Data Loading...

Hawarya Flipbook PDF

newfile


258 Views
53 Downloads
FLIP PDF 1.07MB

DOWNLOAD FLIP

REPORT DMCA

06

17

አገር ግንባታ በኢትዮጵያ፤ ከትናንት እስከ ነገ

የኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭነት እውነት ወይስ ተረት?

በአገሪቱ ውስጥ በየአካባቢው የነበሩትን ልማዳዊ የህግ ሥርዓቶች ከማስወገድ ይልቅ በላያቸው ተደርበው አገልግለዋል:: ከአጥቢያ እስከ ዙፋን ፣ ከጭቃ እስከ ምስለኔ በተዘረጋ መዋቅር የሰላም ፣ የፍትህና የግብር ሥርዓት ማስተዳደሪያ ሆነዋል

አውሮፓውያኑ የፈጠራ ታሪካችውን አስተማሩን፤ የነፃ የትምህርት ዕድል ሰጡን:: እኛም ያስተማሩንን አጠናን:: ያንን ለሌሎችም ማስተማር ጀመርን:: የአርኮሎጂ ዕውቀት እየሰፋ ሲሄድ ግን የተማርነው ትምህርት ስህተት ሆኖ ተገኘ

23 የዘር ፍጅት ቀጣዩ የኢትዮጵያ ፈተና?

29 የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ፈተናዎች አንዳንድ ነጥቦች

ሐዋርያ

ሐዋርያ 1ኛ ዓመት ቁጥር 001 ነሐሴ 5 2012

አዲስ አበባ እንዴት ትመራ?

ዋጋ 20.00

የደህንነታችን ዋስትና አንድነታችን እንጂ አመለካከታችን አይደለም በአጣዳፊው የኅብረተሰብ ችግር ላይ አተኩረው መጣር ይኖርባቸዋ። ለሕዝቡ ችግር መድረስና አስፈላጊውን ትብብር በማስቻል ለአደጋው መፍትሔ በማፈላለግ ላይ መትጋት የሚኖርባቸውንም ያህል በዚህ ክፉ የዘመን አጋጣሚ ውስጥ ችግር የወለደው ግኝት ለመፍጠርና ሁኔታውን ወደ መልካም አጋጣሚነት ለመለወጥ አቅዶና ተባብሮ መራመድ ለማንም ሳይሆን ለአጠቃላዩ የሀገሪቱ ሕዝብ ደህንነት ዋስትና ነው። የጋራ ችግር ወይም አደገኛ ገጠመኝ ከሚፈጥራቸው መልካም ነገሮች ውስጥ መተሳሰብንና መረዳዳትን፤ መግባባትንና ፍቅርን ነው። ስለሆነም አሁን ያለንበት መጥፎ አጋጣሚ ከውስጡ መልካም ነገርን እንድናገኝ ከሚያስችሉን ውጤቶቹ አንዱ በመካከላችን ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን ማደስ፤ የእርስ በርስ ጥላቻንና ቁርሾን መሻር፤ የልዩነት ግንብን ማፍረስ … የመሳሰሉ ማኅበራዊ እሴቶቻችንን መልሰን እንድንገነባ ማስቻሉ ነው። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተ ወረርሽኝ በሀገራችን ውስጥ እጅግ ሳስቶ ለቆየው ማኅበራዊ ግንኙነታችንና ሀገራዊ አንድነታችን ፍቱን መድሃኒት ሊሆን ይችላልና በአግባቡ እንጠቀምበት። ማንንም ከማን ሳይለይ በሁላችን ላይ የመጣው ኮሮና ቫይረስ ለያንዳንዳችን የሕይወት ዋስትና እርስ በርሳችን መደጋገፍንና መተሳሰብን ስለሚያስገነዝበን ትንንሹን ልዩነታችን ንቀን በትልቁ ማንነታችን ላይ ሊያጋምደንና አንድ ሊያደርገን ይችላል። ይህ ጊዜ እርቀ ሰላም ለመፍጠር፤ በአዲስ መንፈስና ጉልበት ለመራመድ ልዩ የሆነ አጋጣሚ ይፈጥራል። የእርስ በርስ ጥርጣሬ፣ ጥላቻና ግጭት የጋራ ውድቀትን ያስከትል እንደሆነ እንጂ አሸናፊ የሚያደርገው አካል ወይም የኅብረተሰብ ክፍል አይኖርም፡፡ አደገኛውን የኮሮና ወረርሽኝንም ሆነ በአገራችን የሚታየውን ልሂቅ ሠራሽ የፖለቲካ በሽታ መፍታት የሚቻለው በጋራ በመቆም ብቻ ነው፡፡ ያለንበት ሁኔታ በውጭ ሀገሮች ነዋሪ የሆነውንና ከሀገሩ ጉዳይ ሳይለይ በፖለቲካው እሰጥ አገባ ትግል ተጠምዶ የቆየው ማኅበረሰብ በትውልድ ሀገሩ ላይ መንፈሱን ጣል አድርጎ የበኩሉን አስተዋጽዖ ሊያደርግ የሚችልበትን ሁኔታ አግባብነት ባለው የግንኙነት ትሥሥር መቆራኘት ይችል ዘንድ የሚጋብዝ ነው፡፡ ሰፋፊ ሀገራዊ ምክክሮችን ለማካሄድና እሳቢዎችን ለመዘርጋት የልሂቃን ልብና አእምሮ የሚገጣጠሙበት ወቅት ነው። የግስጋሴያችን ሀ-ሁ ሰላማችንና በነጻነት ራሳችን ብቁ ለማድረግ ያለን የጋራ ፍላጎት በመሆኑ መከባበርና ፍቅር በሰፈነበት ተሐድሶ ታንጸን እንድንነሳ ሐዋርያ የበኩሏን አስተዋጽዖ ለማድረግ እንደገና ተጠምዳ “ሱብ!” ብለች።

ሐዋርያ

ምኞትና ፍላጎት ደርሻቸው ለየቅል ቢሆንም ሰፍረው የሚከለሉበት ወሰንና ተጉዘው የሚደርሱበት ዲካ የላቸውም። ኅብረተሰብ በየዕድገቱ ደረጃ እየፈፀመ ለሚያልፋቸው ክንዋኔዎች የሽረት ሽረት ሕግ ተውኔት ሆነው ተከታታይና አዳዲስ ክስተት በመሆን ለቀጣዩ ለውጥና ዕድገት ቀስቃሽና ጽንሥስ እየሆኑ ሌላ ብዙ አዳዲስ ምኞቶችንና ፍላጎቶችን ሲያፈልቁ ይኖራሉ። ይሁን እንጂ በግል ስሜትና አመለካከት ተጋርዶ በምኞትና በፍላጎት ፈረስ ሲጋልቡ አዙሮ ማየትና ከፊት የሚጋረጥን አደጋ አስቀድሞ መመርመር እየቀረ “አያ በሬ ሆይ ሳርሳሩን ስታይ፤ ገደል…” የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው። በምኞት አውሊያ ፈረስና ሚዛኑን ባልጠበቀ የፍላጎት አራራ ዞር ብሎ ሳያዩ ሽምጥ መጋለብ ድንገት ዳገቱ ላይ ክምብል ደፋ ሊያደርግ ስለሚችል፤ ቢያንስ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ቦታ ላይ ዞር ብሎ መመልከትና መርምሮ መራመድ ያስፈልጋል። ዛሬ የደረስንበት የጊዜ ገጠመኝም ይህን የሚያስገነዝብ ነው፤ የሰው ልጅ አድጌ ተመንድጌያለሁ ብሎ ህዋን ክንፍ ሠርቶ ሲዳውር ከኋላው ሃፍረቱን ያልከደነ ደካማ ፍጡር መሆኑን ህቅ እስኪለው ማወቅ ችሏል። ዛሬ ላይ መላው የዓለም ኅብረተሰብ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-፩፱) በተባለ ተውሳክ ተጠምዷል። ሀገራችን ኢትዮጵያም እንደ አንድ ግዛታዊ የዓለም ክፍል ጽዋውን አብራ በመጎንጨት ላይ ናት። ከግዛቷ ውጭ በተለያዩ ምክንያቶችና አጋጣሚዎች በሁሉም የዓለም ገጽ ላይ የተበተኑ ልጆቿም በያሉበት የምጻቱ ተካፋዮች ሆነዋል። ከሀገራቸው ርቀው በተለይም በአፍሪካና በዐረብ ሀገሮች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችና ሠራተኞች ወትሮውንም እንደ ትርፍ ሰው ተቆጣሪዎች ነበሩና ዛሬ ደግሞ በኮቪድ፩፱ ወረርሽኝ ዘመን ከተጠጉበትና ላባቸውን አፍስሰው ከሚሠሩበት ኅብረተሰብ ውስጥ እንደ ብጣሪ ተንጓለው ዳር የሚጣሉበት ጊዜ ነው። የወረርሽኙ ጦስ ለሚከተሉት ዓመታት በምጣኔ ሀብት ሥሪቱ ላይና በማኅበራዊ የግንኙነት ትሥሥሩ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ምስቅልቅሎሽ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። እያንዳንዱ ሀገር በሩን እየዘጋ ዜጋዎቹን የሚንከባከብበትና ተወላጆቹም በነፍስ ወከፍ ከወረርሽኙ ለመከላከልና ራሳቸውን ለመጠበቅ ድርሻ እንዲኖራቸው ኃላፊነት በመውሰድ የሚረባረቡበት ጊዜ ነው። የመንግሥትና ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅኝት፤ የምሁራንና የሕዝቡ ግንኙነት ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ተባብሮ በመሻገር ላይ ያተኮረ እንዲሆን ጊዜው የግድ ይላል። ምሁራንና በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስተዳደሮች ከተቀናቃኝ አቻ የፖለቲካ አካሎች ጋር አለመቻቻልን አቻችለው ወደተሻለ ቀን ለመድረስ

ማኔጅንግ ኤዲተር - ሙሉቀን ሙጬ ዲዛይን ሀብ

3

አዲስ አበባ እንዴት ትመራ?

ዘላለም እሸቱ

አዲስ አባባ ትልቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሆናለች:: በኦሮሞ ብሔርተኞችና በሌሎች መሀከል ሰፊ ልዩነቶች እየተነሱና ከተማዋ የግጭት ማዕከል የመሆን ዕድል እንዳላት እየታየ ነው:: በእርስዎ አስተያየት በከተማዋ ላይ የሚነሱ መሠረታዊ የልዩነት አጀንዳዎች ምን ምን ናቸው? ከተማዋ የግጭት ማዕከል እንዳትሆንስ ምን ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል? የፌደራል ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች የዋና ከተማ ጉዳይ በውዝግብ የተሞላ ነው:: ይህ ውዝግብ ለዋና ከተማነት የሚሆነውን ቦታ ከመምረጥ ጀምሮ ዋና ከተማው የሚተዳደርበት መንገድና የከተማው የወደፊት ዕድገት ጋር ሊያየዝ ይችላል:: ይህ ውዝግብ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ቤልጀም፣ ደቡብ አፍሪካ ጨምሮ በአብዛኞቹ ፌደሬሽኖች ላይ ተከስቷል:: አሁን አዲስ አበባ ላይ የሚታየው ውዝግብም መታየት ያለበት ከዚህ አንጻር ነው:: በእኛ ሁኔታ የሚታየውን ችግር የሚለየው ውዝግቡን ለመፍታት የምንሄድበት መንገድ ሳይንሳዊ አለመሆኑና እንዲያውም ውዝግቡን የሚያባብስ መሆኑ ብቻ ነው:: ከዋና ከተማ ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ውዝግብ መነሻው በአብዛኛው ሦስት ፍልጎቶችን ማስታረቅ አለመቻል ነው:: የመጀመሪያው የፌደራል መንግሥቱ ፍላጎት ሲሆን ይህም የፌደራል

4

መንግሥቱ ከማንም ተጽዕኖ ነጻ በሆነ መልኩ ዋና ከተማዋን በማሳደግ፤ ከተማዋ ብሔራዊ ሚናዋን (National Role) እንድትወጣና ብሔራዊ ምልክት (National Symbol) እንድትሆን ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ይገለጻል:: ኹለተኛው ፍልጎት የዋና ከተማው ኗሪዎች ፍላጎት ሲሆን ይህም የከተማው ሕዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር በሚያደርገው ጥረት ይገለጻል:: በሦስተኛነት የፌደራሽኑ አባል በሆኑ አካላት/ክልሎች የሚንጸባረቀው ፍልጎት ሲሆን በተለይ በጅኦግራፊ ወይም በታሪክ ከዋና ከተማው ጋር ግንኙነት ያላቸው/ አለን ብለው የሚያስቡ ክልሎች የተለያዩ ፍልጎቶችን ሊያነሱ ይችላሉ:: እንደ ቤልጀም (ብራሰልስ) ባሉ ፌደሬሽኖች ደግሞ ከአውሮፓ ኅብረት መቀመጫነት ጋር በተያያዘ የሚነሳ አራተኛ ፍልጎት ሊኖር ይችላል:: የነዚህ ፍላጎቶች አለመጣጣም አንዳንዴም መጣረስ ነው እንግዲህ ለውዝግብ መነሻ የሚሆነው:: በእኛ ሁኔታም በአዲስ አበባ ላይ የሚታየው ውዝግብ መነሻው ከዚህ የተለየ አይደለም:: በአዲስ አበባ ላይ የሚንፀባረቁ ፍልጎቶችን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል:: በአንድ በኩል ጅኦግራፊን/ታሪክን በመጥቀስ በአዲስ አበባ ላይ ጫፍ የረገጠ ብሔርተኛ ቡድን የሚያነሳው የባለቤትነት ጥያቄ ይታያል:: አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት የሚል በይዘቱ የፌደራል መንግሥት ሊይዘው የሚገባውን ፍልጎት የሚያንጸባርቅ ሐሳብም የሚሰማ ሲሆን አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች

ናት የሚል በዋናነት የአዲስ አበባ ኗሪዎችን ፍልጎት የሚያንጸባርቅ ሐሳብም ጎላ ብሎ እየተሰማ ነው:: እነዚህ ፍልጎቶች በፌደራሊዝም አውድ ሲታዩ የአዲስ አበባ ሁኔታ (status) ምን መሆን አለበት ለሚለው ጥያቄ የሚኖራቸውን መልስ የተለያየ እንደሚሆን መታወቅ አለበት:: ለምሳሌ አዲስ አበባ የእኛ ናት የሚሉና በአዲስ አበባ ላይ የባለቤትንት መብት የሚያነሱ አካላት ዋነኛ ፍልጎት የአዲስ አበባ ሁኔታ እንደ ኦትዋ (ካናዳ) እንዲሆን ማድረግ ነው:: በዚህም መሠረት አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ (A City in a Member State Model) እንድትሆንና በኦሮሚያ ሥር እንድትተዳደር ይፈልጋሉ:: አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት የሚለው ሐሳብ የአዲስ አበባ ሁኔታ እንደ ዋሽንግተን ዲሲ እንዲሆን የሚፈልግ፣ አዲስ አበባን የፌደራል ግዛት የሚያደርግ (A Federal District Model) መሆኑን መረዳት ይገባል:: አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች የሚለው ሐሳብ አዲስ አበባን እንደ ብራሰልስ (ቤልጀም) አንድ የፌደሬሽኑ አባል ክልል እንድትቆጠርና ኗሪው እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር (A Member State Model) የመፈለግ አዝማሚያን የሚሳይ መሆኑን መረዳት ይቻላል:: ስለዚህ አዲስ አበባን በተመለከተ በሚነሱ ሐሳቦች ጀርባ አዲስ አበባ በየትኛው ሞዴል ትተዳደር የሚለው ትልቅ አጀንዳ ያለ መሆኑን

ማወቅ ግድ ይላል:: የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ሲቪክ ማኅበራት አቋም ሲይዙም ሆነ መግለጫ ሲያወጡ ጉዳዩን በዚህ አውድ ሊያዩት ይገባል:: እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ እያንዳንዱ ሞዴል የራሱ የሆነ ጥንካሬና ድክመት ያለው መሆኑ ነው:: ለምሳሌ እነ ዋሽንግተን (አሜሪካ)፣ አቡጃ (ናይጀሪያ) የሚከተሉትን Federal District Model የሚባለውን ብናየው ፌደራል መንግሥቱ በዋና ከተማው ላይ ሰፋ ያለ መብትና ቁጥጥር እንዲኖረው የሚያደርጉ ሲሆን ፌደራል መንግሥት ሥራውን በነጻነት እንዲሰራ ከማድረጉም በላይ ዋና ከተማው የሁሉም ሕዝብ እና ክልሎች ማዕከል እንዲሆን ያደርጋል:: ይሁን እና የከተማውን ሕዝብ ራስን የማስተዳደር መብት በተወሰነ መልኩ የሚገድብበት አጋጣሚ ይስተዋላል:: እነ ብራሰልስ (ቤልጄም) የሚከተሉት A Member State Model ዋና ከተማው ማንኛውም ክልል ያለውን መብት ያለው ሲሆን በተጨማሪ የዋና ከተማነት ሚናም እንዲኖረው ያደርጋል:: የከተማውን ኗሪ ራስን የማስተዳደር መብት በማረጋገጥ በኩል የተሻለ ቢሆንም የፌደራል መንግሥትን እንቅስቃሴ ይገድባል፤ እንዲሁም እንደዋና ከተማ እያገለገለ ያለው ክልል ያልተገባ ተጽዕኖ በመፍጠር በፌደራሽን አባል ክልሎች መከካል እኩል የሆነ ቁመና እንዳይኖር ስለሚያደርግ በሌሎች አባለት ዘንድ ቅሬታ ምንጭ ይሆናል:: በኹለቱም ሞዴሎች ከተሞቹ እያደጉ ሲመጡ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ግጭት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ:: እነ ኦትዋ (ካናዳ) የሚከተሉት A City in A Member State Model ዋና ከተማውን በሚገኝበት ክልል ሕግ እንዲተዳደር ስለሚያደርግ የፌደራል መንግሥቱን ዋና ከተማው ለሚገኝበት ክልል ጥገኛ ያደርገዋል:: የፌደራል መንግሥቱ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በክልሉ ይሁንታ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የፌደራል መንግሥቱን ጥንካሬ ይጎዳዋል:: እንዲሁም ዋና ከተማው የሚገኝበትን ክልል ባህል፣ ቋንቋ ብቻ እያንጸባረቀ በሌሎች ፌደራሽን አባላት ላይ ቅሬታና ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋል:: የዚህ ሞዴል ዋነኛ ጥቅም ከዋና ከተማ መስፋት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ማስቀረት ብቻ ነው:: እነዚህን የፌደራል መንግሥቱን፣ የከተማውን ኗሪና የፌደሬሽን አባላትን (ክልሎችን) ፍልጎቶች ለማስታረቅ የፌደራል ሥርዓት ሲቀረጽ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው አካላት ድርድር በማድረግ የደረሱበትን አስታራቂ ሐሳብ ሕገ መንግሥት ላይ በማስፈር በዋና ከተማ ዙሪያ ለሚነሱ ውዝግቦች መቋጫ/አመላካች መንገድ ያስቀምጣሉ:: የዋና ከተማውን ሁኔታና ሞዴል፤ የዋና ከተማውን ስፋት፤ ከፌደራል መንግሥቱና ከክልሎች በተለይ አጎራባች አካባቢዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያመላክታሉ:: ከዚህ አንጻር ሲታይ የኢፌደሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 አንዳንድ ነገሮችን በለሆሳስ ማለፉ አሁን ለሚታየው ውዝግብ አስተዋጽዖ አድርጓል ማለት ይቻላል:: በሽግግር መንግሥት ወቅት አዲስ አበባ እንደ አንድ ክልል (ክልል 14) ሆኖ የነበረ ሲሆን አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ይህን የአዲስ አበባ ሁኔታ (A Member State Model) ቀሪ አድርጎታል:: አዲስ አበባ የፌደራል ሥርዓት ከመመሥረቱ በፊት በዋና ከተማነት የነበረ በመሆኑ፤ አዲስ አበባ አሁን ያለው ኦሮሚያ ክልልም ሆነ አማራ ክልል ከመኖራቸው በፊት

የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት ከማለት ባለፈ ፌደራል መንግሥት በአዲስ አበባ መሬት ላይ ባለቤት መሆኑን፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሕግ የማውጣት ሙሉ ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ በግልጽ አለማስቀመጡና ጉዳዩን በገደምዳሜ ማለፉ አሁን ላለው ችግር አስተዋጽዖ አድርጓል:: በአጭሩ ሕግ አውጭዎቹ ያሰቡትን Federal District Model በግልጽ ሕገ መንግሥቱ ላይ አለማስቀማጣቸው አሁን ለሚታየው ውዝግብ በር ከፍቷል::

ሕገ መንግሥቱ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት ከማለት ባለፈ ፌደራል መንግሥት በአዲስ አበባ መሬት ላይ ባለቤት መሆኑን፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሕግ የማውጣት ሙሉ ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ በግልጽ አለማስቀመጡና ጉዳዩን በገደምዳሜ ማለፉ አሁን ላለው ችግር አስተዋጽዖ አድርጓል

የነበረ ከተማ በመሆኑ የትኛውም ክልል የባለቤትነት መብት ሊያነሳበት አይችልም:: “ለኋላም ኋላ ስላላው” እንደ ሕዝብ እኔ የአዲስ አበባ ቀደምት ሕዝብ ነኝ በሚል ታሪክን መሠረት አድርጎ የሚቀርብ ክርክር ውኃ የሚቋጥር አይደለም:: በተለይ ኢትዮጵያ በውስጣዊ ግፊት ምክንያት ከአሕዳዊ ሥርዓት ወደ ፌደራላዊ ሥርዓት የተቀየረች አገር በመሆኗ (Holding together Federation) የትኛውም ክልል በአዲስ አበባ ላይ የባለቤትነት ጥያቄ ሊያነሳ አይችልም:: ይህ ዓይነት ጥያቄ በዋናናት በራሳቸው ሉዓላዊ የነበሩ ግዛቶች ተሰባስበው አንድ ፌደሬሽን ሲፈጥሩ (Coming Together Federations) የሚነሳ ጥያቄ ሲሆን እነዚህ በራሳቸው ሉዓላዊ የነበሩ ግዛቶች ለዋና ከተማነት የሚሆን ቦታ አዋጥተው ይሰጣሉ ወይም አንዱ ግዛት በፈቃደኝነት ቦታ ይሰጣል ወይም በአንዱ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ከተማ ለዋና ከተማነት ይመረጣል:: የአዲስ አበባ ሁኔታ ከዚህ ሁሉ ውጭ መሆኑ እየታወቀ ሕገ መንግሥቱ አዲስ አበባ

በመቀጠል ስለ ልዩ ጥቅም ያለው ያልተስተካከለ አረዳድ በራሱ ችግር ፈጥሯል:: ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት A Federal District Model እና A Member State Model የሚከተሉ አገሮች ከከተማው ማደግ ጋር በተያያዘ ከጎረቤት ክልሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው አይቀርም:: ለዚህም የተለያዩ መፍትሔዎችን ያስቀምጣሉ:: የኢፌደሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 ስለ ልዩ ጥቅም ያስቀመጠው ድንጋጌ ከዚህ አንጻር መታየት ይኖርበታል:: እዚህ ላይ ግን ኹለት ነገሮችን ማስመር ያስፈልጋል:: የመጀመሪያው ልዩ ጥቅም የሚሰጠው ለምንድን ነው? ልዩ ጥቅም ምን ምን ነገሮችን ያካትታል? የሚለው ወሳኝ ነጥቦች ናቸው:: የመጀመሪያው ኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም የሚያገኘው የአዲስ አበባ መሬት ባለቤት (ownership) ስለሆነ አይደለም:: ኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም የሚያገኘው የአዲስ አበባ ጎረቤት ስለሆነ ብቻ ነው:: ስለዚህ የልዩ ጥቅም መነሻው ጅኦግራፊ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል:: ልዩ ጥቅም የሚባለው ምንምን ነገሮችን ያካትታል የሚለውም በሚዛኑ መታየት አለበት:: አዲስ አበባ ለኦሮሚያ ክልል እዳ ብቻ አይደለችም፤ ጸጋም ጭምር ናት:: ለምሳሌ ከሌሎች ክልል መንግስታ በተለየ መልኩ የኦሮሚያ መንግሥት መቀመጫ አዲስ አበባ ላይ መሆኑ በራሱ እንደ ልዩ ጥቅም መታሰብ አለበት:: በአዲስ አበባ ማደግ ጋር በተያያዘ በዙሪያው ለሚገኙ ኗሪዎች የሚፈጠረው የሥራ ዕድል፤ የመሠረተ ልማት ግንባታ፤ የትምህርትና ጤና አገልግሎት አቅርቦት እንደ ጥቅም መቆጠር አለበት:: እዚህ ጋር አብሮ መታየት ያለበት የልዩ ጥቅሙ ተቋዳሽ የሚሆነው ማንኛውም የኦሮሞ ብሔር አባል ሳይሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኘው፣ ከከተማው መስፋፋት ጋር በተያያዘ ተጽዕኖ ያረፈበት ማኅበረሰብ/ ግለሰብ ብቻ መሆን ይገባዋል:: ስለዚህ የልዩ ጥቅሙን ወሰን እና መነሻ ምክንያት በሚገባ መረዳት ያስፈልጋል:: በአጠቃላይ የአዲስ አበባ ጉዳይን ለመፍታት ችግሩን በፌደራሊዝም አውድ በማየትና የሌሎች አገሮችን ልምድ በማጥናት የሰለጠነ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል:: ከላይ ያየናቸውን የፌደራል መንግሥቱን፤ የአዲስ አበባን ኗሪና የፌደሬሽን አባላትን (ክልሎችን) ፍልጎቶች ለማስታረቅ ትልቁን ስዕል፣ ይኸውም የሕዝብ ተጠቃሚነትንና ከየትኛውም ክልል ሆነ ቡድን ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፌደራል መንግሥት እንዲኖር ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ ውይይት አስፈላጊ ነው:: ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሌሎች ፌደራል አገሮች ኹለተኛ ዋና ከተማ ማሰብም ይገባል:: ከዚህ አንጻር የአማራ ብልጽግና ደብረ ብርሃን እንደ ኹለተኛ ዋና ከተማ በእጩነት ማቅረብ አለበት:: ይህ በሚሆንብት ጊዜ አማራ ክልልም ሆነ የፌደራል ሥርዓቱ በአጠቃላይ ተጠቃሚ ይሆናሉ::

5

አገር ግንባታ በኢትዮጵያ፤ ከትናንት እስከ ነገ ቴዎድሮስ ኀይለማርያም (ዶ/ር)

ንድፈ-ሐሳባዊና ታሪካዊ መግቢያ አገር ግንባታ ምንድነው ? በመጀመሪያ “አገር ግንባታ” (nation-building) የሚለው እሳቤ በአማርኛው አጠቃቀሙ የብሔርተኝነት ሦስት አዕማዶች ከሆኑት አገር፣ ሕዝብና መንግሥት በአንዱ ላይ ብቻ የቆመ ይመስላል:: ስለዚህም ለእንግሊዝኛው የተሻለው አገላለጥ “ብሔር ግንባታ” ነበር:: ይሁን እንጂ አገር ያለ ሕዝብና መንግሥት፤ ሕዝብ ቢያንስ በምኞት ደረጃ ያለ አገርና መንግሥት፤ መንግሥት ደግሞ ያለ አገርና ሕዝብ የተሟላ ትርጉም አይሰጡም:: የአገር ግንባታም ሊኖር አይችልም:: ስለዚህም አገር ግንባታ ስንል ግዛታዊ ብቻ ሳይሆን ሕዝባዊና መንግሥታዊ መልኮችንም ያካተተ የአገራዊ ብሔር ግንባታ ሂደት መሆኑን እንረዳለን:: ሁለተኛ “ግንባታ” የሚለው የምህንድስና እሳቤ

በተለምዶ ታቅዶና ታልሞ ብሔራዊ ማንነት፣ አንድነትና ዘላቂነት የመፍጠርና የማደራጀት ተግባር የሚል አንድምታ ስላለው ጥንቃቄ ያስፈልገዋል:: ምክንያቱም በግንባታው ተግባር ላይ ያልታሰበባቸው ክስተቶችና የጋራ ተሞክሮዎችም የበኩላቸውን ሚና ስለሚጫወቱ:: ስለዚህም አገር ግንባታ ከዜሮ የሚጀምር ወይም ከሌላ ማኅበራዊ ቅርፅ አዲስ አገር የመፍጠር ጉዳይ ብቻ አይደለም:: እንዲያውም በአብዛኛው በነባር ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችና ማንነት ላይ የሚመሠረት የጥራትና ይዘት ማሻሻል ሂደት ሲሆን ይታያል:: ሦስተኛ አገራዊ ብሔር ወይም ብሔራዊ መንግሥት ግንባታ ፖለቲካዊ ርዕዮትን ከባህላዊ ንቅናቄ ያጣመረ ሂደት ነው:: የብሔር አመሰራረት አንድ ሕዝብ ከጋራ ታሪክ፣ ነባራዊ ሁኔታና በተለይም ከመፃኢ እጣፈንታው ጋር በሚኖረው ኅሊናዊ ቁርኝት ይወሰናል::1 ማለትም ብሔር ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ልሣናዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ የመሳሰሉት

ነባራዊ ግንኙነቶችና እነዚህ በጋራ ንቃተ ኅሊና ውስጥ በሚፈጥሩት ሐሳባዊ ነጸብራቅ ጥምረት የተዋሐደ ማኅበረሰብ ነው::2 ብሔራዊ መንግሥታት በኀይል ቢመሠረቱም በአስተማማኝና ዘላቂ መሠረት ላይ የሚቆሙት በቂ ሕዝባዊ ተቀባይነት ሲያገኙ ነው::

መንግሥት ግንባታና ብሔር ግንባታ የአገር ግንባታ ፖለቲካዊና ባህላዊ ሂደቶች በተግባር የተወሳሰቡና የማይነጣጠሉ ናቸው:: ሆኖም ከትንታኔ አኳያ በሁለት ከፍለን በመንግሥት ግንባታና በብሔር ግንባታ ዘርፎች ልናያቸው እንችላለን:: መንግሥት ግንባታ ለአገር አስተዳደር የሚያገለግሉ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊና ሥርዓታዊ መዋቅሮች ላይ ያተኩራል:: በተለይም ወታደራዊና ኤኮኖሚያዊ ሀብቶችን የማማከል፤ የመሬት ስሪትና የግብር

1. T.H. Eriksen, Nationalism and Ethnicity (London: Pluto Press, 1993) ,p.12. 2. Miroslav Hroch, “From National Movement to the Fully-formed Nation: The Nation-building Process in Europe,” in Balakrishnan Gopal(ed), Mapping the Nation (New York and London:Verso,1996),p.79.

6

ሥርዓት የመዘርጋትና የመቆጣጠር፤ የፍትሕና ሕግ ሥርዓት የማቆምና የማስከበር ተግባራትን ያጠቃልላል:: በሌላ በኩል ብሔር ግንባታ አገራዊ ማንነትና ሥነ ልቡናዊ አንድነት ላይ የሚያተኩር ሂደት ነው:: ለዚህም ሲባል የጋራ ርዕዮተ ዓለም መንደፍ፣ የጋራ ሥርዓተ ትምህርት፣ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶችንና ትዕምርቶችን ማደራጀት፣ ማበልፀግና መጠበቅን ያካትታል:: የተሟላ የአገር ግንባታ የሁለቱም የመንግሥትና የብሔር ግንባታ ድምር ውጤት ነው::3 በየዘመኑ የመንግሥት አቋም መጠናከርና ተግባራዊ መስፋፋት ለብሔርተኝነት መፈጠርና መጎልበት ወሳኝ ነው:: መንግሥት በጦርነትም ሆነ በሰላም የአገር ግንባታ መሪ ተዋናይ ይሆናል:: ለብሔራዊ ጉዳዮች አጠቃላይ ማዕቀፉን በማመቻቸትና ዘውጋዊ ወይም ብሔረሰባዊ ድንበሮችን በመወሰን ረገድ ብርቱ ሚና ይጫወታል::4 ስለዚህም ማናቸውም ጥናት በመንግሥታዊ ርዕዮቶች፣ ሥርዓቶች፣ ተቋማትና ሕግጋት ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት:: ሆኖም እይታችን የሚሟላው እነዚህ ላዕላይ ኀይሎች በማህበረሰቦች አቋም ላይ የሚያስከትሉትን ታህታይ ውጤቶችና ተጽዕኖዎች በሚዛናዊነት ሲያዋሐድ ነው:: በአጠቃላይ አገር ግንባታ ነባራዊና ኅሊና፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ፣ መንግሥታዊና ሕዝባዊ መልኮችን ያቀናጀ ሂደት ነው:: ይህንን ሰፊና ውስብስብ ሂደት ለመመርመር ታሪካዊ ሥነ-ዘዴ ምቹ አቀራረብ ነው:: የዚህ አንዱ ምክንያት እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ብሔራዊ መንግሥታት ታሪካዊ ማኅበረሰቦች መሆናቸውና ታሪክ በህልውናቸው ላይ ማዕከላዊ ሚና ስለሚጫወት ነው:: ሌላው ምክንያት ታሪካዊ እይታ በመንግሥትና ብሔር ግንባታ መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነት፣ እንዲሁም የሁለቱን ሂደቶች መስተጋብር በረዥሙ በመመርመር የአገር ግንባታውን ለውጥና ቀጣይነት አሟልቶ ለመገንዘብ ስለሚያስችል ነው:: በዚህ ጥናት የኢትዮጵያን ረዥም የአገር ግንባታ ሂደት ለመመርመር የመንግሥታዊና ብሔራዊ ግንባታ ዘርፎችን ያቀናጀ የትንታኔ ማዕቀፍ እንጠቀማለን:: ለዚህም ሲባል ከላይ በቀረበው አጭር የብሔርተኝነት ንድፈ ሐሳባዊ ግንዛቤ መሠረት አራት የግንባታው አዕማዶችን ለይቶ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል:: እነዚህም 1) የጋራ ርዕዮተ ዓለም፤ 2) ሕዝባዊ ባህል፤ 3) የጋራ ተቋማትና መዋቅሮች፤ 4) የጋራ ሕግጋት፣ ወግና ልማዶች ናቸው:: በቅድሚያ እነዚህ በታሪክ ውስጥ ያለፉበትን ውጣ ውረድ በመከለስ አጠቃላዩን አገራዊ ምስል ለማግኘት እንሞክራለን::

ከታሪክ አንጻር ብዙውን ጊዜ መንግሥት ግንባታ ከብሔር ግንባታ ሲቀድም ይታያል:: በአገር ግንባታው ሂደት መንግሥትና ሕዝብ የሚጫወቱት ሚናም እንደየዘመኑ ተጨባጭ ሁኔታ ሊለያይ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ ይዘቱ ሊዋዥቅ ይችላል:: በመንግሥት ግንባታ ረገድ የሚከሰቱ ውጣውረዶች በብሔር ግንባታውም ላይ አዎንታዊም አሉታዊም ተጽዕኖ ያሳድራሉ:: ለምሳሌ መንግሥቱ በውስጣዊ ሽኩቻዎች ሊዳከምና ሊከስም፣ አልፎም በቅኝ አገዛዝ ሥር ሊወድቅና ሊጠፋም ይችላል:: በተጓዳኝ የብሔሩ ባህላዊና ኅሊናዊ ህልውና እነዚህን ተግዳሮቶች በመቋቋም ፀንቶ ሊዘልቅ፣ አለያም ሊበረዝና መልኩን ሊቀይር ወይም ከናካቴው ሊጠፋም ይችላል::



ጥናታችን ዓላማ ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ከመፈተሽ በላይ ከተመክሯችን ለነገውም የአገር ግንባታ ጥረት የሚበጀንን ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ ነው:: ስለዚህ የኢትዮጵያ አገር ግንባታ አራቱ አዕማዶች የነበራቸውን ድምር ፋይዳ ወይም የግንባታውን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ ስኬትና ውድቀት የምንገመግምበት አጠቃላይ መስፈርት ያስፈልገናል:: የማንኛውም አገራዊ ብሔርተኝነት ግብ የመንግሥቱን ሕጋዊና ፖለቲካዊ ድንበር ከብሔሩ ባህላዊና ሥነ ልቦናዊ ድንበር ለማጣጣምና የጋራ አቅጣጫ ለማስያዝ ነው:: ይህንን ግብ ታሳቢ በማድረግ የብሔርተኝነት ጥናት ምሁራን የአገር ግንባታን ባሕርይ ከሚመዝኑባቸው ዐበይት መስፈርቶች መካከል ሂደቱ በተለይ 1) ማንነት፤ 2) አንድነት፤ 3) ዘላቂነት ከመፍጠሩ ላይ እናተኩራለን::5

የኢትዮጵያ አገር ግንባታ ታሪካዊ እርከኖች የኢትዮጵያን የአገር ግንባታ ሂደት ከታሪክ አንጻር ለመረዳት የየራሳቸው ልዩ ባሕርያት ባላቸው በሁለት ዐበይት እርከኖች መክፈል ያስፈልጋል:: የመጀመሪያው የታሪካዊት ኢትዮጵያ (historic Ethiopia) ወይም ብሔረ ኢትዮጵያ የታሪክ አንጓ በቅጡ ከማይታወቀው ጥንታዊ መነሻው ጀምሮ የዘመነ መሳፍንት እስካከተመበት እስከ 19ኛው ምዕት መንፈቅ ድረስ ይዘረጋል:: የዚህ ቅድመ ዘመናዊና ልማዳዊ አገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ሃይማኖታዊነት ነው:: ሃይማኖት የማኅበረሰቡ ሕይወት አስኳል የሆነበትና የኢትዮጵያዊነትን ተፈጥሮ፣ ህልውናና ራዕይ በመለኮታዊ ፍልስፍና የሚረዳና የሚተረጉም ነው:: ሁለተኛው ከአፄ ቴዎድሮሥ ንግሥ የሚነሳው የዘመናዊት ኢትዮጵያ የታሪክ አንጓ የአውሮፓ የቅኝ

ተስፋፊነት ስጋት ካስከተለው የዘመናዊነት ምኞት ጋር የተከሰተ ሲሆን፣ የ“አዲሲቱ ኢትዮጵያ” (ተሃደስቲ ኢትዮጵያ) እሳቤ ብለን ልንሰይመው እንችላለን:: በሃይማኖታዊነት ፋንታ ዓለማዊነትን የብሔራዊ ሕይወት ማዕከል ያደረገው ይህ የአገር ግንባታ ሂደት ኢትዮጵያዊነትን ከፖለቲካዊ ርዕዮት አኳያ የሚረዳና የሚተረጉም ነው:: በመጤና እንግዳ ፍልስፍና፣ በአዲስ አስኳላ አፈራሽ ልሂቃዊ መደብ፣ ለአዲስ ቁሳዊ ሥልጣኔ የተሰለፈ ነው:: በታሪካዊትና በዘመናዊት ኢትዮጵያ መካከል ያለውን ዝምድና አስመልክቶ በታሪክ ምሁራን መካከል የተራራቁ አመለካከቶች ይንፀባረቃሉ:: ለአንዳንዶች እነዚህ ፍፁም አንድ ሲሆኑ፣ በሌላኛው ጥግ ደግሞ ሁለቱ ኢትዮጵያዎች በጭራሽ አይገናኙም:: በዚህ ጥናት ውስጥ ለማሳየት እንደሚሞከረው እነዚህ ሁለት የአገር ግንባታ እርከኖች ከመንግሥት ግንባታም ሆነ ከብሔር ግንባታ አኳያ መሠረታዊ ልዩነቶች ቢኖሯቸውም በበርካታና ውስብስብ ድሮች የተቆራኙ፣ የቀጣይነትና ለውጥ ነፀብራቆች ናቸው:: ስለዚህ “ለወደፊቱስ ምን ይበጀናል?” የሚለውን ጥያቄ በታሪክ ተመክሮ ለመመለስ ሁለቱን ሂደቶች በንፅፅር መመርመር የግድ ይሆናል::

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት የጥናታችን ዐቢይ ትኩረት የሆነው የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ ከዜሮ አልተነሳም:: ከቀድሞው ብሔረ ኢትዮጵያ የሚለዩትን መሠረታዊ ባሕርያት ያገኘው ነባሩን በማሻሻል፣ ከባዕድ በማዳቀል፣ ከናካቴው አስወግዶ በመተካት ነው:: ከዚህ አልፎም አዳዲስ ርዕዮቶች፣ ባህሎችና እሴቶ፣ ተቋማትና ሥርዓታት በመፍጠር ጭምር ነው:: ይህንን ሰፊ የለውጥና ቀጣይነት ሂደት ከአራቱ የአገር ግንባታ አዕማዶች አኳያ በየተራ እንመርምር:: 2.1. ከጋራ ርዕዮተ ዓለም አንፃር የብሔሮችን ማንነትና ታሪክ ለመረዳት ዋናው ቁልፍ ርዕዮተ ዓለማቸው ነው:: ምክንያቱም ርዕዮታቸው አጠቃላይ ፍጥረተ ዓለሙን የሚተረጉሙበት፤ ማኅበራዊና ኅሊናዊ ድንበሮቻቸውን የሚደነቡበት፤ የገዛ ውልደታቸውን፣ ዕድገታቸውንና ተስፋቸውን የሚከትቡበት ፍኖተ ካርታ በመሆኑ ነው:: ደረጃውና ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ሁሉም ብሔሮች ማንነታቸውን የሚረዱበትና የሚያስረዱበት፤ እንዲሁም ሕዝባቸውን ማኅበራዊ አቅጣጫ የሚያስይዙበት ርዕዮት ይፈጥራሉ፣

3 Anthony D. Smith, National Identity (USA: University of Nevada Press, 1991). 4 Pierre L.Van den Berghe, “Ethnies and Nations: a Genealogy Indeed,” in Atsuko Ichijo & Gordana Uzelac, When is the Nation? Towards an Understanding of Theories of Nationalism (London and New York: Routledge, 2005) ,p.121. 5 Richard Handler, “Nationalism and the Politics of Culture in Quebec” , In George, E., Clifford Marcus, and James Madison (eds), New Directions in Anthropological Writing: History, Poetics, Cultural Criticism (The University of Wisconsin Press: 1988), pp.6-8. 6 Michael Freedman, Introduction to Ideology (Oxford: Oxford University Press, 2003),P. 41.

