብ ሰሐራን አፍሪካ ደረጃ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የባንክ ተደራሽነት ያላት አገር ሆናም ተመዝግባለች:: የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከሰሐራ ባሉ የአፍሪካ አገሮች በአማካይ 43%፣ በኬንያ 82% በሩዋንዳ 50 % ሕዝባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ያላቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ግን 20 ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አለው::ይህም ማለት ከ80 በላይ ሕዝባችን የባንክ ተጠቃሚ አይደለም ማለት ነው:: በብሔራዊ ባንክ ደረጃ በተያዘው ዕቅድ መሠረት 80 በመቶው ሕዝብ በ5 ኪሎ ሜትር ራዲየስ የፋይናንስ ተቋም አገልግሎት እንዲያገኙ በዕቅድ ቢያዝም፣ ለማሳካት ተጨማሪ ባንኮችና የነባር ባንኮች ቅርንጫፎች መስፋፋት የግዴታ ይሆናል ማለት ነው::

ለደንበኞቹም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው ነው:: ወደ ተሻለ አሠራር እንዲገቡ የሚያስችል እና ወረቀት ተኮር (paper based) የሆነውን አሠራር የሚያስቀር የባንክ ቴክኖሎጅ ይዞ ይመጣል:: የመንግሥት መመሪያ ከተሻሻለ አዳዲስ አገልግሎቶችንና ምርቶችን ለማስተዋወቅ በሚያስችል ሁኔታ በመዋቀር ላይ ይገኛል::

ለምሳሌ፡ Syndicate Loan (ከሌሎች ባንኮች ጋር በመተባበር ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የብድር አገልግሎት መስጠት)፣ የግብርናውን ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የብድር አገልግሎት መስጠትና አንድ ላይ መሥራት፣  Idea Financing (ትልልቅ እና ለአገር ጠቃሚ ሐሳብ ያላቸወን ግለሰቦችና ድርጅቶች የብድር አገልግሎት መስጠት)፤ ለአገር ውስጥ ኅብረተሰብ በረጅም ጊዜ የቤት መግዣ የብድር አገልግሎት መስጠት፤ ለዲያስፖራው ከ510% ተቀማጭ በሆነ ለአጭር፣ ለመካከለኛና ለረጅም ጊዜ የቤት መግዣ ብድር መስጠት፤ ባንኩ የትኩረት አቅጣጫው ኢንቨስትመንትና ቴከኖሎጅ በመሆኑ ከተከፈለ ካፒታሉ ውስጥ 20% የሚሆነውን ከድርጅቶችና ከግለሰቦች ጋር በጋራ ለኢንቨስትመንት አገልግሎት ያውለዋል:: ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ የአማካሪ ቡድን የሚመድብ ይሆናል:: ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአገራችን ያለው ሕዝብ አንጻራዊ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በተለይም ወደ መካከለኛ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ ቁጥር መጨመሩ ወደ ክፍለ ኢኮኖሚው ለመግባት የተሻለ ምቹነት ይኖረዋል:: በትውልድ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች በባንክ ኢንዱስትሪው እንዲሳተፉ ብሔራዊ ባንክ መፍቀዱ እና ስቶክ ኤክስቸንጅ ማርኬት የመከፈት ዕድሉ ሰፊ መሆኑ ወደ ኢንዱስትሪው መቀላቀሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል:: በምሥረታ ላይ የሚገኜው ጃኖ ባንክ በማክሮ ኢኮኖሚው ውስጥ የባንክ አገልግሎቱን ክፍተት በመሙላት የኅብረተሰቡን ዕድገት የማፋጠን ድርሻ መወጣት የሚችል ተቋም ይሆናል:: ጃኖ ባንክ በቴክኖሎጅ ካደጉ ባንኮች ጋር በትብብር ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸው የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ያስችላል::

የጃኖ ባንክ ተልዕኮ ራዕይ እና እሴቶች

ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት 3. የባንኩ ዓላማዎች  ባንኩ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጥ እና በትኩረት የሚሠራባቸው ዘርፎችም ኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጅ ናቸው፤  የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየት እና በማጥናት ኢንቨስተሮች እንዲሳተፉ ማድረግ፤  ለሀገር ሊጠቅሙ የሚችሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን የብድር አቅርቦት እንዲገኙ ማድረግና በጋራ ማደግ (Idea Financing)፤  የገጠሩ የኅብረተሰብ ክፍል የባንክ አገልግሎት እንዲያገኝ ማገዝና የኑሮ ለውጥ እንዲያመጣ በጋራ መሥራት፤  ኢንቨስትመንትና ሥራ ፈጠራን መደገፍ፤  ጤና፣ ትምህርትና የቴክኖለጅ ፈጠራን መደገፍ ናቸው::

4.

የጃኖ ባንክ አክሲዮን ባለቤት የመሆን ጥቅም



ባንኩ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የሚደገፍና አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እና ዲስፖራውንም በስፋት የሚያሳትፍ በመሆኑ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት አንዱ ይሆናል::



በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በመቅጠር ዘርፉን እና ባለ ድርሻውን ማሳደግን ያለመ በመሆኑ የዚህ ባንክ ባለቤት መሆን ጥቅሙ ከፍተኛ ነው::



የባንኩ ዓላማ ለትርፍ የሚቋቋም ቢሆንም አገርን በማሳደግ እና ለኅብረተሰቡ ተገቢውን አገልገሎት በጥራትና በብቃት ለመስጠት ያለመ ነው::

5.የአክሲን ሽያጭ የአገሪቱ የብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት ያሟላ እና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሲደርግ የቆየ ሲሆን የባንኩ አክሲዮን ባለቤት መሆን የሚፈልግ ድርጅትና ግለሰብ ከዚህ በታች ስማቸው በተዘረዘሩት ባንኮች (በሁሉም የኢትዮጵ ባንኮች) በኩል አክሲን መግዛት ይችላል:: 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ለኅብረተሰባችን የሚያቀርብ ባንክ መገንባት::

4. አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.

ባንኮች የሚሰጡት ምርትና አገልግሎት ተመሳሳይና ነባር በመሆኑ በዲጅታላየዜሽን ዘመን ቀድሞ የነበረውን የባንክ አሠራር መከተል የሀብት ብክነት የሚያስከትልና የሥራ ጥራትንም የሚቀንስ ስለሆነ ዲጅታላይዜሽን የጃኖ ባንክ አሠራር ይሆናል:: ከዚህ በፊት የነበረውን የቢዝነስ ሞዴል መቀየር አስፈላጊ እና ወቅቱ የሚጠይቀው አሠራር ነው::

ቴክኖሎጅን እና በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኀይል በመጠቀም ዘመናዊ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ለኅብረተሰቡ ማቅረብና የባንኩን ባለቤቶች ፍላጎት ማሳካት::

ጃኖ ባንክ ዲጂታላየዜሽንን የሚያስተዋውቀው የባንኩን የተንዛዛ ወጭ ለመቀነስ ለሚያስፈልግና ገቢውንም ከፍ ለማድረግ የታለመ ሲሆን፣

o ኅብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል o ዘመናዊ

ቴክኖሎጅን

በመጠቀም

1. የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 1000.00 (አንድ ሺሕ) ብር ሲሆን መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት 5 ወይም አምስት ሺሕ ብር ነው:: 2. አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ብዛት 100,000 (አንድ መቶ ሺሕ) ወይም 100,000,000.00 (አንድ መቶ ሚሊዮን) ብር ነው:: 3. የሥራ ማስኬጃ ክፍያው ቃል የተገባውን ጠቅላላ መጠን 5% ነው:: 4. የአክሲን ግዥ ለመፈፀም አዲስ አበባ በሚገኜው የባንኩ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ወይም ስማቸው በተጠቀሱት ባንኮች የተዘጋጀውን የሽያች ቅጽ መሙላትና የሚጠየቁ መረጃወችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል:: 5. የሚገዙትን ጠቅላላ የአክሲዮን መጠን በዝግ ሒሳብ እና ቃል የገቡትን የአክሲን መጠን 5 % የሥራ ማስኬጅያ ክፍያ በተንቀሳቃሽ ሒሳብ ገቢ ማድረግ ይገባቸዋል:: 6. የአክሲዮን ግዥ ሲፈጽሙ የጠቅላላ የአክሲዮኖችን ዋጋ 50 % ከፍለው ቀሪውን በሁለት ጊዜ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በኹለት ጊዜ መክፈል ይቻላል:: 7. አክሲን የሚገዙ ግለሰቦች ማሟላት የሚገባቸው ነገሮች 7.1. የታደሰ መታወቂያ (ፓስፖርት) መንጃ ፈቃድ 7.2. በልጆች ስም መግዛት ለሚፈልግ የልደት ካርድ እና የአባት/እናት/ወይም የአሳዳጊ መታወቂያ 8. አክሲን የሚገዙ የሚገባቸው ነገሮች

ድርጅቶች

ማሟላት

8.1.የድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንገድ ምዝገባና የግብር ከፋይነት መለያ 8.2. አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል ሕጋዊ ውክልና

አድራሻ

3. ዓባይ ባንክ አ.ማ

o ኅብረተሰቡ የባንኩ የጀርባ አጥንት መሆኑን መገንዘብ

6.የአክሲን ሽያጭ ዝርዝር መግለጫ

2. ዳሸን ባንክ አ.ማ

ራዕይ

እሴቶች

17. ዘመን ባንክ አ.ማ.

