እኔና የስደት ጉዞዬ Flipbook PDF

እኔና የስደት ጉዞዬ
Author:  2

105 downloads 312 Views 39MB Size

Recommend Stories


Porque. PDF Created with deskpdf PDF Writer - Trial ::
Porque tu hogar empieza desde adentro. www.avilainteriores.com PDF Created with deskPDF PDF Writer - Trial :: http://www.docudesk.com Avila Interi

EMPRESAS HEADHUNTERS CHILE PDF
Get Instant Access to eBook Empresas Headhunters Chile PDF at Our Huge Library EMPRESAS HEADHUNTERS CHILE PDF ==> Download: EMPRESAS HEADHUNTERS CHIL

Story Transcript

እኔና

የስደት ጉዞዬ

1

እኔና

የስደት ጉዞዬ

2

ስለመጽሐፉ አስተያዬትም ሆነ ትችት ከታች ባለዉ የኢሜል አድራሻ ቢልኩልኝ አመስጋኝ ነኝ:

የደራሲዉ መብት በሕግ የተጠበቀ ነዉ

ከሞላ ይግዛው ሽበሽ. (አስማረ







e-mail. [email protected]

እኔና

የስደት ጉዞዬ

3

==ሁሉም ትዝታ ነዉ== እልም ያለዉ ጫካ ጊሚራ እንዴት ነሽ ለስድስት ቀናት የተኛንብሽ አንበሳዉ ሲያገሳ ዝሆን ሲተራመስ ወፎች ሲዘምሩ ባነድ ላይ ሲያወሩ ያስደስቱን ነበር ተኝተን ከዱሩ ትዝ አለኝ አኮቦ ወንዙ ሸንተረሩ የሰንብሌጡ ሣር ፋፋቴዉ ማማሩ ፍራሽ አላሻንም ስንትኛ ከሣሩ ኢትዬጵያ ሀገራችን ደንብሯን ተሻግረን በሰላሳ ቀናት ገባን ወደሱዳን የሱዳን በርሃ ጭልጥ ! ያለዉ ሜዳ ትንኝ ረግረጉ አይ ያየነዉ ፍዳ ረሃብ ቢጠናብን አጥተን የምንሆነዉ አንድ የገማች አዉሬ ከጅብ የተረፈች ነበር የበላነዉ እሷስ ምኗ ጠቅማ በጣም የተራብነ መራመድ አልቻልንም ዛዝለን ወደቅነ የሱዳን ወታደር የጥቁር ጎታታ









































ሩጦ ማያመልጥ ወይ ተኩሶ አይመታ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

እጁን እየላሰ ሲሆን ማታማታ ከስቃይ ላይ ጣለን ከርሃብ በሽታ ግን ጥሎ አልጣለንም አምላክ ረዳነ ገሤ አዉሬ ገድሎ ነብሳችን አዳነ

ትዝ ይለኛል ካርቱም ሞቃታዉ አገር ኖርነዉ ሁለት ወራት ምንም ሳንናገር ቢቸግረን ጊዜ ግራ ቢገባን ለሁለተኛ ስደት ዬጋንዳ ተጓዝን

በነጭ ዓባይ ጉዞ ለሃያሁለት ቀናት ገንፎአችን አለቀች ካርቱም የገዛናት ግን ችግር ነዉና ተታግለን ደረስናት

እንዴት ነሽ ዩጋንዳ የኢዲአሚን ሀገር ነፃም አልተለቀቅን ኑሮ እስር ቤት ነበር ትዝ አለኝ ካምፓላ ያች እስር ቤታችን ያራገፍንባቱ ቅማል በላያችን

ያች እስር ቤታችን ከምድር በታች ለሥድስት ወራቶች ቤታችን ሆነች ቆራጣ ብርድ ልብስ ቅማል የሞላባት





































ከወዲያ ከወዲህ ስንጎታትታት

4

እኔና

የስደት ጉዞዬ

አስታዉሳታለሁ እሷም ትዝታ ናት ያች ጠባብ ክፍል ጣዉላ ላይ ምኝታ እንሞላት ነበረ ሲሆን ማታ ማታ

ያ !! መጥፎ ወታደር ጨካኝ አረመኔ በሚይዘዉ ዱላ ወገኑን ሲገርፈዉ ዓይኖቹን ሲያጠፋዉ ጥርሶቹን ሲያወልቀዉ አስታዉሰዋለሁ እሱም ትዝታ ነዉ

የ አሚን አስተዳደር የሌለዉ ስርዓት ለሰሚዉ ይገርማል ባወራ ተረት ምግብ ትልቅ ሆቴል መኝታ እስር ቤት

አሁን ይገርመኛል አልፎ ሳስታዉሰዉ ከእሣት ወደ እረመጥ እንዴት ይሄዳል ሰዉ

ሁሉም ነገር ያልፋል ጊዜዉን ጠብቆ የማይረሳዉን ትዝታዉን ትቶ



























====================

5

የስደት ጉዞዬ

6

መታሰቢያነቱ

ከተለየኋት ጊዜ ጀምሮ እኔን በህይወት እስክታገኝ ድረስ ጫማ ሳትለብስ በባዶ እግሯ እየሄደች : ከአልጋ ላይ አልተኛም ብላ መሬት ላይ እየተኛች ሌት ተቀን እኔን በሰላም እንዲያገናኛት አምላኳን ስትማፀን ለኖረችው መተኪያ የማላገኝላት ዉድ እናቴ ወ/ሮ ነጠረች ኃይሉ: እና ለአባቴ ግራዝማች ይግዛው ሽበሽ እንዲሁም

የእናቴ ምትክ ለሆነችዉ ዉዷ ባለቤቴ ዓለምፀኃይ ተፈራና ልጆቻችን ሚካኤል ሞላ አዳም ሞላና ለመጽሐፉ ሽፉን ዲዛይን በማድረግ ለረዳችኝ ልጄ ታምራለች ሞላ:: እናም ከስድስተኛ እስከ 11 ኛ ክፍል ከሱ ጋር ሆኜ እንድማር ለረዳኝ የናቴ ታናሽ ወንድም ለኔ አጎቴ አቶ በላቸው ጌታሁን መታሰቢያ ይሁንልኝ ለስደተኛው ጓዴ ገሠሠ ዲባባ እንዲሁም በዩጋንዳ ፖሊሶች በግፍ ተኮላ ና ስምረት ብርሃኑ::

ለተገደሉት የስደት ጓዶቼ ለአቶ













በተጨማሪም ለኢትዮጵያን ሕዝብ ውርደትና የሀገርን ውድቀት አናይም በማለት ወያኔን ሲታገሉ ታሪክን በደማቸው እየጻፉ ለተሰውና በእስር ለተሰቃዪ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ለሆኑት የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ::



እኔና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

7

ምስጋና ፣ ይህችን አጭር እኔና የስደት ጉዞዬ በሚል በስደት ውጣ ውረድ ህይወቴ ዉስጥ የገጠመኝን አስቸጋሪ ፈተናዎች እና አደጋዎች አልፌ አሁን ላይ ሆኜ አንደ ታሪክ ለመዘከር ላበቃኝ አምላክ ምስጋና ይድረሰው :: መጽሐፏን እንድጽፍ ላበረታታኝና አንዳንድ የተሳሳቱ አባባሎችን በማረምና ቃላቶችን በማስተካከል ለረዳኝ ውድ ጓደኛዬ :







ለአቶ ተሰማ ገልጋይ ገሠሠ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

8

መግቢያ ይህ እኔና የስደት ጉዞዬ: በሚል የተጻፈ አጭር እዉነተኛ የህይወት ዉጣ ዉረዶችን የሚተርክ መጽሐፍ ሚያዝያ 27

ከጅማ

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ: ጊሚራ አዉራጃ

ሚዛን ተፈሪ ዘምቶ፣

የደቡብ ሱዳን በርሃን

ለ36 ቀናት

በእግሩ ተጉዞ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ይገባና እንደገና ለሁለተኛ ሥደት በነጭ ዓባይ ወንዝ በመርከብ ተጉዞ:

ላይ ለ22 ቀናት

ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን አልፎ

በጭነት መኪና ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ከደረሰ በኁላ በካምፓላ ማዕከላዊ እስር ቤት (Kampala Central police station) ለ6 ወራት ከታሰረ በኋላ በአምባ ገነኑ ፕረዘዳንት ኢዲ አሚን ዳዳ ፊት ቀርቦ በተደረገለት ምህረት ይፈታል:: ካምፓላ ለ3 ዓመታት በዩጋንዳ ቴክኒካል ኮሌጅ የኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ትምህርቱን አጠናቆ ኬኒያ ናይሮቢ በፊሊፕስ ካምፓኒ ሁለት ዓመት ከሰራ በኋላ ለሦስተኛ ስደት በአይሮፕላን በሮ ጀርመን ገብቶ በሀምበርግ ከተማ በሜዲያ ኤሌክትሮኒክስ ቴክኒክ ትምህርቱን አጠናቆ እንደገና ለአምስተኛ ስደት ስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የመጨረሻ የሥደት አገሩ ይደርሳል።







ለብዙዎች ስደት እንደ አንድ የጥሩ ኑሮ መፈለጊያ ዘዴ አድርገዉ የሚመለከቱት አሉ ፣እርግጥ ነዉ ሥደትን ለጥሩ ኑሮ መፈለጊያም የሚጠቀሙበት በርካቶች ይኖራሉ ነገር ግን ስደት በጭንቅ ጊዜ ህይወትን ለማዳን የሚደረግ የጭንቅ ጊዜ ምርጫ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

9

በዚህ ምክንያትም መንግሥታቱ ሥደትን በሁለት ይከፈሉታል አንደኛዉ አገር ዉስጥ በሚደረግ የፖለቲካ ፍትጊያ በሥልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት በሰዉየዉ ወይም በሴትዬዋ ላይ የመኖር መብቱን ወይም መብቷን ገፎ ህይወታቸው አደጋ ላይ ትወድቅና የመጨረሻ የመኖር መፍትሄዉ ተወልደው ያደገበትን አገርና ወላጅ ዘመዶቹን ጥሎ በድንገት ሕይወትን ለማዳን የሚደረግ ሥደት ሲሆን: በተባበሩት መንግሥታት የጀኔቫዉ ስምምነት (The 1951 Refugee Convention ) መሰረት አንድ ሰዉ ባለዉ የፖለቲካ ወይም በእምነቱ ምክንኒያት ባለዉ መንግሥት ሊደርስበት የሚችለዉን የሰዉ ልጆች መብት የሚጥስ ሁኔታ ሲፈጠር ከዚህ ለማምለጥ በሆነ መንገድ አገሩን ጥሎ የሚሲሰደድ ነው:: ሁለተኛዉ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ የሚደረግ የሥደት ዓይነት ( economic refugee ) የሚባለው ነዉ : እነዚህ ሁለት ዓይነት ተሰዳጆች ምክንያታቸዉ ቢለያይም ከየደረሱበት ሀገር የሚገጥማቸዉ ችግር ተመሳሳይ ነዉ :: ሁለቱም በየደረሱበት ሀገር

ህብረተሰቡ ያለዉን ቋንቋና

የኑሮ ሥርዓት ለመለማመድ እንደገና እንደ መወለድ ሀ ብሎ ማንኛዉንም ነገር መማር ግድ ይላል: በዚህም ምክንያት የብዙዎች ህይወት የተወሳሰበና ችግር የበዛበት ይሆናል። በሥደት ዓለም ዉጤታማ ለመሆንና በቶሎ ከህብረተሰቡ ጋር ለመዋሃድ ዋናዉ ያለህን ክብር፣ አትንኩኝ ባይነትና ኩራትን





ወደኋላ አዉልቆ መጣል ያስፈልጋል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

ይህ ከሆነ ብቻ ነዉ የሰጡትን

10

ሥራ ሠርቶ በቀላሉ

ክሕብረተሰቡ ጋር ተግባብቶ ጥሩ መኖር የሚቻለዉ:: ስደት ሁሉንም እኩል በአግዳሚ ወንበር የሚያስቀምጥ ትልቅና ባገራቸው የተከበሩትን ሁሉ እኩል የሚያይ

ነው::

በስደት ዓለም እኔ የተማርኩ የተከበርኩ ጥሩ ሥራና ጥሩ ኑሮ እኖር የነበርኩ እንዴት ያለ ሙያዬ ይሄን ሥራ እሰራለሁ የሚል ከሆነ ችግር ላይ ይወድቃል:: በመሆኑም ሥደት አዋራጅ በመሆኑ የመጨረሻ ምርጫ ሲጠፋ ብቻ የሚወሰድ ዉሳኔ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ:: በርካቶች በዓየርም ሆነ በዉቅያኖስ ዉድና መተኪያ የለላት ህይወታቸዉን ቀብድ አስይዘው በሰላም ወደሚፈልጉት አገር መድረስ የቻሉ እድለኞች ናቸዉ። ይሁን እንጂ የሚገጥማቸውን መከራና ችግር

ብርድና

ቸነፈር : ርሃብና እንግልት: በጥበብና በጥንካሬ ተቋቁመው ከአሰቡት ቦታ የሚደርሱ በርካቶች ናቸው:: ምንም እንኳን የችግሩ ደረጃ ቢለያይም እኔም እንደነዚሁ የሚገጥማቸውን ዉጣዉረድ በህይወታቸዉ ተወራርደዉ ያሳለፉትን የችግር ዘመን ወደኋላ ለመመልከት ከቻሉት ሰዎች አንዱ በመሆኔ









አምላክን አመሰግናለሁ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

11

ምዕራፍ - 1

የጅማ አብዮት፣ ጊዜው የጃንሆይ መንግሥት ሊወድቅ የሚንገዳገድበት ጊዜ ነበር 1966 ዓ ም አጋማሽ ነው እድሜዬ 18 ና የሚይዝያ ሁለተኛ ደረጃ

ት /ቤት 11ኛ

27

ክፍል ተማሪ ነበርኩ።

ጓደኞቼም ከተለያዬ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰብን ነበርን:: እኔና ጓደኞቼ ለጥናት እንዲያመቸን ብለን በጋራ በግምት ከ5 ስኩየር ሜትር የማትበልጥ ክፍል ነበረችን። በዚህች ክፍል ዉስጥ የግል የሆነ ልብስም ሆነ ቆሳቁስ አልነበረም: ሁሉም የጋራ ሀብት ነበር ። ኃይማኖት : ዘርና ቋንቋ : የየራሳችን የግል ጉዳይ ሲሆን አማርኛ የሁላችን መግባቢያ ቋንቋ ነበር:: የአንድ ልጅ የወር ቀለብ ከቤተሰብ ሲላክለት የሁላችንም ደስታ ነበር ፣ ተያይዘንም መጀመሪያ ምግብ በልተን ከዚያም ሻሂ ቤት በመሄድ በራድ ሻሂና ቡሾች በቁጥራችን ይታዘዛል: ጫትም ይጨመርበታ ::

ከጫቱ ላይ እኔ ስለማልጋራቸዉ

ይናደዳሉ ብዙ ጊዜ እንድቅም ቢያግባቡኝም አልሆነም ፣









ወድጀም ሳይሆን አንድ ቀን ሞክሬዉ ስለታመምኩ ነበር።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

12

ከዚያም ጨዋታዉ ቀልዱ ከተካሄደ በኋላ ወዲያዉ ወደ ሀገራችን የፓለቲካ ሥርዓት ብልሹነትና በገበሬው ላይ የሚደርሰውን ስቃይ እያነሳን እንወያያለን ፣ በተለይም የነ ራሥ መስፍን ስለሽ ከገጠር

እስከ ከተማ መሬት በግል

በመያዛቸው የሚያወያዪን ጉዳይ ነበር :ይህም ስላልበቃቸዉ በጅማ ከተማ ጣሊያን ሰርቷቸው የሄደው ህንፃዎች ሳይቀሩ የተያዙት በራሥ መስፍንና መሰሎቻችው በመሆኑ እጅግ ያናድደን ነበር። የዓፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት በዚህ ጊዜ እየተዳከመ በመሄድ ላይ በመሆኑ ፣ ሚኒስትሮቻቸዉም የእንዳልካቸው ቡድን፥ የአክሊሉ ቡድን፥ የልዕልት ተናኘወርቅ ቡድንና የልዑል አሥራተ ካሣ ቡድን፣ በሚል ተከፋፍሎ እርስ በርስ በመፎካከርና የየራሳቸውን ቡድን ለማብዛትና ለማጠናከር ሲሉ ዘመዶቻቸዉንና መሰሎቻቸዉን በየበኩላቸዉ ይሾሙና ይሽሩ ነበር። ይህም ስርዓቱን ደካማና ጥርስ የሌለው አንበሳ አድርጎት ነበር። በዚህ ላይ የተጠናከረ የመምህራን

ማህበር፥ የታክሲ

ማህበር: የስራተኞች ማህበርና በግልጽም ባይሆን በህቡዕ የተደራጀ የተማሪዎች ማህበር ነበር። የተማሪው እንቅስቃሴ





በየጊዜው ስለሚያገረሽ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

13

በየት/ቤቱ የሚጻፉ ድርሰቶች፣ የሚገጠሙ ግጥሞችና የሚሠሩ ቲያትሮች ስለ ሀገር መበሳቆል፣ ሰለ ህዝብ መብትና ፍትህ መጥፋት ስለ መሬት ላራሹ የሚያተኩሩ ነበሩ። ትኩሱ ኃይል የተማሪው ህብረተሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፓሊስ ጋር የሜያደርገውን የድንጋይ ዉርወራና የትግል ፍልሚያ ቀጥሏል።ከፖሊስ ጋር ሲታገል የሞተ ተማሪም እንደ ጀግና ይቆጠራል ይዘፈንለት፤ ይገጠምለት፣ ተይዞ የታሰረም ተማሪ በተማሪዎች ዘንድ ጀብዱ እንደሠራ ይደነቅ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን በትምህርት ሚኒስተር ሴክተር ሪቪዉ(sector review) የሚባል የትምህርት ፓሊሲ ተነደፈና ቀረበ። ይሀ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በየጊዚዉ ለሚያገረሽዉ የተማሪዉ አመጽ ከጨሰዉ ላይ ቢንዚን እንደማርከፍከፍ ሆነ። ወዲያዉም ፓሊሲዉን የመምህራን

ማህበር (የህንድ

ዓይነት ካስት ሲስተምን በተለይም የድሃ ልጅ ድሃ፣ የሀብታም ልጅ ሀብታም ሆኖ እንዲቀር ታስቦ የተዘጋጀ መሳፍንታዊ ስርዓት እንዲቀጥል ሆን ተብሎ የተጠና ነው) በሚል







የመጀመሪያውን የተቃውሞ ምዕራፉን ከፈተ።

እኔና

ብዙም

የስደት ጉዞዬ

14

ሳይቆይ ተማሪው ተቀበለውና ትግሉ ተቀጣጠለ።

በዋና ዋና ከተማዎች ፖሊስ በጥይትና በሚያስለቅስ ጭስ ተማሪዉ በድንጋይ ፊት ለፊት ገጠሙ ። እኛ የምንኖርባት የጂማ ከተማም ተናወጠች። ”ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራ እንደ ሆ ቼ ሚ ኒ እንደ ቼ ጉቤራ፤”ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ ” ”መሬት ላራሹ ፤” በማለት መዝሙሩን እናቀልጠዉ ገባን:: ቀኑን በዉል አላስታዉስም አንድ ቀን በጥዋት ጀምረን እንደተለመደዉ የጅማ ከተማ ፖሊስ በጥይትና በሚያስለቅስ ጭስ፣ እኛ በድንጋይ ከመርካቶ እስከ ፈረንጅ አራዳ ስንታገል አረፈድን ።

ያች ቀን ሦስት ተማሪዎች ሞትና

በርካታ

ተማሪዎች መቁሰል ምክንያት ሆነች ፣ ስድስት ስዓት ሲሆን የመምህራን ማስልጠኛ ተማሪዎች መጥተው እኛን በመቀላቀል መርካቶንና ፈረንጅ አራዳ የሚያገናኘውን መንገድ ዘግተው ከመንገዱ ላይ ቁጭ አሉና ግደሉን እንጂ አንነሳም አሉ:: በዚህ ጊዜ ፖሊሶቹ በተቀመጠ ሕዝብ ላይ ለመተኮስ በመቸገራቸው

ሁኔታውን ላለቆቻቸዉ በማስተላለፍ ላይ

እንዳሉ የመምህራን ማሰልጠኛ ዲሬክተር አቶ ሁሴን ኢስማኤል በተማሪዎቹና በፓሊሶቹ መካከል በመግባት ጥይት





ከተኮሳችሁ መጀመሪያ እኔን ግደሉ በማለት ቆመ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

15

አንዳንድ የሀገር ሽማግሌዎችም ቀስ በቀስ እየመጡ ተቀላቀሉት የከተማዉ ሕዝብና ተማሪዉ ተዳምሮ ያሉትን ፖሊሶችና ፈጥኖ ደራሾች ቀለበት ውስጥ አስገባቸዉ:: ሁኔታዉ ተወጠረ

በየአቅጣጫዉ በዉል

ጉምጉምታና ጫጫታ

በረከተ፣

የማይታወቅ

አንዱን ሌላው

በማይሰማማበት ሁኔታ ላይ የሕዝብ ድምፅ ከፍ ብሎ ይሰማ ጀመር።ወንድማቸዉ ወይም ልጃቸዉ የሞተባቸዉና የቆሰለም ወገን ያላቸዉ እየየዉን ያቀልጡት ጀመር::

በዚህ ጊዜ አንድ ያልተጠበቀ ነገር ተፈጠረ እሱም የአባዲና ፖሊስ

ኮሌጅ ምሩቅ መኮንኖች በህዝብ ላይ ጥይት

አንተኩስም፤ ተኩሱ ብለንም ትእዛዝ አንሰጥም አሉና ለበላይ መኮንኖች ተቃውሞ አደረጉ ::ሳይቆዩ የሚያዟቸውን ወታደሮች አሰልፈው ከተማሪዎች ጋር አመጹን ተቀላቀሉ : ከተማዋ ተናወጠች፣ ወታደሮችና ተማሪዎች ባንድ ላይ መተባበራቸዉን ያ ዬ የከተማዉ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ በመዉጣት ትግሉን ተቀላቀለ። ከዚያም በመጀመሪያ የደጃዝማች ፀኃዬ እንቁሥላሴ የጡት ልጅና የመዘጋጃ ቤት ከንቲባ ወደ ነበረዉ ወደ አቶ ሰለሞን







ቢሮ በመሄድ ቢሮዉን ከበብነዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

16

አቶ ሰለሞን የደጃዝማቹ ጉቦ አመላላሽ በመሆን የጅማን ነጋዴ ያስመረረና በዚያም ዉለታው የከንቲባነት ሹመት በደጃዝማች ፀኃዬ የተሾመ ነበር። ይህም የሕዝብ ጥላቻዉን አበርትቶበታል፤ ይህን

አጋጣሚ በመጠቀምም

የመጀመሪያዉ የማጥቃት ዘመቻ ወደ ማዘጋጃ ቤት አተኮረ ። አቶ ሰለሞንን ለመያዝ ወዳለበት ቢሮ በቀጥታ ሰልፉ እየተመመ ተጓዘና የመዘጋጃ ቤቱን ሕንፃ ዙሪያዉን በመክበብ

መዝሙርና

መፈክሩ ቀጠለ።ከፖሊሶች ጋር

መግባባት ስለነበር ሕዝቡ ወደህንፃዉ እንዳይጠጋ አድርገው ወደ ቢሮዉ በመጠጋት እጁን እንዲሰጥ በደምፅ ማጉያ ቢጠየቅ ማን ሊነካኝ አለና ከፎቅ ላይ ሆኖ በያዘዉ መትረዬስ ወደ ህዝቡ አቅጣጫ ጥይቱን አርክፍከፈው።

ሆኖም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ

ማንም እንደማይደርስለትና

ፖሊሶችም ከህዝብና ከተማሪዎች ጋር መተባበራቸዉን ሲረዳ ጠመንጃውን በመጣል እጁን ለፖሊስ በመስጠት በቁጥጥር ስር ዋለ። አንድ የሕዝብ ጠላት በቁጥጥር ስር በመዋሉ ለትግሉ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆነ:: የበለጠ ጉልበትና ትብብርም ሰጠ፣

በተማሪ

በሕዝብና







በፖሊስ መካከል አንድ የጋራ የትግል ምእራፍ ተከፈተ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

17

አሁን ትግሉ በተማሪና በፖሊስ መካከል መሆኑ ቀርቶ በሕዝብና በመሳፍንቶች መካከል ሆነ።ከዚህ በኋላ ከተማዋ በተማሪዎች ቁጥጥር ስር ወደቀች፣ ወዲያዉ በአንድ ሰዓት ውስጥ ከተማሪ ፥ ከህዝብና ክፖሊስ የተውጣጣ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቋመ ። የዚህ ኮሚቴም ሊቀመምበር ዳሪክተር አቶ ሁሴን ኢስማኤል

የመሞህራን ማሰልጠኛ እንዲሆን ተስማማንና

የቀሩትን የህዝብ ደም መጣጮች የምንላቸውን በማደን ለዚህ ሁሉ ቁንጮ ወደሆነው ወደ ደጃዝማች ፀኃዩ እንቁሥላሴ ቤተመንግሥት በመሄድ ዙሪያዉን ከበብን:: ደጃዝማቹ በሰላም እጃቸዉን

እንዲሰጡ

በተመረጡ

መልክተኞች አማካይነት እጀዎን ይስጡ ቢባሉ አሻፈረኝ አሉ ተባለ: እንዲያዉም ”እኔ ፀኃዬ እንቁስላሴ እንኳን ለተማሪ ለጣሊያንም እጄን አልሰጠሁም ” አሉና

ቤተመንግስቱን

በከባድ መትረየሶች በያዙ ታማኝ ጠባቂዎቻቸው ዙሪያዉን ጠምደው ቁጭ አሉ። በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ልዬ ፈጥኖ ደራሽ ጦር ተልኮ ኑሮ ከከተማው 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መስፈሩን ሰማን፤ አሁን ቀኑ መሽቶ ስለነበር በሌሊት እንዳያመልጡ በማለት ዙሪያዉን ከበብን ጠንከር ጠንከር ያሉና ከግቢዉ ሊወጡ ወጣቶችን በግቢዉ በሮች





ቢሞክሩ ሊቋቋሙ የሚችሉ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

18

አሰለፍንና ምግብና ዉሃ ወደ ግቢዉ እንዳይገባ ተደረገ:: የቀረዉ ሕዝብ የቤተመንግሥቱን ዙሪያ በመክበብ እሣት እንደን ስንጠብቅ አደርን።ጧት ጉህ ሲቀድ ከአዲስ አበባ ከንጉሡ በተላኩ አንድ ሚንስተርና በአንድ ጀኔራል የሚመራ ልዑካን በሄሌኮፕተር መጥቶ ጂማ አየር ማረፊያ አረፈ። በዚያው አየር ማረፊያዉም

ላይ ከተቋቋመዉ ኮሚቴ ጋር

ንግግር ጀመሩ። ከደጃዝማች ፀኃዩ ጋርም ድርድር ተደረገና ደጃዝማች ፀኃዪ አዲስ አበባ ሄደው ፍርዳቸዉን እንደሚያገኙ ንጉሡ ቃል ገብተዋል ተባለ። ይህነኑም የተደረሰዉን

ስምምነት ለህዝብ

ተነገረ።የአወጣጣቸዉ ነገር ግን በሰላም እንዲሆን ህዝቡን ተማፀኑ። ከበባው እንዲነሳም ተነገረ። ይህ ከሆነ በኋላ ከአዲስ አበባ የመጡት መለክተኞች ወደ ቤተመንግሥቱ በር ተከፈተላቸዉና ገቡ። ከደጃዝማች ፀኃዬ ጋር ለብዙ ጊዜ ሲወያዪ ከቆዩ በኋላ ደጃዝማቹም ለመልቀቅ መስማማታቸዉን ለሕዝብ ተገለፀ ። የግቢዉንም በር እንድንለቅ በድምፅ ማጉያ ተነገረ: በዙሪያው ለጥበቃ የተሰለፉት

የደጃዝማቹ ታጣቂዋች

መትረየሳቸውን ወደ ሕዝቡ በማነጣጠር በተጠንቀቅ ቆሙ። ሦስት ጥቁር ማርቸዲስ መኪናዎች በቀስታ







በመሽከርከር ወደ ቤተመንግሥቱ ዋና በር ቀረቡ: :

እኔና

የስደት ጉዞዬ

19

የቤተመንግስቱ በር ከመከፈቱ በፊት በድጋሜ በደምፅ ማጉያ መንገዱን ልቀቁ መኪናዎቹ ሊያልፉ ስለሆነ መንገዱን ልቀቁ ተባለ:: በሕዝብ በኩል ግን የሰማ አልነበረም እንዲያዉም ወደ ዋናዉ በር በተጨናነቀ ሁኔታ ተጠጋ : የመኪና መንገዱን ለዓይን እስኪደክም ድረስ ዘጋው ። ደጋግሞ ቢያስጠነቅቅም የሚስማ አልተገኘም : የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መንገዱ ልቀቁ አሁንም ሰሚ አላገኘም:: በዚህ ጊዜ ከየመኪናዎቹ መስኮቶች አጭር መትረየሶች ብቅ ብቅ በማድረግ መጀመሪያ አንድ ጥይት ከአንደኛው መኪና ለማስጠንቀቂያ ተተኮሰ፤ በዚህ ጊዜ ከግቢዉ አጥር ላይ የተጠመዱት መትረየሶች በየአቅጣጫው ማሽካካት ጀመሩ። ሕዝቡ መተራመስ ሲጀምር በሦስቱ መኪናዎች ብቅ ብቅ ያሉት ኡዚዎች ያላቸዉን ጥይት ከሕዝቡ ላይ እያርከፈከፉ በፍጥነት ወደ ጂማ አየር ማረፊያ ሽመጠጡ። የደጃዝማች ፀኃዩ ቤተ መንግሥትም ከፍ ካለ ቦታ የተሰራ ሲሆን አየር ማረፊያውም ከቤተመንግስቱ ባልሳሳት ወደ 2 ኪሎ ሜትር







ይሆናል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

20

ቤተመንግሥቱን ከአየር ማረፊያው የሚያገናኝ ቀጥ ያለና ከከተማው ካሉት መንገዶች የሰፋ ስለነበር ግቢው ሲከፈት መንገዱ እስከ አየር ማረፊያዉ የሚበሩትን ተሽከርካሪዎች ማየት ይቻላል፣ ታዲያ ደጃዝማች ፀኃዩና አጃቢወቹም የያዙት ጥይትእስኪያልቅ ድረስ በመንገድ ቆሞ ባገኙት ሁሉ እየተኮሱ ቆማ

በምትጠብቃቸው ሄሌኮፍተር

ወደ አዲስ አበባ

በረሩ። በሕዝቡ በኩልም ከባድ መተራመስና ድንጋጤ ነገሰ:: የቆሰለዉና የሞቱትን ለማንሳት እርብርቦሽ ተደረገ ። በዚህ ጭፍጨፋ 9 ሰዎች ሲሞቱ 18 ቁስለኞችን ወደ ሆስፒታል አጓጓዝን።ይህ የንጉሱ እንደራሴ

ደጃዝማች ፀኃዬ እንቁ

ሥላሲ በጎጃም ሕዝብ ተቃዉሞ ምክንያት ከጎጃም ተነስተዉ ለከፋ ክፍለ ሀገር እንደራሴ ሆነዉ እንደመጡ ፣ መጀመሪያ ያደረጉት ወንድሞቻቸዉን በአካባቢ እንዲሾሙ አደረጉ:: በዚህም ምክንያት

ደጃዝማች ታደሰ እንቁሥላሴን

የኤሊባቦር ጠቅላይ ገዥ አድርገዉ ሾሙ : ከዚያም ሌላው ደጃዝማች ወርቁ

እንቁሥላሴን

የአጋሮ አዉራጃ ገዥ

አድርገዉ በመሾም ምዕራብ ኢትዪጵያን በመቆጣጠር የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣናቸዉን አጠናከሩ። በዚህም ምክንያት የጠሉትን ሰዉ ከግዛቴ ዉጣ በማለት ያባርሩ ነበር





እያሉ ብዙ ሰዎች ያማርሯቸዉ ነበር::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

21

ደጃዝማች ፀኃዪ የሚያዉቁት የልማትሥራ ሀዉልት ማሰራትና ከተማ ማስዋብ

ነበር :: ጎጃም እያሉ

የደብረማርቆስ አደባባይ ላይ የኃይለሥላሤን ድል አድርገዉ ሲገቡ የሚያሳይ ሀዉልት ሰርተዋል። ይህም የተሰራዉ በጎጃም ሕዝብ ገንዘብ ተሰብስቦ ስለነበር ሕዝቡ በምሬት በመንቀሳቀስ ተቃዉሞዉን ስላሳየ ከዚያ እንዲነሱ ተደርገዉ ወደ ጅማ ተዛወሩ : ጀማም ከመጡ በሁዋላ በቀጥታ ሥራ የጀመሩት ሀዉልት በመስራት ነበር :: ጂማ አንደመጡም የጃንሆይን: እናት ኢትዬጵያ ሃዉልትና ሊሎችም የአንበሳ ሃዉልቶች አሰርተዋል። ይህን ለማድረግ ግን የጂማ ነጋዴ ተበዝብዟል: ታስሯል፤ ከሃገር ተባሯል። እኒህ የጣሊያን አርበኛ የኃይለሥላሲ ታማኝ ወደጅ የሆኑት ደጃዝማች ፀኃዩ ወደ ጂማ ሲመጡ ከአይሮፕላን ወርደው በቀረበላቸው ጥቁር ማርቼዲስ ከመግባታቸው ተሰልፈዉ ይጠብቋቸው

በፊት

የነበሩትን ባለስልጣናትና ያገር

ሺማግሌዎች ሲጨብጡ የነበራቸው በራስ መተማመን ከፍ







ያለ ነበር፡፡

እኔና

እኒህ

የስደት ጉዞዬ

እንዳንበሳ ግርማቸው

22

የሚያስፈራዉ ታላቁ ሰዉ

ደጃዝማች ፀኃዬ እንቁ ሥላሴ በክብር ታጅበው ከገቡበትና ከኖረበት ቤተመንግሥት እንደ ወንጀለኛ ተከበው ቀናት ከቆዬ በኋላ ታጅበው በመጡበት

እንዲወጡ ተደረጉ::

ለሦስት

መንገድ ተባርው

እኔና

የስደት ጉዞዬ

23

እድገት በህብረት ዘመቻ ብዙ ሳይቆይ የለዉጡ እሳት እየጋለ ስለሄደ ለማርገብ በሚል ንጉሡ የካቢኔ ለዉጥ በማድረግ የአቶ አክሊሉ ኃብተወልድ መንግሥት በልጅ አንዳልካቸዉ መኮነን እንዲተካ አደረጉ ።ልጅ አንዳልካቸው ለብዙ ዘመናት የተበላሸዉን ሥርዓት ለመቀየር ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው

ቢወተዉትም

የሚሰማቸው አላገኘም: : በዚህ ምክንያት

ከተለያዪ ክፍሎች የተውጣጣ የጊዜያዊ

ወታደራዊ ደርግ በማቋቋም ” ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ” በሚል መሪ ቃል የለዉጥ ፈላጊዉን ሕዝብ ቀልብ ሳበ :: ከወጣት እስከ አዛዉንት ድጋፉን ሰጠ:: በእጅጉም ተደገፈ በየተገፑበት ሁሉ አልቆየም:

አበባ ተበረከተላቸወ። ሆኖም ብዙ

ተማሪዉ "በወታደራዊ መንግሥት ዴሞክራሲ

አይመጣም በመሆኑም ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም" የሚል









እንቅስቃሴ ጀመረ ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

24

ደርግም ይሄን ለማስታገስ በሚመስል መልኩ እድገት በህብረት በሚል መርህ 60 ሽህ ተማሪዎችን ወደየገጠሩ ተመድበዉ እንዲያገለግሉ ተላኩ። እኔም ከነዚህ ወጣት ዘማቾች መካከል አንዱ በመሆን ጅማ ክፍለ ሀገር በጊሚራ አዉራጃ

ዋና ከተማ ሚዛን ተፈሪ

ምድብ ጣቢያ ተመደብኩና በመሄዴ ከነበሩኝ ጓደኞቼ ጋር ተለያየን። ከጧት እስከማታ ባንድ ላይ በደህናዉም በደጉም ተሳስበን እንኖር የነበርነዉን ወጣት ተማሪዎች ወደተለያየ ቦታ እንደማንገናኝ አድርገው በተኑን :: ይህ የተማሪዎች መበተንም

ለወታደራዊ

ደርጉ ለጊዜዉም ቢሆን እፎይታ





ሰጠዉና ወደ እርስበርሳቸዉ ትግል ጀመሩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

25

ሚዛን ተፈሪ ዘመቻ ጣቢያ ፣

ሚዛን ተፈሪ ከአፋፍ ላይ የተመሰረተች ዉብ ከተማ ነች:: በጊዜዉ ከጂማ ጋር የሚያገናኛት የመኪና መንገድ ስላልነበረ በአውሮፕላን ነበር የተጓዝነዉ :: እንደ ደረስን ሕዝቡ ማረፊያ ቤት የእንጨት አልጋ ሠርቶ በሰፊው ደግሶ በታላቅ ክብር ተቀበለን::ሕዝቡ ዘማቾችን አንደ ብርቅ ያዩን ነበር:: ስናወራም በታላቅ አክብሮት ይመለከተን ነበር። ይህ ተወዳጅነትና መከበር ግን ብዙ አልቆየም። ከተለያዩ ቦታዎች

ባህልና ቋንቋ የመጡ ተማሪዎች የተለያየ

አስተሳሰብና እንቅስቃሴ አራማጆች ተፈጠሩ።

አስተሳሰቡ ወደ ተገባር ሥራ እየተቀየረ ጠንካራ የአካባቢ ገበሬዎችንና ትንሽ ያላቸዉን ነጋዴዎችን አዳሃሪ እና ቡርጃ የሚል ስም ይለጠፍባቸዉ ጀመር: እየቆየም ሠራተኞችን በማነሳሳት የአሠሪዎቻቸዉን ንብረት እየዘረፉ ማከፋፈል ጀመሩ:: በዚህ ምክንያት አንዳንድ በዘማቾች ድርጊት









የተበሳጩ ወደ ጫካ መሸፈት ጀመሩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

26

በዚህ ሁኔታ የተበሳጨን በአዝማቻችን አማካኝነት ተሰበሰብንና አሰራራችን ሥርዓት የሌለዉና መረን እየለቀቀ በመሄዱ ከተሰጠን ተልዕኮ ጋር የተጻረረ ነዉ እየተሰራ ያለው በሚል ሀሳብ ተወያዪን። ዘማች ሕዝብ ማስተማር፣ መንገድ መሥራትና ለልማት በር መክፈት እንጅ የፍርድ ቤት ሚና መጫወት የለብንም አልን:: በተቃራኒዉ ያሉ ዘማቾች ይህ እናንተ የምትሉት ለፊዉዳሎች ዘብ መቆም ነዉ :: በመሆኑም አርፋችሁ እኛ የምንሠራዉን ደግፋ ሲሉ ዛቱ:: በስብሰባዉ ላይ መከፋፈሉ በጣም አያየለ በመሄዱና ከቃላት ወደ መሣሪያ መማዘዝ ተሸጋገርን ሁኔታዉ እየከፋ ሄደና ካምፑን ጥለዉ በሚሄዱ ዘማቾች ላይም ደርግ በመንገድ እየያዘ እርምጃ መዉሰድ በመጀመሩ





አማራጭ አገር ለቆ መሰደድ ብቻ ሆነ።

እኛ የነበረን ብቸኛ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

27

ምዕራፍ - 2 ለስደት ጉዞ ቀኑ ሰኞ ነበር : በጋው አልቆ ክረምቱ የሚገባበት ወራት ስለነበረ አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ይዘንባል : እንዳጋጣሚ በዚህ ቀን ኃይለኛ ዝናብ ሲዘንብ ዋለ: ይሄም ለኛ እቃችን ለመጠራረፍና ለመዘጋጀት ጥሩ አጋጣሚ ሆነልን: ምክንያቱም ብዙ በየመንገዱ የሚዘዋወር ሰው አልነበረምና ነው:: ቀኑን የምንችለውን ያህል እቃችን ስንሸክፍና ስንጠቀልል ዋልንና ደብዛዛዋ ፀሃይ ጠልቃ ጨለማው እየነገሰ ሲሄድ ሰው ሳያየን ጉዞአችን ለመጀመር አመች ጊዜ ሆነልን ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሲሆን በተከራየነው በመንገድ