7

ያበለፅጋሉ፣ ይጠብቃሉ::6 በዘመናዊት ኢትዮጵያ አፈጣጠርና ግንባታ ከሁሉ የላቀውና መሠረታዊው ለውጥ ርዕዮተ ዓለማዊ ነው:: የታሪካዊት ኢትዮጵያ ማንነት መሠረት ሃይማኖትና ፖለቲካ፣ መንፈሳዊና ሥጋዊ በግልፅ የማይለዩበት አሃዳዊ ርዕዮተ ዓለም ነው:: በይሁዶ-ክርስትና እምነትና አስተምህሮ የተቃኘውና በተለምዶ “ሰለሞናዊ ትውፊት” የሚባለው ይህ ብሔራዊ ርዕዮት የአገሪቱን ታሪካዊ ለውጦችና ተመክሮዎች እያጣጣመ በዘመናት የተሸመነ የትውስታዎች፣ ትዕምርቶችና እሴቶች ድር ነው::7 በማኅበረሰቡ አንኳር ሥጋዊና መንፈሳዊ ትኩረቶችና ክስተቶች ላይ የሚያጠነጥን፣ እውነታና ፈጠራ የተቀላቀሉበት የብሄራዊው ስብዕና አፅመ ታሪክ ነው:: የኢትዮጵያን ማንነት፣ ሉዓላዊነትና ዘላለማዊ እጣፈንታ ይነድፋል:: የመንግሥቱ አፈጣጠር፣ አወቃቀርና ተልዕኮ፤ የሕዝቡ የደምና የታሪክ ዝምድናና ልዩ ባሕርይ ሁሉ መሠረት ነው:: የኢትዮጵያ አቋም፣ መንፈስና ራዕይ የሚገለፁባቸው ቁልፍ ባህላት፣ እሴቶችና ትዕምርቶች ምንጭ ነው:: በአንጻሩ የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ መሠረት ሃይማኖትና ፖለቲካ፣ ምድራዊና ሰማያዊ የተነጣጠሉበት ብዝሃዊ ርዕዮተ ዓለም ነው:: በምዕራብምሥራቅ ዓለማዊ ፍልስፍናና አስተምህሮ የተመራውና ቁሳዊ ብልፅግናና ግብ ያደረገው ይህ ታሪካዊ ሂደት በአጭር ጊዜ ሁለገብና ሥርነቀል ለውጦችን በማስከተል የአገሪቱን ብሄራዊ መልክ በማያዳግም የቀየረ ነው:: ከአፄ ቴዎድሮሥ አንስቶ የአዘማኞቹ ነገሥታትም ሆነ የሪፑብሊካውያኑ መሪዎች ዋነኛ ምኞት የምዕራቡንና የምሥራቁን ቁሳዊ ሥልጣኔ ቀድቶ ለመትከልና ለማስፋፋት፣ ሕዝቡንም በዚህ ፀጉረ ልውጥ ሥርዓት አስልጦ ለማስገባት የታለመ ነበር:: የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ መሪ ቃል “አዲሲቱ ኢትዮጵያ” ልንለው እንችላለን:: በአመዛኙ ወደፊት አቅጣጫ የተቃኘ፣ ባዕዳን ርዕዮቶች የተፈራረቁበት፣ እንግዳ ተቋማትና ሥርዓታት የቆሙበት፣ አዳዲስ ማኅበራዊ መደቦች የተፈጠሩበት ነበር:: የመንግሥት ግንባታውም ሆነ የብሔሩ እሳቤና መገለጫዎች ለውጣውረድና ለውዥቀት የተጋለጡበት ነበር:: ከለዘብተኛ ጥገናዊ እስከ ሥርነቀል አብዮታዊ ጥጎች የተራመደው አገራዊ ብሔርተኝነት የኢትዮጵያዊነትን መደባዊና እምነታዊ ቅጥሮች አፍርሶ በሰፊና አካታች ሕዝባዊ ሉዓላዊነት ተክቶታል:: ከብሔርተኝነት መርሆች አኳያ የአገር ግንባታው ያለፈበትን ታሪካዊ ሂደት በሦስት ምዕራፎች ልንከፍለው እንችላለን::

የመጀመሪያው በሥርወ-መንግሥታዊ መርህ (dynastic principle) የቀጠለ ጥገናዊ ምዕራፍ ከዘመነ መሳፍንት ማክተም አንስቶ እስከ 1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ድረስ ያለው አንድ ምዕተ ዓመት ገደማ ነው:: ይህ ከብሔረ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊት ኢትዮጵያ መሸጋገሪያ እርከን የአገር ግንባታው ታሪካዊና ባህላዊ መሠረቱን በጅምላ ሳይለቅቅ በዝግታና በጥንቃቄ (በጃፓን አርአያነት) እየመረጠና እያዋዛ ለማዳቀልና ለማሻሻል የሚሻ ነበር::8 እያደር ኢትዮጵያዊነት ከባህላዊና እምነታዊ ወደ ሕጋዊና ፖለቲካዊ የዜግነት እሳቤ ያዘነበለበት ነበር:: የ1923 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በተለይ ከአድዋ ጦርነት (1888 ዓ.ም) በኋላ ስልታዊና ሥርዓታዊ ፈር የያዘው የዘመናዊነት ሂደት ከፍተኛ ነጥብ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል:: ሆኖም የፋሽስት ጣልያን ጣልቃ ገብነት (19281933 ዓ.ም) ይህን ታዳጊ ሂደት በማደናቀፍ በአገር ግንባታው ይዘትና አቅጣጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል:: ጣልያን በአምሥቱ የወረራ ዓመታት ያስከተለችው ጉዳት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ህልውና እስካሁንም የሚፈታተን ነው:: የፋሽስት አስተዳደር የኢትዮጵያዊነትን መሠረቶች ማኅበረሰቦች፣ እምነቶች፣ ተቋማትና ሥርዓቶች፣ ታሪክ፣ ባህል፣ እሴቶች፣ ትዕምርቶችን (ስሟንም ጭምር) ጠራርጎ ለማጥፋት የታለመ ነበር:: የኢትዮጵያን ብሄራዊ ድር ለመበጣጠስ በዘውግ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ አውራጃ፣ መደብ፣ ትውልድና ሞያ በመከፋፈል ማኅበራዊ ጥላቻ፣ ግጭትና ቀውስ በማባባስ ስልት ላይ ያተኮረ ነበር::9 ይህ የተሳካ የቅኝ ወረራ በ1933 ዓ.ም. ወደ አልጋው የተመለሰውን አፄያዊ ሥርዓት ምዕራባዊ ሥልጣኔን በፍጥነት መቅዳትን ብቸኛው የብሔራዊ ህልውና ዋስትና አድርጎ እንዲቆጥር አስገድዶታል:: እያደርም ፈሩን የለቀቀ የዘመናዊነት ጉጉትና የባዕድ አምልኮ ነግሦ፣ ምዕራባዊነት በተራማጅነት ተወድሷል:: ታሪካዊውና አገር በቀሉ ደግሞ በወግ አጥባቂነት፣ ዘልማዳዊነትና ኋላ ቀርነት ተፈርጇል:: በውጤቱም ግንባታው አገራዊ ወዝ እያጣ፣ ነባሩ የኢትዮጵያዊነት እሳቤ በአዲስ ብሔራዊ ርዕዮት እንዲተካ ግፊት አስነስቷል:: በተለይም ከ1950ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የዘመናዊው ሥርዓት ተስፈኛው የአስኳላ ትምህርት ቀመስ መደብ በአገዛዙ ላይ በማመጽ፣ ተፃራሪ መልክና መንፈስ ያላቸው አገራዊና ዘውጋዊ ርዕዮቶች ሊፈጠሩ ችለዋል::10 ሁለተኛው በአብዮታዊ መርህ (revolutionary principle) የተመራው ምዕራፍ በ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት የፖለቲካ ሥልጣን በተቆናጠጠው

በወታደራዊው አገዛዝ (ከ1966- 1983 ዓ.ም) ዘመን የተከናወነው ሥር ነቀል የርዕዮተ ዓለም ለውጥ ነበር:: አጠቃላይ ሥርዓተ ማኅበራዊ አብዮት የተካሄደበትና የኢትዮጵያን ብሔራዊ አቋምና መንፈስ እንዲሁም የመንግሥቱን መዋቅር፣ ባሕርይና ተልዕኮ በእንግዳ ሶሻሊስታዊ ርዕዮት አፍርሶ የሠራ ሂደት ነበር:: በተለይም በመንግሥት ግንባታው ረገድ የተከናወኑት ሥር ነቀልና ዘላቂ ለውጦች ኢትዮጵያን በሪፑብሊካዊ ቅርፅና በሕዝባዊ ሉዓላዊነት መርህ ላይ ለማቆም አስችለዋል:: በአንጻሩ ደርግ ከአነሳሱ ጀምሮ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት አቋሙና በብሔር ግንባታ ጥረቱ ጽንፍ አልረገጠም ነበር:: በተማሪው ንቅናቄ የተቀነቀኑት ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ርዕዮቶች ለኢትዮጵያ ባዕድና የማይበጁ ናቸው የሚል እምነት ነበረው:: ይኹን እንጂ “ኢትዮጵያ ትቅደም” የተባለው አገር በቀል ብሄርተኛ አቋሙ በሲቪሉ የግራ ሃይል የሰላ ትችት ስለተሰነዘረበት የሶሻሊስቱን መስመር ለመከተል ተገድዷል:: ስለዚህም በታህሣሥ 11 ቀን 1967 ዓ.ም ባወጣው ‹‹ህብረተሰባዊነት›› በተባለው የፖለቲካና ኤኮኖሚ መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያዊነትን ከሶሻሊዝም ለማዳቀል ሞክሮ ነበር:: በደርግ ትንታኔ መሰረት ህብረተሰባዊነት ከኢትዮጵያ አፈር ፣ ታሪክ ፣ ባህልና ኃይማኖቶች የመነጨ ፍልስፍና ነው:: ከታላላቅ ኃይማኖቶቻችን የሰብአዊ እኩልነት አስተምህሮ ፣ ከአብሮና ተካፍሎ መኖር ባህላችን ፣ እንዲሁም በብሄራዊ መስዋእትነት ካሸበረቀው ታሪካችን የሚመነጭ የፖለቲካ ፍልስፍና ነው:: የህብረተሰባዊነት አምስት ቁልፍ መርሆች ብሄራዊ ሉዐላዊነት ፣ ብሄራዊ አንድነት ፣ ብሄራዊ በራስ መተማመን ፣ የሥራ ክቡርነት እና የህዝብ ጥቅም ቀዳሚነት ናቸው::11 ወታደራዊው አገዛዝ ከሲቪሉ ግራ ክንፍ የወረሰው ሶሻሊዝምን ብቻ ሳይሆን የንቅናቄው መቂናጥ የነበረውን የብሄረሰቦች ጥያቄን ጭምር ነበር:: ይህን በተመለከተ በሚያዝያ 12 ቀን 1968 ዓ.ም የታወጀው ‹‹የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት ፕሮግራም›› (ኢብዲአፕ) አገዛዙ ከተቀናቃኞቹ ጋር ያለውን መሰረታዊ ልዩነቶች በግልፅ ያስቀምጣል:: ኢብዲአፕ የመደብ ተቃርኖን ከብሄረሰባዊ ፣ ኃይማኖታዊና ጾታዊ ተቃርኖዎች በሚያስቀድመው ማርክሳዊ መርህ መሰረት የብሄረሰቦችን ባህላዊ ነፃነት ያረጋግጣል:: ነገር ግን ፖለቲካዊ ነፃነትን በአካባቢያዊ ራስገዝነት ይወስናል:: የሲቪሉ ሃይል በተለይም በውስጡ የተቀፈቀፉት ዘውጋዊ ድርጅቶች የመደብ ተቃርኖን የበላይነት

7 Anthony D. Smith, The Ethnic Origins of Nations (Oxford: Blackwell, 1986),pp. 15, 24, 57-58. 8 Bahru Zewdie, Pioneers of Change in Ethiopia. The Reformist Intellectuals of the Early Twentieth Century (Addis Ababa: AAUP, 2002). 9ብርሃኑ ድንቄ ፣ ቄሳርና አብዮት ፣ ገፅ 30-31. 10 ተድላ ዘዮሃንስ ፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ (አዲስ አበባ ፤ 2004 ዓ.ም).

8

ለይስሙላ ቢያቀነቅኑም ፣ በተግባር ብሄረሰባዊ ጥያቄን ከሁሉም ተቀዳሚ አድርገው ተሰልፈው ነበር:: ሶስተኛው በዘውጋዊ መርህ (ethnic principle) የተመራው የአገር ግንባታ ምዕራፍ የአማፂያን ሃይሎች ጥምር የሆነው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዲግ) ደርግን በትጥቅ ትግል ገርስሶ መንበረ ሥልጣኑን በግንቦት 1983 ዓ.ም ከተቆናጠጠበት ይነሳል:: ዘውጋዊ ርዕዮት የበላይነቱን የተቀዳጀበትና አገዛዙ ወታደራዊ ድሉን ወደ ሥርነቀል የአገር ግንባታ ሂደት የተረጎመበት ምዕራፍ ነው:: ለዚህ የዋለው የኢህአዲግ ብሄራዊ ርዕዮተ ዓለም በ1975 ዓ.ም ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ሲመሰረት አንስቶ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትህነግ) መሪ የፖለቲካ አስተምህሮ የነበረው ‹‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ›› ነው:: አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወደ ተግባራዊ ህግ የተቀየረባቸው ገዥ ሰነዶች የሽግግር ቻርተሩ (ከሐምሌ 15 ቀን 1983 እስከ ነሃሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም) እና በነሃሴ 1987 ዓ.ም የታወጀው የኢፌዲሪ ህገ መንግሥት የአገዛዙን ዘውግ ተኮር ርዕዮት መሰረታውያን ያሳያሉ:: ኢትዮጵያ አሃዳዊ ብሄር ሳትሆን ብዝሃዊ ወይም የብሄሮች ብሄር ናት:: ብሄራዊ መሰረቷም ህዝባዊ ሉዐላዊነት ሳይሆን ዘውጋዊ ሉዐላዊነት ነው:: ስለሆነም ዜግነታዊ ብሄርተኝነት በዘውጋዊ ብሄርተኝነት ተተክቷል:: ‹‹ብሄሮች ፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ፖለቲካዊ ነፃነት በማጎናፀፍ የመንግሥቱ አስተዳደራዊ መዋቅር መሰረት ተደርገዋል::12 ምንም እንኳን ቻርተሩም ሆነ ህገ መንግሥቱ የአገራዊው መንግሥት አሃዳዊ ፣ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስለመሆኑ በግልፅ ባይወስኑም በተግባር የተሰራው መዋቅር ዘውጌ ፌዴራላዊ ነበር:: በታህሣሥ 2 ቀን 1984 ዓ.ም የታወጀው ‹‹የብሄራዊ ክልላዊ ራስገዝ አዋጅ ቁ.7/1984›› “ብሄር ወይም ብሄረሰብ ማለት በአንድ ኩታ ገጠም መልክዐ ምድር የሚኖር ፣ አንድ የሚያግባባ ቋንቋና የአንድነት ሥነልቡና ያለው ህዝብ ነው” ሲል ቢያብራራም ፣ ኢህአዲግ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አስተዳደራዊ እርከኖችን ለመወሰን የተጠቀመው ዋነኛ መስፈርት ቋንቋ ነበር::13 የህገ መንግሥቱ አወዛጋቢ አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ 5 በዚህ ላይ የጨመረው ማሻሻያ የጋራ ባህልን ብቻ ነው::14 በአጠቃላይ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም የተመራው የኢህአዲግ አገር ግንባታ በብዙ ረገድ ከቀደሙት አገዛዞች ይቃረናል:: ወታደራዊውና ዘውዳዊው አገዛዞች የዘውግ ፖለቲካን እንደ ብሄራዊ አንድነት ስጋት ሲቆጥሩት ፣ ኢህአዲግ ህጋዊና

ተቋማዊ ቁመና በማላበስ የብሄራዊ አንድነት ዋስትና አድርጎታል:: አሃዳዊና የተማከለ ብሄራዊ መንግሥትን አፍርሶ ብዝሃዊና ያልተማከለ ዘውጋዊ መንግሥት ገንብቷል:: ከግል መብቶች ይልቅ ለቡድን መብቶችና ነፃነቶች አፅንኦትና ቅድሚያ ሰጥቷል:: ኢህአዲግ አገራዊ ብሄርተኝነትን ችላ ከማለት አልፎ በጠላትነት በመፈረጅም ይወቀሳል::

2.2. ከህዝባዊ ባህል አንፃር ብሄሮች በፖለቲካዊው መንግሥት ቢመሰረቱም ቅሉ ፣ ማንነታቸው ዘላቂ ዋስትና የሚያገኘው በባህል አንድነት አማካኝነት ነው:: የኢትዮጵያዊነት ልዩ ባህሪ ወይም ብሄራዊ አቋም የተፈጠረው የትውልዶች ማህበራዊ ዝንባሌዎችና ተመክሮዎች በጋራ ታሪክ ላይ ባከማቹት የባህል አሻራ ነው:: የዚህ የባህል አሻራ አንዱ ዘርፍ የሆነውና ማህበረ-ሥነልቡናዊ ባህሪ ያለው ባህል በአጠቃላይ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እውቀት ፣ ግብረገባዊነትና ሌሎች እሴቶችን ይመለከታል::15

አጠቃላይ ሥርዓተ ማኅበራዊ አብዮት የተካሄደበትና የኢትዮጵያን ብሔራዊ አቋምና መንፈስ እንዲሁም የመንግሥቱን መዋቅር፣ ባሕርይና ተልዕኮ በእንግዳ ሶሻሊስታዊ ርዕዮት አፍርሶ የሠራ ሂደት ነበር

ከላይ የገለፅነው የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ርዕዮተ ዓለም ረቂቅና ሃሳባዊ ነው:: ከየአገዛዙ ዕድሜና ከንዑስ መደቦች ወይም ጠባብ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅፅር አይዘልም:: በአንፃሩ ባህል ረቂቁና ውስብስቡ በሰፊው ህዝብ ውስጥ የሚገዝፍበትና ህያው የሚሆንበት ዋነኛው መንገድ ነው:: በሌላ አነጋገር ባህል ለኢትዮጵያ አገር ግንባታ ወሳኝ ሃይል የሚሆነው ገዥውን ርዕዮተ ዓለም ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ የዕለት ተዕለት ህይወት አካል ሲያደርግ ነው:: የብሄረ ኢትዮጵያ ባህል እምብርት ኃይማኖት ነው ብለናል:: ከ4ኛው መቶ አጋማሽ ወዲህ ታቦት ክርስትና የይሁዲነትና ክርስትና ቁልፍ ትዕምርቶች የሆኑት ፅላተ ሙሴውና ግማደ መስቀሉ የሚሰናሰሉበት፣ የኢትዮጵያ ጥንታዊነትና በኩረ መንግሥትነት ማረጋገጫና የብሄራዊ እምነቱ ኦርቶዶክስ ክርስትና ዋነኛ መለያ ሆኖ አገልግሏል:: ኢትዮጵያዊነት በየደብሩና ጎጡ የሚሰበክበት መድረክ፤ ኢትዮጵያውያን በየእለቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩና አውደ ዓመቱ ማንነታቸውን በጋራ የሚያድሱበት ትዕምርታዊ ቁርባንም ነበር:: ከዚህም በላይ ኦርቶዶክስ ክርስትና የኢትዮጵያዊነት አስኳልና የዜግነት ቀንደኛ ቅድመ ሁኔታ በመሆን ፣ ገዥና ተገዥን ሳይለይ የብሄሩን አባላት በእኩልነት የሚያሰናስል ርዕዮታዊ ባህል ነው:: በአጠቃላይ በአገሪቱ የተገነባው ሰፊ ህዝባዊ ባህል መሰረት ነው:: ብሄራዊ ፊደል ፣ ሥነፅሁፍ ፣ ቀን መቁጠሪያ ፣ ፍልስፍና ፣ ቅኔ ፣ ህግጋት ፣ ሥርዓተ አምልኮ ፣ አልባሳትና ቁሳቁስ ፣ ኪነጥበብና ኪነህንጻ ፣ ሙዚቃ ፣ ሥነጽሁፍ ፣ የመፅሃፍት ድጎሳ ፣ ህዝባዊ በዓላትና አውዳመቶች ፣ የትምህርት ሥርዓቱና መላው ብሄራዊ የህይወት ዘይቤ በኦርቶዶክሳዊ ኃይማኖት ላይ የቆመ ነበር::16 የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ሂደት ኢትዮጵያዊነት ከአሃዳዊ የባህል ግንዛቤ ይልቅ እንደ ብዝሃዊ ባህላትና ማህበረሰቦች ድምር የተቆጠረበት ነው:: ከጠባቡ የብሄረ ኢትዮጵያ ባህላዊ ወሰን በመውጣት ወደዳር የተገፉ እምነቶችንና ማህበረሰቦችን ለማካተትና መላውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚያስተሳስር የጋራ ብሄራዊ ባህል ለመገንባት ያለመ ነው:: ሆኖም በነባሩና በአዲሱ መካከል የሚኖረውን መስተጋብር በመወሰን ረገድ የብሄር ግንባታው አስኳል የሆነው ባህላዊ ለውጥ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ገጥመውታል:: ትልቁ ተግዳሮትም ከዚህ ሰፊ ባህላዊ ቅርስ ውስጥ የቱን መውሰድ ፣ የቱን መተው ፣ የቱንስ ማሻሻል ይቻላል ፤ ሌሎች ማህበረሰቦችስ አስተዋፅአቸው ምንድነው የሚለው ነበር::

Andargachew Tiruneh, The Ethiopian Revolution: 1974-1987(Cambridge University Press:1993/1995), pp.86-87. Transitional Government of Ethiopia Charter, Negarit Gazetta, 15 Hamle 1983. 13 Fasil Nahom, Constitution for a Nation of Nations (The Red Sea Press: 1997), pp.44-45. 14 The 1995 FDRE Constitution. 15 Day and Thompson, Theoriziang Nationalism (New York: Palgrave Macmillan, 2004), p.96. 11

12

9

በአጠቃላይ የዘመኑ አቅጣጫ ዓለማዊነት እየጠነከረ ፣ ኃይማኖት ከብሄራዊ ባህል ጋር ያለው ግንኙነት እየላላና ባህል እንደ ግለሰባዊ ምርጫነት የተቆጠረበት ነው:: ሆኖም በዘውዳዊው ሥርዓት የብሄረ ኢትዮጵያን ባህላዊ ቅርስ ለአዲሱ ባህል ግንባታ ለማዋል ጥረቶች ተደርገዋል:: የዚህ ሁነኛ ምሳሌ ዕድሜ ጠገቡ የቤተክህነት ትምህርት በዘመናዊው ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ አስተዋፅኦ የሚያበረክትበትን መንገድ የመፈለግ ጥረት ነው::17 የግዕዝን ሥነፅሁፋዊ ሚና በአማርኛ የመተካት ዓይነት አንዳንድ ሂደቶች የመንግሥቱ ተፈጥሮአዊ እድገት ውጤቶች ነበሩ:: በተለይ እስከ ወታደራዊው አገዛዝ ማብቂያ ድረስ የትምህርት አጠቃላይ ግብ የጋራ ብሄራዊ ተስፋና እሴቶችን የሰነቁ ፣ በአገሪቱ ባህልና ታሪክ መሰረት የያዙ ፣ በዘልማዳዊና ደመነፍሳዊ ወገንተኝነት ያልተሰናከሉና ሃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎችን መቅረፅ ነበር:: ስለዚህም በመላ አገሪቱ ሁሉን አካታች እሴቶችንና ትዕምርቶችን ለማበልፀግ ንቁ ሙከራዎች ይደረጉ ነበር:: ለምሳሌ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በሚያዚያ 19 ቀን 1917 ዓ.ም ከተከፈተ ጀምሮ አማርኛ የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ በወታደራዊውም መንግሥት ከግዴታ ትምህርት ዓይነቶች አንዱ ሆኖ ዘለቋል:: የኢትዮጵያ ታሪክም ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት የጋራ ኮርስ ይሰጥ ነበር:: ከ1940 አንስቶ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ ትምህርት ቤቶች በወጥነት የብሄራዊ መዝሙር ወይም ሰንደቅ ዓላማ ሥርዓትን ያከናውኑ ነበር::18 ዘመናዊ ብሄሮች ትምህርት ቀመስ በመሆናቸው የትምህርት መሰረቱ እየሰፋ ቢያንስ ማንበብና መፃፍ የሚችል ህብረተሰብ ሲፈጠር ሌሎችም ኢመደበኛ የትምህርት መንገዶች ጠቀሜታቸው እየጎላ መጥቷል:: በዚህ ረገድ ዘመናዊ የመገናኛ ብዙሃን በአገር ግንባታው ፖለቲካዊም ባህላዊም ዘርፎች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አዳዲስ ተቋማት መካከል ናቸው:: በመስከረም 1914 ዓ.ም የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፣ በ1916 ዓ.ም ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ምስረታ ተነስተው እያደር የየወቅቱን ቴክኖሎጂ በመከተል የተስፋፉት ጋዜጦች ፣ መፅሄቶች ፣ የሬዲዮንና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የመንግሥትን ዓላማ ለማስረፅ ፣ የህዝብን ድምፅ ለማሰማትም ይሁን የጋራ አገራዊ አስተሳሰብ ለመቅረፅ በጣም ጠቃሚ መድረኮች ነበሩ::19

ሌላው ከትምህርት መስፋፋት ጋር ህዝባዊ መልክ እየያዘ የመጣው ባህላዊ ተቋም ኪነጥበብ ሲሆን ፣ በተለይ በቅድመ አብዮት ጀምሮ የዘርፉ አብይ ትኩረት ታሪካዊ ጭብጦች ፣ ብሄራዊ ጀግኖች ፣ የዘመናዊነትንና የኢትዮጵያዊነትን ብሄራዊ አጀንዳዎችና እሳቤዎች የሚያንፀባርቁ ነበሩ:: በ1950ዎቹ መጨረሻ በዚህ ረገድ የታየው አጠቃላይ ኪነታዊ እመርታ አንኳር መገለጫዎች የአማርኛ ሥነፅሁፍ ፣ ሙዚቃና ሥነጥበብ ልምላሜ ጊዜ የማይሽራቸው ድርሰቶችን ፣ ተውኔቶችን ፣ ጥዑመ ዜማዎችን አፍርቷል:: አጠቃላዩ ሂደት በዋነኝነት በአማርኛ ቋንቋ አማካይነት የሚገለፅ አዲስና ዘመናዊ ባህልና አስተሳሰብ በአስተማማኝ መመስረቱን አብስሯል:: በሌላ በኩል የአብዮተኝነት መንፈስ በአዲሱ ምሁራዊ መደብ ውስጥ እየጎላ ሲመጣ ፣ ብሄራዊው ባህል ወርደ ጠባብና መላው ኢትዮጵያን የማይወክል ስለመሆኑ ተገቢ ጥያቄ ተነስቶበታል:: የኮሚኒስታዊ ርዕዮት የበላይነቱን ሲይዝ በባህል ላይ በተለይ በኃይማኖታዊ ባህል ላይ ቀጥተኛና እጅ አዙር ጥቃት ተከፍቶበታል:: ኢአማኒነት በወታደራዊው አገዛዝ የመንግሥት ይፋዊ ‹‹ኃይማኖት›› ሆኗል:: የአገር ባህል ከእለት ተእለት ህይወት እየራቀ እንደ ብርቅ ትርኢት የታየበት ፣ ሰፊ የምዕራባዊና ምሥራቃዊ ባህል ወረራ የተፈጠረውን ክፍተት የሞላበት ሂደት ተከስቷል:: አግድምም በመላ አገሪቱ የተለያዩ ባህላዊ ማህበረሰቦች መካከል መስተጋብራዊ እመርታ በመፈጠሩ ፣ ፈጣን ባህላዊ ልውውጥና ለውጥ ከማዕከልና ከከተሞች አልፎ ገጠሩንና ዳር አገሩን ጭምር ያዳረሰበት ነው:: የዚህ ድርብ አገራዊና የባዕድ ባህል አስተላላፊ ደግሞ በተለያዩ ሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎቶች በመላ አገሪቱ የተሰማራ አማርኛ ተናጋሪ ልሂቅ ነበር:: ሆኖም ዋነኛው የዘውጋዊ ቡድኖች ተቃውሞ የተመሰረተው ከባዕዳዊው የምዕራብ ምሥራቅ ባህል ይልቅ በአገራዊው የባህል ተፅእኖ ላይ ነበር:: ይህም እያደር ከእርስ በርስ መረዳጃና ባህላዊ ድርጅቶች ወደ ዘውጋዊ የፖለቲካና ወታደራዊ ድርጅቶች ፣ ከባህል ነፃነት ጥያቄ ወደ ፖለቲካ ነፃነት ትግል ተሸጋግሮ ለመንግሥቱ ከፍተኛ ተግዳሮት ደቅኗል:: በዚህ ረገድ ዘውዳዊውና ወታደራዊው አገዛዞች የተከተሉት ብሄራዊ ፖሊሲ ባህላዊ ይዘት የሌለው ፖለቲካዊ አንድነት ፋይዳ ቢስ ነው የሚል ነበር:: የሁለቱ የባህል ግንባታ አቅጣጫና ይዘት እንደ ርዕዮተ ዓለማቸው የተራራቀ ቢሆንም ቅሉ ፣ የባህል ውህደት

ስልታቸው ግን ኢትዮጵያን በአንድ ቡድን ባህል ስር የሚጨፈልቅ ‹‹assimilationist›› አልነበረም:: የባህላዊ ማህበረሰቦች መሰረታዊ ልዩነቶች እንደተጠበቁ በቁልፍ ብሄራዊ ምልክቶች የተዋሃደና ከዘውጎች የላቀ አገራዊ ባህል የመገንባት ‹‹integrationist›› እንጂ::20 የግንባታው ቀንደኛ መሳሪያዎችም አማርኛ ቋንቋና ብሄራዊ የትምህርት ሥርዓት ነበሩ:: ስለዚህም ዘውጋዊ ባህሎችና ማንነቶች ባይደፈጠጡም ጠንካራ ዘውጋዊነት በሁለቱም አገዛዞች ይከለከልና ብሄራዊነት በውስጠ ታዋቂነት ይበረታታ ነበር::21 ከዚህ አኳያ የኢህአዲግ የባህል ፖሊሲ የተገላቢጦሽ ነው:: ዘውጋዊ ማንነቶችንና ባህሎችን በየራሳቸው ክበብ የሚገድብና የሚያጋንን ፤ አገራዊ ባህሎችንና ትስስሮችን የሚያዳክም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል:: ኢህአዲግ የሚያራምደው ብዝሃዊነት ‹‹በህብረ-ባህላዊነት›› / multiculturalism/ ይገለፃል:: ነገር ግን በተግባር የዋለው የባህል ፖሊሲው የህብረ-ባህላዊነት ቁልፍ እሳቤ የሆነውን በማህበረሰቦች መካከል መስተጋብርን የመፍጠር ፣ ብዝሃነትን በአንድነት ውስጥ የማስተናገድ ሚዛናዊ ቀመር የለውም:: ስለሆነም በመቀራረብና መተዋወቅ ፈንታ መራራቅንና ባይተዋርነትን የሚያባብስ ፣ ሰፊ የተራክቦ መንገዶችንና እድሎችን ከመዘርጋት ይልቅ በጠባብ ፖለቲካዊ ጥቅም ላይ ያተኮረ አፍራሽ ‹‹disintegrationist›› ነው::

2.3. ከጋራ ተቋማትና መዋቅሮች አንፃር የኢትዮጵያ አገር ግንባታ ሌላው ፈርጅ በዘመናት የተፈጠሩና የዳበሩ የአገሪቱን ማህበራዊና ፖለቲካዊ አደረጃጀት መልኮች ፣ ተቋማትና መዋቅሮችን ይመለከታል:: ከጥገናዊነት እስከ ሥርነቀል ለውጦች የዘለቀው የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ ሂደት ፣ በአዲስ ራዕይ አዳዲስ ተቋማትና መዋቅሮች የተዘረጉበት ፣ አዳዲስ ማህበራዊ መደቦችም የተፈጠሩበት ነበር:: ከሁሉም ግንባር ቀደሙ አጠቃላይ ሥርዓተ ማህበራዊ ለውጥ ነው:: የብሄረ ኢትዮጵያ ማህበራዊ መዋቅር በግብርና መሰረት ላይ የቆመ ፣ ከአጥቢያ እስከ ዙፋን በተዘረጋ የመሬት ሥሪትና የግብር ሥርዓት የተሳሰሩ ባላባታዊ ፣ ካህናዊ ፣ ወታደራዊና አርሶ አደር መደቦችን ያቀፈ ተዋረዳዊ እርከን ነው:: በአንፃሩ የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ግንባታ በሂደት ይህንን በዝባዥ ሥርዓተ ማህበር አፍርሶ አገሪቱን በብሄራዊ እኩልነት መርህ ላይ መስርቷል:: ከ1966ቱ አብዮት በኋላ የባላባቱ መደብ

16 Wudu Tafete, “The Ethiopian Orthodox Church, the Ethiopian State and the Alexandrian See: Indigenizing the Episcopacy and Forging National Identity, 1926-1991,” (Ph.D. Dissertation: University of Illinois at Urbana-Champaign, 2006), p.4.

17 MoI files: No. መሃወቂ፣ 63.1.12.03፤ ‹‹ስለሚመጣው ዘመን ቤተ ትምህርት ለአማርኛና ለግዕዝ ትምህርት የሚያስፈልገውን እቅድ ለመመርመርና ለማስታወቅ የተመረጠ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባ›› (1937 ዓ.ም).

18 መርሥኤ-ሀዘን ወልደቂርቆስ ፣ አማርኛ ሰዋሰው (አዲስ አበባ ፤ 1948 ዓ.ም)፣ ገፅ 3. GPNRS Files: Letter of the Imperial Ethiopian Government to the Gambella Awraja Schools Administration, No.1083/2/19, Hidar 21/1944. 19 Bahru, Pioneers, pp. xi, 188.