8.3. ማኅበራትና ዕድሮች የተመሰረቱበት የፈቃድ ሰርተፊኬት

የባንክ አገልግሎት ያልተዳረሰው (የገጠሩ የኅብረተሰብ ክፍል) የባንክ አገልግሎት የማግኜት ዕድሉ ዝቅተኛ ሲሆን ሦስት አራተኛው የንግድ ባንኮች የሚገኙት በከተሞች አካባቢ ሲሆን በተለይም 37% ቅርንጫፎች የሚገኙት በአዲስ አበባ ከተማ ነው::

ተልዕኮ

16. ወጋገን ባንክ አ.ማ.

5. ቡና ባንክ አ.ማ. 6. አዋሽ ባንክ አ.ማ. 7. አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ. 8. ብርሃን ባንክ አ.ማ. 9. የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. 10. ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. 11. እናት ባንክ አ.ማ.

ተጨማሪ ማብራሪያ ከጃኖ ባንክ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በአካል በመገኘት ወይም በየአካባቢው ያሉ የባንኩ አደራጆችን ያነጋግሩ:: አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ቦሌ መድሐኒያለም አካባቢ፣ መድኃኒዓለም ሞል (ኤድና ሞል ፊት ለፊት) ስ.ቁ. 0911808415 0930028524 0930032610 0911808435

12. አንበሳ ባንክ አ.ማ.

Email: [email protected]

13. ንብ ባንክ አ.ማ.

Telegram: Jano Bank S.c

14. ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ0

Facebook: Jano Bank S.c

15. ሕብረት ባንክ አ.ማ.

Whatsup: Jano Bank S.c

18 ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

መጻሕፍት መደብር

አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ስታዲየም፣ ናሽናል ታወር

0911 00 67 05 / 0924 40 84 61

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

19

ቁጥር 007

ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት...

ከገፅ 11 የዞረ

ሕገ መንግሥት አወዛጋቢ አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ 5 የጨመረው ማሻሻያ የጋራ ባህልን ብቻ ነው::

ዜጎቿ በሚሊዮኖች የሚሰቃዩባት ወህኒ ቤት ሆነች::

በመጀመሪያ ደረጃ የፌዴራል ሥርዓቱ አንዳችም ሞራላዊም ሕዝባዊም ቅቡልነት የለውም:: ሕወሓት ኢትዮጵያን በአፈሙዝ ፣ ያለሕዝብ ይሁንታ፣ ያለበቂ ጥናትና ያለብልሃት ወደ ጽንፈኛ ጎሰኝነት ያዘለለበትና በድቡሽት ላይ የቆመ መዋቅር ነው:: ምንም እንኳን ቻርተሩም ሆነ ሕገ መንግሥቱ የአገራዊውን መንግሥት አወቃቀር በግልጽ ባይወስኑም በተግባር የተሠራው መዋቅር ዘውጌ ፌዴራላዊ ነበር::

በኢሕአዴግ ዘውገኛ ሥርዓት የሕዝቦች እኩልነት የለም:: በሕግ የተደነገገ የበላይነትና የበታችነት፣ የባለቤትነትና ባዳነት አለ:: አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ እርከኖች ያሉት፣ ንዑሳን ማኅበረሰቦችና ቡድኖች ብዙሃንን የሚያሽቆጠቁጡበት አገዛዝ ነው:: በግልጽ መድልዖ ላይ የተመሠረተና ዓይን ያወጣ የአንድ ብሔረሰባዊ ቡድን አገዛዝ ነው:: አንዱን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ፣ ሌላውን ደግሞ የእጅ አዙር ባሪያ በማድረግ እያሸማቀቀ የሚኖር ነው:: በዚህ የከፋፋይነት ማዕቀፍ መሠረታዊ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እንዳሻው የሚጥስ አረመኔ ሥርዓት ነው:: የአገሪቱን አንጡራ ሀብት ያለቅንጣት ይሉኝታ በአንድ ብሔረሰብ ስም የሚዘርፍ ቀማኛ ስርዓት ነው:: እውነተኛውና የለየለት የብሔር ጭቆና የሰፈነው በዘመነ ኢሕአዴግ ነው::

ለመሆኑ የዚህ ሥርዓት የማያጨቃጭቅና አስተማማኝ መሠረት ምንድን ነው? በሕግ የተመሠረተባቸው ግዛታዊ አንድነት፣ የቋንቋ አንድነት፣ የጋራ ሥነ-ልቦና፣ የባህል አንድነት የሚባሉት መስፈርቶች በተግባር ካለው ክልላዊ መዋቅር ጋር በፍፁም አይሰምሩም:: ማለትም መስፈርቶቹ ቀድሞውንም በተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ አልተመሠረቱም:: ኢሕአዴግ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አስተዳደራዊ እርከኖችን ለመወሰን የተጠቀመው ዋነኛ መስፈርት ቋንቋ ነበር:: ሕወሓት የዘረጋው የጎሳ ሥርዓት በዘመናት መስተጋብርና መቻቻል የተፈጠረውን ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ማኅበራዊ ሚዛን በቀላል ፖለቲካዊ ቀመር ሰትሮ ለማጠናቀቅ የማይቻል መሆኑን አልተገነዘበም:: ሆኖም በሕገ መንግሥቱ ላይ ምናባዊ መስፈርቶቹ የተቀመጡትበት ኹነኛ ምክንያት አላቸው:: ይህም እያንዳንዱ የክልል ባለቤት የሆነ ማኅበረሰብ ሌሎች በመጤነትና በባዕድነት የተፈረጁትን ነዋሪ ማኅበረሰቦች እያባረረም፣ እየጨፈለቀም ይሁን እየገደለ ግዛቱን በማፅዳት ብቸኛ ማንነት እንዲገነባ በግብነት ነው:: ስለዚህም የጎሳ ፌዴራሊዝሙ ታሪክን ለማሻሻልና ወደፊት ለማራመድ ሳይሆን የአገሪቱን ተፈጥሯዊ ሂደት የኋሊት ለመቀልበስ የተወጠነ ምህንድስና ነው:: ከብዝሃነት ጎሳነትን፣ ከመቻቻል መቃቃርን፣ ከመቀራረብ መራራቅን፣ ከመተማመን መጠራጠርን፣ ወዘተ. ለማስፈን የታለመ ስልት ነው:: የሕወሓት የዘውግ ፌዴራሊዝም ለፍትሕና ርትዕ አልቆመም:: በገራፊና ተገራፊ መርህ የሚመራ የበቀል ሥርዓት ነው:: ጭቆናን፣ ግፍና መድልኦን ከብሔራዊ ደረጃ አውርዶ በክልልና በብሔረሰብ ደረጃ በሕግና በፖሊሲ የተከለና የሚደግፍ አገዛዝ ነው:: ስለዚህም ባዕድ ቋንቋና ባህል ተጫነብኝ ይል የነበረው ጫኝ ሆነ:: ተገፋሁ ተበደልኩ የሚለው ገፊና በዳይ ሆነ:: ተነቀልሁ፣ ተነጠቅሁ የሚለው ነቃይና ነጣቂ ሆነ:: ኢትዮጵያ

ዘውጋዊነትና ማንነታዊ ቡድነኝነት በመንገሡ ምክንያት፣ ዜግነት ሕገ መንግሥታዊም ተግባራዊም ህልውና አጥቷል:: ግለሰብ ዜጋ ፍጹም ተውጧል፣ ተደምስሷል:: በምትኩ ጎሰኝነት በእለት ተዕለት መስተጋብር ድረስ በመዝለቁ ተራ የግል ፀብ እንኳን ቀርቷል:: በብሔረሰብ ስም ዘረፋ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግብረ ሰዶማዊነት አፀያፊነቱ ቀርቶ የሚፈቀድና የሚያስመሰግን ሰናይ ምግባር ሆኗል:: አረመኔያዊነቱም ወንጀሉም ብሔረሰባዊ ሽፋንና ከለላ ተሰጥቶት ሰላማዊ ሰልፍ እስከማስወጣት እንደደረሰም ታዝበናል:: በአጠቃላይ አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢፌዲሪ መንግሥታዊ መዋቅር ለአገር ግንባታ የተሠራ አይደለም:: በአንድ አገርና ፖለቲካዊ ሥርዓት ውስጥ እንደሚኖር ሕዝብ ቅንጣት ብሔራዊ መንፈስ የለውም:: የባህል ፖሊሲ ዘውጋዊ ማንነቶችንና ባህሎችን በየራሳቸው ክበብ የሚገድብና የሚያጋንን ፤ አገራዊ ባህሎችንና ትስስሮችን የሚያዳክም ነው:: ቢያንስ የብዝሃነት መርህ ኅብረ-ባህላዊነት (multiculturalism) የሚፈልገውን በተለያዩ ማንነታዊ ማኅበረሰቦች መካከል ቀጭን ድልድይ እንኳን አልዘረጋም:: የጋራ መስተጋብርን የመፍጠር፣ ብዝሃነትን በአንድነት ውስጥ የማስተናገድ ሚዛናዊ ቀመር የለውም:: ኢትዮጵያውያንን ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በሚል ማደናገሪያ የተከፋፈሉና በራቸውን ዘግተው የሚቀመጡ ባላንጦች አድርጓል:: የጋራ እሴቶችና ግቦች እንዳይኖራቸው አድርጓል:: ስለሆነም በመቀራረብና መተዋወቅ ፈንታ