መሪያችን

አማካይነት መንገዳችን በሌሊት ቀጠልን:: ጉዞአችን ለጊዜው ከዚያ ቦታ ሰው ሳያየን ማምለጥ እንጂ እንዴትና በየት አድርገን ወጥተን ወደ ሱዳን የጠረፍ ከተማ እንደምንደርስ በትክክል አናውቅም ነበር:

ብቻ ሱዳን

ከኢትዬጵያ በስተምዕራብ አቅጣጫ እንደሆነ እርግጠኞች









ነበርን ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

28

ወደ ምዕራብ የፀሃይን መጥለቂያ ተከትለን በያዝነው አቅጣጫ ማሳያ

(ኮምፓስ) እየተረዳን በመጓዝ ከአንደ

የሱዳን ግዛት ውስጥ መድረስ እንደምንችል ተስፋ አርገናል ። ከባዱ ጨለማ ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተደምሮ የጉዞአችን አቅጣጫ ለማየት የምንጠቀመው በያዝነው የደበዘዘ የእጅ ላምባዲና (ባትሪ) ነበር :: ከዚያም በላይ ከሰው ለመሰወር ስንል

መንገድ እያሳበርን ጫካ ጫካውን ሄደን

ከምንፈልገው መንገድ ለመድረስ ብዙ ጊዜ ወሰደብን:: የዘመቻ ጣቢያዉን ወደ ኋላ በመተው የበበቃን ጫካ ማህል እየስነጠቅን ለብዙ ሰዓታት ከተጓዝን በኋላ የተሽከምነው ቁሳቁስ ክብደቱ እየተሰማን እግራችን ወደኋላ ከሚጎትተን ጭቃ ጋር ተዳምሮ ስለደከመን እረፍት እንድናድርግ ተስማማንና

ከአንድ ትልቅ ዛፍ ስር ጀርባችን በማስደገፍ

ተጠግተን ቁጭ አልን።ድቅድቅ ያለው የበበቃ ደን ከጨለማዉ ጋር ተዳምሮ የሚያስፈራ ኃያል ግርማ ነበረዉ ፤ በዚያ ላይ አንበሶች ያገሳሉ:: ዝሆኖች ደኑን ሲያተራምሱት ይሰማሉ : ወፎች ከዛፍ ወደዛፍ ይፈተለካሉ:

አንዳንዶቹ ይዘምራሉ ፤ ያፏጫሉ

በጠቅላላዉ ልዩ ዓለም ዉስጥ ያለን ይመስል ነበር። በዚህ ሁኔታ ሁላችንም በየግላችን በሃሳብ ውቅያኖስ ተዉጠን







ሳናስበዉ አንድ ሰዓት ተኩል አሳለፍን ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

29

አብሮን የነበረዉ የመንገድ መሪ ተነሱ ሲል ሁላችንም እንደመባነን ነበር የተነሳነዉ:: በዝምታ ፈረስ ሁላችንም እንደጋለብንና ምን እናስብ እንደነበርም አልተጠያየቅንም:: እያንዳንዳችን ምን እናስብ እንደነበር ለማወቅ አዳጋች አልነበረምና መልሱ ቀላል ነበር:: ከናታችን ማህፀን ተፈጥረን ተወልደን : ነብስ አዉቀን አድገን በደስታና በሃዘን አብረን ያሳለፍናቸዉ ዘመናት:

የእምብርክክ እየዳህን

ከዚያም ቁመን መሮጥ እስክንችል ድረስ የተሽከሙን ወላጆቻችን: አብረን ያደግነዉ ጓደኞቻችን: በጠቅላላዉ ማንነታችን አዉቆ ሰዉ ከሚለን ህብረተሰብ ትንሹ ጋሼ ትልቁ ልጄ ከሚለን ወገናችን ፣ ከሮጥንበት ከፈነጠዝንበት መሬት የምንለይበትና የምንሰናበትበት ጊዜ ነበር::

አወ ! ሞት ወይም ድነት ነዉና በደርግ ካድሬዎች ተይዘን ከምንሞት ለማምለጥ ወደፊት ከመግፋት በቀር ሌላ ምርጫ አልነበረንም ። ሸክማችን በወገባችን ላይ በማድረግ ረጅሙን መንገድ

ተራምደን በዚህ ሰዓት እንደርሳለን





ወደማንለዉ የእግር ጉዞ በከባዱ ጨለማ ተያያዝነዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

30

አሁንም ሰዉ እንዳያየን ጥንቃቄ ማድረግ ስለነበረብን ዋና መንገዱን በመተዉ በረጅሙና ጫካ ጫካዉን እየተጓዝን ብዙ ከሄድን በኋላ ወደዋናው መንገድ በመግባት እስከ ሌሊቱ ስምንት ስዓት

ድረስ ጉዞአችን በነፃነት ቀጠልን::

ሆኖም የተሽከምነዉ ጓዝ ክብደቱ እየጨመረ የሚሄድ መሰለን:

ትንሽ ተራምደን ማረፍ ሆነ በዚህ ምክንያት

ጉዞአችን እንዳሰብነዉ ፈጣን አልሆነም። ከአንድ ዛፍ ሥር እረፍት ካደረግን በኋላ ጉዞ ጀመርን መንገዱ ጥሩ ነዉ: ታላላቅ ዛፎች ወደበዙበት ጥቅጥቅ ያለ የበበቃ ደን አካባቢ ስለደረስን ጨለማዉ ከደኑ ጥላ ጋር ተዳምሮ እየበረታ ሄደ:: በዚህ ላይ የበርሃ አዉሬዎች በተለይ ዝሆኖች የሚመመገቡበትና ዉሃ የሚፈልጉ የዱር አራዊቶች የሚተራመሱበት ጊዜና አካባቢ ስለደረስን ሰዉ እንዳይዘን የነበረን ፍርሃት ተለዉጦ የበርሃ አዉሬዎች እንዳይበሉን የሚለዉ ሥጋት እየገነነ ሄደ :: ድንገት አዉሬ ቢተናኮለን የምንከላከልበት የያይዝነዉ መሳሪያ የእንጨት ጦርና ጩቤ ብቻ ነበር :

ሆኖም ይህን

ጨለማን ተገን አድርገን እንድናልፍ የምንፈልገዉን ቦታ የግድ ማለፍ ስለነበረብን ጉዞአችን ቀጠልን:: ይሁን እንጂ በቀን ጉዞ ስድስት ሰዓት የሚወስደዉ መንገድ በሌሊት ጉዞ





አስራ ሁለት ሰዓት ወሰደብን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

31

ከጧቱ አስራ ሁለት ሲሆን ማለፍ የፈለግነዉን ቦታ አለፍንና ትንሽ እረፍት ካደረግን በኋላ ጉዞኧችን በመቀጠል እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ተጓዝንና ከአንዲት ትንሺ መንደር ደረስን :: መንገዳችንም በዚሁ መንደር አቋርጦ ስለነበር በመንደሩ ቀጥታ በመሄድ ለሰዉ ለመታየት ስላልፈለግን መንገድ በማሳበር አቋርጠን አለፍንና ድካምና ረሃብ ስለ በዛብን ትንሺ እረፍት ለማድረግ በመወስን ከአንድ ዛፍ ሥር እረፍት አደረግን።መሪያችን ከዚህመንደር እንጀራ ይሽጣልና ሄጄ ገዝቼ ልምጣ የሚል ሃሳብ አቀረበ :: እኛም ሳናቅማማ ሃሳቡን ተቀበልነዉ:: እንዲያዉም እንጀራ ለመጨረሻ የምናይበት ጊዜ ሊሆን ይችላልና ብንበላ ጥሩ ነዉ ሲል ገሠሠ ሃሳቡን በማጠናከር ደገፈዉና ካለን ገንዘብ ሰጥተን

ላክነዉ:: እስኪመለስ

እሳት አንድደን ሻሂ አፍልተን እየጠጣን ጠበቅነዉ።እንጀራ ለማምጣት የሄደዉ የመንገድ መሪያችን ይመጣል ብለን ስንጠብቅ

እሱስ ለካ ሂዶ ለቀበሌ

ማህበር ሊቀመንበሩ

ነግሮት ኑሮ ሊቀመምበሩ ከሰዎች ጋር ከተፍ አለ: ያላሰብነዉ ዱብእዳ ስለሆነ ሁላችንም ከተቀመጥንበት በድንጋጤ ተነሳን: ግን ምን ያደርጋል ዙሪያችን ጠመንጃና ጦር በያዙ



የአካባቢዉ ሕዝብ ተከበናል።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

32

ጤና ይስጥልኝ አቶ ሞላ አለ አቶ ማሞ ከሁለት ሳምንት በፊት ሕዝብ ሰብስቤ ለቀበሌ ሊቀመንበርነት እኔ ስለነበርኩ ያስመረጥኩት:: ከዚህ ሰዉ ጋር በደንብ እንተዋወቃለን:: ስለ ሀገር ፖለቲካ ሁኔታም በመጠኑ አዉርተናል ፣ የት ትሄዳለህ ዛሬ? እነዚህ የማላዉቃቸዉ ሰዎችስ ከየት መጡ? ሲል በአክብሮት መልክ ጠየቀኝ :: በዉስጡ ጥርጣሬ ቢታይበትም በቀጥታ በከዳተኛነት ሊወነጅለኝ አልደፈረም:

ምክንያቱም ዘማች በመሆኔና

ሕዝብ ለማደራጅት ብዙ ጊዜ እመላለስ ስለነበር ነዉ::ሁላችንም በድንጋጤ ተዉጠናል፣ ያለን የማምለጥ ተስፋ ጠባብ ሆነ፣ የምንተነፍሰዉ ንጹህ ዓየር ወደ መርዝነት የተለወጠ መሰለን:: ብስጭት ተስፋ መቁረጥ ተደራረበብን፣ ሆኖም ብስጭታችን በደረቅ ፈገግታ ለዉጠን

እንደምታዉቀዉ የተለመደ

ሥራዬን ለማከናወን ወደ ጉራፈርዳ ቀበሌ ማህብር ለማቋቋም ነዉ የምንሄደዉ፣ አልኩት:: ፅአቶ ማሞ በመልሴ አልረካም ”የዛሬዉ ለሥራ አካሄድህና የሌላዉ ጊዜ የተለዬ ነዉ ምክንያቱም አንደኛ በሌሊት ስትጓዙ እንዳደራችሁ፣ ሁለተኛ ሰዉ እንዳያያችሁ ጫካ ጫካዉን እያሳበራችሁ





ስትጓዙ እንደመጣችሁ መሪያችሁ ነግሮኛል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

33

ይሄም ከከባድ ጥርጣሬ ላይ ጥሎኛል : ደግሞስ እኛ እናንተን ተስፋ ያደረግነዉ ኢትዮጵያ ሀገራችን ባንድነት እንገነባለን: እንሠራለን : የአሰራሩን አይነትም በናንተ አስተማሪነት በኛ ተከታይነት እናንተ በምታወጡልን የሥራ እቅድ አማካይነት ሀገራችን እንገነባለን የኛም ኑሮ ያልፍልናል ብለን ተስፋ ስናደርግ እናንተ እኛንና ድሃ ሀገራችሁን እየጣላችሁ ወደ ማታዉቁት ባዕዳን ሀገር የምትኮበልሉ ከሆነና ሃገሪቱ የተማሩ ወጣቶችን ካጣች ምን ይዘን ሃገራችን ልንገነባ እንችላለን ? :: ደግሞስ ሀገር በደላ ጊዜ መኖሪያ በከፋ ጊዜ ጥለዋት ለጠላት አጋልጠዋት የሚፈረጥጡ ነች እንዴ?» አለ፤ በዚህ ጊዜ ሁላችንም ደማችን ፈላ ይህን የተናገርከዉን ሃሳብና ቃላት ያስተማርኩህ እኔ ነኝ ::አንተ አገር የሚለዉን ቃልና የሀገርን ትርጉም ከማወቅህ በፊት ሀገራችን በመሳፍንቶች ተበዘበዘች ::

አራሹ ገበሬ ተጨቆነ ድሃዉ ያላግባብ ተገረፈ ፍርድ ተጓደለ: ትክክለኛ ዲሞክራሲ ጠፋ የመሰብሰብና በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ ነፃነቱን አጣ ሕዝቡ የራሱን መሪ የመምረጥ መብት ተነፈገዉ : ነጋዴዉ እንዳይነግድ ገበሬዉ እንዳያርስ





ጸሐፊዉ እንዳይጽፍ : ተማሪዉ እንዳይማር ተደረገ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

34

እያልን በየቀኑ መፈክር ይዘን ስንጮህ፣ ፖሊስ በጠመንጃና አስለቃሽ ጭስ ሲያባርረን በዱላ ሲደበድበን አንተና አንተን የመሰሉት ዜጎች »ተማሪ ጠገበ አሁን ምን ይዉረድ ብለዉ ነዉ!! ንጉሥ መገልበጥ ተራራ እንደመናድ ማለት ነዉ ደግሞስ ኃይለሥላሴ ወርደዉ ማንን ለመተካት ነዉ!?»| እያላችሁ ትሰድቡንና ታፌዙብን የነበራችሁት እናንተ ነበራችሁ አይደል እንዴ?።

አሁን ደግሞ አምባገነኑን ወታደር በመደገፍ የወታደሩን የፕሮፓጋንዳ ቃላቶች እየሰበሰባችሁ በኛ ላይ ታፌዙብናላችሁ:: አዋቂ ለሀገር ተቆርቋሪ ለመምሰል ለሥራ ታጥቆ የተነሳዉን ሕዝብ እንዳይሠራና በቃላት

ድርደራ

እንዲያሽበርቅ ልታደርጉት ትሞክራላችሁ?።ደግሞ እንሥራ ስንል በየጫካዉ እየቆማችሁ እንደ ሽፍታ ይህችን ሹመታችሁን በመጠቀም ሰዉን ማጉላላት ጥቅም መቃረሚያ እንዳደረጋችሁት እናዉቃለን፣ አሁን ደግሞ አትሥሩ ነዉ የምትለዉ!?።

ይህ ከሆነ አሁን ሂደን ለሚመለከተዉ ባለስልጣን እናመለክታለን ከዚያም ለድካማችንና ለመጉላላታችን







ተጠያቂ ትሆናለህ? አልነዉ፡:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

35

በማስፈራራት ዛቻ በዚህ ጊዜ አቶ ማሞ ትንሽ እንደመፍራት አለ፣ እኛም ዘዴአችንና ማስፈራራታችን ለጊዜዉ የሰራ መሰለን:: ቢሆንም አቶ ማሞ ሊለቀን ብዙ ካቅማማ በኋላ እንደገና ሃሳቡን በመቀየር » በሉ ለማንኛዉም እንሂድና የሚበላ ነገር ልጋብዛችሁና እናንተም አረፍ በሉ እኔም በነገሩ ላስብበትና አረፍ ብላችሁ ትሄዳላችሁ» አለ :: እኛም

ከሱ ጋር በመሄድና ለተጨማሪ የሕዝብ ከበባ

የሚዳርገን መስሎ ስለታየን አይ ስለግብዣዉ እናመሰግናለን ነገር ግን ለሥራ ስለምንቸኩል ቶሎ መሄድን እንመርጣለን አልነዉ :: እንግዲያዉ እሽ በዚህ ካልተስማማችሁ ሄጄ የሚጠጣ ነገር ይዤላችሁ እስክመጣ ድረስ ከዚሁ ጠብቁኝ አለንና ጥሎን ወደሰፈር ተመልሶ ሄደ ። አሁን እርስ በርሳችን ለመወያየት እድል አገኘን እንጀራ ሊገዛ የተላከዉ መሪ አልመጣም ነገሩ ተንኮል እንዳለበት ቢገባንም ለጊዜዉ መፍትሄ መስሎ የታየን ከዚያ ቦታ ቶሎ መጥፋት ስለሆነ







የፈታታነዉን ጓዛችን አሳሰርን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

36

ሆኖም ከንቱ ሙከራ ሆነብን ወዲያዉኑ መጠጥ ላምጣላችሁ ያለዉ አቶ ማሞ በመጠጥ ፋንታ ጠመንጃ የያዙ ተጨማሪ ሰዋች ይዞ ደረሰ :: አሁን ምንም መዉጫ ቀዳዳ እንደሌለን ተረዳን:: ሳናስበዉ ጠመንጃና ጦር በያዙ ገበሬዋች ተከበናል በየትኛዉም አቅጣጫ ማምለጫ የለም :

የመኖር

ተስፋችን ጨለመ ከንዴት የተነሳ ጉሮሮአችን ደረቀ መናገር ስላቃተን በአይን ብቻ መተያየት ሆነ :: ሁላችንም በሃሳባችን የሚታየን እንደፍየል ታስረንና

ተጎትተን

ሂደን ወታደር ተቀብሎ የአብዬቱ ጠላቶች ሀገራቸዉን የከዱ ወዘተ በማለት ግንድ አስደግፎ ጥይት ሲቆጥርብንና ጓደኞቻችን ወዳጅ ዘመድ ቁሞ ሲመለከት ነበር በሃሳባችን የሚታየን። » እጅ ወደላይ አለ አቶ ማሞ የጠመንጃዉን አፈሙዝ ወደኛ በማዞር እኛም እጃችን

ወደላይ አንከረፈፍን

ከወገባችን ለክፉም ለደጉም ብለን የታጠቅነዉን ጩቤ ፈታታንና አስረከብን::ሌላ መሳሪያ መያዝ አለመያዛችን ለማረጋገጥም ሰዉነታችን ከፈተሸ በኋላ መሳሪያ





በያዙት ገበሬዎች ታጅበን ወደሰፈር ከወሰዱን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

37

ከዚያም ከአንዲት ጠባብ ጎጆ ሶስታችንም አስገብቶን የጎጆዋን ዙሪያ ጠመንጃና ጦር የያዙ ገበሬዎች ዙሪያዉን ከበዉ እንዲጠብቁ አደረገ። »አሁን በቃ የኛ ነገር አለቀ አከተመ እንደ በግ ተጎትተን ተወስደን በአረመኔዉ ወታደራዊ ደርግ መታረዳችን ነዉ፤ ሌላ ምንም እድል የለንም ወይኔ የኔ ነገር ዘላለም ለስቃይና ሰቆቃ ያደለኝ» አለ ሐጎስ እንባዉን በግራቀኝ ዓይኖቹ እያጎረፈ በንዴት፣ አዎ ሐጎስ ሊያለቅስ ይገባዋል ከሁላችንም በእድሜ ይበልጣል ሐጎስ በኤርትራ ክፍለ ሀገር ተወልዶ ያደገዉና የተማረዉ በኤርትራ አስመራ ከተማ ነበር:: አዲስ አበባ በመምህራን ማሰልጠኛ ከተመረቀ በኋላ በብዙ የኢትዬጵያ ግዛቶች እየተዘዋወረ ብዙ ወጣቶችን አስተምሯል :: በኋላም አዲስ አበባ በመሄድ የኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዴሬክተር በመሆን ለብዙ ጊዜ ከሰራ በኋላ የግል ተምህርት ቤቶች ማህበር የአመራር አባል በመሆን ለሦስት ዓመታት እንዳገለገለ በንጉሣዊዉ አገዛዝ





የፖለቲካ ቅራኔ የተነሳ ባደረገዉ ተቃዉሞ ምክንያት

እኔና

የስደት ጉዞዬ

በንጉሡ የፀጥታ ኃይሎች

38

ተይዞ ብዙ እንግልትና

ግርፋት ከደረሰበት በኋላ አፄ

ኃይለሥላሴ ከስልጣን

እንደወረዱ በተደረገዉ የፖለቲካ እስረኞች ምህረት መሰረት ተለቀቀ::

ሐጎስ

በደረሰበት ግርፋት ስቃይ ምክንያት ጤንነቱ

በጣም ስለታወከ በጊዜዉ የቻይና ሀኪሞች ጂማ መጥተው ደህና ዝና እግኝተዉ ስለነበር

ለህክምና

ወደነሱ መጥቶ ሲታከም ከቆየ በኋላ ትንሽ ስለተሻለዉ ከዚሁ ጂማ ከሚገኘዉ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ የግል ት/ቤት (በአጎቴ

በአቶ በላቸዉ ጌታሁን ተቋቁሞ የነበረ)

የአስተማሪነት ሥራ ስላገኘ ሲያስተምር ነበር : ከገሠሠ ጋር ለመተዋወቅና አብሮ ሀገር ለቆ የመሰደድ ሚስጥር ሊካፈል የቻለዉ:: በኋላም የሀገሪቱ ሁኔታ የወታደሩ አምባገነንነት እየጎላ ሕዝብ ያለጥፋት ከቤቱ እየታፈነ መታሰርና መገደል ስለበዛ ነገሩ ከሱ በራፍ ሳይደርስና የሀገሪቱ ደንበር እንደ





በርሊን ግንብ ሳይታጠር ለማምለጥ የወሰነዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

39

ቀደም ብለን ከገሠሠ ጋር በደብዳቤ ያደረግነዉ ዝግጅት ስለነበረን እሱንም ከእቅዳችን እንድንጨምረዉ ስለጠየቀኝ እኔም በነገሩ ተስማማሁ። ሐጎስ ከዚህ በፊት ያደረገዉ የፖለቲካ ተቃዉሞና የደረሰበት ቅጣት ከዚያም በምህረትና ማስጠንቀቂያ መለቀቁን ሲያስበዉ ሁለተኛ ጊዜ ሀገሩን ጥሎ ሲኮበለል በመያዝ ወንጀል ክህደት የሚጠብቀዉ ፍርድ ከሞት በቀር ሌላ እንደማይሆን ግልጽ ስለሆነለት ነበር::በዚህ ላይ የኤርትራ ተወላጅ ነዉ:: (ኤርትራያን

ከኢትዮጵያ የመገንጠል ትግል ጀብሀ (EPLF) በሚባል የነፃ አዉጭ

ድርጅት አማካኝነት ትግል

እየተካሄደ ነዉ) ::

የአንዲት ሴት ልጅ

አባት ሲሆን

ሐጎስ ባለትዳርና እሷም የ11ኛ ክፍል

ትምህርቷን ጨርሳ ከጓደኞቿ ጋር በአዋሽ ዘመቻ ጣቢያ ተመድባ እንደምትሰራ አጫዉቶኛል። እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲደራረብ ሊያስለቅሰዉና ሊያሳዝነዉ ይችላል ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ በሰዉ እጅ ተይዞ ተጎትቶ መገደሉ ሁለተኛ ሞት ነበር። ጥፋቱ የኛ ነዉ ሲል ገሠሠ ንግግሩን ቀጠለ በንዴት አንጀቱ እያረረ የሚያሰማዉ ድምፅ ከጉሮሮዉ እየተቆራረጠ ፊቱ ቀልቶ በግራቀኝ አይኖቹ





የተንቀረዘዘዉ እንባ የጧት ጤዛ መስሏል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

40

ብዙ ጊዜ ገሠሠ ሲናደድ ከመናገሩ በፊት እንባዉ ይቀድመዋል በጣም መናደዱን የማዉቀዉ በእንባዉ መፍሰስ ነዉ። ገሠሠ በአለማያ እርሻ ኮሌጅ ትምህርቱን እንደጨረሰ በአየር ኃይል ኤሮናቲክ ኢንጅነሪንግ ትምህርቱን ጨርሶ በም/ መ አለቅነት ማዕረግ በኋላ

ተመርቆ ሲያገለግል ከቆየ

ከአየር ኃይል እንዲወጣ በጠየቀዉ መሠረት

በስንብት ወጥቶ ኑሮዉን የሬዲዬ መጠገኛ ሱቅ ከፍቶ እየሠራ በሚያገኘዉ ኑሮዉን እየገፋ ነበር::

የገሠሠ ጓደኞች ከፖሊስና ዓየር ኃይል የተመረቁ እና በሚያዚያ 27 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪዎች

ነበሩ:

ያስተምሩ የነበሩ

ማታ ማታ ከሥራ ሲወጡ

እየተገናኙ ስለ ሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ አዘዉትረዉ ይወያዩ ነበር:: አልፎ አልፎም ከሚሠራበት ሱቅ እየሄዱ ቁጭ ብለዉ ይወያዩ ነበር:: እኔም ገሠሠን የተዋወኩት





ከዚሁ የሬዲዮ ሱቅ ነበር::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

41

ታዲያ ደርግ ስልጣኑን እንደተቆጣጠረ እነዚሁ ከሱ ጋር በፖለቲካ ይከራከሩ የነበሩ መኮንኖች የደርግ አባል እየሆኑ

በብሔራዊና በክፍለ ሀገር ደረጃ ተመድበዉ

ሲሰሩ በሰላም ጊዜ

በፖለቲካ አቋማቸዉ ከነሱ ጋር

የማይስማሙ የነበሩትን እየለቀሙ ማሰር ጀመሩ:: ገሠሠም

ነገሩ ከሱ ሊደርስ እንደሚችል ስለተረዳና

ካሰሩትም በቀላሉ እንደማይለቁት ስላወቅ ተይዞ ከመሰቃየቱ በፊት አገር ጥሎ ከመሄድ ሌላ አማራጭ የሌለዉ ሁኔታ ስለደረሰ የሚወዳት ሀገሩን ጥሎ ለመሰደድ ቆረጠ ::ይህ ያለዉዴታ ግዴታ ስደት ያናደደዉ ገሠሠ አሁን በቀበሌ ማህበር አገር ጥሎ ሲፈረጥጥ የተያዘ ከሀዲ ተብሎ በነዚያ ጓደኞቹ ፊት መታየትን ከሞት ያልተሻለ ዉርደት ስለመሰለዉ ነበር በብስጭት እንባዉ የወረደዉ። ለማንኛዉም ገሠሠ ንግግሩን ሳይጨርስ አቶ ማሞ መጣና በሉ እንሂድና በበቃ ካምፕ አድረን ጧት ወደ ሚዛን ተፈሪ እንሄዳለን በማለት ጉዟችን ወደ በበቃ





እርሻ ካምፕ አደረግን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

42

እንዳይደረስ የለምና ከተባለዉ የበበቃ እርሻ ጣቢያ ፀኃይዋ ጠልቃ ጨለማዉ የሚተካበት ጊዜ ስለነበር ገበሬዎች ከሥራ ወደቤታቸዉ ከብቶቻቸዉን እየነዱ ወደየቤታቸዉ የሚከወኑበት ጊዜ ነበር የደረስነዉ:: ይህችን የእርሻ ጣቢያ ከዚህ በፊት እየተመላለስኩ ሕዝቡን በመሰብሰብ ስለሀገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የህብረተሰብ እድገት ብዙ ተወያይተናል በተለይ ለመዉጣት ጉዞ ጀምረን ከመያዛችን አንድ ሳምንት በፊት ከዚሁ የእርሻ ጣቢያ ከሚሰሩት ባለሥልጣናት ጋር አንድ ሌሊት ስንወያይ አድረናል::በዚህ ጊዜም ትልቅ መግባባትና መቀራረብ አድሮብን ስለነበር ስንለያቸዉም ወንድማዊ በሆነ ስሜት ነበር የሸኙን::

አሁን ግን

እንዚሁ እንደወንጀለኛ ታስረን ሲያዬን ምን ይሰማቸዉ ይሆን?:: አቶ ማሞ ከአንዲት ደሳሳ ጎጆ አስገባንና አሁንም መሣሪያ በያዙ ሰዎች እንድንጠበቅ ካደረገ በኋላ ከእርሻ ጣቢያ

ወደ

እርሻ

አሥተዳዳሪዉ

በመሄድ ከዚህ

ሊያድሩ የማይችሉ እስረኞች ስላሉኝ ወደ ሚዛን ተፈሪ የሚያደርስ መኪና ይታዘዝልኝ በማለት ትእዛዛዊ ጥያቄ





አቀረበ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

43

ባለዉም የገበሬ ሊቀመንበርነት ሥልጣን በመጠቀም ማስፈራራት ጨመረበትና አንድ መኪና ከነ ሾፌሩ ተፈቀደለት::አዎ!

ያሰብኩት አልቀረምና ላንድሮበሩን

እየነዳ የመጣዉ ባለፈዉ ከቤቱ ስንወያይና ስንደሰት ያደርንበት ሰዉ ነበር እሱም እኛ መሆናችን ባየ ጊዜ በጣም ደነገጠ የሚናገረዉን አጣ ብቻ ተቃቅፈን ስንሳሳም ማሞም ግራ ገባዉ:: ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላም ወደ ማሞ ዘወር በማለት »እነዚህማ ሁልጊዜ እዚህ እየመጡ እየሰሩ አይደለም እንዴ! የሚሄዱት አሁን ምን አድርጉ ነዉ የምትላቸዉ እንደዚህ እንደ ወንጀለኛ አሥረህ የምትነዳቸዉ ደግሞስ የኢትዮጵያን ደንበር እስካላለፉ ደረስ በሀገራቸዉ ጫካ የትስ ቢሄዱ መብታቸዉ አይደለም እንዴ? አለና ማሞን በደም ፍላት ጠየቀዉ:: ማሞም

” አንዴ የመሰለኝን እንዳደርግ ስልጣን

ተሰጥቶኛል ለዚህም ይሠራል በማለት ሕዝቡ መርጦኛል ከዋናዉ ጣቢያ ወስጄ ንፁህነታቸዉን





አረጋግጣለሁ ነፃ ከሆኑም እኔ በወንጀሉ እቀጣለሁ» ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

44

ሰዉየዉ ሌላ ሊያደርገዉ የሚችለዉ ነገር ስለሌለ ትንሽ ጊዜ ወስዶ

መፍትሄ ለመፈለግ እንዲረዳዉ በማሰብ

ይመስላል እሺ ካልክ እንግዲህ አሁን ግዜዉም ስለመሽ እነሱም ስለደከሙ ባይሆን ከዚህ አድረዉ ነገ ጧት ላድርሳችሁ አለና ከማሞ መልስ ሳይጠብቅ መኪናዉን አስነሳ:: ማሞም እያቅማማ ተቃዉሞ ሳያሰማ መኪና ገባና

ዉስጥ

ቁጭ በማለት የተከተሉትን ዘቦችም ሦስቱን

ታጣቂዎች አስቀረና ሌሎቹ ሂደዉ አድረዉ ጧት እንዲመጡ አዘዛቸዉና በመኪና ወደ ዋናዉ ሰፈር ሂደን ከጣቢያዉ አስተዳዳሪ ቤት ገባን:: ከዚያም ብዙ በፊት የሚያዉቁኝ የሰፈሩ ሰዎች አንድ ባንድ በመምጣት ግቢዉን ሞሉት:: ሁኔታዉ አናደዳቸዉ ማሞን ቢገድሉት በወደዱ ::ግን ደግሞ ከመንግስት ጋር ላለመጋጨት ፈሩ : ሆኖም በሆነ መንገድ እኛን ከዚህ ለማዉጣት በሙሉ ልብ ተስማሙ ፤ግን እንዴት? ማሞም በነገሩ እየቆየ ቢቆጭም አሁን እኛን ቢለቅና አንዱ ሄዶ ቢያሳብቅ እዳ እንደሚገባ





ገመተ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

45

እዉነትም ነበር በኛ ፋንታ የፍየል:

ወጠጤ

ይዘፈንበታል ስለዚህ እሱን የማያስነካ እኛንም ከዚያ አምልጠን ወደምንፈልግበት ወደሱዳን የምንገባበት እድል በምን አይነት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት ሌሊቱን ተሰብስበን ስንመክር ካደርን በኋላ በአንድ ነገር ላይ ተስማማን እንዴት? እንዴትማ

አንደኛ ማሞ

በእቅዱ መሰረት ጉዞዉ በመኪና መሆኑ ቀርቶ በእግር እንዲሆን ሁለተኛ ሁሉም የያዝነዉ ድብል ሸክም አህያ እንዲጫን ሦስተኛ የአህያዉ ጭነት ወደአንድ በኩል ያመዘነ እንዲሆን:: እሱም የሚረዳዉ ጭነቱ ቶሎቶሎ ወደአንድ ጎን ስለሚያጋድል ጠመንጃ ይዘዉ የሚያጅቡን ሰወች ከጭነቱ ላይ ሲያተኩሩ እኛ ወደተመረጠልን ጫካ ስንደርስ በፍጥነት በጫካዉ ዉስጥ ሩጠን በመግባት ማምለጥ እንድንችል ሲሆን ማሞም ራሱን ላለማጋለጥ ከአጃቢወቹ ላይ በመጮህ ራሱን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ እንዲረዳዉ በሚል የማምለጥ ዝግጅቱ





ተቀየሰ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

46

ከአቶ ማሞ ማምለጥ የጧትዋ ፀኃይ ጮራዋን ፈንጥቃ በቀዝቃዛዉ ሌሊት የተንቆረዘዘዉ ጤዛ በመንገዱ ዳር ዳር የዘመመዉን የሰንበሌጥ እሣር አዝሞታል፣ ሠራተኞች በጧት ተነስተዉ ማጭድ መዶሻቸዉን በትክሻቸዉ ላይ ተሽክመዉ ወደየሥራቸዉ ይጓዛሉ:: እኛም ልብሳችንና ይዘን የነበረዉን ቀራቀንቦ በታሰበዉ መሰረት በአንድ አህያ ተጫነ : አጃቢዎቹ መሣሪያቸዉን አንግበዉ ከፌትና ከኋላ በመሆን ጉዞ ወደ ሚዛን ተፈሪ ጀመርን። እንደታሰበዉም አንድ ኪሎሜትር እንደተጓዝን ባንድ ወገን ቀሎ ባንደኛዉ ከብዶ የተጫነዉ አህያ በየጊዜዉ እያጋደለ ይወድቅ ጀመር::አጃቢዎቹም በየ መቶ ሜትሩ አህያዉን እያስቆሙ ጭነቱን ማቃንት ሆነ :በእንደዚህ ሁኔታ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር እንደሄድን አሁንም የአህያዉ ጭነት አጋደለና ወደቀ አጃቢዎቹ እንደተለመደዉ ለመጫን ሲቆሙ አቶ ማሞ የጧት አይነምድር ለመውጣት ለመዉጣት ወደጫካ ገባ አለና







ሱሪዉን ፈትቶ ቁጭ አለ : ስናይ ኣኛ ብቻችን ነን ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

47

ብዙ ጊዜ አልወሰድንም እርስ በርስ ተያየን : አሁን ነዉ የማምለጫ ጊዜ አለ ገሠሠ:

ወዲያዉም ጥቅጥቅ

ወዳለዉ በበቃ ጫካ ተፈተለክን:: አንድ ደቂቃ እንደተጓዝን ነበር አጃቢዎቹ መሰወራችን የተረዱት ሆኖም በድንገት ስለነበር ጫካ ዉስጥ የገባነዉ በየት አቅጣጫ እንደሄድንም ለማወቅ ስለተቸገሩ ይመስላል ብቻ አካባቢዉን በጠመንጃ ተኩስ አናወጡት :: ይሁን እንጂ እኛን ለማየትም ሆነ : ለመያዝ አልቻሉም ለማንኛዉም እኛ በግምት ለግማሽ ሰዓት ያህል እንደተጓዝን ማምለጣችን አረጋገጥንና ከዚያዉ ጫካ ዉስጥ ረፍት በማድረግ

ቀኑን ሙሉ ዉለን ማታ

ወደተባልነዉ ቦታ ሂደን ከተዘጋጅልን ቤት ገባን:: አቶ ማሞም ለብሳችን በአህያ እንደጫነ ወደ ሚዛን ተፈሪ የዘመቻ ጣቢያ ሂዶ እንደደረስ ዘማቾች ተቀብለዉ እነሱን ገድለህ ጥለህ ልብሳቸዉን ይዘህ ወደኛ መምጣትህ ሽልማት ለማግኘት ብለህ ነዉ? ::የጣልክበትን እስከምትነግረን ድረስ ከዚሁ መቆየት እለብህ በማለት እሥር ቤት እንዳስገቡት ሰማን። ከተዘጋጅችልን ጎጆ ትንሽ እንደቆየን አንድ ሰዉ ተመድቦልን

ወዲያዉኑ ጉዞአችን ወደ ሱዳን ደንበር





በሌሊት ጉዞ ጀመርን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

48

ሁለተኛዉ መንገድ መሪ አቶ ዳምጤ፣ ዳምጤ እባላለሁ ተወልጄ ያደኩት በመንዝ አዉራጃ ነዉ:: ከዚህ አካባቢ ወርቅ ከሚገዙ ሰዎች ጋር መስራት ከጀመርኩ ይሄዉና አሁን አሥር አመት ሊሆነኝ ነዉ:: በዚህም ምክንያት አካባቢዉን እንደ ተወለድኩበት አካባቢ ነዉ የማዉቀዉና ሀሳብ እይግባችሁ ሰዉም ቢያገኘን እኔን ስለሚያዉቁ ችግር የለም አለን ራሱን በመተማመን። አሁን የጨለመዉ ተስፋችን ተለወጠ:

ወደብርሃን ዉጋገን

የደከመዉ ሰዉነታችን ሁሉ እንደገና ሃይል

አገኘ ቢሆንም ጨለማዉ ገፍቶ ስለነበርና በዚያ አካባቢ ያንበሳዉ መንጋ ይበዛል : ዝሆኑ ይተራመሳል:: ጨለማው እየበረታ ለዓይን ከሩቅ ለማዪት ቀርቶ ተጠግቶም አስቸጋሪ ሆነ: በዚያ ላይ የምንሄደው መንገድ ይዘን ሳይሆን ደን እየጣስን ነው እየገፋን በሄድንቁጥር ከአውሬ ጋር የመጋጨቱ አደጋ እየ በረታ ሄደ: ያለን ምርጫ ከዚሁ ዛፍ ስር እሳት አንድደን አዳር ማድረግ ነበርና

ዳምጤ እሳት አነደደና እየሞቅን







በተቀመጥንበት ተጋድመን አደርን ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

49

ከሽፍታ ጋር መጋጨት በጧት ተነስተን ሰዉ የሚሄድበትን መንገድ በመተዉ ደኑን እየጣስን ጉዞ ጀመርን ፣ ዳምጤ በፊት ሆኖ ጤዛ ያዘለዉን የሰንበሌጥ ሣር በሁለት እጆቹ ዉሃ እንደሚዋኝ ሰዉ እየገላለጠ አነድ ሰዓት ከተጓዝን በኋላ ነበር ካንድ ከተደገነ የጠመንጃ አፈሙዝ

ፊት ለፊት

የደረስነዉ :: ሰዉየዉ ዳምጤን

ባየ ጊዜ እንደ ብራቅ በመጮህ

ወደኛ የደገነዉን ጠመኘጃ ወረወረና ጩኸቱን ቀጠለ:: ምንድን ነዉ!! አልነዉ ዳምጤን ፣ ሰዉየዉ ለካ ሦስት ሰዉ ገድሎ በፖሊስ ስለሚፈለግ ብቻዉን በጫካ ኑሮዉን አድርጓል:: በየጊዜዉም ፖሊስ ይመጣል እያለ ስለሚሰጋ ሁልጊዜ እንደባነነ ነዉ የሚኖረዉ ፣ ታዲያ እኛን የዘመቻ ልብስ መለዮ ለብሰን ባየን ጊዜ ፖሊስ ሊይዘኝ መጣ በማለት ሳንቀድመዉ ሁላችንም ባንድ ጠይት ለመግደል ይጠባበቃል፤ በድንገት የሚያዉቀዉን ደምጤን ያያል :







እነማንን ይዘህብኝ መጣህ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

50

አለ ! አይ ሀኪሞች ናቸዉ ይለዋል ዳምጤ ::በዚህ ጊዜ ነበር ወይኔ ሳላዉቅ ፖሊስ መጣብኝ ብየ ገድያችሁ ነበር በማለት እየዬዉን ያቀለጠዉ:: ሽፍታዉ ለማደሪያ ከሰራት የሣር ጎጆ ዉስጥ አስገባን ባንዲት ቅል ማር በጠበጠና አንዲት የእንጨት ስር የ መሰ ለች ነገ ር ጨ መ ረበ ት የ ተ በ ጠ በ ጠ ዉ ማ ር ወዲያዉኑ ፈላና የደረቀ ጠጅ ሆነ :: ያን ጠጅ ባንድ የቅል ፋጋ ቀድቶ ሰጠንና እየተቀባበልን ጠጣነዉ : ግሩም ጠጅ በማለት አደነቅነዉ ዉእውነትም

ግሩም

ነበር ፤ትንሽ የሚበላም ሰጠንና ከበላን በኋላ ሸኝቶን ተለያየን::