10

ሲከስምና የኤኮኖሚ መሰረቱ መሬት ወደ ህዝብ እጅ ሲዛወር ፣ አዳዲስ የሠርቶ አደርና ንዑስ ከበርቴ መደቦች ፣ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ሥርዓቶች ተስፋፍተዋል:: የብሄረ ኢትዮጵያ አገር ግንባታ ተቋማዊ ምሶሶዎች ቤተመንግሥትና ቤተክህነት መሰረት ከጥንታዊት አክሱም ይነሳል:: በጋራ ኃይማኖታዊ ርዕዮትና ባህል የተቆራኙ የአገር ግንባታው ፖለቲካዊና መንፈሳዊው ክንፎች ናቸው:: ይሁን እንጂ በዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ እነዚህ ተቋማት በዓላማና ተግባር ለመነጣጠልና አቋማቸውንና ሚናቸውን ለመቀየር ተገድደዋል:: በተለይ ቤተመንግሥት በ1966ቱ አብዮት ሥርነቀል ለውጥ ተደርጎበታል:: ሰለሞናዊ ሀረግ የሚቆጥረው ዘውድ ተገርስሶ በሪፑብሊካዊ መንግሥት ተተክቷል:: የአገዛዙ ቅቡልነት መሰረት ከሥልጣነ መለኮት ወደ ሥልጣነ ህዝብ ተቀይሯል:: የዘውዱ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ትዕምርትነቱ አብቅቷል:: የርዕሰ ብሄርና ርዕሰ መንግሥት ጣምራ ውክልናውም በአዲሱ ሪፑብሊክ ተለያይተዋል:: በወታደራዊ መዋቅር የተደራጀው ባላባታዊ ገዥ መደብ በሲቪል መዋቅር ወደተደራጀ ወታደራዊ መደብ ተቀይሯል::22 አሃዳዊም ቅርፅ ይኑረው ብዝሃዊ ፤ ዘውዳዊም ይሁን ሪፑብሊካዊ ፣ አብዮታዊም ሆነ ዘውጋዊ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ መንግሥት እያደር በአቅሙ ፣ በተደራሽነቱና በባህሪው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል:: ዘመናዊው መንግሥት ከሠራዊቱና ደህንነት ተቋማቱ አንስቶ ቁልፍ የሃይልና ምጣኔ ሀብታዊ ምንጮችን በመጠቅለል ጉልበት አዳብሯል:: በ1900 ዓ.ም ከተሞከረው የሚኒስትራዊ አደረጃጀት ተነስቶ በመላ አገሪቱ የተንሰራፋ ቢሮክራሲና በሲቪል አገልግሎት ሃይል የሚታገዝ ሰፊና ጥልቅ መዋቅር መፍጠር ችሏል:: በድህረ ጣልያን በ‹‹ውስጥ አገዛዝ ደንብ›› ቁጥር 1 ፣ 1934 የጀመረው የተማከለ አገራዊ አስተዳደር የመዘርጋት እርምጃ በ1940 ዓ.ም ከጠቅላይ ግዛት እስከ ወረዳ አስተዳደር መስርቶ አጠናቅቋል:: ይህ የጠቅላይ ግዛት አስተዳደር ሥርዓት ከዚህ በኋላ ጉልህ ለውጥ ያደረገው በ1955 ዓ.ም ሐረርጌ ለሁለት ተከፍሎ ባሌ ሲፈጠርና ኤርትራ ስትደመር ነበር::23 ከአብዮቱ ወዲህ የጠቅላይ ግዛት አስተዳደር ወደ ክፍለ ሀገር የተቀየረው በተወሰኑ ማሻሻያዎች ነበር:: ሆኖም መንግሥት ከቀበሌ እስከ ማዕከል በተዘረጋ የአስተዳደር መዋቅር ፣ በትይዩ በተደራጁ በርካታ ህዝባዊና የሞያ ማህበራት ፣ እንዲሁም በጥልቅ የፓርቲ ሰንሰለት አማካኝነት ቁጥጥርና ተደራሽነቱን አረጋግጧል::

በድጋሚ የ1984 ዓ.ም ድንጋጌ ይህንን ታሪካዊ መሰረት ያለውን የክፍለ ሀገር አስተዳደር ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ቀይሮ አዲስ ዘውጋዊ የክልል መንግሥታት ተክቷል:: በአጠቃላይ መንግሥቱ ከልማዳዊው የሰላም ማስከበር ፣ ግብር መሰብሰብና ፍትህ ሰጪነት ሃላፊነቶቹ ወጥቶ በማህበረሰቡ ሁለገብ ህይወት ላይ ዋነኛ ተዋናይ ፤ የሥልጣን ፣ የክብርና የጥቅም ምንጭ ሆኗል:: እንዲያውም መንግሥቱ ሌሎችን ባህላዊና ልማዳዊ ተቋማትን የማግለል ፣ የመጠቅለልና የመዋጥ ባህሪው እየገነነ መጥቷል:: የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ በጥልቅ የነካት ሁለተኛዋ ተቋም ቤተክህነት ናት:: ይህቺ ተቋም የኢትዮጵያዊነት እሳቤ አፍላቂ ፣ አስተዋዋቂና አራማጅ በመሆን ለሺህ ዘመናት ዘልቃለች:: የብሄሩን ባህላዊና ህሊናዊ ድንበር አስፋፍታለች:: የብሄራዊ ታሪክ ዘጋቢና የቀጣይነት መሃንዲስ ፣ መንግሥቱ ሲዳከም ብሄራዊውን መንፈስ የምታተጋ ሆና ቆይታለች:: በዘመናዊት ኢትዮጵያ ቤተክህነት ከቤተመንግሥት ጋር የነበራት አንድነት ላልቷል ፣ የኤኮኖሚ ጉልበቷ ሳስቷል ፤ ከብሄራዊ ፖለቲካ ተገልላ በመንፈሳዊ ተግባሯ እንድትወሰን ተገድዳለች:: የቤተክህነትን የብሄር ግንባታው ርዕዮተ ዓለማዊና ባህላዊ ሚና የተረከቡት አዳዲስ ተቋማት በዋነኝነት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ትምህርት (መገናኛ ብዙሃን ጨምሮ) ናቸው:: የዘመናዊነት ተቀጥላ የሆነው የፖለቲካ ሥርዓት በአገሪቱ የፖለቲካ ባህል ላይ ያልተመሰረተ ፀጉረ ልውጥ ተቋም ነበር:: ከአፄው ዘመን እስከ ኢህአዲግ የዘለቀው ፓርላማ ከአስፈፃሚው መንግሥት ነፃ ወጥቶ እውነተኛ የህግ አውጪ ተቋም ለመሆን አልቻለም:: የፓርቲ ፖለቲካም ቢሆን ሀቀኛ የብዝሃዊነትና ዲሞክራሲ መሳሪያ ለመሆን አልበቃም:: በተለይም በአገር ግንባታው ውስጥ የመንግሥቱ ዋነኛ ርዕዮተ ዓለማዊ ክንድ ምኑም ኢትዮጵያዊ የማይመስለው ወገንተኛ ፓርቲ ነው:: የፓርቲ ፖለቲካ በባእድ ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሰረተና ኃይማኖታዊና ባህላዊ ቅድመ ሁኔታዎች የሌሉት ባለሰፊ አውድ ተቋም ነው:: ሆኖም ይህ ዓለማዊ ተቋም ከአስገዳጅነት ያለፈ ስር በሰፊው ህዝብ ውስጥ አልሰደደም:: ከነባሩ ባህልና ማህበራዊ እሳቤ በተቃራኒ የቆመና በጥራዝ ነጠቅነት የቀረ ነበር:: ከአገሪቱ ያልተቀዱት ጥቂት መለያ ትዕምርቶቹም እጅግ ጠባብና ከየአገዛዙ ያለፈ እድሜ አልነበራቸውም:: ቤተክርስቲያን በምዕመኖቿ ላይ ያላትን ያክል ጠንካራ ተፅእኖ አልነበረውም::

ዘመናዊ ትምህርት በ1901 ዓ.ም ጀምሮ በተለይ ከ1920ዎቹ ወዲህ ሲስፋፋ ፣ ከአገር በቀል ኃይማኖታዊ ትምህርት ሥርዓቶች የተለየ ቅርፅና ይዘት ነበረው:: ተልዕኮውም ዓለማዊውን እውቀት ፣ ክህሎትና ሞያ በማስጨበጥ አዲሱን ትውልድ በመንግሥቱ የዘመናዊነት ዓላማ መቅረፅ ነበር::24 ለዚህ ሃላፊነት የተሰጠው የትምህርትና ሥነጥበብ ሚኒስትር በ1923 ዓ.ም ሲመሰረት በአቡኑ መሪነትና በንጉሱ የበላይ ጠባቂነት ስር ነበር:: ያምሆኖ በድህረ ጦርነቱ እንዳዲስ ከሚኒስትር መ/ ቤት እስከ መሰረተ ትምህርት ጣቢያ ተቋማዊ ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ፣ ሰብአዊና ቁሳዊ ግብአቶች የሚቆረጡለት ግዙፍና ወጥ የትምህርት ሥርዓት ተዘረጋ:: ከ1941 ዓ.ም ጀምሮ መንግሥት የመሰረተ ትምህርት ቤቶችን በመላ አገሪቱ በማቋቋም ትምህርት ለሁሉም ዜጎች መዳረስ የሚገባው ህዝባዊ መብት አደረገው:: ሂደቱ በአብነትና መድረሳ አሸጋጋሪነት ተነስቶ በ1943 ዓ.ም እስከ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚደርስ የሥልጠና ፣ ትምህርትና ምርምር መሰረት ተጣለ:: ዘመናዊ አስተሳሰብ የሚያራምድ ፣ በዘመናዊ እውቀት ፣ ክህሎትና ሞያ የታጠቀ ሰፊ መሰረት ያለው መደብ ተፈጠረ::25

2.4. ከጋራ ህግጋት ፣ ወጎችና ልማዶች አንፃር ብሄራዊ የህግ መደላድል ማለትም የወል ህግጋትን ፣ ብሄራዊ ወጎችና ልማዶችን መፍጠር ፣ ማስፋፋትና ማስከበር ሌላው የኢትዮጵያ አገር ግንባታ አካልና የአንድነት መሳሪያ ነው:: የታሪካዊት ኢትዮጵያ ልማዳዊ ህገ መንግሥቶች ተደርገው የሚቆጠሩት ክብረ ነገሥት ፣ ፍትሃ ነገሥትና ህገ ወሥርዓተ መንግሥት ከዘመነ አክሱም የሚነሳው ብሄራዊ የህግ ሥርዓት ግንባታ ጥረት አንኳር ውጤቶች ናቸው:: ህግጋቱ በመንግሥት ፣ አገርና ህዝብ መካከል የሚኖሩትን ግንኙነቶች የሚወስኑና የሚገዙ በመሆን አገልግለዋል:: እነዚህ ሰነዶች የተዘጋጁት በአገሪቱ ታሪክ የተከሰቱትን ታላላቅ የሃይል አሰላለፍ ለውጦች ፣ የመንግሥቱን መስፋፋትና መጠናከር አቅጣጫዎችን ተከትለው ነበር:: ትኩረቶቻቸው የየዘመናቸውን አንገብጋቢ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ላይ ነበር:: በአተገባበራቸውም በአገሪቱ ውስጥ በየአካባቢው የነበሩትን ልማዳዊ የህግ ሥርዓቶች ከማስወገድ ይልቅ በላያቸው ተደርበው አገልግለዋል:: ከአጥቢያ እስከ ዙፋን ፣ ከጭቃ እስከ ምስለኔ በተዘረጋ መዋቅር የሰላም

20 John Markakis, “Social Formation and Political Adaptation in Ethiopia”, JMAS, II,3(1973),pp.361,370. 21 Ibid, p.372. Christopher Clapham, “Centralization and Local Response in Southern Ethiopia”, African Affairs, 74, 294(Oxford University Press: 1975), p.78. Carmichael, “Approaching Ethiopian History,” pp.120 & 121. 22 Messay Kebede, Survival and Modernization, Ethiopia’s Enigmatic Present: A Philosophical Discourse. (NJ: The Red Sea Press, 1997). p.81. 23 MoI Files:No.1.2.68.05.

11

፣ የፍትህና የግብር ሥርዓት ማስተዳደሪያ ሆነዋል:: ያምሆኖ ከብሄርተኝነት አኳያ ትልቁ ቁምነገራቸው በተለያዩ ማህበረሰቦች ፣ መደቦችና ክልሎች መካከል የጋራ ሥርዓተ ህግጋትና ወጎችን በማበረታታትና የትስስር መንፈስን በማስፈናቸው ነው:: ዘመናዊ መንግሥታት ህጋዊ ተቋማት በመሆናቸው ህግ አውጭ ፣ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈፃሚ ተብለው በሶስት አበይት ክፍሎች ይዋቀራሉ:: ምንም እንኳን ይህ ዓይነቱ መዋቅራዊ ሙከራ ከ1900 ዓ.ም ቢጀምርም ፣ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፈጣን ፣ ሰፊና ውስብስብ የህግ ሥርዓት ግንባታ ሁነኛ መነሻ 1923 ዓ.ም ነው:: በተለይ በሃምሌ 1923 የታወጀው የተፃፈ ህገ መንግሥት አገር በቀሉን ከባዕዱ ለማዳቀል የሞከረ የመንግሥቱ ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ ነበር:: ይህ ሰነድም ሆነ በዚያው ዓመት የወጣው የዜግነት ህግ ዘመናዊት ኢትዮጵያን በህጋዊ ማህበረሰብነት ለመመስረት የሚደረገው ጥረት አካል ነበር:: ሌላው በ1923 ዓ.ም የወጣው የመጀመሪያው የወንጀል ህግም ለአገሪቱ ዘመናዊ የፍትህ ሥርዓት ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነበር::26 የ1923ቱ ህገ መንግሥት በአገር ግንባታው መንግሥታዊና ብሄራዊ ፈርጆች ላይ ካደረጋቸው መሰረታዊ ማሻሻያዎች አንዱ በመንግሥቱ ረዥም ታሪክ ተግዳሮት ከሆነው የሥልጣን ሽኩቻና ቀውስ የፀዳ ፣ ጠንካራና የተረጋጋ ዘውዳዊ ተቋም መመስረት ነው:: በአዋጁ አንቀጾች 3 እና 4 አልጋውን ከሰፊ ሥርወ መንግሥታዊ መሰረቱ አላቅቆ በኃይለሥላሴ ሀረግ ብቻ መወሰኑ ፣ ‹‹ለአልጋው ወራሽነት ያለውን ማናቸውንም ብዥታ ለመከላከልና በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን ፅኑ ጉዳት ለማስቀረት›› ነው::27 ነገር ግን ይህ የማዘመን እርምጃ የዘውዱን የብሄራዊ አንድነት ምልክትነት አደጋ ውስጥ ጥሎታል:: ሌላው የህገ መንግሥቱ ፋይዳ ዘመናዊ የዜግነት ድንጋጌ ማስተዋወቁ ነበር:: ከብሄረ ኢትዮጵያ ባለሁለት እርከን (ኃይማኖታዊ - ህጋዊ) የዜግነት ተመክሮ ኃይማኖታዊውን ቅድመ ሁኔታ በማስቀረት በግዛተ መንግሥቱ ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በእኩልነት ህጋዊ ዜግነትን አጎናፅፏል:: ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጆች በሙሉ የግዛተ አጼው ዜጎች በአንድነት ብሄረ ኢትዮጵያን ይመሰርታሉ›› ይላል::28 ይህ ሰነድ ገና ያልበሰሉም ቢሆኑ ዘመናዊ የዜግነት መብቶችና ግዴታዎች እሳቤን ለማስተዋወቅም ሞክሯል:: የተሻሻለው የ1948 ዓ.ም ህገ መንግሥትም የመንግሥቱን ብሄራዊ አቋም የሚያጠናክሩ ድንጋጌዎችን አስፍሯል:: በዋነኝነት አማርኛ ለአንድ

በአገሪቱ ውስጥ በየአካባቢው የነበሩትን ልማዳዊ የህግ ሥርዓቶች ከማስወገድ ይልቅ በላያቸው ተደርበው አገልግለዋል:: ከአጥቢያ እስከ ዙፋን ፣ ከጭቃ እስከ ምስለኔ በተዘረጋ መዋቅር የሰላም ፣ የፍትህና የግብር ሥርዓት ማስተዳደሪያ ሆነዋል ሚሊኒየም ገደማ በልሣነ መንግሥትነት ቢያገለግልም ፣ በይፋ የመንግሥቱ የሥራ ቋንቋ መሆኑ ተደንግጓል::29 ብሄራዊ ሰንደቁን ዓለማዊና አካታች ለማድረግ የአንበሳው (ቤተመንግሥት) እና መስቀሉ (ቤተክህነት) ምልክቶችን አስቀርቶ ሌጣውን በአረንጓዴ ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ወስኖታል::30 በሌላ በኩል ብሄሩን ሙሉ በሙሉ ከዘውዱ በመነጠል እውነተኛ የህዝባዊ ሉዐላዊነት እሳቤ ያንፀባረቀው የ1966ቱ ረቂቅ ህገ መንግሥት ነበር::31 ይህ ተግባራዊ ለመሆን ያልታደለ ሰነድ በዜግነት ረገድ (አንቀፅ 23) ማንኛውም ከወላጆቹ አንደኛው ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆኑን ደነገጎም ነበር::32 መንግሥትና ኃይማኖትን የማለያየት ግፊት የጀመረው በቅድመ ፋሽስት ወረራ ቢሆንም ፣ ቤተመንግሥትና ቤተክህነትን ከርዕዮትና ግብር አንድነት የነጣጠላቸው የ1966ቱ ህዝባዊ አብዮት ነበር:: ዘውዳዊው አገዛዝ ሲገረሰስ በመንግሥቱና በብሄሩ መካከል የነበረው አሃዳዊነትም በይፋ እንዲቀርና በርዕሰ ብሄርና በርዕሰ መንግሥት እንዲከፈል ተወሰነ:: ነገር ግን በጥንታዊው ዘውድ እግር የተተካው አዲሱ ፕሬዚዳንታዊ ርዕሰ ብሄር የኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ ተምሳሌት የመሆን ክብርን ለማግኘት አልቻለም:: በአጠቃላይ በዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ ሂደት ሥርዓተ ህግጋት ፣ ወጎችና ልማዶችን አስመልክቶ የተከናወኑት ለውጦች የየአገዛዙን ርዕዮተ ዓለም የሚያንፀባርቁ ነበሩ:: የዘውዳዊው አገዛዝ ጥገናዊ ማሻሻያ ዓለማቀፋዊ የሥነህግ ተመክሮዎችን እየቀዳ ደረጃ በደረጃ የሚገነባና በሥርዓተ ማህበሩ ላይ መሰረታዊ ለውጦችን ያላስከተለ ነበር:: ከላይ ከተጠቀሱት ሥርዓተ ህግጋት ለውጦች በተጓዳኝ የአገር ግንባታ መሰረቶች በሆኑት በአስተዳደር ፣ መሬት ስሪት ፣ በመዋዕለ ነዋይና በግብር ሥርዓቱ ላይ የተደረጉት ለውጦች ጉልህ ቢሆኑም ፣ ለአዲሱ ንዑስ ከበርቴ

ምሁራዊ መደብ ግን ለዘብተኛና አድሃሪ ነበሩ:: ስለዚህም እነዚህ አበይት ሥርዓተ ማህበራዊ ለውጦች የተካሄዱበት አብዮትና ወታደራዊው አገዛዝ የፖለቲካ ፣ ኤኮኖሚና ማህበራዊ ግንኙነቶች በሥርነቀል ሁኔታ የሚቀይሩ እርምጃዎችን ወስዷል:: በፈራረሰው ሥርዓት ምትክ የሚገነቡ መንግሥታዊና ብሄራዊ መዋቅሮችና ተቋማትን ፣ እንዲሁም ለነዚህ የሚስማሙ ህግጋትን ማውጣትና ተጓዳኝ ወጎችና ልማዶችን ማዳበር ነበረበት:: ይሁን እንጂ ደርግ ህገ መንግሥቱን በ1980 ዓ.ም እስካወጣበት ድረስ በአዋጅና ድንጋጌ ሲያስተዳድር ቆይቷል:: ኢህአዲግ በሰኔ 1983 ዓ.ም በድል አድራጊነት ምኒልክ ቤተመንግሥት ሲገባ የደርግ ህገ መንግሥት ገና በአግባቡ በስራ መዋል አልጀመረም ነበር:: ስለዚህም የመጀመሪያው ተግባሩ ይህንን የሚተካ ሥርዓተ ህግ ለመመስረት የሚያገለግል የሽግግር ቻርተር ማውጣት ነበር:: የኢህአዲግ አገዛዝ በዘውጋዊ ርዕዮቱ ላይ ተመስርቶ ያካሄደው የአገር ግንባታ ተግባር በከፊል ያለፉትን ሥርዓቶች ቅርሶች ለማፈራረስና አዲስ መንግሥታዊና ብሄራዊ ግንባታ ለማድረግ ያለመ ነበር:: የዚህም ሥርነቀል ተግባር እምብርት በርካታ ክልላዊ መንግሥታት ከነሙሉ ህገ መንግሥታቸው ፣ የህግና ፍትህ ሥርዓትና መንግሥታዊ ወጎችና ልማዶቻቸው በአዲስ ትልም መገንባት ነበር::

የአገር ግንባታው ባህሪያት የማንኛውም የአገር ግንባታ መድረሻ ግቦችና የብሄርተኝነት ርዕዮተ ዓለምና ንቅናቄ የሚያጠነጥንባቸው ቁልፍ ጉዳዮች ብሄራዊ ማንነት ፣ አንድነትና ዘላቂነት ናቸው::33 ከላይ ከአራት አምዶች አኳያ የተመለከትነው የኢትዮጵያ አገር ግንባታ ሂደት ልዩና ግልፅ የብሄራዊ ማንነት ንቃተ ህሊና ፈጥሯል? ጠንካራ የብሄራዊ አንድነት መሰረት ጥሏል? የአገሪቱን ህልውና ቀጣይነት አረጋግጧል?

24 ሀዲስ አለማየሁ ፣ የትምህርትና የተማሪቤት ትርጉም (አዲስ አበባ ፤ 1948 ዓ.ም)፣ ገፅ 122 ፣ 108. MoI Files: No.08.09, የመንግሥትን አስተዳደር መሻሻል ለማጥናት የተቋቋመው ኮሚቴ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ራፖር (አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 1957 ዓ.ም). 25 GPNRS Files: The 1953(1945 E.C) Annual Report of the Awraja Governor’s Office, No.232/ G/2, Nehassie 24/1945.Ibid., pp.120-137, 188-194. 26 Margery Perham, The Government of Ethiopia (1969), pp.140-41. 27 The 1931 Constitution.

12

በደምሳሳው ሲታይ በጥንታዊትና ታሪካዊት ኢትዮጵያ የተጣለው የብሄራዊ ማንነት መሰረት ለአገሪቱ አንድነትና ህልውና ወሳኝ ኃይል ሆኖ ከማገልገሉም በላይ በትውልዶች ቅብብሎሽ ወደ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ዘልቋል:: ይሁን እንጂ ዘመናዊው መንግሥት የወጠነውን አዲሱን ብሄርተኝነት በመገንባት ረገድ ማንኛውም አዘማኝ መንግሥት የሚያጋጥሙት የማንነት ፣ የአንድነትና የዘላቂነት ተግዳሮቶች ተደቅነውበት ነበር::34

3.1 ማንነት ብሄራዊ ማንነት አንድ ብሄር ውስጣዊ አንድነቱንና ከሌሎች አቻዎቹ ልዩነቱን የሚረዳበት ታሪካዊና ማህበረ-ሥነልቡናዊ ግንዛቤ ነው:: በኢትዮጵያ ማንነት አመሰራረትም ሆነ ግንባታ ረገድ ራስ-ገለፅነት (self-definition) ወሳኝ ነጥብ ነው:: ራስ-ገለፅነት ማለት አንድ ህዝብ የጋራ መጠሪያውን ከመሰየም ጀምሮ እያደር በውስጡ የሚጎለብትና የቡድኑን ማህበራዊና ህሊናዊ ድንበሮች የሚያሰምር ፤ አባላቱ ስለራሳቸው ያላቸውን ግንዛቤ የሚያዳብር አዳጊ የማንነት ስሜት ነው::35 ኢትዮጵያዊ ማንነት በታሪክ ሂደት በውስብስብ ድሮች የተገመደና ለብሄሩ አባላትና ለተቀረውም ዓለም ጭምር ‹‹ማነው ኢትዮጵያዊ ?›› የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፣ ህዝብና መንግሥት ብሄራዊ ማንነት ነው:: ስለዚህ እንደማንኛውም ብሄርነት የስሜትም የፖለቲካም ማህበረሰብነት ድምር ነው:: በአንድ ወገን መተሳሰሪያው የጋራ ርዕዮት ፣ ታሪክና ባህል የሆነና ያለፈውን እድልና ፈተና ተመርኩዞ የወደፊቱን እጣፈንታ ተስፋ የሚያደርግ የጋራ ስብዕና መንፈስ ነው:: በሌላ ወገን ኢትዮጵያዊነት በግዛተ መንግሥቱ የሚገኙ ዜጎች ሁሉ በፖለቲካዊ ማህበሩ አባልነት በቀጥታ በትውልድ የሚቀዳጁት ህጋዊ ሰውነት ወይም ዜግነታዊ ማንነት ነው:: ከዘመነ አክሱም እስከ 1966ቱ አብዮት በበላይነት የዘለቀው የብሄረ ኢትዮጵያ ማንነት በሥጋዊና መንፈሳዊ ወይም ትውልዳዊና ርዕዮታዊ (ኃይማኖታዊ) ዝምድና ላይ የተዋቀረ ግንዛቤ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ነገዳዊ ፣ አውራጃዊ ፣ ባህላዊና መደባዊ ዝንጉርጉርነት በደም

፣ በታሪክና በእምነት የሚቃየጡበት አሃዳዊ ማንነት ነው::36 የብሄረ ኢትዮጵያ ማቋቋሚያ ሰነድ የሚባለው ክብረ ነገሥት ይፋ እስከወጣበት እስከ መካከለኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጥብቅ መሰረት የያዘው የዚህ ማንነት ጥምር ባህላዊ መልኮች የኃይማኖት ጥራትና የሥልጣኔ የበላይነት ናቸው:: የኢትዮጵያን የእምነት ጥንታዊነት ፣ ንፁህነትና ትክክለኛነት ፤ የሥልጣኔዋን ገናናነት ፤ የመንግሥቷን ቀጣይነትና የነገሥታቷን ግርማዊነት ፤ የህዝቧን ኃይማኖተኝነት ፣ ደግነት ፣ ጀግንነትና ነፃነት ወዳድነት ያካትታል::37 ኢትዮጵያውያን በረዥም ታሪካዊ መስተጋብር ያዳበሩት የማንነት ሥነልቡና ወደኋላ ከታሪካዊትውፊታዊ መነሻቸው ፣ ወደፊት ከአገራቸውና መንግሥታቸው እጣፈንታ ጋር የተቆራኘ ነው:: ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ከመንግሥታት ሁሉ መርጦ በፀጋውና ረድኤቱ የማይለያትና ልዩ መሲሃዊ እጣፈንታ የተላበሰች ቅድስት አገር ፤ ብሄራዊ ራዕይዋም የፈጣሪዋን ተልእኮ መፈፀም መሆኑን አጥብቆ ያምናል::38 በሶስት ሺህ ዘመናት በሚሰላ ርዕዮታዊ ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሱ ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ጠንካራና ዘላቂ የማንነት ስሜት አዳብሯል::39 ይሁን እንጂ በተለይ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በመንግሥቱ የኃይል መዋዥቅ ፣ በእስላማዊ ኃይሎች ፣ በኦሮሞና ሌሎችም ዳራዊ ህዝቦች ፍልሰትና ወረራ ምክንያት በመንግሥትና ብሄር ግንባታው ሂደቶች ላይ ተደጋጋሚ መደናቀፍና አለመጣጣም ተከስቷል:: እስልምና ቀስ በቀስ ከጠረፋማው ወደ ማዕከላዊው ግዛት በመስፋፋት አንዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቀለም ሊሆን ችሏል:: የዚህ ሂደት ከፍተኛ ነጥብ የሆነው የግራኝ አህመድ ጦርነት (1517 – 1536 ዓ.ም) እስልምናን በክርስቲያናዊው ደጋማ እምብርት የተከለና የላቀ ተፅእኖ ላሳደረው የኦሮሞ ህዝብ መስፋፋት በር የከፈተ ነበር:: ከ16ኛው ምዕት ለጥቆ የነበሩት ሶስት ምዕታት የኢትዮጵያን ባህላዊና ፖለቲካዊ መልክዐ ምድር ለዘለቄታው የቀየሩ ፣ ነባሩን ብሄራዊ ርዕዮትና መንግሥት ያዳከሙና ከሞላ ጎደል የዘመናዊውን ኢትዮጵያ ገፅታ የቀረፁ ታላላቅ ክስተቶች አስተናግደዋል:: ማዕከሉን ጎንደር ያደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት ከ1625 እስከ 1761 ዓ.ም እነዚህን የእስላም - ኦሮሞ ጥምር ሃይሎች

ግስጋሴ መክቶ ሥልጣኑን ለማጥበቅ ፣ ቤተክህነትንና ጦር ሠራዊቱን ለማጎልበት አልቻለም:: እንዲያውም ሰፊውን የአገሪቱን ደቡባዊ ግዛት ተቀምቶ ለህልውናው የሞት ሽረት የሚታገል ነበር:: ዘመነ መሣፍንት (1761 – 1847 ዓ.ም) ይህ ሂደት በብሄራዊ ማዕከሉ ፍፁም መንኮታኮት የተደመደመበትና እስልምናና ኦሮሞነትን ያጣመሩ የየጁ የጦር አበጋዞች ሥልጣነ መንግሥቱን የተቆጣጠሩበት ዘመን ነበር:: ብሄራዊ መንግሥቱ በአውራጃዊ ኃይሎች የተከፋፈለበት ፣ ሰለሞናዊው ዘውድ ማዕረጉን ተገፍፎ ለታሪካዊ አንድነት ትዕምርትነቱ ሲባል ብቻ የተጠበቀበት ዘመን ነበር:: የየጁ መሳፍንት ባለፉት ሶስት ምዕታት በማዕከላዊውና ዳራዊው ማንነቶች መካከል የተደረገው ሰፊ መስተጋብርና ውህደት ውጤቶች ናቸው:: ስለዚህም በብሄራዊው ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉበት አቅም አዳብረዋል:: የብሄረ ኢትዮጵያን ማንነት አስገዳጅ መስፈርት ለማሟላት ኦርቶዶክስ ክርስትናን ተቀብለዋል:: አማርኛንም ልሣነ መንግሥት አድርገው ቀጥለዋል:: የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአገር ግንባታ የወረሳቸው ሁለት የብሄራዊ ማንነት እርከኖች ናቸው:: በአንድ ወገን በፖለቲካዊም ባህላዊም (በዋነኝነት ኦርቶዶክስ ኃይማኖት) ዝምድና የተሳሰሩ ፣ የአገሪቱ ጠንካራና ግልፅ የማንነት ስሜት መሰረቶችና የአገር ግንባታው አስኳል ማህበረሰቦች:: በሌላ ወገን ደግሞ ብሄራዊ ማንነታቸው በመንግሥቱ ፖለቲካዊ ዝምድና የተወሰነ ፣ ከማዕከሉ በተለያየ የስሜትና ታማኝነት ርቀት ላይ የሚገኙ ዳራዊ ማህበረሰቦች ናቸው:: የብሄረ ኢትዮጵያ አሃዳዊ ማንነት በርካታ ባህላዊና ኃይማኖታዊ ማህበረሰቦችን ያገለለ ነበር:: ዘመናዊው የአገር ግንባታ የኢትዮጵያዊነትን አገራዊ ፣ ህዝባዊና መንግሥታዊ ማንነት ግንዛቤ የማሻሻልና የመቀየር ሂደት ነው:: ዓላማውም የአገሪቱን ብዝሃነት በእኩል ማስተናገድና በስሜታዊውና ፖለቲካዊው ፣ በአስኳሉና ዳሩ ማንነቶች ድንበር መካከል ያለውን ርቀት ማጥበብ ነበር:: ይህ ኢትዮጵያዊነትን የማዘመን አዎንታዊ እርምጃ ተቀዳሚ ትኩረቱ የኢትዮጵያን መለኮታዊ ስብዕና ወደ ዓለማዊ ስብዕና መለወጥና አሮጌውን ባለሁለት እርከን ማንነት በአንድ ህጋዊ ማንነት ወይም ዜግነት መተካት ነበር::

28 The 1931 Constitution, Article 1. 29 Ibid.: Article 124: Article 125. 30 The Revised Constitution of 1955, NEGARIT GAZETA, 15th Year, No.2, Addis Ababa, November 4, 1955: article 1; article 21. Articles 38 and 40.

31 The 1974 Draft Constitution, Article 1.1. 32 Ibid., Articles 1.2, 1.3, 5, 7, 23. 33 Handler (1988), pp.6-8.

34 Christopher Clapham, Third World Politics: an Introduction (University of Wisconsin:1985/1988), p.16. 35 Day and Thompson, p.148.

13

ይሁን እንጂ ዘመናዊው የማንነት ግንባታ ጉልህ ውሱንነቶችም ነበሩበት:: ዘመናዊት ኢትዮጵያ እንደ ብሄረ ኢትዮጵያ ለአዲሱ የአገር ግንባታ የሚሆን ግልፅ ፣ ጠንካራና ዘላቂ ርዕዮተ ዓለም አልገነባችም:: በተለይ ከተማሪው ንቅናቄ አንስቶ በደርግና በኢህአዲግ አገዛዞች ጭምር በጅምላ ተቀድተው ለአገር ግንባታ የዋሉት ፖለቲካዊ ርዕዮቶች ባዕድ ፣ ግልብና ዋዣቂ በመሆናቸው የብሄሩን ማንነትና እጣ ፈንታ በግልፅ አያስቀምጡም:: የዘመነ ደርግ የአገር ግንባታ ከብሄር ግንባታ ይልቅ የመንግሥት ግንባታ ያመዘነበት ነበር:: በሙሉ ልብ ያልተያዘው የሶሻሊስት ኢትዮጵያዊነት ግንባታ ህዝባዊ መሰረት ስላልነበረው ህልውናው ከአገዛዙ እድሜ አልዘለለም:: ዘመነ ኢህአዲግ ደግሞ አገራዊ ብሄር ግንባታው ፍፁም ችላ ተብሎ በንዑስ ብሄራዊ ማንነቶች ግንባታ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር:: ዘውጋዊ የፌዴራል ሥርዓቱ ‹‹ህገ መንግሥታዊ አርበኝነት›› የሚባለውን ሳይቀር የአገራዊ ማንነት ግንባታን ያዳከመ ነበር:: ስለዚህም የጋራ ህዝባዊ ባህልና እሴቶች እየከሰሙ ፣ ከብሄራዊ ማንነት ይልቅ አካባቢያዊና ዘውጋዊ ማንነቶች እየጎሉ መጥተዋል:: በአጠቃላይ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ በአገሪቱ ያሉትን ብዝሃዊ ማንነቶች የሚሻገር የጋራ ልዕለ ዘውጋዊ ስብዕና ሊፈጥር አልቻለም:: የአዲሲቱ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ የብሄረ ኢትዮጵያን ቅርስ በአግባቡ ለመጠቀም አልቻለም ወይም አልፈለገም:: ወይም ደግሞ ለታሪካዊው ማንነት የረባ አዲስ አማራጭ አላቀረበም:: ዘመናዊው ትውልድ ለባዕዳን ተፅእኖ የተጋለጠና የማንነት ቀውስ የሚያራዠው መጢቃ በመሆኑ ፣ ለመናፍቃዊና ጨለምተኛ አስተሳሰቦች ሰለባ ሆኗል:: የመንግሥቱ ህልውና የተመሰረተው በሥልጣኔ አራማጅነት ስለሆነ ፣ ብሄራዊ ራዕዩ የምጣኔ ሀብታዊ ብልፅግና ነው:: ስለዚህም ለአዲስ ብሄራዊ ማንነት አስተማማኝ መሰረት አልተጣለም::

አንድነት ብሄራዊ አንድነት ማለት የተለያዩ ማንነትና ፍላጎት ያላቸውን ማህበረሰቦችና ቡድኖችን በጋራ ታሪክ ፣ ባህልና ራዕይ ማስተሳሰር ነው:: በህዝብና መንግሥት መካከል ፣ በመንግሥት ልዩ ልዩ አካላትም መካከል የሚፈጠር የግብርና የዓላማ አንድነት ነው:: ብሄራዊ አንድነት መሰረታዊ ልዩነቶችን ሳይጨፈልቅ ብዝሃነትን በቁልፍ ላዕላይ ትስስሮች የሚያዛምድና የተቀናጀ መስተጋብራዊ ሥርዓት የሚፈጥር አንድነት ማለት ነው::40

ታሪካዊው ኢትዮጵያዊነት በርዕዮታዊ ፣ ባህላዊ ፣ ታሪካዊና ሥነልቡናዊ አንድነት ላይ የቆመ ብሄርተኝነት ነው:: አገርን ፣ ህዝብና መንግሥትን በአንድ አስተምህሮ ፣ በአንድ መንፈስ ፣ በአንድ ልሣን ፣ ለአንድ ዓላማ የሚያቆራኝ ማህበረሰብ ነው:: ከንጉሥ እስከ ባላገር ያሉ ማህበራዊና መደባዊ እርከኖች ሽቅብ በጋራ ርዕዮትና ባህል እየታረቁ የአንድነት መንፈስ የሚጋሩበት ማህበር ነው:: ብሄር የሚለው የግዕዝ ቃል እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊነት የማይነጣጠል ተፈጥሮአዊ አንድነት አላቸው:: የብሄረ ኢትዮጵያ አንድነት ከላይ ለፖለቲካዊው መንግሥትና ለኦርቶዶክስ ኃይማኖት በሚኖር ታማኝነት ፣ ከታች ደግሞ በማህበረሰቦች ታሪካዊና ባህላዊ አብሮነት ሀረጎች የታሰረ ነበር:: ዘውዳዊው መንግሥት የኢትዮጵያ አስኳልና ዳር ማህበረሰቦች አንድነት አብይ ተቋማዊ ሰንሰለት ነበር:: የፖለቲካ ሥርዓቱ በማዕከላዊና (centripetal) ተስፈንጣሪ (centrifugal) ኃይሎች መካከል በሚደረስ ሚዛን ላይ የተመሰረተ ነበር:: የኢትዮጵያ መንግሥት በረዥም ታሪኩ በግዛቱ ያሉትን ዘውጋዊ ፣ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ብዝሃነቶች በአንድነት የማሰለፍ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አቅም አደርጅቷል:: በመላ አገሪቱ የሰላም ፣ የፍትህና የግብር ሥርዓት ዘርግቶ በጋራ ህጋዊና ፖለቲካዊ ማዕቀፎች ያስተሳስራል:: በዜግነት መብቶችና ግዴታዎች ያስተሳስራል:: በጋራ መስዋዕትነትና አርበኝነትም ብሄራዊ አንድነት ያጠናክራል::41 ከመንግሥቱ በተጓዳኝ የአገሪቱ ብዝሃዊ ማህበረሰቦች በበርካታ ድንበር ተሻጋሪ ሀረጎች የተሰናሰሉ ነበሩ:: ከጋራ መልከዐ ምድር ጀምሮ የጋራ ኃይማኖቶች ፣ ቋንቋዎች ፣ እሴቶች ፣ ተመክሮዎች ፣ አብሮ መኖርና ሰጥቶ መቀበል ያደረጃቸው እድሜ ጠገብ ማህበራዊ ግዴታዎች ፣ ደንቦችና ወግ ልማዶች የአንድነቱ ታህታይ መሰረቶች ናቸው:: እንደ ክርስትናና እስልምና ያሉ ነባር ኃይማኖቶች ዘውጋዊና አካባቢያዊ ድንበሮችን የሚሻገሩና በጋራ ባህላዊና ፖለቲካዊ አውድ ላይ የበቀሉ ናቸው:: ግዕዝ የብሄራዊ አንድነት አማርኛ ደግሞ የመንግሥታዊና ህዝባዊ አንድነት መሣሪያዎች ሆነው አገልግለዋል:: የአገር ግንባታው የስሜትና የፖለቲካ ገፅታዎች መሳ ለመሳ የሆኑበትና ፍጹም ብሄራዊ አንድነት ያለው አገር የሚገኘው በተምኔታዊው ዓለም ብቻ ነው:: ኢትዮጵያውያንም ስለአገራቸው ፣ መንግሥታቸውና ብሄራዊ ማንነታቸው የሚኖራቸው ስሜትና ቅንዐት ወይም አገር ወዳድነት ፣ አርበኝነትና ህዝባዊነት መንፈስ በማንኛውም ወቅትና በመላ አገሪቱ ወርድና ቁመት

ወጥና ያልተዛነፈ ሊሆን አይችልም:: ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋነኝነት የመንግሥቱ ፖለቲካዊ ቁመና በተለዋወጠበት ፍጥነትና ስፋት ልክ ፣ በማዕከሉና ዳርቻው ወይም በነባሩና አዲሱ ማንነቶች መካከል በቂ ባህላዊና ትዕምርታዊ ትስስር አለመደርጀቱ ነው:: የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የዜግነት ህግ ያቆመው ፣ በፖለቲካዊውና ስሜታዊው ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ክፍተት በመድፈን ብሄራዊ አንድነትን ለማጎልበት ነው:: ዘላቂነት ባይኖራቸውም በህዝብና መንግሥት መካከል አዲስ ባህላዊና ርዕዮታዊ አንድነት ለመፍጠርም ሙከራዎች ተደርገዋል:: ነገር ግን ከጥረቶቹ ሁሉ በመንግሥቱ ላይ የተደረጉት ሥርነቀል መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ለውጦች በከፍተኛ ደረጃ የተማከለና ጠንካራ ተቋም መፍጠር ተሳክቶላቸዋል:: በአጠቃላይ ዘመናዊ ኢትዮጵያዊነት ያበበበትና አገሪቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደተዋሃደ ብሄራዊ መንግሥትነት የቀረበችበት ወቅት መቼ ነው ቢባል የ1950ዎቹ አሰርት ይመስላል::42 በሌላ በኩል አስገራሚነቱ በመጭው ዘመናት ለአገር ግንባታው ጥረት ፅኑ ተግዳሮት የሚደቅኑ ተቀናቃኝ ርዕዮቶችና ኃይሎችም ያቆጠቆጡት በዚሁ አሰርት ነበር:: ዞሮ ዞሮ የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ የታሰበውን ብሄራዊ አንድነት ለማምጣት አልቻለም:: የዘውዳዊው መንግሥት የማዘመን እርምጃዎች በታሪካዊት ኢትዮጵያ አስኳል ማህበረሰብ መካከል የፈጠረው ስንጥቅ ቀዳሚው ተግዳሮት ነበር:: ኃይለሥላሴ አልጋውን ከታሪካዊው ብሄር ቁርኝት ለመነጠል ያወጁት የገደብ ህግ መራር ተቃውሞ የገጠመው የሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥት ተጋሪ ከነበሩ ወግ አጥባቂ አውራጃዊ መሣፍንቶች ነበር::43 በሌላ ወገን የዘውዱ ዘገምተኛ ተራማጅነት ያላረካቸውና ለበለጠ መሰረታዊና ትርጉም ያላቸው ለውጦች ግፊት የሚያደርጉ ኃይሎችም ከራሱ ከመንግሥቱ ውስጥ በመነሳት በ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እስከማድረግ ደርሰዋል:: ከ1960ዎቹ መባቻ አንስቶ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ኡደት እየተቆጣጠረ የመጣው የአዲሱ ትውልድ ሥርነቀል አብዮተኝነት በአባቶቹ ላይ ሙሉ ትውልዳዊ ጦርነት በመክፈት ፣ ከናካቴው የታሪክና የባህል እትብቱን የበጠሰና የአገር ግንባታውን ሽግግር ያከሸፈ ነበር:: አማፂው ትውልድ በውስጡ የተፈለፈሉትን

36 Adrian Hastings, The Construction of Nationhood: Ethnicity, Religion and Nationalism (Cambridge &New York: Cam bridge University Press, 1997/2007). 37 Eriksen, Ibid., p.103; pp.108-109. 38 ክብረ ነገሥት. 39 አለቃ ታዬ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ (አዲስ አበባ፤ ቅድስ ጊዮርጊስ ማተሚያ ቤት 1914 ዓ.ም) ገፅ 21. 40 Handler, pp.6-8. Steven Grosby, (1991), p.240.