መራራቅንና ባይተዋርነትን የሚያባብስ፣ ሰፊ የተራክቦ መንገዶችንና ዕድሎችን ከመዘርጋት ይልቅ በጠባብ ፖለቲካዊ ጥቅም ላይ ያተኮረ አፍራሽ (disintegrationist) ነው:: ከፋፍለህ ግዛ የሥርዓቱ ምሰሶ በመሆኑ ሁሉም በየጎሳው ከታጠረስ በኋላ ምን ይከሰታል የሚል አርቆ አሳቢነት ከጥያቄ ውጭ ነበር:: ሕወሓት ከበቀል ሥነ-ልቦና ፀድቶ በሆደ ሰፊነትና አርቆ አሳቢነት ስለአገር ግንባታ ቢሠራ ኖሮ እንዲህ ያለ ሥርዓት በኢትዮጵያ አይፈጠርም ነበር:: ከአጭርና ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ የላቀ ራዕይ ቢኖረው እንዲህ ያለ ከቅኝ አገዛዝ የከፋ ሰው በላ ሥርዓት አይዘረጋም ነበር:: ዛሬ በአገራችን የምናየው ዝብርቅርቅ መሠረታዊ ምክንያት የጎሳ ፌዴራል ሥርዓቱ ከአነሳሱ በቅጡ ያልመለሳቸው ጥያቄዎች ድምር ውጤት ነው::

3.የመፍትሔ ሐሳቦች ዛሬስ ለአገራችን ምን ዓይነት የአገር ግንባታ ያስፈልጋታል የሚል አማራጭ ከማቅረባችን በፊት ኹለት ነገሮች እናንሳ:: አንደኛ ከላይ ባየናቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ሙከራዎች የነበረው ቁልፍ ጥያቄ ብዝሃነትን ከአንድነት እንዴት እናስተናግድ ነው:: በንድፈ ሐሳብ ደረጃ በዘውግ ማንነትና በፖለቲካ ሥልጣን መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት የለም:: በተግባራዊነትም ሚዛን የቋንቋና የባህል ጥያቄዎች በአሃዳዊም በፌዴራላዊም ሥርዓተ መንግሥታት ውስጥ ሊስተናገዱ ይችላሉ:: ኹለተኛ ማናቸውም አዎንታዊ የአገር ግንባታ፤ የመንግሥቱን አወቃቀርም ሆነ የብሔራዊ መንፈሱን ይዘት የሚወስነው የየአገሩ ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታ ነው:: ከሁሉም በላይ ደግሞ ወሳኙ መነሻ የሕዝብ ይሁንታ ነው:: በግንባታው ሂደት መንግሥት ማዕከላዊ ቦታ ቢኖረውም፣ በተጓዳኝ ከታች በሰፊው ሕዝብ ፈቃዳዊ ጥረት የሚደገፍ መሆን አለበት:: ይህን ታሳቢ በማድረግ፤ በቅድሚያ ለአገር ግንባታው መሠረት የሚሆን ግልፅና አካታች ርዕዮተ ዓለም መንደፍ:: ዘላቂ አገር ግንባታ ከእኔ ይልቅ የኛ መንፈስን በሚፈጥሩ አገር በቀል የጋራ እሴቶችና ግቦች ላይ መመሥረት አለበት:: ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብን ከመንግሥት፣ እንዲሁም የመንግሥትን አካላት በአዎንታዊነት የሚያቀራርብ መሆን አለበት:: የአገሪቱን ቀጣይነትና የሕዝቡን ጥቅም የሚያረጋግጥና የወደፊት እጣ ፈንታቸውንም በግልፅ የሚያስቀምጥ መሆን አለበት:: ቀጥሎ መንግሥቱ በአወቃቀሩም በግቡም እውነተኛ አገራዊነት ይኑረው:: በበኩሌ በፌዴራላዊነቱ ቢቀጥልም ከሌጣ ዘውጋዊነት/

ምርትዎንና ድርጅትዎን

ሲራራ ጋዜጣ ላይ ያስተዋውቁ

ቋንቋ ይልቅ ታሪክንም፣ ባህልንም፣ አስተዳደራዊ ምቹነትንም ወደሚያካተቱ አሐዶች ይቀየር:: ብዝሃነትና አንድነትን በዴሞክራሲ አማካይነት የሚያቻችል ሊሆን ይገባል:: ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ከአገር ዐቀፋዊ ትብብር ይልቅ የፉክክር ማዕቀፍ እንዳይሆን፣ በክልሎችም ሆኑ ክፍለ አገሮች መካከል ጠንካራ ድንበር ተሻጋሪ ትስስሮችን መፍጠር ያስፈልጋል:: ሦስተኛ በሕዝቦችም መካከል እውነተኛ ኅብረ ባህላዊነት የሚያሰፍን መሆን አለበት:: ከዘውጎች የዘለለ ብሔራዊ ባህል መፍጠርና ማዳበር ወሳኝ ጉዳይ ነው:: አገራዊነትና ዘውጌነት ሽቅብም አግድምም የሚደጋገፉበትን መንገዶች መተለም ያስፈልጋል:: የዜጎችን ባህላዊ አድማስ በድምር በሚያሰፉ፣ ማኅበራዊ ወረትን በሚያዳብሩና እርስ በርሳቸው በሚመጋገቡ ለውጦች መተለም አለበት:: ማንኛውም አዎንታዊ የግንባታ ጥረት ታሪካዊና ባህላዊ ቀጣይነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል:: አራተኛ መሠረቱ ሰፊ የሆነ ማኅበረኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎችንም ማካተት አለበት:: በትምህርት፣ በመሠረተ ልማት፣ በዘርፈ ብዙ ምጣኔ ሀብታዊም ሆነ ማኅበረሰባዊ ልማት ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና መልከዐ ምድራዊ ድንበሮችን የሚያቆራርጡ ሰፊ ትስስሮችንና መደጋገፎችን ማበልፀግ ያስፈልጋል:: በመጨረሻ በአፈጻጸሙ ረገድ አገር ግንባታ ከዜሮ የሚጀምር ሳይሆን ነባሩን የሚያጠናክር፣ የሚያሻሽልና አዲስ የሚፈጥር ስልቶችን ያቀናጀ መሆን አለበት:: በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግና በቡድናዊና ግላዊ፣ በዘውጋዊና ብሔራዊ፣ በብዙሃኑና ንዑሳን፣ ወዘተ. መካከል ሚዛኑ የተስተካከለ መሆን አለበት:: በአገር ግንባታው ሂደት ማን ምን እንዴት ይሥራ? የሚለውን በጥንቃቄ ማዘጋጀት ታላቅ ትኩረት የሚጠይቅ ሥራ ነው:: የፖለቲካ ተዋናዮች፣ መንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት የሕዝባቸውን ብሔራዊ ማንነት በመቅረፅ ጥረት ላይ ሊሠሩ የሚፈቀድላቸው፣ የሚበረታቱት፣ የሚፈለግባቸው ወይም የሚከለከሉት ተለይቶ ሊታወቅ ይገባል:: የአገር ግንባታው ባህላዊ ዘርፍ ሕዝባዊ ትዕምርቶችን በየትኞቹ የጋራ እሴቶች ላይ ይገንባ፤ ከታሪካችን የጋራ ትውስታን በመገንባቱ ጥረት የቱ ይፈቀድ፣ ይበረታታ ወይም ይከልከል የሚሉትን በቅጡ የሚለይ ሊሆን ይገባል:: የአገር ግንባታው በልሂቃዊ መደቦች፣ በውሱን ቡድኖችና ማዕከሎች ተንጠልጥሎ እንዳይቀር በስፋትና በጥልቀት ከሕዝባዊነት ጋር ማጣጣም ተገቢ ነው::

ስልክ ቁጥር፡- +251-922-58-0561 [email protected] www.theblacklionafrica.com

20

ሲራራ

መንግሥት የግሉን ክፍለ... አይችልም:: ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አስተዳደሩ እና የሕዝብ አስተዳደሩ እርስ በርሱ ተወዛግቧል:: የኢኮኖሚ አስተዳደሩ ነፃና በገበያ ላይ የተመሠረተ ቢሆን ኖሮ የሕዝብ አስተዳደሩ ብሔር ላይ ቢመሰረትም ችግሩ እንደ አሁኑ የገዘፈ አይሆንም ነበር:: ኢኮኖሚው ግን ነጻ መውጣት አለበት:: የሕዝብ አስተዳደር እና የኢኮኖሚ አስተዳደር መለያየት መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም የኢኮኖሚ አስተዳደር የሚጠይቀው ችሎታን እንጂ ማንነትን ስላልሆነ ነው:: ምናልባትም በሐሳብ የተራራቁ የዜጋና የዘውጌ የፖለቲካ ድርጅቶች መሃል ቤት ሊመጡ የሚችሉት የሕዝብ አስተዳደር እና የኢኮኖሚ አስተዳደርን ለያይተው የኢኮኖሚ አስተዳደሩ በገበያ ኀይላት እና ዕውቀት ባላቸው የማክሮ ኢኮኖሚ አመራር ሰጪዎች እንዲመራ የሕዝብ አስተዳደሩ ‹የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ› እንደሚባለው በማንነት ላይ እንዲመረኮዝ ሲያደርጉ ነው:: አንድ ኢኮኖሚ ሊለማም ሊያድግም የሚችለው እንደ የአካባቢው ሁኔታ ዘርፍ ለይቶ ማልማት ሲቻል ነው:: ኢትዮጵያን ሰሜን እና ደቡብ እንኳን ተብሎ ቢከፋፈል:: ደቡቡ በግብርና እና ለግብርና ምርት ማቀነባበርያ የተመቸ ሁኔታ አለው:: ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ሰፊ የማዕድን ሀብት ያለበት ነው:: ድንጋይ እምነበረድ ወርቅ የብርጭቆ ፋብሪካዎች ግብዓት የሚሆኑ ማዕድናት አሉት:: የአገሪቱን የፖለቲካ ውዝግብ በኢኮኖሚ መነጽር ከተመለከትነው ዋናው ምክንያት የደቡቡ ለም የእርሻ መሬት በቀላሉ የሚለማና የሰሜኑ ድንጋያማ መሬት በግለሰብ ደረጃ ሊለማ የማይችል መሆኑ እንዲሁም ባለፉት መንግስታት ትኩረት ስላልተሰጠው ሕዝቡ በልቶ ለማደር ወደ ደቡብ መሰደድ ስለተገደደ ነው:: አገሪቱ አድጋ የኢኮኖሚ ፍልሰቱ ከሰሜን ወደ ደቡብ እና ከደቡብ ወደ ሰሜን አቻ ለአቻ ሲሆን የባህል የማኅበራዊ የኢኮኖሚ መስተጋብሩ አድጎ ለግጭት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች በራሳቸው ይከስማሉ::