የአኮቦ ሕዝብ እንግዳ አቀባበል ከግማሽ ቀን ጉዞ በኋላ ትንሽ ሰፈር ደረስንና አዳር ሆነ.:: ያካባቢዉ ነዋሪዎች ሴቱም ወንዱም ልብስ የማይለብሱ ናቸዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቅ ሰዉ እንደተፈጠረ እርቃኑን ሆኖ ማየት ለገሠሠና ለሀጎስ









አዲስ ነገር ይሁን እንጂ ለኔ አዲስ ነገር አልነበረም::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

51

ምክንያቱም ከዚያ በፊት ወደ እድገት በህብረት ዘመቻ ከመዝመቴ በፊት ወደማጂ የኢትዮ ሱዳን ደንበር ጠባቂዎች ከሚገኙበት ቦታ ሄጄ ነበር :: አካባቢዉ የሚኖሩት ሱሪና ብሔረሰቦች የሚባሉ ሲሆኑ ወንዶቹ ፍጹም እንደተፈጠሩ ናቸዉ :: በተፈጥሮ ጠቁሮች ናቸዉ: ታዲያ ከዚያ ጠቁረታቸዉ ላይ በነጭ ጭቃ ሰዉነታቸዉን ይሸልሙታል ከጭንቅላታቸዉ

ላይ የሚቀቡት ቀይ ጭቃ ልዩና

ፀጉሯን ቀለም የተቀባች አፍሪካዊት ሴት ያስመስላቸዋል: የፊት ጥርሳቸዉ ይወልቃል፣ ጆሮአቸዉ ይበሳና ቆዳዉን በመለጠጥ ሰፌ እንዲሆን ይደረግና ለዕቃ መያዥያ ይጠቀሙበታል:: በተለያየ ምክንያት እርስ በርስ ስለሚደባደቡና ከብቶቻቸው ጋር

አብረው

ሰለሚዉሉ ረዥም ዱላ

ሁሉም ይይዛሉ ወንዶቹ የሚኖሩት በከብት ጥበቃና ባደን ሲሆን የቤት ውስጥ

ሥራና እርሻ የመሳሰሉትን







የሚሰሩት ሴቶች ናቸዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

52

ሴቶቹም እንደወንዶቹ ራቁት ሲሆኑ በትንሽ ቆዳ መሳይ ነገር ሀፍረተስጋቸዉን ይሸፍናሉ: የታችኛዉ

የፊት

ጥርሳቸዉ ይወልቅና የታች ከንፈራቸዉን በመብሳትና ብዙ ጊዜ በመለጠጥ ያሰፉታል::ከዚያም ትንሽ ምጣድ የመሰለ ገል ከጭቃ በመስራት ያሰገቡበታል በዚህ ሁኔታ በየጊዜዉ በመወጠር ያሰፉትና እንደከንፈራቸዉ ሁኔታ ይሰፋል በጣም ሰፊ የከንፈር ምጣድ ያላትም ሴት ቆንጆ ተባላለች ሴትም በዚህ አካባቢ ቆንጆ የሚያሰኛት ይኸዉ የከንፈር መስፋት ነዉ ::

በሱሪና ባህል ለጃገረድ ከማገባቷ በፊት ከብዙ ወንደ ጋር የግብረሥጋ

ግንፑነት ማድረግ

አለባት ፤ይህም አንዱ

የተፈላጊነትና የቁንጅና መለኪያ ነዉ። ልጃገረዷ ባል የምታገባዉ ከብዙ ወንድ ጋር መገኛኘቱ ሲበቃት ነዉ ::

የሚገርመዉ ግን በዚህ ከወንድ ጋር ግንኑነቷ እንዳታረግዝ የምትበላዉ እፅ ነገር እንዳለ ሲሆን ለመዉለድ ስትፈልግም እንደዚሁ ካገባች በኋላ የምትበላዉ ሌላ የተለየ እፅ አላቸዉ:: ባል ካገባች በኋላ





ግን ልጅ ትወልድና ባሏን ማገልገል ትጀምራለች ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

53

ባል ለማግባት ስትፈልግ ግን ያካባቢዉ ሕዝብ ይሰበሰባል ፤ባል ፈላጊዋ ልጃገረድም ትቀርባለች : ለማግባት

የሚፈልጉ ጎረምሶች ይቀርቡና

እያንዳንዳቸዉ ለዉድድር ያዘጋጁትን ዱላ ይዘዉ ለዱላ ዉድድር ይቀርባሉ : በዚህ የዱላ ዉድድር ያሽነፈ ልጅቷን ያገባል። በድብድቡ ጊዜ ካልሆነ ቦታ ተምትቶ አንደኛዉ ቢሞት ገዳዩ በሬ አርዶ ሕዝቡን ይጋብዝና እንደ ደም ካሣ ተቆጥሮ ነገሩ በዚያ ያልቃል::

እንግዲህ ልጃገረዷ

ካገባች በኋላ ግን ግብረ ሥጋ ከባሏ ጋር ስትፍልግ ባሏ ከብት የሚያጥጣበትን ቦታ ስለምታዉቅ ከቦታዉ በመሄድ እሱ የሰጣትን ዱላ ተክላ ትሄዳለች ባልም የትኛዋ ሚሰቱ ዱላዉን እንደተከለችዉ ስለሚያዉቅ ዱላዉን ይዞ ማታ ወደሰፈር ይሄዳል ከሰፈሩ ሲደርስና ዙሪያዉን ከተሰሩት ጎጆዎች ማህል ላይ ይቀመጣል:: ከዚያም ሚስቶቹ ባላቸዉ እንደመጣ ሲረዱ ሁሉም ያዘጋጁትን ምግብ እያመጡ ያቀርቡለትና ወደ ጎጇቸዉ ሲገቡ አባዉራዉ ምግቡን በልቶ ሲጨርስ ሴቶቹም የተረፈዉን ወስደዉ ይመገባሉ :: ከዚያም ዱላዉን ከተከለችዉ ሴት ቤት ይገባና ለሱ መኝታ ከተሰራችዉ





መደብ ላይ ይተኛል ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

54

ጎጆዋ ሁለት መደብ ሲኖራት ከመደቦቹ መሀል እሣት የሚነድበት ምድጃ አለ :: መጀመሪያ ከየራሳቸዉ መደብ ከተኙ በኋላ ለመገናኘት ሲፈልግ በዱላዉ በመምታት ምልክት ያሳያትና ሴትዮዋ ወደ ሰዉየዉ መደብ በመሄድ ጉዳያቸዉን ይፈፅማሉ። ስለዚህም እኔ ከነዚህ ሰዎች ጋር ትንሽ ስለቆየሁ ለኔ እነዚህን ልብስ አልባ ሰዎች ሳይ አዲስ ነገር ያልሆነበኝ። የደረስነዉ ወደማታ ነበርና ሴቱም ወንዱም ሁሉም እንደተፈጠሩ ነበሩ:: እኛ ከነደደዉ እሳት ፈንጠር ብለን ተቀመጥን :: እነሱ በእሳቱ ዙሪያ ተቀምጠዉ ያዘጋጁትን ምግብ ከመመገባቸዉ በፊት ለኛ አንድ ዶሮ ይዘዉ መጡና እኛዉ ራሳችን አርደን እንድንበላ ሰጡንና ዳምጤ ተቀበለና ዶሮዋን አረደና ጠባብሶ በላን:: ትንሽ ቆይተዉም አታሟቸዉን እየመቱ በባህላቸው መዝፈን ጀመሩ : ወጣት ልጃገረዶች

ያጎጠጎጠ

ጡታቸዉን ገትረዉ ከወተት በነጣ የጥርስ ፈገግታ







እያቀነቀኑ የሚያደርጉት ዉዝዋዜ እጅግ ይማርክ ነበር።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

55

ከዚያም ጥግ ይዘን የደከመዉን ጎናችን ሰንበሌጡን እሣር

እንደ ጉዝጓዝ ተጠቅመን ድንጋይ ተንተርሰን

አደርን:: ጧት ከእንቅልፋችን እንደነቃን ዳምጤ አንድ መንገድ የሚያሳይ አገናኘንና ወደ ቤቱ ተመለሰ። ከአዲሱ መንገድ መሪ ጋር ወደ አኮቦ ወንዝ አቅጣጫ ጉዞ ጀመርን፣ የጧቷ ፀሓይ ፈንጥቃ ከሚያምረዉ የተፈጥሮ ዉበት ጋር ተቀናጅቶ ጥዋቱን

የሚያምር

አድርጎታል።ትንሽ ሰዓታት እንደተጓዝን ነበር ከአንድ ቁልቁለት ቦታ ተንደርድረን በድንገት ደልዳላ ቦታ ላይ ከተተከለች ድንኳን በር ላይ የደረስነዉ:: በድንኳኗ በር ላይ የፖሊስ የበርሃ ባርኔጣ በእንጨት ላይ ተንጠልጥሏል ፣ድንኳኗ በር ላይ አንድ መካከለኛ እድሜ ያለዉ ሰዉ መሣሪያዉን ከጎኑ አጋድሞ ፊትለፊቱ የተቀመጠዉ አሽከሩ የሚያነደዉን እሳት እየሞቀ ቁጭ ብሏል :: ስናየዉ የመሰለን ጠረፍ ከሚጠብቁት ወታደሮች አንዱ ነው ብለን አመን ግን ፊት ለፊት ከተያየን በኋላ የት







መሸሽ ይቻላል ብንሮጥስ የት ልናመልጥ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

56

እንዲያ እግራችን እየራደ ሰዉነታችን እየተንቀጠቀጠ ወደፊት እንጂ ወደኋላ የመመለስ እድል አልነበረንምና በመንተፍረቱ ተጋፍጠን ወደሱ ተጠጋንና ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በነደደዉ እሳት ዙሪያ እንድንቀመጥ ጋበዞን ተቀመጥን:: ለምን እንደመጣን ጠየቀን : ሐጎስ ፈጠን ብሎ ወርቅ ነጋዴዎች ነን አለዉ ፣ አካባቢዉ የወርቅ ቆፋሪዎች ቦታ ስለሆነ ፣ ሰዉየዉም የዋዛ አልነበረምና ለመሆኑ የወርቅ ዋጋ ስንት ደርሷል አሁን አለ ሀጎስ ቀልጠፍ ብሎ 80 ም 90ም ይሸጣል አለ ፈገግ አለና ወሬዉን በመቀየር ሰሞኑን ብዙ ሰወች አገር ጥለዉ ወደጎረቤት አገር እየተሰደዱ ነዉ ይባላል ለመሆኑ ችግሩ ምንድን ነዉ? አለ:: እኛም ሊሆን ይችላል እኛ ግን የሰማነዉ የለም ለመሆኑ ወደየት ሄዱ ይባላል? አልነዉ ሰሞኑን የጠረፍ ጠባቂ ወታደሮች መጥተዉ ወደጎረቤት አገር የሚሄዱ ሰዎች





ስታዩ ቶሎ ለኛ ሪፖርት አድርጉልን ብለዉን ሄዱ አለ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

57

በዚህ ጊዜ እሱ ወታደር እንዳልሆነና ወርቅ ነጋዴ እንደሆነ ስለተረዳን ፍርሀታችን ለቀቀን አያይዘንም ባካባቢዉ ወዳሉ ወርቅ ቆፋሪውች መሄድ እንደምንፈልግ ነገርነዉ:: እሱም አቅጣጫዉን በጁ እየጠቆመ አሳየን መሄድ የፈለግነዉም ወደዚያዉ ስለሆነ ተጣድፈን እነሱን አናግረን እንመለሳለን ብለን ተለየነዉ።ትንሽ አንደሄድን ወርቅ ቆፋሪዎች ያረፉበት ካምፕ ደረስን:: ግን ሰዎቹ ወደቁፋሮ ስለሄዱ አንድ የካምፕ ጠባቂ ብቻ ሥጋ በድሰት እየቀቀለ አገኘነው:: ሰላም ካልነዉ በኋላ ወርቅ ነጋዴዎች እንደሆን ነግርነው ስላካባቢዉ ጠየቅነዉ ሀሳባችን ከነሱ መካከል ወደ ደቡብ ሱዳን የሚወስደን መንገድ አዋቂ ለመፈለግ ነበር ነገር ግን ሁሉም ወደ ቁፋሮ ስለሄዱ እስኪመለሱ ጠብቋቸዉ ስላለን ቁጭ ብሎ መጠበቅ ግድ ሆነና ተቀመጥን። ከቀኑ 12ስዓት ሲሆን ሁሉም ተመለሱ፤ ሰላምታ ከተለዋወጥ በኋላ ትንሽ እንደቆየን አንድ ከጋምቤላ ለወርቅ ቁፋሮ የመጣ ወጣት ወደኛ መጣና በጥሩ





አማርኛ ራሱን በማስተዋወቅ የጋምቤላ የ8ኛ ክፍል

እኔና

የስደት ጉዞዬ

58

ተማሪ እንደሆነና ከትንሽ ግዜ በኋላ ሂዶ ትምህርቱን እንደሚቀጥል ነገረንና እናንተን በተመለከተ እነዚህ ሰዎች እየተወያዩ ነዉ አለን። ምን እያሉ ? እሱማ በቀደም የጠረፍ ወታደሮች መጥተዉ በዚህ ወደሱዳን ጠፍተዉ የሚሄዱ ዘማቾች አሉና እንዳያችሁ ለኛ ንገሩን ለናንተም ይዛችሁ ካስረከባችሁ መንግሥት ሽልማት ይሰጣል ስላለ ሽልማቱም እንዳያመልጣችሁ ብለው ስለሄዱ እናንተን ሆን ብለዉ ወስደዉ ለመስጠት እየተወየዩ ነዉ አለን:: እኛም ቅጭም ባለ መልክ እኛ ወርቅ ነጋዴዎች ነን አሁንም ከዚህ ማዶ ካለዉ ካምፕ ነዉ ሂደን የምናድረዉ : እንዲያዉም አሁን ስለመሸብን ቶሎ ሳይጨልም እንሂድ ከፈለጋችሁ ተከተሉን አልንና ለመሄድ ተነሳን ለሰዎቹም ይሄንኑ ስለነገራቸዉ ተረጋጉና እሽ አሉ :: ወዲያዉ ወደ ሰውየዉ ካምፕ የምንሄድ መስለን ትንሽ እንደተጓዝን መንገድ ቀይረን





ወደተቃራኒዉ በሩጫ ተጉዘን አመለጥን ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

59

ምዕራፍ- 3 አኮቦ ወንዝ፣ ከወርቅ ቆፋሪዎቹ ተለይተን በሰባራ መንገድ ተራራ እየወጣን ዳገት እየወረድን ጉዟችን ቀጠልን :: ግን አንዱን

ተራራ ወጥተን እንደገና እንወርዳለን መሪ

የለንም ካርታ ወይም ኮምፓስ የለንም ለነገሩ ከእንደዚህብ ያለ ጠፍ ቦታ ምኑ ተብሎ ምኑ ይባላል ባካባቢዉ ከዱር እንስሳት በቀር ሰዉ የሚባል ነገር የለም ብቻ አንዳንዴ ከብቶች ያደሩበትን ቦታ እናገኛለን የሄዱበትን አቅጣጫ እየተከተልን ብዙ እንጓዛለን ነገር ጎን ሰዉ ልናገኝ አልቻልንም :: ከወርቅ ቆፋሪዎቹ ከተለየን አሁን አምስተኛ ቀናችን ሆነ:: ከዚህ ሁሉ ጉዞ በኋላ ወደመጣንበት መመለስም የማይሞከር ነዉ : ወደፊት እንዳንሄድ የት ብለን ! በካርታ ያነበብነዉ የደቡብ ሱዳን ፒቦር ከተማ የሰማይ







ያህል እራቀን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

60

በጣም ተስፋ ከመቁረጣችን የተነሳ እርስ በርሳችን መጣላት ጀመርን:

ለማንኛዉም ለጊዜዉ ካለንበት

ለማደር የምናነደው

እንጨት ስንለቃቅም አታሞ

የሚመታ የሰዉ ድምፅ ሰማንና ሰዉ ! አለ ገሠሠ :: እኔም ዘፈን ሰማሁ አለ ሀጎስ ተቀበለና ወዲያዉ ጊዜ ሳናጠፋ እየተሯሯጥን ወደ ምንሰማዉ ድምፅ ሄድን:: ከአካባቢዉ ስንደርስ ከሰወቹ ከመድረሳችን በፊት አንድ ትልቅ ወንዝ

ደረስን ይህ

ወንዝ

የተሻገርነዉ

ለካስ ከአምስት ቀናት በፊት

የአኮቦ ወንዝ ነበር፣ ሰሞኑን ከባድ ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ወንዙን ያለ ዋናተኛ

እርዳታ

መሻገር የማይሞከር

በመሆኑ ማዶ ያሉትን ሰዎች እንዲሰሙን ጮክ ብለን ተጣራን:: ጥሩ አጋጣሚ ሆነና ሰወቹ ወዲያዉ መልስ ሰጡ: እና መጥተዉ አሻገሩን:: ለካስ የኢትዮጵያን ደንበር አልፈን ሱዳን መሬት ያለን የመሰለን ከዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ









ስንሽከረከር ነዉ : የተቀበሉን ሰዎቹም ኢትዮጵያዉያን ነበሩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

61

አሁን እኛ ለሰዎቹ ለምን አንደመጣን አሳማኝ ምክንያት መስጠት ነበረብን ለዚህም ራሳችን የመንግሥት ሀኪሞች አድርገን አቀረብን :: በአካባቢዉ ሰንከትብ ሰንብተን መዳህኒት ለማምጣት ወደሱዳን ከተማ ፒቦር ሂደን መዳህኒት ማምጣት ስላለብን መንገዱን የሚያዉቅ ሰዉ ተባበሩን አልናቸዉ:: ለማሳመን እንዲሆንም ከያዝኩት የፈንጣጣ ክትባት መዳሃኒት ባጋጣሚ ይዘን ስለነበር ልጆችን ከተብናቸዉ። በዚህ ጊዜ አመኑን: የሚሸኘንም ተነጋገሩና አንድ ጀግና መረጡ:

እሱም ብቁነቱን ለማሳየት ጦሩን እየነቀነቀ

ፎካከረ ነገሩ ግራ ገባንና ብዙም መመራመር ሳንፈልግ አደርንና በጧት ተነስተን እንደገና አኮቦ ወንዝን ተሻግረን ጉዞ ጀመርን:: መንገድ መሪያችን ትንሽ ትንሽ ኦሮሞኛ ከመናገሩ በቀር የምንግባባዉ በጥቅሻ ነው ፣ ሰዉየዉ ጀግና ነዉ!፣ እያንዳንዷን ቋጥኝ ያዉቃታል : ቁምጣ ሱሪዉን በግራ ተክሻዉ

ሰቅሎ ጦሩን በቀኝ እጁ ሰግሮ ይዞ ዓይኑ











በያንዳንዷ ቁጥቋጦ ያማትራል ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

62

ትንሽ እንደሄድን ተከሻዉ ላይ የሰቀለዉን ሱሪ ታጠቀ እኛንም የያዝነዉን ዱላ ጠበንጃ አስመስለን እንድንይዝ አዘዘን :: አኛም

እሱ እንዳለን አደረግን

የለበስነዉ

የዘማች ልብስ ከወታደር ልብስ ጋር ስለሚመሳሰል እኛንም ወታደሮች አስመስሎናል:: የሰዉየዉ ሁኔታና እያደረገ ያለዉ የጦርነት አይነት ዝግጅት ግን ከዚያ ማንም አገር ከማይቆጣጠረዉ በርሃ ላይ ግራ አጋባን ብዙ አልተራመድንም ሰዎች ከሩቅ ወደኛ አቅጣጫ እየመጡ እንደሆነ በጁ እጣቱን ቀስሮ አሳየን :: ሰዎቹ የታጠቁ ናቸዉ : ከዚህ ምድረ በዳ ሰዉ ማየት ለብዙ ቀናት ከሰዉ የተለየ ሰዉን ይናፍቃልና በተለይም በሱዳን መሬት ለኛ ልዩ አጋጣሚ መስሎ ታየን:: ሰዎቹ እየቀረቡ ሲመጡ መሪያችን ጥሩ ቦታ እንድንይዝ አደረገን:

ለነገሩ ከኛም መካከል ገሠሠ የዓየር ኃይል

ምሩቅ ስለነበርና እኔም ከዘመቻ ጣቢያዉ እያለን ራስን መከላከል በሚል ወታደራዊ ስልጠና ወስጄ ነበር እናም







ጥሩ የመከላከያ ቦታ መረጥንና ያዝን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

63

ሰዎቹም መምጣታቸዉን ቀጠሉና 200 ሜትር ያህል ሲደርሱ ሰዉየዉ ድምፁን ከፍ አድርጎ እነዚህ ወታደሮች ናቸዉ ብትመጡ

ከዚህ በኋላ አንድ እርምጃ ወደዚህ

እናንተን ገድለን መሣሪያችሁን ማርከን

እንሄዳለን አላቸዉ። እነሱም በድንጋጤ አልፎ ለመሄድ እንጂ ለማጥቃት እኮ አደለም አሉ፣

እናንተን

የለም የናንተ መንገድ

በዚያ እንጂ በዚህ አደለም እልቅስ እንዳትበላሹ: ወደምትሄዱበት ቀጥሉ አላቸዉ :: በዚህ ጊዜ ተመለሱና ወደሚሄዱበት አቅጣጫ ለእይታ እንደተሰወሩም

መንገድ ቀጠሉና ሄዱ ትንሽ ከያዝነው ምሽግ ወጥተን

የምንሄድበትን አቅጣጫ ቀይረንና በሌላ በኩል መሮጥ ጀመርን:: በጣም ብዙ ከሮጥን በኋል ፀሐይዋም እየደከመች ስትሄድ መሪያችን ወደ አንድ ተራራ ወሰደን ከተራራዉ ጥግ ስንደርስም የእግር ዱካ ለማጥፋት ደንጋይ ብቻ እየረገጥን ተራራዉን ወጥተን ከአንድ ዋሻ ዉስጥ ገባን መሪያችን

እኛን ወደ ዋሻው ውስጥ እንድንገባ





አድርጎ ከዋሻዉ በር ላይ ጦሩን ወድሮ ቁጭ አለ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

64

ቀኑን ሙሉ ያለምግብ ስንሮጥ ስለዋልን ሰዉነታችን ዝሎ ስለነበር እንቅልፍ አሸለበን ሆኖም ግን እንቅልፍ ሳይሆን ቅዠት ነበር በመካከል ሀጎስ ስለፈራ ተነሳና ቦታ ቀይሩኝና እኔን ወደ ዉስጥ አስተኙኝ አለ:: በፍራቱ ተሳሳቅንና አስተኛነዉ፣ የሳቅነዉ አንድ ቀን ከሀጎስ ጋር

ስለፖለቲካ ስናወራ ኤርትራ ሂዶ ለነፃነት

መዋጋት እንደሚፈልግ አጫዉቶን ስለነበር ታዲያ እንደዚህ የምትፈራ ከሆነ እንዴት ሂደህ ለመዋጋት አሰብክ አልኩትና ተሳስቀን ተኛን። ጨለማዉ ተገፎ የጧት ጎህ ሲቀድ መንገድ መሪያችን ተነሱ እንሂድ አለ : የመጣንበትን መንገድ ትተን በሌላ በኩል አሳብረን ተራራዉን እንደወረድን እነዚያ መንገድ ላይ ያገኘናቸዉ ሰዎች ትናንት ማታ ወደ ተራራዉ ስንወጣ ዱካችን ለማጥፋት ድንጋይ እየረገጥን መሄድ ከጀመርንበት ቦታ ላይ እሳት አንድደዉ ተኝተዉ





አየናቸዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

65

መሪያችን በአመልካች ጣቱ እየጠቆመ አያችሁ ዱካችን ባናጠፋ ኑሮ ሌሊት መጥተዉ ይገድሉን ነበር አለ ፣ እንዴ ለምን ይገሉናል ምን አደረግናቸዉ? አልኩት ምንም አላደረግናቸዉም ግን እነዚህ ሰዎች በህይወታቸዉ ሰዉ ፈልገዉ ገድለዉ ብልቱን ይሰልቡና ወስደዉ ከሰፈራቸዉ ጀግና በመባል እየፎከሩ የሚፈልጓትን ሚስት የሚያገቡት ከዚያ በኋላ ነዉ:: አህ!ታዲያ የሰለቡትን ብልት ምን ያደርጉታል? እሱማ በደንብ ደርቆ ከግድግዳ ላይ ይሰቀልና እንደ ጌጥ እቃ አስረዉ ያጌጡበታል እናም

የጀግንነት መለያ ይሆናል

።ይገርማል አለ ገሠሠ ለካስ እንደዚያ ሰዉ በናፈቀን ግዜ ከብት የሚያረቡ ዘላኖች መስለዉን የከብቶችንና የሰው ዱካ እየተከተልን ስንፈለሰግ የሰነበትነዉ ራሳችን ሄደን ልንገደልና ልንሰለብ ነበር አለ !? ይገርማል አለ:: ሐጎስ ቀበል አደረገና ወይኔ ልጀን ሳላያት በሱዳን በርሃ ደብዛዬ ሊጠፋ ነበር አሁንስ ገና መች አለቀልኝ! ። አለና በዛ ትላልቅ ዓይኖቹ እንባዉን እንደ ጅረት አወረደዉ።እረ እባካችሁ እኛስ

ከሰዉ ልንገናኝ ተቃርበናል ይሄ ምስኪን መንገድ መሪያችን እኮ ገና የመጣነዉን በርሃ ተመልሶ ሊጓዝ





ነዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

66

አስቡ አነዚያ ሰዎችም ሆኑ ሌሎች እንደነሡ ዓይነቶች እኮ ብዙዎች ይኖራሉ አልኩና ለማጽናናት ሞከርኩ። ወዲያዉም አሁን ከአደጋ ነፃ ነንና የምንበላዉ እንፈልግ አለና መሪያችን ጦሩን ቀስሮ እየተሳበ ያዘግም ጀመር : ሳይቆይ ካጠከባችን የአሳማ መንጋ ጋር ተያየን:: መሪያችን ፈጠን ብሎ ወደ አዉሬዎቹ ተፈተለከ ::

ትንሽ እንደሮጠ አዉሬዎቹ ከርከሮዎች

ስለነበሩ

ሩጠዉ ጉድጓድ ዉስጥ ገብተዉ ተሰወሩ : መሪያችን ግን ተስፋ አልቆረጠምና ከጉድጎዱ በር ቆሞ ጦሩን አዘጋጅቶ በእግሩ ጉድጓዱን እየመታ ከርከሮ: ከሮ: ብሎ ቢጣራም ሰምቶ ብቅ ያለ ከርከሮ አልነበረም:: አሁን ድካሙም ርሃቡም እየተጫጫነን መጣ: የሐጎስ ጫማም ተቀደደና በእግሩ ደም ይፈስ ጀመር:: በጨርቅ ቢጤ አሰርንለትና እንደምንም አዝግመን ከአንዲት ጎጆ ቤት ደረስንና ለማደር እረፍት አደረግን;;ከፊታቸዉ ፈገግታ የማይለያቸዉ ጠና ያሉ እናት ነበሩ: እንዳጋጣሚ





የተቀበሉን ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

67

የበቆሎ እሸት ጊዜ ስለነበረ በቆሎ ትበላላችሁ ብሎ ጠየቀን : በጣም እንጂ ! አልኩት : ከገመመዉ እሳት ላይ የሴትዮዋን ብዙ የደከሙበትን በቆሎ እያበሰለ ይሰጠን ጀመር :: ይህ ምሽት እጅግ የማረሳዉን የልጅነት ትዝታዬን የቀሰቀሰብኝ ወቅት ነበር :: አዎ: በትዝታ ፈረስ ወደኋላ ሸመጠጥኩና ወደ ትውልድ ሰፈሬ ደቡብ ጎንደር እብናት ወረዳ ዝሃ ሚካኤል

በምትባል ትንሽ

የገጠር መንደር ነበር ተወልጄ ወደዚህ ዝባዝንኬ ዓለም የመጣሁት:: ዝሃ ሚካኤል ከባህር ዳር 120 ኪሎ ሜትር ከደብረታቦር 40 ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን የምትገኝ ቦታ ስትሆን ለእብናት ከተማ 15 ኪሎ ሜትር የምትቀርብ ቦታ ሆና በተራራ እንደ ”በ ” ቅርፅ ሆና ከትልቁ ወንዝ እርብ ግድብ 10 ኪ/ሜትር ስትርቅ ክረምት ከበጋ የማይደርቅ ወራጅ ወንዝ መሃሏን ሰንጥቆ ወደ እርብ የሚቀላቀለው ጥቁር ውሃ ለአካባቢው የመኖር ዋስትና ሆኖ ቆይቷል:: አካባቢዉ በደን የተሸፈነ በመሆኑ ለእርሻና ከብት እርባታ አመች ነው :: ገበሬዉ ትንሽ አርሶ ብዙ የሚያመርት

ቢሆንም ጣሊያን ከሰራዉ ኮሮኮንች





መንገድ በቀር ከእድገት የራቀ ነው።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

68

በዝች የገጠር መንደር ትልቁም ትንሹም ማታ ማታ ሲሆን ማህል ላይ በሚነደው እሳት ዙሪያውን እንከብና አባቴ በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ጊዜ ጣሊያንን እንዴት እያደፈጡ ይወጉት እንደነበር እያነሳ የአርበኝነት ተጋድሎዉን በኩራት:

የሠራዉን ጀብዱዎች

ከተዋጋባቸዉ ቦታዎች ጋር እያጣቀስ ያወጋን ነበር ።

እኔም የሱ ተጋብቶብኝ ነዉ መሰለኝ ጥቃት አልወድም: አባቴ የሠራዉን የአርበኝነት ጀብዱ እኔም እንድሰራዉ እመኝ ነበር:

በዚህም የተነሳ

በጣም ትንሽ ሆኜ

ትልቆቹን ሁሉ እደበድብ ነበር:: ከሰፈሩ ልጆች በጣም ቀጭን ስለነበርኩ ግብግብ ሲገጥሙኝ ወዲያዉ ይደበልሉኛል: እኔም በስር እሆንና ደረታቸዉን እንደድመት በእንክሻና በጥፍሬ ስቧጭራቸው በላይ ሆነዉ ኡ ኡታቸዉን ያቀልጡታል: ቶሎ ገላጋይ ካልመጣ ደረታቸዉን ጃርት የበላዉ ዱባ





ሳላስመስላቸው አለቃቸውም ነበር ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

69

በዚህ የተነሳም ዝናዮ ከሰፈር አልፎ

ደብሩን

በሙሉ

ስላደረሰዉ ትንሹም ትልቁም ይፈሩኝ ነበር: ፀባዬን

አባቴም ይህን

በጣም ይወደው

ነበር : እንዳዉም ሁሉም ሰዉ እንዲፈራኝ

ሆን

ብሎ

ያላደረኩትን

ሁሉ

እኔ

እንዳደረኩት

እያደረገ

ያስወራልኝ ነበር :: በአንድ ወቅት ወደማታ ላይ እንደተለመደው ካባቴ ጋር ከአፋፍ ላይ ቁጭ ብለን ሳለ ልጆች

ከማዶ ይጣራሉ: ከነሱ ጋር የነበሩ አዳኝ

ዉሾችም ይጮኃሉ፣ አባቴ ቶሎ ቤልጅጉን አቀባብሎ ሲሄድ እኔም ተከተልኩት:: ከቦታዉ እንደደረስን ከአንድ ዛፍ ላይ

ትልቅ ነብር

ተቀምጦ ውሾቹ ከስር አነጋጠዉ ይጮሃሉ :: አባቴ እኔን ወደ ኋላዉ አደረገኝና ነብሩን አነጣጦሮ





ገደለዉ።

በ3 ጥይት

እኔና

የስደት ጉዞዬ

70

የወደቀዉን ነብር ይዘን ሰፈር ስንደርስ ይሄዉላችሁ ሞላ ተኩሶ የገደለዉ ነብር፣ አለና አሞገሰኝ :: ወሬዉ ሰፈሩን አልፎ ደብሩን አዳረሰዉ:: ከዘያማ ማን ደፍሮኝ !

ሁሉም ይፈራኝ ያደንቀኝም

ጀመር። ይህ ደግሞ እኔም በጀብደኝነቴ ቀጠልኩበትና ያለ አቅሜ እንደ ትልቆቹ ራሴን ማዬት ጀመርኩ: ፀባዬ ሁሉ ጀብደኝነት ሆነ እልክኛ በመሆኔ

ተሸንፎ መግባት

የማይሞከር ነዉ:: ታዲያ አንድ ቀን ታላቅ ወንዱሜና ጓደኞቼ የሚያድሩት ዉጭ ከብቶችን እየጠበቁ ስለነበር እኔም ዉጭ ማደር አለብኝ ብዬ ተነሳሁ: አባቴም ፈቀደልኝ ሌሊቱ ጨረቃ ደምቃ የምትታይበት ምሽት ስለነበር:: ከዋከብቶች እንደ ቆሎ ሰማይ ላይ ፈሰዉ አንዱ ወደ አንድ አቅጣጫ እንደ ሮኬት ሲተኮሱ ይታይ ነበር: ይሄን እያየን ትንሽ እንደቆየን

አሁን ሂደን በቆሎ አናምጣ







ተባለ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

71

የት ? አልኳቸዉ ከዚያ ማዶ የአጎታችን በቆሎ ሰርቀን እንምጣ አሉኝና ቀስብለን ድምፅ ሳናሰማ ሂደን በቆሎውን ጨንግዘን: ጨንግዘን : ተሸክመን መጣንና በገመመዉ እሳት እየጠበስን ስንበላና

ስንጫወት

አደርን:: ከዚያም ይሄን ምስጢር ለማንም እንዳትናገር የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጠኝ እኔም ላልናገር ቃል ገባሁ:: በማግስቱ

አባቴ ነገ ቤተክርስቲያን አብረኸኝ

ስለምትሄድ ከቤት ታድራለህ አለኝ እኔ ደግሞ ሞቼ እገኛለሁ አልኩ ፣ እንዴ!

ይሄን ልጅ ምን

አስለምዳችሁታል ሲል አጉረጠረጠ:: ሁሉም ፀጥ አሉ አባቴ ቁጣዉን ትቶ ከት ብሎ ሳቀና ረስቼ ለካ!

የበቆሎ ጊዜ ነዉ ለመሆኑ የማነን ጓሮ

አራቆታችሁ ? አለ የመለሰ የለም ሁሉም አንገታቸውን ደፍተው ፀጥ አሉ:

እኔ ቀበል አድርጌ እንዴት አወክ?

አንተም በልጅነትህ ስታደርግ ነበር ማለት ነዉ!? ታዲያ እኛን ለምን ትከለክላለህ እኛም በጊዜያችን

ማድረግ





አለብን እኮ: አልኩ አባቴ መቆጣቱን ትቶ በሳቅ ፈነዳ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

72

ቤቱ ሁሉ ሳቅ በሳቅ ሆነ ፣"አንተን ባረገኝ"! አለ ታላቅ ወንድሜ ከቤቱ ላባታችን ደፍሬ የምናገር እኔ ብቻ ነበርኩ ምናልባት የመጨረሻ ልጅ ስለሆንኩም መሰለኝ አባቴ ከሁሉ ልጆች እኔን ይፈራኛና ይሳሳልኝ ነበር :: ሌሎቹ በጥፋታቸዉ ይገረፋሉ:

እኔ ግን ባጠፋም

አልገረፍም ነበር : አንድ ቀን ከእህቴ ልጅ ጋር ጥጃ ስንጠብቅ ቀን ላይ ቁጭ ብለን ድባ ቅጭት በመጫወትላይ እያለነ ጥጆቹ ሂደዉ የአጎታችን ሰብል አወደሙት :: አጎቴም ተበሳጭቶ

ለአባቴ ተናገረ: አባቴ ሁኔታውን

ለማየት ሲመጣ ቁጭ ብለን ድባ ቅጭት እንጫወት ነበር:: ቀና ስንል ከፊታችን ለበቅ ይዞ ሊገረፈን መጥቷል የእህቴ ልጅ ተነስቶ ተፈተለከና ካንድ ጫካ ገባ እኔ እንደቆምኩ ፈጥጨ ቀረሁ:: አባቴ በያዘዉ ለበቅ ሊያሳርፍብኝ ስላልፈለገ ፣ አጠገቡ ከነበረዉ ቁጥቋጦ ቅጠል ቆርጦ መጣና ደግሞ አይሮጥም! አለና ቂጤ ላይ በያዘው ቅጠል ቸፍ ሲያደርገኝ እኔም ተፈተለኩና እንደ እህቴ ልጅ ጫካ





ገባሁና አመለጥኩ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

73

በዚያዉ ምሽት ላይ ከወንድሞቼ ጋር ማታ በቆሎአችን ስንበላ አደርንና ጥፋታችን ተረስቶ ወደ ጥጃ ጥበቃችን ተሰማርተን ዋልን። ስለ በቆሎ እሸት ብዙ ገጠመኞች ነበሩኝና በዚህ የስደት ጉዞ ላይም እንደዚህ ሲገጥመኝ ለኔ ትልቅ የሰፈሬን ትዝታ ቀሰቀሰብኝ ::ደግሞም ትዝታ ብቻ አደለም ለኔ አሁንም ቢሆን የመጀመሪያ የምግብ ምርጫዬ በቆሎ እሸት ከምንም ምግብ መሀል እንደምርጫ ቢቀርብልኝ የማስቀድመው ይሆናል።

ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ በተራበና በዛለ ሰዉነት ላይ በቆሎ ሳገኝ ደስታዬ

ወሰን አልነበረዉም ::በጧት

ተነስተን ከአንድ ትልቅ የሱዳን ሰፈር ደረስንናን ሕዝቡ እኛን ሲያይ ሁሉም የሰፈሩ ሰዎች በሙሉ ወጡ :: አኛን ከአንድ አግዳሚ ወንበር አሰቀመጡንና ዶሮዎችን ማስደድ ጀመሩ እየያዙም





አዳኝ ደረደሯቸዉ::

ከፊታችን ግዳይ አንደጣለ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

74

በመንገድ መሪያችን አማካኝነት ለምን እንደሆነ ጠየቅናቸዉ ፣ አንድ ሽማግሌ ተነሱና እንኳን

ከብዙ

አደጋ ወጥታችሁ በሰላም ከዚህ ደረሳችሁ፣ ከዚህ በኋላ ሊገጥማችሁ ከሚችለዉ አደጋ ሁሉ በሰላም አምልጣችኋል::

በማለት ያለፍንበት ቦታ እንኳን ለኛ ላካባቢው ስውም የሚፈራ አደገኛ እንደነበር ስንረዳ የበለጠ አስደነገጠን እኛ ሳናውቅ ተጉዘን ሂደን ገድለው አረመኔዎች

ከሚሰልቡ

እጅ ልንወድቅ እንደነበር ስንረዳ ከዚህ

ያወጣንን ፈጣሪያችን አመሰገን:: ሽማግሌው ቀጠሉና እኛ በባህላችን እነግዳ ሲመጣ አዉሬ አድነን ነበር የምንጋብዛችሁ:

ነገር ግን አሁን

ይሄን ለማድረግ ጊዜ ስለሌለ በምትደርሱበት እነዚህን ዶሮዎች ጠብሳችሁ ብሉ ያመጧቸውን ዶሮዎች

ሁሉ

በማለት እየያዙ

በሸኝዎች አስዘው

ተሰናበቱን :: ከዚያም ወደ ቦማ

የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ጣቢያ ሄድን







ለመጀመሪያ ጊዜ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቅን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

=ቄሱእንዴት ይረሱኝ==== ቆዳ ዉሃ ነክረዉ በእንጨት ላይ ወጥረዉ ትንሽ መጣረቢያ በባልጩት ላይ ስለዉ ጠጉሩን ፍቀዉ ፍቀዉ ብራናዉን ሰርተዉ አበቦች ፈልገዉ ወይም አፈር ምሰዉ ቀለሙን በጥብጠዉ ከአሞራ ክንፍ ላባ እንደ ብዕር ቀርጸው ወይም ከሸንበቆ ጠርበዉ አለስልሰዉ ፊደል ሀ ሁ ብለዉ እራሳቸዉ ፈጥረዉ የሀገር ታሪክን ተመራምረዉ አዉቀዉ በመጽሐፍ ጽፈው በእንጨት ድጓስ ሠርተዉ ለትዉልኢድ አትርፈዉ እኔን ልጃቸዉን ከጓዳ ጎትተዉ አርጩሜዉን ይዘዉ ጆሮየን ቆንጥጠዉ በፀባይ አንፀዉ በል ና!! ሀ ሁ ቁጠር ብለዉ አስተምረዉ አ ቡ ጊዳዉንም ሁሉን አስቆጥረዉ ለመጻፍ ለማንበብ ለማጥናት ያበቁኝ ማወቅ መመራመር ለማሰብ ያስቻሉኝ አዛዉንት አባቴ ቄሱ እንዴት ይረሱኝ ለብዙ ዘመናት ታሪከ አስከብርዉ ነገሥታትን ሹመዉ ሕዝቡን አስተባብረዉ ድንበር አስከብረዉ ጠላት አሳፍረው















