14





ርዕዮታዊ ልዩነቶች በማቻቻል የራሱን አንድነት ለማስፈን ፣ በአገራዊ ጉዳዮችም የጋራ መግባባት መፍጠር አልቻለም:: ከናካቴው በጠላትነት እየተቧደነ ከሃሳብ ወደ ትጥቅ ሽኩቻ በመካረር ለውድቀት ተመቻቸ:: ከዚሁ አብዮታዊ ትውልድ የተገነጠለው ዘውጋዊ ጎራም የኢትዮጵያን ብሄራዊ አንድነት በግልፅ ለመፈተን ታጥቆ ተሰለፈ:: በአገሪቱ ውስጥ ከኃይል በመለስ የጋራ የፖለቲካ አውድ ጠፋ::

፣ ታሪክና ትውስታ እንዲሁም ስለመፃኢ እጣፈንታው የሚኖረውን ቀጣይነት ይመለከታል:: ከጊዜ አንፃር ዘላቂነት በታሪክ ያልተቋረጠና የተመዘገበ ቀጣይነት ነው:: ይህ ማለት ግን በለውጥ ውስጥ ያለ ቀጣይነት ነው:: አንድ ብሄር የቀጣይነት ስሜቱን ሳያጣ ከፊሉን ወይም ጠቅላላውን ውጫዊ ባህሪያቱን ሊለውጥና ሊተው ይችላል::44 የኢትዮጵያ አገር ግንባታ መድረሻ ግብ ብሄራዊ ቀጣይነትን ማረጋገጥ ነው:: በዚህ ረገድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ዘላቂነት አንዱ መሰረት ግልፅ ብሄራዊ ርዕዮትና ራዕይ ነው:: ሰለሞናዊው ትውፊት ከይሁዲነት አልፎ ወደ ክርስትና የተሻገረ ታሪካዊ ፣ ባህላዊና ሥነልቡናዊ ዘላቂነት መስርቷል::45 ብሄረ ኢትዮጵያን በኃይማኖታዊ ሀልዮትና በሥርወ መንግሥታዊ መርህ በማረቅ የመንግሥቱን መረጋጋት ፣ ፅናትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ አስችሏል:: እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊነት የማዕዘን ድንጋይና የአገር ግንባታው ዘላቂ መሰረት ሆኖ አገልግሏል::46

በ1966 ዓ.ም አብዮቱን ከዳር ያደረሰው ወታደራዊ ደርግ በአገራዊ አንድነት ረገድ የማያወላውል አቋም ነበረው:: እንዲያውም የአገዛዙ ርዕዮት እምብርትና የቅቡልነቱ መሰረት ብሄራዊ ሉዐላዊነትና አንድነት ነበር:: እነዚህን ከባዕዳን ወራሪዎችም ሆነ ከዘውጋዊ አማፂያን ተከላክሎ ለማስጠበቅም ለ17 ዓመታት ሃልዮታዊና ወታደራዊ ዘመቻ አድርጓል:: ንዑስ ብሄራዊ የማንነትና የመብት ጥያቄዎችን ከሰላም ይልቅ በጉልበት ለማፈን ሞክሯል:: ይሁን እንጂ የደርግ ሶሻሊስታዊ ኢትዮጵያዊነት እጅግ መሰረተ ጠባብ በመሆኑ ዓለማቀፍ የሶሻሊስቱ ጎራ ከደረሰበት ውድቀት ጋር አብሮ ሊንኮታኮት ችሏል::

ሌላው የኢትዮጵያ አገር ግንባታ ዘላቂነት መሰረት ህዝባዊ ባህል ነው:: ኢትዮጵያውያን ከቀደምት አባቶቻቸው ባህሎችና እሴቶች ቅርስ ጋር ያላቸውን የቀጣይነት ስሜት ይመለከታል:: እነዚህ ባህላዊ መሰረቶች እንደ ኃይማኖት ያሉ ሁሉን አቀፋዊ (universal) ባህሪ ያላቸው ፅኑ እሴቶች ይሁኑ እንጂ ፣ እያንዳንዱ ትውልድ ለኢትዮጵያዊነት ባህላዊ ንጣፍ የየተመክሮውን ድርሻ ማዋጣቱ አይቀርም:: በዚህ ዓይነት የለውጥና ቀጣይነት መወራረስ ህዝባዊው ባህል ከታሪክ እየተስማማ የኢትዮጵያን ማንነት በጊዜና በቦታ የሚያሸጋግር ዋነኛው ድልድይ ነው::

የደርግ መውደቅ እንደ አንድነቱ ጎራ ሽንፈት ተቆጥሯል:: ስለዚህም በወታደራዊ ድል ሥልጣን የያዘው የኢህአዲግ የአገር ግንባታ በአሸናፊው ዘውጋዊ መርህ ላይ የተመሰረተ ነበር:: አገራዊ አንድነትን አክስሞ በዘውጋዊ አንድነት ላይ ፌዴራላዊ ሥርዓትም አዋቅሯል:: ይሁን እንጂ በአገራዊና ህዝባዊ ሉዐላዊነት የተተካው የብሄር ፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሉዐላዊነት ከአንድነት ይልቅ መነጣጠልን ያበረታታ ይመስላል:: እያደር ማህበራዊና ፖለቲካዊ ክፍፍሎች የገነኑበት ፤ በብሄራዊና ንዑስ ብሄራዊ ማንነቶች መካከል ባላንጣነት የተካረረበት ሥርዓትን ወልዷል:: በደምሳሳው የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ ሂደት ፖለቲካዊው መንግሥት ባህላዊውን ብሄር አለቅጥ የተጫነበት ወይም ወደዳር የገፋበት ነበር:: ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎችም ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የተነሳ ፣ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ከጥንካሬው ይልቅ ልፍስፍስነቱና ተከፋፋይነቱ ሊያመዝን ችሏል:: ከናካቴው ከኢትዮጵያዊነት መንፈሱ እየራቀ ወደ ዘውጋዊና አውራጃዊ ጥጋጥግ በመንሸራተቱ ርዕዮታዊ ውዥንብር ፣ ሰፊና መዋቅራዊ የማህበረሰቦችና ቡድኖች ፍትጊያና ግጭት ፣ አልፎም ብሄራዊ የመበታተን ስጋት አስከትሏል::

ዘላቂነት ዘላቂነት የአገር ግንባታውን ታሪካዊና ህሊናዊ ቀጣይነት የሚያሳይ ግንዛቤ ነው:: በተከታታይ ትውልዶች መካከል ስለአንድ ማህበረሰብ የጋራ ባህል

ማንኛውም አዎንታዊ የግንባታ ጥረት ታሪካዊና ባህላዊ ቀጣይነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል:: በአዲሱ የብሄርተኝነት እሳቤ ውስጥ ነባሩን ማንነት ችላ ማለት ፅኑ ግድፈት ነው

የኢትዮጵያዊነት እሳቤ ለረዥም ዘመናት ተጠብቆ ሊኖር የቻለው በሰፊው ብሄራዊ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ ነው:: ለዚህም አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያዊነት አዳዲስ ርዕዮታዊና ወታደራዊ ኃይሎችን ለማስተናገድና በየጊዜው የሚፈጠሩ ለውጦችን ለማጣጣም ያለው አንፃራዊ አቻቻይነትና ክፍትነት ነው:: አጠቃላይ የሥርዓቱ ማህበራዊ ክፍትነትና የእድገት መሰላሎችን ዘርግቶ ከአስኳል ማህበረሰቡ ውጭ ያሉ ዘውጎችንና ባህሎችን ማካተቱ የአገር ግንባታው በራስ የመተማመን ምልክት ነው::47 በየዘመኑ ኢትዮጵያ ስትዳከም መልሳ የምታንሰራራው በባህላዊና መንፈሳዊ ጥንካሬዋና አቻቻይነቷ ነው:: በዚህ ረገድ ታሪካዊው የአድዋ ድልም ሆነ የአምስቱ ዓመታት የአርበኝነት ተጋድሎ መንግሥትና ብሄር በአገሪቱ ህልውና ላይ ያላቸውን ታሪካዊ ሚና በግልፅ ያሳዩ ናቸው:: የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ ሩሲያና ጃፓን በተሳካ ሁኔታ የአውሮፓን ቅኝ ወረራ

40 Handler, pp.6-8. Steven Grosby, (1991), p.240. 41 Merid Weldearegay, “Southern Ethiopia and the Christian Kingdom ,1508-1708. With Special Reference to the Galla Migrations and their Consequences.” (Ph.D. Dissertation: London SOAS,1971),pp.65-67,72. 70-71,74. 42 Bahru Zewde(ed), Documenting the Ethiopian Student Movement: An Exercise in Oral History (Addis Ababa:2010),p.1. 43ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፣ ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ (ኢንግላንድ ፤ ባዝ 1929 ዓ.ም) I, ገፅ.147.

15

የመከላከል ብቃቱንና ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ጥልቅ ታሪካዊና ማህበራዊ መሰረት እንዳለው ያረጋገጡ ናቸው:: በተለይ የአምስቱ አመታት የጀግንነት ተጋድሎ የኢትዮጵያውያን ጠንካራ የብሄራዊ ማንሰራራት አቅም ምስክር ነው::48 የአዲሲቱ ኢትዮጵያ እሳቤ ብሄራዊ መሰረቱን ከእምነት ወደ ፖለቲካዊ ርዕዮት በመቀየሩ ፤ ለኢትዮጵያዊነት ሰፊ ትርጉም የሰጠና ብዝሃዊነትን የሚያስተናግድ እርምጃ መሆኑ አይካድም:: ነገር ግን እያደር አቅጣጫውን የሚያስቱ ድክመቶችንም የፀነሰ ነበር:: በተለይ የግንባታው ርዕዮተ ዓለም ጉራማይሌና ከአገዛዞች ዕድሜ የማይሻገር በመሆኑ የተነሳ የሚያስከትላቸው ለውጦች ቀጣይነት አልነበራቸውም:: ከባህላዊ ግንባታ አኳያ ነባሩን ባህላዊ ቅርስ መልኩን አሻሽሎ ለመጠቀም የተደረገው ጥረት አመርቂ አልነበረም:: ከባህል ፣ ትምህርትና ማስታወቂያ ሚኒስትሮች አንስቶ የብሄር ግንባታውን የሚመሩ መንግሥታዊና ህዝባዊ አካላት ዘመናዊና አካታች ባህል ለመገንባት ያደረጉት ጥረት በርዕዮታዊና መዋቅራዊ ውዥቀት የተጎዳ ነበር:: የባህል ቀጣይነቱ አብይ መዘውር የነበረው ዘመናዊ የትምህርት ሥርዓት አገራዊ መሰረቱን ትቶ ሙሉ በሙሉ በባእድ አስተምህሮ መተካቱ ትውልዳዊ የባዕድ አምልኮና የባህል ውልቃት ያስከተለ ይመስላል::49 የግራ ዘመሙ አብዮተኛ ትውልድ የአገር ግንባታ እሳቤ በነባሩና አዲሱ ፣ በጥንታዊውና በዘመናዊው ፣ በሩቁና በቅርቡ መካከል ተቃርኖአዊነትን አስፍኗል:: ቀጣይነትን ሳይሆን አዲስ ጀማሪነትን ታሪክ ሰሪነትን የሚያራምድ በመሆኑ ረዥም የታሪክ እይታና ሃላፊነት መንፈስ ተዳክሟል:: በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክ ግፋ ቢል ከአፄ ቴዎድሮሥ የሚሻገር አልነበረም:: ከነባሩ ኢትዮጵያዊነት ጋር የሚጣጣምበት ብልሃት ባለማግኘቱ ፣ እትብቱን ቆርጦ የመጣል ሂደት ውስጥ ገብቷል:: በተለይም የደርግና ኢህአዲግ አገዛዞች የተከተሏቸው ስልቶች የባህል ፖለቲካ ተፅእኖ ያረፈባቸው ፣ በብሄራዊና በዘውጋዊ ማንነት ላይ አፅንኦት የሚያደርጉ ፣ አንዱ ለሌላው ተቃርኖአዊና አፍራሽ ነበሩ:: ወታደራዊው አገዛዝ የብሄረ ኢትዮጵያ ቅርስ በጅምላ ሰፊውን ህዝብ የማይወክል የፊውዳል ቅርስ ነው በማለት አውግዞ ከአዲስ ለመነሳት ሞከረ:: በተራው ኢህአዲግ ደግሞ ከእኔ በፊት የነበሩት ሥርዓቶች በሞላ አንድ ዓይነትና በጅምላ ብሄረሰቦችን የማይወክሉ ናቸው በማለት ሌላ አዲስ ግንባታ ጀመረ:: በአጭሩ ዘመናዊው የአገር ግንባታ መሰረተ ሰፊ ፣ አስተማማኝና ዘላቂ ብሄራዊ ባህልና ማንነት ለመገንባት አልታደለም::

የሚያደርግ ሊሆን ይገባል::

ምን ይደረግ ? የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ከሥርወ መንግሥታዊ ወደ አብዮታዊ ከዚያም ወደ ዘውጋዊነት ባደረገው ታሪካዊ ጉዞ ምክንያት የጥንታዊነትና ዘመናዊነት ፣ ዜግነታዊነትና ዘውጋዊነት ፣ ባህላዊነትና ፖለቲካዊነት ፣ ወዘተ መንትያነቶች በአገሪቱ ብሄራዊ ማንነት ግንዛቤ ፣ የብሄርተኝነት ፖለቲካና ጥናት ውስጥ በሰፊው ይንጸባረቃሉ:: ስለዚህም ተቀዳሚው እርምጃ እነዚህን ጉራማይሌዎች የሚያስተናግድ ለአገር ግንባታው መሰረት የሚሆን ግልፅና አካታች ርዕዮተ ዓለም መንደፍ ይሆናል:: ህዝብን ከህዝብ ፣ ህዝብን ከመንግሥት ፣ እንዲሁም የመንግሥትን አካላት በአዎንታዊነት የሚያቀራርብ መሆን አለበት:: የአገሪቱን የታሪክና ባህል ቀጣይነት የሚያረጋግጥና መፃኢ እጣፈንታዋንም በግልፅ የሚያስቀምጥ መሆን አለበት:: ከዚህም አልፎ አገራዊነት/ብሄራዊነትና ዘውጌነት የሚደጋገፉበትን መንገዶች መተለም ያስፈልጋል:: ምንም እንኳን ለብሄራዊው መንግሥት የሚኖር ውዴታና ታማኝነት መገለጫ እንደየማህበረሰባዊና ወቅታዊ ጭብጦች ቢወሰንም ፣ አገራዊነት ከዘውጌነት ንቃተ ህሊና ጋር አብሮ ተባብሮ ሊኖር ይችላል:: ኢትዮጵያና ብሄረሰቦቿ በተቃርኖ የቆሙ ሳይሆኑ ፣ ተደጋጋፊዎችና አንዱ ያለሌላው የተሟላ ትርጉም የማይሰጡ ናቸው:: ከታሪካችን እንደምንገነዘበው የአገሪቱ ህልውና ምርጫ በአሃዳዊነትና በመበታተን መካከል አይደለም:: ሁለቱም ተሞክረው ያላዋጡ መንገዶች ናቸው:: ስለዚህም ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአገር ግንባታ ሥርዓት ብዝሃነትና አሃዳዊነትን በዴሞክራሲ አማካይነት የሚያቻችል ነው:: ፌዴራሊዝም ለብዝሃነት ባለው ትኩረትና ዴሞክራሲ ለእኩልነት ባለው ትኩረት መካከል አለመጣጣም የለም:: ብዝሃዊ መንግሥታት በመገንባት ረገድ ቀንደኛው ተግዳሮት ህዝቡ መንታ ዘውጋዊና ብሄራዊ ማንነት እንዲላበስ ማስቻል ነው:: ለዚህም ማንነት ንብርብራዊ ተፈጥሮ እንዳለውና በደመነፍሳዊ ጥጎች ብቻ እንደማይገደብ መገንዘብ ያስፈልጋል:: ያለንበት ፌዴራላዊ ሥርዓት በዋነኝነት በቋንቋ መሥፈርት የተሰራ መሆኑ መሰረታዊ ግድፈቱ ነው:: በተጨማሪ አብዛኞቹ የፌዴራል ሥርዓታችን ግዛታዊ አሃዶች ታሪካዊ መሰረት የላቸውም:: ይህም የክልሎችን ተቀባይነት አሳንሶታል:: ስለዚህም ተመራጩ የአገር ግንባታው ርዕዮት የባህል ነፃነትን ወይም ራስ ገዝነትን ኢግዛታዊ (በኮንሶሽየሽናል ዴሞክራሲ ተመራጩ)

የፌዴራል ሥርዓቱን ከዘውጋዊነት ወደ አስተዳደራዊነት አሃዶች መቀየር ብቻ አይበቃም:: አሁን እንደሚታየው ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ከአገር አቀፋዊ ትብብር ይልቅ የክልሎች ፉክክር ማዕቀፍ እንዳይሆን ፣ በክልሎችም ሆኑ ክፍለ ሀገራት መካከል ጠንካራ ድንበር ተሻጋሪ ትብብሮችና ትስስሮችን መፍጠር ያስፈልጋል:: የአገር ግንባታ እቅዶች የዜጎችን ባህላዊ አድማስ በድምር በሚያሰፉ እርስ በርሳቸው በሚሰናሰሉና በሚመጋገቡ ለውጦች መተለም አለበት:: ከርዕዮታዊና ባህላዊ ጉዳዮች በተጨማሪ መሰረቱ ሰፊ የሆነ ማህበረ ኤኮኖሚያዊ ተፅእኖዎችንም ማካተት አለበት:: አገር ግንባታ ነባሩን የሚያጠናክር ፣ የሚያሻሽልና አዲስ የሚፈጥር ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስልቶችን ያቀናጀ መሆን አለበት:: ማንኛውም አዎንታዊ የግንባታ ጥረት ታሪካዊና ባህላዊ ቀጣይነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል:: በአዲሱ የብሄርተኝነት እሳቤ ውስጥ ነባሩን ማንነት ችላ ማለት ፅኑ ግድፈት ነው:: በተጨማሪም የአገር ግንባታውን በአገር በቀልና በማህበረሰቦች የጋራ እሴቶች ላይ መመስረትም የማይታለፍ ቁምነገር ነው:: የአገር ግንባታ በሁለት መልኩ በላዕላዊና ታህታዊ መዋቅሮችና ሂደቶች የተቀናጀ መሆን አለበት:: መንግሥት በግንባታው ሂደት ማዕከላዊ ቦታ ቢኖረውም ፣ በተጓዳኝ ከታች በሰፊው ህዝብ ፈቃዳዊ ጥረት የሚደገፍ መሆን አለበት:: በኢትዮጵያ እንደታየው መንግሥታዊ ብሄርተኝነት ራሱ በታሪክና በፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍ ተፅእኖዎችና በፖለቲካዊ ብልጠት የተነሳ አገራዊነቱ ወይም ዘውጋዊነቱ ሊጎላ ይችላል:: ለዚህ ሚዛን የሚያስይዝ ዘላቂ ህዝባዊ ብሄርተኝነት ማስፋፋት ያስፈልጋል:: የአገር ግንባታው በልሂቃዊ መደቦች ተንጠልጥሎ እንዳይቀር በስፋትና በጥልቀት ከህዝባዊነት ጋር ማጣጣም ተገቢ ነው:: በአጠቃላይ በአገር ግንባታው ሂደት ማን ምን እንዴት ይስራ የሚለው ፍኖተ ካርታን በጥንቃቄ ማዘጋጀት ታላቅ ትኩረት የሚጠይቅ ሥራ ነው:: የፖለቲካ ተዋናዮች ፣ መንግሥታዊና ህዝባዊ ተቋማት የህዝባቸውን ብሄራዊ ማንነት በመቅረፅ ጥረት ላይ ሊሰሩ የሚፈቀድላቸው ፣ የሚበረታቱት ፣ የሚፈለግባቸው ወይም የሚከለከሉት ተለይቶ ሊታወቅ ይገባል:: የአገር ግንባታው ባህላዊ ዘርፍ ህዝባዊ ትዕምርቶችን በየትኞቹ የጋራ እሴቶች ላይ ይገንባ ፤ ከታሪካችን የጋራ ብሄራዊ ትውስታን በመገንባቱ ጥረት የቱ ይፈቀድ ፣ ይበረታታ ወይም ይከልከል የሚሉትን በቅጡ የሚለይ ሊሆን ይገባል::

44 Smith, National Identity,p.25. 45 Messay, Surviva, p.57. 46 Adrian Hastings, The Construction of Nationhood: Ethnicity, Religion and Nationalism (Cambridge University Press: 1997/2007), p.150. 47 Hastings (1997), p.27. 48 ተድላ ዘዮሃንስ፣ ገፅ 67 ፤ ብርሃኑ ድንቄ፣ ገፅ.22,29 49 Messay Kebede, Radicalism and Cultural Dislocation in Ethiopia, 1960 – 1974 (New York: University of Rochester Press, 2008).

16

የኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭነት እውነት ወይስ ተረት? ካሳሁን ዓለሙ

1.መንደርደሪያ ‹ትልቅ ነበርን፤ ትልቅም እንኾናለን› ከሚለው የሸገር ሬዲዮ ጣቢያ መርህ ጋር ተያይዞ ከአንድ ጓደኛዬ ስንነጋገር ‹መቼ ነው ትልቅ የነበርነው?› የሚል ጥያቄ በማንሣት ሞገተኝ፤ ላስረዳው ብሞክርም አልተስማማንም:: ግን ደግሞ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ላይ ሙግቶች መነሣታቸው አስደናቂ አይደለም፤ በታሪክ ላይ የሚነሣ የእሰጥአገባ ክርክር መቋጫ አይኖረውም፤ በተለይም ታሪኩ የጥንት ሥልጣኔ አመሠራረተ ጋር ሲያያዝ ደግሞ ክርክሩ ይጦዛል፤ እንኳን ተጥሎ የተረሳና አቅጣጫው ተቀይሮ የኖረ የጥንት ታሪክ ይቅርና ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚቻልበት አንድ ምዕት (መቶ) ዓመት ያልሞላው ታሪክ እንኳን ስንት ጭቅጭቆች ይስተናገዱበታል:: ይሁንና ታሪክን ያለ ማስረጃ ማጥናት እና በእሱም ላይ መከራከር ስለማይቻል ለጥንት ሥልጣኔዎች ምስክር መኾን የሚችሉት ቀድመው ተመዝግበው የሚገኙና ምስክር መኾን የሚችሉ ቋሚ ቅሪቶችን ይዞ መከራከር ይገባል:: በዚህ አከራካሪ እና የማስረጃ አለመስማማት ላይ ተመሥርተን ነው ኢትዮጵያን የጥንታዊ ሥልጣኔ ምንጭ የመኾኗን እውነትነት ለማስረገጥ የምንከራከረው፤ በክርክሩም መጀመሪያ ‹ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ ናት የምንለው ማስረጃዎቹን

ጎትተን ወደ ራሳችን በማምጣት ነው፤ ወይስ ራሳቸው ማስረጃዎቹ ዘግቡን ብለው ጠርተውን ነው?› የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም:: ማስረጃዎቹን የግድ እኛ ጎትተን በማምጣት ከኾነ ‹የሥልጣኔ ምንጭ ነን› የምንለው ስህተት ነው፤ ‹ያሉት ማስረጃዎች ዘግቡን› ብለውን ከኾነ ግን ‹ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ ናት› ብለን መሟገታችን አግባብና አስፈላጊም ነው፤ ከራስ ጋር የተያያዘን የማንነት መሠረትና ማሳያን መናገርም ነውርነት የለውም፤ ግደታም ነው፤ እና ማን ይናገረው? እኔ እዚህ የምሟገተው ‹የጥንት ሥልጣኔ የታሪክ ማስረጃዎች ኢትዮጵያ የዓለም የሥልጣኔ መነሻ መኾኗን ይመሠክራሉ› በሚል ነው:: በዚህም የማስረጃዎቹ መኖር እርግጥ ከኾነ፤ እኔም ያንኑ ተጠቅሜ መከራከሬ አግባብና ትክክል ይሆናል፤ ዝም ማለቴ ግን ‹ግደለሽ›፤ ‹ለማንነቱ ትርጉም የማይሠጥ ደንታቢስ› ያስብለኛል::

2.ሥልጣኔ ምንድን ናት? ምናልባት ገና በመጀመሪያው ‹ሥልጣኔ ራሷ ምንድን ናት?› ብሎ የሚጠይቅ ነገር ሰንጣቂ ሰው አጋጥሞን እንዳንቸገር፤ ምንነቷን በጥቅል መልክ መናገር አይከፋም:: ሥልጣኔ በጥቅል አነጋገር በጊዜው ካለ ማኅበረሰብ የተሻለ ኑሮ መኖር መቻል ነው:: ሥርወ-ቃሉን እጓለ ገብረ-ዮሐንስ ‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ› በሚለው መጽሐፋቸው ዲልማንን ጠቅሰው እንዳብራሩት ከኾነ ከሥልጣን (Authority) ጋር ይያያዛል፤ እንደሳቸው ከኾነ civitia ከሚለው ከላቲኑ አመጣጥ ትርጉም ጋር በማነጻጸር ሲገልጹ የላቲኑ ቃል

ከተሜነትን ያመለክታል፤ ከገጠር ጋር ሲነጻጸር የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ማግኘትን ያንጸባረቃል ማለት ነው፤ በሌላ በኩል የእኛ ‹ሥልጣኔ› የሚለው ቃል ‹‹በአንድ ነገር ላይ ሥልጣን ማግኘት መያዝ ማስገበር ማለት ነው:: ‹እስመ አንተ ሥሉጥ ላዕለ ኩሉ› በኹሉ ላይ ሥልጣን፤ ገዥነትን ያለህ ነህና›፤ ‹አግብርት ሠሉጠ ላእለነ› ባሮች በእኛ ላይ ሥልጣን አገኙ›› የሚለውን በመጥቀስ ገልጸዋል (እጓለ ገብረዮሐንስ፣ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣ ገጽ 32):: ይህም ማለት ሥልጣኔ የሚለው ቃል ገዥነትን፣ ሥልጣን ያለው መኾን፣ ልቆና ተሸሎ መምራትና ማስተዳዳር መቻልን ይገልጻል:: ሥልጣኔ ስለሚለው ቃል ‹ኢትዮጵያ ቃል ለዓለም ማበደር ቢኖርባት የመጀመሪያ መኾን ያለበት ይህ ነው› ብለዋል::

በተለይ ሊቁ የሥልጣኔን ምንነት በሚከተለው ገለጻ አምቀውና አሟልተው ገልጸውታል፡‹‹ሥልጣኔ ማለት መጀመሪያ ሰው በሕሊናው ውስጥ ያሉትን ሀብታት መርምሮ ተረድቶ መሪነቱን ካወቀ በኋላ ዝቅተኛውን የስሜት ወይም የፍትወት ዓለም አርቆ ገርቶ ለኅሊናው ያስገበረ እንደኾነ በራሱ ላይ ሥልጣን ያለው የኾነ እንደኾነ የሚሰጠው ቅጽል ነው:: ሁለተኛ በዙሪያው ያሉትን ሥነ-ፍጥረቶች ለራሱ እንዲያገለግሉ ለማስገበር የሚያደርገው ጥረትና ከዚያም የሚገኘው ውጤት ሥልጣኔ ይባላል፤ በመጀሪያው በኩል ያደረገው

17

ምንም እንኳን የሚያጠራጥር ቢኾንም በሁለተኛው በኩል በጣም ርቆ ሔዶአል::›› (ገጽ 36-37) ስለዚህ ሥልጣኔን በአሁን ዘመን አስተሳሰብ ብንመነዝረው በኢኮኖሚ በልፅጎ፣ በፖለቲካ የተሻለ የመወሰን አቅምን አዳብሮ እና በዕውቀት አቅም በልጦ መገኘት አድርገን ልንወስደው እንችላለን፤ በድሮው ጊዜ ግንዛቤ ደግሞ በመንፈሳዊም ኾነ በሥጋዊ አኗኗር ከሌሎች መሻልን ይገልጻል፤ መንፈሳዊ ክፍሉ የሃይማኖት አምልኮና ሥርዓት መሻሻልን፣ የሞራልና የሥነ-ምግባር ደረጃ መብለጥን ሲያመለክት፤ ሥጋዊ ክፍሎ የአሠራር ጥበቦችን፣ የአስተዳደር ሥርዓትን፣ የግንባታ፣ የሥነ-ጽሑፍ፣ የቅርጻ-ቅርጽ እና የአሣሣል መሻሻልን፤ በፍልስፍና፣ በትምህርት ሥርዓት መብለጥን ያመለክታል:: በሌላ አገላለፅ ሥልጣኔ ከታሪክ ክሰተት ውስጥ የተሻለ አኗኗርን ገንዘብ ያደረገ ማኅበረሰብ ደረጃን የሚመለከት የዘመኑ የገዥነት ደረጃ ነው::

3.የሥልጣኔ መነሻዋ ስንት ሥፍራ ነው? የት የት? በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ዓይነት አቋሞች እንዳሉ ነው የሚታወቀው፤ አንደኛው ሥልጣኔ በአምስት የተለያዩ ሥፍራዎች ለየብቻ መፍለቋን የሚሞግት ሲሁን ሁለተኛው ደግሞ ‹የሥልጣኔ ምንጯ አሐድ (አንድ) የጋራ ሥፍራ ነው› የሚል ነው - ከሥፍራ አንጻር፤ ሥፍራው ደግሞ በዚያ የሚኖርቱን ሕዝቦች (ማኅበረሰብ) ይወክላል:: የመጀመሪያው መሟገቻ በማስረጃ የተደገፈና ትክክል ከኾነ ‹ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ ናት!› ያልነው ሐሳብ ገደል ይገባል፤ ባይኾን ‹ኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከተጀመረባቸው አገሮች አንዷ ናት› የሚል የክርክር መነሻ ሊኖረን ይችላል፤ ትክክለኛው ባለ ማስረጃ አቋም ሁለተኛው ከኾነ ግን ክርክራችን መነሻ ይኖረዋል፤ የሚቀረው ‹አንዷ የሥልጣኔ ምንጭስ ኢትዮጵያ ናት ወይስ ሌላ አገር?› የሚል ይሆናል::

ያመጣው ምክንያት መመርመር ይኖርበታል፤ እንዲሁም በእነዚህ ሥፍራዎች ሥልጣኔያቸውን አበልፅገው የነበሩት አንድ ዓይነት ሕዝቦች ናቸው ወይስ የተለያዩ የሚለው ጥያቄ አብሮ ይከሰታል:: በእነዚህም ጥያቄዎች ‹ተመሳሳይ የሥልጣኔ አሻራዎች የተከሰቱት ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ባሕርይ ተመሳሳይነት የተነሣ ነው ወይስ ከእነሱ ውጭ የኾነ በእነዚህ ሥፍራዎች የተሠራጨ ሥልጡን ሕዝብ ኖሮ ያ መሥርቶት ነው?› በሚል ተጨማሪ ምክንያቶችና ማስረጃዎች መኖራቸው ይፈተሸበታል:: ከማስረጃዎች ምስክርንነት የተነሣ በእዚህ አቋም ዙሪያ የሚነሱ ብዙ ጥያቄዎችም አሉ:: ለምሳሌ በተለያየ መንገድ የተገኙት ማስረጃዎች እንደሚመሰክሩት ከኾነ በጥንት ዘመን የነበረው የዓለም የሥልጣኔ ባህል ተመሳሳይነት የተንፀባረቀበት ነበር:: ታዲያ ይኸ ለምንና እንዴት ሊኾን ቻለ? ማለትም በአምልኮ ሥረዓት፣ በግብርና አሠራር፣ በሐውልትና በግንባታ አሠራር፣ በሥነ-ጽሑፍና በፊደል ሥርዓት፣ ወዘተ የጥንት ሥልጣኔዎች የተመሳሰሉት ለምንድን ነው? እንዴትስ በዚያን ዘመን በነበረው ሁኔታና ቴክኖሎጂ የባህል መወራረስ አጋጠመ? የባህልና የንግድ መስተጋብርስ ሊከሰት ቻለ? የሥልጣኔ አቅጣጫና መገለጫው ተመሳሳይ መኾኑ ብቻ ‹ለምን? እንዴት ሊኾን ቻለ?...› የሚሉ ጥያቄዎችን ያግተለትላል:: ይህም ብቻ



3.1. የብዙህነት የሥልጣኔ ምንጭ ንድፈ-ሐሳብ



የዚህ አቋም መሟገቻ የዓለም የሥልጣኔ መነሻዎች የሚላቸው ግብፅ (በዓባይ ወንዝ)፣ ሜሶጶጣሚያ (በኤፍራጤስና ጤግሮስ ወንዞች)፣ ቻይና (በያንግትዝ ሸለቆ)፣ ሕንድ (በኢንዱስ ሸለቆ) እና ኢንካና ማያ (በደቡብ አሜሪካ) ናቸው:: እነዚህ ሥፍራዎች የጥንታዊ ሥልጣኔ ቅሪቶች የተገኙባቸው፤ የጥንቱ ሥልጣኔ ማስመስከሪያ ሥፍራዎች ናቸው:: ይህ ከኾነ የሚኖረው ጥያቄ አንደኛ ‹ሥልጣኔያቸው ተመሳሳይነት ነበረው፤ ወይስ የተለያየ ነው?› የሚል ሲኾን በሁለተኛ ደረጃም ‹የየትኛው ሥልጣኔ ቀዳሚነት አለው?› በሚልም ይጠየቃል:: እነዚህ ሁለት ጥያቄዎችም የሥፍራን፣ የጊዜንና የሕዝቦች መስተጋብርን በመጠቆም ተያያዥነት አላቸው፤ ከእነዚህ ሥልጡን ከነበሩ ሥፍራዎች አንዱ ከሌላው ጋር ተመሳሳይነት ኖሮት ቀዳሚነት ያለው ከነበረ፤ ቀዳሚ የኾነው ለዳኅራዊው ሥልጣኔ እንደ ምንጭነት መወሰዱ ምክንያታዊነት ይኖረዋል (ምሉዕ ባይኾንም)፤ ተመሳሳይነት ኖሮት ኹሉም በተመሳሳይ ዘመንም የተከሰቱ ከኾነ አንድነቱን

18

አውሮፓውያኑ የፈጠራ ታሪካችውን አስተማሩን፤ የነፃ የትምህርት ዕድል ሰጡን:: እኛም ያስተማሩንን አጠናን:: ያንን ለሌሎችም ማስተማር ጀመርን:: የአርኮሎጂ ዕውቀት እየሰፋ ሲሄድ ግን የተማርነው ትምህርት ስህተት ሆኖ ተገኘ

ሳይኾን የሥልጣኔ ደረጃዎቻቸውም ተቀራራቢነት ይታይባቸዋል፤ የተጀመሩበት ዘመናት መቀራራብና መከታተልም የሚያመለክተው የእነዚህ ሥፍራዎችን የሥልጣኔ ተመጋጋቢነትና ተወራራሽነት ይመስላል:: እንደገናም የንግድ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚገልጹ ማስረጃዎችም አሉ፤ ይህ ከኾነም ሥልጣኔ ከአንዱ ወደ ሌላው እየተያያዘችና እየተስፋፋች ሄዳለች ማለት ይቻላል፤ ራሷን ችላ በተለያየ ሥፍራ መብቀሏን አያስረግጥም:: በተጨማሪም እነዚህ የሥልጣኔ መነሻ የተባሉ ሥፍራዎች (በግብፅ፣ በሕንድ፣ በቻይና፣ በባቢሎን፣ በደቡብ አሜሪካ) የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎቻቸው ያሁኖቹ ነዋሪዎች ሳይሆኑ ጥቁር ሕዝቦች ነበሩ፤ ይህ ከኾነ እንዴት በኹሉም ሥፍራ ይህ ሊከሰት ቻለ? ጀማሪዎቹ ጥቁሮች ከነበሩ እንዴት ኋላ ሥልጣኔያቸው ተቋረጠ? ‹ጥቁሮች ነበሩ› የሚለው ግን ጭቅጭቅ እንዳለበት መረዳትም ያስፈልጋል፤ ‹የጥቁር ሕዝቦች ምሁራን የጥቁሮችን የሥልጣኔ ቀዳሚነት ለማሳየት የፈጠሩት መከራከሪያ ነው› የሚሉ ምሁራን አሉ:: ግን የጥቁሮችን የሥልጣኔ መሥራችነት የሚመሠክሩ ብዙ የጥንት ታሪክ ማጥኛ ማስረጃዎች እንዳሉ ማበል አይቻልም:: ለምሳሌ ሕንድ የአርያን ዘሮች አሸንፈው ሳይቆጣጠሯቸው በፊት የሕንድን ሥልጣኔ የመሠረቱት ጥቁሮቹ እንደነበሩ ታሪካቸው ይመሠክራል፤ የአሜሪካ ቀይ ሕንዶች ነጮች ሔደው ሳይቆጣጠሯቸው በፊት ገናና ሥልጣኔን ገንብተው እንደነበር የሐውልትና የቅርሳቅር፣ እንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ምሥክሮቻቸው ያስረዳሉ፤ መካከለኛው ምሥራቅን በሥልጣኔ ያቀኑት የኩሽ ልጆች መሆናቸው ይታወቃል፤ ግብፅንም እንደዚሁ:: ስለዚህ የተለያዩ ሥፍራዎች የተከሰቱ ሥልጣኔዎች ጀማሪዎቹ ጥቁር ሕዝቦች ናቸው የሚለው መከራከሪያ በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለም:: በአጠቃላይ ግን ለሚነሱባቸው ጥያቄዎች የአፀፋ ተሟጋቾቹ የሚሰጡት ማብራሪያ ቢኖርም አጥጋቢ አልኾነም:: አንዳንዶቹም የዝግመተ-ለውጥን የዘመን መገመቻዎች ተጠቅመው ‹የዕድሜ ማራዘሚያ› በመውጋት የሥልጣኔ ዘመናቸውን ‹የሩቅ፣ ሩቅ!› ለማድረግ የሞከሩ ሞልተዋል:: የዝግመተ-ለውጥን ግመታ ምናልባት ‹ሲያዘግም ቅርቡ ሩቅ ሆኖበት ሊኾን ይችላልና እንተወው:: እሱን እንኳን ብናልፈው በእነዚህ በተባሉት የሥልጣኔ መነሻዎች ውስጥ ተንፀባርቀው የሚገኙት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ሥልጣኔ አሻራዎች ሥፍራ አልተሰጣቸውም:: ለምን? ጥያቄው ያለው እዚህ ላይ ነው:: ለምሳሌ የጥንት ኢትዮጵያውያን ኀያልነትና ሥልጡንነት በጥንታዊያን ግብፆች ሔሮግሊፊክና በሕንዶች ሳንስክሪት ጽሑፎች ተጠቅሶ ይገኛል፤ በግሪኮችና በሮማዊያን ጸሐፍት በተረት መልክም ይሁን በታሪክነት ተዘግቧል፤ እንዳውም ከዚያ ባለፈም ኢትዮጵያውያን ነገሥታትንና ንግሥቶችን እንደ አምላክ ማምለክ ሁላ እንደነበረ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ:: ለምሳሌ ኦሲሪስ (Osiris)፣ ዚየስ (Zeus) እና አፖሎ (Apollo) የተባሉት የጣዖታት ስሞች ከኢትዮጵያ ነገሥታት የተወሰዱ ናቸው ይባላል (Drussilla D. Hounstoun, Wondeful Ethiopians, p.22-23)::