ርዕዮተዓለማዊ አመለካከት የሚመነጭ ነውና የኢትዮጵያ መንግሥት እየተጓዘ ስላለበት ማኅበረሰባዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ እምነት አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ:: እነ ሶቅራጥስን የመሳሰሉ የጥንት ፈላስፎች በአገር መሪነት ደረጃ ፈላስፎች ቢሰማሩ ሕዝብን አስተካክለው ይመራሉ ብለው ያስቡ ነበር ይባላል:: ፍልስፍና ወደ ሙያዊ ሥነ ጥበቦች ከተከፋፈለበት ጊዜ ጀምሮ ግን የጥበብ ተመራማሪዎችና የአገር መሪዎች ሚና ተለያይተዋል:: ፈላስፎች መሪዎች እንሁን ሲሉ ሐሳባቸውን በሕዝብ ላይ ስለሚጭኑ ወደ አምባገነንነት ሲቀየሩም አይተናል:: ካርል ማርክስ ቀደምት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሰላማዊ ለወጦች በተለይም በፈረንሳይ አብዮቶች የተካሄዱባቸውን ግልብ ሐሳቦች (Utopian Socialism) በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ያልተመረኮዙ በማለት በመደብ አምባገነንነት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ጽንሰ ሐሳብ ቢነድፍም ሌኒንን ስታሊንን ማኦ ዜዱንግን የመሳሰሉ መሪዎች ግን ጽንሰ ሐሳቡን አሻሽለው የፍልስፍናውንም የመሪነቱንም ሥልጣን ደርበው ስለያዙ የራሳቸውን ሐሳብ ፈጻሚና አስፈጻሚ በመሆናቸው ወደ አምባገነን መሪነት ተቀይረዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ንድፈ ሐሳቦችን በማሻሻል የራሳቸው ፍልስፍና ነው በሚሉት ነገር ግን ከሌሎች የተቀዳ

ከገፅ 7 የዞረ ያለበት

በኢኮኖሚክስ ‹ኢኮኖሚክ ሪጅናላይዜሽን› የሚባል በእምቅ ሀብት ላይ የተመሠረተ የምርት አደረጃጀት ክፍፍል ሳይንስ አለ:: የአንድን አካባቢ እምቅ ሀብት አይቶ በዛ ላይ መሥራት መቻል ነው:: የቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን በተላይ ሦስተኛው የአምስት አመት እቅዳቸው ይህን ነው የሚያሳየው:: የስምጥ ሸለቆን ተከትሎ እነ አዋሽ መትሀራ፤ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ፣ የተንዳሆ ጥጥ ልማት ወዘተ ወደ ልማት የገቡት በንጉሱ ሦስተኛው የአምስት አመት የልማት እቅድ ነው:: ብዙ ባለሀብቶች ሀብታቸውን በአካባቢው አፍሰዋል:: ዛሬ ድረስ የጥጥ ልማት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ምንጫቸው እዚያ ነው ያለው:: ሌሎችም እንደ የወላይታ እርሻ ልማት ፕሮግራም (WADU) የአርሲ እርሻ ልማት ፕሮግራም (CADU) የሚባሉ ነበሩ:: እንደዚህ ዓይነት ኢኮኖሚክ ሪጅናላይዜሽን ለአንድ አገር ዕድገት በጣም ጠቃሚ ነው:: ነገር ግን አሁን እንደ ፋሽን ሆኖ ሁሉም ቦታ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይገነባል:: ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባቱ ላይከፋ ይችላል ግን ምን አይነት ኢንዱስትሪ ፓርክ ነው የሚገነባው? ለምንስ ነው የሚገነባው? ለወደብ ቅርብ ነወይ? ትራንስፖርት አለ ወይ? ጥሬ ዕቃ አለ ወይ የሚሉ ነገሮች በአግባቡ መመለስ መቻል አለባቸው:: ነገር ግን የጎረቤቱን እያየ ለእኔም ይደረግ መሆን የለበትም ከፉክክር መንፈስ መውጣት መቻል አለብን:: ለምሳሌ የኦሮሚያ ክልል 2010 ‹ጂ.ቲ.ፒ 2› አገራዊ ዕቅዱን ትቶ “የኢኮኖሚ አብዮት” ብሎ የራሱን እንቅስቃሴ ጀመረ:: አማራ ክልልም ቆየት ብሎ “የኢንዱስትሪ አብዮት” ብሎ ተከተለ:: ኹለቱ ክልሎች አገራዊ ዕቅዱን ትተው የየራሳቸውን ዕቅድ ነድፈው ወደ ሥራ ገቡ በዚህ መሃል የማዕከላዊ መንግሥት የሥራ ድርሻ ምን እንደሆነ ግራ ነው የሚያጋባው:: ሲራራ፡- የኢንዶውመንት ድርጅቶች የሚባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው ተቋማት መኖር በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ተጽዕኖ እንዴት ያዩታል? አቶ ጌታቸው፡- አንድ ኢኮኖሚ መመራት

የምንከተለውን የኢኮኖሚ...

መጋቢት 12 2012

ከገፅ 15 የዞረ

ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ስም ሥልጣንን ጠቅልሎ በመያዝ የቅርብ አጋሮቻቸውን ሐሳብ እንኳ የማይቀበሉ ወደ አምባገነን መሪነት የቀረቡ ሰው ነበሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም የመደመር ፍልስፍናቸውን የአገርን ኢኮኖሚ ለመምራትና ፖሊሲ ለማውጣት እጠቀመዋለሁ ካሉ ወደ አምባገነን መሪነት ሊቀየሩ እንደሚችሉ ከታሪክ ልንረዳ ይገባል:: ምሁራን እንዲወያዩበት እየተባለ ዳር ዳር እየተባለ አንደሆነም እየተመለከትን ነው:: ታላቁ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፍልስፍና ጠንሳሽ ኬንስ ስለ ፈላስፎችና መሪዎች የተለያዩ ሰዎች መሆን ሲጽፍ፡- “ከልሂቃን አመለካት ተጽዕኖ ነጻ የሆኑ የሚመስላቸው የተግባር ሰዎች ብዙ ጊዜ የአንድ ሙት ኢኮኖሚስት ሐሳብ ባሕሪያዎች ናቸው፤ ከአየር ላይ ድምጽ የሚሰሙ እብድ ባለሥልጣናት ከስሜታዊነታቸው የሚነጹት ከጥቂት ዓመታት በፊት ሲሞነጫጭር ከነበረ ምሁር ነው፤” ብሎ ነበር:: በእንግሊዘኛው እንዲህ ይላል፡“Practical men, who believe themselves to be quite exempt from any intellectual influences, are usually the slaves of some defunct economist. Madmen in authority, who hear voices in the air, are distilling their frenzy from some academic scribbler of a few years back.”

በውድድር ነው:: የኢንዶውመንት ድርጅቶች በአገሪቱ ላይ የፈጠሩት ትልቁ ችግር ውድድር እንዳያድግ ማድረጋቸው ነው:: ለጊዜው ትልልቅ የጠቅልልነት ወይም የሞኖፖል ሥርዓት ፈጥረው ነበር:: ለምሳሌ በግንባታው ዘርፍ ትልልቅ ሥራዎችን እነሱ ይይዛሉ:: በሥራቸው ደግሞ ኦሊጎፖሊ (oligopoly) ሥርዓትን ፈጥረዋል:: ውድድር የሌለበት ገበያ ጥራት የሌለው ገበያ ነው የሚፈጥረው:: ተቋማቱ ገበያውን ሲረብሹ ነው የቋዩት:: ትልልቅ ሥራዎቸን እየወሰዱ በበርካታ ዘርፎች የአገር ውስጥ አምራቾች እንዳያድጉ አድርገዋል:: ሲራራ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግት የዐሥር ዓመት የኢኮኖሚ ዕቅድ ነድፎ ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው:: ዕቅዱን የማየት ዕድል ገጥሞዎት ከሆነ፣ በዕቅዱ ላይ ያለዎትን አስተያየት ቢገልጹልን?