ኢትዬጵያን በጽሑፍ በዓለም አሳዉቀዉ

75

እኔና

የስደት ጉዞዬ

76

ለሚመጣዉ ትዉልድ ብለዉ አቆይተዉ እኒያ ቄሱ አባቴን እንደምን ልርሳቸዉ መምሬ ባኢድሜአቸዉ ዲግሪ አልነበራቸዉ ለትዉለድ ማሰብን ማን አስተማራቸዉ? መምሬ ያስረዱኝ እስኪ በኔ ሞት ለምን ነዉ የጣሩት ለጥበብ ለእዉቀት? ልዩ ሚስጥር ይኖር መምሬ የሚያዉቁት እድሜዎን በሙሉ ሲጥሩ የሞቱት ደበሎዎን ለብሰዉ መቋሚያዎን ይዘዉ ለቤተክርስቲያን ቆመዉ አገልግለዉ በስመ አብ ወ ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ብለዉ ያስተማሩኝ ቅኔዉን ያስቀኙኝ ድጓ ያስጨረሱኝ ግዕዝ ዕዝል አራራይ ዜማዉን ያዜሙኝ ግብረገብ ደግነት ብለዉ የነገሩኝ የሀገሬን ድንበር ጠቁመዉ ያሳዩኝ ሙትላት ለኢትዬጵያ ብለዉ የመከሩኝ እኒያ ቄሱ አባቴ ዛሬ እንዴት ይርሱኝ =========//=============. * ይህ ግጥም መጀመሪያ በህፃንነት እድሜዬ ፊደል አስቆጥረዉ ዳዊት አስደግመዉ

መፃፍና

ማንበብ ላስቻሉኝ የሰራዉዲ ደብር የቄስ ት/ቤት አስተማሪዬ ጭለአባ ስቡህ መታሰቢያ እንድትሆንልኝ







































ነዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

77

ምዕራፍ - 4 ቦማ- የደቡብ ሱዳን ጠረፍ ከተማ ከሚዛን ተፈሪ የዘመቻ ጣቢያ ወጥተን ለ22 ቀናት የሌሊትና ቀን ጉዞ ከተጓዝን በኋላ ነበር ከአንድ የደቡብ ሱዳን ጠረፍ ከተማ ቦማ የደረስነዉ:: ቦማ ከአፋፍ ላይ የተከተመች ትንሽ መንደር ስትሆን ኑዋሪዎቹም የደቡብ ሱዳን ጠረፍ ጠባቂ ወታደሮችና ቤተሰቦቻቸዉ ናቸዉ ። እንደደረስን ለደቡብ ሱዳኖች እኛ በመልክ ቀላ ያልንና አለባበሳችንም በመንገድ የተበጣጠቀ የዘመቻ ቱታ በመሆኑ ለህብረተሰቡ እንደ አዲስ መጤ

አድርገዉ

አዩን: ህፃናትም እየከበቡ ፀጉራችን በመዳሰስ ተሳሳቁብን:: ከጥቂት ጊዜ

በኋላ ወደ ከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ቢሮ

ገባን: ፖሊስ አዛዡም በአማርኛ ቁጭ እንድንል ከነገረን በኋላ እኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የጋምቤላ ፖሊስ አባል ነበርኩ: ጡረታ ከወጣሁ በኋላ ወደዚህ መጥቼ በደቡብ









ሱዳን ፖሊስ አባል ሆኜ በአዲስ እየሰራሁ እገኛለሁ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

78

በመሆኑም እናንተን የማስተናግዳችሁ እንደራሴ ወገኖች አድርጌ ስለሆነ ምንም ስጋት አይግባችሁ ካለ በኋላ ለምን እንደመጣን የያንዳንዳችን ቃል ተቀብሎ ከመዘገበ በኋላ ሲጨርስ ምን ትፈልጋላችሁ ሲለን : ባንድ ቃል ምግብ አልነዉ። ምግብ ከዚህ ቦታ የምንኖረዉ በወታደር ራሽን በመሆኑ ችግር ነዉ : ለማንኛዉም ለግዜዉ ያመጣችኋቸዉን ዶሮዎች አዘጋጅተዉ እንዲሰጧችሁ አዛለሁ ብሎ አንድ ወታደር በመጥራት እመድባለሁ ብሎ አንድ ወታደር ሰጥቶ ትእዛዝ ሰጥቶት ተለያዬን ተለያየን። አኛም ዶሮዎ ደርሳ መች በበላን ስንል በጉጉት ከቆየን በኋላ ወደ አንድ ጎጆ ተጠርተን ገባን :እኛና ሌሎች 2 ፖሊሶች አምስት ሆነን

እንዳገራችን ወጥ ተሰርቶ

መረቁንና አጥንቱን ልንበላ ተዘጋጅተን ሳለ የተወሰኑ ብልቶች ተጠብሰዉ ማህል ላይ ቀረቡ : አንዴ ሁላችንም እጃችን ስንልክ አምስቱን የዶሮ ብልቶች አነሳን :: በሁለተኛ አነዳንድ አልደረሰምና ቆራርጠን ተካፍለን







እጃችን ልሰን አደርን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

79

በነጋታዉ ጧት የፖሊስ አዛዡ ወደኛ መጣና ተገናኘን :ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እሱም የደቡብ ሱዳን ነፃነት ትግል ጊዜ ለወታደራዊ ስልጠና ኢትዮጵያ ሂዶ እንደነበርና

ንቅናቄዉም የመሣሪያና

የሽምቅ ውጊያ ስልት ስልጠና እርዳታ በግርማዊ ጃንሆይ ፈቃድ ያገኙ

እንደነበር ካወራን በኋላ ኑ ላሳያችሁ

በማለት የመሣሪያ ግምጃቤቱን ከፍቶ ከኢትዮጵያ በእርዳታ የተሰጣቸውን አልቢንና ምንሽር መሣሪያ አሳየን:: አያይዞም ግርማዊ ጃንሆይ የነፃነታችን አባት ናቸዉ ይሄን ሁሉ እርዳታ እያደረጉልን

ከታገልን

ብለዉ ከኒሜሪ ጋር አደራድረው

በኋላ እርቅ

ይሄዉና ዛሬ

የንቅናቄዉ መሪ የሱዳን ምክትል ፕሬዘዳንት ሲሆን የአኛኛ ተዋጊ ሠራዊትም ወደ መደበኛ ሠራዊት ተቀይሮ እየሠራ ይገኛል:: አሁን ደቡብ ሱዳን ራስገዝ ስቴት ሆኖ እየኖርን ነዉ አለ። እኛም በጃንሆይ ብልህነትና የፖለቲካ ስልት





ተገርመን ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

80

ለካስ ንጉሥ ባገሩ አይከበርም የተባለዉ እዉነት ነዉ እኛ ምኑንም ሳናዉቀዉ በወጣት ጭንቅላት በቅጡ ባልተረዳነዉ የግራ ፖለቲካ አዕምሯችን ደንዝዞ ከማጥላላት በቀር ማመዛዘን የሚባል ነገር አልነበረንም።

ግርማዊ ጃንሆይ ይኽውና

ለደቡብ

ሱዳን የነፃነት አባት ሆነዉ ዘፈንም መዝሙርም ይዘመርላቸዋል። ከዚያ በኋላ ሻምበሉ አስጠራንና ወደ ቢሮዉ ሄድን: ወደ ማላካ

ከተማ ትሄዳላችሁ ነገር ግን የምትሄዱት

መጀመራያ ፒቦር ከተማ ነው:: ከዚያ ድረስ የሚኬደው በእግር ሲሆን መንገዱም 10 ቀናት ይወስዳል: በመንገድ ላይ ከተማም ሆነ ሰፈር ስለሌለ ወታደሮች ሰጥተናችሁ በመንገድ አውሬ እያደኑ ያደርሷችኋል አለን። እስካሁን ከኢትዮጵያ ከወጣን 22 ቀናት በእግራችን ተጉዘን በርሀብ እና ድካም የሰዉነታችን ኪሎ እጅጉን ቀንሷል። አሁን ደግሞ ሌላ የ10 ቀን የእግር ጉዞ ይጠብቀናል : ገና ስናስበዉ ኃሞታችን: ፈሰሰ የበለጠ ደከመን ግን ምን ምርጫ አለን መንገዱን ከመጋፈጥ





ሌላ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

81

በነጋታው ከተሰጡን 3 ወታደሮች ጋር በድምሩ 6 ሁነን ወደ ፒቦር ጉዟችን ጀመርን:: አስቸጋሪ መንገድ እንደሚሆን አስቀድሞ አዛዡ አስጠንቅቆን የነበረ ቢሆንም በጆሮ የሰማነዉ በተግባር ስናየዉ እዉነትም አስቸጋሪ የሚለዉ ቃላት ብቻዉን አይገልፀዉም ነበር :: ደቡብ ሱዳን

አብዛኛዉ በዉሃ የተዋጠ ሜዳ መሰል

መልካዓ ምድር ነዉ:: ከሩቅ ሲያዩት የለበሰዉ እሣር የሽንበቆ ያህል ትልልቅ ነዉዉስጡ ረግረግ ዉሃ ነዉ :: እሱን ሰንጥቆ ለማለፍ የአካባቢዉን መንገድ አዋቂ መኖሩ ግድ ነዉ:: እነዚህ የተሰጡን ወታደሮች እያንዳንዷን ቋጥኝ ያዉቋታል :: ሁለቱ ከፊት አንዱ ከኋላ ሆነን ለ”3 ቀናት ለስንቅ ብለዉ የሰጡንን የበቆሎ ዶቄት በሞቀ ዉሃ እየበጠበጥን በመጠጣት ተጓዝን: ሆኖም ስንቋም እያለቀች እኛም እየደከምን ሄድን: አዉሬ ለማደን





እየሄዱ ብዙ ጥይት እየተኮሱ ባዶ እጅ ይመለሳሉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

82

ከጊዜ ወደ ጊዜ በአዉሬ አደኑ ላይ ተስፋ እየቆረጥን ሄድን:: አሁን ምግብ የለም: ሰዉነታችን ዝሏል : በጠቅለላዉ በ5ኛዉ ቀን ሰዉነታችን ደከመና መራመድ ቀርቶ መቆም አልቻልንም :: ከአንድ ዋርካ ስር እረፍት ተባለና አረፍን ከዋርካዉ ስር የወዳደቁትን ፍሬዎች ከአዕዋፋት የተረፈውን

እየለቃቀምን በላን:

ለነገሩ

ህይወታችን ለማቆየት ያህል ይረዳን ብለን እንጂ ምንም አልጠቀመን ። ግዜዉ እየመሸ ሲሄድ አንድ ሀሳብ መጣልኝ: እሱም እነዚህ የሱዳን ወታደሮች ተኩሰዉ አዉሬ መግደል ካልቻሉ ለምን እኛ አንሞክርም ለነገሩ እኮ ከኛ ዉስጥ ገሠሠ የዓየር ኃይል ወታደር ነበር ታዲያ ለምን አንተ አትሞክርም አልኩት:: በዚህ ኃሳብ ሱዳኖችም ገሠሠም ተስማማንና ጠበንጃቸዉን ይዘን እነሱን መንገድ መሪ አድርገን ወደ አደን ሄድን እንዳልኩትም ብዙ አልሄድንም አንድ የኮረኬ መንጋ ወደኛ ሲመጣ አየን: ከዚያማ ገሠሠ በተማረዉ የወታደር ዘዴ በደረቱ እየተሳበ ቀረበና በአንድ ጥይት ትልቁን ገረደሰዉ: አዉሬዉ ወደቀ እኛም በደስታ





ፈነደቅን?::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

83

ድካማችን ጠፋና መዝለል ና መጨፈር

ጀመርን

ከዚያም ሥጋዉን ዘለዘልንና በእሳት እንደ ቋንጣ አደረቅነዉ እሱንም አንደምንችለዉ ተከፋፍለን ጧት ሲነጋ ተነስተን ጉዞ ጀመርን። መንገዱ አስቸጋሪ ነበር የደቡብ ሱዳን መልካ ምድር ሲያዩት ጭልጥ ያለ ሜዳ በቅርቅኃ መሳይ እሣር ተሸፍኖ ዉስጡ ዉሃ ነው :: ታዲያ በዚህ በሳር በተሸፈነ ዉሀ ዉስጥ በእግር መሄድ መላ ሰዉነታችን ዉሃ ዉስጥ ከነልብሳችን ሲነከር የልብሳችን ክብደት ከድካም ጋር ተጨብሮ ተራምደን ከፈለግነዉ ለመድረስ አልቻልንምና ከአንድ ቦታ እንድናድር ተወሰነና ቦታ ከአንድ ዘላኖች ጥለዉት የሄዱት ጎጆዎች ስላገኘን

ሰፈርን : ግን ከዚህ ቦታ

የከብቶች ፍግና ሽንት ያለበት በመሆኑ ቢንቢዉ ኃይለኛ ሆነብን:: እሳት አንድደን እቃችንም አስቀምጠን ፖሊሶቹም የቦታዉን ፀባይ ስለሚያዉቁት ድንኳን ይዘዉ ነበርና ከሱ ዉስጥ ገብተዉ ተኙ : እኛ የት እንግባ ሰማይ ምድሩ ቢምቢ ብቻ ሆነ:

ስንት ሚሊዬን እንደሆኑ መቁጠር

ባልችልም አካባቢዉን ልክ እንደ አንበጣ መንጋ





አካባቢዉን ሸፈኑት::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

84

ሌላ ቦታ ለመሄድ ብንፈልግስ የት ይኬዳል: ሁሉም ቦታ ዉሀ ነዉ። እየመሸ ሲሄድማ በጠቅላላዉ የለበስነዉን ልብስ እየበሱ ይጠዘጥዙን ጀመር:: ቢጨንቀን አንዷን ጎጆ አቃጠልናት: እሱም አልረዳም ፣ ከአንድ ጎጆ ዉስጥ ፍጉን አቀጣጠልንና ጭስ ብቻ አደረግነዉ።

አልሆነም : ከስር ጭስ አጭሰን እኛ ከጎጆዉ ጣራ ላይ ወጥተን ከስር በሚጮሰው

ጭስ እንደዶሮ እየታጠን

ለመተኛት ሞከርን : ትንሽ

ከቢምቢው ብንድንም

ጭሱን ግን ለመቋቋም ተቸገርን:: ግን የት ይኬዳል! ከዚሁ እንደተሰቃዬን

እንቅፍ

አይበለውና ስንገላበጥ ነጋና በጧት ተነስተን ጉዟችን ቀጠልን። በግምት 7 ስዓት ከተጓዝን በኋላ ፒቦር ከምትባል ከተማ ደርሰን :: ፒቦር እንደደረስን ለፖሊስ አዛዡ ሪፖርት አድርገን እረፍት አደረግን:: መጀመሪያ እንደደረስን የጠየቅነዉ ምግብ ነበር : ከዚያም የምግብ ችግር እንዳለ ተነገረንና







ለግዜዉ የምናርፍበት ቦታ ተሰጥቶን እረፍት አደረግን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

85

ካረፍንበት ቦታ ፖሊስ አዛዡ በአንድ ትልቅ ጎድጏዳ ሰሀን ሙሉ የዳቦ ፍትፍት ላከልን :

ምግቡ ብዙ ስለነበር

የማንጨርሰዉ መስሏቸዉ ያመጡልን ሁለት ወታደሮች ስንበላ ቁመዉ ይመለከቱን ነበር እኛ ግን በማይታመን ሁኔታ ያን ሁሉ ምግብ ባንዴ አወደምነዉ እንኳን የሚተርፍ እንዳዉም የበለጠ ርሃብ ለቀቀብን እንዴ! ሰዉ ሲራብ ለካ ምግብ ሲያገኝ በልቶ አይጠግብም! እጃችን እየላስን ባዶዉን ሰሀን መለስንላቸዉ:: በበነጋታው የጣቢያዉ አዛዥ አስጠራንና ስለኛ ትንሽ ካወራን በኋላ አሁን ከዚህ ወደ መላካል ትሄዳላችሁ ከዚያ ለመድረስ በእግር ከሆነ 8 ቀናት ይወስድባችኋል አለ

አይ ብዙ ደክመናልና በእግር አንሄድም ካላችሁ

ደግሞ ለሠራዊቱ ደመወዝ የሚከፍል ሄሌኮፍተር ከአራት ቀን በኋላ ስለሚመጣ ጠብቁና በሱ እንልካችኋለን:: እንደኔ ብዙ ስለተንገላታችሁ ቆይታችሁ ብትሄዱ እመክራለሁ: እስከዚያም

ብዙ ምግብ ባይኖረንም

ከወታደሮች ስንቅ ተካፍለን እየበላን ትቆያላችሁ አለንና





በዚሁ ተስማምተን ወደ ማረፊያችን ሄድን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

86

በተባለዉ ቀን ትመጣለች የተባለችዉ ደመወዝ ከፋይ ሄሌኮፕተር ከሁለት ቀን መዘግየት በኋላ መጣች : እኛም ወደሄሌኮፍተሯ ተሯሩጠን ሄድንና ቆምን : አብራሪዎቹ አንድ ወጣት መቶ አለቃና አንድ ኮረኔል ነበሩ:: ከመምጣታቸዉ በፊት ስለኛ በቴሌግራም ተነግሯቸዉ ስለነበረ ወጣቱ አብራሪ ወደኛ በቀጥታ መጣና እስላሞች ናችሁ ክርስቲያኖች

ሲል

ጠየቀን : እኛም

ባንድ ቃል ሳናመነታ ክርስቲያኖች ነን አልነዉ። ይሄን ሲል የሰማዉ አብራሪ ኮረኔል መጣና አይዟችሁ ችግር የለም አለን፣ እሽ እናመሰግናለን ብለን ደመወዝ







ከፍለው እስኪጨርሱ ድረስ መጠባበቃችን ቀጠልን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

87

የደቡብና ሰሜን ሱዳን ወታደሮች ፍጥጫ፣ ፓይለቶቹ የመጡበትን ለሠራዊቱ ደመወዛቸዉን ከከፋፈሉ በኋላ : በሄሌኮፖተር ገብተን ወደ ሱዳን አኮቦ ከተማ

በረን አረፍን ። ከዚህ ቦታ ያልጠበቅነዉ ነገር

ተከሰተ:

የአኮቦ ከተማ ፖሊስ አዛዥ

አኛን ሲያይ

የሄሌኮፍተር አብራሪዎችን መጥቶ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዊያን ናቸው:: በድብቅ ከአገር አውጥታችሁ ልትወስዱ ነዉ : ይሄም ህገወጥ ሥራ ነዉ : አለና አብራሪዎቹ ላይ አፈጠጠ:: ወጣቱ አብራሪም በትህትና ከማስረዳት ይልቅ በተራዉ አንተ ምን አገባህና ትጠይቀናለህ

አለና በማንጓጠጥ

መለሰለት : በዚህ ጊዜ የፖሊስ አዛዡ ደሙ ፈላ :: በንቀት ስለመለሰለት እንዴት እንደዚህ ትመልስልኛለህ እኔ እኮ የበላይህ ነኝ አለና ልቀቁኝ ሲል መጥተው

ተደፈርኩ

ብሎ ያዙኝ

ከየት መጡ ሳይባል የደቡብ ወታደሮች

ዙሪያዉን ከበው

ሄሌኮፕተሯ እንዳትነሳ









አደረጉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

88

እኛንም ጨምረው ካለንበት እንዳንቀሳቀስ

አዘዙ :

ባንፃሩ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች ከዚያው ከሚገኘው ካምፕ መሣሪያቸዉን እየያዙ መጥተው ለውጊያ የሚሆን ቦታ ቦታ ያዙ : መሬት ቁልቢጥ ሆነች:: እነዚህ የደቡብሱዳን ተዋጊዎች እርዳታ የደቡብ

ሱዳን

በግርማዊ ጃንሆይ ነፃ አውጭ (SPLAን)

መሥርተዉ ለ17 ዓመታት ከሰሜኑ

ሱዳን ጋር ሲዋጉ

ከቆዩ በኋላ አሁንም በጃንሆይ አስታራቂነት የንቅናቄው መሪ

ጆን ጋራንግ የሱዳን ምክትል ፕረዜዳንት

እንዲሆንና ተዋጊዎቹም ደቡቡን የሱዳን ፁጥታን እንዲቆጣጠሩ

ክፍል

ተስማምተው እንዲሠሩ

ቢስማሙም : አልፎ አልፎ ግጭቶች እየተከሰቱ ነበር። የግርማዊ ጃንሆይ

መንግሥት ወድቆ የወታደራዊው

ደርግ ቢተካም ከነዚህ ከደቡብ ሱዳን የቀድሞ ተዋጊዎች ጋር አሁንም የጠበቀ ወዳጅነት አንዳላቸው ብዙ የSPLA ተዋጊዎች አጫውኝ ነበር:: በዚህም ምክንያት በዚያ የሚያልፉትን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

እየያዘ ለኢትዮጵያ መንግሥት







መስጠት ድረስ የዘለቀ ግንኙነት ነበራቸው::

እስከ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

89

ይህ ደግሞ በሱዳን መንግሥት እውቅና ያልነበረውና በዓለም አቀፍ ህግም ተፃራሪ አሰራር ነበር:: በዚህና በሌሎች ምክንያቶች

እየተፈጠረ ያለን

የእርስ በርስ

መናናቅና ቅራኔ ምክንያት ተግባብተዉ መሥራትና መኖር አልቻሉም: ይህም በመሆኑ በትናንሽ ነገር ሁሉ እያሳበቡ መሣሪያ መማዘዛቸውን ቀጥለዋል :: አሁን

የኛን

በሄሌኮፍተሯ መጓዝ

ምክንያት

ይሁን

እንጂ ከላይ እንደጠቀስኩት ጥላቸው ሥር የሰደደና 17 ዓመታትን ያስቆጠረ የእርስ በርስ ጦርነትና የብዙ ሽህ ሕዝብ ህይወት የቀጠፈ ነበር:: ሁኔታዉ እየተካረረ ሲሄድ አንደኛዉ አብራሪ ኮረኔል በጣም የረጋና የበሰለ አስተዋይ ሰዉ ነበርና ከአካባቢዉ አንድ ሽማግሌ አስጠርቶ ወዲያዉ ነገሩን ማረጋጋት ጀመረ :: እኛን በተመለከተም ከዲስትሪክት ኮሚሽነሩ (አዉራጃ አስተዳዳሪዉ)

ሥደተኞች እንደሆንና ወደ

ካርቱም ዉሰዱ ተብለዉ የሚያሳይ የተጻፈ

ትእዛ እንደተሰጣቸዉ

ደብዳቤ የታሽገውን ፖስታ ቀዶ





አሳያቸዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

90

እነዚህ ሰዎች ህጋዊ ስደተኞች እንጂ ወንጀለኞች አደሉም እኛም ከባለስልጣን ታዘን እንጂ

በራሳችን

አይደለም የምንወስዳቸው ሲል አስረዳቸዉ:: በዚህ ጊዜ የጥቁሮች የፖሊስ አዛዡ በማብራሪያዉና በሽማግሌዎቹ ተማመነና ጉዟችን እንድንቀጥል ፈቅዶልን:: አኮቦን ለቀን በምሽት ማላካል ከተማ ገብተን አደርን:: በበነጋዉ ከቀኑ 7ስዓት ሲሆን ኮስቲ ከሚገኘዉ የሱዳን ጦር ሰፈር አረፍን:: ኮስቲ ከዓባይ ወንዝ ዳርቻ ያለች ከተማ ብትሆንም ሙቀቱ ኃይለኛ ነበር ::

ከሄሌኮፍተራ ወርደን ወደ መኮንኖች ክበብ ከፓይለቶቹ ጋር ሄድን : የሱዳን ወታደሮች በማረጋቸዉ ይለያያሉ እንጂ የሚለብሱት ከተራ ወታደር እስከ ጀኔራል ድረስ አንድ ዓይነት ቀለም ያለዉ ልብስ በመሆኑ እየተደነቅን ወደምግብ አደራሽ ሄድንና መሬት ላይ ከተነጠፈ ስጋጃ





ላይ ሁላችንም ዙሪያዉን ከበን ተቀመጥን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

91

ወዲያው ማህል ላይ ምግብ በትሪ

አምጥተው

አስቀመጡ : በጣም ቆንጆ ምግብ ነበር ከበግ አሮስቶ እስከ ሰላጣ በያይነቱ በትሪዉ ላይ ተዘረገፈና ሁላችንም በጃችን የቻልነዉን እያነሳን እንድንበላ ተጋበዝን:: እኛ ከ36 ቀናት የበርሃ እግር ጉዞ በኋላ በርሀብ ከስተን በጣም ተጎድተን ነበርና በልተን ልንጠግ አልቻልንም :: መኮንኖቹ ትንሽ እንደበሉ እጃቸዉን ጠራረጉ እኛም ምግቡ እያስጎመጀን ሆዳችን እንደራበዉ ኢትዮጵያዊ ይሉንኝታ ያዘንና እጃችን ሰበሰብን::እንዳገራችን ብሉ ብሎ የሚያግደረድረን አላገኘንም እንጂ ያን ሰሃን ሙሉ ምግብ ባዶ ለማስቀረት እንችል ነበር: ግን ምን ያደርጋል! እየራበን ተዉነዉ። ከኮስቲ ተነስተን ከቀኑ በ10 ስዓት ሲሆን ካርቱም አይሮፕላን ማረፊያ ደረስን። ሱዳን ካርቱም ወታደራዊ ዓየር ማረፊያ እኛን የጫነችዉ ሄሌኮፍተር አኮብኩባ የሱዳን ጦር ዓይሮፐላኖች ከቆሙበት (hangar) ወረድን፣: እንደወረድን

መካከል ቆመችና

ሶቢየት ሰራሽ ተዋጊ ጀቶች





ተኮልኩለው እያየን ፈዘን ቀረን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

92

ገሠሠ አላስቻለዉምና እነዚህ ጀቶች ተዋጊዎች ናቸዉ ወይስ መለማመጃ ሲል አብራሪዉን

ጠየቀዉ::እሱም

አይ እነዚህ ሱዳን ሰፊ ስለሆነ ለደንበር አሰሳ (Reconnaissance aircraft) ናቸዉ የተገጠመላቸው

ካሜራ

ስለሆነ ፎቶ ግራፍ ለማንሳት

የሚያገለግሉ ናቸዉ አለ፣ ይህን በማለት ላይ እያለ ወዲያዉ ወደ ቢሮ ተጠራና ትንሽ ቆይቶ ፊቱ ደም ለብሶ መጣና መኪና ዉስጥ አስገብቶ ወደ ደህንነት ቢሮ ወስዶን ተመለሰ :: የሱዳን ደህንነት ቢሮ ትንሽ ቃላችን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አንድ ሆቴል ወስደዉ አድርሰውን ሄዱ ::አብራሪዉ ለካ ፊቱ የተለዋወጠዉ ከአለቆቹ ለምን እነዚህን ሰዎች አምጥተህ ያሉንን አይሮፕላኖች ታሳያለህ በሚል ነበር እዉነት ለመናገር እኛም በኋላ ምን ዓይነት ዝርክርኮች





ናቸዉ ብለን ተችተናቸዋል።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

93

ካርቱም፣ የካርቱም ከተማ የሁለት ዓባዬች

መጋጠሚያ ስትሆን

ደልዳላ ሜዳ ላይ የተቀመጠች ከተማ ነች፣ እንደ ወላፈን ይጋረፋል ፣ አቧራው

ሙቀቱ

እንደ ጉም ደመና

ይሸፋናል:: ሰዉ ወንዱም ሴቱም ስስ ቀሚስ (ጀለብያ) ይሉታል ነዉ የሚለብሱት፣ ጫማቸዉ ሸበጥ ነጠላ ጫማ ሲሆን ሁሉም ራሳቸዉን ይጠመጥማሉ፣ አንዳንዴ ከሙቀቱ የተነሳ መተንፈስ ሁሉ ያስቸግራል:: ትንሽ ረፋዱ ላይ ቢሮም ሱቅም ይዘጋና ቤት ዉስጥ ሆኖ ኤሌክትሪክ ማቀዝቀዣን ለኩሶ መቀመጥ ነዉ:: ሌሊትም የሚተኛዉ ዉጭ አንሶላ መሳይ ጣል አድርጎ

ነዉ::

ታዲያ ጧት ሲነሱ አቧራ ለብሶ መነሳት ነዉ :: እንደተነሱ በቀጥታ ወደ

ሻወር ካልተገባ ችግር

ነዉ::አረብኛ ስለማንችል እኛ በጣም ከሕዝቡ ጋር መግብባት አስቸገረን: በጠቅላላዉ ኢትዮጵያ ተወልዶ ላደገ ሰዉ ሱዳን ለመኖር መጀመሪያ ጊዜ ትልቅ ፈተና







ይሆንበታል ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

94

በዛ ላይ የጀብሃ ታጋዮች ከተማዉን ሞልተዉታል በሱዳን ዉስጥ ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረዋል

ማለት

ይቻላል: ሱዳንን የሚያስተዳድር ሁለተኛው መንግሥት ኤርትራውያን ናቸው ሲል ሱዳንን በደንብ የሚያውቃት ኢትዮጵያዊ አቶ አሰፋ ዋሴ ያጫወተኝ እውነቱን ነበር:: ከኢሚግሬሽን እስከ ደህንነት ቢሮ ተሰግስገው ይዘውታል :: ታዲያ ጀብሃዎች እንደኛ ዓይነቱንና የነሱን የመገንጠል ዓላማ የማይደግፈዉን በጨለማ ያፍኑና በጆንያ ከተዉ ዓባይ ወንዝ ይጨምሩታል። ይህንና ሌሎችም ችግሮች ተጨምረው በጠቅላላዉ ለኛ የምንቆይበት አገር ሆኖ አላገኘነዉምና ከአንድ ወር ቆይታ በኋላ ወደ ዩጋንዳ ለመሰደድ ወሰን።ምክንያቱም የኛ ካርቱም መቆየት

ራሳችን አደጋ ላይ መጣል ሆኖ

ስላገኘነዉ ነዉ:: በተለይ የጀብሃ (ELF) ሰዎች እኛ ከነሱ ጋር ተቀላቅለን ከሰላ ማሰልጠኛቸዉ ቦታ ሄደን ከሰለጠን በኋላ ለኢህአፓ እንድንታገል ቢጠይቁም እንቢም እሽም ሳንል ቆዬን በኋላ ደግሞ የሱዳን የስደተኞች መ/ቤትም ከሱዳን (UNHCR) ተስማምቻለሁና ከሰላ ትሄዳላችሁ





አሉን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

95

እኛም አሁን ነገሩ ከላይ እስከታች የተያያዙ መሆናቸዉን ተረዳን: ስለዚህ ሌላ ከዚህ የምናመልጥበት ዘዴ በቶሎ ካላገኘን እንደማይለቁን ተረዳን:: በዚያ ላይ ለጀብሃ ጥያቄ

እንቢም እሽም ሳንል

ስለጠፋንባቸዉ እነዚህ የደርግ ሰላዬች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ ስላደረባቸዉ ለመግደል እንደሚፈልጉን ሰማን:: በዚያ ላይ ከመካከላችን ሐጎስ የኔና የገሠሠን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለንን የማያወላዉል የፖለቲካ አቋም ስለሚያዉቅ እኛን እየተደበቀ ከጀብሃ ሰዎች ጋር እንደሚገናኝ ደረስንበት::ስለዚህም እኛ የነበረን ምርጫ







ከሐጎስ ተደብቆ በቶሎ ካርቱምን መልቀቅ ነበር ።

የስደት ጉዞዬ

96

* ከ36 ቀናት የእግር ጉዞ በኋሉ ካርቱም እንደገባን (1975 EC)



ከግራ ወደቀኝ እኔ ሞላ ይግዛው ከመሃል ገሠሠ ዲባባ ከቀኝ በኩል ኃጎስ ብርሃኔ



እኔና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

97

ምዕራፍ - 5 ጉዞ በነጭ ዓባይ ላይ፣ ጠይቀን ባገኘነዉ መረጃ መሠረት ለስንቅ የሚሆኑን ነገሮች እንደ ድስት : ለገንፎ እስከ

ደቡብ

የሚሆን ዱቄት: ከሰል: ፈርሜሎና

ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ድረስ የሚያደርሰን

የባቡርና የመርከብ ትኬት ገዝተን ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲሆን ካርቱምንና ሐጎስን ወደኋላ ትተን : መጀመሪያ በባቡር እስከ ኮስቲ ተጓዝን :: ባቡሩ እንደ ሰርዲን በደቡብ ሱዳናዊያን ተሞልቶ ስለነበር ከሱዳን ሙቀት ጋር የፉርጎዉ ጠረን እጅግ የሚሰነፍጥ ነበር፣ እንደምንም ችለን ኮስቲ ደርሰን አደርንና ጧት ተነስተን ከሰዉ ጋር እየተጋፋን ወደ መርከቧ ገባን። መርከቧ 3 ትልልቅ ጀልባዎች ባንድ ላይ በካቦ ተጠጋግተዉ ታስረዉ አንድ ባለሞተር ጀልባ ከኋላ ሆኖ የነጭ ዓባይን ዉሃ ወደ መጣበት

(ሽቅብ) እየገፋ የሚሄድ መርከብ ነበር ።

ከመርከቡ አንደኛ ማዕረግ የመሰሉ ጥቂት ክፍሎች ስለነበሩ ተሻምተን ቦታ ለመያዝ ቻልን፣ ሌላዉ ሕዝብማ ምኑ









ቅጡ:ገብቶ እንደ ስርዲን ታጨቀ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

98

ጊዜዉ የክረምት ጊዜ ስለነበር የነጭ ዓባይ የዉሃዉ ግፊት ጠንካራ በመሆኑ የመርከቧን

ፍጥነት የዔሊ ጉዞ

አድርጎታል:: እኔና ገሠሠ ሙቀቱ ስላስቸገረን ከመርከቡ ጣራ ላይ ወጣንና ቦታ ስንፈልግ ሁለት ከናዳዉያን ቱሪስቶች የያዟት ጎጆ መሳይ አየንና ወደነሱ ጠጋ ብለን በኢትዮጵያዊ ባህል አክብሮት ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ መቀመጥ እንችል እንደሆነ ጠይቀን ፈቀዱልንና ተቀመጥን ። ከዚሁ ጎጆ ሳንወጣ

በነጭ ዓባይ ዉሃ ላይ

ጥቂት ቀናት

እንደተጓዝን አንድ ምሽት የሱዳንን መልክዓ ምድር እንደ ፀሐይ በምታበራዉ የጨረቃ ብርኃን ከአድማስ እስከ አድማስ እያየን ቁጭብለን ተፈጥሮን እያደነቅን

ስናወራ፣ ገሠሠን

አየህ

ትመስላለች እኮ!