በተጨማሪም የኢትዮጵያውያንን ግዛት ስፋትና የሥልጣኔ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ የጥንት ታሪክ የካርታ መረጃዎችም ይገኛሉ:: እና ይህ ኹሉ ከኾነ ለምን ቢያንስ ከአምስቱ ወይም ከስድስቱ የሥልጣኔ ምንጮች ውስጥ ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀረች? ምክንያቱን የሚያውቁት ንድፈ-ሐሳቡን ያስቀመጡት ምሁራን ናቸው:: እኛ ግን መጠርጠር እንችላለን፤ ‹ምን አልባት የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ለእነዚህ ሥልጣኔዎች መሠረታቸው እንደኾነ ስላወቁ ወደ አንድ የጋራ መነሻ እንዳይወስደን ብለው ይኾን?› ብለን እንጠይቃለን:: ወይም በአጸፋተዘረኝነት ዕይታ ‹ምናልባት ኢትዮጵያውያኑ ጥቁር ኾነው ስላገኟቸው፤ ንድፈ-ሐሳቡን ያቀረቡት ምሁራን ደግሞ ነጮች ኾነው (ወይም የነጮች ቅጂዎች ኾነው) ጥቁር ሠልጥኖ ነበር ማለት ከብዷቸው (ቀፏቸው) በማወቅ ከሥልጣኔ ተጋሪነት ያስወገዱት ይኾን?› በማለትም እንገምታለን (የመገመት መብታችንን በመጠቀም):: በሌላ አገላለፅ የሥልጣኔ ብዙህነት መነሻ ንድፈሐሳብ ኢትዮጵያን ከሥልጣኔ ተጋሪነት ስለሚያገል ከዚህ ጽሑፍ ዓላማም ጋር አብሮ አይሄድም:: ስለዚህ የእዚህ አቋም ሙግት በመልስ አልባነቱ ትተነው (ዝግ በር ፖሊሲ እንደ ዐፄ ፋሲል) እንለፍና ይልቁንም ሚዛን የሚደፋውን የሁለተኛውን አቋም መሟገቻ እየዳሰስን ይኸኛው አቋም ምን ያህል ችግር እንዳለበት እንረዳዋለን::

3.2.የአሐዳዊ የሥልጣኔ ምንጭ ንድፈ- ሐሳብ ይህንን አቋም አራማጅ ሊቃውንት መደምደሚያ ‹የዓለማችን ሥልጣኔ ከአንድ የጋራ መነሻ ፈልቃ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ፈሳለች› የሚል ነው:: እዚህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስም ያስቻሏቸውን የተለያዩ ማስረጃዎችም አስቀምጠዋል:: ከእነዚህ ማሰረጃዎች መካከልም የሥልጣኔዎቹ ቅሪቶች፣ የሥነ ተረት ማሳያዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች፣ የታሪክ ፍሰቶች ወደ አንድ አቅጣጫ በመምራት ቅድሚያውን ይይዛሉ:: ዋና የአሐዳዊያን የሥልጣኔ ምንጭ ምስክር የጥንታዊ ሥልጣኔ ማሳያ ቅሪቶች መገኘት ነው:: ይህም ማለት በሥነ ምድር ጥናት (Archaeology)፣ በሥነሰብእ ጥናት (Anthropology) እና በሥነ-ልሣን ጥናት (Linguistic) የዓለማችን ሥልጣኔ ከአንድ ከተወሰነ አካባቢ ከሚኖሩ ማኅበረሰቦች መነሣቱን ማረጋግጥ የሚያስችሉ ብዙ ማስረጃዎች ማግኘት ተችሏል:: በዚህም የጥንት ዘመን ሥልጣኔ ማሳያዎች የኾኑት የሐውልት አሠራር፣ የግብርና አጀማመር፣ የአምልኮ ሥርዓት፣ የጊዜ አቆጣጠር፣ የባህል ውርርስ፣ የልምድ ድርጊት፣ የፊደላት አቀራረፅ፣ የሥነ-ጽሑፍ ሥርዓት፣ የሥነድምፅ ልማድ… ተመሳሳይነትና ተያያዥነት የሥልጣኔ መነሻ አንድ ስለመኾኑ መስካሪዎች ኾነው ተገኝተዋል:: ለምሳሌ እንዴት ተመሳሳይ ሐውልት በኑቢያ (እና በአክሱም) እንደተሠራው በደቡብ አሜሪካም ተሠርቶ ሊቆም ቻለ? እንዴትስ በእነዚህ በተራራቁ ሥፍራዎች ያሉ ሐውልቶች የአሠራር ጥበባቸው ሊመሳሰል ቻለ? እንዴትስ እነዚህ ማኅበረሰቦች ተመሳሳይ የሆኑ የቤት እንስሳትን ማልመድ ቻሉ? በእንስሳት የማረስ

ሥርዓታቸው ሊመሳሰል የቻለበትስ ምሥጢር ምንድን ነው? ለምሳሌ የህንድ ገበሬዎችና የኢትዮጵያ ገበሬዎች የአኗኗር ሥርዓት ተመሳሳይ የኾነው በምን ምክንያት ነው? እንዲሁም የፊደላት ሥዕላዊ አቀራረፅ፣ አደራደርና የአጻጻፍ ሥርዓታቸው መመሳሰል ይንጸባረቅበታል፣ ምንጩ አንድ ካልኾነ እንዴት ይህ ሊኾን ቻለ?... ጥያቄዎቹ በሥነ-ምድር ጥናቶች በተገኙ ማስረጃዎች እየተደገፉ ሲመረመሩ የጋራ መስተጋብር እንደነበራቸው ያረጋግጣሉ:: የቋንቋዎቻቸው ሥርዓቶችና የአነጋገራቸው ልማዶች ሲፈተሹ ዝምድናቸውን ያጸድቃሉ:: ሌላው የጥንት ጊዜ የሥልጣኔ አጀማመርን ለመመርመር ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው የሥነ ተረት ጥናት (mythology) ነው:: መጀመሪያ መታወስ ያለበት ተረት የሚፈጠረው የተከሰተ ነገር ከጊዜ ቆይታ የተነሣ እየተጋነነ ወይም ከሌላ ታሪክ ጋር እየተደባለቀ ሲነገር መኾኑ ነው፤ ሌላ ችግሩ እንዳለ ኾኖም የቆዩ ሕዝቦች ታሪክ መንገሪያና ማንነት ማወቂያነቱ እውነት ነው:: በዚህ በሥነ-ተረትም የአንድ ማኅበረሰብ ትውፊት፣ ሥነ ቃል፣ ትረካ… ከሥነ ምድር ጥናትና ከተመዘገቡ የታሪክ ማስረጃዎች ጋር በማነጻጸር ይጠናል፤ ከሥነ-ሰብእ ጥናትና በሥነ-ልሣን ጥናት ትክክለኛው እየተበጠረ ይለያል፤ ከዚያም ያለው የጋራ መስተጋብርና ልዩነት ይመረመራል፤ ይተነተናል:: የሥልጣኔ ምንጭን በሚመለከት በተደረጉ የሥነ ተረት ጥናቶችም ሥልጣኔ የጋራ መነሻ ያለው መኾኑን የሚመሰክሩ ኾነው ተገኝተዋል:: ለምሳሌ የጥፋት ውሃ መከሰት በብዙ ማኅበረሰብ በተረት መልክ የሚተረክ ታሪክ መኾኑ መረጋገጥ ተችሏል:: በዚህ ትረካም የኖህ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ገለፃ ጋር ተመሳሳይ በኾነ መልኩ በቻይናም ይተረካል:: እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገበው የዐሥሩ አባቶች ታሪክ ከግብፆች ዐሥር አማልክትና ከከለደዊያን ዐሥር ነገሥታት ታሪክ ጋር ተመሳስሎ ተገኝቷል (R.Noorbergen; 1977; Secrets of the Lost Races: the most controversial view of the past since, page 10-30:: ይህም ‹እንዴት አንድ ዓይነት ሊኾን ቻለ?› በሚል ጥያቄ መነሻነት ሲመረመር ስለ ሰው ዘር አመጣጥ የጋራ መነሻ መኖር ብዙ ይናገራል:: በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አንጻር ስንመለከትም በጥፋት ውሃ የተነሣ ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ያለው የሰው ዘር መጥፋቱን፤ ከጥፋት ውሃም ኖኅና ቤተሰቦቹ መትረፋቸውን እናውቃለን:: ስለዚህ ከአዳም እስከ ኖኅ ያለው ታሪክ የሥልጣኔ አጀማመር መከራከሪያ ሊኾነን አይችልም:: በዘፍጥረት ምዕ. 9፡ ቁ. 18-19 ላይ ስለ ኖኅ እንዲህ በሚል ተመዝግቦ እናገኛለን፤ ‹ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው፤ ከእነርሱም ምድር ኹሉ ተሞላች።› ይላል:: ከእነዚህ የኖህ ልጆችም በተለይ የካም ልጆች የያዙት ሥፍራ ሥልጣኔ ተመሥርቶ የተስፋፋበት ነበር፤ እነሱም በኃያልነታቸው የተመሠከረላቸው እንደነበሩ ይገልጻል:: ለምሳሌም የካም የመጀመሪያ ልጅ ኩሽ ኢትዮጵያን፤ ምጽራይም ግብፅን (ምሥርን) ያቀኑ ናቸው፤ የኩሽ ልጅ ናምሩድ ደግሞ ባቢሎንን ገንብቷል:: በተለይ ናምሩድን በሚመለከት ‹እርሱም በምድር ላይ ኃያል መኾንን ጀመረ። እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ

ነበረ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።› የሚል ገለጻ እናገኛለን:: የናምሩድን ገናናነትና አነዋወሩን በሚመለከት መሪ ራስ አማን በላይ ከኢትዮጵያ ወደ ባቢሎን ሄዶ ከተማን እንደገነባና በባቢሎን ግንብ መፍረስ የተነሣም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ግዛቱን አስፋፍቶ እንደኖረ ገልጸውታል (መሪ ራስ አማን በላይ፣ 1985፣ የጥንቷ የኢትዮጵያ ታሪክ ትንሣኤ፣ ገጽ 22-23):: በመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣኔያቸው የተመዘገበላቸው የዓለማችን ክፍሎችም እነዚህ የካም ዘሮች የሠፈሩባቸው ሥፍራዎች ስለሆኑ (በተለይ ባቢሎንና ግብፅ) እነሱ በዚያን ዘመን በሥልጣኔ ማማ ላይ ወጥተው የበላይነትን ይዘው እንደነበር እንረዳለን:: ይህም ማለት ፕራሚዶችን አሁን ሱዳን በሚባለው (በጥንት ጊዜ ሱባ ከዚያ በኋላም ሳባ፣ ሜርዌ (ኑብያ)) መገንባት የጀመሩትና ወደ ግብፅ ያስፋፉት፣ ከዚያም አልፈው ባቢሎንን የመሠረቱት የኩሽ ልጆች ናቸው:: እንዲሁም የኩሽ ወንድም የኾነው ከነዓንን በአሁኑ የመካከለኛው ምሥራቅ እስያ (እስራኤል፤ ፍልስጥኤም እና ሌሎቹን ጨምሮ) ግዛቱን አስፋፍቶ እንደነበር እንመለከታለን:: ስለዚህ እነዚህ የካም ዝርያዎች በሠፈሩበት በዓባይ ተፋሰሶችና በመካከለኛው ምሥራቅ እስያ ሥልጣኔያቸው ገናና እንደነበር መገንዘብ ቀላል ነው:: ከሴም ዘሮች መካከል የሚታወቁት የአብራሃም ዘሮችም ቢሆኑ ሥልጣኔንና ሥርዓትን የተማሩት ከግብፆች፣ ከኢትዮጵያውያንና ከከነዓናውያን እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል:: ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ከተገኙ የሥነ-ምድር ጥናቶችና የሥነተረት የባህል መስተጋብሮች ጋር አገናኝተን ስንመለከት የሥልጣኔ መነሻ እዚህ አካባቢ እንደነበር ይጠቁመናል:: ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክሮች፣ ከሥልጣኔ ቅሪቶችና ከሥነ ተረት ትሪካዎች በመነሣትም የዓለም የታሪክ ፍሰት በናይል፣ በጤግረስና ኤፍራጥስ፣ እንዲሁም በኢንዱስ ሸለቆዎች ተያይዛ ተስፋፍታለች ማለት ይቻላል:: ይህ ማለት የሥልጣኔ አገኛኘቷ አንድ የጋራ መነሻን ምክንያት ያደርጋል፤ ከኾነም የሥልጣኔ አየር የነፈሰችው ከአንድ ከተወሰነ አካባቢ ተነሥታ ነው ማለት ይሆናል:: ‹ከየት አካባቢ?› ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ የሠጠው አንደኛ ሥልጣኔ በግብፅ ከሌሎቹ ቀድማ የመገኘቷ ምሥጢር፤ ሁለተኛ የተገኙ ማስረጃዎችም የግብፅን መሠረትነት ማመልከታቸውና ሜሶጶጣሚያን ማስከተላቸው ነው:: ይህ ከኾነም ሥልጣኔ ከግብፅ ተነሥታ፣ በሜሶጶጣሚያ ተንፈራጣ ወይም እነ ባቢሎንን ጎንፋ በሕንድና ቻይና እንዲሁም በደቡብ አሜሪካ በኢንካና ማያ ተንሠራፍታ እንደነበር ማረጋገጫ አላት ማለት ነው:: ይህ ራሱን የቻለ የክርክር ነጥብ ነው፤ በሚከተሉት መከራከሪያዎች እየጠራ ይሔዳል::

4.ዓባይ! ዓባይ!... ከዚህ በላይ እንደጠቆምኩት ሊቃውንቱ ‹ሥልጣኔ በዚህ መልክ ከአንድ አካባቢ መንጭታ ዓለምን እንዴት ልታጥለቀልቅ ቻለች? የትኛው አካባቢስ ነው ቀደምት

19

መነሻዋ?› ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ያላደረጉት ጥረት የለም:: ይሁንና ምርምራቸውን ወደ ጥንታዊ መሠረት ሲወስዱት ሥልጣኔ ከዓባይ (ከግዮን) ሸለቆ መፍለቋን፣ ወደ ሌሎች የዓለማችን ክፍል ለመንሠራፋትም መነሻዋ የእኛዋ ኢትዮጵያ መሆኗን የተገኙት ማስረጃዎች ኹሉ እየመሠከሩ እንዳስቸገሯቸው (የማይታበል ሐቅ እንደኾነባቸው) መስክረዋል፡- የዓባይ ወንዝ በርዝመቱ አንደኛ እንደኾነው የሥልጣኔ መነሻነቱም ረዥም ነው:: ሊቃውንቱ ሥልጣኔ ከዓባይ መንጭታ ወደ ሌሎች ዓለማት ተንሠራፍታለች በሚለው አቋም ለመስማማት ቢሞክሩም ‹የዓባይንስ ሥልጣኔ ማን መሠረተው?› በሚለው ላይ ክርክሮች ተነሥተዋል፤ የክርክሩ ማጠንጠኛም ‹በዓባይ ሥልጣኔ ዙሪያ በጣም የታወቀው የግብፅ (የፎርዖኖቹ) ሥልጣኔ ነው፤ ግብፅ የምትጠቁመው ደግሞ የዓባይን ታህታይ ክፍል ነው፤ ይህ ከኾነ የጥንቱ የግብፅ ሥልጣኔ እዚያው ፈለቀ ወይስ ከዚያ ውጭ ከነበረ አካባቢ ፈልቆ ነው ግብፅ ያጥለቀለቃት?› የሚል ጥያቄ አፍጥጦ መጥቶባቸዋል:: የዚህ ጥያቄ ችግር የበለጠ ሲጨምርም ሌላ ጥያቄ ይወልዳል፤ ‹የግብፅ ሥልጣኔ ከእሷ ውጭ ባሉ ሕዝቦች መሥራችነት የተጀመረ ከኾነ ምኑን የሥልጣኔ ምንጭ ኾነችው?› የሚል ሌላ የተጠየቅ ጥያቄን ያስከትላል:: እነዚህ ተባባሪ ጥያቄዎችም በዓባይ የሥልጣኔ ምንጭነት ዙሪያ የሚነሱ ሦስት የመከራከሪያ አቋሞችን (መላምቶችን) ይፈጥራሉ:: እነሱም፡1.

የዓባይ ሸለቆ ሥልጣኔ የኢንዶ ኤሮፓውያን ሥልጣኔ ውጤት ነው፤

2. የታችኛው ዓባይ ሸለቆ ሕዝቦች የጀመሩትንና ያዳበሩትን ሥልጣኔ የላይኛው ዓባይ ሸለቆ ሕዝቦች ተቀብለው እያሻሻሉ ተጠቅመውበታል፤ 3. የላይኛው ዓባይ ሸለቆ ሕዝቦች የጀመሩትን ሥልጣኔ የታችኞቹ ዓባይ ሸለቆ ሕዝቦች ተቀብለው አሻሽለውታል የሚሉት ናቸው:: ከአማራጭ መላምቶቹም ‹የግብፅ ሥልጣኔ የተመሠረተው በሌሎች ከኾነ ሌላ ቀደምት የዓለም የሥልጣኔ ምንጭ አለ› የሚል መከራከሪያ ይወለዳል:: ኾኖም ሊቃውንቱ በእነዚህ መላምቶች ላይ ተከራክረውም አንደኛውን በማጽደቅ ተባብረዋል፤ ምክንያቱም የተገኙት ማስረጃዎች ኹሉ ወደ አንደኛው በማድላት ‹ዓባይ ከላዕላይ ወደ ታህታይ ፈሶ የግብፅን ሕይወት እንደሆናት ሥልጣኔንም አምጥቶ አበልፅጓታል› የሚል መከራካሪያ ሠልጥኖባታል:: ‹ሥልጣኔ ከታህታይ ነው የመጣው ማለት ውኃ አሻቅቦ ይፈሳል› ከማለት ጋር ተመሳሳይ ነው የሚል ሙግት ተደንቅሮ ሊቃውንቱን ፈትኗቸዋል፤ ለማንኛውም ለንጽጽር እንዲመቸን አቋሞቹን በተወሰነ ደረጃ እየዘረዘርን እንመልከታቸው::

4.1.ሥልጣኔ ከኢንዶ-እስያ ወደ ላዕላይ ዓባይ የዚህ አቋም መከራከሪያ ‹የግብፅን ሥልጣኔ የጀመሩት ከእስያ (በተለይ ከሜሶጶጣሚያ) የመጡ ሕዝቦች ናቸው፤ ስለዚህ ግብፅ ዋናዋ የሥልጣኔ መነሻ ተደርጋ ልትወሰድ አይገባትም› የሚል ነው:: በግልጽ አነጋገር እዚህ መከራከሪያ ‹የሜሶጶጣሚያ ሥልጣኔ ከግብፅ ይቀድማል፤ ሜሶጶጣሚያ ደግሞ የነጮች

20

ሥልጣኔ መነሻ ናት› የሚል ስውር አቋምም አለው፤ ይህንን ግን የዘረኛ ነጮች አመለካከት የፈጠረው ዕይታ ነው እንጂ እውነታነቱ ሚዛን አይደፋም:: ይህንን የምንለው ወደን ሳይኾን የአስተሳሰቡ መነሻ የፈጠረው ተጽዕኖ ዝም ብሎ ለማለፍ ስለማያስችል ነው:: ምክንያቱም ይህ የዘረኝነት አመለካከትም የፍረጃ አደጋ ስላለበት ነጻ ኾኖ ለመከራከርም ያስቸግሯል፤ ‹ጭቃ ውስጥ ገብተው ሲጫወቱ መለዳደፍ የማይቀር ነው› እንዳሉት ሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ነጭ ኮት የለበሰ ሰውንም ‹ኮትህ ነጭ ነው› ማለት አማራጭ የለውም:: ቀድሞ ችግሩ የተፈጠረው ደግሞ ‹ከዚያኛው ቤት› ነው፤ ምክንያቱም በእነሱ እሳቤ ጥቁር ሕዝቦች አስተሳሰባቸው ዝቅተኛ ስለኾነ ቀድመው ሠልጥነው ነበር ማለት አይቻልም::

በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ተብለው ይጠሩ የነበሩትን ሕዝቦች ታሪክ ሲመረምሩም መነሻ ቤታቸውን እዚሁ አለንበት የዓባይ መነሻና ተፋሰሱን አድርገው፤ ግብፅን አሠልጥነው፣ በጎረቤቶቻቸው በእስያና በሌሎች አህጉራት ተንሠራፍተው፣ አሁን የህንድ ውቅያኖስና የአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚባሉት ቀላያትን (ውቅያኖስ) በስማቸው አስጠርተው በመርከቦቻቸው እየቀዘፉ፣ በጥበቦቻቸው እየመረመሩ የሥልጣኔው በር ከፋች በመኾን፤ ዓለምን ተቆጣጥረውት እንደነበር የማያብሉት ጥንታውያ ማስረጃዎች ምስክር ኾነው አግኝተዋቸዋል

ለዚህም ሁለት የታወቁ ፈላስፎቻቸው የጻፉትን መጥቀስ በቂ ነው:: በ19ኛው መ/ክ/ዘ የነበረው ዕውቁ ፈላስፋ ሔግልስ ‹አፍሪካ ለዓለም ታሪክ ያደረገችው የሚታይ የሥልጣኔ እንቅስቃሴ ወይም የምትካፈለው የልማት አስተዋፅኦ የላትም፤… የግብፅ ሥልጣኔም የአፍሪካን መንፈስ አይጋራም::› ብሏል:: ለዚህ የሔግል አስተሳሰብ መነሻ ከሆኑት መካከል ታላቁ ፈላስፋ አማኑኤል ካንት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፤ ለካንት ጥቁር ሕዝብ ግማሽ ሰው እንጂ ሙሉ የማሰብ ስብእና የለውም፤ ስለዚህ ጥቁር ሊኾን የሚችለው እንደ እንስሳ በማሰልጠን የጉልበት ሠራተኛ ብቻ ነው:: በዚህ የተነሣ ሔግልም የግብፅን ሥልጣኔን ቢያይም የማያስብ ሠልጥኖ ነበር ለማለት ከበደው፤ የሚያየውን ለማመን ተቸግሮ ለሚያስቡት ለነጮች ሰጣቸው:: የእነዚህ የአውራ ሊቃውንት አስተሳሰብ ደግሞ ምን ያህል የመምራትና የመቅረጽ ኃይል እንዳለው ለመገንዘብ ሌሎቹ ፍልስፍናዎቻቸው ያላቸውን ክብደት ማየት ብቻ ይበቃል፡- ካንትም ካንት ነው፤ ሔግልንም ሔግል ማለት በቂ ነው:: በእነዚህ (እና መሰል) ፈላስፋዎች እሳቤ በመመሥረትም አውሮፓውያን ‹አፍሪካን የሥልጣኔ አልባነት› ስላረጋገጡ አህጉሪቱን ምን እንዳላት እንዲመረምሩና ሕዝቡንም ለማሰልጠን እንዲተጉ አነሳሳቸው፡- ቢያስ የጉልበት ሥራን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ:: ‹አፍሪካውያን መሠልጠን የሚችሉበት አቅም አልነበራቸውም› በሚል አስተሳሰብም ሥልጣኔ ከአውሮፓ እየተነሳች ወደ አፍሪካ ጎርፋለች የሚል አቀራረብ ምሁራኑን ሊያጥለቀልቃቸው ችሏል፡እንደ ቅኝ ግዛታቸው ማለት ነው፤ የቅኝ ግዛት አሳብ መነሻውም ይህ ነው:: እንዲሁም በጥንት ሥልጣኔ ውስጥ ምንም ዓይነት የሥልጣኔ አሻራን በአውሮፓ ውስጥ ስላጡ ሜሶጶጣሚያንና ግሪክን አመጋግበው ግብፅን ተቀጥላ አደረጓት፤ ጥቁርነቷንም ክደው የግድ በነጭ ሸማ ሸፈኗት:: በእውነታው ግን የግብፅም ኾነ የሜሶጶጣሚያ ሥልጣኔ የጥቁሮች የምስክር ሐውልቶች እንጂ እነሱን አያውቃቸውም፤ እነሱ የዚያን ጊዜ በበረዶ ሀገር ዋሻ ውስጥ ተደብቀው ነበር:: እዚያ ደግሞ ምስክር ሊሆናቸው የሚችልም ምንም ነገር ስላልሠሩ ከዋሻ ወጥተው የወረሩትን የእኛ ነው ብለው ለመከራከር በቁ:: ግሪኮችም ቢሆኑ የሥልጣኔ ባለቤት የሆኑት ከግብፅ የሠረቁትን ጥበብ የእኛ ነው በማለታቸው መሆኑ ማረጋገጫ ከቀረበበት ከርሟል (Stolen Legacyን ይመለከቷል)::

የዚህን አስተሳሰብ ምክንያት፣ ስልትና ያመጣውን ውጤት ዶ/ር ላጵሶ ጌ.ድሎቦ ከ‹አውሮፓውያን የማንነት ችግር› ጋር አያይዘው እንዲህ አብራርተውታል፡‹… ከዚህ ቀደም ስለኛ ሲነግሩን የነበሩ አውሮፓውያን ማንነትን በግልፅ እንመርምር:: ከኹሉ አስቀድሞ አውሮፓ የማንነት (Identity) ችግር ያለበት አህጉር ነው:: … ከዘመናት በኋላ… አውሮፓውያን ሳይንስና ቴክኖሎጅን አስፋፍተው በየብስ ያቃታቸውን በባሕር ተጉዘው ዓለምን በቅኝ ግዛትነት ያዙ:: አፍሪካን የባሪያ ገበያ፣ የምዕራብ ንፍቀ ክበብ አህጉራትን አውስትራሊያንና ኒውዚላንድንም መኖሪያቸው አደረጉ:: ከዚህ በኋላ የማንነት ጥያቄ ተነሳ:: ጀርመኖች፣ አንግሎሳክሰኖችና ፍራንኮች ባርበሪያንስ ስለነበሩ ከዚያ የተገኘ ሥልጣኔ ስላልነበር ፊታቸውን ወደ ግሪክ ሥልጣኔ አዞሩ:: ይህንን ያደረጉት የማንነት ጥያቄ ለመመለስ ነው:: ከሮማውያን ሕግን፣ ከግሪኮች ዴሞክራሲን ወሰዱ፤ ያም ስላልበቃቸው ክርስትናን አጠነከሩ:: የግሪክን ሥልጣኔ ሲመረምሩ ከግብፅ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ሆኖ አገኙት፤ ግን አምነው መቀበል አልፈቀዱም:: ምክንያቱም ባሪያ አድርገው የገዙትን አፍሪካዊ፣ የሰው ዘር አይደለም ብለው የካዱትን ሕዝብ የሥልጣኔ ምንጭ ነው ብለው ለመቀበል አዳገታቸው:: ሆኖም ሥስት የጥቁር ሕዝብ ሥልጣኔዎችን አግኝተዋል:: የግብፅ፣ የኑቢያና የአክሱም ሥልጣኔዎች ናቸው:: እነዚህ ሥልጣኔዎች አፍሪካዊ ሥልጣኔዎች ናቸው ብለው ለመቀበል አልፈለጉም:: ይህን ያልተቀበሉት የሚያካሂዱትን የባሪያ ንግድ የሚቃረን በመሆኑ ነው:: ስለኾነም አውሮፓውያን አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ:: በመግባታቸውም ‹ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በመፋቅ አቢስኒያ› በሚል ስያሜ ተኩት:: የአንድን ነገር ሕልውና ለማጥፋት መጀመሪያ መጠሪያውን መቀየር የተለመደ አካሄድ መሆኑን ካርል ማርክስ በአንጽንዖት መግለጹን እዚህ ላይ ማስታወስ ያስፈልጋል:: ይህንን ካደረጉ በኋላ አውሮፓውያኑ የፈጠራ ታሪካችውን አስተማሩን፤ የነፃ የትምህርት ዕድል ሰጡን:: እኛም ያስተማሩንን አጠናን:: ያንን ለሌሎችም ማስተማር ጀመርን:: የአርኮሎጂ ዕውቀት እየሰፋ ሲሄድ ግን የተማርነው ትምህርት ስህተት ሆኖ ተገኘ:: ሥነልሳን የሴም ቋንቋዎች በዐረብያ፣ በባቢሎን ከመነገራቸው በፊት ፊኒቃውያንና አይሁዳውያን ከመገኘታቸው በፊት ቢያንስ ከ10 ሺሕ ዓመታት በፊት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ይነገሩ እንደነበር አረጋገጠ:: ቋንቋዎቹ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሄዱት ከአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ተነስተው እንደኾነም አሳየ:: ዶ/ር ላጲሶ የገለጹትን የአውሮፓውያንን የታሪክ ቅሰጣ ስልት ቀድመው ከተረዱት የአገራችን ሊቃውንት መካከል አለቃ አስረስ የኔሰው አንዱና ግንባር ቀደሙ ናቸው:: በየገዳማቱ በመዞር መርምረው እስኪረዱ ድረስም ይህ ቅሰጣ ትክክለኛ አቅጣጫ መስሏቸው እንደነበርም አልሸሸጉም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሐፊዎችን በዚህ ቅያስ ተታለው እንደነጎዱ ገልጠዋል:: ‹የሮማውያን አሳብ የኢትዮጵያን ጥንታዊ መሠረቷን እያጠፋን ስንጽፍ ማንኛውም ዓለም የእኛን አሳብ ከተቀበለን በኋላ በኢትዮጵያም የሚወለዱ ልጆች በዓለም የሚገኘውን ታሪክ እየተከተሉ ይለምዱትና

በኛ ሐሳብ ለመሄድ ይችላሉ በማለት አሳባቸውን በዚህ ወስነው ስለተነሱ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ከብራና መጽሐፍ አገኘነው እያሉ፤ በፈረንሳዊ ጽሑፍ እያሳተሙ ለዓለም ባለታሪኮች ኹሉ ስለ አስተላለፉት ያነን መሠረት የሌለውን ጽሑፍ የሌላው አገር ሰው ይቅርና የኢትዮጵያ ልጆች እንኳ እውነት እየመሰላቸው ያንን እየገለበጡ ለወጣቶች ሲያቀርቡ ይገኛሉ::… ለተጻፈው ታሪክ መደገፊያ የሚኾን በታላላቆቹ ገዳማት አገኝ እንደኾነ በማለት በተላላቆቹ ገዳማት እንደተቻለኝ እየተዘዋወርኩ ከመረመርኩ በኋላ የነሱን ታሪክ የሚደግፍ ጥንታዊ ጽሑፍ ሳላገኝ ስለቀረሁ…› በማለት ሐሳባቸውን ከገለጹ በኋላ በሌላ ገጽ ላይ ደግሞ ‹… እነ አለቃ ታዬን፣ እነ ብላቴን ጌታ ኅሩይን፣ አታለውበት እንደነበር ጽሑፋቸው ያስረዳናል:: ይህም ጽሑፍ የዮቅጣን ልጆች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር የሚል ጽሑፍ ስላዩ ሐሰት አይጻፍም መስሏቸው በመታለል የነሱን ተከትለው በታሪክ መጽሐፋቸው ስለጻፉት ነው፤ በሀገራችን የሚገኙ ጸሐፊዎች ኹሉ ይህንን ጽሑፍ እየተከተሉ ጽፈው የሚገኙ ብዙዎች ናቸው፤ እኔም ራሴ እንደዚሁ ተከትዬ በታሪክ መጽሐፌ ጽፌው ነበር:: ግን ሳይታተም በመቆየቱ የተሻለ መንገድ ለመስጠት ያባ ጋስፓሪን መጽሐፍ አገለገለኝ::› የአለቃ አስረስ የኔሰውን መጽሐፍ መሠረት አድርገው የጻፉት ዶ/ር አየለ በክሬም ይህንን በአውሮፓውያን የተደረገውን የማስቀየስ አስተሳሰብ external paradigm ይሉታል፡- አስተሳሰብ በማራገብ የጻፉትን በመሞገት:: ‹በእውነቱ የኢትዮጵያ ታሪክ መነሻ ደቡባዊ አረብ ነው የሚለው አስተሳሰብ የሚያግዘው ማስረጃ መታጣት ተሰናስሎ ርዕዮታዊ እይታ ላይ ያርፋል እንጂ ታሪካዊ መሠረት ላይ አይደለም፤ ይህም በ19ኛው መ/ክ/ዘ የቄሣራዊ አውሮፓውያን ፈጠራ እንቆቅልሽ መሆኑን ማረጋገጫ ነው:: አፍሪካንም የአውሮፓውያን ቀጣይ ቅኝ ግዛትነት እውነት ለማድረግ ብቻ ሳይኾን ለአዲሱ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተፈበረከ ፈጠራ ነበ:: የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክም አወዛጋቢ የኾነው ቀድመው በእዚህ እይታ አቅጣጫውን ስላስቀየሩትና በየገዳማቱ የሚገኙትን የታሪክና የትውፊት ምስክሮች እንደተረት በመቁጠር ስላጣጣሏቸው ነው:: በአጠቃላይ ይህ አቋም የዓባይ ሸለቆ ሥልጣኔ ‹ምንጩ የኢንዶ ኤሮፓዊያን ሥልጣኔ ነው› የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ ማስረጃ የሌለው፣ በዘረኝነት ልክፍት የተገመተ፣ ተቀባይነት እያጣ የመጣ እሳቤ ነው:: ዕይታው ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ግን የታሪክ ማስረጃዎችን ከዓለማዊ ጎራም ኾነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምስክሮች ማረጋገጥ ይቻላል:: በሚቀጥሉት ንዑሳን ርእሶች እንመለከታቸዋለን::

4.2.ሥልጣኔ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያን የዚህ የሁለተኛው አቋም መነሻ ታችኛዋ ምሥር (ግብፅ) ናት፤ ማለትም የሥልጣኔ አየር ከታህታይ ግብፅ ተነሥታ በዓባይ ሸለቆ ወደ ላዕላይ ወደ ኑቢያ፣ ፑንት፣ ደአማትና አክሱም (በጥቅሉ ኢትዮጵያ) ነፍሳለች የሚል አስተሳሰብ መነሻው ነው:: ለምሳሌ አባ

ጋስፕሪን ገብረማሪያም ‹የኢትዮጵያ ታሪክ› በሚለው መጽሐፋቸው፡‹ግብፃውያን ከ2500 ዓመት ከጌታችን ኢየሱሰስ ክርስቶስ ልደት በፊት ጀምረው ወርቅና ሌላ ክብር ዕቃ ለመፈለግ በኒል ዓባይና አትባራ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ይገቡ ነበር:: እነሱ የመጡበት ዘመን ኦሪት ከመጻፉ በፊት ስለኾነ የአገሪቱን ስም ኩሽ ብለውት ሄዱ:: … እስካሁን ድረስ በግብፅ የሚገኙት የቀድሞ ዘመን ምስሎች ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ በወሰዱት ወርቅ የተሠሩ ናቸው:: … የቀድሞዎቹ ኢትዮጵያውያን (የኩሽ ዘሮች) ግብፃውያን ከሀገራቸው እየተሰደዱ መጥተው በኢትዮጵያውያን ውስጥ ወርቅ የሚገኙባቸውን ቦታዎች እየፈለጉ በለቀምት፣ በሌቃ፣ በማጂ፣ በጉባ፣ በሸጎሌ እስከ ኦጋደን ድረስ የሚገኘውን የወርቅ ማዕድን እየፈለጉ ቆፍረው መውሰዳቸውን ካዩ በኋላ የወርቅ ማዕድንን ጥቅም ዐወቁ:: እንዲሁም እየሠለጠኑ ከድንጋይ ዘመን ወደ ወርቅ ማዕድን ዘመን ደረሱ:: ከዚህ በኋላም ጥቂት በጥቂት ወደ ነሐስና ወደ መዳብ ዘመን ደረሱ::› ብለው አስቀምጠዋል:: አሁን የታሪኩን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ‹አባ ጋስፕሪን ይህንን ለማለት ያስቻላቸውን ማስረጃ ከየት አመጡት? ነው ያለ ማስረጃ ነው እንደ ልብወለድ የሚዘግቡት?› ብለን ስንጠይቅ፤ መሠረት የሌለው የፍረጃ ዘገባ ኾኖ እናገኘዋለን:: አባ ጋስፕሪን ዐውቀውም ይሁን ሳያውቁ፣ በቅንነትም ይሁን በክፋት የገለፃቸው መሠረት ‹የጥንት ኢትዮጵያውያን ሥልጣኔ ከግብፅ የመጣ ነው፤ ግብፆች ደግሞ ኩሾች አይደሉም::› እያሉን ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ግብፆች የኩሽ ወንድም የምጽራይም ዘሮች ናቸው፤ ይህም ማለት ሁለቱም የካም ልጆች ናቸው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከምጽራይም ልጆች ይልቅ ኃይልነታቸው የተገጸው የኩሽ ልጆች የእነ ናምሩድ ነው:: ‹በሌላ መረጃዎችስ ምን ያህል አሳቡን የሚደግፍ ነገር ይገኛል?› ከተባለም ጥያቄው በእንጥልጥል ይቆማል እንጂ አያራምድም:: ከላይ እንደጠቀስነው ግን የመነሻ አስተሳሰቡ የሥልጣኔን መነሻ ደቡብ አረቢያ (ሚሶጶጣሚያ) በማድረግና የግብፅን ሥልጣኔ ተከታይ አድርጎ በመውሰድ ላይ ይመሠረታል:: በሌላ በኩል ይህ (የጥንት የኩሽ ሥልጣኔ ከታህታይ ግብፅ የመነጨ ነው የሚለው) አስተሳሰብ (መርህ) ግብፆች ጥቁር አፍሪካውያን አይደሉም በሚል የ‹ኢንዶ ኤሮፓውያን ሥልጣኔ የዓባይ ሸለቆ ሥልጣኔ መሠረት ነው› ወደ ሚለው የሔግል የዘረኝነት ሙግት የሚያዘነብል ነው:: ያለበለዚያ ግን ‹የታህታይ ግብፅ የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ከየት የመጡ ናቸው?› ብለን ብንጠይቅ ለመልሱ ከላዕላይ ግብፅ የእነሱም ቀደምት መነሻቸው ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ነበር ከማለት ያለፈ ሌላ የትውፊትም ኾነ የታሪክ ቅሪት የኾነ ማስረጃ አይገኝም:: እንዲሁም በተለመደው የታሪክ ዘገባ የተቀመጠው ማስረጃ የሚያሳየውም ከዚህ መላምት ተቃራኒውን ነው:: ለምሳሌ ተበታትና የነበረችውን ግብፅ በማዋሐድ አንድ አደረጋት የሚባለው ሜነስ የላዕላይ ግብፅ ፈርኦን (ንጉሥ) እንደነበረ ይታወቃል:: እንዳውም በጥንት ጊዜ የነበሩ ግብፆች በላዕላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቷቸው በአማልክት አገር የሚኖሩ ሰዎች እንደኾኑ አደርገው ነበር:: ለምሳሌ

21

አትሸፕሱት የተባለችው የግብፅ ንግሥት፣ የ‹ፑንት› ምደርን (የኢትዮጵያ ምድር) የአባቷ ቅድስት አገር አድርጋ ነበር የምትቆጥራት:: ባጠቃላይ የተለያዩ የታሪክ ማስረጃዎች ሥልጣኔ እንደ ውሃዋ ከላዕላይ ተነስታ ወደ ታህታይ መፍሰሷን እንጂ ወደ ላዕላይ መወንጨፏን አልመሰከሩም::