አቶ ጌታቸው፡ዕቅድ ዝም ብሎ አይዘጋጅም:: መከተል ያለበት ቅደም ተከተል አለ:: ከምንም ከምንም ቀድሞ ጽንሰ ሐሳብ የሚመረጠው ከተጨባጭ ሁኔታ ተነስቶ ነው:: ከተጨባጭ ሁኔታ ወደ ጽንሰ ሐሳብ መሸጋገር ይቻላል:: ከጽንሰ ሐሳብ ወደ ፖሊሲ መሸጋገር ይቻላል:: ፖሊሲ ሲኖር እሱን መሠረት አድረጎ እቅድ ይዘጋጃል:: ከዕቅድ ወደ ተግባር ይኬዳል:: እነኚህ ቅደም ተከተሎች አምስት የኢኮኖሚ አስተዳደር እርከኖች ናቸው:: አሁን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ አለኝ ሲባል፣ አራተኛ ደረጃ ላይ ተደርሷል ማለት ነው:: አሁን ለወጣው ዕቅድ በመጀመሪያ የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ምንድን ነው? ገና አልተጠናም:: የምትከተለው ጽንሰ ሐሳብም በትክክል አልተለየም:: አልተብራራም:: አይታወቅም:: የትኛውንም ሁኔታ ለመወሰን አሁን ያለንበት ሁኔታ በጥናት ተለይቶ መቅረብ መቻል አለበት:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በመደመር መጽሐፍ ላይ ብቻ ተንተርሶ አይደለም:: መደመር መጽሐፍ ፖለቲካውንም፣ ሶሾሎጂንም፣ ኢኮኖሚውንም ሁሉንም ነገር በመነካካት የያዘ ነው:: አንዱን ዘርፍ ለምሳሌ ኢኮኖሚውን ነጥሎ ትንታኔ የሰጠ ጉዳይ አይደለም:: የብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ፕሮግራምም ወደ ፖሊሲና

ለማጠቃለል ያህል፣ በ1950ዎቹ መጨረሻ፣ ሴዑልን ጨምሮ፣ በከተሞች አካባቢ የነበረው “አስጊ ሕዝብ” ከጋዜጠኞች፣ ከምሁራን እና ከኮሌጅ ተማሪዎች የተውጣጣ ነበር ብሎ መናገር ይቻላል:: ይህም ከቀድሞው የገበሬ ማኅበረሰብ የተለየ፣ በከተሞች ላይ የተመሠረተ፣ አዲስ ሲቪል ማኅበረሰብ ማቆጥቆጡን አብስሯል:: ምንም እንኳን ዋነኛው ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› ገና ቢሆንም፣ አዲሱ ሲቪል ማኅበረሰብ፣ ሴዑልንና ሌሎች ትላልቅ ከተሞችን ማዕከላቱ አድርጎ ማቆጥቆጥ ጀምሮ ነበር:: ስለዚህ፣ “የሚያዝያ 19 አብዮት” በ1950ዎቹ መጨረሻ ባቆጠቆጠው የከተማ ሲቪል ማኅበረሰብ ላይ የተመሠረተ ነበር:: “የሚያዝያ 19 አብዮት” የ‹ኢ ሲንግ ማን› አምባገነን አገዛዝ ከሌላው የማኅበረሰብ ክፍሎች

ቁጥር 007

ወደ ዕቅድ ለመግባትና የአገር ዕቅድ ሆኖ ለመቅረብ መጀመሪያ ፓርቲው አሸንፎ ሥልጣን ይዟል ወይ? የጥምረት መንግሥት ነው ወይ? የሚመሠርተው ተጣማሪው ፓርቲ የኢኮኖሚ መመሪያው ምንድን ነው? የሚሉት ጥያቄዎች ገና ጥሬ ናቸው:: ስመረጥ እሠራዋለሁ የሚለው ዕቅድ ከሆነም በመንግሥት ሀብት እና ንብረት የፓርቲ ፕሮግራም እና እቅድ ማዘጋጀትም ሕጋዊ አይደለም:: የዴሞክራሲን ሂደት የሚሸረሽርና የሌሎቹን ፓርቲዎች ተወዳዳሪነት የሚገድብ ነው:: በኢኮኖሚ አዲስ እቅድ ከመውጣቱ በፊት ያለንበት ሁኔታ በደንብ መታየት አለበት:: አሁን ያለው የመንግሥት ጉድለት (State Failure) ነው ወይስ የገበያ ጉድለት (Market Failure)? የሚለው ጉዳይ በደንብ መታየት አለበት:: ሲራራ፡- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኮኖሚውን በተመለከተ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴስ እንዴት ይገመግሙታል? አቶ ጌታቸው፡ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኮኖሚያዊ እቅዳቸውን ሲጠየቁ የሚሉት ነገር ተመሳሳይ ነው:: ለምርጫ ጊዜ ነው የማቀርበው ይላሉ:: ካወጣሁት ሌላው ይሰርቀኛል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው ያነሳሉ:: እኔ ግን ስለ አቅማቸው እጠራጠራለሁ:: ሙሉ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ይቅርና በትናንሽ ጉዳዮች እንኳን ድምፃቸውን ሲያሰሙ አይታይም:: ለምሳሌ በዋጋ ንረት ላይ ‹ለምን መጣ?› ብለው መንስኤዎችን የሚተነትን የተፎካካሪ ፓርቲ እስካሁን አላየንም:: ሽንኩርት ተወዳደ ሲባል ‹አዎ 20 ብር ገብቷል› ከማለት ውጭ ምን ተናግረተው ያውቃሉ:: ለምን 20 ብር ገባ ብሎ ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው? ብሎ የሚተነትንና መንግሥትን የሚሞግት ወይም ፖሊሲውን የሚተች ፓርቲም ይሁን ፖለቲከኛ የለም:: የተራቀቁት በማንነት ጥያቄ ላይ ብቻ ነው:: አብዛኛው ፖለቲከኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮን አይከታተልም፤ አያነብም፤ ቢያነብም እንኳን አይገባውምም፤ አይጠቀምበትምም:: አንድም ይህ አይሆንም መደረግ የለበትም ብሎ በኢኮኖሚ ጉዳይ የሚከራከር ፖለቲከኛ ገጥሞኝ አያውቅም::

ዴሞክራሲን የማስፈን... በዚህ የተነሳ የከተማ ሕዝብ ቁጥር በብሔራዊው ነጻነት ማግሥት ከነበረው 3.47 ሚሊዮን፣ በ1955 ወደ 5.28 ሚሊዮን አድጓል:: ማኅበራዊ ለውጦች የትምህርት መስፋፋትንም አስከትለዋል:: የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የገቡት ተማሪዎች ብዛት በ1945 ከነበረው 1.86 ሚሊዮን፣ በ1958 በእጥፍ ያህል ጨምሮ 3.62 ሚሊዮን ሆኖ ነበር:: በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በ1945 ከነበረው 7,800 በ1961 በዐሥራ አምስት እጥፍ ያህል ጨምሮ፣ እስከ 140,000 ደርሶ ነበር:: ከዚህ በተጨማሪም፣ በ1950ዎቹ ጋዜጦች እና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ተጽዕኗቸው እየገዘፈ ከመምጣቱም በላይ፣ የሕዝቡን በአምባገነኑ ሥርዓት መከፋትና ሥርዓቱ ላይ የሚሰነዝረውንም ትችት ለማሰራጨት በእጅጉ አስተዋጽዖ አድርገዋል::

1ኛ ዓመት

ከገፅ 16 የዞረ

የበለጠ ባመረሩበት ወቅት መሆኑና ያን ጊዜ የተባበሩ ግዙፍ እርምጃዎችን መውሰድ የሚችሉ ብቸኛ ቡድኖች በነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች መመራቱ ልብ ሊባል የሚገባው ሌላው ጉዳይ ነው:: የሆነ ሆኖ፣ እ.ኤ.አ በ1960 የተከሰተው የሚያዝያ 19 አብዮት ዴሞክራሲን የማስፈኑ ንቅናቄ ከታች መጀመሩን አብስሯል:: የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ከላይ የተሰጡና በፀረ ኮሚኒስቱ አምባገነን መንግሥት ለይስሙላ ብቻ የተቀመጡ እንዲሆኑ ሁሉ የተደረጉ ናቸው:: ሆኖም፣ በሚያዝያ 19 አብዮት ምክንያት፣ ዴሞክራሲ ከታች በተነሳ ዴሞክራሲያዊ ቅርፅ ዳግም ተወልዷል:: ነገር ግን፣ በየሚያዝያ 19 አብዮት የተገኘው ዴሞክራሲያዊ ሽግግር፣ በ1961 የ‹ፓርክ ቹንግ ሂ› ወታደራዊ መንግሥት በግንቦት 16ቱ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ሲጨብጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ተንኮታኩቷል:: ከዚያ ወዲያ፣ የደቡብ ኮሪያ ዘመናዊ ታሪክ በ‹ፓርክ› ወታደራዊ አምባገነን መንግሥት እና በተቃውሞ በዘለቀው የ‹ዴሞክራታይዜሽን› ንቅናቄ መሃል በተፈጠሩ ግጭቶች እና ፍጥጫዎች የተሞላ ሆነ:: በየሚያዝያ 19 አብዮት እና በግንቦት 16 መፈንቅለ መንግሥት ወደ ፖለቲካው መድረክ ብቅ ያሉት ተማሪዎችና ወታደሮች በእነዚያ ግጭቶች እና ፍጥጫዎች ላይ የመሪነት ሚና ተጫውተዋል::