ጨረቃዎን!! የአገራችን ጨረቃ

አልኩት ጨዋታ ለማድመቅ ብዬ ”እ እ አየህ ጨረቃና ፀሐይ ለሁሉም አንድ ናቸዉ ጊዜያቸዉን ጠብቀዉ እኩል ይበራሉ” ለሰዉ ልጅ ሳያዳሉ እኩል ጥቅም የሚሰጡ እነሱ ብቻ ናቸው አለ :: ዓየሩም እንዲሁ በነፃ ማንንም ሳንለምን የምንተነፍሰዉ





ከአምላክ የተሰጠን ፀጋ ስለሆነ ነዉ አለ,,::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

99

በዚህ ሁኔታ እያለን ከጎጆዋ ያስጠጉን ከናዳዉያን ሀሽሽ ጠቅልለዉ ይጀነጀኑ ጀመር እኛንም እንፈልግ እንደሆነ ጠየቁን አይ አናጨስም አልናቸዉ በኋላ ትንሽ ቆዩና ብርዱ እየቀዘቀዘ ሲሄድ ይሄ ለብርድ ጥሩ ነዉና ሞክሩት አሉን እሽ እንሞክረዉ አልንና አንዴ ስስበዉ በትንታ አሰቃየኝ:: ትንሽ ሲሻለኝ መጀመሪያ ስለሆነ ነዉ ብለዉ ሳቁብኝና ስትደግምበት ይተዉሃል እኛም እንደዚህ ነዉ የለመድነዉ አሉኝ እንደገና ተቀበልኩና ሳብኩት ፣ እንዳዉም የሁለተኛዉ ባሰብኝ ከዚህ በኋላ በቃኝ አልኩና ተሸፋፍኜ ለመተኛት ሞከርኩ ትንሽ እንዳሸለብኩ ቅዤትና ብርድ ተፈራረቀብኝ:: በድንገት ከሱዳኖቹ ኡኡታ ሰማሁና ባንኜ ስነሳ እዉነትም ከጣራ ከተቀመጡት አንዱ ተንሸራቶ ወደ ውሃው ስለወደቀ ማዳን ይቻል እንደሁ እርዳታ መጥራታቸዉ ነበር : ግን አልሆነም በዚያ ላይ መርከብ አቁሞ ከወራጅ ዉኃ ዉስጥ ሰዉ ፈልጎ ለማግኘት ስለማይቻል መርከቧም ጉዞዋን ቀጠለች የገባዉም ለአዞ እራት ሆኖ ቀረ። በጧት ለመነሳት ስላልቻልኩ ገሠሠ ሊቀሰቅሰኝ ቢሞክር ሰዉነቴ በኃይለኛ ትኩሳት ግሏል : የገዛነዉ ዱቄት ስላለቀ ከገንፎ ወደ ሙቅ ቀይረን ትንሽ ትንሽ ፉት እያልን ነበር የምንቃመሰዉና አሁን ስላመመሀ አንተ ጠጣ ብሎ





ኩባያዉን ቢሰጠኝም ተቀብዬ መጠጣት አልቻልኩም::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

100

ገሠሠ ግራ ሲገባዉ ከካናዳዎቹ የሆነ ክኒን ለምነና ሰጠኝ ክኒኑን ውጬ ተሸፋፍኜ ተኛሁ።ጧት እንደምንም ብነየ ስነሳ

እራብ ለቆብኛል ፣ ምግብ እየጨረስን ስለነበረ

ወደሙቅነት የተቀየረችዉ ዱቄትም ተመናምናለች አሁን እንለምን ብንልስ ከዚህ መርከብ ላይ ማን ይለመናል ብለን ጨነቀን :: ገሠሠ ሲፈራ ሲቸር ጓደኛዬ ስለታመመ ምግባችንም ስላለቀ ምን እንደማደርግ ጨንቆኛል ሲል

ከናዳዎቹን

አማከራቸዉ :: እነሱም እርስ በርስ ተያዩና ከያዙት የሾርባ እንክብል ሰጡን: እሱን : ገሠሠ በዉኃ አፍልቶ ሰጠኝና ጠጥቼ ተኛሁ።ሌሊቱን በላብ ተጠምቄ አደርኩ ሊነጋ ሲል ሰዉነቴ እየቀለለኝ ሄደ ትኩሳቱም ጠፋና በምትኩ ራብ ለቀቀብኝ ግን ምግብ እንደሌለን ትዝ አለኝና ተስፋ ቆረጥኩ ወዲያዉ ስቁነጠነጥ ገሠሠ ከእንቅልፉ ነቃና እንዴት አደርክ አለኝ:: አሁን ደህና ነኝ ከበሽታዉ ያገገምኩ ይመስለኛል ራቡ ግን ልነግርህ አልችልም አልኩት፣::ባነጋገሬ አዘነና እይዞህ ከስዓት በኋላ ጁባ እንገባለን ከዚያ ዳቦ ፈልገን ገዝተን ትበላለህ አለኝ እዉነትክን ነዉ ዛሬ ጁባ እንደርሳለን ? አልኩኝ :: የደስታ ሲቃ እየተናነቀኝ: አዎ ዛሬ እኮ 22 ኛ ቀናችን ነዉ መጓዝ ከጀመርን:: አለኝ ወይ ጉድ ቀኑም ለካ ጠፍቶብኛል





አልኩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

101

እንዳለዉ ወደ ዘጠኝ ስዓት ጁባ ገባንና መርከቡ ቆመ:: እኛም ወርደን ከዚያዉ ዳቦ ይዘዉ ወደመርከቡ ለመሸጥ የመጡ ልጆች አገኘንና የቻልነዉን ገዛን:: ጁባ ከተማ ወደ ዩጋንዳ የሚወስድ መንገድ ጠይቀን

እየሄድን እያለን አንድ

የጭነት መኪና የሚነዳ ሶማሌ አገኘንና ወደዩጋንዳ መሄድ እንደምንፈልግ ስንነግረዉ ግቡ አለና አብረን ጉዞ አደረግን:: የሱዳን ዩጋንዳ ደንበር ሙሊሌን ያለችግር በጭነት መኪና አለፍንና ከዩጋንዳ ወታደራዊ ካምፕ ደረስን:: የዪጋንዳ ደንበር ጠባቂ ወታደሮች

ፍተሻ ብለዉ

አስወረዱን: ከዚያም ከየት እንደመጣንና ወደየት እንደምንሄድ ጠየቁን እኛም ከኢትዮጵያ እንደመጣንና ወደ ካምፓላ መሄድ የምንፈልግ ሥደተኞች ነን ስንል መለስንላቸው : ዘቦቹም በራሳቸው

መወሰን ስላልቻሉ

አዛዦቻቸውን ደዉለው ቢጠይቁ አንድ ክፍል አስገቧቸውና ከዚያ ይደሩ አሏቸው:

ከዚያ አንድ ባዶ ክፍል አስገብተው

ቆለፈብንና አደርን ፣። ጧት ተረኛ ጠባቂ መጣና ከክፍሉ አስወጥቶ በሚያልፍ የጭነት መኪና አሳፍሮ

ወደ ጉሉ ላከን። ጉሉ የሰሜናዊ

ዩጋንዳ ዋና ከተማ ነች ቆንጆና ንጹህ ነች ብዙም ከተማዋን ለማየት ሳንችል ያመጣን ሾፌር ፖሊስ ጣቢያዉ አስረከበንና





ሄደ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

102

እኛም ለግዜዉ ማረፊያ ቤት ቆዩ ተብለን ከዚያዉ ፖሊስ ጣቢያ እንድናድር አንድ ክፍል ተሰጠንና ተኝተን አደርን።

ጧት የጣቢያዉ አዛዥ መጥቶ የተለመደዉን ጥያቄ ከየት እንደመጣንና የት ለመሄድ እንደምንፈልግ ጠያየቀንና ፍላጎታችን ከተረዳ በኋላ ነገ ወደ ካምፓላ መኪና ፈልጌ እልካችኋለሁና ለዛሬ ካደራችሁበት ክፍል እደሩ አለንና ለሚወስደን ሰዉ ትእዛዝ አስተላልፎ ተለየን። በመካከሉ አንድ ችግር ተፈጠረ እሱም ድንበር ላይ ያሳደሩን የዩጋንዳ ጠረፍ ወታደሮች በጧት ተነስቶ ወደጉሉ የላከንን ወታደር አዛዡን ሳያስፈቅድ እንደላከንና የደህንነት መኮንኑ መጀመሪያ የኛን ቃል መቀበል እንደሚፈልግ ገልጾ ለጉሉ ፖሊስ አዛዥ መልሶ

እኛን

እንዲልክለት

ቴሌግራም

ይልካል:: የጉሉ ፖሊስ አዛዥ ግን በነገሩ ባለመስማማት አንተ ጦር ሠራዊት ስለሆንክ ሥደተኞችን መመርመር አትችልም መመርመር የሚችለዉ ፖሊስ ስለሆነ እኛ መርምረን የማያስፈልገዉን ሥራ እየሠራን ስለሆነ ሰዎቹን መልሰን ወዳንተ የምንልክበት ምክንያት የለም: አለና ቴሌግራም







መልሶ ለሙሊሌ ጠረፍ መኮነን ላከለት::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

103

የጉሉ ፖሊስም በዉሳኔዉ በመጽናት እኛን ወደካምፓላ እንድንሄድ ወሰነ። በጧት ሁለት ፖሊሶች በዳትሰን መኪና ጭነዉን ወደ ካምፓላ ተጓዝን ከ7ስዓት የመኪና ጉዞ በኋላ ካምፓላ ሴንተራል ፖሊስ ጣቢያ አስረከቡንና እኛ ወደ እስር

ቤት ስንገባ እነሱ ወደ መጡበት ተመለሱ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

104

ምዕራፍ- 6 ዩጋንዳ ማዓከላዊ እስር ቤት ( Centeral police station)ይህ በመሀል ካምፓላ ተንሰራፍቶ የተቀመጠዉ የግዜያዊ የሰዎች ማጎሪያ የተሠራዉ በእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ግዜ ሲሆን የአገሬዉን ዜጎች አንበርክከዉ እያስገበሩ እንቢ ያለዉንና ነፃነቱን የሚጠይቀዉን በዚህ እስፈሪ እስር ቤት ብዙ የንፁሃንን ሕይወት የቀጠፉበት ቦታ ነዉ :: ከነፃነት በኋላም የተተካዉ ጥቁር አምባ ገነን በራሱ የማይተማመን ኮሽ ባለ ቁጥር የሚደነብር በመሆኑ ዜጎችን አፍኖ እያሰቃየ መግዛትን መርጧል። በዚህም ምክንያት በአምባ ገነኑ ኢዲያሚን ዳዳ ከጌቶቹ የተማረዉን በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ያለፍርድ እየታፈኑ የሚያሰቃዩበትና የሚገድሉበት ቦታ ሆኗል። ከዚህ ጣቢያ እንደደረስን የተረከበን አንድ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ለማስተባበርና ተጨማሪ የፀጥታዉን ዘርፍ ለማጠናከር ከሰሜኑ ክፍል የመጣ ኮረኔል ነበር:: አጋጣሚ ሆኖ እኛ ካምፓላ በገባንበት ቀን ዩጋንዳ የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀመምበር ስለነበረች

የዓመቱን የአፍሪካ







መሪዎች ስብሰባ የሚካሄደዉ ከዚሁ ካምፓላ ነበር ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

105

ለዚህ ስብሰባም ለመካፈል የአፍሪካ መሪዎች ወደ መዲናዋ እየገቡ ነበር ::የኛም አገር ሚሪ የነበሩት የደርጉ ሊቀመምበር ጀኔራል ተፈሪ በንቲ ለዚሁ ስብሰባ ካምፓላ ገብተዋል ይህ የቀን መጋጠም ደግሞ ለኛ ጥሩ አልሆነም እኛ የለበስነዉ ከሰዉነታችን ለሁለት ወራት ያልወለቀዉ የዘመቻ ዩኒፎርም ነበር ሲያዩን ወታደር የነበርን ነዉ የመሰልነዉ ስለልብሱ ሲጠይቁን የዘማች ልብስ ነዉ:: ብንልም ልናሳምናቸዉ አልቻልንም:: ለማንኛዉም መፍትሄዉ እስከ ስብሰባዉ ፍጻሜ እናንተን ማሰርና ማቀየት ነዉ ስብሰባዉ እንዳለቀ ትወጣላችሁ በሚል ወደ ዚሁ እስር ቤት እንድንገባ ተደረገ። እሥር ቤቱ በጣም ብዙ ሰዉ የሚይዝ ትልቅ አደራሽ ይመስላል እኛ ከምድር በታች ከሚገኝ አንድ ክፍል ለብቻችን ተሰጠንና ገባን ክፍሉ በሩ ጥግ በመሆኑ ወደ እስር እየተጋፈፈ እየተገረፈ ወደ ዋናዉ ማጎሪያ የሚጣለዉን በክፍላችን ቀዳዳ እናያለን፣

በተለይ ማታ ማታ ሲገረፋ

የሚሰማዉ ጩኸት፣ይረብሻል : ሲያቃስቱ መስማት አዕምሮን





ያማል:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

106

ብዙ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚስተናገድበት እስር ቤት መታሰር የሚዘገንን ነዉ ፣: የኢዲ አሚን ልዩ ነብሰገዳይ ወታደሮች የታወቁ ናቸዉ :: የሚለብሱት ወታደራዊ ዩኔፎርሞ ከቀይ ቦኔት ጋር ሆኖ መልካቸዉም አብዛኞቹ ከራሱ ከኢዲ አሚን ብሔር ተመልምለዉ የመጡ በመሆናቸዉና በቂ ትምህርት ስለሌላቸዉ እንግሊዝኛ ከእንግሊዝኛ ይልቅ ኪሷሂሊ ይቀናቸዋል:: በዚህም ምክንያት ፖሊሶቹ ደግሞ ቢያንስ ሁለተኛ ደረጃ የጨረሱ ናቸዉ እንግሊዘኛን እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ ይናገሩታል ይጽፋሉ:: በዚህ ምክንያት የአሚን ቀይ ቆብ ለባሽ ወታደሮችና ፖሊሶቹ አይግባቡም ይህ ስለሆነም ቀይ ለባሽ የአሚን ቅልብ ወታደሮችና በፖሊሶቹ መካከል መናናቅ አለ:: በዚህላይ ቀይ ለባሾች ወደ እስር ቤት ያመጡት ሰዉ በበነጋዉ መጥተዉ ራሳቸዉ መጥተዉ ካልወሰዱት ሰዉየዉ ከዚያዉ ይኖራታል እንጂ የሚለወቀዉ የለም አንዳንዴ አምጥቶ ያሰረዉ ወታደር ለሥራም ይሁን ለእረፍት ከሄደ ታሳሪዉ ከዚያዉ እስር ቤት መኖሩ ነዉ::

ያለዚያ ግን

ሁል ጊዜ ያሰሩትን ራሳቸዉ መጥተዉ ይወስዱታል :ወሰዱት





ማለት ደግሞ ይሄን ዓለም ተሰናበተ ማለት ነዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

107

አንድ ቀን አንድ ከታንዛኒያ ለሥራ የመጣ ሰዉ በነዚሁ ቀይ ባርኔጣዎች ተይዞ መጣና ተቀብሎ የመዘገበዉ ፖሊስ ነገሩ ቀላል ስለመሰለዉና የዉጭ አገር ዜጋም በመሆኑ ቶሎ የሚወጣ መስሎት አመጣና እኛ ካለንበት ክፍል አስገባዉ: ሰዉየዉ በጣም ፈርቶና ተጨንቆ ነበር ለምን እንደዚያ እንዳሰበ ስላልገባን ልናጽናናዉ ብንሞክርም አልሆነም ::

” የኔ ነገር አልቆልኛል ወስደዉ ይገድሉኛል አለን: ለምን ምን ስርተሃል ብንለዉ የሠራሁት ምንም የለም ወንጀሌ ከታንዛንያ መምጣቴ ነዉ ይሄም ኢዲ አሚንና የታንዛንያዉ መሪ ፕሬዘዳንት ኔሬሬ ስለተጣሉ የነበረዉን የምስራቅ አፍራካ ሕብረት አፍርሰዉ ባቡሮቹንም በየ ሀገሩ ዘርፈዋቸዋል ሠራተኞቹንም እንደዚህ እያደረጉ እየገደሏቸዉ ነዉ እኔም ወንጀል ሠርቼ ሳይሆን የዚሁ የነሱ ጥል ሰለባ በመሆኔ ነዉ። አለ እንዳለዉ አልቀረም ብዙ ሳንቆይ ባለ ቀይ ቆቦች መጡና







ይዘዉት ሄዱ እሱም እንባዉ ባዓይኑ እያቀረረ ተለየን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

108

እንዲሁ አንድ ከሱዳን ወደ ሴንተራል አፍሪካ በእግራቸዉ ለመሄድ ሲሞክሩ በበርሃዉ ማዓበል ተዉጠዉ ብዙዎቹ ሲሞቱ አንድ ተርፎ ወደ ዩጋንዳ ለመግባት የቻለ ኢትዮጵያዊ ወጣት ከዚሁ ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት ያመጡና በስህተት ዩጋንዳኖች ከሚታሰሩበት ያስገቡታል ::

ይህ እስር ቤት ዙሪያውን ሁለት ፎቅ ሆኖ ማህሉ ሰፊ ቦታ ያለዉ የሆነና ጧት ጧት እሥረኞች ወጥተዉ የሚቆጠሩበትና ትንሽ ሰዉነታቸዉን የሚያፍታቱበት ሜዳ መሳይ

ሴሆን ማህል ላይ የሚከፈትና የሚዘጋ ክዳን ያለዉ

ጉድጓድ ያለዉ ሲሆን ዙሪያዉን በሽቦ የታጠረ ሆኖ እሥረኞች ከአጥሩ ዙሪያ ሆነዉ ከዚህ ጉድጓድ ገብቶ የሚቀጣዉን እስረኛ ለማየት የሚያስችል ነዉ። ታዳያ ወጣቱም ከዚህ ከዩጋንዳ እስረኞች ጋር ነበር ለአራት ቀን የቆየዉ፣ በአራተኛዉ ቀን ግን አንድ ደግ ተረኛ መኮነን እስረኞችን ሲቆጥር ከሱ ደርሶ ሲጠይቀዉ ኢትዮጵያዊ እንደሆነና የመጣዉም የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደሆነ ይነግረዋል በዚህ ግዜ ተረኛ መኮንኑ በስህተት ከዚያ እንደገባ ስለተረድቶ

አዉጥተወዉ እኛ ወዳለንበት





ክፍል አመጡት::

እኔና

ወጣቱ

የስደት ጉዞዬ

109

እንደመጣ እኛን ሲያገኝ በጣም ተደሰተና

ያሳለፈዉን ችግር ብዙ ካጫወተን በኋላ ከሁሉ የከፋዉ ግን አንድ ያየሁት ነገር

ነዉ አለ እንዴት አልነዉ እናንተ

እኮ

ከዚህ እንደ ገነት ነዉ የምትኖሩት እዚያ ክፍል እኮ ሲኦል ነዉ። በተለይ ትናንት ያየሁትን እስከ እለተ ሞቴ አልረሳዉም አለ እና ? የሆነዉን እንዲህ ሲል ጀመረ ” 10 የሚሆኑ ጥቁር ቀይለባሾች ከምሽቱ ሁለት ስዓት ገደማ በሩን ከፍተዉ ገቡና ሁለት እስረኞችን በስም ጠርተዉ እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ ከሜዳዉ ማህል ካለዉ ጉድጓድ ከፍተዉ

ሁለቱንም

እየወረወሩ ጣሏቸዉ:: ሁለቱም ራቁታቸዉን ናቸዉ ከዚያ እስረኞችን በሙሉ ወጥተዉ ዙሪያዉን እንዲቆሙ አደረጉና ጉድጓድ ዉስጥ ያስገቧቸዉን እስረኞች ለያንዳንዳቸዉ ስለት ማሸቴ ሰጧቸዉና እርስ በርሳቸዉ እንዲጨፋጨፉ እና አሸናፊዉ ብቻ በነፃ እንደሚለቀቅ ካልሆነ ግን ከዚያዉ እንደሚገደል ትእዛዝ ሰጧቸዉ። እንቢ ያለ በሌላኛዉ እንዲገደል አዘዙ







ከዚያም እርስ በርሳቸዉ መከታከት ጀመሩ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

110

በመጀመሪያ ትንሽ ከተፈላለጡ በኋላ አንደኛዉ ሌላኛዉን ለመግደል ስላልፈለገ እሱን በእንቢተኛነት በሚል ዙሪያዉን ከቆሙት ወታደሮች በጥይት ገደሉትና ሌላ ተፋላሚ ከዉጭ ወርዉረዉ አስገቡ:: እሱም ከመሞት የምድን መስሎት ግደል የተባለዉን ለመግደል ሲከታከቱ ቆይተዉ መጨረሻ ሁለቱም ዝለዉ ጭንቅላታቸዉ ተፈላልጦ ተያይዘዉ ሲወድቁ ከዚያዉ በጥይት አሰናበቷቸዉ። ዙሪያዉን ከበዉ የሚመለከተዉ እስረኛ ሁሉ በኃዘን ተሸማቆ ወደየክፍሉ እንዲገባ ተደረገ የተወሰኑት ተመርጠው

የሟቾችን አስከሬን ወስደዉ እንዲቀብሩ

ታዘዉ ሄዱ። ይህ ሌሊት በሕይወቴ ካየኋቸዉ ዘግናኝ ነገሮች በአዕምሮዩ ተቀርጾ የሚኖር የዘላለም ጠባሳ ነዉ”. አለና ሁኔታው እየዘገነነው አጫወተን።

አዎ

በዚህ አይነት

እኛ ዉነትም እድለኞች ነበርን ቀን

ወጥተን ስንዞር ዉለን ማታ ማታ እስር ቤት ከተሰጠን ክፍል ገብተን እናድራለን ::

ነገሩ እኛ ኢትዬጵያዉያን ስለነበርን

በኢዲ አሚን ላይ ምንም አደጋ እንደማናደርስ ስለተማመኑ







መስለኝ ብዙም አልተሰቃዬንም::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

111

እየቆየን በጋንዳ ፖሊሶች ጋርም እናወራ ነበር:: ከፖሊሶቹ መካከል በዪኒቭርሲቲ ደረጃ የተማሩና ስነ ስርዓት ያላቸዉ ነበሩ:: የኢዲ አሚን ልዩ ወታደሮች ግን መሀይሞች ስለሆኑ ሕዝቡ ይንቀናል የሚል የዝቅተኛነት ስሜት ስላላቸዉ ጥላቻቸዉን በመግደልና በመደብደብ ይወጣሉ:: እድሉ ከነሱ ፊት ለፊት የገጠመዉ ሰዉ ለነሱ የማይመስል ከሆነ እሱን አያርገኝ: ከመደብደብ እስከ መገደል የሚወሰነዉ ከዚያዉ ባሉበት ቦታ ላይ ነዉ::ምክንያቱም እነሱ የፈለጉትን የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው (Kill with impunity):: ቀይ ባርኔጣዎች ባካባቢው ከታዩ ድመት እንዳየች አይጥ ሁሉም ባገኘው ቦታ ካልተደበቀ እሱን አያርገኝ :: አንድ ቀን

ከእስር ቤት ወጥተን ምግብ ለመብላት ስንሄድ

መንገድ ላይ ነብር እንዳዬ ሚዳቋ ሕዝቡ እየበረገገ እኛ ወዳለንበት

አቅጣጫ

ሲሮጥ

አየን : አያይዞም የጥይት

ተኩስ ይሰማል ግራ ገባንና እኛም እንዳንጨፈለቅ በሚል ወደመጣንበት ተመልሰን መሮጥ ጀመርን::መቼም ዪጋንዳ በቆየንበት ወቅት

የተማርነዉ ነገር ቢኖር ሰዉ ከሮጠ





መሮጥ ተሰልፎ ካየን ደግሞ መሰለፍ ነዉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

112

ሩጫዉ ከአሚን ገዳይ ወታደሮች ለማምለጥ ሲሆን ሰልፉ ደግሞ የሚሽጥ ነገር መንግሥት አምጥቷል ማለት ነዉ በተለይ ስኳር ዳቦና ጫማ:: ተሰላፊዉ እቃዉን በሆነ ገንዘብ ገዝቶ ከዚያዉ አትርፎ ይሽጠዋል ይህ የሆነዉ ህንዶች ወጥተዉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከተንኮታኮተ በኋላ መሆኑነዉ:: ታዲያ ብዙ ከሮጥን በኋላ

መጠለያ

ቦታ ይዘን ከቆምን

በኋላ አንዱን ምን እንደሆነ ነገሩ ስጠይቀዉ ወታደሮች በአሚን ላይ ያልተሳካ የመግደል ሙከራ ስላደረጉ አሁን የእሱ-የእሱ-- የሱሱ ቀ-ቀ ይ ባርኔጣ ለባሽ ወታደሮች በንዴት ያገኙትን

ሁሉ እየገደሉ ነዉ አለን : በድንጋጤ የሮጠበት

ትንፋሹ እየተቆራረጠ :: እኛም ይህን እንደሰማን

ምግቡን ትተን ቶሎ ወደ እስር

ቤታችን ገብተን ሳንወጣ አደርን :: ጧት ሁሉም ሰዉ ወደ ካምፓላ ስታድዬም

እንዲሄድ በሬዲዬ ተነገረና እኛም

የሚሆነዉን ለማዬት ከሕዝቡ ጋር ሄድን:: ሕዝቡ ስታድዬሙን ሞልቶታል አንዳንዶች ፊታቸዉን ሸፍነዉ የዉስጥ ለቅሶ ይንሰቀሰቃሉ ከስታዲዬሙ ማህል







አሽዋ የሞሉ በርሚሎች በተርታ ተሰልፈዉ ተደርድረዋል:::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

113

ትንሽ እንደቆየንና ሕዝቡም ጨርሶ ገብቶ ቦታዉን እንደያዘ ዓይናቸዉ በጥቁር ጨርቅ የተሸፈኑ ሰዎች እጃቸዉ ወደኋላታስሮ በቀይ ቆብ ወታደሮች እየተገፉ መጥተዉ ከቆሙት

በርሚሎች ጋር

በገመድ ከወገባቸዉ ታሰረዉ

ቆሙ:: ትንሽ እንደቆየን እነዚሁ የኢዲ አሚን ቀይ ቆብ ወታደሮች በሰልፍ መጡና ከታሰሩት ሰዎች ፊት ለፊት በተጠንቀቅ ቆሙ

ወዲያዉም ጠመንጃቸዉን አቀባብለዉ ሁሉም

ታስረዉ ወደቆሙት ሰዎች አነጣጠሩ አዛዡ ተኩስ የሚል ትዕዛዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ:: በተጠንቀቅ የቆሙት

ወታደሮች ሁሉም በአዉቶማቲክ

ክላሽ መጀመሪያ ሁሉም አንዱን ተኩሰዉ ገደሉ እንደተመታ ሰዉየዉ ከወገቡ በላይ ያለዉ ገላዉ ወደታች ጎንበስ በማለት ይችን ዓለም ተሰናበታት::ቀጥሎ አዛዡ አሁንም ተኩስየሚል ትዕዛዝ ሰጠ አሁንም የሚቀጥለዉን ተገዳይ እንደዚሁ ሁሉም አነጣጥረዉ ሰዉነቱን በሳሳዉ እንደመጀመሪያዉ ከወገቡ በላይ ያለዉ ሰዉነቱ እጥፍ አለና ቀረ:: ለሥስተኛዉ ተገዳይ ሲዘጋጁ ሁሉም ተገዳዪች ድምፃቸዉን ባንድ ላይ ከፍ በማድረግ ኢዲ አሚን ነብስበላ ነዉ የዬጋንዳ ሕዝብ ትግላችሁን አጠናክራችሁ ይሄን ታይራንት አስወግዱ







የሚል ድምፅ አሰሙ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

114

አሁን አንዳንድ መግደላቸዉ ቀረና ሁሉምባንዳ አንዳንዶቹን በአዉቶማቲክ ክላሽ ጨፈጨፏቸዉ::ሁሉም

ዉደፊት

በማጎንበስ አገራቸዉንና የሚወዱት ሕዝባቸዉን ሳይታደጉ በዚሁ ተሰናበቱ:: ዩጋንዳ የነበሩ የህንድ ተወላጆች በ90 ቀናት ዉሰጥ ምንም ሳትይዙ ዩጋንዳን ለቃችሁ እንድትወጡ በማለት ኢዲ አሚን ባዘዘዉ መሠረት

ሁሉም በሚባል ደረጃ በያገሩ በተለይም

ከናዳና ናይሮቢ እድሜ ልካቸዉን ያፈሩትን ኃብትና ድርጅት እየጣሉ

ሲሄዱ አንድ ባንክ ዉስጥ ይሰራ የነበረ

አልወጣም ከዚሁ ግደሉኝ ከነበረዉ

ሕንድ

በማለቱ እኛ ከታሰርንበት

እስር ቤት አንድ ክፍል ተሰጥቶት ይኖር ነበር:

ክፍሉ ከኛ ፊት ለፊት ስለነበር:: እየተገናኘን ብዙ እንድናወራና ስለ ዩጋንዳ ከሱ ለማወቅ እረድቶናል አንድ ቀን ለምን ኢዲአሚን ህንዶችን ጠላቸዉ ምናልባት

እናንተ እንደሚባለዉ በኢኮኖሚ አገሪቱን

በዝብዛችኋል ? ስል ጠየኩት:: አደለም አሱ አልነበረም አለ እዉነታዉ ኢዲአሚን ብዙ ሚስቶች ማግባት ይፈልግ ነበር ። አንድ ቀን አንድ ሁለተኛ ደረጃ ት /ቤት ሲጎበኝ አንዲት የ17 ዓመት ልጅጃገረድ ያይና እሷን በትልቅ ሠርግ ያገባል: ከዚያም እንዲሁ ሌላ የህንዶች ት/ቤት ሲጎበኝ አንድ የህንድ







ልጃገረድ ያይና ላግባት ብሎ ይጠይቃል::

እኔና

ቤተሰብ

የስደት ጉዞዬ

115

እንቢ እንዳይሉ ፈሩና ለግዜዉ እሽ ይሉና

ሌላ

የሚያመልጡበት ዘዴ ይፈልጋሉ: ይኸዉም ልጅቷ ስትሰማ ራሷን አንቃ ገደለች በማለት ልጅቷን ማስወገድ ነበር። ኢዲ አሚን ሰርግ አድርጎ ልጅቷን ለመዉሰድ መልክተኞች ሲሄዱ ልጅቷ በፒያኖ ገመድ ራሷን ሰቅላ ተገኘች::

በዚህ

የተናደደዉ ኢዲ አሚን " ይሄን ያደረጉት ቤተሰቦቿ ናቸው : ይሄም እኔ ጥቁር ስለሆንኩ አኔን አግብታ ዘራቸዉ ከጥቁሮች እንዳይቀላቀል በማለት ነዉ :: ህንዶች አገራችን የሚኖሩት ሀብታችን ወደዉ እንጂ እኛን ወደዉ አይደለም ::

ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የለበሱትን ብቻ ይዘዉ አገራችን ለቀዉ እንዲወጡ

ለማድረግ

ኢዲ አሚን

የሜዲያ ተቋማትን

አስጠራ::: ሁሉም የሜዲያ አውታሮች ሲስበሰቡ::











” ስሙ ! ዛሬ ሌሊት በህልሜ አምላክ አንድ ነገር ነግሮኛል እሱም አንተ ከአፍሪካ ትልቁ መሪ ነህ ስለዚህ ህንዶች የአገርክን ኢኮኖሚ እየበዘበዙ ስለሆነ ከዪጋንዳ ባስቸኳይ አስወጣቸዉ ብሎ ነግሮኛል:"በመሆኑም ከአሁን ጀምሮ ማንኛውም ዩጋንዳ የሚኖር ህንድ የለበስውን ብቻ እየያዘ በ90 ቀናት ውስጥ እንዲወጣ: ይሄን የማያከብር በራሱ የፈረደ መሆኑን ይወቅ”

እኔና

የስደት ጉዞዬ

116

በማለት አወጀ ህንዶቹ ምርጫ ስላልነበራቸዉ ሁሉም ተጠቃለዉ ወደ ናይሮቢ ሂደዉ የተለያዪ አገራት በመልሶ ማቋቋም ተከፋፍለዉ ወሰዷቸዉ: አሚንም

በሰሜን

የሚኖሩ ዘመዶቹን አስመጥቶ ያለሙያቸዉ እና ያለሥራ ችሎታቸዉ ህንዶች ለዘመናት ሠርተዉ ያፈሩትን ሱቆችና ድርጅቶች እየዞረ በነፃ አደላቸው። እዉነታዉ ይሄ ነዉ "

ብሎ አጫዉቶኝ ነበር:::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

117

ምን ችግር ቢገጥመዉ ፣ ምን ሆድስ ቢብሰዉ፣ ከእሳት ወደረመጥ እንዴት ይሄዳል ሰዉ፣!!

ይሁን እንጂ ጓደኞቼ ሲወጡ እኔ የምሄድበት አገር ስለለኝ ከዚሁ በሰብአዊ መብት

ስም ጥገኝነት ጠይቄ ይሄዉና

መልስ እየጠበኩ በዚህ ሁኔታ እኖራለሁ አለ። ደብዳቤ ጽፈን

ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች

ኮሚሽን (UNHCR) በጠየቅነዉ መሰረት

ኮሚሽነሩ

ከፕረዜዳንቱ ቢሮ ድረስ ወስዶን ኢትዮጵያወያን የፖለቲካ ስደተኞች መሆናችን

ካስረዳ በኋላ ለፖለቲካ ጥገኝነት

እንዲሰጠን ካልተሰጠንና ኢትዮጵያ ብንመለስ ግን የአገሪቱ አስተዳደሪ ደርግ ይገለናል አልን:: ኢዲ አሚንም አንዳንድ ነገሮች ከጠያዬቀን በኋላ ከደርግ ጋር ተጣልቶ ነበርና: እኛም ከመምጣታችን በፊት ይሄን እናዉቅ ስለነበር : እንዳሰብነዉ ያለ ችግር ምህረት አድርጎ የስደተኛ መብት ወዲያዉ

እንዲሰጠን

ለአገር ዉስጥ

ሚኒስትሩ "የዩጋንዳን ሕግ አክብረዉ እስከኖሩ ድረስ ትምህርት ለሚፈልግ ትምህርት ሥራ ለሚፈልግ ሥራ ስጧቸዉ "













አሰናበተን ::

ብሎ አዘዘና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

በዚህ መልክ የዩጋንዳ የሥደተኛነት ፈቃድ ከአገኘን

118 በኋላ

ገሠሠ ኢትዮጵያ እያለም የሬዲዬ ጥገና ይሠራ ስለነብር ወዲያዉኑ በዚሁ ሥራ ሲጀምር ::እኔ ትንሽ ቆይቼ ዩጋንዳ ቴክኒካል

ኮሌጅለኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ትምህርት

ተመዝግቤ መማር ጀመርኩ። በዩጋንዳ ቴክኒካል ኮሌጅ የሚሰጠዉን የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት እየተከታተልኩ በማገባደጃ ላይ የሚጠይቀዉን የሥራ ልምምድ ለአንድ ዓመት ለመሥራት ካምፓላ ማግኜት ስላልቻልኩ ናይሮቢ ሄጄ መሥራት ስለነበረብኝ ተጻጽፌ ባገኘሁት በፊሊፕስ ካምፓኒ እንድሠራ ስለፈቀዱልኝ ለመሄድ በመዘጋጄት ላይ እያለሁ የዩጋንዳ ታንዛንያ ጦርነት ተጀመረ:: ጦርነቱ ባልተጠበቀ ፍጥነት ሂዶ ካምፓላን ያናዉጣት ጀመር:: ከኮሌጁ ዶርምቶሪ እንደተኛን ከታንዛንያ ጦር የሚተኮሰዉ የመድፍ ጥይት እያለፈ ካለንበት አካቢቢ ይፈነዳ ጀመር: ሳይቆይ የኢዲ አሚን መኖሪያ አካባቢ ዒላማ እንደነበርና ባካባቢዉ ያሉ ቤቶችም እየተቃጠሉ እንደሆነ ሰማን::







ብዙም ሳይቆይ የታንዛንያና ተቃዋሚው አስርገው ያስገቧቸው ተዋጊዎች ካምፓላ ከተማ ውስጥ የአሚን ቀይ ለባሽ ገዳይ ወታደሮችን ባነጣጠረ መልክ በያሉበት ያረግፏቸዉ ጀመር: እነዚህ እንደ ጭራቅ ይፈሩ የነበሩ ነብሰ በላዎች እየተጠቁ እንደሆነ ያየ ሕዝብም ተዎጊዉን እየተቀላቀለ ባገኘዉ ሁሉ ያሳድዳቸዉ ጀመር::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

119

ብዙም ሳይቆይ ኢዲ አሚን በሄሌኮፍተር አገር ለቆ እንደወጣ ተሰማ:: ከዚያም የአሚን ቅልብ ወታደሮች ከእዝ በማፈንገጥ ሁሉም ያገኙዉን እየዘረፈ ወደየጎረቤት አገሩ መፈርጠጥ ጀመረ:: በዚህ ጊዜ የውጭ ዲፕሎማቶች ነጭ ጨርቅ እያውለበለቡ ባገኙት መንገድ በካንቮይ ወደ ናይሮቢ ጉዞ ጀመሩ ::



እንዳጋጣሚ አንድ የጀርመን ዜጋ የሆነ አስተማሪዬ ወደ ናይሮቢ ይሄድ ስለነበር መኪናዉን አስነስቶ ሊሄድ ሲል አገኘሁትና እኔንም እንዲወስደኝ ለምኜ ጉዞዉን ተቀላቀልኩና ናይሮቢ በሰላም ገባሁ።

የስደት ጉዞዬ

120

ምዕራፍ-7 ናይሮቢ-ኬንያ ናይሮቢ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ዘመናዊና በኢንዱስትሪ የበለጸገች ከተማ ስትሆን በውስጧ ከሁሉም አገሮች በሚባል መልኩ ዜጎች ተሰባስበዉ የሚኖሩባት ከተማ ነች:: ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣች በኋላ የአገሪቱ የመጀመሪያ ፕሬዘደንት የነበሩት ጆሞ ኬንያታ በቅኝ ገዥዋ እንግሊዝ ሞግዚት ስር እንዳለ በሚመስል መልኩ አገሪቱን እየመሩ ቆዬ::

የጆሞ ኬንያታ መንግሥት በውስጡ ከምክትል ፕሬዘዳንቱና ከጥቂቶቹ በቀር በኩኩዪ ብሔረስብ ተወላጆች የተሞላ ነበር::







ኬንያታ እንደሞቱ የተተኩት ፕሬዘደንት ሞዬ የኬናታን አሻራ (ሌጋሲ) ለማስቀጠል በሚል ምንም የሥርዕትና የሰው ለውጥ ሳያደርጉ በዚያው ስለቀጠሉ ተሿሚዎቹ ሚኒስትሮችም ያው በኬናታ ጊዜ እንደነበረው ቀጠሉ ::



እኔና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

121

ይህ ደግሞ የነበረውን ሙስናና በዘር መጓተትን እንደያዘ እንዲቀጥል አደረገ::የኬንያን ኤኮኖሜ ሰንገው የያዙትን በቅኝ ግዥዎች ጊዜ እንግሊዞች የባቡር ሀዲድ እንዲሠሩ ያመጧቸው የህንድ ተወላጆች ሲሆኑ የፖለቲካውንና ፀጥታ ክፍሉን እንግሊዞች የበላይነቱን ይዘው ይዘውሩታል:: አገሬው ኬንያዊው ግን የበይ ተመልካች ሆኖ በችግር ይሰቃያል: በዚህ የተነሳ የወንጀል ሥራና ስርቆትን እንደ ባህል አድርገው ይዘውታል::በናይሮቢ በሰላም ወጥቶ መግባት ችግር ነው : በየ አገሩ በፖለቲካ ተሰዶ ወደዚሁ ከተማ የተሰበሰበው የፖለቲካ ስደተኛም አብዛኛው በስርቆትና ቱሪስት በመጠጋት የእለት ጉርስ ለማግኘት የሚያደርጉት ትንቅንቅ አይጣል ነው:: ናይሮቢ ለአዲስ አበባው የአብዮታዊ መንግሥት ወዳጅ በመሆኗ የኢትዮጵያ የሥለላ መረብ ጥላውን የጣለባት ቦታ ስለሆነችም ስደተኛው እርስ በእርስ እንዳይተማመን አድርጎታል :: ናይሮቢ እንደደረስኩ በበነጋዉ ፊሊፕስ እንድጀምር የተነገረኝ ቀን ሳይደርስ ወደ ካምፓኒው ሄድኩና በጦርነት ምክንያት ቀድሜ መምጣቴን አስረድቼ መጀመር እችል እንደሆነ ጠየኩ::







የፊሊፕስ ካምፓኒ ፕላንንት ኢንጅነር (plant Engineer Mr Singh) ሚስተር ሲንግ የሚባል የህንድ ተወላጅ ነበርና ሳነጋግረዉ እንዳዉም ቀድሜ በመምጣቴ ያስደሰተው መሆኑን ገልጾ ሥራዬን በነጋታዉ እንድጀምር ነገረኝና አብሬዉ እንድሰራና እንዲያለማምደኝ ከአንደ ጃኮብ የሚባል የካምፓኒው ቴክኒሻን ጋር አገናኘኝና የመጀመሪያ ሥራዬን ጀመርኩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

122

ሁለት ዓመት የናይሮቢ ቆይታዬና የምሠራበት በፊሊፕስ ካምፓኒ በጣም ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩና የዩጋንዳ ጦርነትም ስላለቀ ዩጋንዳ ሂጄ የትምህርት ሰነዶችን ማምጣት ነበረብኝና ወደ ዩጋንዳ ለመጏዝ ወሰንኩ:: ቀኑ ዓርብ ጥቅምት 1979 ከቀኑ በ12 ስዓት ነበር ከናይሮቢ ተነስቼ በአዉቶቡስ ወደ ካምፓላ የተጓዝኩት፣ በታንዛኒያና ዩጋንዳ ጦርነት መነሳት ምክንያት ትቸዉ የሄድኩትን የትምህርት መረጃዎች ለማምጣትስገሰግስ ኬንያ ጠረፍ ከተማ ቡስያ የደረስኩት:: ከተማዋ በጣም ትንሽ ነች በግምት ወደ ሁለት ሽህ ሕዝብ ይኖርባታል ከከተማዋ መካከል ካለዉ አዉራ መንገድ በስተቀኝ አንድ በየጊዜዉ ሰዉ የማይለየዉ ቤት ተገትሮ ይታያል። በዚህ ቤት ዉስጥ ሁለት ክፍሎች አሉ አንደኛዉ የይለፍ ቪዛ ቢሮ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በድብቅ የሚገኙትን የክንትሮባንድ እቃዎች መፈተሻ ቤት ነዉ። በዉስጡ የሚተራመሱት ወታደሮች የሚመጣዉን ሰዉ ቀድመዉ ለማናገር ሲሽቀዳደሙ በዕዉነትተግተዉ ለሚከፈላቸዉ ደመወዝ ጥሩ አገልግሎት የሚሰጡ ይመስላሉ::







ግን ይህ ሁሉ ሺሚያ ለግል ጥቅም ጉቦ የሚበላበት ሰዉ ፍለጋ መሆኑን የተረዳሁት በኋላ በደረሰብኝ ችግር ምክንያት ነበር። እንደማንኛዉም ሰዉ ወደ ቪዛ ሰጪዉ ክፍል ገባሁና ፊት ለፊት ለተቀመጠዉ የፖሊስ መኮነን ያለኝን የዩጋንዳ የአገር ዉስጥ ሚኒስተር የሰጠኝን የስደተኛ ፓስፖርት አዉጥቼ ሰጠሁት::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

123

ፓሱን ገለጠና ዘቀዘቀዉ ምንም የወደቀ ነገር አልነበረም ቀና ብሎ አየኝ በማያያዝም ”አንተ ዉጭ ቆይ እስክጠራህ አለኝ ” ::ቲእኔም ነገሩ ሳይገባኝ ከቢሮዉ ወጣሁና ዉጭ ቆምኩ።ከኔ ጋር በአዉቶቡስ የመጡት ተሳፋሪዎች አንድ ባንድ እየገቡ የማለፊያ ማህተም እያስደረጉ ወጡና ሁሉም ተመልሰዉ ወደ አዉቶቡሱ ገቡ። ፓሴን የያዘዉ ፖሊስ ጠራና ወደ ቢሮዉ አስገባኝ ወንበሩን ወደኋላዉ ለጠጠና ያበጠ ቦርጩን ገልብጦ በመቀመጥ ” የት ነዉ የምትሄደዉ ? ሲል የሰጠሁትን ፓስፖርት በአዲስ እያገላበጠ ያልጠበኩትና መልስ የማያስፈልገዉ ጥያቄ አቀረበ :: ምክንያቱም ከዚያ ቦታ በዚያ መንገድ ሰዉ ወደሌላ ሊሄድ አይችልም ወደ ዩጋንዳ ካልሆነ በቀር በዚያ ላይ : የያዝኩት የዩጋንዳ ዶኩሜንት ስለሆነ እኔን ዩጋንዳ እንዳልገባ አይከለክለኝም :: ካምፓላ ነዋ! አልኩት መለስ አደረገና ኬንያ እስካሁን የቆየህበትን ፈቃድ አምጣ አለኝ ይህ ጥያቄም በራሱ አስፈላጊ ያልሆነ ነበር ምክንያቱም በምስራቅ አፍሪካ ህግ የኬንያና ዩጋንዳ ሕዝብ ቪዛና መኖሪያ ፈቃድ አያስፈልገውምና ነዉ : ሆኖም ፖሊሱ የፈለገዉ ጉቦ እንድሰጠዉ ነበር::እኔ ደግሞ ሌሎቹን በሰላም አሳልፎ እኔን በመጠየቁ በጣም ቢያናድደኝም ::











ይሁንለት ብዬ የያዝኳቸዉን የመሥራያ ቤቴን ወረቀቶች አሳየሁት ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