4.3.ሥልጣኔ ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ ከዚያም…. የግብፅ የጥናት ሊቆች ‹ግብፅን ማን አሠለጠናት?› ብለው ላነሱት ጥያቄ፤ የጥንት ኢትዮጵያውያን ‹እኛ!› ብለው መልስ ሰጥተዋቸዋል:: በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ተብለው ይጠሩ የነበሩትን ሕዝቦች ታሪክ ሲመረምሩም መነሻ ቤታቸውን እዚሁ አለንበት የዓባይ መነሻና ተፋሰሱን አድርገው፤ ግብፅን አሠልጥነው፣ በጎረቤቶቻቸው በእስያና በሌሎች አህጉራት ተንሠራፍተው፣ አሁን የህንድ ውቅያኖስና የአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚባሉት ቀላያትን (ውቅያኖስ) በስማቸው አስጠርተው በመርከቦቻቸው እየቀዘፉ፣ በጥበቦቻቸው እየመረመሩ የሥልጣኔው በር ከፋች በመኾን፤ ዓለምን ተቆጣጥረውት እንደነበር የማያብሉት ጥንታውያ ማስረጃዎች ምስክር ኾነው አግኝተዋቸዋል:: ይህንን የበለጠ ጠልቆ መመርመር የፈለገ ጎግልን ይጎልጉለው የሥልጣኔን ፍሰት ከጥንት ካርታ ጋር አያይዞ ያቀርብለታል:: ይህም ማለት ‹የግብፅ ሥልጣኔ ከላዕላይ ከኢትዮጵያ የመነጨ ነው› የሚለው መከራከሪያ ብዙ ማስረጃዎች ያሉት ነው፤ በጥንት የግሪክ፣ የሮማና የአይሁድ የታሪክ ጸሐፊዎች የተጠቆመ፣ የሐውልት ላይ ጽሑፎችና ትውፊቶች (ሥነ ቃሎች) ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች ጋር በመገናዘብ ያረጋገጡት ሐቅ ነው:: በእነዚህ ማስረጃዎችም በብዛት ተገልጾ የሚገኘው ሥልጣኔ ከላዕላይ ግብፅ መፍለቋን ነው፤ ታህታይ ግብፅ ግን ከላይ እየጎረፈ በመጣላት ጥበብ ተጠቅማ ነው የሥልጣኔ መስኖዋን ያስፋፋችው፤ የላዕላይ ግብፅ ሥልጡንነት ደግሞ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ነበር፡- ‹አራት ነጥብ!› አሉ ጠቅላያችን ሲጠቀልሉ:: እዚህ ላይ ዶ/ር ኃይሌ ወልደሚካኤል ‹አብሮነት በኢትዮጵያ› በሚል ርዕስ በ1984 ዓ.ም ባሳተሙት ድንቅ መጽሐፋቸው ከገጽ 4-5 ያስቀመጡትን ነጥብ ብጠቅስ ብቁ ገለጻ ይሠጠናል ብዬ አምናለሁ:: ‹የዓባይ ሸለቆ የዓባይ ወንዝ ውጤት ነው:: የዓባይ ወንዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ሥጦታ ነው:: የዓባይ ሸለቆም የመጀመሪያው ጉልህ ማኅበራዊ ሕይወት የተደራጀበት፣ የተፈጥሮ ክስተቶች ግንዛቤ ያገኙበትና የሰው ልጅ ጉልህ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሥነ ምግባርና የሣይንስ ሥርዓትና ምሥጢር የለየበትና በየፈርጁ ያደራጀበት ነው:: መደበኛ ግብርና ማለትም ከብት ማርባት፣ አዕዝርት መዝራት፣ የመገልገያና የማምረቻ መሣሪያዎችን ማምረት፣ አልባሳት መሥራት፣ ከብቶችን በወተት፣ በሥጋ፣ በትራንስፖርትና በእርሻ ምንጭነት መጠቀም፣ በመስኖ እርሻ መገልገል፣ በውሃ መጓዝ፣ በአንድ አምላክ ማምለክ፣ የጽሁፍ ባህል ማመንጨት፣ የሃይማኖት ካህን ማፍራት፣ አስከሬን ማቆየት፣ የጂኦሜትሪን ሳይንስ ማዳበር ወዘተ የመሳሰሉ ኹሉ ብልጭታዎች መጀመሪያ የታዩት በዓባይ ሸለቆ ውስጥ ነው:: በሌላ አነጋገር ለመጀመሪያ የሰው ልጅ በተናጠል

22

ሳይኾን በተደራጀ መልክ በተፈጥሮ ጋር በውል የታገለበትና በኋላም የሰው ልጅ ከራሱ ጋር መታገል የጀመረው በዓባይ ሸለቆ አካባቢ መኾኑ ተረጋግጧል::› ይህ የዶ/ር ኃይሌ ገለጻ በብዙ ሰነዶች የተደገፈ፣ በተለይም በግብፅ ጥናት ሊቃውንት የሚቀነቀን ነው:: ለምሳሌም እነ ዱርሲላ ሆስቶንን፣ የእነ ዮሐንስ ጃክሶንን፣ የእነ ቸክ አንታ ዶዮፕን፣ የእነ ቻንስለር ዊሊያምስን፣ የእነ ማርቲን በርናልን፣… ሥራዎች መመልከት ይቻላል:: የብዙ ብዙ ማስረጃዎችን ከጥንታዊያ ዶሴዎች (ዶክመንቶች) በመልቀም አቅርበውልናል፤ ማስረጃዎቹም ‹ጥንታዊት ኢትዮጵያን እያወደሱ ከምሥጢራዊ ሕዝቦች መኖሪያ ምድርነት እስከ የአማልክት ማደሪያ ቅድስትነት አድርሰዋታል፤ እግዚአብሔር ራሱስ ሕዝቦቹ የሆኑትን እሥራኤላውያን ‹ለእኔ እናንተ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁንምን?› አይደለም እንዴ ያላቸው? ከሀገራችን ታሪክ ጸሐፊዎች ግንባር ቀደም የሆኑት ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ ምንም እንኳን በአሁኑ ዘመን የታሪክ ሊቃውንት ተቀባይነት የለውም በማለት ቢያጣጥሉትም በጥንት የታሪክ ጸሐፊዎች የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከግብፅ ይቀድማል ተብሎ መመዘገቡን ገለጽዋል:: ማጣጣላቸውን የአመለካከት ጉዳይ ስለኾነ ብንተወዉ የሚባለውን ግን እንደሚከተለው ነው ያቀረቡት፡ነገር ግን የታሪክ አባት የሚባለው ስመ ጥሩው ሔሮዱትስ ወደ ግብፅ መጥቶ ዓባይንም ጎብኝቶ በጻፈው የታሪክ መጽሐፉ እንደዚሁ ዲዮዶር የሚባለው የሮማ ታሪክ ጸሐፊ ከግብፅ በፊት ሥልጡንና ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ መሆኗን፤ እሷም ግብፅን ወራ መያዟን ግብፅንም  (18) የኢትዮጵያ ነገሥታት እንደገዟት፤ ራሷ ኢትዮጵያ ግን በማንም ተገዝታ የማታውቅ አገር መሆኗን፤ ነገሥታቱም ሕዝቡም በጣም ሥልጡን፣ ደግ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰላማዊ፣ በጦርነት ጊዜ ዠግና ጎበዝ መሆናቸውን እያጋነኑ ጽፈዋል:: ኢትዮጵያም በአገር (ጊኦግራፊ) አቀማመጧ ከፍተኛ (ላዕላይ) ግብፅግን ወደታች (ታሕታይ) ዓባይም ከላይ ከኢትዮጵያ ወደ ታች ወደ ግብፅ እየፈሰሰ እንደሚያጠጣት አፈርም እያቀበለ እንደሚመግባት፣ እንደዚሁ እንደ ውኃው አወራረድ ሥልጣኔን ለግብፅ የሠጠጭ ኢትዮጵያ መሆኗን እነዚሁ የታወቁት የጥንት ጸሐፊዎች እነሱንም የተከተሉት ኹሉ አስፋፍተው ጽፈዋል:: በኋላ ግን ግብፅ ደግሞ ከኢትዮጵያ ያገኘችውን ሥልጣኔ አስፋፍታ እንደገና የ፲፰ና የ፲፱ኛው ዲናስቲ ነግሥታት ኢትዮጵያን መልስው እንደገዙ ከዚያ ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን አይለው እንደገና ግብፅን ይዘው የ፳፭ኛውን ዲናስቲ (ሥርወ መንግሥት) እንደመሠረቱና እንደገዙ ተጽፏል::› ብለው አስቀምጠዋል:: (ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ፣ አክሱም ዛጉዬ፤ ገጽ 42) ባንድ ወቅት የግብፅ ጥናት ሊቅ የኾነው ፀጋዬ ገ/ መድኅን በጦቢያ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ፡‹አፍሪካ የመጀመሪያዊቱ የሰው ዘር መገኛ ብቻ ሳትኾን፤ የቋንቋና የፊደል፣ የጽሑፍና የአሐዝ፣ የሙዚቃና የዳንስ፣ የቅርጻቅረፅና የሥዕል፣ ወዘተ መፈጠሪያ ምድር እንደመሆኗ የመጀመሪያይቱ የዓለም ባህል እናትነቷም ዛሬ በማያፈናፍን ማስረጃ ተረጋግጧል:: ዛሬ፣ የማንነቷ ጥያቄም ግልጥ ያለ መልስ ያገኘው በዚህ በሳይንሳዊ እውነታ ላይ ተመሥርቶ ነው:: …

ቅድመ-ታሪክ ጻሐፍት (antiquity historians) እንደነ ፕሉታርክ እንደነ ፕሊኒ ያሉ፣ ኋላም እንደነ ዲዮርዳኖስና እንደነ ሄሮዶቶስ ያሉ፣ ገና የግሪክና ሮማ ሥልጣኔዎች ከማበባቸው በፊት በካም አበው ሥልጣኔ ላይ ተመሥርተው የሰውን ዘር የሥልጣኔ አመሠራረት መመዝገብ የጀመሩት:: ከደቡብ ምሥራቅ ሜዲቴራኒያ ማዶ እስከ ማዳጋስካር ባሻገር፣ ከሕንድ ውቅያኖስ በመለስ እስከ ቀይ ባሕር ግራና ቀኝ ያለው ዝርያ፣ ካምም (ኩሽም) አልነው ጥቁር ግብፅ፣ ሳቢያም አልነው ኢትዮጵያ፣ ሐበሻም አልነው ኑቢያ፣ የአንድ የካም ዘር ግንድ ልጅ፣ የአንድ አጥንትና ደም ወንድምና እህት መኾናቸውን ደጋግመው ዘግበውታል::…. በማለት አብራርቷል:: (ጦቢያ መጽሔት ቅጽ 5 ቁ.11፣ 1990 ዓ.ም)

ፀጋዬ በሌላ የጦቢያ ላይ ጽሑፉ ደግሞ ዦዥር ፖዠኔን በመጥቀስ፡ ‹የካም እናት አቴቴ፣ የዛሬ ዐሥር ሺሕ ዓመት በፊት፣ ከኢትዮጵያ ወደ ጥንታዊት ጥቁር ግብፅ ወረደች:: ከዚያም ‹ኧስ ኧስ› (ኢሲስ) በኋላም ‹እሴት› (እሰይ) እየተባለች ወደ ግሪክና ሮማ (ላቲን) ተሻግራ ከአምስት ሺሕ ዓመት በላይ ተመለከች:: ባለብዙ ሺሕ ስመ ውዳሴ (ዌዲሴ odyssey) ተባለች:: ‹ኢስስ› ጌታ የሱስ ከተወለደ በኋላ እያደር ወደመረሳት ደረሰች:: ቀጥሎም እመቤታችን ማሪያም የእመ ፀሐይ (ኢሲስ) አድባርን እጅግ ብዙ ስመ ውዳሴዎች እመ ብርሃን እየተባለች ወረሰች::› ብሏል:: (ጦቢያ መጽሔት አምስተኛ ዓመት ቁ.3 1989) ማስረጃዎቻችን በጣም አስተማማኝነት አላቸው፤ ካስፈለገም ስለ ኢትዮጵያ የጥንታዊ የታሪክ ምንጭነት የጥንት የታሪክ ጸሐፊዎች የሠጧቸውን አስተያየቶች መጥቀስ ይቻላል:: ከእነዚህ ጥንታዊያን ምሁራን መካከልም የቢዛንታንያ ጆኦግራፊ ባለሙያ የኾነው እስጢፋኖስ የሰጠው አስተያየት ሊታለፍ የማይገባው ነው:: እስጢፋኖስ ‹ኢትዮጵያ በምድር ከሚገኙ አገሮች ኹሉ አምላክን ማምለክና በሕግ ሥርዓት መመራት የተጀመረባት የመጀመሪያዋ ሀገር ስትኾን ዜጎቿም የአምልኮ ሥርዓትንና በሕግ ሥርዓት መመራትን የጀመሩ ሕዝቦች ናቸው::› የሚል ቃል አስፍሯል:: (Jackson, 1939, Ethiopia and the Origin of Civilization) በዚህ ዙሪያ Ethiopia and the Origin of Civilization እና Wonderful Ethiopians of Ancient Cushite Empire (2ኛው ፒራሚድ ገንቢዎቹ ኢትዮጵያን በሚል ርዕስ በአማርኛ ተተርጉሟል) የሚሉ መጻሕፍት ሰፊ ማብራሪያ ይሠጣሉ:: እነሱን መመልከት በጣም አስፈላጊ ነው:: መጽሐፎቹ እኛ እንደተረት እየቆጠርን የተውነውን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከግብፅ፣ ከግሪክ፣ ከሮማ፣ ከዕብራውያንና ከሌሎች አገሮች ጥንታዊ ጸሐፊዎች ማስረጃዎችን በመሰብሰብ በማስቀመጥ የሞገቱ ናቸው:: በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እንደ ዐባይ ወንዝ የሥልጣኔ መነሻ የነበረች አገር መኾኗ የማስረጃ ሚዛኑ ከፍተኛ ነው፤ እንደ ዓባይ ወንዝ የሥልጣኔዋም እርዝመት ቀዳሚ ነው፤ በዚህ ዐስተሳሰብ ላይ ኾነን ማሳያዎቹን ለሚቀጥለው ለመመልከት እንሞክራለን:: እስከዚያው ይቆየን! ያቆየን!

የዘር ፍጅት ቀጣዩ የኢትዮጵያ ፈተና? ሳምሶን ኃይሌ



ናልድ ዱቶን የተባለ ጸሐፊ “The Psychology of Genocide, Massacres and Extreme Violence: Why Normal People Come to Commit Atrocities” የተሰኘውን መጽሐፉን (2007) ሲጀምር፡- “አሁን ሰብአዊውን ገመና ስላወቅሁት፣ የመጽሐፌን መታሰቢያነት ለውሻዬ አድርጌዋለሁ፤” ይላል:: ምናልባትም ያሳለፍነው ክፍለ ዘመን ገድል በታሪክ ድርሳናት ሲዘከር ከሁሉ ጎልቶ የሚታይ ጉዳይ ቢኖር የሰው ልጅ በገዛ ራሱ ላይ የፈፀመው ሰቆቃና ጭካኔ መሆኑ አይቀርም::

አሳይተዋል:: በዚህም ዓለማችን ከርዕዮተ ዓለማዊ ግጭቶች ወደ ማንነት ግጭቶች ስለመሸጋገሯ ብዙ ተጽፏል፤ ተተንትኗል:: ይህ የኋልዮሽ ሽግግር በዘር፣ በደም፣ በቋንቋ ላይ ወደተመሠረተ ደመነፍሳዊ ማኅበር መሆኑ ያስከተለው የጥላቻ ፖለቲካ ደግሞ አጠቃላይ ሰው በሰውነቱ አብሮ በሠላም የመኖርን ብቻ ሳይሆን ጭራሹን የማኅበረሰቦችን በምድር ገጽ የመቆየት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል:: ብሔረሰቦች በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ እየያዙ በመጡ መጠን ደግሞ ብሔረሰቦችን ከምድረ-ገጽ የማጥፋት ሙከራዎች እዚህም እዚያም እየጎሉ መጥተዋል::

ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ባለፉት መቶ ዓመታት ፍጅቶችና መቅሰፍቶች በማይታመን ፍጥነት ጨምረዋል:: አገሮች ከመላው ክፍለ ዓለማት ተቧድነው ኹለት ታላላቅ ጦርነቶችን ተዋግተዋል:: በዚህም ከ100 ሚሊዮን ሰዎች በላይ አልቀዋል:: መንግሥታት በየክፍለ ዓለማቱ፣ በየቀጠናውና በየጎረቤቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጦርነቶች አድርገዋል፣ ብዙ ሚሊዮኖችም አልቀዋል:: ሠላሳ ኹለት አገሮች በተካፈሉበት በአንደኛው የዓለም ጦርነት (1906-10 ዓ.ም.) በሠላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰው አደጋ 14 በመቶ ሲሆን፣ ስድሳ አንድ አገሮችን ባሳተፈው በኹለተኛው የዓለም ጦርነት (1931-37 ዓ.ም.) 67 በመቶ፣ በክፍለ ዘመኑ መገባደጃ ደግሞ ወደ 90 በመቶ አሻቅቧል:: አፍሪካውያን ነጻነታቸውን ለማግኘት የከፈሉት መስዋዕትነት ድኅረ-ነጻነት ከተፋሰሱት ደም ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም::

በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ በተለይም በቦስኒያና በኮሶቮ፣ እንዲሁም በአፍሪካውያኑ በሩዋንዳ፣ ቡሩንዲና ኮንጎ የማይታመኑ እልቂቶችን አይተናል፤ታዝበናል:: በጎረቤታችን ሱዳን በዳርፉር መቶ ሺሕዎች በገዛ መንግሥታቸው ጋሻ ጃግሬነት ሲጨፈጨፉ ታዝበናል:: ደቡብ ሱዳን እንኳን ነጻ በወጣች ማግስት እንደገና ወደ እርስ በርስ ግጭት በመግባቷ እጅግ ብዙዎች በብሔረሰባዊ ማንነታቸው ምክንያት አልቀዋል:: በዚህ ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ አደጋዎች ማገርሸታቸውን እየታዘብን ነው:: የአዲሲቱ አገር ሦስተኛ ዓመታዊ የልደት ክብረ በዓል ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ባከበረች ማግስት በዴንካና ኑዌር ጎሳዎች መካከል የተነሳው የእርስ በርስ ጦርነት በዓለም ዐቀፍ ሸምጋዮችም የሚፈታ አልሆነም:: እንዲያውም አገሪቱ ከመወለዷ ወደመምከኑ እያዘገመች ይመስላል::

በተለይም ከሶሻሊሰቱ ካምፕ መፈራረስ በኋላ በዘውጌና ሃይማኖታዊ ማኅበረሰቦች መካከል የሚደረጉ ቀጥተኛ ግጭቶች በመጠንም፣ በአውዳሚነትና ዘግናኝነትም ከፍተኛ እመርታ

አካባቢያችን የዓለም የጦርነትና የደም መፋሰስ ቀጠና ከመሆኑም በላይ፣ በአገራችንም ቢሆን ላለፉት ሃያ ዓመታት የተጫነብን ብሔረሰባዊ ማንነትን አልፋና ኦሜጋ ያደረገ ፖለቲካ በማኅበረሰቦች መካከል ያሉ ድልድዮችን በመስበር፣ ጥላቻንና መካረርን የማፋፋሚያ መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል:: በአገራችን ማኅበራዊ ግጭቶች ከድንገተኛና ውሱንነት አልፈው ወደ ሰፊና ስልታዊ የዘር ጥቃት ድርጊቶች እየተሸጋገሩ

መምጣታቸውን፣ የዘር ጥላቻ በስሙ ሐውልት ማስቀረጹን እየታዘብን ነው:: በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች እያሰለሱ የሚከሰቱት ዜጎችን የማፈናቀል ወንጀሎች በምን ዓይነት ሁኔታ ወደ ዘር ማጥፋት ዘመቻዎች እንደሚለወጡ በትክክል መተንበይ አይቻልም:: ቀጥለን በዘር ላይ ተመርኩዘው ከሚፈፀሙ ጥቃቶች ዋነኛው የሆነውን ‹ጄኖሳይድ› ወይም የዘር ማጥፋት ወንጀልን ዓለም ዐቀፋዊ መልክ፣ መንስኤዎቹንና ሒደቱን እንዲሁም የዘር ጥቃቶች እንዴት ደረጃ በደረጃ እንደሚያድጉና ምንስ መፍትሔ ሊፈለግላቸው እንደሚገባ ባጭሩ እንመለከታለን::

የዘር ፍጅት በብሔረሰብና በእምነት ላይ ተመርኩዘው ከሚደረጉ ጥቃቶች መካከል እጅግ አሰቃቂ የሆነውና የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ተብሎ የሚታወቀው ‹ጄኖሳይድ› ነው:: ‹ጄኖሳይድ› የሚለውን ቃል የጅምላ ዘር ማጥፋት ተግባርን እንዲገልጽ በ1936 ዓ.ም. የፈጠረውና በዓለም ዐቀፍ ሕግጋት ውስጥ እንዲካተት ከፍተኛ ጥረት ያደረገው ራፋኤል ለምኪን የተባለ አይሁዳዊ ምሁር ነበር:: ወቅቱም ናዚ ጀርመን ለአይሁዳውያን “የማያዳግም መፍትሔ” ያለችውንና በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ወደር ያልተገኘለትን ጭፍጨፋ የምትፈፅምበት ነበር:: ይህንን ድርጊት ከሰብአዊ ጥቃቶች በልዩ ወንጀልነት ለመፈረጅ በመጀመሪያ የዘር ማጥፋትን ትርጉም መወሰን አስፈላጊ ነበር:: ስለሆነም የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በታኅሣሥ 1939 ዓ.ም. ያሳለፈው ውሳኔ ቁጥር A/Res/96(I) የ‹ጄኖሳይድ› ጥቃት ክልል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቡድኖችን እንዲያካትት ተስማማ:: ነገር ግን ከሁለት ዓመታት በኋላ በታኅሣሥ 1941 የፀደቀው A/RES/260A (III) ደንብ ጠባቡን በዘርና

23

በእምነት ማንነት ላይ ያተኮረውን ትርጉም እንዲይዝ በመደረጉ፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀልን ስለመከላከልና መቅጣት ስምምነት” (አንቀጽ 2) መሠረት፣ ‹ጄኖሳይድ› የሚባለው አንድን ብሔረሰብ፣ ዘውግ፣ ጎሳ ወይም ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ በጠቅላላው ወይም በከፊል ለማውደም በማሰብ የሚከተሉት አምስት ተግባራት ሲፈፀሙ ነው፡(1) የቡድኑን አባላት መግደል፤ (2) በቡድኑ አባላት ላይ ጽኑ አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት ማድረስ፤ (3) በማኅበረሰቡ አኗኗር ላይ በሙሉ ወይም በከፊል አካላዊ ጥፋት ለማስከተል የተሰላ እርምጃ መውሰድ፤ (4) በማኅበረሰቡ ውስጥ ወሊድ እንዳይደረግ ወይም እንዳይኖር የታለመ እርምጃ መውሰድ፤ (5) የማኅበረሰቡን ሕፃናት በግድ ወደሌላ ማኅበረሰብ ማዛወር:: ከዘር ማጥፋት ጋር ተቀራራቢ ትርጓሜ ያለውና ብዙ ጊዜም በተለዋጭነት የሚውለው “ዘር ማጽዳት” (ethnic cleansing) የተባለው ሲሆን፣ ይህ ድርጊት ደግሞ አንድን ማኅበረሰብ ከኖረበት አካባቢ በኀይል ማፈናቀልን ይወክላል:: ምንም እንኳን ስቃይን፣ ስደትንና ግድያን ቢያካትትም የዘር ማጽዳት ዓላማው ተጠቂውን ማኅበረሰብ በሙሉ ወይም በከፊል ማጥፋት አይደለም ይባላል:: ይሁን እንጂ የዘር ማጽዳት እርምጃ በጊዜ ካልተገታ ወደ ዘር ማጥፋት መሸጋገሪያ መሆኑን በመገንዘብ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤው በ1984 ዓ.ም. ዘር ማጽዳት የዘር ማጥፋት ዓይነት እንደሆነ ወስኗል:: ሌላውና ሰብአዊ ወንጀሎች የሚለው እሳቤም በሠላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ መጠነ ሰፊና የተቀናጁ ጥቃቶችን የሚመለከተው ሲሆን፣ በተመሳሳይ በአንድ ዘር፣ ብሔረሰባዊ ወይም ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ ላይ ብቻ የተነጣጠረ አይደለም:: ዘር ማጥፋት ከሰብአዊ መብቶች ጥሰት እጅግ የላቀ ተግባር ነው:: ዘር ማጥፋት ሌላ የእርስ በርስ ጦርነት፣ ሌላ የጎሳና የዘውግ ግጭት ወይም የከሸፈ ወይም የመከነ መንግሥት ተምሳሌት ብቻም አይደለም:: በሰው ለጆች ላይ ከሚያደርሰው እኩይ መቅሰፍት የተነሳ፣ ዘር ማጥፋት በራሱ በሥልጣኔ ላይ የተቃጣ አረመኔያዊ ጥቃት ተደርጎም ይቆጠራል:: በዚህም መሠረት በሶማሊያ መንግሥት ውድቀት የተነሳ የተፈጠረው ነውጥና ፍጅት በቦስኒያ፣ በሩዋንዳ፣ በኮሶቮና በዳርፉር ከታዩት ድርጊቶች የተለየ ነው:: ‹ጄኖሳይድ› እንደፊተኛው ግብታዊ ወንጀል ሳይሆን፣ በአደገኛና መሰሪ የፖለቲካ ኤሊቶች ታስቦና ታቅዶ በስልት የሚፈጸም አረመኔያዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ዘመቻ ነው:: እነዚህ ልዩነቶች የጸጉር ስንጠቃ ጉዳይ አይደሉም:: የዘር ማጥፋትን በተመለከተ በርካታ የተራራቁ ምሁራዊ አስተያየቶች ቢኖሩም፣ አጠቃላይ ተቀባይነት ያገኘውና ወንጀሉን ለመከላከል፣ ለማስቆምም ሆነ ለመቅጣት አመቺው ብቸኛው ሕጋዊ ትርጓሜ ከላይ የተቀመጠው ነው:: እንደ ዊሊያም ሻባስ ያሉ የሕግ ባለሙያዎች እንደሚስማሙበት የዘር ማጥፋትን ለመዳኘት የሚያገለግል የሕግ ማዕቀፍ ሰባት አንቀጾችን ካካተተው ከኑረምበርግ መርሆችና ከጄኖሳይድ ስምምነት ጀምሮ ለግማሽ ምዕተ ዓመት የኖረ በመሆኑ አዲስ መቅረጽ አስፈላጊ አይሆንም::

24

ተዋናዮች ጭካኔና አረመኔያዊነት ቀለም፣ ብሔረሰብ፣ ዘውግ፣ ሃይማኖት፣ መደብ፣ ርዕዮተ ዓለም ወዘተ. አይለይም:: በሁሉም ክፍለ ዓለማት፣ በሁሉም ዘመናት፣ በሁሉም ሥርዓታት ተከስቷል:: ኮሚኒስቶቹ እነ ስታሊን፣ ማኦ ሴቱንግ፣ ቺያንግ ካይሼክና ፖልፖት በጨፍጫፊነታቸው ሂትለርን የሚያስከነዱ ነበሩ:: የሰው ልጆች በጃፓን፣ በካምቦዲያ፣ በኮንጎ፣ በቡሩንዲ፣ እንዲሁም በቅርቡ በመካከለኛው አፍሪካና በሶሪያ ተቃዋሚዎች መካከል እንደተከሰተው የጠላትን ሥጋ እስከመብላት ድረስ ወደ አውሬነት እንደሚወርዱ በተደጋጋሚ ታይቷል:: ሥልጣኔ የሰው ልጅን ባሕርይ ያሻሽለዋል የሚለው አስተያየት እጅግ አከራካሪ ነው:: ራሱ የሰው ልጅ የመጠፋፋት አቅም በኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ዕድገት ደረጃ ብቻ የሚወሰን አለመሆኑ ገሃድ ሆኗል:: የሩዋንዳው “የሜንጫ ጭፍጨፋ” ከናዚዎች ሳይንሳዊ የጥፋት ዘዴዎች በአምስት እጥፍ ስሉጥና አውዳሚ ነበር:: በ100 ቀናት ብቻ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉትን የቀጠፈ ሲሆን፣ ሰማንያ በመቶውን ቱትሲዎች የጥቃቱ ሰለባ አድርጓል:: ስመጥሩ የፖለቲካ ሳይንቲስትና በፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ሥር የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የነበሩት ዝቢግኒው ብርዚንስኪ እንዳሉት “ቀደም ባሉት ጊዜያት አንድ ሚሊዮን ሕዝብን ከመግደል ይልቅ መቆጣጠር የቀለለ ነበር:: ዛሬ ግን አንድ ሚሊዮኖችን መግደል ከመቆጣጠር በአጅጉ የቀለለ ሆኗል፤” (ሀጋን 2009):: የዘር ማጥፋት በዘፈቀደና በድንገት የሚቀሰቀስ ሳይሆን ታስቦና ታቅዶ የሚከወንና የራሱ ተዋናዮችና ውስጣዊ ሒደቶች ያሉት ብቻ ሳይሆን በቡድን የሚከወን ድርጊትም ነው:: የዘር ማጥፋት ወንጀል ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ሥነ ልቦናዊ መልኮችን ያካተተ ሰፊ ሒደት ውጤት ነው:: እስከዛሬ እንደታየው የዘር ማጥፋት በዋነኝነት የሚቀነባበረውና የሚፈጸመው መንግሥታዊ ሥልጣን በጨበጡ የፖለቲካ ኤሊቶችና ደጋፊዎቻቸው በመሆኑ ወንጀሉን ለመከላከል፣ ለማስቆምም ሆነ ጥፋተኞችን ለፍርድ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል:: ሥልጣን የጨበጡ ቡድኖች በዘር ጥቃት ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ሊሆን ይችላል:: በጀርመን የናዚ ፓርቲው ግልጽ የሆነ ፀረ ሴማዊ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ገና ሂትለር ሥልጣን ከመያዙ በፊት ጀምሮ ለ15 ዓመታት የተካሄደ ነበር:: ሂትለር መንግሥት እንደመሠረተ በቀጥታ ሕልሙን ተግባራዊ ማደረግ ጀመረ:: በአይሁዳውያን ላይ የተከተለው ፖሊሲ በጦርነቱ ዋዜማ በ1931 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ከጀርመን ሕይወት ውስጥ አገለላቸው:: ለውድመት ተመቻቹ:: በኮሶቮና በቀሪው ዩጎዝላቪያ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ዕቅድ የተነደፈውና መስከረም 1979 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው በሰርቢያ የሳይንስና ሥነ ጥበብ አካዳሚ አማካኝነት ነበር:: ይህም ሰነድ ሚሎሶቪች ሥልጣን እንዲቆናጠጥና ዓላማውን በተግባር እንዲያውል ረድቶታል:: በሩዋንዳም ከጥላቻ ዘመቻው እስከ ግድያ ትዕዛዙ ድረስ ሂደቱ የተመራው በመንግሥት ፖለቲከኞች አማካይነት ነበር:: ሁቱ መራሹ አገዛዝ የጥላቻ ፖለቲካ

ሲያካሂድ የነበረው ቢያንስ ለአርባ ዓመታት ገደማ እንደነበር አይዘነጋም:: ቱትሲዎች በጦር ኀይሉ ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንዲያጡ መደረግ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ግልጽ መድልዎና በደል ይደርስባቸው ነበር:: የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ ፀረ ቱትሲ ፕሮፓጋንዳዎችን ያሰራጩ ነበር:: በ1995 ዓ.ም. የፈነዳው የዳርፉር ጭፍጨፋም የሱዳን መንግሥት የሃያ ዓመታት ፀረ ጥቁር/አፍሪካውያን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና ፖሊሲ ፍሬ ነበር:: ከደቡብ ሱዳን ነጻነት በኋላ ደግሞ ፕሬዚዳንት አልበሽር በንቀት ‹ዙርጋ› እያለ የሚጠራቸውን ሦስት የዳርፉር ብሔረሰቦች ማለትም ዳር፣ ማሳሊትና ዛግዋን መሬት የጃንጃዊድ ዐረብ ሚሊሻዎች ከመደበኛው የመንግሥት ሠራዊት በማበር እንዲነጥቁ፣ ነዋሪዎቹን እንዲያሰቃዩ፣ እንዲገድሉና እንዲደፍሩ፣ መንደሮችን በጠቅላላ እንዲያወድሙና ከብቶችንም እንዲወርሱ አድርጓል:: ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው በሥልጣን ያለው አገዛዝ ዋና ተዋናይ ይሁን እንጂ፣ የዘር ጥላቻን በማራገብና ሕዝቦችን ለመጠፋፋት በማዘጋጀት በኩል መንግሥትን የሚቃወሙ ብሔረሰባዊ ወይም ፖለቲካዊ ቡድኖችም ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ:: እነዚህ ቡድኖች አቅማቸው እስከፈቀደ ድረሰ በጠመንጃም ሆነ ያለጠመንጃ የሚፋለሙትን መንግሥት ከአንድ ወይም ከሌላ ብሔረሰብ ጋር በማዛመድ የዘር ጥላቻና ተቃውሞ ይቀሰቅሱበታል:: አገዛዙ ለፖለቲካቸው የሚመች ከሆነም ደግሞ በዴሞክራሲ፣ በፍትሕና በእኩልነት ስም በሕዝቦች ውስጥ የሚነፈርቅ ጠላትነት ይዘራሉ:: ነገር ግን በሠላምም ይሁን በአመጽ ሥልጣን ካልያዙ፣ ወይም ከፍተኛ ማኅበራዊ ነውጥ ካልተፈጠረላቸው በስተቀር እኩይ ዓላማቸውን በተግባር የማዋል ዕድል የላቸውም:: ከሥነ-ልቦና አንጻር ስናየው ደግሞ ሰፊ የዘር ጥቃቶች አመንጪዎችና አንቀሳቃሶች በበታችነት ስሜት የሚሰቃዩ የፖለቲካ ኤሊቶች ናቸው:: ከነዚህ ውስጥ ምሁራን በተለይም በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ ርዕዮተ ዓለሙን በመንደፍና በማስፋፋት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ:: የጥላቻው ደረጃ ወደ እብደት ደረጃ ሲሻገር ደግሞ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የዘረፋ ቡድን ካፖዎች፣ የለየላቸው ንኮችም ሳይቀር በብሔረሰብ ወይም በሃይማኖት ተቆርቋሪነት ስም ብቅ ብቅ ይላሉ:: ለአብነት ያህል እንደ ዶብሪካ ኮሲክ (ሰርቢያ)፣ ፈርዲናንድ ኒህማና (ሩዋንዳ)፣ ዶ/ር ጎብልስና (ጀርመን) ዶ/ር ሊዎን ሙገሴራ (ሩዋንዳ)፣ አረመኔው ሳይካትሪስት ራዶቫን ካራዲችን የመሳሰሉ ምሁራንን መጥቀስ ይቻላል:: የዘር ጥቃት በሰፊው ሲተገበር ቢያንስ በተርታው ሕዝብ ውስጥ የተወሰነ ተቀባይነትና ተባባሪነት ማግኘት የግድ ነው:: በጥላቻ የተዋጠና የማያመነታ የካድሬ ቡድን እስካለ ድረስ ደግሞ ሰፊውን ሕዝብ በውድም በግድም ወደ ጥፋቱ ማኅበር ማስገባት ይቻላል:: ማባበል፣ መደለል፣ ማስፈራራት፣ ማግለል፣ መቅጣት፣ መሳቂያ ማድረግ፣ ቀስ በቀስ ተግባር ላይ የሚውሉና በአረመኔያዊ ተግባሮች ላይ ለመሳተፍ የሚያመነቱን ለመቀላቀል የሚውሉ ስልቶች ናቸው:: በጀርመንና በሩዋንዳ ታይተዋል:: ተመራማሪዎች እንደሚሉት አመጽ አንድ ጊዜ

ከተጫረ በተዋናዮቹ ውስጥ እመርታዊ ለውጥ ያስከትላል:: በግለሰቦች ማንነት፣ በማኅበራዊ ደንቦች፣ በተቋማት፣ እንዲሁም በወግ ልማዶች ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖ ድርጊቱ የተለመደና ተራ እንዲመስል ያደርገዋል:: ክፉ አትዋል የሚለው ብሂል “ከፍ ባሉ” የቡድኑን ንጽሕና፣ መልካምነትና ደህንነት በመጠበቅና ጠላቶችና አጥፍቶ የተሻለ ማኅበረሰብ መፍጠር በሚሉ የሞራል መርሆዎች ይተካል::

ሁሉ ስሜቶች የተቀላቀሉበት የበታችነት መንፈስ ደግሞ የፖለቲካም ሆነ ኢኮኖሚ የበላይነት የማያጠፋው መሆኑ አንዱ አወሳሳቢ ችግር ነው:: ኒኮላስ ሮቢንስና አዳም ጆንስ “Genocide by the Oppressed” በሚል ርእስ በሳተሙት መጽሐፍ (2009) አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ኀይሎች (በሕዳጣን?) የሚካሄዱ ጭፍጨፋዎችን በማጥናት ረገድ ከሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ግንባር ቀደሙ በነባራዊው እውነታና በኅሊናዊ ግንዛቤ መካከል የሚስተዋለው ተገላቢጦሽ/ተቃርኖ ነው:: ሩዋንዳን ለአብነት ብንወስድ የሁቱዎች ብሔራዊ የበላይነት ከ1952 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ቢመሠረትም፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ግን የተዋረድ ግንዛቤው ሊለወጥ አልቻለም ነበር:: የቱትሲዎች ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ቁሳዊና አካላዊ የበላይነት ላይ የተመረኮዙ ፍረጃዎች በሰፊው የሁቱ ማኅበረሰብ ውስጥ የቅናት፣ የበቀልና የስጋት ምንጮች ነበሩ:: ሁቱዎች ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ እነዚህን ስሜቶች ከማጥፋት ይልቅ ቅኝ ገዥዎች በፈጠሯቸው የሐሰት እምነቶች ራሳቸውን ኮድኩደው ቀጠሉ::

ለመሆኑ የዘር ማጥፋትን የመሰሉ ዘግናኝ ድርጊቶች መሠረታዊ መንሥኤዎች ምንድናቸው? የባህል፣ ቋንቋና እምነት ልዩነቶች፣ የሀብት ክፍፍል ችግሮች፣ የፖለቲካ ሥልጣንና ውክልና፣ የዘመናዊነት ተጽዕኖዎች፣ የሰው ልጅ እኩይ ተፈጥሮ ወይስ ውስብስብ የሥነ ልቦና ችግሮች? የሚገርመው ነገር የዘር ጥቃቶች በዓላማም ሆነ በግብ በዘርና በእምነት ማንነት ላይ የተመሠረቱ ይሁን እንጂ፣ ለምሳሌ እንደ ሩዋንዳ ባሉት አገሮች የብሔረሰብ ድንበሮች፣ ቋንቋ፣ ባህል ወይም እምነት ቀዳሚ የግጭት ምክንያቶች አልነበሩም:: የዘር ጥቃትን በተለያየ ደረጃ የሚፈጽሙና የሚያስፈፅሙ ቡድኖች ቢያንስ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ይኖራቸዋል:: አንደኛው ፖለቲካዊ ምክንያት ሲሆን የጥቃቱ ዒላማ የሥልጣን ተቀናቃኝ ሊሆን፣ አገዛዙን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ተብሎ የሚገመትን ብሔረሰባዊና ሃይማኖታዊ ቡድን በተቻለ መጠን ሰጥ ለጥ አድርጎ ለመግዛት፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ ከምድረ ገጽ ጠራርጎ ለማጥፋት የሚፈጸም ድርጊት ነው:: ኹለተኛው ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሲሆን በተለይም በአንድ ብሔረሰብ ውስጥ ተሰባጥረው የሚኖሩና በኢኮኖሚው የተለያየ ዘርፍ እጅግ በተሳካላቸው ቡድኖች ላይ ያነጣጠረ ነው:: በእነዚህ ስኬታማ ማኅበረሰቦች የቢዝነስ እንቅስቃሴ ላይ አሉባልታዎች ከመንዛት፣ ከማሻጠርና አድማ ከማድረግ ጀምሮ ከፍተኛ ቀረጥ በመጣልና በመውረስም ጭምር እስከማክሰር ይሄዳል:: በገጠርማ አካባቢዎችም ከመሬታቸው የማፈናቀልና የመቀማት እርምጃዎች ይወሰዳሉ:: በተለይ በአገራችን በበርካታ አካባቢዎች የተደረጉ “በመጤነት” የተፈረጁ ማኅበረሰቦችን በማስፈራራትና በማስገደድ ማባረር እነዚህን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መልኮች ያቀላቀለ ከመሆንም አልፎ፣ የጥቃቱ አበጋዞች ወደፊት ለሚመኙት “ንጹሕ” ክልልና አገር መንገድ የሚያዘጋጅ ሒደት ተደርጎ ይቆጠራል:: ከላይ እንደጠቀስነው ማኅበረሰቦችን በኃይል በማስገደድ ከመኖሪያቸው የማፈናቀል ዓለም ዐቀፍ ወንጀል “ዘር ማጽዳት” ተብሎ ይታወቃል:: በዘር ጥቃት መንስኤነት የሚታወቀውና ረቀቅ ያለው ምክንያት ሥነ ልቡናዊ ሲሆን በተለይም ደግሞ ዋነኞቹን አሉታዊ ስሜቶች በቀል፣ ቅናትና ስጋትን ይጨምራል:: የዚህ አጠቃላይ መንፈስ መንስኤዎች ታሪካዊም ነባራዊም፣ እውነታም ምናባዊም ሊሆኑ ይችላሉ:: በቀል ጥቂትም ቢሆን ታሪካዊ ይዘት ያለውና ላለፉ ጉዳቶች መካሻ የሚፈልግ ስሜት ሲሆን፣ አቀራረቡም በፍትሕና ርትዕ ስም ይሆናል:: ቅናት ደግሞ በተቃራኒው ቡድን ነባራዊም ሆነ ምናባዊ ሀብት፣ ተሰጥኦ ወይም ዕሴት ላይ የተመሠረተ፣ ነገር ግን ማኅበራዊ ተቀባይነት የሌለው መንፈስ በመሆኑ ራሱን እንደ እኩልነት፣ አገር ወዳድነት፣ ተቆርቋሪነት፣ ወዘተ ባሉ መልኮች የሚገልጥ ነው:: ስጋት ታሪካዊውንም፣ ነባራዊውንም፣ መጻኢውንም አቅጣጫዎች የሚዳስስ በራስ ያለመተማመን ስሜት ነው:: እነዚህ