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ማስታወቂያ

21

22 ሕግ ፍትሕ አስተዳደር

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007

ከሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር የት ላይ ነን? ያው የቀድሞዎቹ ናቸው::

በቅርቡ ከተቋቋመው ‹መድኅን የሰብአዊ መብቶችና የልማት በጎ አድራጎት ድርጅት› ሥራ አስኪያጅ አቶ በላይነው አሻግሬ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል:: አቶ በላይነው አሻግሬ ጠበቃና የሕግ መምህር ናቸው::

የተሻሻለው ሽብርን ለመከላከል የፀደቀው አዋጅ እስካሁን ታትሞ የወጣ አይመስለኝም፤ እኔም አዋጁን ለማየት ብጠይቅ አልታተመም ተብያለሁ፤ ስለዚህ የመጨረሻ ገዥው የአዋጁን ድንጋጌዎች ይዘት ማግኘት አልቻልኩም:: ነገር ግን በረቂቅ እና በውይይት ሂደት ላይ እያለ ረቂቁን የማግኘት ዕድል ነበረኝ:: በዚያ ረቂቅ የፀረ-ሽብር ሕግ መሠረት ከቀድሞው አዋጅ ቁጥር 652/2010 በርካታ በጎ የሚባሉ ማሻሻያዎችን አይቼበታለሁ::

ሲራራ፡- በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ምን ይመስላል? አቶ በላይነው፡- እንግዲህ የሰብአዊ መብቶች ስንል አሁን ባለው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በምዕራፍ ሦስት ሥር በ33 አንቀጾች የተዘረዘሩት እና ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውና የፈረመቻቸው የዓለም ዐቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችን የሚያጠቃልል ነው:: ሁሉም የሰብአዊ መብቶች አፈጻጸማቸው በመብቶቹ የዕድገት ደረጃ እና ከመንግሥት በሚጠበቀው ግዴታ ልክ መብቶቹ የተለያዩ ናቸው:: በደረጃ ስንመለከታቸው የመጀመሪያ ትውልድ፣ ኹለተኛ ትውልድ እና ሦስተኛ ትውልድ ሰብአዊ መብቶች ተብለው እንደሚከፋፈሉ ይታወቃል:: መንግሥት የሰብአዊ መብቶችን በተመለከተ ያለበትን ግዴታ እንደ መነሻ አድርገን ስንወስድ ደግሞ ሰብአዊ መብቶችን የሚከበሩ፣ እንዳይጣሱ የሚጠበቁ እና መንግሥት እንዲያሟላቸው የሚጠየቁ ናቸው:: አንዳንዶቹ የሰብአዊ መብቶች በፍጥነት መስተካከል ወይም መከበር የሚሹ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ እንዲሟሉ ወይም እንዲጠበቁ ረዘም ያለ ጊዜ የሚሹ ናቸው:: ስለዚህ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ስናነሳ እነዚህን ጉዳዮች ግምት ውስጥ በማስገባት ነው:: ወደ ኢትዮጵያ ጉዳይ ስንመለስ፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም:: እያንዳንዱን የሰብአዊ መብቶች እንዴት ባለ ሁኔታ እየተያዙ ነው የሚለውን መፈተሽ ይቻላል:: እስካሁን ድረስ ዜጎች በሕይወት የመኖር መብታቸው፣ አካላቸው በደኅንነት ተጠብቆ የመቆየት መብታቸው፣ የተረጋጋ ኑሮ የመኖር መብታቸው፣ ገደብ የሌለበት ከቦታ ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴ፣ ያለ ወንጀል ጥፋት ያለመታሰር መብት፣ የአካል ደኅንነት መብት፣ ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ትምህርት የማግኘት መብት፣ የንብረት መብቶች፣… እነዚህን እና ሌሎችን መብቶችን ስንመለከት፣ አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ገና በዝቅተኛ ደረጃ ያለ ስለመሆኑ ከኛ ከዜጎች በላይ ምስክር የለም:: በአገራችን ውስጥ ስንመለከተው የከረምነው ሕዝብን በጅምላ የማፈናቀል፣ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የማፈናቀል፣ ተማሪዎች ታፍነው የት እንደደረሱ እንኳ የማይታወቅበት፣ ለዚህም ትክክለኛ መረጃ ከመንግሥት ማግኘት አለመቻሉ፣ በዜጎች ላይ የሚፈፀመው አሰቃቂ ግድያ፣ የቤተ-አምልኮዎች መቃጠል፣ ሕግ ተላላፊዎች ምንም ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው መቀመጣቸው፣ የዜጎች ንብረት መውደም፣… ብዙ መዘርዘር ይቻላል:: እነዚህ ሁሉ የሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ ሁሉም ሕዝብ እየተመለከተ፣ መንግሥትም እነዚህን የሰብአዊ መብቶች እንዲያስከብርለት እና እንዲጠብቅለት በተደጋጋሚ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲጠይቅ ኑሯል:: ጥያቄውን በአጭሩ ለመጠቅለል ያክል የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በአገራችን ገና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው:: ሲራራ፡- በሕገ መንግሥት ደረጃ ስለ ሰብአዊ መብቶች ብዙ ቢባልም በተግባር ሰፊ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው:: ምክንያቱ ምንድን ነው ይላሉ?

ሲራራ፡- ከሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር እነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከመጡ ወዲህ የታዩ በጎ ለውጦች ምን ምን ናቸው? የሚቀሩትስ ምንድን ናቸው?

አቶ በላይነው፡- የሰብአዊ መብቶችን በትክክል የማስፈፀም ችግር ማለትም የማክበር፣ የመጠበቅ እና የማሟላት ጉዳይ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች አሉት:: የመጀመሪያው መንግሥት ራሱ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር በቂ ቁመና ያለው አይመስልም:: ነበረው ብለን ብንነሳ እንኳ የሰብአዊ መብቶችን ከማክበር ይልቅ የራሱን የሥልጣን ኮርቻ ከማደላደል ላይ ነው ትኩረቱ:: በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቹ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ሕገ መንግሥታዊ መሠረት አለው ብዬ አስባለሁ:: ምክንያቱም የፌዴራሉም ሆነ የአንዳንድ ክልሎች ሕገ መንግሥቶች ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝምን የሚከተሉ በመሆኑ፣ የተለያዩ ክልሎች የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆችን ከክልላችን ውጡ ለማለት በቂ መሸሸጊያ ሆኗቸዋል:: ስለዚህ በሰላም የመኖር መብት፣ ንብረት የማፍራት መብት፣ ያለ ገደብ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት እና የመኖር መብት፣ የአካል ደኅንነት እና በሕይወት የመኖር መብት፣ በዚህ ሕገ መንግሥታዊ መርህ መሠረት እየተጣሰ እንደሆነ መናገር ይቻላል:: ለዚህም ነው የችግሩ ምክንየት ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው ነው ያልኩት:: በመቀጠል ደግሞ አንዳንድ ሐሰተኛ የታሪክ ትርክቶች እና አረዳድ ብዙ ፈተና እንዳመጣ የሚታወቅ ነው:: ይኸውም የአማራን ሕዝብ በታሪክ ጨቋኝ እንደሆነ ከ1950ዎቹ ወዲህ ሲተረክ የነበረው የተጣመመ የታሪክ አረዳድ አሁን ላለንበት መመሰቃቀል ያደረገው አስተዋጽዖ ቀላል አይደለም:: የአማራን ሕዝብ ከዚህ ጋር ለይቼ መናገሬ፣ አንደኛ መንግሥት ይህን ለዘመናት ፕሮፓጋንዳ ሲሠራበት የኖረ እና ለካድሬዎች ማሰልጠኛ የሆነ ስለሆነ ሲሆን፣ ኹለተኛ ደግሞ የአማራ ሕዝብ በዚህ የተዛባ የታሪክ አረዳድ ተጨባጭ ጉዳት ስለደረሰበት ነው:: በዚህ ምክንያት አማራ እንደ አንድ ሕዝብ፣ ሌሎች ደግሞ ከፊል የሰብአዊ መብት ጥሰት ገጥሟቸዋል:: ዞሮ ዞሮ የታሪክ አረዳድ ለሰብአዊ መብቶች አለመከበር የራሱ ሆነ አስተዋጽዖ አለው ለማለት ነው:: ሌላው ደግሞ የመንግሥት ልፍስፍነት ነው:: እንደሚታወቀው መንግሥት የሕዝብን

ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ሙሉ ኀላፊነት አለበት:: ይህ ኀላፊነት የማንኛውም መንግሥት ተቀዳሚ ኀላፊነት ነው:: ነገር ግን መንግሥት ይህን ኀላፊነቱ ካልተወጣ ለበርካታ የሰብአዊ መብቶች መጣስ ምክንያት ይሆናል:: ሕዝብ በግፍ የሚገደለው፣ ሰው በደቦ የሚገደለው፣ በግፍ ከቀዬው የሚፈናቀለው፣ አብያተ ክርስቲያናት እና መስጎዶች የሚቃጠሉት፣ ሰው በሰላም ውሎ መግባት የማይችለው መንግሥት ሕዝቡን የመጠበቅ ግዴታውን ስላልተወጣ ነው:: ይህ ሁሉ ችግር ደግሞ በአንድ በኩል የመንግሥት አቅም ማጣት ነው ሲባል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ከዚህ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጀርባ ምን ትርፍ እያገኘበት ነው የሚል ጥያቄን መፍጠሩ አይቀርም:: አጠር ሲደረግ ግን መንግሥት በራሱ አቅመ-ቢስነት ወይም መንግሥታዊ ግዴታውን አለመወጣቱ እንደ አንድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት ሊወሰድ ይችላል:: ሲራራ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት “አሸባሪዎች እኛ ነን፤ ከዚህ በኋላ አጣርተን ነው የምናስር” ብለው ነበር:: ሆኖም የፀረ ሽብር ሕጉ አሁንም አልተሻሻለም:: በርካታ ሰዎችም እየተጠየቁበት ነው:: ይህ እንዴት ይታያል? አቶ በላይነው፡- እርግጥ ነው ዐቢይ አሕመድ “አሸባሪው መንግሥት ነው” ብለዋል:: ደግሞም ነው:: እንደ መረጃ ያክል የቀድሞው የፀረ-ሽብር ሕግ (አዋጅ ቁጥር 652/2001) መሻሻሉን አውቃለሁ:: ይህ አዋጅ ከ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በክለሳ ላይ ቆይቶ አሁን በቅርቡ መፅደቁን ይታወቃል:: ነገር ግን አዋጁ ፀድቆ እስኪወጣ ድረስ በርካታ ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች በዚህ በተነቀፈ አዋጅ ተከስሰው እንደነበር ይታወሳል:: አሁን ያለው አገዛዝ (ብልጽግና ፓርቲ) ከስም በስተቀር የቀድሞው (ኢሕአዴግ) እንደሆነ ሊዘነጋ አይገባውም:: ስለዚህ ቀድሞው አዋጁ ንጹሐን ሰዎችን ማጥቂያ እንደሆነው ሁሉ እስኪሻሻል ድረስ አገዛዙ ማጥቃት የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች ቢያጠቃበት የሚገርም አይደለም:: ቅድመ ዐቢይ ያው ኢሕአዴግ፤ አሁንም ስሙ እንጅ ያው ብልጽግና፤ አመራሮቹም ከሕወሓት አመራሮች በስተቀር

አቶ በላይነው፡- ሁላችንም የምናውቀውና መዘንጋት የሌለብን ነገር ከዶ/ር ዐቢይ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በፊትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ኢትዮጵያን እየመራ ያለው ድርጀት ያው የቀድሞው ኢሕአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ ነው:: ከዐቢይ መምጣት ወዲህ በጉልሕ የታዩ ለውጦች እንዳሉ ሁሉ ከእሱ በፊት ከነበሩት አመራሮች የባሰ እንዳለ ደግሞ የማይታበል ሐቅ ነው:: ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ወዲህ በተለይ ሁሉም የፖለቲካ ኀይሎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው እንዲታገሉ ወይም እንዲያታግሉ መደረጉ፣ በፕሬስ ላይ የነበረው አፈና ላላ ማለቱ፣ አንዳንድ አፋኝ አዋጆች እንዲሻሻሉ መደረጋቸው፣ ከኤርትራ ጋር የነበረው የጦርነት ሁኔታ መቋጨቱ እና ሰላም መውረዱ፣ የተለያዩ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር መፈታታቸው እንደ በጎ ለውጥ ልንወስደው እንችላለን:: ከዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ግን እነዚህ ለውጦች በሕዝብ ትግል እና መስዋዕትነት የተገኙ እንጅ አገዛዙ ፈቅዶ ያመጣቸው አለመሆናቸው ነው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ እንደሚነገረው በአገዛዙ ውስጥ ያሉትን አመራሮች እና ለውጥ ላይ ነን የሚሉትን ከራሳቸው አገዛዝ ጭቆና ያላቀቃቸው የሕዝብ መስዋዕትነት መሆኑ ነው:: ለውጥ አለ ቢባል እንኳ አሁንም ያ ለውጥ የሚባለው አሁንም በአገዛዙ መዳፍ ውስጥ ያለ መሆኑ፣ የሕዝብ መስዋዕትነት ዳር ሳይደርስ እንዳይቀጭ ያሰጋል:: በርግጥ የሕዝብን የለውጥ መስዋዕትነት በአደራ ተረክቦ፣ አስቀጥሎ የሚጠበቀውን ትክክለኛ የለውጥ ፍላጎት ሊያሳካ የሚያስችል መስተጋብር እና ታማኝ ተቋም ነበረን ወይ ለማለት አያስደፍርም:: ከዐቢይ ሹመት ወዲህ ምን ይቀራል የሚለው ጥያቄ በተመለከተ፣ አዎ! ብዙ ነገር ይቀራል:: ምንስ ተጀመረና! ሕግ ማሻሻል አንዱ መንገድ እንጅ የጉዞ መጨረሻ አይደለም:: ሲቀጥል ደግሞ አሁንም ለውጡን እመራለሁ የሚለው ያው አገዛዝ በመሆኑ ወደ ቀድሞው መገለጫ ባሕርይው እንደማይመለስ ምንም ዋስትና የሚሆን ነገር የለም:: ይህንንም በከፊል አይተነዋል:: ሰዎች ያለ በቂ ማስረጃ በእስር እንዲማቅቁ ተደርገዋል፤ የፖለቲካ ዝንባሌያቸው ብቻ ታይቶ የታሰሩት በተለይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ አመራሮች እና ደጋፊዎች እስራት በቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም:: በዚህ ጉዳይ ላይ ድርጅቱ (አብን) በተለያየ ወቅት የሰጣቸው መግለጫዎች ማየት በቂ ነው:: ሌላው ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሕዝብ ተረጋግቶ እየኖረ ነው ለማለት አይቻልም፤ አብዛኞች ነገ ምን ይፈጠር ይሆን? ንብረታችን ይወድም ይሆን? ቤታችሁ ይፍረስ ወይም መኖሪያችሁን ለቃችሁ ውጡልን እንባል ይሆን? በሚል ስጋት ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ ቁጥሩ ቀላል አይደለም:: ወደ ገፅ 19 ዞሯል

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ይህ የሕዝብ ስጋት ተራ ስጋት አይደለም፤ ይልቁንም ራሱን የቻለ ተደጋጋሚ ድርጊት ስለታየ ነው:: ከዶ/ር ዐቢይ ሹመት ወዲህ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ለዘመናት ሲኖርበት ከነበረው መኖሪያው ለቀህ ውጣ እየተባለ ለአስከፊ መፈናቀል እና እንግልት ተዳርጓል:: በዚህ በኩል ሕዝብ ምንም የኑሮ ዋስትና የለውም:: እንዲያውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ተፈናቃይ ብዛት ከሶሪያ በልጣ መገኘቷ ይታወሳል:: ይህ ለብዙ ሺሕ ዓመታት ተቻችሎና ተከባብሮ ለኖረ ሕዝብ ከባድ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው:: ሌላው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ያለው የተማሪዎች መፈናቀል ጉዳይ ነው:: እንደሚታወቀው በዚህ ዓመት በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለይም ደግሞ የአማራ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መማር ባለመቻላቸው ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው ይታወቃል:: እስካሁን ድረስ እነዚህ ተማሪዎች እንደተበተኑ ናቸው፤ መንግሥት ለእነዚህ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ ተማሪዎች መፍትሔ ሳይሰጥ ይኼው ሰባተኛው ወር እየተጋመሰ ነው:: በዚህ መሃል ከዩኒቨርሲቲ ተፈናቅለው ወደ ቤተሰብ የሚመለሱ ተማሪዎች ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ሰለባ ሆነዋል፤ አካላቸው ጎደሉ አሉ፤ የሞቱም አሉ:: ታፍነው አሁን ድረስ የት እንዳሉ የማይታው በርካታ የአማራ ተማሪዎች እንዳሉ እና መንግሥትም ለነዚህ ለታፈኑ ተማሪዎች ምንም ሳይደርስላቸው፣ የት እንዳሉ እንኳ ለተማሪዎች ቤተሰብ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይሰጥ እስካሁን ድረስ አለ:: ይኸው ችግር በዚሁ ከቀጠለ ይልቁንም ከሥር ከሥር አስተማማኝ መፍትሔ ካልተሰጠው በሚቀጥለው ዓመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ተማሪዎች እንዴት እንደሚቀጥሉም በሙሉ ልብ መናገር የሚቻል አይመስለኝም:: ጠቅለል ባለ መልኩ የሕዝብ ደኅንነት ማረጋገጥ አልተቻለም:: ሌላው መነሳት ያለበት ኢኮኖሚያዊ ችግር የወጣቱ ሥራ አጥነት ነው:: በአገራችን በየዓመቱ ከስድስት መቶ ሺሕ በላይ የዩኒቨርሲቲ፣ የኮሌጅ እና የቴክኒክ ምሩቃን ትምህርት ጨርሰው ወደ ሥራ ዓለም ይቀላቀላሉ:: ነገር ግን ይህን የተማረ የሰው ኀይል ለመቀበል የሚያስችል የሥራ ዕድል የለም:: ያለው የአምራች ዘርፍ ይህን ያክል የተማረ