124

ይሁን እንጂ የሱ ፍላጎት ገንዘብ እንጂ መረጃ አልነበረምና፣ እንደገና ዓይኖቹን እያጉረጠረጠ ይህ በቂ አደለም ሁሉን ነገር አጣርታችሁ ሳታዉቁ ሰዉን ታማርራላችሁ አሁን በዚህ ምክኒያት እስር ቤት ልጨምርህ እችላለሁ:: ይሄን አታዉቅም አለ ! ቀና ብሎ እንደገና ከእግር እስከራሴ እየተመለከተ፣ እኔም ነገሩ ጥፋተኛ እንዳልሆንኩ ባውቅም የፈለገዉን ለማድረግ መብት እንዳለዉ ስለተረዳሁ በዝምታ ታገስኩት። በኋላ መለስ አደረገና የጠረጴዛዉን ኪስ እየሳበ ለመሆኑ ስንት ገንዘብ ይዘኃል ? አለና ጠየቀኝ ወዲያዉኑ ጉቦ አምጣ ማለቱ ገባኝና ያለኝ አምሳ የኬንያ ሽልንግ ነዉ አልኩት::







ለመሄድ ከፈለክ 100 አድርገዉ አዉቶቡሱም ይሄዉና ጥሎህ ሊሄድ ነዉ ሲል ትዓዛዙን አስተላለፈ፣ እኔም ከመጉላላት ሰጥቼ ከማለፍ ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ አዉጥቼ ጠረጴዛዉ ላይ ወረወርኩለትና የይለፍ አስመትቼ ወደ ካምፓላ ጉዞይን ቀጠልኩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

125

ዩጋንዳ ከጦርነት በኋላ: የዩጋንዳን ኬላ ጠባቂ ወታደሮች ብዙ ስላላስቸገሩኝ ወዲያዉ ኬላዉን አልፈን ወደ ዩጋንዳ ግዛት ዉስጥ ገባን ይሁን እንጂ አገሩ በፊት እንደማዉቀዉ አልነበረም:: ዩጋንዳ ዉብ አረንጓዴ የለበሰች በተፈጥሮ ያማረች ሀገር ነበረች:: አሁን በጦርነቱ ምክንያት ለምልመዉና አብበዉ ይታዩ የነበሩ ኮረብታዎች አልፎ አልፎ ተቃጥለዋል: በየመንገዱም የተቃጠሉ ታንኮችና የጦር ሠራዊት መኪናዎች ጊዜአቸዉን ጨርሰዉ ወደ አፈርነት ለመቀየር ካሉበት ፈራርሰዋል። ባካባቢዉ የነበሩ አንዳንድ ቤቶችም ተቃጥለዉ ወደ አመድነት ተቀይረዋል። በምትኩ በየ አሥር ኪሎ ሜትሩ አዲሶቹ የዩጋንዳ ወታደሮች መኪኖችን እያስቆሙ ይፈትሻሉ፣ ከዚያም ገንዘብ: ሲጋራ ይለምናሉ፣ በተለይ የዩጋንዳ ኢንዱስትሪ ከተማ ከምትባለዉ ጂንጃ ስንደርስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ተሽከርካሪዎችን አንድ ባንድ እየጠየቁ ያሳልፋሉ::







የወታደሮች ብዛትን ያዩ አንዳንድ መንገደኞች በድንጋጤ ሲርበደበዱ ያሳብቅባቸዉ ነበር ፣ የኔም ተራ ደረሰና መታወቂያየን አሳየሁ መታወቂያዬ ላይ ኢትዮጵያዊ ስለሚል ያለምንም ማንገራገር በክብር አሳለፉኝ።ካምፓላ የተወረረች ከተማ መስላለች ሱቆች ተመዝብረዉ ባዶ ቀርተዋል : መስኮታቸው እንደ ተሰባበረ ክፍት ሆኖ ጥገናን ይጠብቃል : በፊት ሳዉቃው ሰዉ ይተራመስበት የነበረዉ ቦታ አሁን የተወረረ መስሏል: ያ ሁሉ መተራመስ አይታይም::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

126

እንደ መብረቅ ነጎድጓድ ሰማዪን እየሰነጠቁ የከተማውን ሕዝብ ጆሮ ያደነቁሩ የነበሩት የኢዲ አሚን ዳዳ የጦር ጀቶች አሁን ድምፃቸዉ አይሰማም። ለካስ ኢዲ አሚን የጦር ሚግ አይሮፕላኖቹን ሁል ግዜ በካምፓላ ከተማ ላይ አብራሪዎች እንዲለማመዱ ያደርግ የነበረዉ ሕዝቡን ለማሸበር ነበር: እንጂ መለማመጃ ቦታማ አጥተዉ አልነበረም። እና ዛሬ ከኢዲ አሚን ሚጎች ነፃ የሆነች ካምፓላ ሆናለች።

ጓደኛዬ ተኮላ ከሚኖርበት ቤት ሄድኩና አረፍኩ። ምሽቱን በመንገድ ስለገጠመኝ ሁኔታ እያወራን ጥሩ አመሸን ከዚያም እንበላበት ከነበረዉ ሆቴል ተያይዘን ሄድን ሆቴሉ በዩጋንዳ የታወቀ ዘመናዊ ስለነበር ”ካምፓላ ኢንተር ናሽናል ሆቴል ” ብሎ የሰየመዉ ኢዲ አሚን ነበር ይላሉ። የዛሬን አያድርገዉና ድሮ የሚገቡበት በአብዛኛዉ የዉጭ ዲፕሎማቶች፣ ደህና ገንዘብ ያላቸዉ ነጋዴዎችና በነፃ ፈርመው የሚበሉ የኢዲ አሚን ወሬ አነፍናፊ ገዳይ ወታደሮች ነበሩ። አሁን ግን የዩጋንዳ ተቃዎሚዎች ተዋጊ መኮንኖች (Ugandas resistance army officers) እና የታንዛንያ ወታደሮች ናቸዉ።









ሆቴሉም እንዳልሆነ ሆኗል: የምግብ ምርጫ አልነበረም የተገኘዉ የበቆሎ ገንፎ ወይም (ኡጋሊ) የሚሉት ምግብ ብቻ ነበር :::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

127

ብዙ ምርጫ ስለሌለን ያለዉን አዘዝነና ቢራ ብንል አልተገኘም በጣም ጥቂት ሰዎች ለጉራ ያገኟትን አንድ አንድ ቢራ ዘረጴዛዉ ላይ ሳትነሳ እንድትቆይ ያስቀምጧታል ያላገኙትን ለማስጎምጀት ነዉ ይሏቸዋል ።እኛም ራታችን በልተን በእግራችን ቀጠልን::

የምንሄደዉ ዎናዉን መንገድ ይዘን ስለነበር ከተማዋን በምሽት ለማየት እድል አገኘን: በዚህ መንገድ ድሮ በአሚን ጊዜ የቀይ ቦኔት ለባሾች በመኪና ሲያልፉ የተገኘ ሰዉ ሚስቱንም መኪናዉንም ተቀምቶ ባዶውን ነበር የሚሄደው:: አሁን ግን ያሁሉ የለም የኢዲ አሚን ገዳዮችም የሉም::ጦርነቱ እንደተጀመረ ከመዎጋትይልቅ ያገኙትን እየዘረፉወዳመቻቸው አገር ፈርጥጠዋል::ላይመለሱ ተሸኝተዋል። በአጠቃላይ ለሕዝቡ ትልቅ እፎይታ ሁኗል:: አሁን መሸማቀቅ የለም በሁሉም ሰዉ ፊት የሚታየዉ ፈገግታና :የነገው ተስፋ ብሩህ እንደሚሆን ይመስላል ::







ካምፓላ በሥስት ቀናት እጨርሳለሁ ያልኩት ሥራበነበረዉ የአስተዳደር ዉስብስብነትና መተራመስ ምክንያት አንድ አሥራ አምስት ቀናት ወሰደብኝ እና በአሥራ ስድስተኛዉ ቀን ተመልሼ ወደ ናይሮቢ ታክሲ ይዜ ቡስያ ጠረፍ ተጓዝኩ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

128

ከተማዋ እንደደረስኩ ወደዚያዉ ጉቦኛ ፖሊስ ቢሮ አመራሁና የይለፍ ጥያቄዮን አቀረብኩ፣ ሀሳቤ ባለፈዉ ሰጥቻለሁና ዛሬ ያለ ችግር ያሳልፈኛል የሚል ነበር : ግን ነገሩ ተለዋወጦ ጠበቀኝና አሁንም ያዉ 100 ሽልንግ ክፈል ሲለኝ እንዳጋጣሚ ሁለት እንግሊዞች ገብተው ከኔ ቀድመዉ ያለ ምንም ጥያቄ ማህተም መቶ ሰጣቸዉና ሄዱ :: እኔ ግን እንደቆምኩ ቀረሁ :: ምነዉ ለነሱ ሰጠህና እኔን ታጉላላኛለህ አልኩት ” አንተማ የኩኩዬን ፀባይ ስላላወክ ነዉ ” ? አለኝ ምን ማለትህ ነዉ አልኩት ::

አየህ እኔ ኩኩዩ ነኝ ማለቴ ነዉ አለኝ ” እንደገና ታዲያ ኩኩዩ የሆንክ እንደሆነ ከኔ ቪዛ ጋር ምን አገናኘዉ!! በንዴት ሰዉነቴ እየተንቀጠቀጠ፣ (Speak with money my friend , money Speaks even in America)” አ”አየህ አለ ኩኩዩ የትም ቦታ ስታገኝ በገንዘብ መናገር እንጂ በአፍህ መለፍለፍ ትርጉም የለዉም” አለኝ :: ነገሩ አሁንም የገንዘብ ጥያቄ መሆኑ ገባኝና በጣም ተናደድኩ::







አጉል እልህም ያዘኝና እኔ የገንዘብ ማተሚያ ፋብሪካ የለኝም: በሄድኩ በመጣሁ ቁጥር ላንተ መንግሥት ያላወቀዉ ቀረጥ የምከፍልበት ምንም ምክንያት የለም:: በሕጉ መሠረት በነፃ ማለፍ ስችል አንተ ግን የመንግሥትን ቢሮ ተጠቅመህ እኔን ታበሳጨኛለህ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

129

ደግሞ አብረውኝ ለመጡት ፈረንጆች ያለ ምንም ችግር ሲያልፉ እኔ አፍሪካዊ ስለሆንኩ ታሰቃየኛለህ። ወይስ እኔ ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ነዉ ? ስል በምሬት ተናገርኩ:: እኛ አፍሪካዉያን እርስበርስ ስንጎዳዳ ለፈረንጆች መሳቂያ እንሆናለን:: አንተ ደግሞ በጣም የምትገርም ሰው ነህ! እንዴት ነጮችን አሳልፈህ እኔን ታሰቃየኛለህ፣ በእልህ ከሆነ ደግሞ እኔ የምከፍለዉ የለኝም እንዲያውም አለቃህን ማነጋገር እፈልጋለሁ አልኩት።





ምንም አልተናገረም ብቻ ፊት ለፊቱ ካለዉ አግዳሚ መቀመጫ እንድቀመጥ አዘዘኝና ተቀመጥኩ። ወዲያዉ ወታደሮች መኪና አመጡና ግባ አሉኝ :ገባሁና ወደ አንድ የሰዎች ማጎሪያ እስር ቤት ወሰዱኝ። ምንም ማድረግ ስለማልችል እንደወንጀለኛ መሳሪያ በያዙ ወታደሮች ታጅቤ እስር ቤት ተወረወርኩ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

130

ምእራፍ -8 የኬንያ ቡስያ እስር ቤት፣ ቀኑ ዓርብ ስለነበር የግድ እስከ ሰኞ ከዚሁ እሥር ቤት ማሳለፍ አለብኝ ምክንያቱም ለፍርድ የምቀርበዉ ሰኞ ሲደርስና ፍርድ ቤቱ የሚወስንብኝን ቅጣት ሲወስን ብቻ ነው።ወደ ወህኒ ክፍል ከመግባቴ በፊት በኪሴ ያለኝን ገንዘብ መታወቂያና የያዝኳቸዉን ጥቂት ልብሶች ለተረኛዉ ፖሊስ በዝርዝር አስረከብኩትና ስጨርስ የለበስኩትንም ልብስ አዉልቄ በቡታንታ ብቻ መግባት እንዳለብኝ ነገረኝ:: እኔም ለምን አወልቃለሁ አልኩት :?ፖሊሱ ዉስጥ በጣም ሙቀት ስለሆነ ልብስ ከለበስክ መተንፈስ አትችልም ልትሞት ትችላለህ አለኝ::









ከሞት ተርፈህ ብትወጣም ልብስህ በጣም መጥፎ ሽታ ስለሚኖረዉ እሱን ለብሰህ ከሰዉ መጠጋት አትችልም:: ስለዚህ ነዉ ማዉለቅና በቡታንታ ብቻ መሆን ያለብህ አለኝ :: ጉድ አያልቅምና እንደታዘዝኩት ልብሴን አዉልቄ አስረከብኩና በቡታንታ ብቻ ወደ ተዘጋጀልኝ የሰዎች ማጎሪያ ክፍል ገባሁ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

131

የእስር ቤቱ ክፍል፣ ከአንድ ጠባብ ጨለማ ክፍል በሩን ከፈተና ወረወረኝ ዉስጡ ጨለማ ነዉ በተለይ ከውጭ ወደውስጥ ለሚገባ ሰዉ እንደገባ ምን እንዳለ ለማየት አስቸጋሪ ነዉ:: በግምት 5 ስኪየር ሜትር ትሆናለች: ከበር በቀር መስኮት የሚባል ነገር የላትም:: ትንሽ ለዓየር ማስገቢያ የምትመስል ቀዳዳ ከጣራዉ ተጠግታ የፀሐይን ጮራ በማሳየት ቀን መሆኑን ታመለክታለች::በስሚንቶ የተለሰነዉ ግድግዳ ና ወለሉ በሰዉ ላበት ቅቤ የተቀባ ይመስላል: ወለሉ አሣ እንደ ላሰዉ ድንጋይ ያሙለጨልጫል ፣ ራቁት ከቆሙትና ከተቀመጡት ሰዎች በቀር ሌላ ነገር የለም:: ከቦታዉ ጥበት አንጻር አዲስ ለገባ ሰዉ የመጀመሪያ ጥያቄ የት ልቀመጥ ሳይሆን የት ልቁም ነዉ ።







ከዚህ ዉስጥ የታጎሩት ሰዎች ሁሉምጥቁሮች ስለሆኑ ከጨለማዉ ጋር ሰዉን መለየት አይቻልም::ብዙ እየቆየሁ ስሄድ በስንጥቁ በር በምትገባዉ ብርሀንና በጣራዉ ጥግ ባለች ቀዳዳ ሰዎችን ለመለየት ሞከርኩ ግን ማነን ከማን እለያለሁ ! ሁሉም ጥቁር በዚያ ላይ ራቁት! ቦታዉ በሙሉ ተይዟል ባንድ በኩል የተቀመጡ ሰዎች አሉ በሌላኛዉ በኩል ለመፀዳጃ የተቀመጠች ባልዲ አለች (ማርያ የሚል ) ስም ስጥተዋታል ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

132

እሷም የአንድ ሰዉ ቦታ ይዛለች በኋላ እንደተረዳሁት ከዚህ ክፍል የገባ ሰዉ ያጎዛ የማይከፍል ከሆነ ለተወሰነ ስዓታት ማሪያን አቅፎ እንዲቀመጥ ይፈረድበታል::ለነገሩ ማርያ ታቀፈች አልታቀፍች ሽታዋ እንደሆነ እንኳን ከዛች ከታፈነች ክፍል ውጭም ቢሆን አካባቢው ይሰነፍጣል;: እንደ ሳዉና ከሚሞቀዉ ክፍል ገና ከመግባቴ ይህ እንደ ፍየል ጉርጅ የሚሰነፍጠዉ ሽታ አጥወለወለኝ :: ለማስታወክ ሲሞክረኝ ያዬ አንድ ሰዉ ሞላ ሲል ስሜን ጠራኝ :: ራሴን ማመን አልቻልኩም ደግሞ ምን አይነት መላክ ከዚህ መጥቶ ጠራኝ ! አልኩ: በህልሜ ያለሁም መሰለኝ ::

የሆነ ምኞት ነዉ እንጂ ከዚህ ዉስጥ እኔን የሚጠራ ሊኖር አይችልም ብዬም ከራሴ ጋር ስሟገት ገና እኔ ሳልመልስ እንደገና ሞላ እኔ መሐመድ ነኝኮ! አንተን ደግሞ ከዚህ ምን አመጣህ አለኝ ?::







ትንሽ እየቆየሁ ስሄድ ጨለማዉን እየተለማመድኩ ሄድኩና ያሉትን ሰዎች ገጽታ በመጠኑም ቢሆን መለየት ቻልኩና መሐመድ ከማህል ከተቀመጡት ሰዎች መካከል ቁጭ ብሎ አየሁት: አዎ የማዉቀዉ ስደተኛዉ ጏዴ ያገሬ ልጅ መሐመድ ነበር።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

133

መሐመድ

አንተ ደግሞ ከዚህ ምን አመጣህ አለና ሰዎቹን እየረገጠ መጥቶ አንገቴ ላይ ተጠምጥሞ ተሳስምን ፣ አዎ ከመሐመድ ጋር ሁለት ዓመት ካምፓላ አብረን ኖረናል ፣: ከዚያ ትንሽ ሲነጋግድ ከቆየ በኋላ በስደተኛ ሌሴ ፓሴ ወደ ሳዉዲአረቢያ ለመሄድ ስላልቻለ ከአንድ ሱዳናዊ ፓስፖርት ገዝቶ የሰውየውን ፎቶ ይነቅልና የራሱን ፎቶ ግራፍ ለጥፎ የአይሮፕላን ቲኬት በመግዛት ሳዉዲ ለመሄድ ወደ ካይሮ በረረ:: ካይሮ አየር ማረፊያ እንደደረሰ ቪዛ አስመትቶ ከተማ ለመግባት የተገዛዉን ፓስፖርት ለግብጽ ኢሚግሬሽን ያቀርባል ፣ የግብፅ ኤሚግሬስንም ፓስፖርቱን ያነባሉ:: በአረብኛ የተጻፈዉ ስም እንዳለ የሱዳናዊዉ ስም ሰይድ አህመድ ይላል በእንግሊዝኛ የተጻፈዉ ስም መሐመድ አህመድ ይላል:: ይህ የማን ፓስ ነዉ ሲሉት የኔ ነዉ:: አንተ ስምህ ማነዉ መሐመድ አህመድ ነዉ ይላል ታዲያ ለምን ነዉ ሰይድ አህመድ የሚለዉ በአረብኛ የተጻፈዉ ? ሲሉት ዓይኑ ይፈጣል :የሚመልሰዉ ያጣል፣ ከዚያ ወደ ግብፆች እስር ቤት ይወርዳል::









ትንሽ ከእስር ቤት ከቆየ በኋላ መሐመድ አንድ ዘዴ ይፈጥራል ይሄዉም ከዚያ በነበረዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተላልኮ ይገናኝና ለኤንባሲዉ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ፓስ ከአገሩ እንደወጣና ከወጣ በኋላ ሥደተኞች ፓሱን ሰርቀዉ የኢትዮጵያ ሰላይ ነህ ብለዉ እንደደበደቡት ፣ ከዚያም ከአንድ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

134

ሱዳናዊ ፓስ ሰርቆ ወዳገሩ ለመግባት ያገኘዉን አይሮፕላን ይዞ ለመብረር ሲሄድ ያጋጠመዉ ወደ ካይሮ የሚበር ስለነበር በዚያው አድርጌ ወደ ኢትዮጵያ እበለራለሁ በሚል እሳቤ ወደ ካይሮ በድንገት እንደመጣና ከዚህ ሲደርስ እንደታሰረ ገልጾ ኤምባሲዉ እንዲረዳዉ ጠየቀ::

በዚህም መሰረት ምንም እንኳን ያቀረበዉ ምክንያት አሳማኝ ባይሆንም በጊዜዉ የነበረዉ አምባሳደር ጥሩ ሰዉ ለዜጎቹ ተቆርቋሪ በመሆኑና በወቅቱ የግብፅና ኢትዮጵያ ግንኙነት ጥሩ ስላልነበረ የኢትዮጵያን ዜጎች በሆነ ባልሆነዉ እያሰራችሁ ታሰቃያላችሁ በሚል ኤምባሲዉ አቤቱታዉን ለግብፆች ባቀረበዉ መሠረት የተፈረደበት 25 ዓመት ተሰርዞ በሁለት ዓመት ከእስር እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ተሰጥቶት ተመልሶ ወደኢትዮጵያ ከመሄድ ይልቅ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ይመጣል። ታዲያ እኔ መሐመድ ግብፅ መታሰሩን እንጂ ከዚያ ተፈቶ መጥቶ ቡስያ እስር ቤት አገኘዋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበርና በጣም ገረመኝ:: ዓይኔንም ማመን አቃተኝ :መሐመድ ! አልኩት ግብፅ ነበር እኮ ታሰርክ ተብሎ የሰማሁት እንዴት መጣህ ከዚህስ እንዴት ታሰርክ አልኩት ።









አዎ ግብፅም ታስሬ ነበር አለ :: መሐመድ እስከ ዓይኑ ያጠለቀዉን ላብ በእጁ እየጠረገ ንግግሩን በመቀጠል ፣ በዚህ ዓለም ለመኖር ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ አንደኛዉ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

135

መታደል: ሁለተኛዉ ደግሞ መታገል ነዉ፣ ታዲያ እኔ ከጧት ጀምሮ ያገኘሁት መታደልን ሳይሆን መታገልን ነዉ፣ ይዤ የተፈጠርኩት:: ሐረር ተወልጄ አዲስ አበባ በስቃይ አደኩ: ለመማር እድል ስላልነበረኝ መጀመሪያ በሊስትሮነት በኋላም በፀጉር አስተካካይነት ተሰማራሁ:: በዚህ ሥራዬ ተደስቼ ቆንጆ የመኖሪያ ቤቶች ሰርቼ እያከራየሁ ሚስት አግብቼ ጥሩ ኑሮ መኖር ስጀምር እንደምታዉቀዉ ደርግ መጣና ጡሩንባ ነፍቶ የደከምኩበትን ሀብት አኔንም ከመሳፍንቶቹ ጋር እኩል ወረሰን። በዚህ በመበሳጨት አገሬን ለቅቄ ወደስደት መጣሁ፣ ይሄዉና ዛሬ አገሬን ለቅቄ ሚስትና ልጆቼን ትቼ በየ አገሩ እስር ቤቶች እሰቃያለሁ። የስደትም ኑሮ ቀላል አለመሆኑን ላንተ መንገር አያስፈልግም።ታዲያ ከዚህ ነሮ ለመዉጣት ያለኝ እድል ጥቁር ገበያ መሥራት ብቻ ነዉ ብዬ አመንኩ፣ ምክንያቱም በግዜ እድል አግኝቼ ተምሬ ልሠራበት የምችልበት ሙያ ስለሌለኝ ነዉ። በዚህ ላይ ሰዉ ዓይኑ እያዬ በርሀብ አይሞትምና ለመኖር ስል የሆነዉን ሁሉ እሞክራለሁ::ነገር ግን እንዳልኩህ የታደልኩ አይደለሁም የመያዝ እንጂ የማምለጥ እድል የለኝም።







ባለፈዉ ግብፅ ሁለት ዓመታት በአረብ እስር ቤት ተሰቃይቼ ከዚህ መጣሁ ከመጣሁ ደግሞ መኖር አለብኝ ለመኖር ደግሞ መብላት ግድ ነዉ ለመብላት ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል፣ ገንዘብ ከሰማይ አይወርድም ሠርተህ እንዳትል ማን ቀጥሮህ ትሰራለህ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

136

ይህ በመሆኑ አጭር ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ፈለኩ እሱም ሰዎች ሲያደርጉ አይቼ ከኬንያ በኃሰት የተሰራ ገንዘብ በቀላል ዋጋ ገዝቼ ባላገሮች ናቸዉና በቀላሉ ሊታለሉ ይችላሉ በማለት ወደ ጠረፍ በመምጣት ገንዘቡን ወደ ዩጋንዳ ገንዘብ ስለዉጥ በኬንያ ደህንነት ሰዎች እጅ ከፍንጅ ተያዝኩና ይሄዉና ከዚህ ቦታ ታስሬ ቢያንስ የአምስት ዓመት ፍርዴን እጠብቃለሁ። እንግዲህ ለኔ እስር ቤት ሆቴሌ ሆኗል። ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም፣ አለና አንገቱን ወደታች አቀረቀሮ ባፍንጫዉ ተንኳሎ የሚወርደዉ ላቡን እየጠረገ ፀጥ አለ።ትንሽ ጊዜ ላቡን ካንጠፍጠፈ በኋላ አንተስ ከዚህ እንዴት መጣህ? በማለት ጠየቀኝ፣ እኔማ ናይሮቢ ለሥራ ልምምድ ሂጄ አንድ ካምፓኒ አግኝቼ ስሰራ ከቆየሁ በኋላ የዩጋንዳ ታንዛንያ ጦርነት ስላበቃ የትምህርት መረጃዎቼን ለማሞጣት ባለፈዉ ሁለት ሳምንታት ወደ ካምፓላ ሂጄ መረጃዎቼን ይዤ ስመለስና የይለፍ ስጠይቅ ጉቦ ካልሰጠኸኝ ብሎ ከፖሊሱ ጋር ተጣላንና ይሄዉ ወደዚህ መኪና ጠርቶ ላከኝ፣ አልኩት:: ለምን ትንሽ አልሰጠኸዉም ! ኬንያ እኮ ያለገንዘብ መንቀሳቀስ አይቻልም አለ :: አይ እኔማ አብረዉኝ የነበሩ ሦስት ፈረንጆች ሳይከፍሉ ስላለፉ እነሱን በነፃ አሳልፎ እኔን መጠየቁ አናዶኝ እንጂ እንደዚህ ሲኦል የምገባ መሆኔን ባዉቅማ ኑሮ አይደለም መቶ ሽልንግ አንድ ሽ ከፍየም ቢሆን ባለፍኩ ነበር አልኩት::







መሐመድ ከት ብሎ ሳቀና አየህ አነዚያ በነፃ አለፉ ያልካቸዉ ፈረንጆችም እኮ ከፍለዋል፣ የሚያደርጉት ከፓስፖርታቸዉ መኃል የተወሰነ ሽልንግ ያስቀምጣሉ ፖሊሱ ስለሚያዉቅ ፓስፖርቱን እየገለጠ የሚያይ መስሎ ይዘቀዝቀዋል ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

137

ያን ጊዜ ከዉስጥ ያለዉ ገንዘብ ከፖሊሱ ጭን ላይ ይወድቃል ያች ገንዘብ ምንም ትሁን ምን ፖሊሱ ማህተም አድርጎ ሰዉየዉን ከዚያ እንዲወጣ ማድረግ ነዉ:: ሌላዉ ማወቅ ያለብህ ኬንያ እስካለህ ድረስ የኩኩዩ ፖሊስና ዉሻ አንድ መሆናቸዉን እወቅ: ልዩነታቸዉ ለዉሻ ሥጋ ለኩኩዩ ብር ካሳየህ የፈለከዉን ማድረገ ትችላለህ። እንደዚህ ከመሐመድ ጋር ስናወራ ጊዜዉ አሁን በግምት ከምሽቱ አምስት ስዓት ሆኗል::ከመንገድ በሆነ ባልሆነዉና ለፖሊስ ጉቦ ያልሰጠ ሰዉ እየተጋፈፈ የሚመጣዉ እስረኛ ያችን ክፍል መቀመጥ ቀርቶ ቆሚያ ቦታ እንድናጣ አደረገን:: አሁን ሁሉም መቆም ግድ ሆነ ሰዉ ከመብዛቱ የተነሳ መቀመጫ ጠፋ። ከዚያ ላይ በየሰዓቱ ጠጥቶ የሰከረዉን ሁሉ እየያዙ አምጥተዉ ይጨምሩታል:ሲያስገቡ ደግሞ በያዙት አለንጋ ጭንቅላት ጭንቅት ጭንቅላቱን ይወግሩታል :: ዘብ የቆመዉ ፖሊስ የዉስጡን መጨናነቅና ማቃሰትሲሰማ በሩን ይከፍትና በያዘዉ አለንጋ ያገኘዉን ወጋግሮ መልሶ በሩን ይዘጋዋል :: ለመደብደብ በሩ ሲከፈት ከዉጭ የሚገባዉ ዓየር የህይወታችን መቀጠል ተስፋ ይሰጠናል።ከሚያስገቧቸዉ ሰካራሞች የጠጡት ወደላይ ሲተናነቃቸዉ ወደማርያ ሄዶ ይለቀዋል፣ ይሄም ካለዉ አስቀያሚ ጠረን ጋር ሌላ አስቀያሚ ሽታ ይጨምርበታል።









እኔና መሐመድ ግድግዳ ተደግፈን ቆመናል :ከፊት ለፊታችን የቆመ ረዥም ሰካራም የጠጣዉ ከበላዉ ገንፎ ጋር ከደረቱ እየፈላ እንደ ጉርና ይገፋ ጀመር:: እንደሚለቅብን ብናዉቅም መሸሻ አላገኘንም የፈራነዉ አልቀረምና ከላያችን ላይ ለቀቀብን : ሽታዉ ለጠላትአይስጠዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

138

የተለመደ ስለሆነ ማንም አልተደነቀም:: እኛም በጃችን ጠራርገን ግማቱን እያሽተትን ከቆምንበት ሆነን ያለፍርድ የተሰጠንን ቅጣት እየተቀበልን ሌሊቱ ነግቶ በሩ እስኪከፈት በጉጉት እየጠበቅን ቆመን አደርን::ሰዉ በመብዛቱ ምክንያት ሙቀቱ እያየለ ጠረኑ እየከፋ ሲሄድ መተንፈስ አልቻልኩም:: ቢጨንቀኝ በመጮህ በሩን አንኳኳሁ:: ፖሊሱ ከፈተና ማነዉ ሲል እኔ ነኝ ልሞት ስለሆነ ትንሽ ልተንፍስ ገንዘብ እሰጥሃለሁ አልኩት ና ዉጣ! አለኝ በሩን ከፈተና ስወጣ ገና ሳይጠይቀኝ;; በያዘዉ አለንጋ አንዴ ቢዠልጠኝ ነብስና ስጋዬ የተለያየች መሰለኝ : ሁለተኛ ሊደግመኝ ሲል ገንዘብ ልሰጥህ ነዉ ለምን ትመታኛለህ አልኩት:፣ የገንዘብ ነገር ሲሰማ የሰነዘረዉን አለንጋ መለሰዉ፣ የገንዘብ ነገር ካሰማኸዉ ኩኩዬ እናቱን ይሸጣል ብሎኝ ነበር መሐመደ::





እንዳለዉም ገንዘብ እንዳስቀመጥኩ ስለሚያዉቅ አወጣና ቦርሳዬን ሰጠኝ፣ 10 ሽልንግ አዉጥቼ ሰጠሁት : አምሥት ደቂቃ አለኝ እሽ አልኩና በሩ ጥግ ቆምኩኝ :የዉጩን ዓየር ሳብኩት ከዉስጥ ያለዉን የገማ ዓየር አወጣሁት ባህር ዉስጥ እንደሚገባ ሰዉ ዓየር ቶሎ ቶሎ ሳብኩና አምስት ደቂቃዉ ሲያልቅ ሁለት ደቂቃ የቆየሁ አልመሰለኝም ነበር ግን መልሶ ወርዉሮ ወደክፍሉ አስገባኝ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

139

ተመልሼ ስገባ እንዲሁ ያዉ ሽታና መታፈን አልቻልኩትም አሁንም አንኳኳለሁ ፖሊሱ ይከፍታል አምስት ደቂቃ አሥር ሽልግ እሰጣለሁ አሁን ታሳሪዎቹም ወደዱኝ ምክንያቱም እኔ ስወጣና ስገባ የሚገባዉ ዓየር ለነሱም ሕይወት መመለሻ ሆነላቸዉ::100 ሽልንግ ላለመስጠት ተጣልቼ እስር ቤት በመግባቴ የበለጠ ያለኝን አራግፈዉ ሊለቁኝ እንደሆነ ገባኝ በዚህ ሌሊት መቶ ሽልንግ ካለኝ ገንዘብ ከፍያለሁ::

ሰኞ ደርሶ ፍርድ ቤት እስክቀርብ ድረስ ስንት ልከፍል ይሆን ደግሞስ ፍርድ ቤቱ ገንዘብ ከፍለህ ዉጣ ቢለኝና ያ ገንዘብ ከለለኝ ከዚሁ እስር ቤት ይመልሱኛል ።በማለት ከጭንቀት ላይ ጭንቀት ጨምረብኝ።

በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሌሊቱን አንግተን ከጧቱ ሦስት ስዓት በር ተከፈተና ለመናፈስ ተብሎ እንደወጣን ከታሳሪዎቹ መካከል ጥቂቶቹ ክፍሉን እንዲጠርጉና የመፀዳጃ ባልዲ (ማርያን) አዉጥተዉ ወደ ዉጭ ሸንት ቤት እንዲገለብጡና በዉኃ አጥበዉ መልሰዉ እንዲያስቀምጡ ታዘዙ::







ቁርስም ምሳም በቀን አንድ ጊዜ ስለሚበላ ምሳ ተብሎ የበቆሎ ገንፎና ከነቀዘ ቦለቄ የተሰራ ወጥ መሆኑ ነዉ በስሃን ለያንዳንዳችን ቀረበ:: ሆን ብለዉ ያነቀዙት ቦለቄ ዉስጥ የተፈለፈሉት ትንኝ መሳይ በራሪዎች በፈላው ዉኃ አብረዉ ስለተቀቀሉ እሬሳቸዉ ተንሳፎ ኡጋሊዉን ሸፍነዉታል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

140

ሽታዉ ከሩቅ ይሰነፍጣል:: መሐመድ ሲነግረኝ ለካ ኬንያኖች ቦለቄዉን ሆን ብለዉ ነዉ እንዲነቅዝ የሚያደርጉት አለኝ :: ለምን አልኩት ከቦለቄ ትንኞቹን ለምግብነት ስለሚፈልጉት አለኝ:: በነገራችን ላይ ኮሌጅ እያለሁም ኡጋሊ ምሳ በቀረበ ቁጥር የማልበላበት ጊዜ ይበልጥ ነበር ምክንያቱም እንደዚህ አይብዛ እንጂ የነቀዝ ትንኞች እየተንሳፈፋ ካልታዩ አይጥማቸዉም።

የቡሲያ እስር ቤት

የበቆሎ ገንፎ ከላዩ

ላይ ከፈሰሰዉ

የትንኞች መንጋ ጋር ሳየዉ ለምርግ የተዘጋጀ ጭቃ አስመስሎታል።

ከምግብነት በጣም የተለዬ ነበር:: ገና

ወዳፌ ሳስጠጋዉ ሊያስታዉከኝ ተናነቀኝና ተዉኩት ::

መሐመድ ከት ብሎ ሳቀና ይሄን ካልበላህ እንዴት በህይወት ትቆያለህ!

ወንድሜ እንደምንም ብለህ ባይሆን ኡጋሊዉን

ብቻ እየመረጥክ ብላ አለኝ አይ ግዴለም ለዛሬ ይቅርብኝ





ባይሆን ነገ ሲጠናብኝ እበላለሁ አልኩት።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

141

==እንጀራ ሸተተኝ == እስኪ ልናገረው ከእውነት ካንጀቴ እናንተም አትሳቁ ላውራ ከእውነቴ እንጀራ ሸተተኝ በሰባት ዓመቴ እዛው ትቸው ነበር ካገሬ ስወጣ በየት አቆራርጦ ዛሬ ሽታው መጣ ነጭ! ጤፍ እንጀራ ከምጣድ የወጣ በየት አቆራርጦ ዛሬ ሽታው መጣ ግሩም የዶሮ ወጥ ብልቱ የወጣ አባት ማዕዱን ቆርሶ እናት ስታወጣ ከእጇ ላይ ነጠቃት እህል ክንፍ አወጣ ስንቱን ጎራ ዘሎ ሽታው ከኔ መጣ አጅሬ ትዝታ ! ምስጋና ይድረስህ ከተስደድኩበት እኔን ማስታወስህ ደን በርሃውን ውቅያኖስ አቋርጠህ አመጣህ እንጀራ ከዕድ ቀምተህ ተመስገን አምላኬ ድካሜ ቀለለኝ ሳልበላም ጠገብኩኝ በተሰደድኩበት እንጀራ ቢሽተኝ ========. ============== *ይህ ግጥም









































በኬንያ እስር ቤት እያለሁ በገጠመኝ የምግብ አለመስማማት ምክንያት የሀገሬን ባህላዊ ምግብ በትዝታ ሳስታዉስ የተፃፈ ነበር:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

142

ከምግቡ ይልቅ ደስ ያለኝ የማይከፈልበት ንፁሁ ዓየር ነበር :: ለካ ዓየር በነፃ አምላክ የሰጠን ትልቅ ሀብት ነዉ፣ ሁሉም ነገር እኮ አስፈላጊነቱ የሚታወቀዉ ሲጠፋ ነዉ። የመቀመጫ ቦታ አገኘንና እኔና መሐመድ ጥግ ይዘን ተቀመጥንና ያቋረጥነዉን ወሬ ጀመርን:: መሐመድ ቀደም ብሎ ከዚህ እስር ቤት የቆየ ስለነበር ከፖሊሶቹ ጋር ተለማምዷል : በክፍሉ ዉስጥም አለቃ አድርገዉ ሹመዉታል ስለዚህም ከነባር እስረኞች የራሱ ፍርድ ቤትና ጠበቆችም ሰይሟል በመሆኑም አንድ አዲስ የገባ እስረኛ ያጎዛ የማይከፍል ከሆነ ጉዳዩ ዳኞች ይሰየሙና ጠበቆች በግራና በቀኝ ሆነዉ ይከራከራሉ:: ዳኞች ግራ ቀኙን ያዳምጡና ፍርድ ይሰጣሉ የፍርድ ቅጣቱ ደግም ጧት ማርያን የሚያፀዳና ክፍሉን የሚያጥብ ይሆናል የጠና ከሆነ ደግሞ የመጨረሻ ቅጣት ይሰጠዋል

እሱም

ማርያን አቅፎ መተኛት ነዉ።ምሳ እንደተበላ እቃዎችንም አጣጥበዉ የሚመልሱ ሰዎች ሥራቸዉን ከጨረሱ በኋላ ተመልሰን ወደዚሁ ማጎሪያ ክፍል ገባን:: መሐመድ የት የት እንደምንቀመጥ ከመደበ በኋላ ተጠባብቀን የተወሰን ለመቀመጥ ቻልን ብዙ ሳይቆይ አንድ





አዲስ ታሳሪ መጣ ገና ከመግባቱ መሐመድ ደሙ ፈላ:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

143

ሰዉነቱ ተንቀጠቀጠ:: ምንሆንክ አልኩት ይሄን ሰዉዬ አታዉቀዉም!!