ከላይ እንደጠቀስነውም ሁቱ መራሹ መንግሥት ቱትሲዎች ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል የበቀል ጭቆና ሲያደርግባቸው ቆይቷል:: በርካታ ቱትሲዎች ተገድለዋል፤ አገራቸውንም ጥለው ተሰድደዋል:: በኋላም በ1950ዎቹ የተሰደዱት ቱትሲዎች ልጆች በ1980ዎቹ መጀመሪያ ወደ አገራቸው በኀይል ለመመለስ የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር የተሰኘ ጦር በኡጋንዳ መሥርተው ትግል ሲቀጥሉ በርካታ ቱትሲዎች ይህን ወታደራዊ ዘመቻ የሚደግፉ አልነበሩም:: ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ የሁቱዎችን የማይሞት ስጋት እንዲያንሰራራ አደረገው:: ቱትሲዎች አሁንም ሥልጣናችንን ቀምተው የጥንቱን አገዛዝ ሊጭኑብን እያሴሩ ነው የሚል ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ተቀሰቀሰ:: አንዳንድ ወቅታዊ አቀጣጣይ ጉዳዮች ሲጨመሩበትማ ሁኔታው ወደ ዘር ማጥፋት ሥነ ልቦና አደገ:: ለምሳሌ ሁቱዎች በነሐሴ ወር 1985 ዓ.ም. የተደረገው የአሩሻ ስምምነት ለቱትሲዎች ያደላ ነው የሚል ቁጭት አድሮባቸው ነበር::

በአገራችን ማኅበራዊ ግጭቶች ከድንገተኛና ውሱንነት አልፈው ወደ ሰፊና ስልታዊ የዘር ጥቃት ድርጊቶች እየተሸጋገሩ መምጣታቸውን፣ የዘር ጥላቻ በስሙ ሐውልት ማስቀረጹን እየታዘብን ነው

በዚህ ላይ ደግሞ ለሁቱ ጽንፈኞች ተአማኒነት መጨመር የቡሩንዲው ሁቱ ፕሬዚዳንት ሜልኮር ንዳዳየ በቱትሲ ጄኔራሎች ጥቅምት 1986 ዓ.ም. መገደሉ ዋነኛው ነበር:: ይህን የስጋት ጡዘት ለመደምደም ሀቢሪማናም በሚያዝያ 1986 ዓ.ም. በአውሮፕላን አደጋ ሕይወቱ አለፈች:: ይህም አገሪቱን ወደ ደም ምድርነት ቀየራት:: በዘመናችን ከፍተኛ የዘር እልቂት በተፈፀመባቸው አገራት በጀርመን፣ በሰርቢያና ኮሶቮ፣ በዳርፉርና በሌሎችም አካባቢዎች የታዩት ተመሳሳይ ሒደቶች ናቸው:: እዚህ ላይ ትኩረታችንን የዘር ጥቃት ርዕዮተ ዓለም ምንድነው? ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ዘግናኝ ወንጀል ለመከላከልም ሆነ ለማስቆም ያልቻለው በምን የተነሳ ነው? የዘር ጥቃትን አስቀድሞ ለማወቅና ለመጠንቀቅ ምን መደረግ አለበት? ወደሚሉት ጉዳዮች እንመልስ:: የዘር ጥቃት የሚገለጥባቸውን መልኮችና ደረጃዎች፣ ችግሩን ለመቅረፍ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ያጋጠመውን ፈተና፣ እንዲሁም በየፈርጁ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የመከላከል እርምጃዎች እንዳስሳለን:: ምድራችን ሰብአዊ ፍጡራን ለመጠፋፋት የተፋጠጡባት አውድማ የመሆኗ ነገር በእጅጉ የሚያሳስብ ነው:: ችግሩን የበለጠ አደገኛ የሚያደርገው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር ማንዘሩን ከናካቴው ለማውደም የሚያስችል

25

አቅም ማበጀቱ ነው:: የሃያኛው ክፍለ ዘመን ከባተ በኋላም አመክንዮና መርህ በጠቋሮቹ የስሜትና ጥላቻ መናፍስት እንደተዋጡ የቀሩ ይመስላል:: በየአቅጣጫው ሕይወት እየረገፈ ደም እየጎረፈ ነው:: የዚህ ሁሉ ፍዳ ደራሲ የሆነው የማንነት ፖለቲካ አሁንም ከመንበሩ አልወረደም:: ታዲያስ ምን ይበጃል? የጥላቻ ፖለቲካ የማንነት አስተሳሰብን ተጣብቶ የሚኖርና በሂደትም ጭራሽ ፖለቲካ የተባለን ነገር የሚያጠፋ መንፈስ ነው:: አደገኛነቱም በከፊል የመደብ፣ የርዕዮተ ዓለምና የእምነት ድንበሮችን ተሻግሮ ከማስተባበር ባሕርይው ይመነጫል:: የዘር ጥቃት አቅጣጫውን የሳተ ጽንፈኛ ብሔረተኝነት ወይም ጎሰኝነት ውጤት ሲሆን፣ ብሔረተኝነት ደግሞ ድሩም ማጉም ታሪክ ነው:: ለዘረኞች “ሌላው” ማኅበረሰብ ብሔራዊ ባላንጣም ታሪካዊ ጠላትም ነው:: ይህን ጠላት ለማጥቃት በሚነድፉት መርሐ ግብር ውስጥም ታሪክ ነክ ፖለቲካ ዋነኛ የብሶት አስታዋሽና አንቀሳቃሽ ኀይል ሆኖ ያገለግላል:: ታሪክ ለጠባብ፣ አጭርና አፍራሽ ግብ እንዲውል እንዳመችነቱ ይፈበረካል፣ ይቃናል፣ ይወላገዳል፣ ይበረዛል ወዘተ. ዘውጌ ብሔረተኞች የታሪክ እስረኞች እንደመሆናቸው መጠን ለአብሮነትና አዎንታዊ መስተጋብሮች የከረረ ጥላቻ አላቸው:: ካሰመሩት ጠባብ ቅጥር ውጭ ያሉትን ታሪኮች በሙሉ የጭቆናና የጨቋኝ ብሔረሰብ ገድሎች በማለት ያጣጥላሉ:: ቆምንለት የሚሉትን ማኅበረሰብ ራስ በቅ፣ ፍጹምና ያልተነካካ አድርገው ይስላሉ:: ዶ/ር የራስወርቅ (1998፣78) እንዳስገነዘቡት “አክራሪ ጎሰኞች የማንነት መጋራትን፤ እንደድልድይ የሚያገለግሉ የብዝሃ-ማንነት ባለቤት የሆኑ ሰዎች መኖር ለሚያራምዱት አጀንዳ አመች አለመሆን በሚገባ ስለሚረዱት ይክዱታል፤ ያጥላሉታል፤ ያወግዙታል:: ጎሳቸውን ወይም ብሔረሰባቸውን በጠባቡ የሚያጥር ትርጉም ያስቀምጡታል:: ንጹሕነቱን መጠበቅንም ዋነኛ ጉዳይ ያደርጉታል፤” እነዚህ ኀይሎች ታሪካዊ ቁስሎችን በመሞዠቅ፣ የግጭት ገድሎችን ነጥሎ በማጋነን የቁጭት መንፈስን ለማፍላት አበክረው ይሠራሉ:: “የትናንቱ ግፍ ሳይበቃን፣ ዛሬም ለጥቃት ተጋልጠናል፤” የሚል ፍርሃት ይዘራሉ:: በነጻነት፣ በፍትሕና ርትዕ ስም ለታሪካዊ በቀል ያነሳሳሉ:: የጥላቻ ፖለቲካ “መሰሪ ጠላታችን ሳይቀድመን እንቅደመው” በሚል የአልሞት ባይ ተጋዳይነት አቋም ለማስፈን የሚታለም/የሚታቀድ ሲሆን፣ ቁልፍ አስተሳሰቡም “አከርካሪን መስበር፣ አፈር ማስጋጥ፣ አንገት ማስደፋት፣ ቅስም መስበር” ወዘተ. በሚሉ ሐረጎች ይገለጣል:: በባሕርይው ይህ የደመኝነት አስተምህሮ በነተበ የታሪክ እውነታ ወይም በለየለት ፈጠራ ላይ የተመሠረተ ነው:: ለምሳሌ የሰርቦች ቁጭት ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በ1381 ዓ.ም. በተደረገው የኮሶቮ ጦርነት ከደረሰባቸው ሽንፈት ይነሳና በኹለተኛው የዓለም ጦርነት በፋሽስታዊው የክሮሽያ ኡስታሻ አገዛዝ እስከተፈጸመባቸው ግፍ ድረስ በቀጭን ክር ያስተሳስራል:: ይባስ ብሎም ቱርኮች በ14ኛው ክፍለ ዘመን፣ ክሮአቶች ደግሞ በ1940ዎቹ ለፈጸሙት በደል በ1990ዎቹ የቦስኒያ ሙስሊሞችን ጭዳ አድርጓል:: በአጠቃላይ ዘውጌ ብሔረተኞችና ጎሰኞች ከዛሬውና ከመጭው ተስፋ ይልቅ ባለፉ ታሪኮች

26

በመኮድኮዳቸው፣ ጠላቶቻቸው አያቶችና ቅድመ አያቶች ናቸው:: በአገራችን አንዳንዶች ደማቸው የሚሞቀው እነሚኒልክ ሲነሱ ሲሆን፣ የሚያባንናቸው “የነፍጠኞች ሴራ ከትናንት እስከዛሬ” ነው:: ይኸው የተወላገደ የተጠቂነት ቅርስ የዛሬን እውነታም በቅጡ እንዳይገነዘቡ ይከልላቸዋል:: ዓለምን ቢጨብጡም ኅሊናቸው ዓይተኛም:: ተመራማሪዎች እንደሚጠቁሙት “ተጨቆንኩ” የሚለው ቡድን ሥነ-ልቦና ጨቋኝ የተባለውን በተመለከተ ካሳደረው ያለመተማመንና የቅናት ስሜት ጋር የተቆራኘ ነው:: እሮሮውም በውኑም ሆነ በሕልሙ ባለጋራውን እያሰበ እንጂ በተጨባጭ ባለበት ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ አይደለም:: ስለዚህም ናዚዎች፣ ሰርቦችና ሁቱዎች ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊው ሥልጣን በእጃቸው ተጠቅልሎ እያለ “ጠላቶቻችን ሊያጠፉን ወይም ሊውጡን ነው፤” የሚለው ደመነፍሳዊ ቅዠት ይረብሻቸው ነበር:: ልብ ሊባል የሚገባው የጥላቻ ታሪክ አበጋዞች የአገምጠቀም ደራሲያን ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑና በየትምህርት ተቋማቱ ውስጥ የተሰገሰጉ “ምሁራን” ናቸው:: እነዚህም ለ‹ጄኖሳይድ› ከሚደረጉ የሥነ ልቦና ዝግጅቶች መካከል ዋነኞቹ በሆኑት ብሔረተኛና ጎሰኛ ስሜቶችን የሚያጠናክሩ አስተሳሰቦችና ተቋማትን በማስፋፋት፣ እንዲሁም የጀግንነት ወኔን በመቀስቀስ ረገድ በቀደምትነት ይሳተፋሉ:: “ያልተበረዘ ያልተከለሰ” ታሪካችንን ለመጻፍ ከኛ በላይ ላሳር ይላሉ:: ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ እስከሆነ ድረስ በጥናትና ምርምር የተለወሰ ውሸትና ክህደት ለማራመድ ቅንጣት አያመነቱም:: አቅማቸው በፈቀደ መጠን የሚወጥኑት የአስተሳሰብ ጽዳት ከታሪክ አሻራዎች ጽዳት ይጀምራል:: ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ መዛግብት፣ የታሪክና ቅርስ መዘክሮች ዋነኛዎቹ ዒላማዎች ይሆናሉ:: የትምህርት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሃንና ሌሎችም ማኅበራዊ መድረኮች በጽንፈኛ አስተምህሮዎች ይቃኛሉ:: የቦታዎች፣ መንገዶች፣ ተቋማት፣ አልፎም የግለሰብ ስሞች ሳይቀሩ ይለወጣሉ:: የሕወሓት/ ኢሕአዴግ መሪዎች የኢትዮጵያ ታሪክና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መልካም ነገሮች እነሱ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ እንደጀመሩ ሊያስገነዝቡን የሚታትሩት ከዚህ አንጻር ነው:: የቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች የሠሩት ሥራ ወይ ከነጭራሹ አይነሳም፤ ከተነሳም በአሉታዊ ጎኑ ብቻ ነው:: የሁቱ “የታሪክ ምሁራን” ልክ በአገራችን እንደተደረገው ቱትሲዎች በሩዋንዳ የሠፈሩበትን ሒደት “የውስጥ ቅኝ አገዛዝ” (internal colonialism) በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲሠሩበት ኖረዋል:: የሰርብና የሁቱ ጽንፈኞች በ1980ዎቹ ባካሄዱት የኅሊና ብዝበዛ፣ በሕዝባቸው መካከል ጥላቻና ፍርሃትን በማንገስ ለዓላማቸው አመቻችተውታል:: ኒል ክረሰል (2002፣ 97) እንደጠቆመው የዘር ጥቃት አስከፊነት የጋራ ማንነት መገለጫዎች በተንሰራሩበት፣ በተጋነኑበትና ለፖለቲካ ጥቅም በተበጃጁበት መጠን የተወሰነ ይሆናል:: በአጭሩ ታሪክ የዘር ማጥፋት ርዕዮት ምሰሶ ነው::

ከጥላቻ ወደለየለት እብደት የዘር ጥቃት ከመቅጽበት ዱብዳ ሳይሆን፣ በዕቅድና በስልት ከፍረጃ እስከ ደም ማፋሰስ የሚሸጋገር ሒደት ነው:: የመጀመሪያው ደረጃም የጥቃቱ ዒላማ የሆነውን

ማኅበረሰብ እኩይነት በሚያጎሉ ቃላትና ትእምርቶች ለይቶ መግለጽ ነው:: ለምሳሌ ደገኛ፣ መጤ፣ ሠፋሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ተስፋፊ ወዘተ. የተለመዱ ቅጽሎች ናቸው:: ይህ ውግዘት ላቅ ሲልም በሚታይና በሚዳሰስ ቁሳቁስ ይገለጻል:: የጥላቻው መሐንዲሶች በአንድ አገር ዜጎች መካከል የማይፋቅ የደመኝነት ሐውልት ይቀርጻሉ:: እንደምሁራን እምነት የፖለቲካ መሪዎች በአደባባይ ዲስኩሮቻቸው፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን፣ በፓርቲ ልሳናት ወዘተ. እንዲህ ያሉ መንፈሶችን ማራገብ ሲጀምሩ የዘር ማጥፋት ሊከሰት እንደሚችል ከሚጠቁሙ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ ነው:: በተለይ ተጠቂዎችን ከመፈረጅ በተለጣጣቂ ኅሊናዊና ማኅበራዊ ክልላቸውን ማጥበብና መዝጋት ዓይነተኛ ስልት ነው:: በንግድ፣ በእንቅስቃሴ፣ በሥራና በትምህርት ዕድል፣ በፖለቲካ ውክልና፣ በፍትሕ፣ በሰብአዊና ዜግነታዊ መብቶችም ጭምር መድልዎ መፈፀምና ማግለል፣ ንብረቶቻቸውን መውረስ፣ ከቀያቸው ማፈናቀል፣ ማሳደድና በማጎሪያዎች ማሰባሰብ ይፈጸማሉ:: ናዚዎች ከሞት ቀጠናዎች በፊት በአይሁዳውያን ላይ ተከታታይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ግድያ ማድረግ ነበረባቸው:: በሰርቢያ የዘር ማጽዳቱ የጀመረው ተወላጅ ላልሆኑ የሥራ ዕድሎችን በመገደብ፣ በነጻነት የመሰብሰብ፣ የመንቀሳቀስና የመገናኘት መብቶቻቸውን በመሸርሸር ነበር:: ከዚህ ሁሉ ቅድመ-ዝግጅት በኋላ የዘር ጥቃቱ ራሱን የቻለና የማይቀለበስ እብደት ይሆናል:: ሰዎች በተነሳሽነትም ሆነ ከፍርሃት ይሳተፉበታል:: ትክክለኛና ተገቢ፣ ወይም ሊያመልጡት የማይቻልና አይቀሬ አድርገው ይቀበሉታል:: ነገር ግን ድርጊቱን ሊቃወሙ የሚፈልጉ፣ በማባበያና የማስፈራሪያ ስልቶች ሰልፍ የማይገቡ ካሉ ደግሞ በባንዳነት፣ በመናፍቅነትና በከሃዲነት መክሰስ ይከተላል:: የናዚ ጀርመን ኹለተኛው ሰው የነበረው ኸርማን ጎሪንግ በ1938 የኑረምበርግ ችሎት ላይ እንደተናገረው “ድምጽ ኖራቸውም አልኖራቸው ሕዝቦች ሁሉጊዜም ለመሪዎቻቸው እንዲታዘዙ ማድረግ ቀላል ጉዳይ ነው:: ዋናው ነገር እየተጠቁ መሆናቸውን መንገር ነው:: ከዚያም ሠላም ፈላጊዎቹን አገር ወዳድነት ስለሚጎድላቸው ለአደጋ እያጋለጡን ናቸው ብለህ ማውገዝ ነው፤” (ዱቶን 2007፣ 109):: ለጥላቻ ፖለቲካ ነጋዴዎች ተጠቂ ቡድኖችን ማግለል በቂ አይደለም:: ከምድረ-ገጽ መወገድ አለባቸው:: ለዚህም ነው በማሕፀን ያሉ ሽሎችን ዘንጥሎ በማውጣት ግንዱን ከነሥሩና ከነአበባው ለማጥፋት መሞከራቸው:: በሌላም በኩል የዘር ማጽዳት ረቂቅ ዓላማው የራስንም የበታችነት ስሜት ጠራርጎ መገላገል ይመስላል:: እንደ ማኅበራዊ ሥነ ልቦና ተመራማሪዎች ግምት ይህ የማይሞት የውርደት ስሜት ለሚታየው ቅጥ የለሽ ጭካኔ ከፊል ምክንያት ይሆናል:: ቁም ነገሩ መግደሉ ብቻ አይደለም:: እንዲያውም ግድያው የማዋረዱ አካል በመሆኑ የአምልኮ ዓይነት ሥርዓት ይታይበታል:: በአስከሬኖች ላይ ሳይቀር ዘግናኝ ድርጊቶችን ከመፈጸም ያደርሳል:: ሆኖም ይህ እብደት እንደ በጎ ተግባር

እንዲቆጠር ወይም ኀሊናን እንዳይወጋ የአክብሮት መጠሪያ ይደለደልለታል:: ሰርቦች አረመኔያዊ ድርጊታቸውን “ማጽዳት” በማለት ሲያቆላምጡት፤ “መጠራረግ፣ ማስወገድ፣ ማባረር” በካምቦዲያ የተለመዱ አገላለጾች ነበሩ:: ሁቱዎች ጭፍጨፋውን “ሥራ”፣ ናዚዎች ደግሞ “ማግለል እና ልዩ እርምጃ” በማለት ይጠሩት ነበር::

ቢል ክሊንተን የአይሁዳውያን ፍጅት (holocaust) መዘክርን ከሩዋንዳው እልቂት ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ሲመርቁ ባደረጉት ንግግር፣ “የታሪኩን ከሃዲዎች እንታገላለን፤ ይህ ጉዳይ በፍጹም እንዳይደገምም ቃል እንገባለን” ብለው ነበር:: ይሁን እንጂ ሌላው ቀርቶ በዚያ የሩዋንዳ ምድር ቁና በሆነችበት ሰዓት፣ የኋይት ሀውስ ፖለቲከኞች ‹ጄኖሳይድ› የምትለዋን ቃል እንኳን በጥንቃቄ ከአደባባይ አስወግደዋት እንደነበር አይዘነጋም::

ዶ/ር የራስወርቅ በተጠቀሰው መጽሐፍ (74-75) ግሪጎሪ ስታንተን የተባሉት ምሁር ያስቀመጧቸውን ስምንት የዘር ማጥፋት ፍጅት ደረጃዎች ጠቅሰው እንደሚከተለው ዘርዝረዋቸዋል፡•

የመጀመሪያው ደረጃ፣ “እነሱ” እና “እኛ” ብሎ ለመከፋፈል በሚረዳ መልኩ ልዩነትን በማስረገጥ የሚደረግበት ምደባ ወይም classification፤



ኹለተኛ፣ እንደልዩ አልባሳት፣ ተንጠልጣይ ምልክቶችና ከዚያም አልፎ በመታወቂያ ካርድ ላይ በሚሰፍር ቃል ወይም ምልክትና እነዚህን በመሳሰሉ መለያዎች አማካይነት “ዒላማዎችን ለይቶ ማተም” ወይም symbolization፤



ሦስተኛ፣ አንዱ ቡድን የሌላውን ቡድን ሰብአዊ መሆን የሚክድበትና ከእንስሳት፣ ተባይና በሽታ ጋር የሚያይዝበት “ከሰብአዊነት ማስወገድ” ወይም የdehumanization ደረጃ፤



አራተኛ፣ የዘር ማጥፋትን ፍጅት ለማስፈፀም አስፈላጊው ዕቅድ የሚዘጋጅበት፤ አስፈጻሚው ኀይል የሚሰናዳበትና የሚታጠቅበት የማደራጀት ወይም የorganization፤



አምስተኛ፣ ለይቶ ለመምታት አመች የሆነው የመለያየት ሂደት የሚከናወንበት በተለይም መሐል ላይ ያለው ሕዝብ ወደ አንዱ ወይም ወደሌላው እንዲከት የሚደረግበት የpolarization ደረጃ፤



ስደስተኛ፣ የፍጅት ሰለባዎች የሚለዩበትና ለዕርድ የሚዘጋጁበት የpreparation ደረጃ፤



ሰባተኛ፣ ራሱ ግድያው የሚጀመርበትና ወደ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ የሚዛመትበት የextermination ደረጃ እንዲሁም



ስምንተኛ፣ አስገራሚውና አይቀሬው ድርጊቱን የመካድ ወይም የdenial ደረጃ ናቸው::

የ“ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ” ሚና ዓለም የጉልበተኞች ርስት ስትሆን ገዥ መርኋም ብሔራዊ ጥቅም የሚባለው ነው:: ይህንን ጥሬ ሐቅ የሚያስተባብል ፍንጭ እስካሁን አልተገኘም:: ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በቦስኒያ፣ በሩዋንዳና በኮሶቮ የተደረጉትን የዘር ማጥፋት ፍጅቶች በቁርጠኝነት ለመከላከልና ለመግታት እንዳልቻለ የሚታወቅ ነው:: ይህ የሆነው ግን ወንጀለኞቹን የሚመለከት ወቅታዊ መረጃና በቂ ወታደራዊ አቅም ሳይኖር ቀርቶ አልነበረም:: ለምሳሌ አሜሪካኖች የሩዋንዳውን እልቂት የዝሆን ጆሮ ይስጠን ብለው ያለፉት በሶማሊያ ከአምስት ወራት በፊት ባጋጠማቸው ውርደት በመሸማቀቃቸው ምክንያት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ:: ነገር ግን ማንም የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ በጨረፍታ የታዘበ እንደሚመሰክረው ለአሜሪካውያን ሰብአዊ ጉዳዮች ከአፍአዊ ልፈፋ ያለፉ አጀንዳዎች ሆነው አያውቁም::

በተደጋጋሚ እንደታየው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላቅ ያሉ ታሪካዊ ኀላፊነቶቹን ለመወጣት ብቃቱም ተነሳሽነቱም ኖሮት አያውቅም:: ከ1984 እስከ 1987 ዓ.ም. በቦሲኒያና በሰረብረንካ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለቁት የተመድ የታጠቁ ወኪሎች አፍንጫ ሥር ነበር:: ምሕረት የለሾቹ የሁቱ አራጆች አሜሪካ መራሹ ማኅበረሰብ የቦስኒያን ጭፍጨፋ ለማስቆም ያለመቻሉንና ሶማሊያንም እንደፍጥርጥሯ አራግፏት መሄዱን በጥንቃቄ ታዝበዋል፤ በቂ ተመክሮ ቀስመዋል:: የጥፋት ዕቅዳቸውን በተግባር ለማዋል ከከንፈር መጠጣ ያለፈ ተቃውሞ እንደማይገጥማቸውም ተረድተው ነበር:: የተመድ የሰብአዊ መብቶቸ ኮሚሽንም ሆነ ዓለም ዐቀፋዊና አሕጉራዊ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሩዋንዳ ‹ጄኖሳይድ› እየተፈፀመ መሆኑን ያሳወቁት ገና ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም፣ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ 1986 ዓ.ም. የ‹ኢንተርሃምዌ› እና የ‹ኢምፑጋሙጋምቢ› ሚሊሻዎች የደም አበላ ሲያጎርፉ “ሃይ!” ያላቸው አልነበረም:: በወቅቱ የመንግሥታቱ የሠላም ኀይሎች የፈጸሙት ቅሌት የጥቂት ምዕራባውያንን ነፍስ ይዞ መፈርጠጥ ነበር:: በመጨረሻው ሰዓት ፈረንሳይና አሜሪካ በጉዳዩ ጣልቃ ለመግባት ሲገደዱም ቢሆን ያደረጉት ተጠቂዎቹን ከመታደግ ይልቅ ግፈኞቹ ወደ ዛየር እንዲያመልጡ መርዳት ነበር::

ዘውጌ ብሔረተኞች የታሪክ እስረኞች እንደመሆናቸው መጠን ለአብሮነትና አዎንታዊ መስተጋብሮች የከረረ ጥላቻ አላቸው፡፡ ካሰመሩት ጠባብ ቅጥር ውጭ ያሉትን ታሪኮች በሙሉ የጭቆናና የጨቋኝ ብሔረሰብ ገድሎች በማለት ያጣጥላሉ፡፡ ቆምንለት የሚሉትን ማኅበረሰብ ራስ በቅ፣ ፍጹምና ያልተነካካ አድርገው ይስላሉ

ማድሊን ኦልብራይት ለመጀመሪያ ጊዜ ዘር ማጥፋቱን በአደባባይ ያመኑት በ1989 ዓ.ም. ሲሆን፣ በ1990 ዓ.ም. ደግሞ ክሊንተን በይፋ ለስህተቱ “ይቅርታ” ጠይቀዋል:: ልብ ብሎ ለተመለከተው ነገሩ ተጨማሪ ለበጣ ይመስላል:: በሩዋንዳ ፍጅት ወቅት የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የነበሩት አፍሪካዊው ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ አንዳችም አዎንታዊ አስተዋጽዖ አላደረጉም:: በወቅቱ የድርጅቱ ጸጥታ ማስከበር ኀላፊና በኋላም የተመድ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሌላው አፍሪካዊ ኮፊ አናንም ቢሆኑ እያንገራገሩ ‹ጄኖሳይድ› መፈጸሙን የተቀበሉት በ1991 ዓ.ም. ነው:: ሆኖም ከዚህ ዘግናኝ ስህተት ትምህርት የቀሰመ ወገን አልነበረም:: በዳርፉር አሜሪካ አለወትሮዋ ቀድማ በ1996 ዓ.ም. “የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል” በማለት ስትጮህ፣ ኮፊ አናን ከማንገራገር አልፈው በ1997 ዓ.ም. ጭራሽ ድርጊቱ አለመፈፀሙን ገለጹ:: የአውሮፓ ኅብረትም (ኋላ ቢቀበለውም) ሆነ የሰብአዊ መብቶች ጠባቂ ድርጅት ለቡሽ አስተዳደር ድጋፍ አልቸሩትም:: በክፍለ ዓለሙ ደም እንደጅረት ሲፈስስ “የወሬ መደብር” ወይም “የአምባገነኖች ክበብ” ተብሎ የሚተቸው የአፍሪካ ኅብረት እንደ ልማዱ ከሕዝብ ግንኙነት ተውኔቶችና ከጣት ቅሰራ የዘለለ ኀላፊነቱን አልተወጣም:: እንዲያውም በዳርፉር ጉዳይማ ዓለም ዐቀፉ ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ ያስተላለፈውን የእስር ትዕዛዝ በጣልቃ ገብነትና በሉዓላዊነትና በ“ቀለም ትምክህተኝነት” ስም በማላከክ ድርጊቱን እስከማውገዝ ደርሷል:: አሳፋሪ የበታችነት መገለጫ ሆኖ በታሪክ መዘከሩ አይቀርም:: ከቅድመ መከላከሉና ጥቃት ከማስቆሙ ውድቀት

27

ባልተናነሰ የድኅረ ጭፍጨፋው የፍርድ ሒደትም ተስፋ አሰቆራጭ ነው:: አንዱ ተግዳሮት ወንጀለኞቹ በሥልጣን ያሉ ወይም በተከታዩ መንግሥት ከለላ ያገኙ መሆናቸው ነው:: ለዚህ ደግሞ አሮጌው የዌስትፋሊያ ግንዛቤ (1641 ዓ.ም.) ወይም የመንግሥታዊ ሉዓላዊነት መርህ መደበቂያ ሆኖ እያገለገለ ነው:: ለምሳሌ ከ1907-8 ዓ.ም. በመሐመድ ታላት የሚመራው የወጣት ቱርኮች አገዛዝ ወደ ኹለት ሚሊዮን የሚሆኑ አርመኖችንና የተወሰኑ ግሪኮችንም አጥፍቷል:: ይህን ወንጀል እስከዛሬም ድረስ ቱርክ ያልተቀበለችው ሲሆን፣ በምዕራቡ ዓለምም ቢሆን ይፋ ዕውቅና የተሰጠው ገና በቅርቡ ነው:: ባለፈው ዓመት የፈረንሳይ ፓርላማ ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ፍጅት መሆኑን ዕውቅና ሲሰጥ የፕሬዚዳንት (ያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር) ኤርዶዋን መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምቶ እንደነበር እናስታውሳለን:: እውነትም ሂትለር በ1931 ዓ.ም ንግግሩ “አርመኖችን ማን ያስታውሳቸዋልና” ሲል ተንብዮ ነበር:: ነገሩ “እኛም ለምንፈጽመው አይሁዳውያንን የማስወገድ እርምጃ ስጋት አይግባችሁ፤” ይመስላል:: በ1951 እና በ1962 ዓ.ም. መካከል ወደ አንድ ሺሕ ገደማ ናዚዎች በጦር ወንጀለኝነት ቢከሰሱም፣ ዕድሜ ይፍታህ የተፈረደባቸው ከመቶ ያነሱ ናቸው:: በተከታዮቹ ዓመታትም ለፍርድ ከቀረቡ ወደ ስድስት ሺሕ ናዚዎች ውስጥ ተመሳሳይ ቅጣት የተፈረደባቸው 157 ብቻ ናቸው:: በተለይ ደግሞ የናዚ ዳኞች በዘመናቸው “ፀረ ናዚ ቀልድ ቀልደሃል” በመሳሰሉ ቀላል ምክንያቶች ጭምር ወደ ሃያ ስድስት ሺሕ ሰዎች በሞት የቀጡ ቢሆንም፣ አንዳቸውም ጥፋተኛ ሆነው አልተገኙም:: በ1931 ዓ.ም. ለተፈፀመው “የናንኪንግ መደፈር” ለተሰኘውና የሦስት መቶ ሺሕ ቻይናውያንን ሕይወት ለቀጠፈው ግፍ በሕግ ተፈርዶባቸው የተሰቀሉት ሰባት የጃፓን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ብቻ ነበሩ:: በተመሳሳይ የቦስኒያው ጭፍጨፋ መሪና አስተናባሪ ስሎቮዳን ሚሎሶቪች (በኋላ በኮሶቮ ጉዳይ እስኪጋለጥ) በ1987 የዴይተን ስምምነት በሠላም ሐዋሪያነት መወደሱ ታላቁ የዘመናችን ምፀት ነው:: ሚሎሶቪች በሄግ ችሎት የተከሰሰው “በሰብአዊ ፍጡር ላይ ወንጀል በመፈፀም” እንጂ በዘር ማጥፋት ፍጅት አልነበረም:: በእስር ቤት ሕይወቱ እስኪያልፍ ድረስ በጄኖሳይድ ወንጀል ለመክሰስ የሚያስችል ማስረጃ ተሰብስቦ አላለቀም ነበር:: የሌሎቹ የጥቂት ሰርብና ክሮአት ጄኔራሎች ጉዳይም በፍትሕ የመቀለድ ያህል ነበር:: የሩዋንዳውም የፍርድ ሒደት ከፍተኛ ንትርክና መሰናክል የበዛበት በመሆኑ የተፈለገውን ያክል አልሄደም:: ከነጆሴፍ ኮኒ የማይሻሉት እንደነ አልበሽር ያሉ ወንጀለኞች በዚሁ በመዲናችን ሳይቀር ደግሞ አሁንም በቀይ ስጋጃ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው:: ይህ የተስፈኛ ዘር አጥፊዎችን ልብ የሚያደነድንና አጥፍቶ ያለመጠየቅ ባህልን የሚፈጥር ድርጊት በእጅጉ መወገዝ ይገባዋል:: ኬኔት ካምፕቤል (2001፣ 2) እንደሚለው ዛሬም ቢሆን ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የዘር ማጥፋት ፍጅት ችግርን ለመፍታት እምብዛም ከቀድሞው የተሻለ ፖለቲካዊም ሆነ ድርጅታዊ መሰናዶና ቁርጠኝነት የለውም::

የኢትዮጵያ ሁኔታ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተደጋግሞ የሚነገር

28

አንድ ነገር አለ:: “የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖተኛና ፈሪሐእግዚአብሔር ያለው ሕዝብ ነው፤ ለብዙ መቶ ዓመታት በክፉም በደጉም አብሮ ያሳለፈ፣ የተዋለደና የተዋሐደ ሕዝብ ነው፤ አንዱ ሌላውን ሊያጠቃ አይችልም፤” ወዘተ. ይባላል:: የሚቀርቡት አስተያየቶችም ከሞላ ጎደል ትክክል ናቸው:: ይኹን እንጂ ማናችንም ብንሆን ልንዘነጋው የማንችለው፣ ባለፉት 50 ዓመታት በዚህች አገር ሲቀነቀን የኖረው የልዩነት ፖለቲካ፣ በተለይም ሕወሓት/ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ያለው ከኅብረትና አንድነት ይልቅ ልዩነት ሲሰበክበት የኖረው አጀንዳ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል:: ሕወሓት የዘረጋው በዘውግ ላይ የተመሠረተ ፌደራላዊ ሥርዓት፣ ይልቁንም ሥልጣኑን ለመስጠበቅ ሲል አንዱን ብሔረሰብ ደግፎ በሌላው ላይ ሲዘምት የቆየበት የጥፋት አካሄድና የዘራው መርዝ እንዲህ በቀላሉ ፈውስ የሚያገኝ አይደለም:: ብዙ ጥረትና መስዋዕትነት ይጠይቃል:: ሕወሓት “የአማራ ገዥ መደብ” በሚል ጭምብል በጠላትነት የፈረጀው የአማራ ሕዝብ ላለፉት 28 ዓመታት በአገሩ እንደባይተዋር ተቆጥሮ ከያለበት ሲፈናቀልና ሲሳደድ መቆየቱ የሚታወቅ ነው:: ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲደርስ የኖረ መከራ በለጋ ዕድሜው መፍትሔ ስላልተሰጠው፣ አሁን ሁሉንም ብሔረሰቦች መለብለብ ጀምሯል:: ጃክ ስናይደር፣ የየአካባቢው ፖለቲከኞች በሚያቀነባብሩት ግጭት … አካባቢያችንን ለቃችሁ ውጡልን … በ2009 ዓ.ም ታኅሣሥ ወር የጀመረውና በ2009 ዓ.ም. ነሐሴ ወር በድጋሚ ያገረሸው በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የጠከሰተው ሰፊ ግጭት የበርካታ ንጹሐን ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር:: ግጭቱ የተቀሰቀሰው በኹለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ቢሆንም በፍጥነት ተስፋፍቶ ሰላማዊ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል ቤት ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉና በርካቶችም ለከፋ ጉዳት እንዲጋለጡ ሆኗል:: የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ኢትዮጵያንም አወዳይ ከተማ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገሉ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸውም ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለዋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተረከቡ በኋላ፣ ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሶማሌ ክልል አቅንተው ነበር:: በዕለቱ ከኅብረተሰቡ ለተወጣጡ የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ፣ ከኹለቱም ክልሎች በርካታ ዜጎች ለሕልፈት የተዳረጉበትነ፣ በርካቶች ለአካል ጉዳት የተጋለጡበትንና ከ700 ሺሕ በላይ ዜጎች የተፈናቀሉበትን በዕርቀ ሰላም እንዲቋጭ ጥሪ አቅርበው ነበር:: “ይልተገባ፣ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠና የሁላችንንም አንገት ያስደፋ የሽንፈት ታሪካችን ነው፤” ነበር ያሉት:: ሆኖም ግጭቱ በዚያ አካባቢ ብቻ ሳይወሰን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች አሁንም እንደቀጠለ ነው:: ለዘር ፍጅት የሚጋብዙ የጥላቻ ቅስቀሳዎችም ተጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው:: አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ዘውግ የለየ ጥቃት በአገራችን እየተለመደ መጥቷል!

ምን ይሻላል?