ሕግ ፍትሕ አስተዳደር 23

ቁጥር 007

የሰው ኀይል ለመቀበል የሚበቃ አይደለም:: በዚህ ምክንያት ሥራ ፈላጊው ወጣት ከዓመት ዓመት እየተከማቸ ይሄዳል፤ መንግሥት ደግሞ ሥራ አጥቶ ለሚቸገረው ወጣት አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር አልቻለም:: ወጣቱን ከዚህ ከመነቸከ የፖለቲካ አዙሪት አውጥቶ ሠርቶ የራሱንም የአገሪቱንም የኢኮኖሚ ችግር የሚያቃልልበት መንገድ ካልተፈጠረለት ይኸው ወጣት ሌላ ጫና እንደሚሆን ማንም አይስተውም:: እና በየዘርፉ ሌሎች ገና ብዙ የሚቀሩ ጉዳዮች አሉ:: ሲራራ፡- በቅርቡ ‹መድኅን የሰብአዊ መብቶችና የልማት በጎ አድራጎት ድርጅት› የተሰኘ አዲስ ድርጅት አቋቁማችኋል:: የተቋሙ ዓላማዎች ምን ምን ናቸው? አቶ በላይነው፡- ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ኹለት ዐበይት ዓላማዎች ያሉት ሲሆን፣ በውስጡ ደግሞ አምስት ንዑሳን ዓላማዎች አሉት:: ሰብአዊ መብቶች እና ልማት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው:: ንዑሳን ዓላማዎቹ ደግሞ በመጀመሪያ፣ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተደነገጉት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ሁሉም የአገሪቱ ዜጎችና እኩልና ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክትትል በማድረግ ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በአጋርነት መሥራት ነው:: ኹለተኛው ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውና ያፀደቀቻቸው አሕጉራዊና ዓለም ዐቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በተግባር እንዲረጋገጡ መሥራት ነው:: ሦስተኛው፣ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የግጭት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ጥናት ማድረግ፣ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በሕግና በፍትሕ አግባብ እንዲፈቱ መሥራት ነው:: አራተኛው፣ ዜጎች ስለ ሰብአዊ መብቶች ምንነት እንዲያውቁ በብዙሃን መገናኛዎችም ሆነ ፊት ለፊት የግንዛቤ ትምህርት መሥጠት፣ መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩና እንዲከበሩላቸው መሥራት ነው:: አምስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚያዳብሩ የተለያዩ የምጣኔ ሀብትና የሥራ አማራጮችን ማሳየት፣ ጥናት ማድረግና የሕዝቡ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዲያድግ መሥራት ናቸው::

የልኂቃን ውድቀት ዋና ዋናዎቹን የሕዝብ ጥያቄዎች ተቀብለው ለመፍታት ጥረት እያደረጉ አይደለም:: ከዚያ ይልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ አክቲቪስት የሚያነሳቸውን አጀንዳዎች በመለቃቀም በአላፊ-ጠፊ አጀንዳዎች ላይ ሲንጠላጠሉ ይስተዋላል:: ድርጅቶቹ አንዱ ሌላውን የሚጎነትል መግለጫ በማውጣት ላይ የተጠመዱት የአክቲቨስቶችን ቀልብ ለመሳብና ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሆነ በደንብ ይታወቃል:: ዘለቄታዊ በሆኑና ሕዝብ ሊጠቅሙ በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ ሳይሆን የማኅበራዊ ሚዲያ ፊት እያዩ በጭፍጫፊ ጉዳዮች ለማተኮር የተገደዱት አዳዲስ አስተሳሰቦችንና አሠራሮችን የማፍልቅ አቅማቸው ስለመከነ እና ስላረጡ ነው:: በመሠረቱ፣ የሁለቱም ድርጅቶች ቦታ መንግሥታዊ ሥልጣን ሳይሆን የታሪክ ቅርጫት ብቻ ነው::

ወልቃይትና ራያ፤ የአጭር ጊዜ መፍትሔ በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል:: ዜጎች በትግራይ ልዩ ኀይል አልሞ ተኳሾች በጠራራ ፀሐይ እየተገደሉና ታፍነው እየተወሰዱ ሲሆን፣ ሁለቱን ክልሎች የሚያገናኙ መንገዶችም እየተዘጉ ነው:: ውጥረቱ ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊመከር ሊዘክር ይገባል:: ከሁሉ በላይ ደግሞ የሁለቱ ዘውጌ ማኅበረሰቦች ልኂቃን ከገቡበት አረንቋ ወጥተው የችግሩ ሳይሆን የመፍትሔው አካል እንዲሆኑ ያስፈልጋል:: በኹለቱ ክልሎች መካከል የሚከሰት ግጭት ከፍ ያለ ውድመት እንደሚያስከትል ሳይታለም የተፈታ በመሆኑ ጉዳዩ በመንግሥትም በኩል ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል:: በእኔ አስተያየት የወልቃይትና ራያ ጥያቄ ሁለቱን ክልሎች ወደ ግጭት ሊስገባቸው



በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ሐምሌ 17 ቀን 2011 በመዝገብ ቁጥር 4307 ሕጋዊ ሰውነት አገኘ



ቦርድ-መር ድርጅት ሲሆን፥ አምስት አባሎች ያሉት ቦርድ የካርድ የበላይ ተጠሪ ነው



ካርድ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ፕሮጀክት (ኢሰመፕ/EHRP) የበለጠ ተደራጅቶ የፈጠረው ድርጅት ነው



ኢሰመፕ ከ2010 በፊት ከ50 በላይ የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞችን የፍርድ ቤት ሒደት ሲከታተል እና ሲዘግብ የነበረ የሰብኣዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን፣ የተለያዩ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን መግለጫዎች ሲያዘጋጅ ከርሟል



ካርድ ዜጎችን ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ የሕዝብ ተወካዮች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚበጁ ፖሊሲዎችን እንዲያወጡ ይታገላል

አይገባም:: ጉዳዩ በንግግር፣ የሁለቱን ወንድም ሕዝቦች አብሮነትና ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ ነው ሊፈታ የሚገባው:: ይህ ደግሞ በሁለቱም ወገን በኩል ቅንነቱና ቁርጠኝነቱ ካለ በደንብ ይቻላል:: እንደ መነሻ ወይም እንደ አጭር ጊዜ መፍትሔ ሊቀመጥ የሚገባው፣ በእነዚህ አካባቢዎች ትግርኛና አማርኛ ቋንቋዎች በጋራ የመንግሥት ተቋማት የሥራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው:: የፖለቲካ ኀይሎችና ልኂቃኑ አርቆ የማሰብ አቅማቸው እጅግ ደካማ ስለሆነ ነው እንጂ አማርኛም ትግርኛም ተመሳሳይ ፊደል የሚጠቀሙ፣ ሁለቱም በርካታ የግዕዝ ፊደላትን የሚወርሱ እህት ቋንቋዎች ስለሆኑ፣ በድንበር አካባቢ በሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ ትግርኛና አማርኛ የጋራ የሥራ ቋንቋዎች ቢሆኑ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጅ የሚሆን ወገን የለም:: ወልቃይትና ራያ ውስጥ አማርኛ ቋንቋ በመንግሥት ተቋማት እንዳይሠራበት ማድረግ ፀረ-ዴሞክራሲያዊነት ብቻ ሳይሆን፣ በኹለቱ ክልሎች መካከል የማይበርድ ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሚሆን ጠንቀኛ አካሄድ ነው:: መታረም አለበት:: ከፍ ብየ እንደገለጽሁት [የአጭር ጊዜ] መፍትሔው ኹለቱንም ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ ማድረግ እና ሁሉም ዜጋ በፈለገውና በመረጠው ቋንቋ አገልግሎት እንዲያገኝ ማስቻል ነው:: እንዲህ ዓይነት አሠራር በብዙ የአውሮፓ አገሮች የተለመደና ትልቅ ሸክም የሚያስቀር የሰለጠነ መንገድ በመሆኑ ሊከብደን አይገባም:: ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ኬላዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ሲቪል ሰርቪሱ ወዘተ… በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ለሁለቱ ክልሎች ግንኙነት የመጀመሪያው መልካም እርምጃ ነው:: ዜጎች በሚችሉትና በሚፈልጉት ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ሙሉ መብት አላቸው:: ከእኛ የሚጠበቀው ያንን መብት ዕውቅና መስጠትና ወደ ተግባር መቀየር ነው::

ራዕይ • ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ተፈጥራ ማየት ተልዕኮ • የዴሞክራሲ መርሖዎችን በማስተጋባት ዴሞክራሲ ብቸኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጫወታ ሕግ እንዲሆን መሥራት ዓላማዎች • ዴሞክራሲያዊ ባሕል በኢትዮጵያ እንዲጎለበት በዴሞክራሲያዊ መርሖች ዙሪያ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መሥራት፣ • መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተጠያቂ እንዲሆኑ ወቅታዊ የመከታተል እና ግምገማ ሥራዎችን መሥራት፣ • አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን ለማምጣት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ምክክር እና ግፊት ማድረግ፣ • ለዴሞክራሲ ተቋማት ሙያዊ እና ቴክኒካዊ ድጋፍ ማድረግ፣ • የሰብኣዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ የፖሊስ ማቆያዎችን፣ ማረሚያ ቤቶችን እና ፍርድ ቤቶችን መከታተልና መገምገም፣ • ምርጫዎችን መታዘብ፣ የሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት መስጠት!

ከገፅ 12 የዞረ

24

ማስታወቂያ

ሲራራ

መጋቢት 12 2012

1ኛ ዓመት

ቁጥር 007