አለኝ አላስታወስኩትም አንተ የት ነዉ

የምታዉቀዉ ? አልኩት :: ይሄ እኮ የኢዲ አሚን የደህንነት ኮረኔል የነበረ ነዉ ስንቱን ሲያርድ ነዉ የነበረዉ እኔንም አንድ ቀን በመንገድ እየሄድኩ እያለሁ በመኪና ሲያልፍ አይቶኝ ወስዶ ያለምንም ምክንያት አሰቃይቶ ነዉ የለቀቀኝ አለ :: ኦህ ታዲያ ምን አሰብክ አሁን? አሁንማ አለና በማጨብጨብ እስረኞቹ እንዲሰሙት አደረገ ክፍሉ ፀጥ አለ፣ ጓዶች! አንድ ነገር ከዚህ ዉስጥ ተከስቷል በመሆኑም

ፍርድ ቤት

በቶሎ ዳኞች

ችሎት ሰይሙ

ጠበቆችም ቦታችሁን ያዙ አለና ትእዛዝ ሰጠ:: ከሳሽ እኔ መሐመድ ተከሳሽ ኮረኔል ኦኬሎ

ወንጀሉ

ስልጣኑን በመጠቀም ሰዉ ከመንገድ አፍኖ በማሰቃየት አለና በስልጣን ላይ እያለ ያደረሰበትን ግፍ ዘረዘረ:: ከዚያም በላይ አንድ ስምረት ብርሃኑ

የሚባል ጓደኛችን እንደዚሁ

ከመንገድ አፍነዉ ወስደዉ አሰቃይተዉ እንዲገደል ያደረገዉ ይሄዉ ሰዉ ነዉ ብለን እንጠረጥረዉ ነበር አሁን ኢዲ አሚን ራሱ ፈርጥጧል: የሱ ነብሰ በላ ገዳዮችም በያገሩ ተሰደዋል :





አንዳንዶቹም እንደዚህ እየተለቀሙ ዘብጥያ እየወረዱ ነዉ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

144

ችሎት ተሰየመ ጠበቆች በግራና ቀኝ ቆሙ: ተከሳሹ ማህል ላይ ተገትሮ ቆመ: መሐመድ በደሉን ካሰማ በኋላ ሰዉየዉ የእምነት ክህደት ቃሉን ስጥ ተባለ:: ኮረኔል ኦኬሎ አዎ አድርጊያለሁ ነገር ግን በወቅቱ የአገሪቱን ዓየር ማረፊያ እስራኤል ኮማንዶዎች

መጥተዉ

በፍልስጤም ሽብርተኞች ተጠልፎ መጥቶ ከቆመው የፈረንሳይ የመንገድ ማመላለሻ አይሮፕላን (Air Franc) ውስጥ የዩጋንዳን

የነበሩትን ታጋቾች ነፃ ለማዉጣት

በርካታ

ወታደሮች ገድለዉ ታጋቾችን ይዘዉ ከተመለሱ

በኋላ ፕሬዜዳንት አሚን ለዚህ አፀፋ ማንኛዉንም የምታገኙትን ተጠርጣሪ አስወግዱ ብለው ትእዛዝ ስለሰጡ ያገኘነዉን ሁሉ እየያዝን መመርመር ጀመርን:: ያን ጊዜ መሐመድ እንደተያዘ እኔ ባልኖር ኑሮ የያዝኩህ ያልቅልህ ነበር : ስምረት ብርሀኑ ያላችሁትም እንደዚሁ በመልክ ቀይም ስለነበር በሰላይነት ለእስራኤሎች የሚሰራ ሊሆን ይችላል በሚል ነዉ ሊገደል የቻለዉ : ስለዚህ እንዳዉም አንተ እኔ ነብስህን በማዳኔ ልታመሰግነኝ ይገባ





ነበር አለና የስምረትን መገደልም እግረመንገዱን አረዳን።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

145

ስምረት ብርሃኑ : ስምረት እንዳዉሮፓ አቆጣጠር በ1955 ዓ ም በቤጌምድርና ሰሜን ክፍለሀገር ተወለደ : ከዚያም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጊዜዉ ቀ •ኃ •ሥ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተብሎ በሚጠራዉ ካጠናቀቀ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የፊሎዞፊ ትምህርቱን በመከታተል የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ደርግ አድገት በህብረት ብሎ ተማሪዎችን ወደየ ገጠሩ ሲልክ ስምረትም ወደ ቤጌምድርና ስሜን ክፍለ ሀገር ተልኮ እየሠራ በነበረበት ጊዜ በነበረዉ የፖለቲካ አለመግባባት በ1969 ዓ ም ወደሱዳን ካርቱም ለመሰደድ ተገደደ :: ካርቱም ትንሽ እንደቆዬ የኒሜሪን መንግሥት ለመገልበጥ በተደረገ ያልተሳካ ሙከራ ኢትዮጵያዉያኖች አሉበት ተብሎ ስለተጠረጠሩ የኒሜሪ የፀጥታ ሰዎች ስደተኞችን ማሳደድና ማሰር ሲጀምሩ::







ስምረት ከካርቱም አምልጦ ካምፓላ ይገባል ፣ ከዚያም የዩጋንዳ የፀጥታ ሰዎች ስምረትን ይዘዉ በማሰር ለ3 ወራት ከቆየ በኋላ ተፈቶ ካምባላ ማኬሬሪ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን ለመቀጠል በመጠባበቅ ላይ እያለ የእስራኤል ኮማንዶዎች በፍሊስጠም ነፃ አዉጭዎች ኢንተቤ አይሮፕላን ማረፊያ ታግተዉ የነበሩትን ባልታሰበ ሁኔታ መጥተዉ ነፃ አድርገዉ ይዘዉ በመሄዳቸው ኢዲ አሚን ያገኘዉን ወዘልዉጥ ሁሉ ሰላይ በማለት እያፈነ መግደል ጀመረ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

146

በዚህ ወቅት ነዉ ስምረት አገር ሰላም ብሎ በካምፓላ መንገድ ላይ ሲሄድ በአሚን አፋኝ ወታደሮች ተወስዶ የተገደለዉ። የስምረት ብርሃኑ የህይወት እሩጫም ከዚህ አቆመ:: እኔም የጏደኛዬን መገደል ከዚሁ የቡስያ ኬንያ እስር ቤት እንዳለሁ ተረዳሁ:: ስደተኛው ጏዴ ነብስህን ይማርው:

የእስር ቤቱ--ፍርድ፣ ፍርድ ቤቱ የከሳሽ ተከሳሽን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ዳኞች ከሳሽ ተከሳሽ ቆመዉ ፍርዳቸዉን እንዲሰሙ

አድርገው

የሁለቱም ጠበቆች የመጨረሻ ንግግር እዲያደርጉ አድል ተሰጣቸዉና የየራሳቸዉን ማጠናከሪያ ብለው ያሰቡትን አሰሙ:: ከዚም ዳኞች የደረሱበትን የፍርድ ዉሳኔ ሰጡ:: ፍርድ: ተከሳሽ ከሳሽን ያለምንም ጥፋት

ሥልጣኑን በመጠቀም

ያደረሰበት እንግልት ከባድ ቅጣት የሚያሰጠዉ ሆኖ ቢገኝም ባንጻሩ በጊዜዉ ባገሪቱ ላይ ተፈጥሮ የነበረዉን ብሔራዊ









ዉርደት::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

147

በሰዉና በንብረት ላይ የደረሰዉን ጥፋት እና በነበረዉ ትርምስ ምክንያት ከሳሹ

ሊደርስበት የነበረዉን አደጋ

በማስቀረት ሕይወቱን ስላተረፈ የወንጀሉን ከባድነት አቅልሎ ለአንድ ሌሊት ማርያን አቅፎ እንዲያድር የወሰነ በመሆኑ የሕግ አስከባሪዎች ዛሬ ሌሊት ቅጣቱን ተፈጻሚ እንድታደርጉ በዛሬዉ ቀን በዋለው ችሎት ወስነናል:: አሉና ችሎቱን ሲዘጉ ሁሉም ለትክክለኛ ፍርዳቸዉ በጭብጨባ አደነቁ።ኮረኔል ኦኬሎም እንደፈረደበት ሌሊቱን በሙሉ ያን ሁሉም የሚፀዳዳበትን ሽታ ታቅፎ አደረ:: በዚህ ዓይነት የቅዳሜን ቀንና ሌሊት አሳልፈን እሁድንም እንደተለመደዉ ወጥተን ያነኑ ኡጋሊ ከነቀዘዉ ቦለቄ ወጥ ጋር ቀረበልን ህይወቴን ለማቆየት ይረዳኝ ዘንድ ኡጋሊዉን ብቻ እየመረጥኩ ሁለት ጉራሽ ጎርሸ መለስኩት: ከመሐመድ ጋር አሁንም ዳር ይዘን ተቀመጥንና ነገ ሰኞ ፍርድ ቤት ስቀርብ ምን ማለት እንዳለብኝ ምክር ጠየኩት::

እሱም ያንተ ቀላል ነገር ነዉ ክሱ የሚሆነዉ የኬንያን ደንበር ያለፈቃድ ጥሰህ ገብተሃል ነዉ የሚሆነው:

ስለዚህ አንተ







በምንም አይነት ጥፋተኛ አደለሁም ማለት የለብህም እለኝ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

148

እንዴት እልልም ወደ ቢሮው ራሴ ሂጀ ነው እኮ የጠየኩት መስጠት ካልፈለገ እኮ አልስጥም ብሎ መመለስ ሲገባው እንዴት የኬንያን ደንበር ያለ ቪዛ ጥሰህ ገብተሃል ይከሰኛል

ብሎ

? አልኩት:: ወንድሜ አንተ የምትለው በሕግ

ለሚገዛ አገር ነው እዚህ ኬንያ ግን ሕግ አይሰራም:: አሁን ልክ አንተ እንደምትለው

ለዳኞች ብታቀርብ ከሳሽ

የሚያቀርባቸው ምስክሮች እስኪመጡ ድረስ ለወራት ከዚሁ ትቆያለህ ስለዚህ ይህ ከሚሆን እንዳልኩህ

ጥፋተኛ

ነኝ

ብለህ ቅጣትክን ብትቀበል የቀለለ ይሆንልሃል:: ስለዚህ ጥፋተኛ ነህ አዎ ጥፋተኛ ነኝ ፍርዴን እቀበላለሁ : ማለት አለብህ አለና መከረኝ ፣ እንዳይደርስ የለምና ሰኞ በሦስት ስዓት ወደ ፍርድ ቤት በፖሊስ ታጅቤ ቀረብኩ ልክ መሐመድ እንዳለዉ የኬንያን ደንበር ያለ ፈቃድ ጥሰህ ገብተሃል አሉ የማህል ዳኛው :: አዎ ገብቻለሁለዚህም ጥፋተኛ ነኝና ፍርድ ቤቱ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ አልኩ:ዳኛው መነፀራቸውን







አስተካከለው እሽ አሁን ፍርድ እናሰማለን አሉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

149

የቡስያ -ኬንያ ፍ/ቤት -ፍርድ: ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ክስ ከሰማ በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጠ:

ፍርድ: ተከሳሽ አቶ ሞላ ይግዛው : የኬንያን ደንበር ያለ ይለፍ ፈቃድ ጥሰህ

በመግባትህ የእምነት

ጥፋትክን

ስላመንክ

ክህደት ቃል ተጠይቀህ

አንድ ሽህ የኬንያ

እንድትከፍል የማትከፍል ከሆነ በአንድ

ሽልንግ

ወር እስራት

እንድትቀጣ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ቀን በዋለው ችሎት ወስኗል አሉኝ:: እኔም እጅ ነስቼ 100 ሽልንግ አልከፍልም ብዬ ከፖሊሱ ጋር የተጣላሁ ሰው አሁን 1000 ሽልንግ እንዲሁም ንፁህ ዓየር ለመተንፈስ ጉቦ 120 ጠቅላላ 1120 ሽልንግ እና ሦስት ቀን የስቃይ እስር

ቤት

ቅጣቴን ከፍዪ

የነፃ ወረቀቴን ይዤ

ከእስር ቤት ስወጣ የሰዉነቴ ሽታ (መጥፎ ጠረን) ከሰው ጋር









የሚያስቀርበኝ አልነበረም::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

150

በጠቅላላዉ ጥንብ ጥንብ ነበር የምሸተዉ በዚህም ምክንያት የኮንትራት ታክሲ ይዤ

ካምፓላ ተመልሼ ወደ

ጓደኛዬ መኖሪያ ቤት ሄድኩኝ :: ካምፓላ እንደደረስኩ ጓደኛዬ አልነበረም በቀጥታ ሳሙና ገዛሁና የገማዉን ሰዉነቴን ታጥቤ ልብስ እየቀየርኩ እያለሁ የጓደኛዬ ጓደኛ መጣና መርዶ ነገረኝ እሱም ተኮላ መንገድ ላይ በዩጋንዳ ወታደሮች በጥይት እንደተገደለ አረዳኝ:: የበለጠ ያላሰብኩት ዱብእዳ

ወረደብኝ ለምን ተብሎ

የማይጠየቅበት አገር መሆኑን አዉቃለሁ በእንደዚህ ዓይነት አገር በስደት ሲኖር በዬ ደቂቃው ህይወትን አስዘህ እንደሆነ አዉቃለሁ ያልታሰበ ሲመጣ ግን ለመቀበል ይቸግራል በጠቅላላዉ የሕይወት ትርጉሙ ጠፋብኝ አገሩም አሰጠላኝ :: ከተኮላ ጋር የተዋወቅነው ከዚሁ ካምፓላ የUNHCR ነበር

ቢሮ

የናይሮቢ ኑሮ ከፖሊስ ጋር ሁል ጊዜ መጨቃጨቁ

ስለሰለቸው ካምፓላ ይሻል ይሆናል በሚል ተስፋ ነበር ተኮላ ወደ ካምፓላ የመጣው :: ካምፓላ እንደመጣም የራሱን ንግድ እየነገደ ራሱን ችሎ ይተዳደር ነበር በዚህ ምክንያት ከዩኤንUNHCR ሂዶ የእርዳታ









ገንዘብ ጠይቆ እያቅም ልመና ማለት ነው ይላል::

እኔና

በዚህ ምክንያት ሰዎች

የስደት ጉዞዬ

151

ጎንደሬው ይሉታል አወ በጣም

ሲበዛ ኩሩ ነው አንዴት ይለመናል ይለን ነበር :: ታዲያ እኔንም ራስክን መቻል አለብህ በሚል እቃ ከጀምላ ሻጮች አውጥቶ ይስጠኝና እቃውን አትርፌ ሽጪ ትርፌን እስቀርቼ ዋናውን እየመለስኩ እንድሰራ አስተማረኝ: በዚህ መልክ እየቆየን በጣም እየተቀራረብን ሄድን:: በትምህርት ትርፍ ግዜዬ ንግድ እየስራሁ

ራሴን ችዬ

እንድኖር አድርጎኝ ነበር:: አሁን ተኮላ የለም ላይመለስ አሽልቧል : ስለዚ ካምፓላ

መቆየቱ አስጠላኝ

ወዲያዉኑ

የኮንትራት ታክሲ ይዤ በሌላ መንገድ ወደ ናይሮቢ ጉዞ ጀመርኩ :: የታክሲ ሾፌሩ ሶማሌ ነበር ከተነጋገርነዉ ዉጭ መንገደኞችን ጫነና የያዘዉን 404 ፔጆ ፒክ አፕ

ፔጆት

መኪና ሞላዉ ምርጫ ስለሌለኝ ዝም ብየ ተቀመጥኩ እኔ ከሾፌሩ ጎን ስለተቀመጥኩ የሚያደርገዉን ሁሉ አየዋለሁ : ጫት በጉንጩ ሞልቶ በላይ በላዮ ይጨምርበታል መኪናዉን ያፈጥነዋል በጠቅላላዉ ሁኔታዉ አላምርህ አለኝ ግን ምን ላድርግ ዝም ብይ አየተሳቀቅኩ መንገዱን ቀጠልን እንደዛ ባለ ፍጥነት ላይ

ሲከንፍ አንድ መኪና እንደሱዉ እየከነፈ







ከፊት ለፊታችን መጣ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

152

መንገዱ ጠባብ ነበር መኪናዉን ለማሳለፍ ዳር ለመያዝ ሞከረ ግን ፍጥነት ስለነበረዉ ጎማዉ መንገዱን ስቶ ገደል ተንከባሎ ከአንድ ዛፍ ጋር ተጋጭቶ ቆመ። መኪናዉ ሲንከባለል መስኮቶቹ ተሰባብረዉ አቧራው

መኪና ዉስጥ

ገብቶ ስለነበር ሁላችንም በአቧራ ተሸፍነን ማየት አንችልም ነበር :: በድንገት የሚያልፍ

የጭነት መኪና መጣና ሰዎቹ

ወርደዉ ከተንከባለለዉ መኪና ዉስጥ እየጎተቱ አንድ ባንድ አወጡን:: የሞተ ባይኖርም አብዛኞቹ በጸና ቆስለዉ ነበር:: እኔን ጎትተዉ አወጡኝና እንድቆም አደረጉኝ ራሴን መመርመር ጀመርኩ ምኔ እንደ ጎደለ ለማወቅ እጄና እግሮቸን እያንቀሳቀስኩ አየሁ ደህና ነኝ : ጭንቅላቴን ዳሰስኩ በአቧራ ከመሸፈኔ በቀር ደህና ነኝ ፣ ተመስገን አምላኬ ከዚህ ሁሉ : መከራ የምታወጣኝ የናቴ ፀሎት ነዉ ብየ አሰብኩ።

አዎ እውነትም ብዙ

መከራ ሲገጥመኝ

የሚያወጣኝ የናቴ ፀሎት ነበር :: እናቴ አፈሩ ይቅለላትና አኔ ከተለየኋት ጊዜ ጀምሮ ከአልጋ ላይ አልተኛም ብላ ከመሬት ነበር የምትተኛው: በጫማ እንደማትሄድና ሁል ግዜ ፀሎትና ለቅሶ ነበር አለችኝ በኋላ





ሂጄ ስጠይቃት እንዳጫወተችኝ።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

153

ከትንሽ ቆይታ በኋላ በዚሁ የጭነት መኪና ተሳፍሬ ናይሮቢ ገባሁ ።እንደደረስኩም ጓደኞቼ ለምን ባልኩት ቀን ሥራዮን ትቼ እንዳልመጣሁ ሲጠይቁኝ የሆነዉን ሁሉ አጫወትኳቸዉ በጣም አዘኑ:: በየቦታው ያሉ ጓደኞቼ ተጠራርተው

ናይሮቢ ኢስሊ ሰፈር

በጋራ እንኖርበት ከነበረው ቤታችን ተሰባሰበው የኃዘንም የደስታም አድርገነው አመሽን:

ምሽቱን

በተለይ የተኮላና

የስምረት ብርኃኑ መገደል እጅግ አሳዘናቸው::

ሁለቱም

ናይሮቢ ይመላለሱ ስለነበር ሁሉም በአካል ያውቋቸው ነበር የተወሰኑትም በጣም የሚቀራረቡ ጏደኛሞች ነበሩ::

አንደገና ዘወር ብለው የነሱን መሞት ረስተው እኔ በስላም በመመለሴ በጣም ደስ ስላላቸው ሀዘኑን ወደ ደስታ ለመቀዪር ሞከሩ:: ለዚህም እንዲረዳቸው ገዝተው ያመጡትን መጠጥ ሸሪና ቢራ በመጠጣት ለመርሳት ሞከርን::ይሁን እንጂ በዚህ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ህይወትን መዝነን በጠጣነው ተዳክመን ስለነበርብሁላችንም እንቅልፍ ድብን አርጎ ወሰደን :: በተቀመጥንበት እንቅልፍ ስላጠቃን ድምፃችን እየጠፋ







ክፍሏ በተኛ ሰው ኩርፊያ ተሞልታ አደረች::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

154

ይህ በዚህ እንዳለ እኔም ኬንያ የመቆዬቴ እድል እየጠበበ ሄደ::ከፊሊፕስ ካምፓኒ የነበረኝ የኮንትራት ጊዜ ከዚህ በፊት ለአንድ ዓመት አራዝመውልኝ ስለነበር ለሁለተኛ ጊዜ ለማራዘም የኬንያን መንግሥት ይሁንታ የሚጠይቅ ሆነ:: እሱ ደግሞ ባለው የሙስና ብልሹነት ምክንያት አስቸጋሪ አደረገው :: ስለዚህ የነበረኝ ምርጫ ኬንያን ጥሎ ወደ ሌላ አገር መሰደድ ብቻ ሆነ: ግን የት ልሂድ? ብዙ የአውሮፓ አገሮች ኢምባሲ ቢሮዎችን ባዳርስም በዪጋንዳ የስደተኛ ፓስፖርት (ሌሲፓሴ) የማይሞከር ሆነ::





እንዳጋጣሚ ከዚህ በፊት ጓደኛዬ ገሠሠ ጀርመን ያለ ቪዛ ገብቶ ነበርና ይሄ ያለ ቪዛ መግባት የሁለቱ አገሮች ስምምነት አሁንም ያልተቀየረ መሆኑን አጣርቶ እንዲልክልኝ በጠየኩት መሠረት ከጀርመን ኢሚግሬሽን አጣርቶ አሁንም በዪጋንዳ ፓስ (ሌሴ ፓሴ) ያለቪዛ መግባት አንደምችል አሳወቀኝ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

155

ምዕራፍ -8 ጉዞ ወደ አውሮፓ: ገሠሠ የነገረኝን ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀምም ቪዛ ሳልጠይቅ ቲኬት ገዝቼ (በኤሮ ፍሎት ዓይሮፕላን ) በርሬ ምዕራብ ጀርመን ፍራንክፈርት ዓየር ማረፊያ አረፍኩ:: ከዚያም ኮስተር ብዪ ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሄድኩና ዪጋንዳ የተስጠኝን ፓስፖርት (ሌሴፓሴ) ለኤሚግሬሽን ፖሊሱ ሰጠሁት:: ፖሊሱ ቀና ብሎ ፎቶውንና መልኬን ካዬ በኋላ ያለምንም ጥያቄ የስድስት ወር ቪዛ መቶ ሲሰጠኝ ማመን አልቻልኩም ነበር :: ወይ ኬንያ...ያ! አልኩ : ባቡር ወዳለበት ብቻዬን አያወራሁ ስሄድ ኬንያ ቢሆን ይሄን ጊዜ ስንት ወር ይፈርዱብኝ ነበር!! ብዙ ሰው አብሮኝ እንዳለ ሁሉ! ብቻዬን ድምፄን ከፍ አድርጌ እያወራሁ ደግነቱ ሁሉም ከጀርመንኛ በቀር ቋንቋዬን ስለማይሰሙ ብዙም ግድ የሰጠው አልነበረም ምናልባትም እብድ ነው ::









ብለውኝም ይሆናል እንጂ:: ጓደኛዬ ወደሚገኝበት ወደ ኮለን ከተማ ከሚወስደው ባቡር ውስጥ ገብቼ ተጓዝኩ:: ኮለን ከገሠሠ ቤት ደረስኩና አራት ዓመት የተለየሁትን ስደተኛው ጓዴን አግኝቼ ያለፈውንም የሚመጣውንም ስንጫወት ሌሊቱ ሳይታወቀን ነጋ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

156

ወይ ጊዜ ጊዜው እንዴት ይሮጣል !! እኔና ገሠሠ ኢትዮጵያ አገራችን ለቀን ወጥተን አንድ ዓመት እንቆያለን አልመሰለንም ነበር: ግን አሁን ይሄውና እንኳን ኢትዬጵያ ተመልሶ መግባት እኛም ከተለያዬን በኋላ ለመገናኘት ይሄውና አምስት ዓመት ሆነን:: ጀርመን ትንሽ ቀናቶች ከስነባበትኩ በኋላም ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከገሠሠ ጋር ተወያዬንና ሰዎችንም ጠያይቀን ባገኘነው መረጃ እኔ ጀርመን እንድቆይ ሊያደርገኝ የሚያስችለኝ ሁለት ነገሮች ብቻ ነበሩ::አንደኛው በፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቅ ሲሆን ሁለተኛው ነፃ ትምህርት ( ስኮላርሽፕ ) ጠይቆ መማር ነበሩ:: ይሁን እንጂ ለጊዜው ጥገኝነት መጠየቁ ብዙ የተጓተተ ጊዜ ወሳጅ ብቻ ሳይሆን ለኔ በዩጋንዳ ዶኩሜንት ጥገኝነት ጠይቆ ማግኘቱ የማይሞከር ነበር :: ምክንያቱም በአውሮፓውያን ህግ አንድ ስደተኛ መጀመሪያ ጥገኝነት ከጠየቀበት አገር የመኖሪያ ፈቃድ ካገኘ ለሁለተኛ በጀርመን አገር የማግኘት መብት የለውምና ነበር::









ስለዚህም ሊሆን የሚችለው እሱም ከሆነ ጥሩ (ኮሚኒስት የሆነ ) ጠበቃ ገዝቶ እየተከራከሩ ጊዜ ማጥፋት ይቻላል: ይሄም አሰልቺና ሞራል የሚያላሽቅ ሂደት ነበር::ሁለተኛው አማራጭ ነፃ ትምህርት (ስኮላር ሽፕ) ፈልጎ ትምህርት የመማር እድልን ተጠቅሞ እየተማሩ መቆዬት ሲሆን የዚህ ችግር ደግሞ ትምህርቱ እንዳለቀ ጀርመንን ለቅቄ እሄዳለሁ ብሎ መፈረምንም ያካትታልና ሌላ ተጨማሪ ችግር ይዞ የሚመጣ ሆነ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

157

ግን ቢሆንም ከአምስት ዓመት በኋላ የሚመጣውን ለመጋፈጥ በመቁረጥ መማርን መረጥኩና ኦቶ ቤኒኬ ከሚባል ጅርጅት (Otto Benecke foundation e•v) ነፃ ትምህርት ጠይቄ በተሰጠኝ መሰረት ለመማር ወሰንኩና መጀመሪያ ማርቡርግ ወደምትባል የዪኒቭርሲቲ ከተማ ሄጄ ለስድስት ወራት ጀርመንኛ ቋንቋ ካጠናሁ በኋላ ለመደበኛ ትምህርት ሀምበርግ ከተማ ተመድቤ ሄድኩ::

የስደት ጉዞዬ

158

ምዕራፍ-9 ሀምበርግ- ጀርመን:

ሀምበርግ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛዋ ትልቁ የጀርመን ከተማና በሰሜናዊ ፣ ምስራቅ እና በምእራብ አውሮፓ መካከል ከሚጓዙት መንታ መንገዶች መካከል ትገኛለች ፡፡ የሀምበርግ የህዝብ ብዛት ከ1,8 ሚሊዮን ነዋሪ ሲሆን የከተማ ዳር ዳር 3 ሚሊዮን ይሆናል፡፡

ሃምቡርግ፣

ከአውሮፓ ትልቁ

የኮንቴይነር ወደቦች ስትሆን

ዋናዋ

በርካታ ትላልቅ ከኤሌክትሮኒክስ እስከ ጦር

ጀቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ያሉባት ከተማ ነች :: በዚህም ምክንያት ከተማዋ ብዙ የተለያዩ ጎብኝዎች እና ተጓዝዎችን

በየአመቱ ከተማዋን ይጎበኛሉ - በዚህም

ምክንያት ለአውሮፓ ቱሪስቶች መናሀሪያ ሆና ትገኛለች::

ጀርመኖች ትልቁ የሚኩራሩበት ነገር ቢኖር የቴክኒክ









ችሎታቸውን ነው : :



እኔና

እኔና

ሲናገሩም

(ሳይንስ

የስደት ጉዞዬ

የጀርመን ዳቦ ነው ይላሉ)

159 በጠቅላላው

ጀርመኖች በጣም ሠራተኞችና የጥበብፕ ሰዎች ናቸው:: ማንኛውም ጀርመን የሚሰራ ነገር ሁሉ የተፈተነና በቀላሉ የማይበላሽ መሆን አለበት ብለው ያምናሉ:: ትልቁ ችግራቸው ሌላውን አገርም ሆነ ሕዝብ መናቃቸው ነው: ከኛ በላይ አዋቂ አለ ብለውም አያምኑም:: ጀርመኖች ከአውሮፓ ኃብታሞች ስለሆኑ ሁሉም ነገር የሚገኘው በገፍ ነው:: በጠቅላላው ጀርመኖች የሥራ ሰዎችም ናቸው አንዴ በስራ ከተጠመዱ እረፍት ዩሚባል ነገር የለም:: ሰውም: ሲያሰሩ ሆነ በረዶ

ይደህመዋል የሚባል ነገር አያውቁም: ዝናብ በሥራ ከተጠመዱ ንቅንቅ የለም : ታዲያ

ሀሉም እንደነሱ መሥራት አለበት ብለው ያምናሉ :: ሀምበርግ ብዙ ዪኒቭርሲቲዎች ሲኖሩ ከከተማው መሀል ተንጣሎ የተቀመጠ የተማሪዎች የምግብ አዳራሽ (ሜንዛ ) የሚባል አለ: ከዚህ የምግብ አደራሽ ተማሪው ሁሉ ይሰባሰብና በትንሽ ገንዘብ ምግብና







መጠጡን በገፍ ይጠቀማል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

160

በተለይ ዓርብ ምሽት እኛ ኢትዮጵያውያን የምንስበሰብበት አንድ

ኃይሌ ፊዳ ኮርነር ብለን የሰየምናት ቦታ ነበረችን :

በኋላ ስሰማ ኃይሌ ፊዳ ከዚህ ነበር ይቀመጥና የኢትዮጵያን ፓለቲካ ይዘውር የነበረው ይላሉ:: ከዚህ ቦታ ከአስተማሪ እስከ ተማሪ ኢትዮጵያዊ አይታጣም:: ከነዚህም መካከል ፕሮፌሰር ባህሩ ዘዉዲ እና ሁለት አሁን ስማቸውን የረሳሁት የአማርኛና ግዕዝ ሀምበርግ ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ የነበሩ

አልፎ አልፎ

ይገኙበታል:: ይህ

ቦታእንደማንኛውም ቦታ አደለም:: የአገር ፖለቲካም የሚተነተንበት ክርክሩ የሚጦፍበት ቦታ ነዉ:: አንዳንዴ ክርክሩ ወደ መቧከስ የሚቀየርበትም ጊዜ ነበር :: በተለይ ቢራን የሚደፍሩ ሰዎች በጀርመን ቢራ በዬ ሰፈሩ

ጀርመን አገሩ ነው:

ነው የሚጠመቀው : ውሃ

አይጠጣም::አንዳንዴ ቢራው ቦቲ ጫማ በመሰለ ብርጭቆ ይቀርብና በጋራ እየተቀባበሉ ይጠጡታል: ታዲያ ከዚህ ቦታ ደግሞ ለተማሪ ተብሎ ሁሉም ነገር ርካሽ ነዉ:: ችግሩ ግን ተማሪዎች

ከፖለቲካው

ጋር ቢራውን

ሲቀላቅሉት ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል ይበዛል :: ይህ በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ከተለያዬ አገራት ለትምህርት







የመጡ ተማሪዎችም እንደኛው በቡድን የሚሰባሰቡ ነበሩ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

161

አንድ ቀን ምሳ

ለመብላት ወደዚሁ ቦታ ( ሜንዛ) ሄድኩ::

ገና ካካባቢው

ስደርስ ዙሪያው ያለወትሮው በጀርመን

ፖሊሶች ታጥሯል :: ነገሩን ለማወቅ ጠጋ ብዬ አንዱን ፖሊስ ጠየኩት::: እሱም ዘመዶችህ እርስ በርስ እየተደባደቡ ስለሆነ መግባት አትችልም አለኝ:: ታዲያ ለምን ገብታችሁ አትገላግሏቸውም አልኩት::እስኪጨርሱ ነው የምንጠብቀው አለኝ :: በዳር ሆኜ

ነገሩን ስከታተል በቡድን ተከፋፍለው

የሚደባደቡት የኢራን ተማሪዎች ነበሩ የአያቶላ ኮሚኒ

ደጋፊና ሌላው

:: አንዱ ቡድን

የድሮውን ንጉስ (ሻህ)

ደጋፊዎች ነበሩ :: በኋላ

ነገሩ በርዶ የቆሰሉትን አንቡላንስ እየተመላለሰ

ሲወስዳቸው የቀሩትንም ፖሊስ ሳይነካቸው በየመጡበት ሲሄዱ እኔም ከሰዉ ጋር

ወደ አደራሹ

ገባሁና ሳይ

ለመቀመጫ የሚሆን ወንበር አልተረፈም ነበር : ሁሉም ለጦር መሳሪያነት አገልግሏል::ምን ወንበር ብቻ ! የቢራ ጠርሙስና የምግብ ሳህኖችም

አልቀሩ ሁሉም







አደራሹ በደም ጨቅይቷል::

ደቋል:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

162

" ለጽዳት ሠራተኞች ትልቅ ሥራ ፈጥሯል አብሮኝ የገባ ጀርመን ተማሪ እየሳቀ

አለ :

አንድ

የሰዎቹ መጎዳት

ሳያሳዝነው:: "ሀምበርግ ጀርመን ለአምስት ዓመታት ያለችግር ትምህርቴን ስከታተል እንዳይደርስ የለምና የተወሰነው ትምህርትም ግዜው ሳይታወቀኝ አለቀና በፈረምኩት መሰረት ከአገር መውጣት አለብህ የሚል ትእዛዝ ከኦቶቤኒኬ ነፃ ትምህርት ድርጅት መጣ :: እነሱ ሀሳባቸው ተመልሼ ወደ ዪጋንዳ እንድሄድ ነበር:: ይሁን እንጂ እኔ ዪጋንዳ የማልሄድበት ብዙ ምክንያቶች አሉኝና መሄድ አልችልም ከምክንያቶቹም አንዱ ኢትዪጵያን ስደተኞች ጓደኞቼ በዩጋንዳ ጦር ሰራዊት መንገድ ላይ የሚገደሉበት አገር ነው ስል የተገደሉት ጓደኞቼን ስም ዝርዝር እንደማስረጃ አቀረብኩ::







ለዚህ ጉዳይ የጀርመን ኤንባሲና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በዪጋንዳ ሁኔታውን አጣርተው እንዲልኩ በተጠየቁት መሰረት መልሰው "ዪጋንዳ ቢመጣ ምንም ችግር እንደማይገጥመው እናረጋግጣለን::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

163

ለዚህም ከመጣ ችግር የሚገጥመዉ ከሆነ እኛ ለማንኛውም ነገር ጋራንቲ እንሰጣለን" በሚል የላኩት ደብዳቤ ጀርመን የመቆዬት እድሌን የበለጠ አጨለመው::



በመሆኑም ጀርመኖች ውል ውል ነው እመለሳለሁ ብለህ ፈርመሃልና በውሉ መሰረት ወደድክም ጠላህም እንመልስሃለን ሲሉ : ደመደሙ::በዚህ ጉዳይ ሰዎችን ሳማክር ጠበቃ ያዝናእየተከራከርክ ለግዜው መቆየት ትችላለህ ባንፃሩ ወደ ሌላ አማራጭ አገር ጠይቅና ካገኘህ ከዚህ መገላገል ትችላለህ አሉኝ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

164

ምዕራፍ -10

ወደ መጨረሻ የስደት አገር ጉዞ: ዙሪያው ሲዘጋብህ ሁሉም ሲጨልም: እንደጭስ ሰርስረህ ለመውጣት ዓልም: አታጣም ቀዳዳ መውጫ አለ ለሁሉም:

አዎ ለሰው ልጅ ቁርጠኝነት ካለው ለሁሉም መፍትሄ አያጣም : የሚለውን እሳቤ እወደዋለሁ አሁን ዙሪያው ጨልሞብኛል ቀሪ ህይወቴን የማሳልፍበት አገር የለኝም: በዚህ መካከል አንድ ፕሮፌስር ግርማ የሚባሉ የአዲስ አበባ ዪንቭርሲቲ መሞህርና የኢሳፓኮ አባል የነበሩ ለጥናት ጀርመን መጥተው ነበርና ሰው አስተዋዉቆኝ::













ከዚሁ ሀምበርግ መጥተው ስንወያይ ስለኔ ያለሁበትን ሁኔታ አጫወትኳቸውና በጣም አዝነው ወደ አገርህ ብትመለስ በተማርከው ትምህርት ብዙ ትጠቅማለህና እኔ መንግሥትን ልጠይቅልህና ኢትዮጵያ ግባ አሉኝ::እኔም ከዚህ ሁሉ መንከራተት ገብቼ አገሬ ላይ ሕዝቤ እንደሆነው ብሆን ብዬ አሰብኩና እሽ አልኳቸው ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

165

ፕሮፌሰሩ ባዘዙኝ መሰረት ቦን ኢትዮጵያ ኤንባሲ ደውዬ ከፕሮፌስር ግርማ ጋር የተነጋገርነውን ፕሮፌሰሩም ስለዚሁ ጉዳይ ከናንተ ጋር እንደተወያዪና እናንተም እንደተስማማችሁ ስለተረዳሁ ነው የምደውለው አልኳችው:: እነሱም ነገሩን እንደሚያውቁትና መመለስም እንደምችል ከነገሩኝ : በኋላ ነገር ግን ብለዉ አንድ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጡ:: "በመቀጠልም በመቀጠል ----አንተ ማን ነህ ? ጀርባህን ዘርዝረህ የሠራኽውን ወንጀል ገልፀህ መንግሥት ይቅርታ እንዲያደርግልህ ይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤ ጽፈህ: ለኛ ትልክና እኛ ደግሞ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ልከን ከዚያ ሲፈቀድልህ ብቻ ነው ቪዛ የምንሰጥህ::" አሉና ፕሮፌሰሩ ያደረጉትን ጥረት ሁሉ ከንቱ አስቀሩት:;







ጊዜዉ ነሐሴ ወር እ •አ •1984 ነበር የአንድ ኢትዮጵያዊ የጀርመን የስደተኛ ዶኩሜንት (ሌሴ ፓሴ) ተውሼ በባቡር ስጓዝ አድሬ ጧት ስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ገባሁ::

የስደት ጉዞዬ

166

ምዕራፍ-11 ስቶክሆልም -ስዊድን

ስቶክሆልም የስዊድን ዋና ከተማ እና የአገሪቱ የባህል ፣ የፖለቲካ ፣ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ነች:: በ 57 ድልድዮች ተገናኝተው ከ14 በላይ ደሴቶች ላይ የተገነባች ሲሆን አረንጓዴ እና በውሃ የተከበበች መሆኗ ለከተማዋ ልዬ ውበት ሆኗታል ፡፡ ስቶክሆልም የስዊድን ዋና ከተማ ሆና በ 1436 ከተመሰረተች ጊዜ አንስቶ ከተማዋ የመንግሥት ትልቁ እና የንጉሣዊው ቤተ ፣ መንግሥት ፣ ፓርላማ እና ማዕከላዊ አስተዳደር መናገሻ ሆና የቀጠለች ውብና ዘመናዊ ከተማ ነች:: ከተማዋ በንፁህናቸው ከሚታወቁት የዓለም ከተሞች መካከል በአምስተኛ ደረጃ የተመደበች ስትሆን የሰሜን አውሮፓ ትልቋ ከተማ ነች እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ ም ሕዝብ ቆጠራ መሰረት 1,5 ሚሊዬን ነዋሪዎች ይገኝባታል፡፡









ስቶክሆልም ባቡር ጣቢያ እንደደረስኩ አንድ ወዳጄ ተቀብሎ ከቤቱ ካሳረፈኝ በኋላ ትንሽ ቀናት ቆይቼ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ ከኢትዮጵያ የመጣሁና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደምፈልግ አስረድቼ ቃሌን ሰጠሁ ::



እኔና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

167

ፖሊሱ ብዙም አላስቸገረኝም ወዲያው በመኪና ወስደው ከአንድ ሆቴል አስቀመጡኝ::በሳምንቱም የራሴ የሆነ አንድ ክፍል ቤት ከነሙሉ እቃው ሰጡኝ:: ለምግብ የሚሆንም በቂ ገንዘብ በየወሩ መደቡልኝ:: አያይዘውም የስዊድንኛ ቋንቋ እንድማር የሚያስችልና የትራንስፖርት ገንዘብ ሰጥተው ለትምህርት አዘጋጅተው: እንድጀምር ነገሩኝና ስዊድንኛ ቋቋን መማር ጀመርኩ:: ቋንቋው ከጀርመንኛ ጋር ብዙ ስለሚመሳሰል ብዙ አላስቸገረኝም:: ጥቂት ወራቶች እንደተማርኩ አንድ ከዓለም የታወቀው ከስዊድን ትልቁ የቴሌፎን ካምፓኒ ኤሪክሶን ቴሌኮም (Ericsson Telecom) የሥራ ማስታወቂያ ለማይክሮ ኤሌክትሮኒክስ ቴክኒክ (Electronics Technic) በማይክሮ ኤሌክትሮኒክስ ትምህርት ያለው ሰው ለመቅጠር እንደሚፈልግ ያወጣውን ማስታወቂያ አየሁና የጀርመን የትምህርት መረጃዬን በማሳዬት ባመለከትኩት መሰረት ተቀብለው ወዲያው ሥራ እንድጀምር ተነገረኝና ተቀጥሬ 3 ወራት እንደ ሠራሁ : "ከዛሬ ጀምሮ የስዊድን ዜግነት ያገኘህ ስለሆነ መጥተህ የስዊድን ፓስፖርትህን እንድትወስድ" የሚል ደብዳቤ ቤቴ ድረስ ልከው ደረሰኝ::







አገሬን ልግባና ላገልግል ስል ጅርባህን :ማንነትክን እስመርምር ተብዬ የተባረርኩ ሰው በወራቶች ቆይታ የዜግነት መብት አግኝቼ ሥራና ቤት ተሰጥቶኝ: ሰውነቴ ታውቆ: አገሬ ያላገኘሁትን መሪዬን የመሞረጥና የመመረጥ መብት የሰጠችኝ ሁለተኛዋ አገሬ ስዊድን : ሰው ለመሆኔ እውቅና ያገኘሁበት አገር ሆነችኝ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