የዘር ጥቃት ጉዳይ ተመራማሪዎች ከላይ በዘረዘርናቸው ባሕርያቱ ላይ የተመረኮዙ የአጭር ጊዜና ዘላቂ መፍትሔዎችን ይሰነዝራሉ:: ይህም የችግሩ ምንጭም ሆነ የመፍትሔው ኀይል ውስጣዊ መሆኑን ከመገንዘብ ይጀምራል:: ሰፊ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳዮችን እንደሚያቅፍ መረዳት ያሻል:: እንደ ስስት፣ ፍርሃት፣ ምኞት፣ ጥላቻ፣ ስህተት የመሳሰሉ ሰብአዊ ባሕርያት ለብዝበዛ የተጋለጡ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል:: ግጭቶች ከትናንሽ አካባቢያዊ ክስተትነት ወደ ሙሉ አቅም የጥፋት ዘመቻነት የሚያደርጉትን ሽግግርም በቅጡ መገንዘብ ይገባል:: የዘር ጥቃትን የመከላከሉ አንዱና ቀዳሚው መንገድ ባለሙያዎች “የዘር ማጥፋት ሰንሰለት” (genocide continuum) የሚሉት ሲሆን፣ ይህም ተራና ጤናማ በሚመስሉ ባሕርያትና ተቋማት የሚንጸባረቁ ታዳጊ በደሎችን ይመለከታል:: በትምህርት ሥርዓትና በመገናኛ ብዙሃን የሚራገቡ ግልጽና ረቂቅ ቅስቀሳዎች፣ በፍትሕና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ በሌሎችም መንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት የሚፈፀሙ ክብረ ነክ አስተምህሮዎችና ድርጊቶች የጥፋት መንስኤዎች መሆናቸውን መረዳት፣ እነዚህን ዝንባሌዎች በመለየት የሚያስተሳስራቸውን ሐረግ ለማወቅና ሕዝብንም ለማስተማር ነቅቶ መጠበቅ ያሻል:: የሕዝብ ቁርሾንና ጥላቻን፣ ከዚያም አልፎ መጠፋፋትን ለማስቀረት ጠንካራ ሥርዓት ማበጀት ያስፈልጋል:: በተለይም ከፋፋይ የማንነት ፖለቲካን በእውነተኛና የተረጋጋ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መተካት አማራጭ የማይገኝለት መፍትሔ ነው:: የፖለቲካ ከባቢውን ማስፋት ለዘብተኞችና ሠላማዊ ፖለቲከኞች በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ ከዝነኛ/ጉልበተኛ መሪዎች የአደገኝነት ዝንባሌ ለመጠንቀቅ፣ አክራሪ ፖለቲከኞችና የጥቅም ስብስቦች በተቻለ መጠን ወደ ሥልጣን እንዳይወጡ ለመከላከል ወዘተ... ይረዳል:: የብሔረሰብ ታሪከኞች እንደሚሉት በአገራችን የሚታዩት ትናንሽ ማኅበራዊ ግጭቶች የማይታረቅ “ታሪካዊ ጠላትነት” ውጤቶች ሳይሆኑ፣ ነባራዊ ምክንያቶች ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን ማስጨበጥ፣ ገንቢ መፍትሔዎችንም ማቅረብ ያሻል:: ማኅበረሰቦች የጋራ ሠላም ለምርጫ የሚያቀርቡት ሳይሆን የህልውናቸው መሠረት መሆኑን ማስገንዘብ፣ ችግሮቻቸውን በጋራ የሚፈቱበትን መንገዶች ማዳበር፣ የጭካኔን ኢሰብአዊ ገጽታዎች ማሳየት፣ ንጹሐን ዜጎች በጥላቻ ቸርቻሪዎች ለጥፋት እንዳይጋበዙ ማንቃት ያስፈልጋል:: በዚህም አለ በዚያ፣ ዘር ማጥፋት የዜሮ ድምር ርዕዮት፣ ለቆስቋሾቹም አትራፊ ሳይሆን የራስ ተሸናፊነት ስልት ነው:: ስለዚህም ሽብር ፈጣሪዎችና የአርማጌዶን ናፋቂዎች በፍትሕ፣ በዴሞክራሲና በነጻነት ስም የሚያደሩትን የብጥብጥ ድር ነቅቶ መጠባበቅ፣ በምሁራዊ ምርምር ሽፋን የሚያሰራጩትን የፈጠራ ታሪካቸውን እየተከታተሉ እጅ በጅ ማፍረስ የእያንዳንዱ ቅን አሳቢ ዜጋ ግዴታ ነው:: ዛሬም፣ ነገም፣ ከነገ ወዲያም ደጋግሞ መጮህ፣ ሳይታክቱና ተስፋ ሳይቆርጡ መጮህ ይገባል!!!

የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ፈተናዎች አንዳንድ ነጥቦች ሄኖክ አክሊሉ

በ1987 ዓ.ም. የፀደቀው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ቀደም ሲል የነበረው አሐዳዊ የመንግሥት ሥርዓት ተቀይሮ በማንነት ላይ የተመሠረተ ፌዴራላዊ ሥርዓት መመሥረቱን ተከትሎ የፍትሕ ተቃማቱም በፌዴራል እና በክልል ደረጃ ተዋቅራል። የፍትሕ ሥርዓት ሲባል ፍርድ ቤቶችን፣ ዐቃቤ ሕግን፣ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤቶችን፣ ጠበቆችን፣ የሕግ ትምህርት ቤቶችን፣ የሕግ ምርምርና ተያያዥ ተቋማትን የሚያካትት ሲሆን፣ ተቋማቱ የሚመሩበትን የአሠራር ሥርዓት ያጠቃልላል። የፍትሕ ሥርዓት የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማስከበር፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን በመደገፍ የማይተካ ሚና እንዳለው ይታመናል። በሕገ መንግሥቱ ላይ የፍትሕ ሥርዓቱን አስመልክቶ በርካታ ተስፋ ሰጪ ድንጋጌዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ድንጋጌዎቹን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የታዩ አንዳንድ ችግሮችን በመዳሰስ ለውይይት መነሻ የሆኑ ሐሳቦችን ማቅርብ የዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ዓላማ ነው።

በሕገ መንግሥቱ የተገቡ የፍትሕ ሥርዓት ተስፋዎች የፍትሕ ሥርዓት ዋነኛ ዓላማ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ መሆኑ ይታመናል። የሕግ የበላይነት አገሪቱ የቆመችበት መሠረታዊ መርሆ እንደሆነም የሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ በግልጽ ተመልክቷል። በፍትሕ ሥርዓት ላይ ትልቅ ሚና አላቸው ከሚባሉ ተቋማት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀዳሚው ነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ለመገንዘብ እንደሚቻለው ነጻ ፍርድ ቤት የተቋቋመ ሲሆን፣ ዳኞችም የዳኝነት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ከማንኛውም አካል ተጽዕኖ ነጻ ሆነው የመሥራት መብታቸው የተጠበቀ እንደሆነ ተደንግጓል። የዜጎች እና ሕዝቦች መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ሕገ መንግሥቱ ላይ አንድ ሰፊ ምዕራፍ ተሰጥቷቸው በዝርዝር ሰፍረው ይገኛሉ። ድንጋጌዎቹ ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም ዐቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ጋር በተጣጣመ መልኩ

መተርጎም እንዳለባቸው ተመልክቷል። በሌላ በኩል በፍርድ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን ዜጎች ለፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብት እንዳላቸው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ላይ ተደንግጓል።

አብዮታዊ ዴሞክራሲ እና የፍትሕ ሥርዓት አንድ የፖለቲካ ሥርዓት የሚቀርጻቸው ፖሊሲዎችም ሆነ የሚፈጥራቸው ተቋማት በአብዛኛው ፈጣሪው ባለው አመለካከት፣ ባዳበረው ባሕሉና የኋላ ታሪኩ ላይ የሚመሠረቱ ናቸው። ሆኖም ወቅታዊ እና ዓለም ዐቀፋዊ ግፊቶች የሚያሳርፉትም ተጽዕኖ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ያምንበት የነበረው ማርክሲስት-ሌኒንስት ርዕዮተ-ዓለም እና ድርጅታዊ አሠራሩን ይመራበት የነበረው የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርሕ ከግንቦት በኋላ ለፈጠረው ፖለቲካዊ ሥርዓት መሠረት እንደሆነ ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ “Ethiopia: Beleagured Opposition under a Dominant Party System” በሚለው ጥናታዊ ጽሑፋቸው ላይ ይገልጻሉ። የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ አክለውም ይህ አስተሳሰቡ እና ባህሉ የጠቅልል (dominant) ዓይነት ባሕርይዎችን በመንግሥትነት ዘመኑ እንዲከተል እንዳደረገው ያስረዳሉ። ሆኖም የቀድሞ ሶቭየት ኅብረት መፈራረስን ተከትሎ የምሥራቁ ጎራ ሲመሽበት ብዙ የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ሳሙኤል ሃንቲንግተን “ሦስተኛው የዴሞክራሲ ማዕበል” ሲሉ በጠሩት እንቅስቃሴ የሊብራል ዴሞክራሲን እና ተቋማት የመቀበል ጫና ውስጥ ገብተዋል። ኢሕአዴግም በከባድ የምዕራባዊያን ጫና አማካኝነት በርካታ የሊብራል ዴሞክራሲ መርሆች ያካተተ ሕገ መንግሥት እና የመንግሥት አወቃቀር እንዲመሠርት ተገዷል። ሕወሓት/ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግል ጊዜ የነበረውን የግንባር-ቀደምነት (የቫንጋርድነት) ባሕርይ በመንግሥትነቱ ጊዜም በመከተል በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ ሕጋዊ ድንጋጌዎች ቢኖሩም ሁሉንም የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት በሙሉ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ለማድረግ በሰፊው ተግቷል።

በሕገ መንግሥቱ ተቋማዊና ግላዊ ነጻነት ያለው ፍርድ ቤትን አቋቁሟል። ነገር ግን የፍትሕ ሥርዓቱ ሕገ መንግሥታዊ የሆነ ነጻነት ቢኖረውም የፖለቲካው ሲስተም ከሚዘወርበት ተጽዕኖ ውጪ ሆኖ ሊኖር እንደማይችል እና ይኼም ቀድሞ በአገሪቱ በነበሩ ሥርዓቶች የቆየውን አካሄድ ተከትሎ ቀጥሏል። ይህን ሐሳብ የሚያጠነክሩት ዶ/ር አሰፋ ፍስሐ “Constitutional Adjudication in Ethiopia” በሚል ርእስ ባዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፋቸው የፍትሕ ሥርዓቱ በኢትዮጵያ እራሱን የቻለ ነጻነት ኖሮት እንደማያውቅ እና ፈጣሪዎቹ የሆኑት ሥርዓት ሞትን ተከትሎ ይፈራርስ እንደነበር አስቀምጠዋል። አገዛዙ አሁንም ድረስ የሚከተለው የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብም የመንግሥት እና ፓርቲን ውሕደት የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ የጠቅልልነት ባሕርይውን ለማራመድ የሚያስችሉ እንደሆነ የሚነግሩን አቶ አደም አበበ “Rule by Law in Ethiopia” በሚለው ጽሑፋቸው ፓርቲው የፍትሕ ሥርዓቱን የራሱን ጥቅሞች ለማራመድ በዓይነተኝነት እንደሚጠቀምበት አስገንዝበዋል። በእንደዚህ ዓይነት የጠቅልል ሥርዓት ውስጥ የፍትሕ ተቋማት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ስላላቸው የይምሰል ነጻነታቸውን ጠብቀው መቆየታቸው ይፈለጋል። ሥርዓቱን ሕጋዊነት እና ተቀባይነት ማሰጠትን ከማስቻላቸውም በላይ የውስጥ እና የውጭ ተቀናቃኞችን ዝም ለማስባል ትልቅ አገልግሎት ይሰጣሉ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ከተቋማቱ ባሕርይ በመነጨ ለሕልውናው አደጋን ሊፈጥሩ የሚችሉ በመሆኑ ትልቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው። የፍትሕ ሥርዓቱን የባለፉት 28 ዓመታት ጉዞ መለስ ብለን ከተቋማቱ በሕገ መንግሥቱ ከተደነገገው ነጻነታቸው አንጻር ስናይም አንድ ወጥነት ያለው አካሄድ አይታይም። ከግንቦት 1983 እስከ ሕገ መንግሥቱ መፅደቅ ድረስ ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ወቅት ትተን እስከ 1997 ድረስ የነበረውን ሁኔታ ስንቃኝ ተቋማቱ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አንጻራዊ ነጻነት አግኝተው የቆዩበት ጊዜ ነበር።

29

በእርግጥ በእነዚህ ጊዜያትም ቢሆን ድርጅቱ ከባድ ውስጣዊ የፖለቲካ መተጋገል የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በገጠመው ጊዜ ሕገ መንግሥቱን በጣሰ መልኩ “የስዬ ሕግ” እየተባለ የሚጠራውን የፀረ-ሙስና አዋጅ በሩጫ በማውጣት ለመጠቀሚያነት ያዋለበት አንድ ማሳያ ነው። እስከ 1997 ዓ.ም. ድረስ የቆየው አንጻራዊ ነጻነት ግን በዚሁ ዓመት የደረሰበትን የምርጫ ሽንፈት እና የተፈጠረውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ ድርጅቱ በከፍተኛ ደረጃ የነጻነትን ምኅዳር የሚያጠቡ እርምጃዎችን የመውሰድ ተግባር ውስጥ ተዘፍቋል። የፍትሕ ሥርዓቱም የዚህ ሰለባ ከመሆን አልዳነም::

አንድ ክፍል ተዋቅሮ የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመባል ራሱን ችሎ ከተዋቀረ ገና ሦስት ዓመቱ ነው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ለብቻ ማቋቋም ያስፈለገበት አንዱ ምክንያት ተቋማዊ ነጻነት እንዲኖረው ለማስቻል መሆኑን ከማቋቋምያ አዋጁ መግቢያ ላይ ለመረዳት ይቻላል። ይኹን እንጂ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ፣ የፖለቲካና የሙያ ሥራዎች ሳይለዩ በአንድ ላይ ተጠቃለው የተሰጡት ከመሆኑ አንጻር የሙያ ሥራው በተለይም ምርመራን የማስጀመር፣ የመምራትና የማቋረጥ ተግባሩ የማከናወን ሒደት በፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር ሊወድቅ እንደሚችልና ሙያዊ ነጻነቱ ፈተና እንደሚገጥመው የዘርፉ ባለሙያዎች ከወዲሁ ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ፈተናዎች የሕግ የበላይነት የሚባለው ጽንሰ-ሐሳብ ሰፋ ያለ ትርጉም እና በርካታ መገለጫዎች አሉት። በዋነኛነት ግን ዜጎች ልዩነት ሳይደረግባቸው በሕግ ፊት ዕኩል ሆነው መታየታቸውንና ሕግ ጥሰውም ሲገኙም ያለ ልዩነት ተጠያቂ የሚሆኑበት ሕገ መንግሥታዊ መርሕ ነው። የሕግ የበላይነት መርሕ በዓለም ዐቀፍ ድንጋጌዎች በግልጽ ሰፍሮ የሚገኝ ሲሆን በብዙ አገሮችም ተቀባይነትን ካገኘ ቆይቷል። ሕግን እንደ አገዛዝ መሣሪያ በሚጠቀሙና ሰብአዊ መብትን ባለማክበር የሚታሙ አገዛዞች ሥልጣን ይዘው በሚገኙበት አገሮች ጭምር በሕገ መንግሥታቸው አካተውታል። ሆኖም በተግባር ሲታይ ግን ለሕግ የበላይነት ተገዥ ለመሆን ቁርጠኝነት የሌላቸው፤ የፍትሕ ሥርዓቱም ባለሥልጣናቱን ለፍርድ ማቅረብ ሲሳነው ይስተዋላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩትም እነዚህ መንግሥታት ዜጎችን በሕግ ለመግዛት እንጂ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ፈቃደኝነት የላቸውም። በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝቷል። የሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ “…በሕግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት፤” ይላል። ይህም የሕግ የበላይነት ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅናን ከማግኘት ባለፈ መሠረታዊ መርሆ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ከሕገ መንግሥቱ በኋላ የወጡ ርዕዮተ-ዓለማዊ እና የፖሊሲ ሰነዶች ላይም ይህንኑ ከመግለጽ ተቆጥቦ አያውቅም። ለሕግ የበላይነት መከበር ፓርላማ፣ ፍርድ ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ፖሊስ፣ ጠበቆች... እንዲሁም ነጻ ሚዲያና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጎላ ሚና አላቸው። የሕግ የበላይነት መርሆው ሕገ መንግሥቱ ላይ መስፈሩ መልካም ነገር ሆኖ በተጨባጭ መሬት ላይ ወርዶ እንዲተገበር ከተፈለገ ግን ተቋማቱ ነጻና ጠንካራ ሊሆኑ፣ አገዛዙም ለተግባራዊነቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ሊኖረው ያስፈልጋል። በተለይም ከባባድ ባለሥልጣናትና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሕግ ጥሰው ሲገኙ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠያቂ የሚሆኑበትን ሥርዓት መዘርጋትን ይጠይቃል። የሕግ የበላይነት በተሻለ ሁኔታ በተረጋገጠባቸው አገሮች ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል ካደረጃጀት ጀምሮ ሰፋ ያለ ተቋማዊና ሙያዊ ነጻነት ተላብሰዋል። በተለይም ከፖለቲካ ተቋማት አላስፈላጊ ተጽዕኖ ነጻ ሆነው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አስፈላጊው ከለላ ይደረግላቸዋል:: በአገራችን ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ዐቃቤ ሕግ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር እንደ

30

እንደሚታወቀው ዋና ኦዲተር ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የመንግሥት የገንዘብ አያያዝ፣ ግዥ አፈጻጸም... ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጉድለትና ብክነት የተገኘ መሆኑን አሳውቋል። በሌላ በኩል በዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ላይ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው የስኳር ማምረቻ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የተጓተተና ለገንዘብ ጉድለትና ምዝበራ በሚያጋልጡ አሠራሮች የተተበተበ መሆኑን መንግሥት በቅርቡ ይፋ ካደረጋቸው መረጃዎች ለመገንዘብ ይቻላል። የሕግ የበላይነት በዳበረባቸው አገሮች ቢሆን ተመሳሳይ ሁኔታ ሲከሰት በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂውን አካል ለፍረድ በማቅረብ ሕዝብም እንዲያውቀው ይደረጋል። በእኛ አገር ግን ይኼ ለመከናወኑ እስካሁን ለሕዝብ ይፋ የሆነ ነገር የለም። ይኽም ከላይ ላነሳነው ነጥብ እንደ አንድ ማሳያ ሊወሰድ የሚችል ነው።

ሥልጣኑና ነጻነቱ እየጠበበ የመጣው ፍርድ ቤት

ሕወሓት/ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግል ጊዜ የነበረውን የግንባርቀደምነት (የቫንጋርድነት) ባሕርይ በመንግሥትነቱ ጊዜም በመከተል በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ ሕጋዊ ድንጋጌዎች ቢኖሩም ሁሉንም የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት በሙሉ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ለማድረግ በሰፊው ተግቷል

ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ባለጉዳዮች የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች የመዳኘት ሥልጣን ያላቸው ሲሆን ሰብአዊ መብትን እና የሕግ የበላይነትን ከማስከበር አንጻር ትልቅ ሚና እንዳላቸው ይታመናል። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነጻ ፍርድ ቤት መቋቋሙ እና ዳኞችም ከሙያቸው ጋር በተያያዘ ከማንኛውም ሦስተኛ አካል ተጽዕኖ ነጻ መሆናቸው ተመልክቷል። የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ወሰን በተመለከተ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ሥልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተሰጥቷል። ይህ ከመነሻው አንስቶ ሰፋ ያለ ክርክር ሲካሄድበት የቆየ ጉዳይ ነው። በመግቢያችን ላይ እንዳመለከትነው የጽሑፉ ዋና ዓላማ በሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈሩና ከፍትሕ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ መርሆዎች በአተገባበር ረገድ የገጠማቸውን አንዳንድ ፈተናዎች ማሳየት ላይ የተገደበ በመሆኑ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ለፌደሬሽን ምክር ቤት የመሰጠቱ አግባብነት ላይ በዝርዝር የምንለው አይኖርም። ነገር ግን ከመነሻው ፍርድ ቤት የተሰጠው ሥልጣን የጠበበ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዳኝነት ሥልጣን በመርሕ ደረጃ ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ የተሰጠ መሆኑን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79 (1) ደንግጓል። ይሁን እንጂ የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን በብዙ መልኩ የሚሸረሽሩ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል። በቅድሚያ ከላይ እንደተገለጸው በሕገ መንግሥቱ ላይ ሕገ መንግሥትን መተርጎም የፍርድ

ቤት ሳይሆን የፌዴራል መንግሥቱ መሥራች የሆኑ ክልሎች የሚገኙበት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኳቸው አባላት የሚወከሉበት ፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። የተቀሩት የዳኝነት ሥልጣኖች በመርሕ ደረጃ ለፍርድ ቤት የተሰጡ ቢሆንም ለሌሎች አካላት በሕግ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78 (4) ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። ድንጋጌውን በጥልቀት ስንመለከተውም በሕግ የተደነገገውን የዳኝነት ሥርዓት የማይከተሉ ሌሎች የዳኝነት ተቋማት ማቋቋም እንደማይቻል ተመልክታል። ይህም የሆነው የዳኝነት ሥራ ፍትሕ ከማስፈን ጋር የተያያዘ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ዕኩልነትን መሠረት ባደረገ ለምሳሌ እያንዳንዱ ተከራካሪ ክርክሩን በአግባቡ እንዲያቀርብ፣ በሌላው ተከራካሪ የቀረበበት ክርክርና ማስረጀ ደርሶት ራሱን እንዲከላከል ዕድል መስጠት መሠረታዊው የፍትሕ አሰጣጥ ሒደት በመሆኑ ነው። ስለዚህም ልዩ ፍርድ ቤቶች ሲቋቋሙ የዜጎችን እነዚህን መሠረታዊ መብቶች የማይጥሱ መሆኑን ማረጋገጥ ከባድ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ። በአገራችን በሕግ አውጪው አካል የተቋቋሙ ከፊል የዳኝነት ሥልጣን (quasi judicial power) ያላቸው አካላት ገቢዎች ሚኒስቴር፣ የቦታ ማስለቀቅ፣ የሸማቾች ማኅበራት፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ አሠሪና ሠራተኛ ቦርድ፣ ማኅበራዊ ዋስትናን... ይጨምራል። እነዚህ ከፊል የዳኝነት ሥልጣን የተሰጣቸው አካላትን በተመለከተ ብዙ አከራካሪ ጉዳዮች ቢኖሩም የከተማ ቦታ የሊዝ ቦርድ የተቋቋመበትን ሁኔታና ከሚመራበት ሥርዓት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ነጥቦችን እንመልከት። የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ተቋቁሟል። ጉባኤው አግባብ ያለው የመንግሥት አካል ይዞታውን እንዲለቅ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሰው የሚያቀርበውን ቅሬታ በይግባኝ የማየት የዳኝነት ሥልጣን ተሰጥቶታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣም አከራካሪው ጉባኤው “በመደበኛው የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ አይመራም” ብሎ ራሱ አስፈጻሚው በሚያወጣው “የተቀላጠፈ” ሥርዓት ይመራል ሲል ያልተገደበ የሥነ-ሥርዓት አካሄድ መፍቀዱና ይኽም በሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ አለመሟላቱን የሚያመላክተው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ጉባኤው በአንቀጽ 29 (3) ላይ ቦታውን (መሬቱን) እንዲለቅ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ተነሽ “በካሳ ክርክር ላይ ካልሆነ በስተቀር ምትክ ቦታን ጨምሮ በሌሎች በሕግም ሆነ በፍሬ ነገር ክርክሮች ላይ ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል” በማለት ጉዳዩ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንዳይሄድ ያስቀመጠው ክልከላ ነው። ይህ አዋጅ በኢትዮጵያውያን ማንነት ውስጥ እጅግ ትልቅ ስፍራ ስላለው የመሬት ጉዳይና በሕገ መንግሥቱ ዋስትና ስላገኘው የንብረት መብት በመሆኑ ልማትን ለማፋጠን ተብሎ ብቻ ቸል ሊባል እንደማይገባውና ትልቅ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ ብዙዎች ያስገነዝባሉ። የዚህ ሕግ ሰለባ ሆንን የሚሉ ወገኖች ጩኸትም በየቀኑ በመገናኛ ብዙሃን መስማት የተለመደ ሆኗል። ፍርድ

ቤቶች

በተለያዩ

ሌሎች

አካላት

ሥልጣናቸውን መነጠቃቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እራሳቸው ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ባላቸው ፍርዶች በሚሰጠው ውሳኔ (አዋጅ ቁጥር 454/1997 ላይ የተደነገገ) ሕገ መንግሥታዊ እና ተፈጥሯዊ (inherent) የሆነውን የዳኝነት ሥልጣናቸውን በርካታ ጊዜ በራሳቸው ፈቃድ አሳልፈው ሲሰጡም ተስተውሏል። እነዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ናቸው በማለት ግልጽ ድንጋጌ በሌለበት እና በጠበበ ሁኔታ መተርጎም ያለባቸውን ልዩ ሁኔታዎች በፍርድ ሊዳኙ የሚችሉት አይደሉም በሚል የሚሰጣቸው ውሳኔዎች ፍርድ ቤት ሥልጣኑን በራሱ ውሳኔ እያጠበበ የመጣ መሆኑን ብዙ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ሲሆን፣ “A Judicial Branch Growing to a Legislative Oligarchy” የሚል አንድ ጥናት ይህንኑ በማንሳት ይከራከራል።

በጉዳዩ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀደም ባሉት ጊዜያት በአብዛኛው አገሮች (ኢትዮጵያን ጨምሮ) አንድ ሰው ወይም ተቋም በአንድ ጉዳይ ላይ መብት ወይም ጥቅም ሳይኖረው ክስ ማቅረብ አይችልም። የሕዝብ አጠቃላይ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ ክስ ማቅረብ የሚችለው ዐቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ግለሰቦችና ሌሎች አካላት ክስ የማቅረብ ዕድል ጭራሹኑ የላቸውም ወይም በእጅጉ የተገደበ ነው። በሒደት ግን አገራት በሕዝብ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችንና በደሎችን ማንኛውም ሰው ወይም አካል በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ጥቅም ባይኖረውም እንኳን ለፍርድ አቅርበው ለተጎጂዎች ፍትሕ ማስገኘት እንዲችሉ በመፍቀድ የሕግ ማዕቀፍ አበጅተዋል። በዚህ ረገድ የሕንድና ደቡብ አፍሪካ ተሞክሮ ለእኛም አገር በአርኣያነት ሊወሰድ የሚችል ነው።

ፍርድ ቤቶች ባለፉት ዓመታት ያላቸው የዳኝነት ሥልጣን በተለያየ መንገድ መሸርሸሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የፍርድ ቤቶች ነጻነት መገለጫ አንዱ የራሳቸውን በጀት ማስተዳደር መቻላቸው ነው። ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79(6) “የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል፤” ቢልም በተግባር ግን የፍርድ ቤቶች በጀት በአስፈጻሚው አካል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በመገኘቱ የዳኞችን ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና በአጠቃላይ የፍርድ ቤቶቹን ዕቅድ በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የአስፈጻሚውን አካል በጎ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ሆኖበታል።

በሕንድ በነባሩ ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሠረት አንድ ሰው ክስ ለማቅረብ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ጥቅም ሊኖረው ይገባ ነበር። ሆኖም በ1979 የአገሪቱ ፍርድ ቤቶች ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ነባሩን የሥነ-ሥርዓት ሕግ በማሻሻል በጉዳዩ ላይ አዲስ አቅጣጫ እንዲቀይሱ ያስቻላቸው አጋጣሚ ተፈጠረ። ይኸውም የሕንድ ጋዜጦች “ባሂር” በተባለች ግዛት ለፍትሕ አካላት ሳይቀርቡ ቢፈረድባቸው እንኳን ሊቀጡት ከሚገባ ጊዜ በላይ በእስር ሲማቅቁና በደል ሲደርሰባቸው የነበሩ ግለሰቦችን አስመልክቶ ዘገባ ያቀርባሉ። በዚህ መነሻነት ከነባሩ የክስ አቀራረብ ሒደት ባፈነገጠ ሁኔታ አንዲት ጠበቃ ለግዛቱ ፍርድ ቤት ክስ ያቀርባሉ። ክሱም ተቀባይነትን አግኝቶ በጠቅላላ አገሪቱ ውስጥ ያሉ በሺሕ የሚቆጠሩ እስረኞች የተፈቱ ሲሆን ቀጥተኛ ጥቅም ባይኖረውም እንኳን አንድ ሰው ወይም ተቋም በሕዝብ አጠቃላይ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ የሕግ ጥሰቶችን ለፍርድ በማቅረብ ፍትሕ እንዲያገኙ የማድረግ መብት እንዲኖረው ተደርጓል።

የዳኞች አመላመል እና አሿሿም በተመለከተም ነጻነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ እስካሁን ወጥነት በሌለው አሠራር የሚካሄድ መሆኑን እራሱ መንግሥት እ.አ.አ. በ2005 ያስጠናው “የተቀናጀ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም” ሪፖርትና ሌሎችም ጥናቶች ያሳያሉ። በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ተጠፍሮ የቆየው ፍርድ ቤት የነቃ ተሳትፎ (Judicial Activism) በማድረግ የሕግ የበላይነትና የዜጎችን መብት የማስከበር አቅሙ በእጅጉ የተገደበ ነው:: ያልሞከርነው ለሕዝብ አጠቃላይ ጥቅም ተሟጋችነት (Public Interest Litigation) ሥርዓት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ላይ እንደተመለከተው ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብት አለው። ዜጎች በሕገ መንግሥቱም ሆነ በሌሎች ሕጎች የተጠበቁላቸው መብቶች ሲጣሱባቸው፣ የጣሰውን ሰው ወይም ተቋም ከሰው ወይም እንዲከሰሱ በማድረግ መብታቸውን ማስከበር ካልቻሉ መብቶቹ ዋጋ አልባ እንደሚሆኑ ይታወቃል። አሁን የምንመለከተው ግን ከሕዝብ ወይም ከተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል አጠቃላይ መብትና ጥቅም ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ጥቅም ወይም መብት የሌለው ሰው ወይም ተቋም ጉዳዩን ወደ ፍትሕ አደባባይ በማቅረብ የኅብረተሰቡን ጥቅም ለማስከበር መብት ያለው መሆን አለመሆኑንና ይህም በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የሚኖረውን እንድምታ በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት ነው::

ከዚህም በላይ ሥርዓቱ የበለጠ እየተለመደና እየዳበረ ሲመጣ የክስ አቀራረብ ሒደቱ ከመደበኛው ሥርዓት ቀለል እንዲል አድርገዋል። በዚሁ መሠረት ክሱን በፖስታ ለመመሥረት እስከሚቻልበት ደረጃ ተደርሷል። በርካታ የመብት ጥሰቶችም ለፍርድ ቀርበው መፍትሔ አግኝተዋል። በደቡብ አፍሪካም ይህ ሥርዓት ከተለመደ የቆየ ሲሆን በአፓርታይድ ሥርዓት ነጮች በጥቁሮች ላይ የሚያደርሱትን መድልዎና የመብት ጥሰት በፍርድ አደባባይ ለመታገል ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደነበረውና በአሁኑ ወቅትም በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ሙያቸውንና ተቋማዊ አቅማቸውን በመጠቀም አጠቃላይ የመብት ጥሰቶችን በፍርድ አደባባይ ለመሞገት ዕድል አግኝተዋል። ሥርዓቱ አቅምም ሆነ ዕውቀቱ የሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እገዛ ማድረጉ፣ የሕዝቦች መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞች ላይ ጥሰት የፈፀሙ የመንግሥት ተቋማትና ባለሥልጣናትን በፍርድ አደባባይ በመገተር ተጠያቂነት እንዲሰፍንና ሙስናን በማገዙ፣ በሒደቱም ዜጎች ስለመብታቸው በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙና በፍትሕ ስርዓቱ ላይ እንዲተማመኑ መርዳቱ፣ በጥቅሉ ለሕግ የበላይነት መረጋገጥና የመብቶች መከበር ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑ ይታመናል። በዚህም የተነሳ ሥርዓቱ

31

በተለያዩ አገሮች ተቀባይነት እያገኘና ምቹ የሕግ ማዕቀፍ ተበጅቶለት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኙ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።

ክስ ለማቅረብ ልዩ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው ተመልክቷል። እነዚህ ድንጋጌዎችን በጥሞና ስንመለከት ምንም እንኳን ከነባሩ ሥርዓት አንጻር ሲታይ የሕዝብን ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጉዳዩ የማይመለከተው ሰው ወይም ተቋም ክስ ለመቅረብ የሚችልባቸው የተወሰኑ ዕድሎች ቢኖሩም በጥቅሉ ሲታይ ግን በኢትዮጵያ ለሕዝብ ጥቅም ሙግት የማቅረብ መብት ተረጋግጧል ለማለት አይቻልም።

በኢትዮጵያ (በሌሎች አገሮችም ሆነ) ዐቃቤ ሕግ መደበኛ ተግባሩ የሆነውን የወንጀል ክስ ማቅረብና የወንጀል ምርመራን ከመምራት ባሻገር በአጠቃላይ የአገሪቱ ሕጎች መከበራቸውን መቆጣጠር፣ እንዲሁም ከሕዝብ ጥቅም ጋር የተያያዙ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ ክስ የማቅረብ ሰፊ ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን ከማቋቋሚያ አዋጁና ከፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል። ቀደም ሲል እንደተመለከተው በአገራችን ዐቃቤ ሕግ ከአወቃቀሩም ሆነ ከተግባሩ አኳያ ሲታይ ከአስፈጻሚው አካል ተጽዕኖ ነጻ ነው ለማለት እንደማስደፍር በጉዳዩ ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ። በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ በተለይም ጠንካራ በሆኑ የመንግሥት ተቋማትና ባለሥልጣናት አማካኝነት በሕዝብ ጥቅም ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ተከታትሎ ለሕግ ላያቀርብ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው። በሌላ በኩል ካለንበት ዕድገትና ሥልጣኔ ደረጃ የመብት ጥሰት የሚፈፀመባቸው አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለ መብታቸው በቂ ግንዛበ የሌላቸው የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው። ግንዛቤው ቢኖራቸውም መብቶቻቸውን ለማስከበር አቅሙም ሆነ ድፍረቱ ላይኖራቸው እንደሚችል ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። ደረጃው ይለያይ እንጂ በየትኛውም አገር ቢሆን ኅዳጣን የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች (minorities)፣ ድሆች፣ አካል ጉዳተኞች... አጠቃላይ መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን በፍትሕ አደባባይ አቅርበው ለማስከበር ሲቸገሩ ይስተዋላል። ይህም ከላይ የተጠቀሰው ተሞክሮ ለአገራችን በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል። በሥራ ላይ ያለው የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት አንድ ሰው ወይም አካል ክስ ለማቅረብ በቅድሚያ በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለበት በአንቀጽ 33 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል። በአንጻሩ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ላይ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚችል ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል አቅርቦ ፍትሕ የማግኘት መብቱ ተከብሮለታል። ይህ ድንጋጌ እንደ ፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ክስ አቅራቢው ሰው ክስ በሚያቀርብበት ጉዳይ ላይ የግድ ጥቅም ሊኖረው የሚገባ ለመሆኑ በግልጽ የሚያስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ የለም። እንዲሁም ለሕዝብ ጥቅም የሚደረግ ሙግት (Public Interest Litigation) እንደዳበረባቸው አገሮች የሕዝብን አጠቃላይ ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም ጥቅም ሳይኖረው ክስ ለማቅረብ ስለመቻሉ በግልጽ አላሰፈረም። በሌላ በኩል ይኽ መብት በግልጽ ሰፍሮ የሚገኘው ከአከባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ሲሆን የአከባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 300/1995 አንቀጽ 11 ላይ አንድ ሰው ወይም ተቋም ጉዳዩ የሚመለከተው መሆኑን ማስረዳት ሳይጠበቅበት በአከባቢ ላይ ጉዳት ባደረሰ በማንኛውም ሰው ላይ ክስ ለማቅረብ እንደሚችል ተደንግጓል:: ጠበቆችን በተመለከተ ደግሞ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 7 ላይ እንደተደነገገው የሕዝብ ጥቅምን አስመልክቶ

32

ከላይ እንደተገለጸው ሥርዓቱ በዳበረባቸው አገሮች መብቱን በሕገ መንግሥትም ሆነ በሌሎች ሕጎቻቸው ከማስፈር ባለፈ መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችን ይደነግጋሉ። በተጨማሪም ክሱን የሚያቀርቡ ሰዎች በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ጥቅም የሌላቸው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደማበረታቻ ከመደበኛው ሥርዓት ቀለል ያለ ክስ የማቅረቢያ ሥርዓት ዘርግተዋል:: ፍርድ ቤቶቻቸውም ቢሆን በጉዳዩ ላይ የላቀ ሚና ለመጫወት የሕግ ማዕቀፍና ነጻነት አላቸው። በእኛ አገር ግን ቀደም ብሎ በቀረበው ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደሰፈረው ፍርድ ቤቶች በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የነቃ ሚና ለመጫወት ያላቸው ዕድል በእጅጉ የተገደበ ሲሆን፣ በአከባቢ ብክለት ጉዳይ ላይ እንኳን መብቱን ከማስፈር ዉጪ በበቂ ሁኔታ ቀለል ያለ የአሠራር ሥርዓት አልተበጀለትም።

ጠበቆችም ቢሆን ፈቃድ የሚሰጣቸውና የሚቆጣጠራቸው በወንጀል ጉዳይ ተከራካሪያቸው የሆነው ቀደም ሲል ፍትሕ ሚኒስትር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመሆኑ፣ ጠንካራና ሙያውን የመቆጣጠር መብት ያለው የሙያ ማኅበር ስለሌላቻው፣ ቀጥተኛ ጥቅም ለማያገኙበት ጉዳይ ልዩ ፈቃድ እንዲያወጡ መገደዳቸው በመብቱ የመጠቀም ዕድላቸውን ያመነምነዋል

ጠበቆችም ቢሆን ፈቃድ የሚሰጣቸውና የሚቆጣጠራቸው በወንጀል ጉዳይ ተከራካሪያቸው የሆነው ቀደም ሲል ፍትሕ ሚኒስትር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመሆኑ፣ ጠንካራና ሙያውን የመቆጣጠር መብት ያለው የሙያ ማኅበር ስለሌላቻው፣ ቀጥተኛ ጥቅም ለማያገኙበት ጉዳይ ልዩ ፈቃድ እንዲያወጡ መገደዳቸው በመብቱ የመጠቀም ዕድላቸውን ያመነምነዋል። በሌሎች አገሮች የበጎ አድራጎት (ሲቪክ) ማኅበራት የሕዝብ ጥቅም ክስ በማቅረብ ረገድ የላቀ ሚና ያላቸው ሲሆን በእኛ አገር ግን ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች አልፎ አልፎ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ከማጋለጥና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን ከማዘጋጀት ያለፈ ሚና ሲጫወቱ አይታዩም። ያለፉት 28 ዓመታት የፍትሕ ሥርዓቱ ጉዞ እንደሚያሳው ራሱ ፓርቲው ለሕዝብ ከሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገ መንግሥት የገባቸውን ቃል ኪዳኖች ማሳካት ተስኖት፣ ይልቁንም የፍትሕ ሥርዓቱ ለፖለቲካ ዓላማ ማሳኪያ ለበርካታ ጊዜ በመዋሉ ሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እጅጉን ተመናምኖ የሚገኝበት የታሪክ አጋጣሚ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያዊያን በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ያላቸው እምነት በከፍተኛ ደረጃ ተመናምኗል:: የፍትሕ ሥርዓቱ በዕውቀት እና በገለልተኛነት ካለመመራቱም በላይ ሥራ አስፈጻሚው እንደፈለገ የሚያሾረው አካል ሆኖ መገኘቱ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለውን ግንኙነት (state-society relation) በእጅጉ አበላሽቶታል:: “በሕግ አምላክ” የሚል ትልቅ የሕግና የፍትሕ አክባሪነትና እምነት የነበረው ሕዝብ በዚህ ደረጃ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት አጥቶ ማየት በጣም አሳዛኝ ነገር ነው:: የፍትሕ ሥርዓታችን ያሉበትን መሠረታዊ የተቋምና የአሠራር ችግሮች ቀርፈን ሕዝብ የሚተማመንበት ዘርፍ እስካላደረግነው ድረስ የአገራችን ጉዞ ወደኋላ እንደሆነ እንደሚኖር ሳይታለም የተፈታ ነው::

33

34