168

ሊሠራ የሚችል ትኩስ ጉልመትና አቅም ያላቸውን ዜጎች አገራቸውን እንዳያገለግሉ በሆነ ባልሆነው እያባረሩ አገር እወዳለሁ: አገር አሳድጋለሁ የሚሉ የአፍሪካ መሪዎች:: አገር ማለት መሬቱ ዳገት ሽንተረሩ ውሃና እፅዋቱ ወይም ከባለፀጎች በተመፀወቱት ገንዘብ የሚገነባው ህንፃና መንገድ ብቻ ሳይሆን በውስጡ ያለው ሕዝብ ጭምር መሆኑን የተረዱ ባለመሆናቸው ጊዜያቸው ደርሶ አንዱ ተረኛ እስኪፈነግላቸው ድረስ የሕዝቡን የመከራ ኑሮ አብዝተውት እነሱም በመጨረሻ ተዋርደው ያልፋሉ:: አገር የሚያድገው ሁሉም ዜጋ የመኖርና የመሥራት መብቱ ሲከበርለት: በየትኛውም ያገሪቱ ክፍል እንደልቡ ተንቀሳቅሶ መኖር መሥራት ሲችል ነው:: ይሁን እንጂ መሪዎች ለፖለቲካ ፍጆታ በቴሌቪዝን መስኮት እየወጡ በሚሰጡት ዲስኩርና ባልተጨበጠ ተስፋ ብቻ አደለም:: አሁን ከብዙ ወጣ ዉረድ በኋላ ስዊድን አገር በህይወቴ እንዳገኝ የምመኘው ሁሉ አግኝቻለሁ : ጥሩ ሥራ አለኝ: የምኖርበት ቤት ገዝቻለሁ: መኪና እለዋዉጣለሁ በያመቱ ከፈለኩት አገር ሄጄ እረፍቴን አሳልፋለሁ: ጥሩ ትዳርና የ3 ልጆች አባት ነኝ ልጆቼ ጥሩ ት/ቤት ይማራሉ ሌላው ቀርቶ የእናትአባት ቋንቋቸውን እንዲያውቁ ተብሎ መንግሥት ልዬ አስተማሪ ቀጥሮ አማርኛ ማንበብና መጻፍ ይማራሉ : እኔም የምፈልገውን መንግሥት እመርጣለሁ እተቻለሁ::









ግን ምን ያደርጋል ይህ ሁሉ በስዊድን መንግሥትና ሕዝብ የተደረገልኝ ደግነት ና እንክብካቤ ከልቤ አልደርስ አለ ::ሀሳቤም ልቤም ኮበለለ: ዳገት ሸንተረሩን ዉቅያኖስ አቋርጦ ከዛች ከተወለድኩባት እትብቴ ከተቀበረባት አገሬ የገጠር መንደሬ ሸመጠጠ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

169

እኒያ ሌትም ቀንም አንድ ጋቢ ለብሰው ያለ እግራቸው ጫማ አፈር የሚገፉት ወገኖቼ ሌትም ቀንም ይታዪኝ ጀመር ::

ሳቃቸውና ደስታቸው ሳይሆን ችግራቸው መራባቸው ከፊቴ እዬመጣ ይደቀን ጀመር:: ግን ለምን የሰው ልጆች የኑሮ ልዩነት እንደዚህ ሊሰፋ ቻለ :: ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከአዕምሮዬ ደወሉን ይዞ ይደውል ጀመር:: መልስ የማላገኝለት ሀኪም የሌለው በሽታ ገጠመኝ:: አንድ ቦታ ስጎበኝ ጥሩ ነገር ሳይ ይህነን ኢትዮጵያ ወስጄ ማስቀመጥ ብችል!! እላለሁ ::ወይም የሰዊድን የፓርላማ በቴሌቪዥን ካሜራ ፊት ሲሟገቱ ሀሳባቸዉን ለማሳመን ሲሞክሩ : ከዚያ ወጥተዉ እርስ በእርሳቸዉ ሲሳሳቁ : በሕዝብ ማመላለሻ ባቡር: አዉቶቡስ ከሕዝብ ጋር እየተጋፋ እያወሩ ሲሄዱ ሳይ ይህ ኢትዬጵያ ቢሆን : የሚለው በሃሳቤ ይመላለስብኛል : ምንም እንኳን ይሄም አገሬ ቢሆንም የኔ መስሎ አይታየኝም ::







አንዳንዴ "የሰው ወርቅ አያደምቅ" እንዲሉ እላለሁ: መለስ አድርጌ ዓለም የሁሉም የሰው ልጆች ነች ስለዚህ ማንም አገርን በጭቃ ጠፍጥፎ የሠራት የለም : እናም አንድ ሰዉ እግሩ ሂዶ የደረስንበት ሁሉ አገሩ ነው::ለምሳሌ አሜሪካኖች :አውስትራልያ ኒውዝላንድ : ካናዳ የመሳሰሉትን ብንወስድ ከዓለም ዙሪያ ተሰባስበው የሚኖሩባቸው አገራት ሲሆኑ ሕዝቦቻቸውም አገራችን ብለው የመጡበትን አገር ረስተው ነው የሚኖሩት::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

170

ታዲያ እኔስ ለምን እንደነሱ አልሆንም ?? ኢትዮጵያ ለኔ ምን አደረገችልኝ? እላለሁ ይህ ግን ለግዜው በሽታዬን ለማስታገስ ራሴን ለማጽናናት ባፌ ብለውም ከአዕምሮዬ ለማውጣት በቂ መልስ አልሆንልህ አለኝ :: ኢትዮጵያ ያላት የተፈጥሮ ሀብት: የዓየር ፀባይ ከዓለም ተመራጭ ከሚባሉት አገሮች አንዷ ሆና ሳለ ለምን አገሬ ወደኋላ ቀረች ? ለምን ሁል ጊዜ የሚገጥሟት መሪዎች ከነሱ አስተሳሰብ ሌላ የሕዝቡን ፍላጎት ማየት አቃታቸው? ለምን የአገሬ ወጣት ሁል ጊዜ በጦርነት ይማገዳል :? ለምን ሁሉም ህብረተሰብ የሚስማማበት የአስተዳደር ሥርዓት መፍጠር አልተቻለም?: የሚሉት ጥያቄዎች ሁል ጊዜ በአዕምሮዬ መመላለሱን ቀጠለ ;;

ስዊድኖች በክረምት ከበረዶ ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ሳይ : በረዶ የሸፈነውን መንገድ በትራክተር ጠርገው ጨውና አሽዋ ነስንሰዉ ጧት ለትራፊክ ነፃ ያደርጉታል: በጋ ሲሆን ደግሞ የተበተነው አሽዋ ተጠርጎ በበረዶ ምክንያት የተሰነጣጠቀውን መንገድ ጠግነው አዲስ አስፓልት ቀብተው ቆንጆ መንገድ ያደርጉታል::







ይህ በየጊዜው ሳያቋርጥ ከረምትና በጋ የሚሰራ ሥራ ነው::ይሄን የሥራ ሞራል ለሀገሬ ሕዝብ ባረገው ኢትዮዮያ የት በደረሰች ነበር ! ለም መሬት ሠራተኛ ሕዝብና ተስማሚ የዓየር ፀባይ ይዘን እንዴት የምግብ እርዳታ እንጠይቃለን :እንዴት ስንዴ ከዉጭ እንገዛለን እያልኩ መብሰክሰክ የዘወትር ተግባሬ ሆነ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

171

ምዕራፍ -12 ወደ አገር ቤት ጉዞ በፖለቲካ ምክንያት ከአገር ከወጣሁ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል: ለስደት የዳረገኝ የደርግ መንግሥት ወድቆ በኢህአዴግ ተለዉጧል ስለ ሀገሬ የምሰማዉ ሁሉ አዕምሮ መሸከም ከማይችለዉ ሁኔታ ላይ ደርሷል: የኢትዮጵያ ነገር ከድጡ ወደማጡ እንደሚሉት ሆኗል: በማይታወቅ የኮሚኒዝም ርዕዮተዓለም የገበሬመን ንፁህ አዕምሮ ሲያደነዝዝ የከረመዉ ደርግ ያለምንም ዝግጅት አገሪቱን ለወያኔ ጀሌ ጥሎ ሂዷል: ያለምንም አገር የመምራት ልምድ የሌለዉ ከጫካ የወጣዉ ወያኔ በምዕራባዉያን ተደግፎ አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ በኋላ አብሮ ተከባብሮና ተዋልዶ በሰላም እየኖረ ያለዉን ሕዝብ የአባት የናት አጥንት እየቆጠረ በፖለቲካ እንዲጎዳኝ ሆነ::







በዚህም ምክንያት አንዱ ባንዱ ላይ እጁን እየተቀሳሰረ እንዲኖር አድርጎዉታል:: ይሄም ከአንድነት ይልቅ መከፋፈልን ፈጥሮ ለአገሪቱ ከባድ አደጋ ከምንግዜዉም በበለጠ ተደግኖባታል: የባሰዉ ደግሞ ህዉሓት በአማራዉ ሕዝብ ለይ ያነጣጠረ የጥላቻ መርዝ በመርጨቹ ምክንያት በሁሉም አቅጣጫ በአማራዉ ላይ የሚደርሰዉ ወከባ ከሁሉም የከፋ መሆኑ ነበር:: ይሁን እንጂ የሄን ሁኔታ ሂጄ ራሴ ለመረዳት ፈለኩ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

172

ስለሆነም ከተለየኋቸዉ ከደብዳቤና ስልክ ሌላ በአካል ያላየኋቸዉን ዘመዶቼን ለማዬት ከትዉልድ አገሬ ከወጣሁ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተጓዝኩ:: ከአዲስ አበባ ሳልዉል ሳላድር በበነጋዉ

በአይሮፕላን

ተሳፍሬ ባህርዳር ዓየር ማረፊያ አረፍኩና የማድርበት ሆቴል ከያዝኩ በኋላ

ከተማዋን

ለመጎብኘት ዘወር

ዘወር ስል ጌወርጊስ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ርሃብና መንገድ ያበሳቆላቸዉ ወንድ ሴት ህፃን ሽማግሌ የተደባለቁባቸዉ ሰዎች በብዛት ሲተራመሱና ፖሊስ ከዚህ ማረፍ አትችሉም እያለ በያዘዉ አለንጋ ሲገርፋቸዉ አየሁና ተጠግቼ ለማጣራት ስሞክር ከሌላ ክልል

አማራ ናችሁ ተብለዉ ተፈናቅለዉ የመጡ

ተፈናቃዮች ናቸዉ አለኝ:: ታዲያ መሄጃ ከሌላቸዉ ከቤተክርስቲያን ሌላ የት ይሂዱ ?? ስለዉ ፖሊሱ

ለጠየኩት ጥያቄ በአግባቡ

ከመመለስ ፈንታ እኔንም ሊመታኝ ሲያንገራግር እያዘንኩ ቦታዉን ለቅቄ ሄድኩ:: ምን አይነተ ዓለም ነዉ ? እኔ በመልክም በቋንቋም በምንም ከማልመስላቸዉ አገር እንደ ሕዝቡ እኩል መብት ተሰጥቶኝ ተዝናንቼ





እኖራለሁ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

173

እንዴት ኢትዮጵያዊ ሌላ ቋንቋ ተናገርክ ተብሎ ዝንተ ዓመት ከኖረበት ቦታ ሀብት ንብረቱን ትተህ ዉጣ ይባላል እያልኩ ብቻዬን ሳወራ በድንገት ኢዲ አሚን ዳዳ ከዩጋንዳ በ 90 ቀናት የለ በ ሱ ትን ብ ቻ

ይዘዉ

ያባረራቸዉ የህንድ ተወላጆችን የእስር ቤት ጏደኛዬ ያጫወተኝ ሁኔታ ታወሰኝ :: እሽ እነዛስ ዉጭ አገር በቅኝ ገዥዋ እንግሊዝ መጥተዉ የሰፈሩ ናቸዉ እነዚህ እኮ አገራቸዉ ነዉ ኢትዮጵያን ናቸዉ

እኮ !!::ሰዉ ካገሩ እንዴት ዉጣ

ይባላል ደግሞስ አማራ ሆኖ መፈጠር ወንጀሉ ምንድን ነዉ ?

ለጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ አድሬ ጧት መኪና

ተከራይቼ ወደ ትዉልድ ቦታዬ ሁል ግዜ በልጅነት አዕምሮዬ ተጽፎ ከማይጠፋዉ ጥጃ የጠበኩበትን ዉሃ የተራጨሁበትን: ገና የተጫወትኩበት : ቦታ ሰራዉዲን በጉጉት ለማዬት ተጓዝኩ:: መንገዱ ድሮ ጣልያን በጦርነት ጊዜ የጠረገዉ ጠጠር መንገድ ምንም መሻሻል ሳይደረግበት እንዳለ ስለሆነ መኪናዉን ከላይ እያነሳ ያፈርጠዋል ጩኽቱ ጆሮ





ያደነቁራል::

የስደት ጉዞዬ

174

አቧራዉ የካርቱምን የአሽዋ ማእበል አስታወሰኝ:: ለወንዝ መሻገሪያ ተሰርቶ የነበረዉ ድልድይ ስላልተጠገነ ፈርሷል: መኪኖች ሕዝቡ ቆፈር ቆፈር አርጎ በሰራዉ ግዜያዊ መሻገሪያ ነዉ የሚሻገረዉ: በየመንገዱ ዳር ብዙ ሚሊዮን ዶላር ፈጅተዉ የተገዙ ሶቢዬት ሰራሽ ታንኮች ተቃጥለዉ በየመንገዱ በቆሙበት ፈራርሰዋል ::

(. * ሦስቱ ወንድማማቾች በስተ ግራ ታላቅ ወንድሜ አቶ አዜ ይግዛዉ ከመሀል እኔ ሞላ ይግዛዉ በስተቀኝ ታላቃችን አቶ ካሤ አሰፋ ከተለየኋቸዉ ከ40ዓመት በኋላ እንደገና ለመገናኘት በቅተን ከአዉሮፓ ሂጄ ጎብኝቻቸዉ ስመለስ እኔ ከተወለድኩበት ቦታ ዝሃ ሚካኤል ላይ እንደገና ስንለያይ እኔን ሲሸኙ የተነሳነዉ ፎቶ 2000 ዓ ም )

በመንገድ ላይ

የማያቸዉ የቀንድ ከብቶች የጎን

አጥንታቸዉ ወጥቶ ቆዳዉ ወደዉስጥ ስርጉድ ብሎ በጣም የተራቡ መሆናቸዉን ያሳብቃል::የሄድኩት





ደቡብ ጎንደር እብናት ወረዳ ሰራዉዲ ቀበሌ ነበር::



እኔና

እኔና

የስደት ጉዞዬ

175

እንደደረስኩ ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ ቦታዉ ተቀያይሯል::

ድሮ

እየተሹለከለክን ድብብቆሽ

እንጫወትበት የነበረዉ ደን ጫካ

አልቆ ዛሬ ባዶ

ምድረበዳ መስሏል: : ግዙፉ ተራራ ተመንጥሮ ዳገቱ ሳይቀር ታርሷል :: በፀኃይ ጊዜ መጠለያ የለም :: መሬቱ ተሸንሽኖ ለእርሻ አገልግሎት እንጂ ለከብቶችና ለልጆች መቦረቂያ የሚሆን የለም ::ለወንዝ መሻገሪያ ተሰርቶ የነበረዉ ድልድይ ስላልተጠገነ ፈርሷል: መኪኖች ሕዝቡ ቆፈር ቆፈር አርጎ በሰራዉ ግዜያዊ መሻገሪያ ነዉ የሚሻገረዉ:: ገበሬዉ የሚያረባቸዉ ከብቶች በልክ ነዉ : ብዙ ላሞች ላርባ ቢል የሚያግጥበት ቦታ ስለሌለዉ ከአንድ ላም በላይ ማርባት አይችልም:: በዚህ ላይ የመሬት አከፋፈሉ ፍትህ የጎደለዉና ለገዥዉ







ፓርቲ ካድሬዎች ብቻ ደህና የእርሻ መሬት ተመርጦ ይሰጣሉ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

176

የቀረዉ ገበሬ የሚያገኘዉ መሬት ለማረስ የሚያስቸግር ቢታረስም ብዙ ምርት የማይገኝበት ነዉ : :የዚህ ዓይነት የመጨረሻ

የማይጠቅም መሬት የሚያገኘዉ የድሮዉ

መንግሥት የደርግ አባል የነበረ ሲሆን

ጎበዝ ገበሬ

ቢሆንም አይሰጠዉም:: መኖር ስላለበት ግን

ከወያኔ ካድሬዎች

ተከራይቶ

ያርሳል ይሄም በተዘዋዋሪ መንገድ እኛ በ60ዎቹ መሬት ለራሹ ብለን ንጉሡን የገለበጥንበት

የትግል ማእከል

ዉጤቱ ተመልሶ ጭቃ እንዲሉ ብዙ ወጣት የተሰዋበት ትግል ዓላማ ከንቱ መቅረቱን ያሳያል::በዚህና በሌሎች ምክንያቶች

የሕዝቡ የኑሮ

ሁኔታ

የመጨረሻዉ

ዝቅተኛ ደረጃ እንዳለ በቀላሉ ማንበብ ይቻላል::

ከአንገታቸዉ ሌትና ቀን የማትወልቀዉና ዉሃ ነክቷት የማያዉቀዉ ጋቢያቸዉ መልኩን ቀይሮ ወደ ጭቃነት ተቀይሯል: ምግብ በደንብ ጠግበዉ በልተዉ የማያዉቁ መሆኑ እንዲሁ በማየት ብቻ ገጽታቸዉ ይነግራል:: በጠቅላላዉ ያሳዝናሉ:ከአንድ ገበሬ ወንድሜ ቤት እንዳድር ተጋበዝኩና

ሄድኩ :ለረጅም ጊዜ ተለያይተን





ነበር የኖርነዉ ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

በአካል ብቻ ሳይሆን በአኗኗርም የምድር

177

ልዩነታችን የሰማይና

ያህል እርቀት ሆኗል ፣ ክብ ሆኖ ከተሰራዉ

አደራሽ ቤት ገባንና በዙሪያዉ ከታሰሩት የቤት እንስሳት ፊት ለፊት ተቀመጥን:: ከኋላችን የታሰሩት ላምና እየተንጠራሩ ፀጉራችን

በሬዎች ከአንገታቸዉ

በሸካራ ምላሳቸዉ ይልሳሉ::

በእጅ ሲከለከሉ መልሰዉ ይመጣሉ : ፍየሎች ቀረብ ብለዉ ልብስ ይጎታታሉ ይታከካሉ በጠቅላላዉ ቤቱ

ድመቶች እየተጠጉ እግር ልዩ ተፈጥሮአዊ ጠረን

አለዉ :: ቆጥ ላይ የተሰቀሉት ዶሮዎች ከላይ ሆነዉ ወደታች እንደፈለጉ ይፀዳዳሉ ማን ተይ ሊላቸዉ ::

ጉድ እኮነዉ ያገራችን ገበሬዎች ኑሮ፣ አፄ ፋሲል ከመቃብራቸዉ ቢነሱ ከነበሩበት የአኗኗር ሁኔታ ልዩነት አይኖርም

ይህ ሁሉ ሆኖ ካመሸን በኋላ የመኝታ ጊዜ

ደረሰና ወደ አንድ ጥግ አግዳሚ ወንበር ላይ አንድ የበግ





አጎዛ ተነጠፈልኝና እንድተኛ ተጋበዝኩ::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

178

በቤቱ ትልቁ ምቾት ያለበት ለእንግዳ የሚዘጋጅ መኝታ መሆኑ ነዉ። እነሱም እያንዳንዳቸዉ ከበሬዎቹ ጋር የታሰረ ገመድ በእጃቸዉ እየያዙ

በየፊናቸዉ ባገኙት

ሁሉ ተጋደሙ ነገሩ ገረመኝና የበሬዎቹን ማሰሪያ ገመድ ለምን ትይዛላችሁ አልኩ ወንድሜ ሳቀና በጃችን የበሬዎችን ”ገመድ ይዘን የምንተኛዉ ጉልበተኛ መጥቶ እንዳይወስድ በማለት ነዉ :አገራችን ሥራት ጠፍቷል መንግሥት የለም ሀብትህን ፣ሚስትህን ጠበንጃ ወድረህ ካልጠበክ ጉልበተኛ መጥቶ ይወስዳቸዋል። ብትጮህ የሚደርስልህ የለም ሁልህም ራስክን አድን ነዉ

የሆነዉ አለኝ ”መቼም

አዉሮፓ ክፉ ምቾት

አስለምዶኛልና እንዳዉ ብዙ በእግሬ ስለተጓዝኩ ደከመኝና ጎኔን ለማሳረፍ ጋደም አልኩ እንጅ እንቅልፍማ እንዴት ተሞክሮ! :: እንዲሁ ስገላበጥና ወንድሜንም በጥያቄ ሳጣድፍ በግምት በኢትዮጵያ ከሌሊቱ 9:00 ስዓት ሲሆን ከማዶ የድረሱልኝ እሪታ ቀለጠ :: ወንድሞቼ ጠበንጃ ያለዉ ጠበንጃዉን የሌለዉ ጦሩንና





ዱላዉን እየያዙ ሲወጡ እኔም እነሱን ተከትዬ ወጣሁ;:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

179

ምንድን ነዉ ? ስል ሁኔታዉን ለማወቅ ጠየኩ:: ” ያዉ በሮች ተሰርቀዉ ነዉ እንጂ አለኝ ወንድሜ ተስፋ በቆረጠ አንደበት "እና አሁን ምን ልታደርጉ ነዉ .? "እንግዲህ አቅም ያለዉ እና መሣሪያ ያለዉ በየበሩ እየሄደ እንዲጠብቅ ለማድረግ ነዉ እንጂ ሌላ ም ይደረጋል" አለኝ:: በኋላ እንዳጣራነዉ አንዱን

ሰዉ ቤቱን ከዉጭ

ዘግተዉ እንዳይወጣ ካደረጉ በኋላ ሁለቱን በሮቹን ወሰዱ ሌሎቹን ጠበንጃ ስለሌላቸዉ አስፈራርተዉ በሮቻቸዉን ቀምተዉ በጠቅላላዉ ከዚያ ቀበሌ በዚህ ሌሊት ተቀምተዉና ተሰርቀዉ በጉልበተኞች በጠቅላላዉ 5 በሮች ተወሰዱ። ጧት በኢትይጵያ 2ሰዓት ገደማ አንደኛዉ በሬ ከታሰረበት በጥሶ እየሮጠ ስላመለጣቸዉ ከባለቤቱ ጋር

መንገድ

ላይ ተገናኘ: አራቱን ለማግኘት አምልጦ በመጣዉ በሬ ዱካ ተከታትለዉ አካባቢዉ ቢደርሱም ዘራፊዎቹ መሣሪያ ይዘዉ ወደነሱ





አሰጠነቀቁ ::

ሰዉ አንዳይቀርብ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

180

በዚህ መካከል ሽማግሌ መሀል ገብቶ ማሸማገል ጀመረ ፣በሽምግልናዉ ዘራፊዎቹ የተሰረቁትን በሮች ለያንዳንዱ 15 000ብር (ሽር) ይሉታል ከፍለዉ እንዲወስዱ ይጠየቃሉ ማህል ላይ በተደረገ ሽሥግልና ለ4ቱ በሮች 30 000 ብር ከፍለዉ በሮቻቸዉን ይዘዉ ተመለሱ። አሁን 2 በሮች የነበሯቸዉ ገበሬዎች አንድ አንድ በሬ በመሸጥ እዳቸዉን ከፍለዉ አንድ በሬ ብቻ ይዘዉ ቀሩ ። ይህ ነገር በዚህ አካባቢ የተለመደ የኑሮ ዘዴ መሆኑን የተረዳሁት ቀበሌና የወረዳዉን አስተዳዳዎችን ካነጋገርኩ በኋላ ነበር

ለምን እንደዚህ አገሩ በስራት

አልበኞች ሲወረርና ሕዝብ ሰላም ሲያጣ ዝም ብላችሁ ታያላችሁ የናንተ መኖር ጥቅሙ ምንድን ነዉ አልኳቸዉ። እነሱም " እኛ ምን እናድርግ የሚሳረቁት እኮ እርስ በርስ ነዉ ዛሬ ይሄኛዉ ቢሰርቅ ተሰራቂዉ ደግሞ ጊዜ ጠብቆ እሱም ይሰርቃል"። እና የናንተ ሚና ምንድን ነዉ አገሩ እኮ መንግሥት ሳይሆን ጉልበተኛ እየተቆጣጠረዉ ነዉ





ለምን የሚሰርቅን ሁሉ አትይዙም ? ::

እኔና

"እንደሱ

የስደት ጉዞዬ

181

እንዳናደርግ 1ኛ አንድን ሰዉ ሲሰርቅ አየሁ

ብሎ የሚመሰክር ከሌለ ማሰር አንችልም በህጉ መሰረት: ምንም እንኳን እሱ እንደሰረቀ ብናዉቅም ":: ሁለተኛ እኛ በጥርጣሬ ይህን ሰዉ ብንይዝም እንኳን ነገ መጥቶ ሊገድለን ይችላል። ስለዚህ ዝም ብለን ከማየት በተለዬ

የምናደርገዉ ነገር የለም አሉ":: ይህ

በዚህ እንዳለ ከህዝቡ ያገኘሁት መረጃ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ የወጣ ህግ ለሌባ እንዳይያዝ የሚያግዝ ነዉ :





ለምሳሌ ድሮ ከአንድ አካባቢ ስርቆት ሲከሰት ያካባቢዉ ሕዝብ አፍርሳታ ክተት በሚል ይሰበሰብና ወፍና ድንጋይ የሚሆን ሰዉ ይመረጥና እነሱ ከሕዝቡም ተመካክረዉ በሚሰጡት ፍርድ ሌባዉ ይያዝ ነበር:: ዛሬ አየሁ ብሎ የሚመሰክር ከሌለ አይያዝም ደግሞስ ጨለማን ተገን አድርጎ የተፈጸመን ነገር አየሁ ብሎ የሚመሰክር እንዴት ይገኛል::

እኔና

የስደት ጉዞዬ

182

ለነገሩ " ሌባ ሰርቆ እስካልተያዘ ድረስ ሥራ ነዉ እጅ ከፍንጅ ከተያዘ ብቻ ነዉ ሌባ የሚባለዉ ብሎን የለ" ያ የሰይጣን ቁራጭ:: ከኢትዮጵያ ሕዝብ 80% የሚሆነዉ ያገሬ አርሶ አደር ገበሬ በዚህ ዓይነት የኑሮ ሁኔታ እየገፋ ይገኛል:: ሌላዉ የህብረተሰብ ምጣኔ ኃብትና ያለዉ የመሬት ጥበት ችግር ነዉ አሁን መሬት ተሸንሽኖ እያንዳንዱ የበሬ ግንባር የምታህል መሬት ነዉ የያዙት:: ከያንዳንዱ ቤተሰብ ቢያንስ ከ7-12 ልጆች ይኖራሉ እነዚህ ልጆች ላቅመ አዳም ሲደርሱ መሬት ከአባት ይዞታ ተቆርሶ ነዉ የሚሰጣቸዉ እንግዲህ አንድ ቤተሰብ ያለዉን ይዞታ ለሰባት ልጆች ቢያካፍል ምን ያህል መሬት ለያንዳንዱ ይደርሳል ? :: የነሱ ልጆችስ ምን ያህል መሬት ያገኛሉ በዚህ ከቀጠለ ባለዉ የሕዝብ መጨመር ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት እንኳን የሚያርሱት መሬት

ቤት የሚሰሩበትም ካገኙ እድለኞች

ናቸዉ፣ በዚያም ሆነ በዚህ ለመጭዉ ትዉልድ







የምናስረክባት ኢትዮጵያ ለጊዜዉ ይችን ትመስላለች።

እኔና

የስደት ጉዞዬ

====ደሳሳ ጎጆዬ==== ያች ደሳሳ ጎጆ ልትወድቅ የዘመመች በሦስት ማገሮች በልጥ የታሰረች ከሰምበሌጡ እሳር ካረግ የተሰራች በእበት ተለቅልቃ በጭቃ ያማረች የትም ቦታ ሁኜ ትዝ ትለኛለች ዘመድ አዝማዶቼ ሆነው ጎረቤቴ ለቡና ሲመጡ ተጠርተው ከቤቴ እንጀራው በሞሰብ ክትፎው በገበቴ ገንቦ ጠላ ወርዶ እያልኩኝ በሞቴ ሲስቁ ሲያወሩ ሲዝናኑ ከቤቴ ትዝታው አይጠፋም ሳለሁ በህይወቴ ያች ደሳሳ ጎጆ የግል የብቻዬ ጠራ ጣራዋን ሳይ ተኝቼ ካልጋዬ አርፍባት ነበረ እያልኩኝ እፎዬ ያች ደሳሳ ጎጆ ባጋም የታጠረች ዓየሯ ውሃዋ ጠረኗ ያማረች በእህሎች ጎተራ በሽርፎች ያበበች በከብቶቹ ጩኽት በአበቦች ያጌጠች ደሳሳ ጎጆዬ ትዝ ትለኛለች እንደዛሬው ሳይሆን እርጅናሳይጥላት የሚያድሳት ጠፍቶ ቀዳዳ ሳይበዛት ነቀዝ ግጦ ግጦ አዝሞ ሳይጥላት በሰው ማዳበሪያ ቆንጥር ሳይበቅልባት ያች ደሳሳ ጎጆ የነበራት ውበት







































































ደጉ ዘመን አልፎ መጥፎው ተተክቷል ዘንድሮስ ጎጆዬ አረም በቅሎባታል ምሰሶዋ ወድቆ ምስጥ ፈልቶባታል ያ ሁሉ ሁካታ ፀጥታ ወርሶታል ሕዝቡም ተፈራርቶ መተማመን ጠፍቷል ግማሹ ተሰዶ አብዛኛውም ሞቷል ወጣቱ በእስር ቤት ቦታውን ሞልቶታል ሕፃን ምግብ አጥቶ በሞት ያቃስታል በሽታ ሰቀቀን ቦታውን ወርሶታል ሬሳው በርክቶ አካባቢው ገምቷል ደሳሳ ጎጆዬ ዛሬስ ምን ነክቷታል

183

እኔና

የስደት ጉዞዬ

=ሰዉ የሚያስፈልገኝ= እናት አረገመኝ አባት አረገመኝ ሰው አላስቀየምኩኝ ሰርቄ አልተያዝኩኝ ውሸት ተናግሬ ሰው አላጣላሁኝ ምግብ ሆነ መጠጥ ሁሉን አላጣሁኝ ምንድን ነው ነገሩ ሌት የሚያባንነኝ በደረቁ ሌሊት ሰው የሚያስፈልገኝ እንቅልፍ የሚነሳኝ ደርሶ እሚያበሳጨኝ መብራት የሚያስበራኝ ደግሞ የሚያስጠፋኝ ብርድ ልብስ አንሶላ የሚያስወረውረኝ ምንድን ነው ነገሩ ሰው ሰው የሚያሰኘኝ ከሰው ጋር ቁጭ ብዬ ስው የሚያሳስበኝ መታመም መረገም ወይስ ምኑ ነካኝ በደረቁ ሌሊት የሚያብረከርከኝ ቀን የሚያበድነኝ ሌት የሚያባንነኝ ስው እያጫወተኝ ሰው የሚያሳስበኝ ምንድን ነው ነገሩ ሌት የሚያባንነኝ ልቤ ጎራ ዘሎ አሻግሮ የሚያዬዉ ስሮጥ ስንደረደር ስባዝን የማድረው ምንድን ነው ነገሩ ሰው የምፈልገው



























































ጫካ የምጥሰው ወንዝ የምሻገረው ግንብ እየገነባሁ ደግሞ የማፈርሰው ስሮጥ ስንደረደር ስባክን የማድረው ምን ይሆን ነገሩ ሰው የምፈልገው!?

184

እኔና

የስደት ጉዞዬ

185

ፍቅር ነው ጥላቻ ወይስ የበሽታ ጎራ እምሻገረው ሲሆን ወደማታ እኔስ ግራ ገባኝ እስኪ ምክር ስጡኝ መተኛት አልቻልኩም ሌት እየባነንኩኝ ሀኪም አማከርኩኝ መዳኃኒት ጠጣሁኝ በጣም ከተማረ ሳይካትሪስት ሄድኩኝ ከቤተ ክርስቲያን ለአምላክ ተማፀንኩኝ ምንም አልተሻለኝ እኔንስ ጨነቀኝ መዳህኒት ፈልጉ ይሄን የሚያስረሳኝ ሰው እፈልጋለሁ ከሞት የሚያስነሳ መቃብር ቆፍሮ ያ! መይሳዉ ካሣ አይቀርም ተቀብሮ አገሬ ሰው አጥታ አንገቴን ሰብሬ አስነሱት ያነን ሰው እንዲመለስ ክብሬ ቦታዋ ትመለስ ከፍ ትበል አገሬ ሰው እፈልጋለሁ ጀግናን የሚያስነሳ መቃብር ቆፍሮ አይቀርም መይሳው እንደ ሰው ተቀብሮ ይሄ ነው ሚስጥሩ ሰው የሚያስፈልገኝ መቃብር ቆፍሮ ጀግና ሚያስነሳልኝ ለዚህ ነው ሌተቀን ሰው የሚያስፈልገኝ ሰዉ እፈልጋለሁ ይሄን የሚረዳኝ መቃብር ቆፍሮ ሰዉ የሚያስነሳልኝ













































*አገሬን ባንድነት አስተሳስሮ ዘመን አሻግሮ ለመጭዉ ትዉልድ የሚያስረክብ ራዕይ ያለዉ ሰዉ በማጣቴ ከብስጭት የተነሳ የተገጠመ:

እኔና

የስደት ጉዞዬ

186

ምዕራፍ -12 ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል: ጉዞ: ይህ የአገር ፍቅር በሽታ ጭንቅላቴን እያናወጠኝ ሌተቀን በመብሰክሰክ ላይ እያለሁ ነብሳቸውን ይማር እና ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ስቶክሆልም መጥተው ካረፋበት ሆቴል ያስጠሩኝና ተገናኝተን ስናወራ ስለ አገራችን ሁኔታና ወያኔ እንዴት በተቋም ደረጃ ፕሮግራም ቀርፆ አማራውንና ኢትዮጵያዊነትን እያጠፋ እንደሆነ እሳቸውም ቢያንስ ይሄን በአማራው ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለዓለም ህብረተሰብ ለማሳወቅ (መአአድ ) (AAPO) በሚል ድርጅት መስርተው እየታገሉ እንደሆነ ልብ በሚሰብር ሁኔታ አጫወቱኝ:: እኔም ስለ ሀገሬ በነበረኝ መጨነቅ ላይ የእሳቸው አገላለጽና በዚህ እድሜያቸው አገርን ለማዳንና ሕዝብን ከመጣበት አደጋ ለመታደግ ሲሉ ትግል መጀመራቸው የበለጠ ለሀገሬ ቁጭ ብዬ ከማሰብና ብቻዬን ከመበሳጨት ከሳቸው ጋር ትግሉን ለመቀላቀልና የተቻለኝን ለማድረግ ቃል ገብቼ ተለያዬን:: ቀደም ብለዉ ድርጅቱንበካባቢያችን መስርተዉ ይንቀሳቀሱ ከነበሩት መሰሎቼ ጋር ትግሉን ለማጧጧፍ ተቀላቀልኩ::





በሰዊድንና ባካባቢዉ ካጠናከርን በኋላ በአውሮፓ ደረጃ አገር ወዳዶችን አስተሳስሮ አሜሪካ ካለው ጋር አጣምሮ መስራት በማስፈለጉም ለንደን ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ሁለት ጊዜ በመሰብሰብ ስለድርጅቱ የወደፊት ሂደትና በተለይም አማራ ብሎ በብሔር መደራጀት ወያኔ በቀደደልን መንገድ መሄዱ ኢትዮያዊነትን ለመሸርሸር መሥራት ነው ይህ ደግሞ የወያኔም ምኞት ማስፈጽም ነው በሚል ብዙ ከተወያዬን በኋላ ብዙዎቻችን በብሔር መደራጀቱ ባይስማማንም ልዩነታችን እንደያዝን ተለያዬን::

መጀመሪያ

እኔና

የስደት ጉዞዬ

187

በዚህ ሁኔታ ትንሽ ከፖለቲካዉ ራሴን አግልዬ እንደቆየሁ ግንቦት7 ብሔራዊ የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ ብቅ አለ :: እኔም ፕሮግራማቸውንና ያላቸውን ራዕይ ሳነብ በተለይ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላዉል የፖለቲካ አቋም ያለዉ ድርጅት ሆኖ ስላገኘሁትና የእኔም አቋም በመሆኑ ብዙ ሳላቅማማ ትግሉን ተቀላቀልኩ:: በዚህ ድርጅት ውስጥ መጀመሪያ በስዊድን ቅርንጫፍ ሰብሳቢነት በኋላ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሲታሰሩ እሳቸው የጀመሩትን የትግል ሥራዎች ይዘን በተለይም በአገር ዉስጥ ድርጅቱን አዋቅሮ መሬት የረገጠ ሥራ ለመሥራት ከጓዶቼ ጋር ጋር ባዋቀርነዉ የህቡዕ አደረጃጀት መራራ ትግል ስናደርግ ቆይተን ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መጥተዉ ጠቅላይ ሚንስተር እንደሆኑ በሳቸዉና በኛ ድርጅት መካከል በተደረገ ስምምነት በአስመራና በአገር ዉስጥ የነበሩ አርበኞችን ይዘን እስከገባን ድረስ ለትግሉ የአቅሜን አስተዋጽኦ አድርጊያለሁ::







የአርበኞች ግንቦት7 ትግልን በተመለከተ እያዘጋጀሁ ባለሁትና በቅርቡ በሚወጣዉ ትረካ በስፋት የሚገለጽ ሲሆን በተለይ ከወያኔ የመረጃ መረብ ጋር የነበረውን ትንቅንቅ ወደፊት እመለስበታለሁ:: ለአሁኑ ግን ይህችን የግል የስደት ጉዞዬንና ዉጣ ዉረድ በዚህ እደመድማለሁ:: ይህ ጽሁፍ አገራቸዉንና ጥሩ ኑሮአቸውን እየጣሉ ስደትን እንደ አማራጭ ለሚመኙ ሁሉ የስደትን እዉነተኛ ገጽታ በ መ ጠ ኑ ም ቢሆ ን ተረድ ተዉ በ አ ገ ራቸዉ ያ ለ ብ ዙ ዉጣዉረድ ሰርተዉ ራሳቸዉንና ወገናቸዉን መርዳት የበለጠ እንደሆነም ለማሳየት ነዉ::

እኔና

==ምነው ነዉ

የስደት ጉዞዬ

አምና በሞትኩ :===

ብዙ መንገድ ሳልሄድ ሳልወጣ ከቤቴ እየተባልኩ ጋሼ በእህት ጎረቤቴ በልቼ ስጠግብ ከማር ከወተቴ ተኝቼ ሲሞቀኝ ከነ ባለቤቴ ልጆቼ ጧት ማታ እያሉኝ አባቴ ከወገኖቼ ጋር ስቄ ተጫውቼ ከመሰሎቼ ጋር ከጏዶቼ አምሽቼ ካለው ሰው ስበደር ባጣም ዋስ ጠርቼ በሀገር ታውቄ ተከብሬ እዪኖርኩ እንዲያ እንዳማረብኝ ምነው አምና በሞትኩ ከዛች ከሰፈሬ ከቦታዬ እንዳለሁ እርሻዬን እያረስኩ ከብቴን እያረባሁ ያገሬን ቡቃያ እንጀራ እየበላሁ የገብሱን ኮረፌ በዋንጫ እየጠጣሁ ላሜን በግሬራ ወተቷን እያለብኩ ገና እየተጫወትኩ ተኩሼ ስመታ ሩጬ እያሽነፍኩ በሕዝብ ተመርጬ አስታራቂ እየሆንኩ እንዲያ እንዳማረብኝ ምነው አምና በሞትኩ







































========================

188

እኔና

የስደት ጉዞዬ

ሞላ ይግዛዉ ሽበሽ (አስማረ) ስቶክሆልም- ስዊድን

ይህችን መጣጥፌን በልኬ ቀረፅኳት







እንደዋዛ አርግዤ አምጬ ወለድኳት

189

እኔና

የስደት ጉዞዬ

190

እኔና

የስደት ጉዞዬ

191

Get in touch

Social

© Copyright 2013 - 2024 MYDOKUMENT.COM - All rights reserved.